tgindex
🌼መዝሙረ _ዳዊት_ማህበር🌼

🌼መዝሙረ _ዳዊት_ማህበር🌼

Статистика

ማንኛውም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስርዓት የጠበቀ አዳዲስ መዝሙሮች እና መንፈሳዊ ጥያቄዎች የሚያገኙት ነው ይቀላቀሉ ለወዳጆ ሼር ያድርጉ የመወያያ Group https://t.me/mezumre_Dawit YouTube channel https://youtube.com/c/WaseGa21

Последний пост
14 апр. 2025 г.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
3 208
+1 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
10,5 тыс
20 постов
Вовлечённость
326,7%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • መርገመ በለስ የሰሙነ ሕማማት የመጀመሪያው ዕለት ዕለተ ሰኑይ መርገመ በለስ ይባላል፡፡ ጌታችን የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግስቱ ከቢታንያ ሲወጣ ተራበ፤ በመንገድም ሲያልፍ ቅጠል ያላት በለስን ከሩቁ ተመለከተ፡፡ ወደ በለሲቱም በቀረበ ጊዜ ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ያንጊዜም ‹‹ከእንግዲህ ወዲህ ለዘለዓለም ከአንቺ ፍሬ የሚበላ አይኑር›› ሲል በለሲቱን ረገማት፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ይህንን ሰሙት፡፡ በዚህም ምክንያት ይህች ዕለት በለሲቱ የተረገመችባት ቀን ናትና መርገመ በለስ ተብላ ትጠራለች፡፡ (ማር.፲፩፥፲፩-፲፬) በዚህ አገላለጽ በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ስትሆን ፍሬ የተባለ ደግሞ ሃይማኖትና ምግባር ነው፡፡ መድኃኒታችን ክርስቶስ ከእስራኤል ፍቅርን፣ ሃይማኖትን፣ ምግባርን ፈልጎ አላገኘባቸውም፡፡ እስራኤል፦ ሕዝበ እግዚአብሔር፣ የአብርሃም ዘር መባልን እንጂ የአብርሃምን ሥራ በመሥራት በምግባር በሃይማኖት ጸንተው መኖር አይፈልጉምና ደግ ሰው አልተገኘባቸውም፡፡ ከዚህም ባሻገር በለስ የተባለች ኃጢአት ናት፡፡ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አግኝቷታል፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሠሩት ለጊዜው ደስ ያሰኛል ኋላ ግን ያሳዝናል፡፡ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም በአንቺ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ሲል ነው፡፡ በለሲቱ ስትረገም ፈጥና መድረቋም በአዳም ምክንያት ያገኘን በደል በእርሱ እንደጠፋልን ለመግለጽ ነው፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር

  • 25 окт. 2024 г.11,4 тыс3

    видео или голосовое, без подписи

  • 25 окт. 2024 г.11,4 тыс2

    🗣አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ‼️‼️‼️ በጣና ሐይቅ ውስጥ ከሚገኙት ጥንታዊያን ገዳማት መካከል አንዷ የጣና ሐይቅ ደብረ ማርያም ገዳም ስትሆን ለባሕር ዳር ከተማ ቅርቧ ገዳም ናት ። የጥንታዊያን ብርቅዬ ቅርሶች መገኛ የሆነችው ደብረ ማርያም የምትተዳደረው በጎብኝዎች በሚገኝ ገቢ ሲሆን ከኮረና ጊዜ ጀምሮ የቱሪስት ፍሰቱ በእጅጉ ቀንሷል ።ይሁን እንጂ አሁን ባለው የክልላችን ወቅታዊ ጉዳይ(ጦርነት) ምክንያት የጎብኝዎች እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ የቆመ በመሆኑ ብርቅዬ ቅርሶችን በመጠበቅ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚያስተላልፉ መነኮሳት እና አገልጋይ ካህናት በችግር ውስጥ ስለሚገኙ የእናንተን እርዳታ ለመጠየቅ ተገደዋል ። ስለሆነም በሀገር ውስጥና በውጩ ዓለም የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ይህንን የገዳሟን የእርዳታ ጥሪ በመስማት በምንችለው አቅማችን ገዳሟን ማገዝ ይገባናል ። ገዳሟን ለመርዳት:- 👉በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ = 1000287176299 👉በዓባይ ባንክ = 2011119236087010 👉በአማራ ባንክ = 9900002724646 ጣና ሐይቅ ደብረ ማርያም ገዳም እያላችሁ ብትልኩ በቀጥታ እንደሚደርሳቸው የገዳሟ አባቶች አሳውቀዋል ። ለበለጠ መረጃ 📞+251910250363 📞+251918021018

  • +++ የጀማሪ ጠባይ +++ መንፈሳዊ ሕይወትን ገና ስትጀምረው ለፍጹምነት ጥቂት የቀረህ ያህል ይሰማሃል። አንተ ጋር ያለው ደስታ እና ሰላም ሌሎች ጋር የሌለ ይመስልሃል። በዚህች ሁከት በሞላባት ዓለም አንተ ብቻ ክርስቶስን እንዳገኘኸው ታስባለህ። የቀረው ሕዝበ አዳም እንዲሁ በከንቱ ሲርመሰመስ የሚውል ባካና ሆኖ ይታይሃል። ታዝንለታለህ፣ አይይይ ይህ ኃጢአተኛ ሕዝብ ምን ይሻለዋል? ትላለህ። የእውነተኛ መንፈሳዊ እድገት መገለጫ ግን ይህ አይደለም። ሰው ወደ እግዚአብሔር እየቀረበ ሲመጣ ከሌላው ሰው ይልቅ የራሱ ጉድለት ይታየዋል። መንፈሳዊነት የሚገልጥልህ ሰዎችን ተመልክተህ የምትፈርድበትን ውጫዊ ዓይንህን ሳይሆን ራስህን አይተህ የምትወቅስበት የውስጥ ዓይንህን ነው። መንፈሳዊ ሕይወትህ ሲጎመራ "አይ ሰው" ሳይሆን "አይ እኔ!" ያሰኝሃል። አባ ማቴዎስም እንዲህ ይላል "ሰው የበለጠ ወደ እግዚአብሔር ሲቀርብ ይበልጥ ኃጢአተኛ መሆኑ እየታየው ይመጣል። ነቢዩ ኢሳይያስ እግዚአብሔርን ካየ በኋላ ከንፈሮቼ የረከሱብኝና የጠፋሁ ሰው ነኝ እንዳለ።" ከብቃት ደርሰህ መላእክት ሲወጡና ሲወርዱ ቢታዩህ እንኳን ሁሉ እንዳንተ ስለሚመስልህ እንደ ዮሐንስ ሐጺር "ሚካኤል ይበልጣል ወይስ ገብርኤል?"  እያልህ ከአጠገብህ የቆመውን ትጠይቃለህ እንጂ "አይይ አንተ እንኳን ገና አልበቃህም። ብዙ ይቀርሃል" ብለህ ወዳጅህን አታናንቅም። ይልቅ "ለእኔ ብቻ ገልጦ ለሌላው እንዲሰውር የሚያደርገው ምንም ቁም ነገር የለኝም" በማለት ከወንድምህ የተሻልህ እንዳልሆንክ በፍጹም ልብህ ታምናለህ። ለመንፈሳዊ ሕይወት አዲስ ስትሆን ገና ጥቂት ጸልየህ፣ ጥቂት ጾመህ፣ ጥቂት መጽውተህ ሳለ ግን ሩጫህን ወደ መጨረሱ የተቃረብህ ይመስልሃል። ጉዞህን በግማሽ እርምጃ ከመጀመርህ ከፍጻሜው ላይ የደረስህ ያህል ይሰማሃል። "እኔን ምሰሉ" ማለት ያምርሃል። ነገር ግን መንፈሳዊ ሕይወት የቱንም ያህል ብትሮጥበት ሁል ጊዜ እንደ ጀማሪ የሚያደርግ ረጅም ጎዳና ነው። ሰማንያ ዓመት በገዳም ሲጋደል የነበረው አባ ሲሶይ ነፍሱ ከሥጋው ልትለይ በቀረበች ጊዜ ብዙ መነኮሳት በአልጋው ዙሪያ ከበውት ሳለ ቅዱሱ "አምላኬ ሆይ፣ እባክህ ለንስሐ የሚሆን ጥቂት ጊዜን ስጠኝ?" እያለ በልቅሶ ሲማጸን ሰሙት። በዚህ የተገረሙት መነኮሳቱ አባ ሲሶይን "አባታችን አንተ እድሜ ልክህን በንስሐ የኖርህ መምህረ ንስሐ ሆነህ ሳለ እንዴት አሁን ጥቂት የንስሐ ጊዜን ትለምናለህ?" ቢሉት፣ ቅዱሱም "ልጆቼ ይህን መንፈሳዊ ጥበብ (ንስሐን) ገና አሁን መጀመሬ ነው" አላቸው። ጌታ ሆይ መንፈሳዊ ሕይወት እኖር ዘንድ አስጀምረኝ፤ ገና ጀማሪ ሳለሁ ደርሻለሁ ከማለትም ሰውረኝ። እንድቆም አትፍቀድልኝ፤ ወደ አንተ ሳበኝ፣ አሳድገኝ።

  • 19 авг. 2024 г.10,1 тыс23

    ​​✞በብርሃን ደመና✞ ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ የታቦሩ ብርሃን በኢትዮጵያ ላይ ያብራ በጎቹ ይቆዩ ከእረኞቹ ጋራ ብርሃን ይዘው ይውጡ ቅዱሳን በጋራ የአብ ድምጽ ይሰማ በነጎድጓድ ግርማ ለሐዋርያቱ በግብጽ የገለጠ የሚወደው ልጁን ለመድህን ሰጠ ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ በጅራፍ ግርፋት ሕይወት የሰጠን በሠለሥቱ ምስጢር በአንድነት ጉንጉን ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ በቀራንዮ ላይ በአምስት ችንካር ቆመ ማየ ገቦ ፈሶ የአዳም ዘር ታከመ ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ ሰላም ትዕግሥት ስጣት ለውዲቷ አገሬ ማስተዋልን ጥበብን ለሙሴው መምህሬ ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ ውረጅ ድንግል በብርሃን ደመና ንዒ ድንግል ከክርስቶስ ጋራ        አዝ= = = = = በጥበብ ሃሳብ ላይ እንዳልነበር ገዝፎ ምን ያለው ነቀዝ ነው ጥቁር ሆኖ ቀፎ ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ ባዶነቱን አይቶ ለታላቅ ንጉሥ ሰው ንግሥቲቱን ሰጥቶ ቀፎውን በማር ሞላው ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ የዶኪማስ ጓዳ ሆኗል ልቦናችን በአንቺ ልብ ይቀናል ማርያም እናታችን ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ ተነሱ ለጸሎት ይበለን አዳም ሰላም ለሁላችሁ ድምጽን አሰማን ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ አውጣን ከዚህ ዘመን ከጥፋት ሀሳብ አገሬን አሻግራት ወደ ከነዓን ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ ተሰአለኒ አምላክ ተለመነኝ አምላክ ሆይ ስማ ህዝብሕን አደራ         አዝ= = = = = በተዋህዶ የጸናች ኢትዮጵያ አገሬ የአዳም ርስቱ የክብሩ ጅማሬ ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ ⭐ ኮከብ የቆጠሩ ቀኗን የቀመሩ አበው ሊቃውንቱ ጥበብን መርምሩ ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ ሞትን ድል የነሱ ጻድቃን የወጡብሽ ስውራን ቅዱሳን የሚጸልዩብሽ ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ ግለጭው ክብርሽን ትውልድ ይመርምርሽ 💚💛❤️ እንቆቅልሽ ስትይ ምን አውቅ እንዳይልሽ ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ ውረጅ ድንግል በብርሃን ደመና ንዒ ድንግል ከክርስቶስ ጋራ        አዝ= = = = = ወአንቲ ውእቱ መሶበ ወርቅ ንጹሕ ሕብስት ዘወረደ እም ሰማያት ስቡህ ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ በጸሎተ ሐሙስ ጽዋ ሕብስትን ሰጠ የዘላለም ሕይወት ምሳሌን ገለጠ ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ የአብርሃም ባራኪ መልከጼዴቅ ካህን የጽዋውን ስርዓት ምስጢሩን ይተንትን ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ ሕብስቱን በመሶብ ጽዋ በማሰሮ ታላቅ ምስጢር አለው ካየነው በአንክሮ ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ ጴጥሮስ ሙሴ - - ኧኸ  ኤልያስ - -ኧኸ ያዕቆብ - - ኧኸ   ዮሐንስ - - ኧኸ በወንጌሉ - - ኧኸ  እንዳየነው - - ኧኸ ተገልጸዋል - - ኧኸ  በተራራው - - ኧኸ ከጌታ ጋር - - ኧኸ  ከአምላካቸው - - ኧኸ በብርሃኑ - - ኧኸ  ተመስጠው - - ኧኸ ከርሞ ሰላም - - ኧኸ  አድርሰን - - ኧኸ ለንስሐ - - ኧኸ   አብቅቶን - - ኧኸ ትንሽ ትልቅ - - ኧኸ ሴት ወንዱን - - ኧኸ ፍቅር ሰላም - - ኧኸ  አድለን - - ኧኸ ለአገራችን - - ኧኸ  ኢትዮጵያ 💚💛❤️ ኧኸ ፍቅር ስጣት - - ኧኸ ሃሌ ሉያ - - ኧኸ ሐዘን ስደት - - ኧኸ  አገር ለቆ - - ኧኸ መለያየትን - - ኧኸ  አርቆ - - ኧኸ ይስጠን ፍቅር - - ኧኸ ይስጠን ምሕረት - - ኧኸ ዛሬም ነገም - - ኧኸ የሁሉ አባት - - ኧኸ(፪) ዓመት ዓመት - - ኧኸ  አድርሰን - - ኧኸ(፫) አገር ሰላም - - ኧኸ   አርግልን - - ኧኸ ዓመት ዓመት - - ኧኸ  አድርሰን - - ኧኸ(፫) አድርሰን - - - ኧኸ(፮)

  • ፈቃዴ ነው የሰውን ነገር ላልናገር ሊቀ መዘምራን ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ፈቃዴ ነው የሰውን ነገር ላልናገር (×2) የኔ ተሸፍኖ ከቆምኩኝ በክብር ፈቃዴ ነው የሰውን ነገር ላልናገር ❖ ህይወቴ በሙሉ በሀጢአት ተመልታ አምላኬ ከማረኝ በፍቅር ዝምታ የሰው በደል ላላይ በእውነት ምያለሁ እኔን ከታገሰኝ ፍቅር ተምሬያለሁ(×2) ❖አዝ በአይኔ ፊት ተጋርዶ ያለውን ምሶሶ እያየ ካለፈኝ በምህረት ታግሶ የሰው ጉድፍ ላላይ በእውነት ምያለሁ እኔን ከታገሰኝ ፍቅር ተምሬያለሁ (×2) ❖ አዝ አንተ ቀራጩ ሰው ያለህ አቀርቅረህ በምህረት ተመለስክ ከኔ ይልቅ ድነህ በአንተ ላይ ስጠቁም የኔን ፀሎት ትቼ የመዳኑ ሰአት አለፉ ቀኖቼ (×2) ❖ አዝ ተቆጥሮ የማያልቅ በደሌ ተከድኖ በሞትና በደል ሀጢአቴን ሸፍኖ ሰው አርጎኝ በሰው ፊት አቁሞኝ ጌታዬ በማንም አልፈርድም ሀጢአተኛ ብዬ/በደለኛ ብዬ (×2) ❖❖❖ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • ፍልሰታ ለማርያም

  • ኑ አብረን እንዘምር የምትችሉ ዘምሩ🙏

  • 21 июл. 2024 г.6 10728из mezmure_dawittt

    እንዘምር      #እሰይ_ነጋ እሰይ ነጋ እሰይ ነጋ ላመሰግንህ ነው አይኔን የከደንኩት አንተን አምኜ ነው(2×) በበደሌ ሳትፈርድ ስትጠብቀኝ አለህ ከኔ በላይ ለኔ ታስብልኛለህ የማታንቀላፋው ትጉህ እረኛዬ ብርሃኑን ያየሁት ባንተ ነው ጌታዬ        አዝ…………… ቀናቶቼን ሰጠሁ ላንተው አሳልፌ በሰላም እተኛለሁ በክንድ አርፌ ተመስገን ማለትን በብርሃን ጨለማ ታስተምረኛለህ በወፎቹ ዜማ      አዝ…………… ትናንት ትናት አልፎ ስላየሁ አዲስ ቀን ከእንቅልፌ ስነቃ እላለሁ ተመስገን አንተ ባታነጋው የጨለመውን አልኖርም ነበረ ዛሬ ባልኩት ቀን     አዝ…………… ሁሉም የሚሆነው እንደየስርዓቱ ባንተ ብቻ እኮ ነው መጨለም መንጋቱ ስላደረክልኝ ምኔን ልክፈልህ ተመስገን ብቻ ነው ሥላሴ ዋጋህ      አዝ…………… በብርሃን ተተካ አስፈሪው ጨለማ እንደእኔማ ሳይሆን ምህረትህ ቀድማ የኔ ያልኳት ዛሬ ነግታ የምትመሸው በጥበቤ አይደለም በበጎነትህ ነው

  • ይህን መዝሙር ትችሉታላችሁ? አወ ከሆነ መልሳችሁ ዘምሩልኝ እስኪ

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 25 июл. 2023 г.16,7 тыс3

    видео или голосовое, без подписи

  • 25 июл. 2023 г.16,4 тыс3

    видео или голосовое, без подписи

  • 25 июл. 2023 г.16,6 тыс4

    ፍልሰታ ለማርያም 😊 ለትውስታ

  • 14 июл. 2023 г.14,2 тыс121

    ሥላሴ ትትረመም ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር (፪) ይገባል ምስጋና ይገባል ውዳሴ ሁሉን ለፈጠረ ለቅድስት ሥላሴ ከዘመናት በፊት ቀድሞ የነበረ ፍጥረትን በሙሉ ለክብሩ ፈጠረ አዝ ልበል ሃሌ ሉያ ኪሩቤልን ልምሰል በእግረ ምስጋና ያሬድን ልከተል ላቅርብ ምስጋናውን ዘምስለ ሱራፌል ውዳሴ ምስጋና ነውና ለልዑል አዝ በስም ሦስት ሲሆን እንዲሁም በአካል በግብርም ሦስት ነው ያለመቀላቀል ፍጥረትን በመፍጠር በአምላክነት በባሕሪይ እና ደግሞም በመንግሥት አንድ አምላክ ነው እንጂ አይባልም ሦስት አዝ በኪሩቤል ጀርባ ዙፋኑን ዘርግቶ ክብሩን ጌትነቱን ከፍጥረት ለይቶ ይኖራል ዘለዓለም በመንግሥቱ ጸንቶ(፪) አዝ ይመስክር ዮርዳኖስ ይናገር ታቦር የአምላክ ጌትነት የሥላሴን ክብር ይኸው በዮርዳኖስ ወልድ ተገለጠ   መንፈስ ቅዱስ ታየ አብም ቃሉን ሰጠ   ዘማሪ ዲያቆን ፍሬዘር ደሳለኝ

  • 8 июл. 2023 г.10,7 тыс20

    ማግኘት የምትችሉ ይህን መጽሐፍ አንብቡት #የበረሃው_ምሥጢር በጣም ድንቅ መጽሐፍ ነው ይህን መጽሐፍ ያነበቡ ቡዙዎች ገዳም ገብተዋል🙏

  • 26 июн. 2023 г.10,6 тыс14

    ግንቦት 26 ዕረፍቱ ለቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ ቶማስ ማለት ፀሐይ ማለት ነው፡፡ ከመጠራቱ በፊት ስሙ ዲዲሞስ ነበር ትርጉሞም ጨለማ ማለትነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመረጣቸው አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት መካከልአንዱ ነው፡፡(ማቴ 10-3 ዩሐ. 20፡24 ሐዋ 1፡3) መንፈሳዊ እድገት ቅዱስ ቶማስ ሲጠራ ከሰዱቃውያን ወገን ስለነበር በትንሣኤ ሙታን(በሙታንመነሳት) የማያምኑት ሰዱቃውያን የወሰደውን ትምህርት ይዞ ጌታችን ከሙታን በተነሳ ጊዜ እጆቹን ካልዳሰስኩ በጦር የተወጋ ጎኑን አይቶ ዳሶ ካረጋገጠ በኋላ ያመነ ደቀመዝሙር ነው በሰዱቃውያን ትምህርት ሰው ከሞተ ሊነሳ አይችልም ብለው ያምናሉና …..በኋላም ቅዱስ ቶማስ የእመቤታችንን ዕርገት ቀድሞ ያየ ሐዋርያ ነው አገልግሎት ለደቀ መዛሙርቱ በ50ኛው ቀን መንፈስቅዱስ ከወረደላቸው በኋላ ያገለግሉት ዘንድ ዓለማቱን በሃገረ ስብከት ከፋፈሉ፡፡ የሐዋርያው ቶማስ ሃገረ ስብከቱ ሕንደኬ ነው፡፡ ወንጌል ለመስበክ ምክንያት ይሆነኛል ብሎ በመስፍኑ ሉክዮስ ቤት በሠላሳ ብር ተቀጥሮ መስራት ጀመረ፡፡ ሕንጻ ማነጽ ሐውልት መቅረጽ እችላለሁ አለ በዚህም መስፍኑ ቤተመንግስቱን ያንጽለት ዘንድ ለቶማስ ብዙ ገንዘብ ቢሰጠው መጸወተው ሉክዮስም ከሄደበት ሲመለስ ይታነጻል የተባለው ሕንጻ የለም ሕንጻውስ ቢለው ድሆቹን አሳየው በሃብት ንብረትህ በሰማይ መንግስት ተሰራልህ ሲለው ነው፡፡መስፍኑም ተቆጣ ይህ ክፉ ባርያ ተጫወተብኝ ብሎ እጅ እግሩን አሥሮ ቆዳውን አስገፍፎ ስልቻ ሰፍቶ በአሸዋ ሞልቶ አሸክሞ ሲያዞረው የሉክዮስ ሚስት አዘነችለት በቃሉ ትምህርት ከልጆችዋ ጋር አምና ነበርና በድንጋጤ ወድቃ ሞተች፡፡ በአንተ ምክንያት ሞተች ስለዚህም ዳግመኛ ሚስቴ ትነሳና በአንተ ልመን የቃልህን ትምህርት ልቀበል አለው፤ ጌታ ቁስሉን አቀዝግዞለት ሕማሙን አስችሎት እርሷ ካለችበት ሄዶ በስልቻው ቢያስነካው ተነሳች በዚህም የእጁን ተዓምራት የቃሉን ትምህርት ሰምቶ ሉክዮስ አመነ ተጠመቀም፡፡ ሰማዕትነት(ዕብ 11-36) ከዚህም በኋላ ስልቻውን ተሸክሞ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወረ ድውያንን እየፈወሰ አእዛብን እያስተማረ እያጠመቀ ቀንጦፍያ ደረሰ ቀንቶፍያም ሰባት ልጆች የሞተበትን ሽማግሌ አዝኖ አገኘው ልጆቹንም ከሞት አስነሳለት የእጆን ተዓምራት የቃሉን ትምህርት እየሰሙ ብዙዎች በወንጌል አመኑ፡፡ ከልጅ እስከ አዋቂ ከባርያ እስከገ ዢ ከሕዝብ እስከ ንጉሥ ድረስ በዚህም ካህናተ ጣኦት ቅንዓት አደረባቸው ስለዚህም ከንጉሥ ከመኳንንት አጣልተው በዚች ዕለት በሰይፍ አስመተሩት የጸሎቱ በረከት በእኛ ላይ ይደርብን!!!

🌼መዝሙረ _ዳዊት_ማህበር🌼 — tgindex