Nexara News
СтатистикаWeb: https://nexara.et/ Telegram Group: @nexaragroup Instagram: https://www.instagram.com/nexara.et/ Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100087504876738
- Последний пост
- 24 апр.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 30
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
ለተከታታይ አምስት (5) ቀናት ከስራ የቀረ ሰራተኛ ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ሊሰናበት ነው። ከእረፍትና ልዩ ልዩ ፍቃዶች ውጭ አንድ ሰራተኛ ለአምስት (5) ተከታታይ ቀናትና ከዚያ በላይ ከስራ የቀረ ሰራተኛን ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳያስፈልግ የሥራ ውልን ማቋረጥ የሚያስችል አዲስ የህግ ትርጉም ተሰጥቷል፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከዚህ በፊት በሰበር መዝገብ ቁጥር 249795 ላይ አንድ ሰራተኛ በተከታታይ ከአምስት (5) ቀናት በላይ ከሥራ ከቀረ አሰሪው ለእያንዳንዱ ቀን ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ የሥራ ውልን ማቋረጥ እንደማይችል ጠቅሶ የሕግ ትርጉም ሰጥቶ ነበር። ሆኖም ሰበር ሰሚ ችሎቱ አሁን ላይ አሰሪው ለእያንዳንዱ ቀን ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ ከስራ ማሰናበት የለበትም የሚለውን የሕግ ትርጉም ሽሮታል። በምትኩ ከእረፍቶችና ልዩ ልዩ ፍቃዶች ውጭ አንድ ሰራተኛ ለአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ከሥራ ከቀረ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳያስፈልግ የሥራ ውሉን ማቋረጥ ይቻላል በሚል ትርጉም ተሰጥቷል። ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ነው። @nexaranews
без подписи
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዚቢሽን እና የአፍሪካ ሪል ስቴት ማህበር ቀጣናዊ ጉባኤን እያስተናገደች ነው፡፡ ይህ ጉባኤ ከሀገራዊ ፋይዳው ባለፈ አዲስ አበባን የዘርፉ የኢንቨስትመንት እምብርት ያደርጋታል ተብሏል:: የኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር እንዳስታወቀው፤ ይህ ዝግጅት ከዛሬ ሚያዚያ 15 ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት ድረስ የሚቆይ ይሆናል፡፡ የዝግጅቱ ዋነኛ ግብ ሻጭና ገዢን፣ የግንባታ ግብዓት አቅራቢዎችንና ተጠቃሚዎችን በአንድ መድረክ ማገናኘት ነው ተብሏል፡፡ ከዚህም ባሻገር በዘርፉ ላይ የተሰሩ የጥናት ውጤቶች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸውና ለዘርፉ ማነቆ ለሆኑ ችግሮችም የመፍትሄ አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡ ተገልጿል። በጉባኤው ላይ የተገኙት የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሔለን ደበበ፤ በግንባታ ላይ የተሰማሩ ተቋማትን በማገዝ ረገድ ሰፊ ስራ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው ዘርፉን ወደ ተአማኒነት ለማስገባት የተለያዩ የህግ ማእቀፎች ተዘጅተዋል ብለዋል፡፡ በጉባኤው ላይ 28 የሪል ስቴት አልሚዎች እና ኩባንያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ኢትዮ ኤፍ.ኤም 107.5 @nexaranews
መርስክ ወደ በርበራ ወደብ የሚደረጉ የጭነት አገልግሎቶችን ለጊዜው ማቋረጡን አስታወቀ የዓለማችን ግዙፍ የመርከብ ድርጅት የሆነው መርስክ ፣ ወደ በርበራ ወደብ የሚደረጉ እና ከወደቡ የሚወጡ አዳዲስ የጭነት ቦታ ማስያዣዎችን ለጊዜው ማቋረጡን በይፋ አስታውቋል። ኩባንያው ለዚህ አስቸኳይ ውሳኔ ምክንያት የሆነው በመርከብ የጉዞ መርሃ ግብር ላይ የተደረገ ለውጥ መሆኑን የገለጸ ሲሆን፣ ይህም ውሳኔ በተለይ በርበራን እንደ አማራጭ የንግድ በር ለምትጠቀመው ኢትዮጵያ ከፍተኛ ተጽዕኖ ይኖረዋል ተብሎ ይገመታል። በቅርብ ዓመታት የበርበራ ወደብ ለኢትዮጵያ ወሳኝ የሆኑ እንደ ማዳበሪያና እህል ያሉ ምርቶችን ለማስገባት ትልቅ ሚና እየተጫወተ የሚገኝ በመሆኑ፣ የአገልግሎቱ መቋረጥ በቀጠናው የንግድ እንቅስቃሴ ላይ የራሱ ጥላ ማረፉ አይቀሬ ነው። መርስክ አዳዲስ የጭነት ጥያቄዎችን መቀበል ቢያቆምም፣ ቀደም ብለው የተጫኑ እና በጉዞ ላይ ያሉ ንብረቶች በታቀደው መሠረት መድረሻቸው እንዲገቡ እንደሚያደርግ አረጋግጧል። በተጨማሪም ድርጅቱ ደንበኞቹ የአቅርቦት ሰንሰለታቸው እንዳይስተጓጎል አሁንም አገልግሎት እየሰጡ ያሉትን የጅቡቲ፣ የሞቃዲሾ እና የሞምባሳ ወደቦችን እንደ አማራጭ እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርቧል። ካፒታል ኢትዮጵያ @nexaranews
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
የአዲስ መሶብ ተንቀሳቃሽ ዲጂታል አገልግሎት ተጀመረ በከተማ ደረጃ የአገልግሎት አሰጣጥን በቴክኖሎጂ ለማዘመን የታለመው “የአዲስ መሶብ” ተንቀሳቃሽ ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተመረቀ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት፣ ይህ አገልግሎት ህዝቡ ወደ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ከመሄድ ይልቅ፣ አገልግሎቱ ራሱ ወደ ህዝቡ እንዲጠጋ የሚያደርግ ነው። ዘመናዊ መሠረተ-ልማት (Unified Infrastructure Model) የተገጠመላቸው እነዚህ ተንቀሳቃሽ አውቶቢሶች፣ ከፀሐይ ብርሃን ኃይል የሚያመነጩና ፈጣን የኢንተርኔት (MPLS) ቴክኖሎጂን የሚጠቀሙ ናቸው። በተንቀሳቃሽ አውቶቢሶቹ የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች፦ 👉 አዲስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) መስጠት 👉 የንግድ ፈቃድ ማውጣትና ማደስ 👉ለመንጃ ፈቃድ የሚያስፈልግ የህክምና ምርመራ ማድረግ 👉የነዋሪነት መታወቂያ ማደስና የልደት ምዝገባ 👉የመንጃ ፈቃድ መስጠትና የተሽከርካሪ ታርጋ ማደስ 👉የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት የመንገድ ፈንድ ክፍያን ማከናወን 👉የብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባና የመረጃ እርማት 👉በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኩል የሚሰጥ የቅድመ ክፍያ የኤሌክትሪክ አገልግሎቶችን ይሰጣል። ይህ አሰራር የመንግስት ተቋማት በየቦታው የዳታ ማዕከል ለመገንባት የሚያወጡትን ወጪ የሚቀንስና የአገልግሎት ጥራትን የሚያረጋግጥ መሆኑ ተገልጿል። @nexaranews
አየር መንገዱ ስድስት የቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኖችን ለመግዛት የሚያስችለውን ስምምነት አፀደቀ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በፈረንጆቹ 2023 ገብቶት ከነበረው ትዕዛዝ መካከል ስድስቱን የቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኖች የግዢ አማራጮች ወደ ጸና ትዕዛዝ መቀየሩን ከቦይንግ ኩባንያ ጋር በጋራ አስታወቁ። ይህ የግዢ ስምምነት አየር መንገዱ ከአዲስ አበባ የሚያደርገውን የአህጉር አቋራጭ በረራ ለማስፋፋት እና እያደገ የመጣውን የረጅም ርቀት የጭነት አገልግሎት ፍላጎት ለማርካት ያለመ መሆኑ ተገልጿል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንደገለጹት፤ የስድስት ቦይንግ 787-9 ድሪምላይነር አውሮፕላኖችን የግዢ አማራጭ ወደ ፅኑ ትዕዛዝ መቀየር ለእኛ ኩራት የሚሰጥ ተግባር ነው። በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ግዙፉን የ787 ድሪምላይነር አውሮፕላኖች ስብስብ የያዘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ እነዚህን ዘመናዊ አውሮፕላኖች ወደ አውሮፓ፣ እስያ እና ሰሜን አሜሪካ ለሚያደርጋቸው ከፍተኛ ተፈላጊነት ያላቸው በረራዎች እየተጠቀመባቸው ይገኛል። ከ170 በላይ ዘመናዊ አውሮፕላኖች ያሉትና ወደ 145 በላይ መዳረሻዎች የሚበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የሰካይትራክስ (SKYTRAX) የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ ሽልማትን ለስምንት ተከታታይ አመታት በማሸነፍ በአህጉሪቱ ያለውን ቀዳሚነት አስጠብቆ ቀጥሏል። @nexaranews
ፕራይም ካፒታል በኢትዮጵያ 6ኛው የኢንቨስትመንት ባንክ በመሆን የሥራ ፈቃድ ተረከበ። ኢትዮጵያ ውስጥ እየተገነባ ያለውን የካፒታል ገበያ ሥነምህዳር ለመቀላቀል የመወዳደሪያ መስፈርቶችን ሲያሟላ የቆየው ፕራይም ካፒታል አክሲዮን ማኅበር (Prime Capital S.C.) ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የኢንቨስትመንት ባንክ የሥራ ፈቃድ ተሰጥቶታል። ኩባንያው በሀገሪቱ የካፒታል ገበያ ታሪክ ፈቃድ ያገኘ 6ኛው የኢንቨስትመንት ባንክ አድርጎታል። የፕራይም ካፒታል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሀቢብ መሐመድ ኩባንያው በዘጠኝ ባለአክሲዮኖች እና በ32 ሚሊዮን ብር መነሻ ካፒታል መመሥረቱን ገልጸዋል። ፕራይም ካፒታል አ.ማ. ወደ ሥራ ሲገባ ፦ ° የኮርፖሬት ፋይናንስ ማማከር፣ ° ካፒታል ማሰባሰብ፣ ° የኩባንያዎች ውህደትና ግዢ (M&A) ጨምሮ ዘርፈ-ብዙ አገልግሎቶችን ለደንበኞቹ እንደሚያቀርብ አስታውቋል። @nexaranews
без подписи
без подписи
без подписи
የቻይና አፍሪካ ኢንተርፕርነርስ ጉባኤ ዛሬ በአፍሪካ ህብረት እየተካሄደ ነዉ። በቻይና አፍሪካ የንግድ ምክር ቤት እና በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ትብብር በተዘጋጀው በዚህ ጉባኤ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀስላሴን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የአፍሪካ ኀብረት የሥራ ኃላፊዎች፣ የግሉ ዘርፍ የሥራ ኃላፊዎችና የሁለቱ ሀገራት ኩባንያዎች ይገኛሉ። ጉባኤውም የቻይና…
የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ (EIB) የልማት ክንፍ የሆነው ኢአይቢ ግሎባል (EIB Global) በኢትዮጵያ ለሚገኙ የግብርና ዘርፍ ላኪዎች የሚውል የ40 ሚሊዮን ዩሮ የብድር ስምምነት ከዘመን ባንክ ጋር መፈራረሙን አስታወቀ። በአዲስ አበባ በተካሄደው የአውሮፓ ህብረት-ኢትዮጵያ የንግድ ፎረም ላይ ይፋ እንደተደረገው፣ ኢአይቢ ግሎባል የ20 ሚሊዮን ዩሮ የብድር መስመር ለዘመን ባንክ የሚያቀርብ ሲሆን፣ ባንኩ በበኩሉ ተመሳሳይ መጠን ያለው የገንዘብ መጠን በማሟላት ለተጠቃሚዎች ያቀርባል። ይህ ስምምነት ኢአይቢ ግሎባል በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኝ የግል የንግድ ባንክ በቀጥታ የሰጠው የመጀመሪያው ብድር በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል ተብሏል። ይህ የፋይናንስ ድጋፍ በዋናነት በግብርናው ዘርፍ ለተሰማሩና ምርቶቻቸውን ወደ ውጭ ለሚልኩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፣ በተለይም ለቡና እና የአትክልትና ፍራፍሬ ላኪዎች የሚውል ነው። የስምምነቱ አንዱ አካል የሴቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ሲሆን፣ ከጠቅላላው የገንዘብ ድጋፍ ቢያንስ 30 በመቶ የሚሆነው በሴቶች ለሚመሩ ወይም ለሴቶች የሥራ ዕድል ለሚፈጥሩ ድርጅቶች እንዲውል ተለይቷል። በተጨማሪም 30 በመቶ የሚሆነው የብድር መጠን የአየር ንብረት ጥበቃንና የአካባቢ ጥበቃን ከግምት ውስጥ ለሚያስገቡ የግብርና ሥራዎች እንዲውል ታቅዷል። @nexaranews
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአቪዬሽን ደህንነት ማሻሻያ አዋጅን አፀደቀ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ስብሰባ፤ የኢትዮጵያን የአቪዬሽን ሴኩዩሪቲ ይበልጥ ለማጠናከር የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ አፅድቋል። ለ20 ዓመታት ያህል ሳይሻሻል የቆየውን ነባሩን አዋጅ ቁጥር 432/1997 የሚተካው ይህ አዲስ ሕግ፤ በዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ስታንዳርድ መሠረት ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችንና አሠራሮችን ተግባራዊ ለማድረግ ያለመ ነው። የአዋጁ መሻሻል በተለይም ከወቅቱ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ውስብስብ የደህንነት ስጋቶችንና ሕገ-ወጥ ጣልቃ ገብነቶችን ለመከላከል ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል። የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ዶ/ር ፈቲህ መሀዲ ባቀረቡት ሪፖርት፤ አዋጁ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ተወዳዳሪነትና መልካም ገጽታ ለማስቀጠል የሚረዳ መሆኑን አስረድተዋል። ምክር ቤቱም የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ መሠረት በማድረግ አዋጁን ቁጥር 1412/2018 አድርጎ በአብላጫ ድምፅ በ2 ተቃውሞና በ2 ድምፅ ተአቅቦ አፅድቆታል። @nexaranews
የቻይና አፍሪካ ኢንተርፕርነርስ ጉባኤ ዛሬ በአፍሪካ ህብረት እየተካሄደ ነዉ። በቻይና አፍሪካ የንግድ ምክር ቤት እና በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ትብብር በተዘጋጀው በዚህ ጉባኤ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀስላሴን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የአፍሪካ ኀብረት የሥራ ኃላፊዎች፣ የግሉ ዘርፍ የሥራ ኃላፊዎችና የሁለቱ ሀገራት ኩባንያዎች ይገኛሉ። ጉባኤውም የቻይና እና አፍሪካን የኢኮኖሚና ቢዝነስ ትስስር ወደ ተሻለ ደረጃ እንደሚያሣድገው ይጠበቃል። @nexaranews
ሀገሪቱ አሁን ላይ ወደ አረንጓዴ ማሽነሪዎችም በሙሉ አቅሟ እየተሸጋገረች መሆኑን የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ታከለ ኡማ በማኅበራዊ የትስስር ገፃቸው ላይ ጽፈዋል፡፡ የተፈጥሮ ጋዝ የሚሠሩ የኤሌክትሪክ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች እና የኢንዱስትሪ መሣሪያዎች አሁን የእቅዱ አካል መሆናቸውን ታከለ ኡማ ገልጸዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶችን በቁርጠኝነት በመጋፈጥ፣ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታን ማፋጠን የአፍሪካን የኢነርጂ ሽግግር በግንባር ቀደምትነት መምራት ነው ሲሉ ስራ አስፈፃሚው አክለው ገልፀዋል። ኢትዮ ኤፍ.ኤም 107.8 @nexaranews