tgindex
Suleyman Mehammed

Suleyman Mehammed

Статистика

በዚህ ቻናል _ የስነ-ልቦና ምክሮች _ የታላላቅ ሰዎች ምክር እና ሀሳቦች _ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች _መሳጭ ታሪኮች እንዲሁም _ግጥሞችም ይቀርቡበታል ራስን መሆን ለሃሳብ አስተያየት እና ለሚኖሩ ጥያቄና መልስ ውድድሮች ምላሾችን እና ሃሳቦትን ለማስቀመጥ ይህን ሊንክ ይጠቀሙ @Sule_bot

Последний пост
13 апр. 2025 г.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
466
−2 за 1 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 008
20 постов
Вовлечённость
216,3%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • የሰዎች ልብ ላይ አለመታመንን መክተት ሚያስከፍለው ዋጋ ብዙ ነው። አለመታመንን ከዛም አልፎ ያ ሰው ከአንተ ጋ ሚያሳልፈው ጊዜ አሰልቺ ታደርግበታለህ። ሁሌም ቢሆን ሰዎች ፊታቸው ስትቆም የተደበቀ ማንነት እና ከሗላ ያለ ድብቅ ውሸት እንዳይኖር ህይወት መጋረጃ ናት የሆነ ቀን ታጋልጥሃለች።

  • ሁሌም በዳይ የነቃ እና የገባው እለት ይበልጥ ሚጐዳው እሱ ነው ፤ ብዙ ማይመለሱ እና ተመናቸው ማይታወቁ ግፎች ሰሪዎችን በልቷቸዋል።

  • ሰው ፈጠነም ዘገየም ፤ አንድ ቀን የሞት እጣ ሚወድቅበት ፍጡር ነው። "ከዕለታት ግማሽ ቀን"

  • የረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም! ሁለንተናዊ ከፍታ ያለው በመኖራቸው ላይ አያበቃም ወደ አኼራ መሻገራቸውም ስኬታማነታቸውም እንዲያበቃ አያደርግም። "መኖሬም ለእናንተ ኸይር ነው ሞቴም እንደዛው" ሰው በህይወት ውስጥ እያለ ስለ ራሱ ከኖር እና በራሱ የህይወት መስመር ውስጥ ካለፈ የግል ስኬቱ ሊሆን ይችላል ቀሪ ማንነት ግን ብዙ አይኖረውም። ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ያለፉትን 1440 አካባቢ አመታት ያለምንም ሶሻል ሚዲያና ቀሪ ምስል እና ቪዲዬ እና ፎቶ በተደራጀ መልኩ ማንነታቸውን ሚያጠና ግሩፕ ንግግራቸው ላይ እንዳይዋሽ። ሰሂህ ፣ ደኢፍ ፣ ሀዲሱ ገሪብ እየተባለ እዚህ ድረስ አወራራቸው አረማመዳቸው ሳይቀር ተገልፇል። በብዙዎች ሲጠቀስ ያለው ባህሪያቸው ፣ ስብእናቸው ፣ ቸርነታቸው ፣ ዱንያን አቅለው መኖራቸው ነው። በዚህ ልክ ምራቁ መሬት ማይነካ ማንነት ያለው ታላቅ ሰው ሚበላው አጥቶ እንደነበረ ማሰብ እና በረሃብ ድንጋይ አስሮ እንደነበረ ማሰብ ምን ያህል የሰው ልጅ ከሳቸው ማንነት ብዙ መማር እንዳለበት ያሳያል ከዱንያ ሰውነት የአኼራ ሰው መሆን የተሻለ ነው። ቢሹ ከሰማይ ወርቅ ማዘነብ እየቻሉ ፣ ሲያሻቸው ደሞ የተመረጡ ምግቦችን መብላት እየቻሉ እንዴት ለምን ዝም አሉ የዘወትር ጥያቄዬ ነው። ሆኖም ግን መልካም ስትሆን ፣ ስምህ ከቀብር በላይ ዳግም ይነሳል ስለዚህም ስትሞት በዙሪያህ ያሉ ሰዎች ብቻ ሳይሆን ሰው ማያቃቸው ሰዎች አባታቸው እንደሞተ እንዲሰማቸው አድርገህ በአንተ መሞት ሚጐዱ ሰዎች መኖር አለባቸው። መኖርህም ጥቅም አልባ እንዳይሆን መሞትህም ከቁጥር ማጉደል በዘለል ትርጉም ማይኖረው አታድርግ። ረሱል መኖራቸው ብዙ ትርጉም ነበረው አሁንም ቢሆን ስማቸው ለችግሮች ሁሉ መክፈቻ ቁልፍ ነው።

  • ከረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የህይወት ተሞኩሮ ሳንወጣ! የአንድ ሰው የስኬቱ ሚስጥር ቤተሰቡ ደካማ ጐኑም ቤተሰቡ ናቸው። በህይወትህ ውስጥ ትልቁ እገዛ ሚመጣው ከቤተሰብህ ነው ፤ በብዝሃነት ስንመለከት ረሱል የዚህ እድል ባለቤት በብዙ አልነበሩም የረሱል የህይወት ውጣ ውረድ በብዙ ነገር የታጠረ ነው። አንድ ሰው በህይወቱ ውስጥ ሚስቱን ፣ አያቱን ፣ አባቱን ፣ እናቱን ፣ 6 ልጆቹን ወዳጆቹን አጥቶ በስተመጨረሻ አንድ ሚሳሳላት ልጁ የእርሱ መሞት ዜና በተሰማ በተወሰኑ ወራት ውስጥ እንደምትሞት ማወቅ ማለት ሀዘኑ ምን ያህል ነው በቦታው ሁናቹ አስቡት። ይሄ ከባድ ፈተና ነው ይህንን ፈተና የደረሰበት ስንትሰው አለ ታድያ እኛ የከበደችን ትንሿ ፈተና ከነብዩ ጋ ሲነፃፃር ምን ድን ነው? ኢሄን ያደረገው አላህ ነው ሆኖም ግን ዳግም ወደ አላህ ይቀረቡ ነበር ታድያ የሁሉም አባት ሆኑ ፣ የሁሉም ሸፍዓ ሆኖ የአላህ ወዳጅ ሆኖ አንድ አንዴ በህይወት ምታጣው ነገር ትልቁን ደረጃ ለማግኝትም ይሆናል በትግስት ፅና።

  • ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ከመካ ወደ ጣኢፍ ሲሄዱ ከመካ የተሻለ ነገር ይኖራል ብለው ነበር የሄዱት ከሚደርስባቸው ግፍ መጠለያ ይሆናል ብለው ነው። ሁሌ ሰው መማር ያለበት ብዬ እና እኔም በህይወቴ የተረዳሁት መልካም ያደርግልኛል ብለህ ያሰብከው ሰው ከጠበቅከው በተቃራኒ ሆኖ ያሳይሃል። ጣኢፍ ላይ ካገኟቸው ሰዎች ውስጥ ከሶስቱ አንዱ የተናገረው ንግግር ሁሌም ይገርመኛል። "አላህ ሰው አጥቶ ነው አንተን ነብይ አድርጐ የላከው?" ይህ ከባድ ልብ ሰባሪ ንግግር ነው ያግዘኛል ካልከው ሰው የተሰጠህ ምላሽ? በህይወትህ ምን ያህል ሰው በዚህ ልክ አስቀይሞሃል። አስብ በአንተ የደረሰ ብቻ አይደለም በታላቁ ነብይም ደርሷል ሁሌም ቢሆን ጉዳይህ ወደ አላህ አዙር። ለሆነው ነገርም አትቀየም

  • የማን "አይዞሽ" ሊደግፍሽ? በማን "እኔን" ልትበረቺ? ዋጥ ልመጂ እምባ ሁሉ በአደባባይ አይዘራም።

  • በህይወትህ ውስጥ ስቅህ ምታልፋቸው ጉዳዬዎች እና የሰውን ልክ ምታቅባቸው ብዙ ቀናቶች ይመጣሉ። ማንም ሰው ከሱ ተቃራኒ ስትሆን አይወድም ሁሌ ልክ ነህ እንድትለው ይፈልጋል በራሱ ስህተት መሞትን ሚመርጥ ሰው አለ ከአንተ ተቃራኒ ሃሳብ ሰምቶ ከሚቀየር ይልቅ።

  • ከፊት ያለውን ማየት ሲቀል ፣ በእጅ ያለውን ማጥበቅ ሲቻል ፣ የሄደ ትናንትን ፍለጋ ሰው የዛሬን እንዴት ይለቃል? እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል ሲሉ አልሰማህም ወደ ፊት እንጂ ወደ ሗላ በመጓዝ ሚገኝ ትርፍ የለም ፤ ወደ ፊት እልፍ ስትል ብቻ ነው እልፍ ሚገኝው። " አለማወቅ "

  • አንድ አንድ ሰዎች አሉ ከባባድ ጉዳዬችህን ሊሸከሙልህ የተፈጠሩ ሚመስልህ በከባዱ ጊዜህ አሉ በደስታህ ጊዜ አላፊው ይከልላቸዋል የውጤቱ መነሻ ግን እነሱ ናቸው። ሁሌም ለአንተ መልካም ሚሆኑ ከምንም በላይ የአንተ ስሜት ሚያስጨንቃቸው። ስለነዛ ሰዎች አስበህ ታውቃለህ? ድል ስታደርግ ሚሸሸጉ ክሬዲቱን ለአንተ ሚሰጡ መልካም ሰዎች።

  • የሰዎችን ችግር ያየ ሰው ፤ የራሱ ችግር ቀላል ይሆንለታል።

  • እንደ ራስ መኖር ጥሩ ነው! ራስን የህይወት ማነቆ ውስጥ መክተት ነው ያለ አቅም መኖር ፤ በራስ የህይወት ገፅ ላይ የተፃፈ ነገር ነው ውብ እሚሆነው። ሚያስከብረውም እንደ ራስ መኖር ነው። የትም ቦታ ብትገኝ እንደ ራስህ መሆንህ ያስከብርሃል እሱኮ በራሱ የህይወት ጉዞ ያለ ነው ያስብልሃል። በሰዎች የህይወት መስመር ውስጥም አያኳትንህም ሁሉም ነገር ይደረሳል እንደ ሰዎች የኖርክ ቀን ማንነትህን ታጣለህ። ለጤናማ የህይወት ቆይታ ፣ ለተረጋጋ እና ለረጋ ማንነት ራስን መሆን እንደ ራስ መሆን ይሻላል።

  • መልካም ሰው ለመሆን ኸይረኛ ሰው ለመሆን ብትፈልግ እንኳን ጊዜው አይመችም። ጥሩ ነገር ማድረግህ እንደ ሞኝነት ሚቆጠርበት ዘመን ላይ ደርሰናል። አንድ አንዴ መልካም ያደረግክለት ሰው እንኳን ሞኝ መስለህ ትታየዋላህ። እኔ መልካምነት ስለ ሰዎች ኸይር ማሰብ እና በሰዎች ሃጃ ላይ መቆም ዋጋ አስከፋይ ቢሆንም እወደዋለው። ትንሽ ጊዜው ሚያስፈራ ይመስላል ኸይር የዋልክለት ሰው ሸንጐ ላይ በዳዬ ነው ብሎም ሊያቀርብህ ይችላል። ስለ ሰው መኖር መልካም ማድረግ እንደ ፋራነት የተቆጠረበት። ስለ ራስ ማሰብ ስልጡንነት የሆነበት ዘመን። ወንድምህ ጓደኛህ የቅርብ ሰው ሙሲባ አጋጥሞት እንዴት እረፍት እንደሚሰጥ አላውቅም።

  • ያለፈው አመት ኸይር ሁሉ ይከተለን ፣ ፈተናና መከራ አብሮን አይጓዝ። የስኬት እና የአፍያ የደስታ ዘመን አላህ ያርግልን። አሚን

  • ብር አለኝ ብለህ ስትጨፍር ታድራለህ! አባት ለልጁ የትምህርት ቤት መክፈያ አጥቷል አንተ ሰርግ ላይ ብርህን ትበትናለህ ደብተር መግዛ አጥቶ ሰው። እንዴት ታድያ ፍቺ አይበዛ ፣ እንዴት በረካ አይነሳ። እስከዛሬ የጨፈርከው ምን ጥቅም አገኝህ ሀፊዝ ልጅ ወጣልህ ምን አገኝህ? ሸኽ አዲል ሀፊዘሁላህ

  • ወንድሞቼ መንገድ ያሳየን ሁሉ መንገድ ሊዘጋብን ነው ብለን አናስበ አጎራረስን የሚያሳይን ሰው ምግብን ሊቀማን እንዳይመስልን ማጉረስ የሚያጠግባቸው ብዙ ሰዎች እንዳሉ ማመን አለብን። ብዙ ክፉ ሰዎች ቢያጋጥሙን የሚያጋጥሙንን ሁሉ ክፉ አናድርግ ክፋታቸውን የማያውቁ ብዙ ሰዎች አሉና ክፉ ነህ እያልን ክፋታቸውን አትቀስቅሱ። ሰዎች ሁሉ ክፉ ናቸው ስልን ክፋታቸው እንወርሳለን ስለነሱ ብዙ ስናወራ ወሬው ታሪካቸው ያንቺ ያንተ እየሆነ ይሄዳል። ደሞ ሌላው በቃኝ ልመጂ እጅሽ ከሞላ ይብቃሽ ወድቆ በነፃ ስላገኘሽ ብቻ ሆድሽን እጅሽን አትጠቅጠቂ በቃኝ ልመጂ እጅሽ ከሞላ ኪስሽ ከሞላ ዳር ላይ ማስቀመጥ ልመድ እጅህ እየሞላ አንድ እየጣልክ አንድ ስታነሳ ከኖርክ ስግብግብ ትሆናለህ። ወድቆ ያገኘሽው ነገር ሁሉ ያንቺ አይደለም እጅሽ ሲሞላ፣ ሆድህም ሲሞላ፣ ኪስሽ ሲሞላ የጎደለበትን አስብ ባዶ የሆነበትን አስቢ። ከረጅም ታሪክ ላይ የተወሰደ

  • ለሰዎች መኖር ምክንያት ከመሆን በላይ ምን ደስታ አለ?

  • ደክመው ደክመው ያለሙትን ሳያሳኩ ማለፍም አለ። ስለዚህ ዛሬ ይሻላል አላህን ለማመስገንም መልካም ሰው ለመሆንም ያሰብነውን ህይወት ለመኖርም።

  • ወንድሜ አትውደቅ! አላህ አይፈትነህ መውደቅ ፈተናው ለወደቀው ሰው ብቻ አይደለም ዙሪያው ላይ ላሉትም ሰዎች ነው። መውደቅ ያስፈራል ምንም ባይኖርህ አለመውደቅህ ስኬት ነው ሰው ፊት መቆም ከባድ ነው ላላየው አይድረስበት ላየው አላህ ይፈርጀው። ሰው ፊቴ ሲቆም ቀድሜ መሸማቀቅ ጀምርያለው ብርክ ብርክ ይለኛል። ከዛ ሰው በላይ እሸበራለው መውደቅ በሰው እጅ ላይ ማረፍ ፈተና ነው። እንደው ከቻልን ሰው ሳይቀድመን እንቅደመው አቅም ካለን ሰው ቤታችን አያንኳኳ ለዝየራ ማንኳኳት እና ለክጀላ ማንኳኳት ይለያል።

  • без подписи