የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ- አማርኛ ልሳን
Статистикаየብልፅግና ፓርቲ የህዝባችንን የዘመናት ጥያቄ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተገቢውን ምላሽ የሰጠ በመሆኑ ለሲዳማ ህዝብ ባለውለታ ነው።
- Последний пост
- 11 мая
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 15 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ብልፅግና ፓርቲን በመወከል ለሲዳማ ክልል ምክር ቤት በሀዋሳ ምርጫ ክልል ፓርቲው ያቀረባቸው እጩዎች፦ ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገርነት የምታደርገው ጉዞ ይሳካ ዘንድ ብልፅግናን ይምረጡ !! #የምርጫ_ምልክታች_የስንዴ_ነዶ_ነው #ኢትዮጵያን_ወደ_ተምሳሌት_ሀገር #sidamaprosperity አማርኛ ገጽ:- https://www.facebook.com/share/1GYi96GQ3s/ Sidaamu Afoo: https://www.facebook.com/profile.php?id=100061239812520&mibextid=ZbWKwL Telegram Amharic Channel https://t.me/sidamaprosperitypary Sidaamu Afoo Channel https://t.me/sidaamujireenyu What's up https://chat.whatsapp.com/J0l8S57J46EAoZyyIoMfyV YouTube : http://www.youtube.com/@sidaamaregionprosperitypar3217 Tik tok http://tiktok.com/@sidamaprosperity
ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ብልፅግና ፓርቲን በመወከል ለሲዳማ ክልል ምክር ቤት በበንሳ ምርጫ ክልል ፓርቲው ያቀረባቸው እጩዎች፦ ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገርነት የምታደርገው ጉዞ ይሳካ ዘንድ ብልፅግናን ይምረጡ !! #የምርጫ_ምልክታች_የስንዴ_ነዶ_ነው #ኢትዮጵያን_ወደ_ተምሳሌት_ሀገር #sidamaprosperity አማርኛ ገጽ:- https://www.facebook.com/share/1GYi96GQ3s/ Sidaamu Afoo: https://www.facebook.com/profile.php?id=100061239812520&mibextid=ZbWKwL Telegram Amharic Channel https://t.me/sidamaprosperitypary Sidaamu Afoo Channel https://t.me/sidaamujireenyu What's up https://chat.whatsapp.com/J0l8S57J46EAoZyyIoMfyV YouTube : http://www.youtube.com/@sidaamaregionprosperitypar3217 Tik tok http://tiktok.com/@sidamaprosperity
ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ብልፅግና ፓርቲን በመወከል ለሲዳማ ክልል ምክር ቤት በአለታ ወንዶ የምርጫ ክልል ፓርቲው ያቀረባቸው እጩዎች፦ ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገርነት የምታደርገው ጉዞ ይሳካ ዘንድ ብልፅግናን ይምረጡ !! #የምርጫ_ምልክታች_የስንዴ_ነዶ_ነው #ኢትዮጵያን_ወደ_ተምሳሌት_ሀገር #sidamaprosperity አማርኛ ገጽ:- https://www.facebook.com/share/1GYi96GQ3s/ Sidaamu Afoo: https://www.facebook.com/profile.php?id=100061239812520&mibextid=ZbWKwL Telegram Amharic Channel https://t.me/sidamaprosperitypary Sidaamu Afoo Channel https://t.me/sidaamujireenyu What's up https://chat.whatsapp.com/J0l8S57J46EAoZyyIoMfyV YouTube : http://www.youtube.com/@sidaamaregionprosperitypar3217 Tik tok http://tiktok.com/@sidamaprosperity
ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ብልፅግና ፓርቲን በመወከል ለሲዳማ ክልል ምክር ቤት በአርቤጎና ምርጫ ክልል ፓርቲው ያቀረባቸው እጩዎች፦ ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገርነት የምታደርገው ጉዞ ይሳካ ዘንድ ብልፅግናን ይምረጡ !! #የምርጫ_ምልክታች_የስንዴ_ነዶ_ነው #ኢትዮጵያን_ወደ_ተምሳሌት_ሀገር #sidamaprosperity አማርኛ ገጽ:- https://www.facebook.com/share/1GYi96GQ3s/ Sidaamu Afoo: https://www.facebook.com/profile.php?id=100061239812520&mibextid=ZbWKwL Telegram Amharic Channel https://t.me/sidamaprosperitypary Sidaamu Afoo Channel https://t.me/sidaamujireenyu What's up https://chat.whatsapp.com/J0l8S57J46EAoZyyIoMfyV YouTube : http://www.youtube.com/@sidaamaregionprosperitypar3217 Tik tok http://tiktok.com/@sidamaprosperity
ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ብልፅግና ፓርቲን በመወከል ለሲዳማ ክልል ምክር ቤት በደሴ ምርጫ ክልል ፓርቲው ያቀረባቸው እጩዎች፦ ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገርነት የምታደርገው ጉዞ ይሳካ ዘንድ ብልፅግናን ይምረጡ !! #የምርጫ_ምልክታች_የስንዴ_ነዶ_ነው #ኢትዮጵያን_ወደ_ተምሳሌት_ሀገር #sidamaprosperity አማርኛ ገጽ:- https://www.facebook.com/share/1GYi96GQ3s/ Sidaamu Afoo: https://www.facebook.com/profile.php?id=100061239812520&mibextid=ZbWKwL Telegram Amharic Channel https://t.me/sidamaprosperitypary Sidaamu Afoo Channel https://t.me/sidaamujireenyu What's up https://chat.whatsapp.com/J0l8S57J46EAoZyyIoMfyV YouTube : http://www.youtube.com/@sidaamaregionprosperitypar3217 Tik tok http://tiktok.com/@sidamaprosperity
ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ብልፅግና ፓርቲን በመወከል ለሲዳማ ክልል ምክር ቤት በጉጉማ ምርጫ ክልል ፓርቲው ያቀረባቸው እጩዎች፦ ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገርነት የምታደርገው ጉዞ ይሳካ ዘንድ ብልፅግናን ይምረጡ !! #የምርጫ_ምልክታች_የስንዴ_ነዶ_ነው #ኢትዮጵያን_ወደ_ተምሳሌት_ሀገር #sidamaprosperity አማርኛ ገጽ:- https://www.facebook.com/share/1GYi96GQ3s/ Sidaamu Afoo: https://www.facebook.com/profile.php?id=100061239812520&mibextid=ZbWKwL Telegram Amharic Channel https://t.me/sidamaprosperitypary Sidaamu Afoo Channel https://t.me/sidaamujireenyu What's up https://chat.whatsapp.com/J0l8S57J46EAoZyyIoMfyV YouTube : http://www.youtube.com/@sidaamaregionprosperitypar3217 Tik tok http://tiktok.com/@sidamaprosperity
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። በብልፅግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በ2018 በጀት ዓመት በሦስተኛው ሩብ ዓመት ያከናወናቸውን የፓርቲ ሥራዎች የዕቅድ አፈጻጸም የሚገመግምበት መድረክ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ ላይ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ እና የፓርቲው ቅ/ጽ/ቤት ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ጨምሮ የሁሉም ዞኖች እና የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የፓርቲ አመራሮች በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩም ላይ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ንቅናቄ፣ የአመራር ብቃት እና የመዋቅሮች ጥንካሬ፣በፓርቲው መሪነት በክልሉ የተከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች እንዲሁም የ7ኛውን ሃገራዊ ምርጫ መንትያ ግቦች ለማሳካት የተሰሩ ስራዎች በጥልቀት በመገምገም ባለፉት ዘጠኝ ወራት የታዩ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠልና ድክመቶችን ለማረም በተለይ የአፈፃፀም ክፍተቶችን በመለየት በቀሪ ሩብ ዓመት በሚከናወኑ ተግባራት ላይ የጋራ አቅጣጫ የሚቀመጥበት መድረክ እንደሚሆን ይጠበቃል። #ኢትዮጵያን_ወደ_ተምሳሌት_ሀገር !! #sidamaprosperity ለተጨማሪ የሚዲያ አማራጮች:- Sidaamu Afoo: https://www.facebook.com/profile.php?id=100061239812520&mibextid=ZbWKwL Telegram Amharic Channel https://t.me/sidamaprosperitypary
የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፡- "በመጀመሪያ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን ለማለት እወዳለሁ በማለት የመልካም ምኞት መግለጫቸውን አቅርበዋል። የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል የጨለማ መሸነፍ፣የብርሃን መገለጥ እና የሞት በድል መንሳት ማሳያ ነው። ይህ ታላቅ በዓል እኛም እንደ አንድ ህዝብ ካለፉት ፈተናዎቻችን ተምረን፣በይቅርታና በአንድነት ወደ ብሩህ ተስፋ የምንሸጋገርበትን ብርታት የሚሰጠን ልዩ ወቅት ነው። የትንሳኤ በዓሉ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የድነት ምልክት፣የፍቅር መገለጫ እና የተስፋ መነሻ እንደሆነም ያስተምራል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ኃጢአት በመስቀል ተሰቅሎ ሕይወትን ሰጥቶናል፤በሦስተኛውም ቀን ከሞት ተነስቶ የዘላለም ሕይወትን አብስሮልናል። የጌታችን ስቅለት የመሥዋዕት ፍቅር እና የትንሣኤው ድል የሰው ልጅ ሁሉ በተስፋ እንዲኖር ያደረገ ታላቅ ክስተት እና የዓለምን ሀጢያት ተሸክሞ የሰዉ ልጅን ከሀጢያት ለማፅዳት በመስቀል ላይ ፍቅሩን የገለፀበት ነው። የዘንድሮውን የትንሳኤ በዓል ልዩ የሚያደርገው የብልፅግና ጉዟችንን አጠናክረን ለማስቀጠል ዳግም ቃል የምንገባበት መሆኑ፤ 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ለማድረግ ዝግጅት እየተጠናቀቀ ባለበት ወቅት ላይ የምናከብረው መሆኑ ነው። አቶ አብርሃም አክለውም እንደገለፁት የዘንድሮውን ምርጫ ዴሞክራሲያዊ፣ተኣማኒና ተቀባይነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ዜጎቻችን ይህንን የመምረጥና ድምፅ የመሆን አጋጣሚውን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በመጠቀም ነገ የሚመራቸውን መንግስትና ፓርቲ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የመምረጥ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል። በመጨረሻም ህዝቤ ክርስቲያኑ በዓሉን ስያከብር መደጋገፍ፣አብሮነትና መረዳዳትን በማጠናከር የተቸገሩትን በመርዳት፣የታመሙትን በመጠየቅና ካለው ላይ በማካፈል የትንሳኤውን እውነተኛ ትርጉም በተግባር ልገልጸው የሚገባ ሲሆን የትንሳኤ በዓል የእርቅ በዓል እንደመሆኑ፣በውስጣችን ያለውን ቂምና ጥላቻ አስወግደን በይቅርታ የምንታደስበት ወቅት ሊሆን ይገባል ብለዋል። በቀጣይ የክልላችን ብሎም የሀገራችንን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በጀመርነው የብልፅግና ጉዞ ላይ የትንሳኤው ብርሃን አዲስ ጉልበትና መነሳሳትን እንደሚፈጥርልን ያለኝን እምነት እገልጻለሁ ብለዋል። በድጋሚ በዓሉ የሰላም፣የጤና፣የአብሮነት እና የብልፅግና እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ። መልካም የትንሳኤ በዓል! አቶ አብርሃም ማርሻሎ የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ #Sidamaprosperity አማርኛ ገጽ:- https://www.facebook.com/share/1GYi96GQ3s/ Sidaamu Afoo: https://www.facebook.com/profile.php?id=100061239812520&mibextid=ZbWKwL Telegram Amharic Channel https://t.me/sidamaprosperitypary Sidaamu Afoo Channel https://t.me/sidaamujireenyu What's up https://chat.whatsapp.com/J0l8S57J46EAoZyyIoMfyV YouTube : http://www.youtube.com/@sidaamaregionprosperitypar3217 Tik tok http://tiktok.com/@sidamaprosperity
без подписи
ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጅ ኀጢአትና በደል ይቅር ባይነቱን ፣ቸርነቱን፣ፍቅሩን፣ትህትናውንና መልካምነቱን ነብሱን እስከ መስጠት በቀራንዮ መስቀል አሳይቷል፦ አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለፋሲካ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሲሉ የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፏል ። የርዕሰ መስተዳድሩ እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት እንደሚከተለው ቀርቧል፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጅ ኀጢአትና በደል ይቅር ባይነቱን ፣ቸርነቱን፣ፍቅሩን፣ትህትናውንና መልካምነቱን ነብሱን እስከ መስጠት በቀራንዮ መስቀል አሳይቷል። ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሁላችን ኃጢያት ስርየት ሲል በመስቀል ላይ የተሰቀለበት ፣በሰው ልጆች እና በእግዚአብሔር መካከል የነበረውን የሞትና የጥል ግድግዳ አፍርሶ ዳግም ዘላለማዊ ህይወት የሰጠበት እለት በመሆኑ ለዚህ ታላቅ መንፈሳዊ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ማለት እፈልጋለሁ። ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ የኃጢያት ቤዛ በመሆን በመስቀል ላይ ተሰቅሎ መሞቱና በሦስተኛው ቀን ከሞት በመነሳት የትንሳዔን ህይወት የሰጠን እሱ ለፈጠረው ለሰው ልጆች ሁሉ ያለውን ታላቅ ፍቅሩን የገለፀበት ዋነኛው መንገድ ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ ትልቁ ስጦታው የዘላለም ህይወት ነው ፤ ይህንን የዘላለም ህይወትን ያገኘነው በመስቀል ላይ ሞት ነው ፤ የመስቀል ላይ ሞቱን የፈፀመው ስለ ሰው ልጅ ፍቅር ሲል ነው ፤ እኛም ፍቅር ትልቅ ትርጉም እንዳለው መረዳት ያስፈልገናል ፤እንዲንዋደድ እንዲንፋቀር ፈጣሪ በቃሉ መክሮናል አዞናልም። ...ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ ብለው ፈጣሪ በቃሉ ነግሮናል። ከእነዚህ የምበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለም። ስለዚህም እርስ በርሳችን እንዲንዋደድ ያስፈልገናል። በፍፁም ልባችን እየተዋደድን ፥እየተሳሰብን ፥እየተረዳዳን፥ እየተጋገዝን ከሆነ ፍቅር መሃላችን አድሮዋል ማለት ነው። ስለሆነም ፍቅር ለሰው ልጆች ሁሉ የሰላም ምንጭና መሰረት በመሆኑ በዓሉን ስናከብር ከጥላቻ ርቀን አንዳችን ለአንዳችን ያለንን በጎነትና ፍቅርን የምትገልፁበትና የምትተሳሰቡበት ዕለት እንዲሆን እመኛለሁ። የሁላችንም የሆነችሁ ሀገራችን ኢትዮጵያ እንድትበለጽግ እየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ መስቀል ሆኖ በተግባር ባሳየን ትህትናና ፍቅር መሰረት ከግላዊ ጥቅምና ፍላጎት ተላቀን፤ እርስ በርሳችን በመተጋገዝና በመተሳሰብ ህዝባዊ ጥቅምን አስቀድመን ለችግሮችና ለፈተናዎች ሳንበገር የሀገራችን የልማትና የብልፅግና ትንሳዔዋን አናፋጥን እላለሁ። እየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች በመስቀሉ ፍቅርን፣ትህትናን፣መልካምነትን፣ሩህሩህነትን እና ለሌሎች ስንል መስዋዕትነት መክፈልን አስተምሮናል። እሱ ባስተማረን ፍቅርና ርህራሄ በአካባቢያችንና በዙሪያችን አቅመ ደካማዎችና ረዳትና ጧዋሪ የሌላቸው አረጋውያንን ያለንን በማካፈል፣ በመርዳትና በመደገፍ በዓሉን በደስታ እናክብር እላለሁ ። በድጋሚ እንኳን ለፋሲካ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!! አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ሚያዝያ 03/2018
без подписи
እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን! የትንሣኤ በዓል በክርስቲያኖች ዘንድ ልዩ ቦታ ያለው በዓል ነው። ሞት የተሻረበትና ሕይወት ዋስትና ያገኘበት ነው። ከሞት ባሻገር ሕይወት፣ ከመቃብር ባሻገር ትንሣኤ መኖሩ የታወጀበት ነው። ሞት መጨረሻ መቃብር መዳረሻ አለመሆናቸው የተረጋገጠበት ነው። በአዳም ምክንያት ወደ ምድር የወረደው ሰው፣ በክርስቶስ ምክንያት ወደላይ የወጣበት ነው። የዘንድሮውን ትንሣኤ የምናከብረው ሀገራችን ኢትዮጵያ በሚያልፍ ፈተና ውስጥ እንዳለች እያሰብን ነው። መንገዳችን ረጅም፣ ጉዟችን ፈታኝ መሆኑን እናውቃለን። ብርሃን እንዳናይ የሚጋርዱ፣ በጥልቁ ጨለማ ጠፍተን እንድንቀር አሥረው ለመያዝ የሚሞክሩ ወጥመዶች ብዙ ናቸው። ወደ ተስፋ ምድር እንዳንሻገር የሚጎትቱ ሰበቦች ሞልተዋል። ዳሩ ግን ከሕማማቱ ወዲያ ትንሣኤ፣ ከዕንቅፋቱ ባሻገር ስኬት እንደሚጠብቀን አምነን እንታገላለን። በትንሣኤው ዋዜማ - ርግጠኞች፣ ተስፈኞች፣ ተስፋ ቆራጮች፣ ወሬኞች፣ ተስፋ አስቆራጮች፣ ተጠራጣሪዎች ነበሩ። ርግጠኞቹ የሕማማቱ ፈተና እንደሚያልፍ ርግጠኞች ነበሩ። የዕለተ ስቅለት መከራ፣ለዕለተ ትንሣኤ ዋዜማ ለመሆኑ ርግጠኞች ነበሩ። የድንጋዩ በር፣ የበሩ ማኅተም እና የመቃብሩ ጠባቂዎች ትንሣኤውን እንደማያስቀሩት ርግጠኞች ነበሩ። የሚናፈሰው ወሬ እና የሚሠራጨው አሉባልታ እድሜው አጭር መሆኑን ርግጠኞች ነበሩ። ርግጠኞችም ስለሆኑ መሥዋዕትነትን ለመክፈል ዝግጁዎች ነበሩ። እውነቱን ለመመስከር ቆራጦች ነበሩ። በመስቀሉ ሥር ለመገኘት ደፋሮች ነበሩ። ተስፈኞቹ የርግጠኞቹን ያህል ሳያዩ የሚያምኑ አልነበሩም። ግን አንዳች መልካም ነገር ይጠብቁ ነበር። የተሰጠውን ትምህርት፣ የተደረገውን ተአምራት ሰምተዋል፤ አይተዋል፤ አንዳች ነገርም ጠብቀዋል። ነገር ግን ተገቢውን መሥዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁዎች አልነበሩም። እውነትን ለመድፈር ቆራጦች አልነበሩም። ሐሰቱን ለመጋፈጥ ዐቅም አላገኙም። ቢያንስ ግን አንደበታቸውን ከክፉ ከልክለዋል። ተጠራጣሪዎች አጥር ላይ የነበሩ ናቸው። በጥብርያዶስ ይበላሉ፣ በጎልጎታ ይክዳሉ። በሆሳዕና ይዘምራሉ፣ በሊቶስጥራ ይሸሻሉ፡፡ ተአምር ለማየት ይመጣሉ፣መከራ ለማየት ይሳቀቃሉ፡፡ ከደስታው አውጡልኝ፣ ከመከራው ጦመኛ ነኝ የሚሉ ናቸው። ተስፋ ቆራጮች በሚያዩትና በሚሰሙት ቶሎ የሚወሰዱ ናቸው። በእውነትና በሐሰት፣ በፍርሃትና በጽናት መካከል ያለው ድንበር የጠፋባቸው ናቸው። ሕማማቱ ሲመጣ በቶሎ ወደ ትዝታ ገቡ። ሁሉንም ነገር የትናንት ታሪክ ብቻ አድርገው ወሰዱት። ሁሉንም ነገር “ልጡ የተራሰ፣ መቃብሩ የተማሰ” አድርገው ቆጠሩት። ከግራ ከቀኝ የሚሰሙት አሉባልታ፣ ከፊት ከኋላ የሚመጣው ጫጫታ፤ ከወዲህ ከወዲያ የሚማጣው እሳት፣ ከዚህም ከዚያም የሚያዩት መዓት አስፈራቸው። ነገን አስረሳቸው። በዚህ የተነሣ ተስፋ ቆርጠው ወደ ኋላ ተመለሱ። ወሬኞች ድሮም ወሬ ስቧቸው የመጡ ናቸው። ምን አለ ምን ተባለ ብለው የተሰባሰቡ ናቸው። የሰሙትንም ያልሰሙትንም፤ የሚያውቁትንም የማያውቁትንም፤ እውነቱንም ሐሰቱንም እያደባለቁ ኢየሩሳሌምን በወሬ ሞሏት። ቢያንስ ከትንሣኤው 15 ዓመት በኋላ ወንጌሉን የጻፈው ማቴዎስ፣ እስከዚያ ዘመን ድረስ ወሬው ብዙ ተቀባይ እንደነበረው ገልጧል። ተስፋ አስቆራጮች ዓላማቸው ሰውን ሁሉ ከትንሣኤ መንገድ ማራቅ ነበር። እነርሱም አይሄዱ፣ ሰውም አያስኬዱ። ከመጀመሪያው አልተቀበሉትም፤ በኋላም አልፈለጉትም። ብዙ ሰዎች እንደተከተሉት ሲያውቁ ደግሞ ቅናት አቃጠላቸው፤ ክፋት አንገበገባቸው። ክርስቶስን ከሰሱ፤ ራሳቸው ምስክር ሆኑ፤ በመጨረሻም ራሳቸው ፈረዱ። መቃብሩን ዘጉ፤ ጠባቂ አስቀመጡ። በማኅተም አሸጉ። ነገር፣ ያለቀና የተቆረጠ መሰላቸው። የትንሣኤ በዓል የእነዚህን ሁሉ እውነተኛ ማንነት የገለጠ ነው። ርግጠኞች የቆራጥነታቸው ውጤት በትንሣኤ አገኙ። ተስፈኞች እንዲህ ለሚያልፍ ጊዜ ባለመጽናታቸው አዘኑ። ተስፋ ቆራጮች አሻግሮ ማየት አቅቷቸው ከቦታቸው በመጥፋታቸው ተፀፀቱ። ወሬኞች በትንሣኤው እውነት የተነሣ ያ ሁሉ ወሬ እንደ ናቡከደነፆር ሐውልት ሲፈረካከስ አዩት። ተስፋ አስቆራጮች የገደሉት ክርስቶስ ሲነሣ፣ የዘጉት መቃብር ሲከፈት፣ ያተሙት ማኅተም ሲቀደድ፣ የመደቧቸው ጠባቂዎች ሲሸሹ በዓይናቸው በብረቱ አዩ። ትንሣኤው የሚነገር ሐቅ፣ የሚታይ እውነት ሆነ። ተጠራጣሪዎች ግን አሁንም አጥራቸው ላይ ሆነው ከግራም ከቀኝም ሳይሆኑ ቀሩ። የኢትዮጵያችንም ነገር እንዲሁ ነው። በኢትዮጵያ ለውጥ ርግጠኞች የሆኑት ዋጋ ይከፍላሉ፤ ርግጠኝነትን ፈርተው ተስፈኞች የሆኑት ቢያንስ አንደበታቸውን ከክፉ ይጠብቃሉ፡፡ ተስፋ ቆራጮች ነገን ማየት ስለሚሳናቸው መንገዳቸውን ይቀይራሉ፡፡ ወሬኞች አውርቶ አዳሪዎች በመሆናቸው የወሬ እንጀራ ይጋግራሉ። ተስፋ አስቆራጮች “ወተቱን አጥቁረው፣ ማሩን አምርረው” የዋሖችን አታለሏቸው፡፡ ተጠራጣሪዎች አንዴ ትኩስ አንዴ ቀዝቃዛ ሲሆኑ፣ ለብ ብለው ቀሩ። ኢትዮጵያችን ግን ትንሣኤዋን እያየች ነው። መግነዙን ፈትታዋለች፣ መቃብሩን ከፍታዋለች፤ ማኅተሙን ቀዳዋለች። ወሬኞች ከመቃብር ጠባቂዎች ጋር ተማክረው የሚያወሩትን ወሬ የምትሰማበት ጆሮ የላትም። ትንሣኤዋን አይለውጠውምና። እሷ ከዚህ በኋላ የምትጠብቀው ዕርገትን ነው። የምትጓዘው ኃይል እንደሚወርድላት አረጋግጣ ነው። ወደኋላ መመለስ የለም። ሕማማት አልፏል፤ዓርብም አልፏል፤ ቅዳሜም አልፏል። ትንሣኤ መጥቷል። በትንሣኤ ሌሊት የተኙ አልሰሙ ይሆናል። በተስፋ አስቆራጮች ተታለው የሄዱ ዜናው አልደረሳቸው ይሆናል። ትንሣኤ ግን እውን ሆኗል። ከቻላችሁ አጥር ላይ ያላችሁ ውረዱ። ተስፈኞች ርግጠኞች ሁኑ። ተጠራጣሪዎች እመኑ። ወሬኞች ከአፍ ወደ መዳፍ ተለወጡ። ምክንያቱም - ኢትዮጵያ ወደ ትንሣኤ ተቃርባለች። የኢትዮጵያ ትንሣኤ ከሚበሰርባቸው ምዕራፎች አንዱ ግንቦት ላይ የሚካሄደው ምርጫ ነው። ትንሣኤን ያለ ሕማማት እንደማናስበው ሁሉ ዴሞክራሲንም ከውጣ ውረድ ነጥሎ ማየት አይቻልም። በዓለም ላይ በደልዳላ መንገድ ተጉዞ ዴሞክራሲን የገነባ ሀገር የለም። ዴሞክራሲና ብልጽግና ያለ ጽናት አይሳኩም። ከእኛ በፊት ዐመጻውን በትዕግሥት የመከቱ ተሻግረዋል፤ ሑካታውን በጽናት ያለፉ አሳክተዋል። ብንመኝም ፈተናውን አናስቀርም፤ መጽናት ግን እንችላለን። ከድህነት መውጫው ብርታታችን፣ ወደ ዴሞክራሲ መድረሻችው ትዕግሥታችን እንደሆነ አምነን ለኢትዮጵያ ትንሣኤ በሙሉ ልባችን እንትጋ!! በድጋሚ መልካም የትንሣኤ በዓል ይሁንልን። ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!! ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ! ሚያዝያ 03 ቀን 2018 ዓ.ም