tgindex
MJ Recovery

MJ Recovery 🧠 የግለ ወሲብ ሱስ አማካሪ ✨ ከሱስ ነፃ ወደሆነ ህይወት አብረን እንጓዝ! 📩 ለበለጠ መረጃ በውስጥ መስመር ያናግሩኝ። @Mj_Recovery

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
13
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
2 576
−7 за 1 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
—
 
Месяц
—
 
Просмотров на пост
209 тыс
13 постов
Вовлечённость
8107,6%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всогО 13
УпОПинаниК
0
канаНОв
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
689
1/48двое суток
789
1/72трое суток
851

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ✅ለ23 አመት በሴጋ ሹሾ የቆያ አንድ ወንድማችን ከውጪ ሀገር ሆኖ ሴጋ የጣለበትን ጠባሳ እና በሴጋ የተነሳ ህይወቱን በጨለማ እያሳለፈ የሚገኝ ወንድማችን ነው ተማሩበት ብሎዋል ቻናል @official_redemption1 በግል ማማከር ለምትፈልጉ inbox DM @Mj_Recovery

  • 30 док. 2023 Đł.373 тыс476212

    ✅ለ23 አመት በሴጋ ሱስ የቆያ አንድ ወንድማችን ከውጪ ሀገር ሆኖ ሴጋ የጣለበትን ጠባሳ እና በሴጋ የተነሳ ህይወቱን በጨለማ እያሳለፈ የሚገኝ ወንድማችን ነው ተማሩበት ብሎዋል ቻናል @official_redemption1 በግል ማማከር ለምትፈልጉ inbox DM @Mj_Recovery

  • 7 док. 2023 Đł.347 тыс21474

    8. ብቸኝነትን አስወግዱ ለረጅም ሰአት ብቻችሁን ላለመሆንና ጊዜያችሁን ከቤተሰብና ከወዳጆቻችሁ ጋር ለማሳለፍ ሞክሩ። በተቻለ መጠን ቀናችሁን በተሻለና ትርጉም ሊሰጥ በሚችል ነገር ላይ አውሉት። እንደ ስፖርት መስራት መጽሐፍትን ማንበብ ወደ መስጂድ /ቤተ ክርስቲያን መሄድ ያሉ ልምዶችን አዳብሩ። እስኪ ከዛሬ ጀምሮ ልታዳብሩት የምትችሉት 5 ልምምዶችን ጻፉ። 9. ተስፋ አትቁረጡ ከዚህ ህይወት ለመውጣት በምታደርጉት ጥረት ውስጥ መውደቅና መነሳት ሊያጋጥማቹ ይችላል። ተስፋ ሳትቆርጡ ከስህተታቹ ተምራችሁ እንደ አዲስ በብሩህ ተስፋ ነገን አሻግራቹ ተመልክቱ። 1ዐ. ግልጽ ሁኑ ይሄን ጽሁፍ ሳዘጋጅ እስከዛሬ ድረስ በዚህ ሱስ የተጠቁና ያማከርኳቸውን ሰዎች ከዚህ ሱስ እንድትወጡ ያስቻላችሁን ነገር ግለፁልኝ ስል ጠይቄ ነበር። በሁሉም ውስጥ ያገኘሁት 2 ሀሳብ ነው። አንደኛው የፈጣሪ እርዳታ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በችግሩ ላይ በግልጽነት ማውራቴ የሚል ነበር። ብዙ ሰው በጉዳዩ ላይ ማውራት ስለሚያሳፍረው እርዳታም ለማግኘት ይቸገራል። ከዚህ ህይወት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመውጣት ከፈለጋቹ ሊረዳቹ ለሚችል ለአንድ ሰው በግልጽ ችግራችሁን መናገር ይኖርባችኋል። በመናገራቹ ብቻ፤ ሚስጥር ያረጋችሁትን ነገር ወደ ብርሃን በማውጣጣቹ ይህ ኃጢያት በእናንተ ላይ ያለውን አቅም ያጣል። ስትደክሙ የሚያማክራችሁ ፤ መቆማችሁን ሁሌ ሚከታተል አንድ ሰው ማረጋቹሁ ፀንታችሁ እንድትቆሙ ብርታት ይሰጣችኋል። ይሄንን ምክር ሰጥቼው የተቀበለ አንድ ወንድም ችግሩን ለጓደኛው አካፈለው። መጥፎ ስሜት ሲሰማው ይደውልና እባክህን እየተቸገርኩ ስለሆነ ጸልይልኝ ይለዋል። ልታማክሯቸው የምትችሉ ሶስት ሰዎችን ጻፉና በማስተዋል እና በፀሎት ታግዛችሁ አንዱን ምረጡ። ይሄን ፅሁፍ ጀምሬ እስክጨርስ የረዳኝ አላህ አመሰግናለሁ   እስከ ዛሬ ለነበረን ቆይታ እጅግ በጣም አመሠግናለሁ ወዳጆቼ  እባካችሁ አሁንም ቻናሉን ሼር አድርጉት እወዳችኋለሁ የሆነ ጊዜ እመለሳለሁ ይሄን ቻናል https://t.me/official_redemption1 ለጓደኞቻችሁ ሼር / ላኩላቸው አድርጉለችሁ እስኪ እስከ ዛሬ ከጎኔ የነበራችሁ ላይክ አድርጋችሁ ወዳጅነታችሁን አሳዩኝ መልካም ምሽት ❤❤❤❤ በግል ማማከር የምትፈልጉ inbox dm @Mj_Recovery

  • 5 док. 2023 Đł.305 тыс10572

    6. ታገሉ! ከዚህ ሱስ መውጣት ሂደት ነው። ለማቆም ከወሰናቹ በኋላ እንኳን መላልሳችሁ ልትወድቁ ወይም እስከ ዛሬ ያያችሁት ምስል ሀሳባችሁ ላይ እየመጣ ልትጨነቁ ትችላላቹ። ይሄ ማለት ከዚህ ህይወት አልተላቀቃችሁም ማለት አይደለም። ቡና ለረጅም ጊዜ ጠዋት መጠጣት የለመደ ሰው እንደሚያዛጋው ማለት ነው እንጂ! አዕምሮአችን ወደ ቀደመው ቦታ እስኪመለስ ከማንኛውም ሱስ ስንወጣ የምናልፍበት ጤናማ ሂደት ነው። ዋናው በጦርነቱ ተሸንፎ እጅ አለመስጠት ነው። ጸንታቹ ከታገላቹና የሚፈልገውን እስከነሳችሁት ድረስ ሱሱ በእናንተ ላይ ያለውን አቅም ያጣል። ከመገባችሁት ግን ያድግና ይውጣቹሃል። 7. ስሜቶቻችሁን ተቆጣጣሩ ፖርኖግራፊ ማየት ሶስት ደረጃዎች አሉት። እነሱም ስሜት / Emotion/፣ ሐሳብ/Thought/ እና ተግባር/Action/ናቸው። ስሜት የምንለው የመጀመሪያው ደረጃ ጭንቀት፣ መከፋት ወይንም ፖርኖግራፊ የማየት ፍላጎት ሊሆን ይችላል። ይህን ተከትሎ ነው ፖርኖግራፊ የማየት ሐሳብ የሚመጣው። መጨረሻ ላይ ሁሉም ወደ ተግባር ይቀየራል። ስለዚህ ራሳችሁን መቆጣጠር የምትችሉት በሃሳብ ደረጃ ሳለ ሳይሆን ገና ስሜት ሲሰማቹ ነው። አንዲት እህቴ “እንዲህ አይነት ስሜት ሲሰማኝ ከቤት ወጥቼ መዝሙር እየሰማሁ የእግር ጉዞ ማድረግ እጀምራለሁ ይሄም በጣም ጠቅሞኛል' ስትል ልምዷን አጋርታኛለች። አንድ ወንድሜ ደግሞ እንዲህ አይነት ስሜት ሲሰማው ስፖርት እንደሚሰራ አጫውቶኛል። ይህ ስሜት ሲሰማቹ ምን ብታደርጉ ጥሩ ነው? 3 ነገሮችን ጻፉና የሚስማማችሁን ነገር አድርጉ።              ✅ይቀጥላል ....✅         መልካም ምሽት  እወዳችኋለሁ ❤❤❤      እባካችሁ ቻናሉን ሼር አድርጉልኝ https://t.me/official_redemption1 ለጓደኞቻችሁ እባካችሁ ቻናሉን ሼር አድርጉ🙏🙏🙏

  • 4 док. 2023 Đł.268 тыс8870

    5 .ቀስቃሽ ነገሮችን ለዩ። ከዚህ በታች ያሉትን ጥያቄዎች ለራሳቹ መልሱ። በብዛት ፖርኖግራፊ የምታዩት የትኛው ሰአት ላይ ነው? ለመጨረሻ ጊዜ ፖርኖግራፊ ያያችሁት መቼ ነው? ፖርኖግራፊ ከመመልከታቹ በፊት ምን አይነት ስሜት (mood) ላይ ነበራችሁ? ቀስቃሽ ነገሮቻቹ ምንድን ናቸው? ስሜትን የሚያነሳሱ የሙዚቃ ክሊፖች ወይንስ ፊልሞች? አንዲት እህቴ ፖርኖግራፊ ይዘት ያላቸውን ነገሮች የምታገኘው ከፌስ ቡክ ላይ ነበር። ከዚህ ህይወትም ሙሉ ለሙሉ መውጣቷን እስክታረጋግጥ ድረስ ፌስቡክ መጠቀሟን አቆመች። ከዚህ በፊት የሰበሰባችሁት ፊልምና ማንኛውም ነገር አሁኑኑ አስወግዱ። ለዚህ ዓላማ የምታገኙአቸው ሰዎች ካሉ ግንኙነታቹን አቋርጡ። ኢንተርኔት መጠቀም ማቆም ካለባቹ አድርጉት። ግድ መጠቀም ካለባችሁም ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ ተጠቀሙ። ወይም እንደ “Covenant eyes* ወይም ' ×3watch'* ያሉ ፕሮግራሞችን ተጠቀሙ ከሕይወታቹ የሚበልጥ ምንም ነገር የለምና! ወደ ፖርኖግራፊ የሚገፋፋቹ ጭንቀት ከሆነ ከጭንቀት መውጫ ሌሎች መንገዶችን ፍጠሩ። ስሙን ሳልጠቅስ ታሪኩን እንዳጋራ የፈቀደልኝን የአንድ ወንድም ሕይወት ላንሳ፤ “ከሚስቴ ጋር ባለን ህይወት ደስተኛ አይደለሁም። እቤት መሄዴን ሳስብ ጭንቀት ይወረኛል። መደበሪያዬ ፖርኖግራፊ ሆኖ ለዘመናት ኖርኩኝ። የትዳሬን ችግር መፍታቴ ከፖርኖግራፊ ሱስ አስመለጠኝ”። የእናንተን ቀስቃሽ ነገርን ጻፉት።          ✅ይቀጥላል ..... ✅የሶሻል ሚዲያ ቻናሎቻችንን Follow እና subscriba ያድርጉት    ቻናል ለብዙ ሰዎች ሼር አድርጉ https://t.me/official_redemption1   መልካም ምሽት እወዳችኋለሁ ❤❤❤❤.. ላይክ አረጉ

  • 3 док. 2023 Đł.236 тыс4662

    5. ለምን እንደምታዩ እወቁ አንዲት እህት ከ4አመት በፊት አስገድዶ መደፈር ደርሶባት ነበር። ለሊት ስትተኛ ያለፈችበት እየታወሳት ትጨነቅ ነበር። ከዚህ ስቃይ ማምለጫ ያደረገችው ፖርኖግራፊ መመልከት ነበር። ለዚህች እህት ፖርኖግራፊ መመልከት የችግሩ መገለጫ እንጂ ዋናው ችግሩ እንዳልነበር ነው። ከዚህች እህቴ ጋር ጊዜ ወስደንም ስናወራ አሰቃቂ ከሆነ ጉዳት በኋላ ሰዎች የሚኖራቸው የስነ ልቦና መቃወስ /Post Traumatic Stress Disorder/ እንዳለባት ማረጋገጥ ችያለሁ። ፖርኖግራፊ መመልከት ሰዎች በህይወታቸው ያልፈቱት የውስጣዊ ችግር መገለጫ ሊሆን ይችላል። ጊዜ ወስዳቹ በሕይወታቹ የሚያስጨንቃችሁን ነገር፤ ያለፋችሁበትን ታሪክ ለመለየት ሞክሩ። ችግሩን በውስጣችንን ተጭኖ ለማስቀረት (repress) ለማድረግ መሞከር ወደ ባሰ ችግር ይወስዳልና ችግሩን ተጋፍጣቹ መፍትሄ ለመስጠት ሞክሩ። YouTube እና ቲክቶክ አካውንተችንን Follow us ይቀጥላል.... መልካም ምሽት እወዳችኋለሁ ❤❤❤

  • 2 док. 2023 Đł.236 тыс185103

    ይህ የምትመለከቱት ሰው ለ50 አመት በሴጋ ሱስ ውስጥ የነበረ ሰው ነው ይህ ሰው በሴጋ ሱስ ምክኒያት ብዙ ነገሮችን ያጣ ህይወቱ የጨለመበት አብዛኛውን የህይወቱን በብቸኝነት እንዲያሳልፉ ይህ ሱስ ምክኒያት ሆኖታል  በጋዛ አንደበቱ ሴጋ ሱስ ህይወቱ ላይ ምን እንዳስከተለበት ምን አይነት ጠባሳ እንዳስከተለበት ለአለም ተነግሮዋል  እንዲህም ብሎዋል የሴጋ ሱስ ባለፈው ማንነቴ ተስሬ እንድቀመጥ አድርጎኛል ጠንካራ እንዳልሆንም አልፈስፍሶ አስቀምጦኛል የፍቅር ህይወት እንደልጀምር ጀምሬም ደስተኛ እንዳልሆን መሰናከል ሆኖብኛል ይህ ሱስ ብቸኛ አደረገኝ ብቸኝነቴም ይህን ብቸኝነቴም ይህን ሱስ እንድ ፈፅም አደረገኝ በዚህ ሱስ ተዘፍቄ እንድቀር ትልቅ ምክኒያት ሆነኝ ሴጋ/ማስተርቤሽን በራሴ እንደልተመማን በራሴ እንድጠራጠር ቦታዬን እና ዋጋዬ እንድጠራጠር አድርጎኛል ከሰዎች ጋር እንደልቀለቀል ከሰዎች ጋር እንደልግባባ ይህ ሱስ አድርጎኛል በአጠቃላይ ይህ ሱስ የማይመለሰውን እድሜዬ ሰርቆኛል ትልቁ ቁጭቴ ይሄን ሱስ  አለመተዌ አይደለም እተወዋለው ብዬ ለወደፊት ቀጠሮ መስጠቴ ነው እጅግ የሚያስቆጨኝ ...!!       ለእናንተ ጥያቄ.? እናንተስ ይሄን ሱስ መቼ ነው የምተውት..? ምን እስከምቶኑ  ድረስ ነው የምትጠብቁት..? ለምን እድሜያቹን እንዲሰርቅ ተፈቅዱለተላችሁ..? ማደግ እና መለወጥ አለባችሁ ጥንካሬ በራሳችሁ ..ላይ ማየት አለባችሁ..! ሱስን ወይም መጥፎ ልማድን መሸነፍ የሚቻለው ... ነገ ላይ አይደለም ዛሬ አና ዛሬ ላይ ብቻ ነው.. ስለዚህ ይህን ሱስ ለመሸነፍ ይህ ቻናል የሚሰጣችሁ ሙሉ መተግበር አለባችሁ ...! እኔን ለመግኘት ቻናለችን ሼር ያድርጉ https://t.me/official_redemption1

  • 1 док. 2023 Đł.209 тыс6661

    4.በሱሱ የተጠቁ ሰዎች ስለራሳቸው የተሳሳተ አመለካከት ይኖራቸዋል። “እኔ አልጠቅምም ፤እኔ ከንቱ ሰው ነኝ ፤እኔ ፈጣሪ ይጠላኛል፤ እኔ ከሰው አንሳለው ፤መቼም ከዚህ ህይወት መውጣት ስለማልችል ስኬታማ ትዳር አይኖረኝም፤ የሚሉ አሉታዊና ተስፋ የመቁረጥ አመለካከቶችን ያዳብራሉ። እንዲህ አይነቱ ለራስ የሚሰጥ የወረደ ግምት በቶሎ ካልተቀጨ ከባድ ወደሆነ አዕምሮአዊ እና ስነ ልቦናዊ በሽታ ያመራል። ለራሱ የተሳሳተ አመለካከት ያለው ሰው ስለ ሰዎች ትክክለኛ አመለካከት ሊኖረውም አይችልም። ሌላው የተሳሳተ አመለካከት የሚሰጠው ለተቃራኒ ጾታ ነው። እስከ ዛሬ በዚህ ጉዳይ ላይ ያማከርኳቸው ወንድሞችና እህቶች ሁሉም ለማለት በሚያስደፍረኝ ሁኔታ ለተቃራኒ ጾታ ዝቅ ያለ አመለካከት እንዳላቸው ገልጸውልኛል።ብዙውን ጊዜ በፖርኖግራፊ ምስሎች ላይ ሴቶች የወንዶች የወሲብ ፍላጎት አገልጋይ ተደርገው የተሳሉ ሲሆን ፖርኖግራፊ የሚመለከቱ ወንዶችም ልክ እንደዛው ሴቶቹን እንደሚመልከቱ ነግረውኛል። ሴቶች ደግሞ ሁሉም ወንዶች ጨካኝና ለስሜታቸው ብቻ የሚኖሩ እንደሆኑ እንዲያስቡ እንዳደረጋቸው አውርተውኛል።በዚህ የተሳሳተ አመለካከት ምክንያት ጤናማ የሆነ የፍቅር ህይወት ለመጀመር የተቸገሩ ጥቂቶች አይደሉም። 5. ትዳርን ይበጠብጣል ከሀገር ውጪ የሚኖር አንድ ሰው ደውሎ እንዲህ አለኝ “እኔ በፖርኖግራፊ ሱስ ከተጠቃሁ አመት ሆኖኛል። በዚህ ጊዜ ውስጥ ብዙ ችግር ገጥሞኛል። በስራ ሰአቴ ላይ ረጅም ጊዜ የማጠፋው ፖርኖግራፊ በመመልከትና ግለ ወሲብ በመፈጸም በመሆኑ እቤት ስገባ ከባለቤቴ ጋር ግንኙነት የማድረግ ፍላጎት የለኝም" የዚህ ሰው ችግር የብዙዎችም ነው። ፖርኖግራፊ የሚመልከቱ ሰዎች በትዳራቸው ያላቸውን እርካታ ያጡታል። የግንኙነት መቃወስም ( Sexual Dysfunction) ሊያጋጥማቸው ይችላል። ይህ ደግሞ ወደ ፍቺ እና የቤተሰብ መበተን እስከማምራት ይደርሳል                     ✅ይቀጥላል .....✅ https://t.me/official_redemption1✅ ቻናሉን ሼር ያድርጉ እኔን ለማግኘት ይምጡ  መልካም አዳር እወዳችኋለሁ ❤❤😍😍

  • 1 док. 2023 Đł.189 тыс248

    inbox ብዙ ልጆች እየመጣችሁ ነው አሁንም እኔ ለማናገር የምትፈልጉ ሰትፈሩ በዚህ ኑ @HAYATU_MUSTEFA

  • 30 нояб. 2023 Đł.207 тыс6763

    ክፍል 2 1. ድብርት / ጭንቅት ፖርኖግራፊ ውስጥ የገባ ሰው ያለበት ሕይወት ትክክል እንዳልሆነ ያውቃል። ስለዚህ ከባድ የሆነ ጭንቀት ይሰማዋል። ብዙ ሰዎች በዚህ ምክንያት ሀፍረት ስለሚሰማቸው በራስ መተማመናቸውን ያጣሉ። ስለዚህ በከባድ የድብርት ስሜት ውስጥ ሆነው ራሳቸውን ከሰው ያገላሉ። 2. አቅምን ይገላል በዚህ ሱስ የተያዘ ሰው በቀን ውስጥ በትንሹ 3 ሰዓት ፖርኖግራፊ በመመልከት ሊያጠፋ ይችላል። ምን ያህል የከበረ ጊዜውን እንደሚያጠፋም አስተውሉ! ከዚህ በተጨማሪ በዚህ ሱስ መጠቃት ኃላፊነትን ቸል ወደማለት ያደርሳል። የፈጠራ ችሎታን ይቀንሳል። በፖርኖግራፊ ምክንያት የአፈጻጸም ብቃታቸው ወርዶ ከስራና ከትምህርት የተባረሩ ሰዎች ጥቂቶች አይደሉም። አስደናቂና ዕምቅ ችሎታ ያላቸው ስንቶችን በፖርኖግራፊ ምክንያት አጥተናቸዋል? 3. ላልተፈለገ ተግባር ያጋልጣል ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ሕጻናትን ከደፈሩ ሰዎች ብዙዎቹ በፖርኖግራፊ ሱስ የተጠቁ ናቸው።ከዚህ በተጨማሪ ፖርኖግራፊ የሚመለከቱ ሰዎች ከማይመለከቱት ጋር ሲነጻጸሩ በ4ዐዐ% ሴተኛ አዳሪዎች ጋር የመሄድ ዝንባሌ አላቸው። የተመሳሳይ ጾታ ፖርኖግራፊ በመመልከታቸው ብቻ ወደ ግብረ ሰዶማዊነት የገቡ ሰዎች እንዳሉም ለማየት ችያለው። ✅ ይቀጥላል ...✅ ✅ ቻናሉን ሼር ያድርጉ https://t.me/official_redemption1✅ መልካም አዳር እወዳችኋለሁ ❤️

  • 29 нояб. 2023 Đł.182 тыс10854

    3. በሌላ ነገር ደስታ አለማግኘት አንድ ሰው ወደዚህ ሱስ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ያስደስቱት የነበሩትን ነገሮች ለምሳሌ ከቤተሰብና ከወዳጆች ጋር ጊዜ ማሳለፍ፣ ወደ ኃይማኖት ስፍራ መሄድ፣ ስፖርት መስራት፣ ፊልም ማየት፣ የእግር ጉዞ ማድረግ ወ.ዘ.ተ በመተው ደስታውን ሙሉ ለሙሉ በፖርኖግራፊ ላይ ካስቀመጠ ይህ ሰው የፖርኖግራፊ ሱስ ውስጥ እንደገባ ያሳያል። 4. ከተጽኖው ጋር መቀጠል በፖርኖግራፊ ሱስ የተጠቃ ሰው በሱሱ ምክንያት ብዙ ነገር እንዳጣ እያወቀ ህይወቱ ወደተሳሳተ አቅጣጫ እያመራ መሆኑን እየተረዳ በዛው ከቀጠለ ሱስ ደረጃ ላይ ለመድረሱን ያሳያል። 5. ሚስጥራዊነት በፖርኖግራፊ ሱስ ውስጥ ያለ ሰው ህይወቱን አጠገቡ ካሉ እና ከሚወዳቸው ሰዎች ሚስጥር ከማረጉ የተነሳ ድብቅ እና ሁለት ገፅታ ያለው ባይተዋር ሰው እንደሆነ ይሰማዋል። ሚስጥሩም እንዳይጋለጥ ያያቸውን ድህረ ገፆች በማጥፋት፤ የት እና ምን ያደርግ እንደነበር ቤተሰቡን እና ጓደኞቹን ሰዎችን ይዋሻል። የሚሰማውንም ሀፍረት ለመሸፈን በማስመሰል ህይወት ውስጥ ይዘፈቃል። 6. ሐላፊነትን አለመወጣት ብዙ ሰዓታትን በፖርኖግራፊ ከማሳለፍ የተነሳ በአግባቡ ስራን አለማከናወን፤ የቤተሰብ፤ የማህበራዊና መንፈሳዊ ሐላፊነቶችን መወጣት አለመቻል እና ገለልተኝነት ሱስ ደረጃ ላይ መደረሱን ያሳያል። 7. የፀባይ መቀያየር በሱስ ውስጥ ያሉ ሰዎች የሚፈልጉትን ባጡ ጊዜ በጣም ብስጩ ፤ ቁጡ እና በጥቂት ነገር የሚናደዱ ይሆናሉ። ከላይ የጠቀስናቸው ዋና የሚባሉት የሱስ ምልክቶች ሲሆን እነዚህ ይቀጥላል ........ መልካም አዳር እባካችሁ ቻናሉን ሼር አድርጉ https://t.me/official_redemption1

  • 29 нояб. 2023 Đł.161 тыс21983

    ከፖርኖግራፊ ሱስ መውጣት ይቻላል! ክፍል 1፥ የፖርኖግራፊ ሱሰኝነት ምልክቶች 1. ከፍተኛ ፍላጎት አንድ ሰው ሱስ ደረጃ ላይ ከደረሰ ለፖርኖግራፊ ከፍተኛ ፍላጎት ይኖረዋል።በውስጡ የማያቋርጥ ፍላጎት ይቀጣጠላል። በማንኛውም ቦታ በማንኛውም ሁኔታ በማንኛውም ሰአት ፖርኖግራፊን መመልከት ይፈልጋል። ከዚህ በተጨማሪ የሚመለከትበትን ጊዜ እየጨመረ ይመጣል። በሳምንት ያይ የነበረ በቀን፤ በቀንም አንዴ ያይ የነበረው ሁለቴ ማየት ከጀመረ፣ በፖርኖግራፊም የሚያጠፋውም ጊዜ እያደገ ከመጣ፤ በሚመለከትበት ጊዜ የሚሰማው መነቃቃት እና ደስታ በሀፍረት፤ ጥፋተኝነት ስሜት እና ፀፀት ሲተካ ነገሩ ሱስ ደረጃ ላይ መድረሱን ይጠቁማል። 2. ለማቆም አለመፈለግ / አለመቻል ሱስ ውስጥ የገባ አንድ ሰው ፖርኖግራፊ መመልከቱን ማቆም አይፈልግም። ሱስ እንደሆነና ችግር መሆኑን እንኳን መቀበል አይፈልግም። ይህም የሚሆነው ሱስ ውስጥ ስለገባና ከዛ ህይወት ቢወጣ ሌላ የሚያዝናናው ነገር ሊያገኝ እንደሚችል ስለማያምን ነው። በሌላ መልኩ ደግሞ ለማቆም እየፈለጉ አለመቻልም የሱሰኝነት ማሳያ ነው። እዚህ ጋር አንድ ወንድም በድምጽ ባስቀመጠልኝ መልዕክት ውስጥ “እኔ ከፖርኖግራፊ ሕይወት ለመውጣት ከ1ዐዐ ጊዜ በላይ ለራሴ ቃል ገብቼ ነበር፤ ነገር ግን ተመልሼ እዛው ሕይወት ውስጥ እገኛለው" ብሎኛል። ይህ ንግግር የሚያሳየው ከባድ የሆነ ሱስ ውስጥ መግባቱን ሲሆን እየተጸየፍነውም የምናደርገው ነገር ሱስ እንደሆነብን ያሳያል። ይቀጥላል ..... ቻናሉን #ሼር ያድርጉ https://t.me/official_redemption1