tgindex
ከጠቢባን ምድር ツ•| አብዱ ~ ሩሚ |•

ከጠቢባን ምድር ツ•| አብዱ ~ ሩሚ |•

Статистика

°| ✍ከአፍቃሪያን ገጽ በፍቅር ቀለም |° •[ ከጠቢባን ምድር! ]• 🌴 دار الحكمآء

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
8
Всего постов
27
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
4 075
−5 за 5 дн.
Сутки
−1
−0,02%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
393
27 постов
Вовлечённость
9,6%
к подписчикам
Постов в день
1,1
всего 27
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
245
1/48двое суток
280
1/72трое суток
302

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • 6- ኦ አንተ ተፈቃሪዬ ሆይ! ማብቅያው በራቀ የእኩይ መሻት በረሃ ላይ ዋለልኩ። ብርሃንህን ከጥላዬ ሳልርቅ ፈለግኩት። ጥላዬ የነፍሴን መልክ እንጂ ሊያሳየኝ አልተቻለውም። ወደ አንተው በባዶ እግር ፣ ምንምነቴን ብቻ ይዤ መምጣት ጀመርኩ። ከአንተ ምሻው ይህ ተራራ ሃፍረቴን የምሸሽግበት የይቅርታ ስፍራህን ብቻ ነው። ፀፀት እና ሀዘኔ ፍሬ ሁኖ ከምድር ስር ይቀበር። እዝነትህ ዝናብ ሆኖ ከሙት እኔነቴ ህያው ሆኜ ላብብ። @ktebiban_meder

  • ከሳሊሆች ሙናጃ . . . [ ግጥሙን በሰነፍ አማርኛ ለመመለስ የተሞከረ ( ይበልጥ አሻሽሉት እስኪ!) ] واذا ما  الليل اسدل ستائره فوق الأنام لجأت إليك  محبوبي و العالمين نيام በሌት! ፍጥረት ሁላ ሲለባብስ ድቅድቅ ፅልመት የኔ ተፈቃሪ. . ወደአንተ አዘግማለሁ ሁሉ ፍጥረት በተኛበት ፡ في  رحابك  تفيض  روحي   هائمة و ينعم  في  مناجاتك  قلبي  بسلام ከደጅህ ዋላይ ሆናለች ነፍሴም ሰላሙን ያገኛል ፡ ሲያወጋህ ልቤም! مولاي  هل  لي من  لدنك  مغفرة وعفوا  لما  قد علق  بالقلب من آثام እንደው ጌትዬ ከአንተ ዘንድ ይኖረኝ ይሆን ምህረት? ይቅርታ! ልቤን የጋረደው የወንጀል ድቅድቃት በአንተ እንዲረታ! إذا أذنبت يا ربي وكان ذنبي عظيم فرجائي  رحمة  تشملني  و احسان ባጠፋ ጌትዬ ምን ቢገዝፍ ውድቀቴ በእዝነት እቅፍህ መሰንበት ፡ ብቸኛ ተስፋ ምኞቴ! أنت الكريم  وجاهك  الأعظم  ملجئ    يااا من  باب توبته مفتوح  في كل آن... . . . . @ktebiban_meder

  • ያ ረብ❤️‍🔥

  • | " وَعَجِلْتُ إِلَيْكَ رَبِّ لِتَرْضَىٰ "          « ጌታዬ ሆይ! ትወድልኝም ዘንድ ወደ አንተ ቸኮልኩ»  |

  • ሀያሉ ፍቅርህ ጠልፎ የጣለው ከራሱ አርቆ ለአንተ ነጠለው ሰባራ ልቡን . . . ደቂቅ አካሉን ደጋግፎ ፣ የናፍቆት እንባን በአይኑ ታቅፎ! ይጠራሀል ፡ ያጠራሃል ከፍጥረታት የለህ አጋር! ለባይተዋር ነፍሱ ሁናት ወዳጅ ፡ ሁናት አጋር! < Abdu | Rumi > @ktebiban_meder

  • 5- አመታትን ደምቆ ለመታየት ፣ ታይቶ ለመታወቅ ፣ ታውቆ ለመደነቅ ማሰንኩ። መሬት በለሆሳስ እንዲህ አለችኝ " ነብያቶች ተናንሰው በተራመዱባት አፈር ላይ አትኩራ!  ለመታየት አትታትር! ይልቅ የታላላቆች ኮቴን ፍለጋ መንገድ ግባ። " ከዚያም በደጋጎች የእግር ኮቴ ወደ ደጁ ልዘልቅ ፣ ወደ አላህ መንገድ በሚያደርሱ ጎዳናዎች ላይ ያለሁ ብናኝ ሆንኩ። @ktebiban_meder

  • ሸይኻችንን ፎሎ እያደረግን ከኢልም ማዕድ ነፍሳችንን እናስጠጋ ሸይኹነል ሀቢብ💚 https://vm.tiktok.com/ZS9hohReThenj-IYHjk/

  • 9 авг.513157

    ወዳጁን በህልሙ ያላየ ፣ ምን አየ ፤ ከሰው የተለየ💔 አላሁመ ሰሊ ወሰሊም ወባሪክ አለይህ🤎 ግጥምና ድምፅ - ኡስታዝ ሰዒድ አህመድ💙 @ktebiban_meder

  • 9 авг.602194

    -4 አንተን ከማወቄ በፊት ብቸኝነቴ እርግማን ይመስለኝ ነበር። ከዛም አገኘሁህ ፡ ኦና የነበረው የልቤ ግድግዳ ስምህን ማስተጋብያ ዋሻ ሆነኝ። አሁን ብቸኝነትን አልፈራም።ይልቅ ልቤ ስር ከአንተ ውጪ ያለ ዘልቆ የስምህን ውብ ዜማ ከመስማት እንዳልታገድ ነው ፍርሃቴ። @ktebiban_meder

  • 3-እንግዳ ስሜ ተዘነጋ ብለህ አትቆዝም። ብዙ ከዋክብቶች ስም ሳይኖራቸው መንገድን ሲመሩ አልተመለከትክምን? አበባዎች ከአላፊ ንፋስ ጋር ግብ ግብ ሲፈጥሩ አትመለከትም። ይልቅ ከንፋሱ ጋር ሚያውድ መዓዛቸውን ቀላቅለው ይከስማሉ። ነፍስ የተፈጠረችው በሰዎች ዘንድ ምትታወስ እንድትሆን ሳይሆን በጌታዋ ዘንድ ምትታወቅበትን ኑር እንድትሸክፍ ነው። @ktebiban_meder

  • 7 авг.572103

    |  ለሊት የአፍቃሪያን ምሽግ❤️‍🩹😊    | @ktebiban_meder

  • 7 авг.613115

    2-  ስንቀ ናፍቆት ወደ አንድ ስፍራ ገና ከመጠጋታቸው በቀዬው ያለ ነገር ይዘትና መልኩን ይቀይር ነበር። የሚያውድ ጠረናቸው የሰዎችን ልብ ወደ ጎዳናው እንዲያቅጣጩ ያስገድዳቸዋል። የመዲና ማቲዎች ጨዋታቸውን ገትተው የጉጉት አይናቸውን ወደ መንገዱ ያደርጋሉ። አዋቂዎች በአክብሮት ከተቀመጡበት ይነሳሉ። መንገደኛም መዋለሉን ትቶ ይጠብቃል።  ተራ የሚባሉ የህይወት እሽክርክሪት አካል የሆኑ ክስተቶች ሳይቀሩ እንደ ቀስት መወንጨፋቸውን ተወት ያደርጋሉ። ጊዜም 'እዝነት' በሰዎች መሃል ስጋ ለብሶ ሲንቀሳቀስ ለመመልከት የግርምት መዝገቡን ገልጦ ይታዘባል። በሁሉም አፍቃሪ ልብ ውስጥ የሰፈረ ልዩ መግነጢስ አለ ፣ ናፍቆት ይሰኛል። ያለ እርሱ ህይወት ወዝ አልባ ናት። አንዳንዴም የህይወትን ቅኔ መፍቻ ። ናፍቆት የስንቅ ማጣፈጫ ቅመም ሳይሆን ታላቅ ስንቅ ነው። @ktebiban_meder

  • ጁምዓ ሙባረካ🩵 @ktebiban_meder