tgindex
🕯️የህላዌ ብዕር✍️

🕯️የህላዌ ብዕር✍️

Статистика

🖋የህላዌ ብዕር ስሜት በቃል… ቃል በብዕር… ✨ እንኳን ደህና መጡ! ✍️ መፃፍ ውስጤ ነው… ስሜትን በቅኔ፣ ትዝታን በወግ፣ ሕይወትን በገጠመኝ፣ ምናብን በልቦለድ እተርካለሁ።🤗 🌿 ወግ • 🌸 ግጥም • 🕰️ ገጠመኝ 📖 አጭርና ረዥም ልቦለድ ❤️ ፍቅር • 🕊️ ሐዘን • ✨ ትዝታ • 🌱 ሕይወት ሁሉንም ታገኛላችሁ… አንዳንዱን ታነባላችሁ፤ አንዳንዱን ደሞ በልባችሁ ታኖራላችሁ። 🖤

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
12 авг.
Постов за неделю
11
Всего постов
23
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
12 авг.
Подписчики
413
+12 Са 3 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
—
 
Месяц
—
 
Просмотров на пост
189
20 постов
Вовлечённость
45,8%
к подписчикам
Постов в день
1,6
всогО 23
УпОПинаниК
4
канаНОв
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
136
1/48двое суток
155
1/72трое суток
168

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • йоС пОдписи

  • йоС пОдписи

  • 📚 አንድ ቻናል… ብዙ ዓለም! ✨ በየቀኑ ስልክህን ስትከፍት ጊዜህን የሚጠቅም፣ ልብህን የሚነካ እና አእምሮህን የሚያበለጽግ ይዘት ማግኘት ትፈልጋለህ? ❤️ እንግዲያውስ ይህ ቻናል ለአንተ ነው! 🚀 በዚህ ቻናል ውስጥ የምታገኙት፦ ❤️ ልብን የሚነኩ ተከታታይ ልብወለዶች 📖 አጫጭርና ረጅም አስደናቂ ታሪኮች ✍️ የፍቅር፣ የሕይወት እና የተስፋ ግጥሞች 💭 ጥልቅ አስተማሪ ጽሑፎች ❤️ ልብ የሚነኩ አባባሎችና ጥቅሶች 🎭 አሳዛኝ፣ አስገራሚ እና ትምህርት የሚሰጡ ታሪኮች ⚠️ JOIN ካላደረግህ የሚቀጥለውን ልብ የሚነካ ታሪክ ልታመልጥ ትችላለህ! 📚 ለራስህ አንብብ። 🤝 ከወደድከው ለጓደኞችህ አጋራ። ከእኛ ጋር ተቀላቀልና በየቀኑ አዲስ ዓለም አግኝ! ✨ 🚀 አሁኑኑ JOIN አድርጉ! ❤️ የሚቀጥለው ምርጥ ታሪክ ምናልባት አንተን እየጠበቀ ነው። 🔗 https://t.me/senoriah

  • 12 авг.1205иС Markal_274

    йоС пОдписи

  • йоС пОдписи

  • 😘🌞

  • 🕯️የህላዌ ብዕር✍️ pinned a photo

  • ያልታመመው ሞተ🙂‍↕️

  • йоС пОдписи

  • 👌

  • ክፍል ሰላሳ ሁለት ፍቅር ወይንስ እምነት #በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ በሩን ተደግፌ አለቀስኩ… ድምፄ ተዋጠ … እንባዬ ግን አልቆ ነበር። ለአፍታ እንባዬን ዋጥ ሳደርግ… ከውጪ… የአብሱ የተሰበረ የሲቃ ድምፅ ተሰማኝ። ልቤ በአንድ ጊዜ ተናወጠ… “ክፈት… አቤኒ…” እንደምትል ተሰማኝ… ወደ በሩ እጄ ተዘረጋ… ልከፍትላት ፈለኩ… ላቅፋት ፈለኩ… እንደ ቀድሞ እጄ ውስጥ እንድትሆን ፈለኩ… ግን… አንድ ነገር ውስጤን አጠነከረ… እኔን ከእሷ በኀይል አራቀኝ… አታፈቅረኝም....አይደል እጄን አወረድኩ… በሩን አልከፈትኩም… ከእንባዬ ጋ መልሼ ተነጋገርኩ… “በቃ…” አልኩ ለራሴ… ከዚያ… ሁሉም ነገር ዝም አለ… ስልኬ ጠራ… አየሁት… እሷ ነች… ልቤ እንደገና መታ… ነገር ግን እጄ አልተንቀሳቀሰም… ዘጋሁባት… ደገመች… ደገመች… እኔም ግን… ደጋግሜ ዘጋሁት… ሰላም ማግኘት ፈለግኩ… ልረሳት ሞከርኩ… ከቤት አልወጣሁም… ምግብ መብላት አላሰኘኝም… ልቤ ለብቻው በሀሳብ ይበላኛል… ሳብሰለስል....በመጨረሻ…እንቅልፍ አሸነፈኝ...ጥቅልል ብዬ ተኛሁ… በንጋታው ጠዋት ከመንቃቴ… ስልኬ መጮህ ጀመረ…አስደነገጠኝ ምንጊዜ እንደከፈትኩት ረስቼዋለሁ… ከብዙ ጊዜ ጥሪ በኋላ አነሳሁ… “አሰላሙ አለይኩም…” ድምፅ ተሰማኝ… ሀጂ ነበሩ… እኔም በደካማ ድምፅ “ወዓለይኩም ሰላም…” አልኩ… ትንሽ ጊዜ ዝም አሉ… እያሰቡ እንደሆነ ተሰማኝ-.... ከዚያ በረጅም ትንፋሽ መናገር ጀመሩ— “ልጄ… ድምፅህ ደህና አይመስልም… ልብህ ደክሞአል…” “ነገር ግን አላህ አይጨክንም… ሰው ቢሰበር እርሱ ይጠግናል…” “ያ የምታስበው የሚሰማህ ህመም… ያልፋል…” “ልጄ… ይቅርታ መማር አለብህ… ለራስህንም… ለሌሎችም…” እኔ ዝም ብዬ እየሰማኋቸው… እንባዬ ከየት እንደመጣ ሳላቅ ዳግመኛ መውረድ ጀመረ… “ና… መስጊድ ና…” አሉኝ በረጋ ድምፅ “ቁርአን ትቀራለህ… ልብህ ይረጋጋል …” “ሰላት ታደርጋለህ… ነፍስ ትዘራለህ…” “ና በቃ… ስለእሷ ማሰብ ይብቃህ ልጄ…” “አላህ ያለው ነገር ይሻልሀል…” “አንተ ገና ትኖራለህ…ብዙ ታያለህ” የነገሩኝ ቃላቸው… እንደ አባት እጅ ልቤን አሸሸገው… እኔ ግን ቃል አጣሁ… “ሀጂ… እኔ…” አልኩ በቀስታ ነገር ግን ሌላ ቃል አልቀጠልኩም… “ና… እንጠብቅሃለን…” አሉኝ እኔም… “እሺ… እመጣለሁ…” አልኳቸው…ደስስ እንዲላቸው ብቻ… ......ተሰነባበትን.... ግን… መሄድ አልቻልኩም… ድፍረቱን አጣሁ ተነሳሁ...እንባዬን ጠራረግኩ ሰውነቴ ከባበደኝ… በስንት ቀኔ ገላዬን ታጠብኩ… መስታወት ላይ ራሴን ስመለከት… ራሴን አላወቅሁትም… ፊቴ ላይ ፂም ሞልቶታል… ዓይኖቼ ደክመዋል… “ይሄ እኔ ነኝ…?” ብዬ አስብኩ… ግን… ውስጤ ባዶ ነበር… ቤቴ ተዝረክርኳል… እንደ ልቤ… ከሰዓት በኋላ… ትንሽ የሆነ ነገር የሚበላ ለመግዛት … በኪሴ ያለውን ብር አራግፌ…ከቤቴ ወጣሁ በስንት ጊዜዬ... መንገድ ጀመርኩ… ነገር ግን…ጥቂት እንደሄድኩ እግሬ አልታዘዝም …አለኝ አካሌ ከባበደኝ… ራሴን አዞረኝ… ሰማይ እና ምድር ተቀላቀሉብኝ… የሰዎች ድምፅ እንደሚርቀኝ ተሰማኝ… “አቤኒ…!” የሚል ድምፅ የሰማሁ መሰለኝ… እሷ ነች…? ወይስ በህልሜ ነው…? አላወቅሁም… ዓይኖቼ ጨለሙብኝ… እግሬ ተንሸራተተ… … ከዚያ… ምንም አልተሰማኝም…ወደቅኩ...ራሴን ሳትሁ....       ይሄ ፅሁፍ 30❤️ ካገኘ🤗        .........ይቀጥላል.........          @Rufaylen13 💫               ✍️ ህላዌ💕

  • `` ሀዘናችሁን ለመውደድ ሞክሩ ምናልባት  እንደምንወደው ነገር ሁሉ እርሱም ይተወን ይሆናል። ``                      -አኒስ መንሱር

  • 🙏

  • 🤪ከይሲ😆

  • #ካነበብኩት አህያው በአጋጣሚ የአንበሳ ቆዳ ያገኝና ይለብሰዋል። "ዛሬማ ማንም አያቀልለኝም!" ብሎ ወደ ቀበሮዎች መንጋ ሲገባ...ቀበሮዎቹ "አንበሳ መጣብን!" ብለው በድንጋጤ እግሬ አውጪኝ ይላሉ። .... አህያው በነገሩ እየተገረመና በደስታ እየፈነጠዘ ወደ ሜዳ አህያዎች ያመራል፤ እነሱም በፍርሃት ተበታተኑ። ቀጥሎ "እስኪ ጉዳቸውን ልይ!" ብሎ ወደ ጅቦች መንጋ አመራ። ጅቦቹም በፍርሃት እየጮሁ መሸሽ ጀመሩ። ... አህያው በደስታ ብዛት ግራ ተጋባ፤ በቃ የደስታውን ጥግ ለማሳየት "አንዴ ልጩህ" ብሎ ማናፋት ጀመረ። በዚህ ጊዜ ጅቦቹ ድምፁን ሰሙት... "ኧረ ይኸ ነገር አህያ ነው!" ብለው ተመልሰው ቦተረፉት ። .... እውነተኛ ማንነት የሚገለጠው ሰው ሁሉንም ነገር በእጁ አስገብቻለሁ ብሎ ባወራ ጊዜ፧ ነው። አፍ ሲከፈት ውስጥ ይታያል አይደል የሚባለው? በሱፍ የተደበቀ ሌባ፤ በፀዓዳ ነጭ ሾር የተደበቀ እድፍ፣ በለስላሳ ምላስ ሾር የተደበቀ እኩይ ልብ አለ። ጊዜ ደግሞ ይገልጣል። ብንችል ራስን መሆን ውብ ነው። @Rufaylen13 💫            ✍️ ህላዌ💕

  • 🌤መልካም እለተ ሰንበት✨

  • #ካነበብኩት ወጣቷ በራሷ ላይ የወተት ማሰሮ ተሸክማ ወደ ገበያ እየሄደች ነበር። በመንገድ ላይ እያለች በሐሳብ ውስጥ ገባች። "ይህን ወተት እሸጣለሁ፤ በገንዘቡ እንቁላል እገዛለሁ። እንቁላሎቹ ዶሮ ይሆናሉ፤ ዶሮዎቹን እሸጣለሁ። በዚያ ገንዘብ አዲስ ልብስ እገዛለሁ። ወጣቶችም ሊያገቡኝ ይመጣሉ፤ እኔ ግን እምቢ ብዬ እንዲህ ብዬ ራሴን እነቀንቃለሁ..." እያለች ራሷን በደስታ ነቀነቀች። ... ወዲያውኑ የወተቱ ማሰሮ ከራሷ ላይ ወደቀና ተሰበረ። ወተቱም በሙሉ ተደፋ። ሁሉም ያቀደችው ሕልም በአንድ ቅጽበት ጠፋ። ... ያልተገኘን ትርፍ እንደተገኘ ቆጥረህ እቅድ አትሥራ። መጀመሪያ ያለህን አረጋግጥ፤ ከዚያ በኋላ ለወደፊቱ እቅድ አውጣ። @Rufaylen13 💫               ✍️ ህላዌ💕

  • 😎''እራሳቹን መስላቹ ዋሉ''🙌      መልካም ቀን🤗

  • ክፍል ሰላሳ አንድ ፍቅር ወይንስ እምነት #በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ “እኔ…እ” አለችኝ አብሱ። ድምጿ እየተንቀጠቀጠ... እኔ ግን ምንም አልተናገርኩም... ልቤ ሌላ ነገር አላሰበም ከአፏ ጥሩ ቃል  እየጠበቅሁ በዝምታ ተመለከትኳት። “እኔ… አንተን ማጣት አልፈልግም…” በቀስታ አለችኝ “የቱ ጓደኛ አለኝ? ወንድምስ አለኝ? ማን አለኝ ከአንተ በቀር?” (ዓይኖቿ እንባ ሞልተው ወደ እኔ ተመለከቱ) “ብቸኛ ነኝ አቤኒ… አንተ ግን… እኔ ሳላውቅ እንኳን ከጎኔ ነበርክ።” እኔ ለጥቂት ሰከንዶች ተመልክቻት...ከዛን “ምን እያልሽኝ ነው?” አልኳት በተሰበረ ድምፅ። እሷ ግን በእንባ እያየችኝ— “ታስፈልገኛለህ… እባክህ አትጥላኝ። ተረዳኝ…” አለችኝ። ረጋ ብዬ ቃሏን ለመስማት እየጓጓሁ፣ “እኮ… ምን ልረዳሽ?” አልኳት። “አንቺ እኔን በቅድሚያ መች ተረዳሽኝ አብሱ?” ዝም አለች። “እኔኮ… አንተ እንደምትወደኝ አላውቅም ነበር…” አለችኝ በሚንቀጠቀጥ ድምፅ። “አሁን ግን… ምንም ማድረግ አልችልም…” በዝምታ እያየኋት ነው.. ለደቂቃ ትንፋሽ ወስዳ— “ደግሞ… የምወደው ፍቅረኛ አለኝ…” ታውቃለህ ኣ... ይሄንን መስማት አልፈለኩም ነበር ኮስተር እያልኩ “ምን?” አልኳት ታውቃለህ የተናገረችውን እንዳልሰማሁ ለማስመሰል እንደገና ጠየቅኳት። “ፍቅረኛ የምትዪውን ሰው አላውቀውም እኔ ስለራሴም አላቅም እኔ እ” ነግሬሀለሁ ጭንቅሏታን እየነቀነቀች እኔ ግን በውስጤ እየተቃጠልኩ… “መቼ ነው ያወቅሽው?” አልኳት። “ከመቼ ጀምሮ ነው ያፈቀርሽው?” እንደገና ዝም። “እሱ… እንደኔ ሆኖልሻል?” ድምፄ ከመራራ ሳቅ ጋ ተቀላቀለ። “ንገሪኝ…” እሷ ግን አንድ ቃል እንኳን አልመለሰችልኝም። እኔ ግን የተደበቀው ሁሉ በውስጤ አፈነዳሁት.... “ለምን ፀጥ ትያለሽ?” “እኔኮ አንቺን ብቻ መርጬ ነበር!” ድምፄ ከፍ አለ። “ሁሉን ነገሬን አጥቼልሻለሁ!” “ኑሮዬን…” “ጓደኞቼን…” “ሰላሜን…” “እምነቴን…” ቃሌ ተቋረጠ። ዓይኖቼ በእንባ ተሞሉ። “ምን ያላጣሁት ነገር አለ?” አልኳት። በደከመ ድምፅ እሷ በፍርሃት ተመለከተችኝ። “ተረጋጋ… እባክህ…” “እባክህ…” እኔ ግን እጄን አነሳሁ። “በቃ…” አልኳት። “በቃ አብሱ…” ጥቂት ሰከንዶች ዝም አልን። ከዚያ እሷ በእንባ እያየችኝ— “ምን ላድርግ አቤኒ? አለችኝ። “እኔም እንጃ…” ። “እኔ ምን ላድርግ?” ተነስታ አንድ እርምጃ ወደ እኔ ቀረበች። “እባክህ…” አለችኝ። እኔ ግን ወደ ኋላ ተመለስኩ። “አትቅረቢኝ…” አልኳት። በሚንቀጠቀጥ ድምፅ— “እኔ… በቃ አንተን አላፈቅርህም…” አለችኝ። ያ ቃል… ዳግመኛ ልቤን ሰበረው። “እንግዲህ… ለምን መጣሽ?” አልኳት እያፈጠጥኩ። “ደግመሽ ልቤን ለመስበር?” እንባዬ በጉንጬ ላይ ወረደ። “አንቺ ልሾሽ ሂድ ብለሽኝ ነበር…” “እኔም ለመርሳት ሞከርኩ…” “ለሶስት ወር…” “ሶስት ወር ሙሉ በዚህ ቤት ውስጥ ራሴን እየጎዳሁ ተቀምጫለሁ…” “አንቺ ግን ዛሬ መጣሽ…” “እንደገና ልቤን ለመክፈት…” “ከዚያ እንደገና ለመስበር!” እጄን በደረቴ ላይ ጫንኩ። “እኔ ምን አይነት የማረባ ሰው ነኝ?” አልኩ ለራሴ። “በሬን ከፍቼ… እንደገና ያስገባሁሽ…” እሷ ወደ እኔ ቀረበች። “እንዲህ አትበል አቤኒ…” አለች። “በቃ… ፍቅረኛህ ባልሆንም…” ቆም አለች። “እህትህ መሆን እችላለሁ…” እኔም ደነገጥኩ። “ምን?” “እህትህ…አንተ ደሞ ወንድሜ” አለች እጄን ለመያዝ እየሞከረች። '' እንድትረጋጋ እፈልጋለሁ…” እጄን ከእጇ ነጠቅኩ። “ልቀቂኝ!” “አቤኒ…” “ወንድሜ መሆን ትችላለህ?” ድምፄ ተንቀጠቀጠ። “ይህ ቃል ከአፍሽ ወጣ?” እሷ እያለቀሰች ነው። “እወድሃለሁ…” አለችኝ ደግማ “ግን…” በእንባ ተንተባተበች። “ልቤን… ምን ላድርገው?” እኔ ምንም አልመለስኩም። “እስኪ ንገረኝ…” አለች። “እኔስ ምን ላድርግ?” የምናገረው ቃል ጠፋኝ። “እስከዛሬ…” አልኳት በቀስታ። “ከአጠገቤ ሁነሽ እያስመሰልሽ ነበር?” “አይ…” አለች በፍጥነት። “እኔ…” “በቃ!” አቋረጥኳት። “እባክሽ… ውጪልኝ።” በእንባ ተመለከተችኝ። “እባክህ…” “ውጪልኝ!” ድምፄ ክፍሉን ሞላው። “እባክሽ… አሁን ውጪልኝ…” እሷም በቀስታ ወደ በሩ ሄደች። በበሩ እጇን እያሳረፈች... ወደ እኔ ተመለከተች። “ይቅር በለኝ…” አለችኝ። እኔ ግን ጀርባዬን አዞርኩባት “ውጪ…” በሩን ከፈተች። ከዚያ ሳትመለከተኝ ወጣች። ጓ! እኔም በኃይል በሩን ዘጋሁት። በሩን ተደግፌ አለቀስኩ.....           ይሄ ፅሁፍ 30❤️ ካገኘ🤗        .........ይቀጥላል.........          @Rufaylen13 💫               ✍️ ህላዌ💕

  • https://t.me/yehiwotmengednameker