ኪነጥበብ ዘሰንበት ት/ቤት
Статистикаየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች የሰንበት ት/ቤትና ግቢ ጉባኤያት መንፈሳዊ ግጥሞችን፣ መነባንቦችን፣ ትረካዎችን፣ ዜናዎችን ፣ደብዳቤዎችን፣ ድራማዎችን፣ እንቆቅልሾችን፣ አጫጭር ጭውውቶችን፣ እንካሰላንቲያዎችንና መንፈሳዊ ማስታወቂያዎችን... የሚቀርቡበት የሰንበት ት/ቤቶች የኪነጥበብ ቻናል ነው።
- Последний пост
- 10 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 836
- 1/48двое суток
- 2 104
- 1/72трое суток
- 2 269
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
( የፍልሰታ መዝሙር ) ወፌ ሰንብታ መጣች በፍልሰታ የተወደዳችሁ የኪነጥበብ ዘሰንበት ት/ቤት ቤተሰቦች እንኳን ለፆመ ፍልሰታ በሰላም አደረሠን አደረሳችሁ !! ከእመቤታችን ዕርገትና ትንሣኤ በረከት እንዲያሳትፈን ፤ የእመቤታችንን ጣዕሟን በአንደበታችን ፍቅሯን በልባችን ያሳድርብን። ፆማችን በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የጽድቅና የበረከት ፆም ያድርግልን። የኪጥበብ ቤተሰብ ይሁኑ ! @sundayschoolstudents የሰንበት ት/ቤት ኪነጥበብ ክፍል !
ትመስሊ ፊደለ ወትወልዲ ወንጌለ ወታገምሪ መስቀለ : (ፊደልን ትመስያለሽ ወንጌልን ትወልጃለሽ መስቀልን ትወስኛለሽ (ትችያለሽ)) ትመስሊ ሰማየ ወትወልዲ ፀሐየ ወታገምሪ አዶናየ : (ሰማይን ትመስያለሽ ፀሐይን ትወልጃለሽ አዶናይን ትወስኛለሽ (ትችያለሽ)) ትመስሊ መሶበ ወትወልዲ ኮከበ ወታፀግቢ ርኁበ : (መሶብን ትመስያለሽ ኮኮባዊ ኅብስትን ትወልጃለሽ ረኃብተኛን ታጠግቢያለሽ) ትመስሊ መቅደሰ ወትወልዲ ንጉሠ ወታገምሪ መንፈሰ ቅዱስ : (መቅደስን ትመስያለሽ ንጉሥን ትወልጃለሽ መንፈስ ቅዱስንም ትችያለሽ) ትመስሊ ጽላተ ወትወልዲ ታቦተ ወታገምሪ መለኮተ : (ጽላትን ትመስያለሽ ታቦትን ትወልጃለሽ መለኮትን ትሸከሚያለሽ) ትመስሊ ደመና ወትወልዲ ኅብስተ መና ወታገምሪ ጥዒና : (ደመናን ትመስያለሽ ኅብስተ መናን ትወልጃለሽ መድኃኒት ጌታንም ትወስኛለሽ (ትችያለሽ)) ትመስሊ ገራኅተ ወታፈርዪ ሰዊተ ወታጸድቂ ነፍሳተ : (እርሻን ትመስያለሽ እሸትን ታፈሪያለሽ ነፍሳትን ታጸድቂያለሽ) ትመስሊ ስኂነ ወትወልዲ መድኅነ ወትፈውሲ ቁሱላነ : (ስኂን የሚባል ሽቱን ትመስያለሽ መድኃኒትንም ትወልጃለሽ ቁስለኞችን ትፈውሻለሽ) ትመስሊ ምሥራቀ ወትወልዲ መብረቀ ወታለብሲ ዕሩቀ : (ምሥራቅን ትመስያለሽ መብረቅን ትወልጃለሽ የተራቆተውን ታለብሻለሽ) ❝ ኦ ማርያም በእንተዝ ናፍቅረኪ ወነዓብየኪ እስመ ወልድኪ ለነ መብልዓ ጽድቅ ዘበአማን ወስጤ ሕይወት ዘበአማን ❞ (አባ ሕርያቆስ) ማርያምን ! ማርያምን እወዳታለሁ !! የተወደዳችሁ የኪነጥበብ ቤተሰቦች ፥ ለእናታችን ለእመቤታችን ለተዋሕዶ ርስታችን ቅድስት ድንግል ማርያም “የፍልሰታ ጾም - ጾመ ፍልሰታ” በሠላም በፍቅር አደረሳችሁ አደረሰን ። የኪነጥበብ ቤተሰብ ይሁኑ ! @sundayschoolstudents የሰንበት ት/ቤት ኪነጥበብ ክፍል !
++ በሠርጋቸው ዕለት ባል ሚስቱን ምን አላት ? በሰርጋቸው ዕለት ባል ለሚስቱ እንዲህ አላት፥ የኔ ፍቅር ከእንግዲህ አንቺ ማለት ለኔ የመኖር ትርጉሜ ነሽ። በእኔ እና ባንቺ መሃል ከእንግዲህ ምንም ዓይነት ድብብቆሽ ሊኖር አይገባም። የኔ ውድ... በፊት እኔ ትልቅ ልጅ ነበርኩ፣ አሁን ግን በድጋሜ ህፃን እሆናለሁ። ትዝ ይለኛል ህፃን እያለሁ ምግብ በልቼ እንደሆነ ወይም እርቦኝ እንደሆነ የምታውቀኝ እናቴ ነበረች። ጥዋት ከእንቅልፍ የምትቀሰቅሰኝ እናቴ ነበረች። ከቤት ከመውጣቴ በፊት መስተካከል ያለበትን ነገሮች አስተካክላ የምትሸኘኝ እናቴ ነበረች፣ ከእንግዲህ ግን እናቴ አንቺ ነሽ። ከእንግዲህ የኔን ደካማ ጎን የምታውቅ ሌላ እናት የለችም። ከእንግዲህ ጥማቴን የምታውቅ ሌላ እናት የለችም። አየሽ ፍቅር፥ ልጅ እያለሁ የሆንኩትን ነገር ሁሉ ለእናቴ ነበረ መጥቼ የምነግራት እሷም ምሥጢሬን ለማንም ነግራ አታውቅም። አሁን ግን እናቴ አንቺ ነሽ ምሥጢሬን የምነግርሽ ላንቺ ብቻ ነው። ለማንም ምስጢሬን አሳልፈሽ አትስጪ። ልጅ እያለሁ ብዙ ጥፋቶችን አጠፋ ነበረ። እናቴም ለጊዜው በጣም ብትቆጣኝም ቁጣዋ ግን ብዙም አይቆይም ወዲያውኑ ተመልሳ መሳቅ ትጀምራለች። የኔ ፍቅር ...ሰው ነኝና ምናልባት በስህተት አንቺንም ላስከፋሽ እችላለሁ። እባክሽን ግን ቂም አትያዥብኝ፣ ጥፍቴን ግን አይተሽ ዝም አትበይኝ ምክር ስጪኝ እቀበላለሁ። የኔ ማር ደግሜ የምነግርሽ ነገር ለሰዎች ወሬ በፍጹም ጆሮ አትስጪ ከእንግዲህ ወዲህ ላንቺ ከእኔ የሚቀርብ ማንም ሊኖር አይችልም ለኔም ካንቺ በላይ ሰው የለኝም። የኔ ውድ የብዙ ሰዎች ትዳር መፍረስ ምክንያት ጎረቤት አልያም የጓደኛ ብዛት ነው ሲባል እሰማለው። እናም እውነት ከሆነ እነዚህን ነገሮች ከልክ በላይ አታቅርቢ። በፈጣሪ ፊት ቃል እገባለሁ፣ እኔም ምርጡ ባልሽ ሁሌም ከጎንሽ መቆም የምችል፣ ከማንም አስቀድሜ ለልጄ፣ ለሚስቴ የሚል መልካም ባል እሆንልሻለሁ። ደስታሽ ደስታዬ፣ ሐዘንሽ ሐዘኔ፣ ሳቅሽ ሳቄ ሆኖ እስከ ዘለዓለም ድረስ ይኖራል። በቃላቶቼ ከምገልፀው በላይ በጣም በጣም እወድሻለው አላት አሉ። ባሎች ሆይ፥ ሴት ልጅ ካንተ መለየት ካልፈለገች ስለምትጨነቅልህ ነው፣ ሴት ልጅ ከተናደደችብህ እያመነችህ፣ ስለከዳሀት ነው፣ ጥያቄ ካበዛችብህ ግልፅነት ስለምታስቀድም ነው፣ ነገሮችን ችላ ብላ ማለፈ ከጀመረች፣ ተስፍ ቆርጣለች ማለት ነው። ባሎች፥ ሴት ልጅ ለአንተ ሴት ልጅ እናት ናት፣ ሴት ልጅ ሚስት ናት፣ ሴት ልጅ እህት ናት፣ ሴት ልጅ ጓደኛ ናት። ሴት ልጅ ከመውደድህ በፊት መጀመሪያ እሷን ማክበር ተማር። ምክንያቱም ካከበርካት እሷን ለመጉዳት የምታስብበት ጊዜ አይኖርህም ዘለዓለም እንዳፈቀርካት ትኖራለህ እንጂ። ለጊዜያዊ ስሜት ብቻ የምታስብ አትሁን፣ እሷ ከስሜትህ በላይ መሆኗ አትዘንጋ። ያለሷ ሕይወትህ ባዶ ነው። ሕይወትህ ትርጉምና ጣዕም እንዲኖረው ፍቅረኛህ፣ እናትህ፣ እህትህ ወሳኝ ናት። አንዳንዱ ልቡ የታወረና የራሱን እንጂ የሷን ሕይወት የማይገደው ሴትን ለትዳር ጠልቶ ለአዳር ብቻ ነው የሚፈልጋት። ይህ ግን ከንቱነት ነው። አድምጣት፣ ተረዳላት፣ ተንከባከባት፣ በቂ ጊዜ ስጣት፣ ሁሌ ከአጠገቧ አትለያት። የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን አንተን እንዲህ አለህ፥ ባል ሆይ ከገዛ ራስህ ሕይወት በላይ ሚስትህን አፍቅራት፡፡ እውነተኞች ኹኑ እንጂ በፍጹም አትለያዩ፡፡ በውጭ ከመቆየት ይልቅ ከሚስትህ ጋር በቤትህ አብረሃት ማሳለፍን ምርጫህ ይኹን፡፡ አክብራት፤ በግልፅም አድንቃት፡፡ ጥፋት ስታጠፋ በትዕግሥት ምከራት፡፡ አብራችሁ ጸልዩ፡፡ አብራችሁ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሒዱ፡፡ አብራችሁ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ንባባትና ስለ ጸሎት ተወያዩ፡፡ ትዳራችሁ እንደዚህ ከኾነ የቅድስና ሕይወታችሁ ከመነኰሳት ሕይወት ጋር የሚነጻጸር ይኾናል። ስለዚህ ባሎች ሆይ ሚስቶቻችሁን እንዲሁ በሏቸው። ይህን ብታደርጉ ፍቅራችሁም እየጨመረ ይሔዳል። የፍቅር አምላክ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅሩን ያብዛላችሁ አሜን። የኪነጥበብ ቤተሰብ ይሁኑ ! @sundayschoolstudents የሰንበት ት/ቤት ኪነጥበብ ክፍል !
++ ኪነጥበብ - መነባንብ !! (ርዕስ - ግቢ-ጉባኤ ትዝ አለኝ) የፍረሽ ቅበላው ትምህርት መጀመሪያው፡ የከረመው ግቢ አየሩን ስንቀስመው፡ ዌል ካም ሩጫው መልካም ግርግሩ፡ የልዩ ጉባኤው እሑድ መርሃ ግብሩ፡ . . . . . . . ትዝ አለኝ. . . . . . . . . ነጭ ነጭ ለብሶ ማስታወሻ ይዞ ለጉባኤ መብረር፡ ቀኖናና ዶግማ ሥርዓት ለመማር፡ ደግሞ ተመልሰን ጭምጨማው ችከላው፡ አቤት ተማሪነት ስንቱን አሳለፍነው። . . . . . . . ትዝ አለኝ. . . . . . . . . የበዓል ዋዜማው ማኅሌት ቅዳሴው፡ በተማሪ ድባብ ተመስጠን ስንቆመው፡ መዝሙር ምስጋናውን በኅብረት ስናወርድ፡ የበዓል ድግሱን የፍቅሩን ማዕድ፡ ስንጎራረሰው ሁላችን አንድ በአንድ፡ . . . . . . . ትዝ አለኝ . . . . . . . . . መሮጥ ለአገልግሎት ማዘዝ መታዘዙ፡ ንስሐ አባትን ለማግኘት መፍጠኑ፡ ጭቅጭቅ ንትርክ ክርክሩ ቁጣው፡ ያ ሁሉ ለመልካም በኛ ዘንድ የሆነው፡ . . . . . . ትዝ አለኝ . . . . . . . ለንግስ ተያይዞ ከተማ ማቋረጥ፡ በማታም በሌሊት ዝማሬውን ማቅለጥ፡ ቅዱሳት መካናት አይቶ ለመባረክ፡ ተራራ ቁልቁለት መውጣትና መውረድ በጉልበት በእንብርክክ፡ መጓዝ በመኪና ወደ ፊት መገስገስ፡ የተቀደሰውን ነክቶ ለመቀደስ፡ . . . . . . . ትዝ አለኝ . . . . . . . . ሱባኤና የሰርክ ማኅበር ፀሎቱ፡ ደካማው በብርቱ ሲታገዝ ማየቱ፡ ኧረ እንዴት ደስ ይላል ያ ሁሉ ትጋቱ። . . . . . . . . ትዝ አለኝ . . . . . . . የህይወት ውይይት በክፍል በክፍል፡ ዛሬ ምን አደረግህ አንችስ ምን አገኘሽ ስንል ስንባባል፡ በጠዋት በማታ ተቀሳቅሶ መሄድ ለህይወት መታገል፡ አቤት መጣፈጡ እንዴት ነፍስ ይገዛል፡ የአንዱን ሸክም ሌላው ሲሸከም ደስ ይላል። . . . . . . . . ትዝ አለኝ. . . . . . . . ከምሥራቅ ከምዕራብ ከሰሜን ከደቡብ፡ የመጣነው ሁሉ ለየራሳችን ግብ፡ መስርተን ተገኝተን ጠንካራ ቤተሰብ፡ በማትናወጠው በስላሴ ወደብ፡ ስንሄድ ስንመጣ ሲያየን ጎረቤቱ ይሉ ነበር አጀብ። . . . . . . . . ትዝ አለኝ . . . . . . . . . ገናና ፋሲካ በዓሉ ሲመጣ፡ ሽር ጉድ ስንል ስንገባ ስንወጣ፡ አምናና ታች አምና እዚህ የነበረ ወንድማችን መጣ፡ ብለን በደስታ አቅላችን ስናጣ፡ ሲገኝ ፍሪዳውን ዳቦውን ሲታጣ፡ ለማቅረብ ስንኳትን በቀንና ሌሊት፡ ውሃውን ስንቀዳ ሊጡን ስናቦካ ሲያምርብን የዛንለት፡ እሳቱ ሲገርፈን ጭቃውም ሲነካን፡ ፍፁም ደስ ይለናል ከሌሎች ጋር ሆነን። . . . . . . . . . ትዝ አለኝ . . . . . . . የግንቦት ልደታ በእንግዶች ታጅበን፡ በጧፍ መብራት ደምቀን በዜማ ረስርሰን፡ ስናከብር ማርያምን እማሆይ ጋር ሆነን፡ . . . . . . . ትዝ አለኝ. . . . . . . . አብሮን የቆየውን ቅድመ አባታችን ቅድመ አያታችን፡ ሲሄድ ሸኝተነው ስትሄድ ሸኝተናት በእንባችን ተራጭተን፡ እኛም ተቀብለን አዲሱን ቤተሰብ በደንብ አቋቁመን፡ ደግሞ ደረሰና እኛም ተሸኝተን ቃል ኪዳኑን ይዘን መስቀሉን አጥልቀን፡ ኢየሩሳሌም ሆይ፡ ግቢ ጉባኤ ሆይ አልረሳሽም ብለን፡ ዘምረን ተጫውተን የልብ የልባችን፡ ምከረኝ ምከሪኝ ምን ላድርግ እንግዲህ እንዲያ ተባብለን፡ . . . . . . . ትዝ አለኝ. . . . . . . . . . ግቢውን አቋርጠን እስራኤልን መስለን፡ ከበሮ እየመታን ነጋሪት ጎስመን መለከቱን ነፍተን፡ ስንጓዝ በአንድ ላይ እግዚአብሔርን ይዘን ማደሪያውን ይዘን፡ ባህረ ጥምቀቱ እንዴት ይረሳኛል፡ ጉባኤው ዝማሬው ልቤን ይንጠኛል። . . . . . . . ትዝ አለኝ . . . . . . ብቻ ሁሉም ነገር እዛ የነበረው፡ ትዝ አለኝ በድንገት ልቤን በረበረው፡ እናቴ ግቢ ጉባኤ በዚሁ እንደምን ነሽ? ይችን ስዕለት ስሚኝ በለመደ ግብርሽ፡ ፍቅርሽ አነሳስቶ ያብረኝ ያክንፈኝ አንዴ ዳግም ልይሽ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን 🙏 በየዓመቱ መጨረሻዎች፥ ብዙዎች ከተለያየ ዩኒቨርስቲዎች መንፈሳዊ ሀብት ታካበቱበት፣ ዲቁናውንና መዝሙራቱን ከተማሩበት ናፋቂ የግቢ ጉባኤ ህይወታቸው የሚለያዩበት ጊዜ ነው፤ እና ለትዝታ ይሁንልን 🙏 ሰንበት ት/ቤታችን ፤ ግቢ ጉባኤያችን !! የኪነጥበብ ቤተሰብ ይሁኑ ! @sundayschoolstudents የሰንበት ት/ቤት ኪነጥበብ ክፍል !
እናት ፥ እናትነት 🤱🤰❤ ከስሞች ሁሉ ምርጥ ስም ከሰው ልጅ ከናፍራት ከወጡ ውብ ቃላት አንዱ “እናት” ነው። የጥሪዎች ሁሉ ምርጡ ጥሪም “እማ” የሚለው ቃል በፍቅርና ተስፍ የተሞላ ነው፤ እርሷም የምትጣፍጥ ቃል ከሰው ልጅ ጥልቅ ልብ የወጣች ናት። እናት ሁሉ ነገር ናት፤ በችግር ሰዓት አማካሪያችን ናት፣ በጭንቀት ሰአት ተስፍችን ናት፣ በድካማችን ሰዓት ጥንካሪያችን ናት፣ እሷ እኮ የፍቅር , የእዝነት፣ የርህራሄ፣ ምንጭ ናት። እናት እንደ መሬት ሁሉን ቻይ ናት። ብትረገጥ ታግሳ ለወግ ማረግ ታበቃለች። ብትነቀፍና ብትተችም ፈገግታዋ አይከስምም። የዘሩባትን መልካም አድርጋ እንደምታበቅል እርሻ ልበ ንፁሁ እንዲሁም መልካም ፍሬ እንደምታፈራ ዛፍ አብራኳ ለምለም የሆነ የውበት የምጨረሻዋ ምዕራፍና የመጨረሻዋ እውነተኛ ዓረፍተ ነገር ነች እናት። ልቧ ከፍቅር ድርና ማግ የተሸመነ ነውና ምን ቢያስቀይሟት የጥላቻ ጥርስ አትነክስም። ፊት ቢነሷት ፊት አትነሳም። እናት የፍጥረት ሁሉ የመጅመሪያ ምሳሌ ናት፣ ሙሉ የሆነ ውበት እና ፍቅር ተምሳሌት ናት። ከሁሉም በላይ እናት የሚተመንላት ዋጋ የላትም፡፡ ከዋጋ በላይ ናትና፣ ብዙ ድንቅ ፍጥረቶች አሉ ፣ ከነዚህ ሁሉ የምትበልጠው ግን እናት ነች! የተወደዳችሁ የኪነጥበብ ዘሰንበት ት/ቤት ቤተሰቦች እንኳን ለእናቶቻችን ቀን አደረሳችሁ አደረሰን 🙏 መልካም የእናቶች ቀን 🤰🤱 🙏❤ የኪነጥበብ ቤተሰብ ይሁኑ ! @sundayschoolstudents የሰንበት ት/ቤት ኪነጥበብ ክፍል !
በምሽቱም ቡናው እየተጠጣ ስለውሎአቸው፣ ስለአገርሰፈሩ፣ ስለነገአቸው፣ ስለልጆቻቸው ባጭሩ ስለህይወታቸው አንዱ ሌላውን እየመለሰ ሲጫወቱ ያመሻሉ። ከዛም ያቺ ብርቱ ሴት ምሽቱ እገፋ ሲሄድ ልጆጇን ታስተኛች በኋላ የውሎ ሁሉ ድካሟ ይመጣና በዠኔዲ አልያም በሳር ወይም በገለባ ፍራሽ እሱም ካለ ነው፤ የመኝታ እረፍት ይገላግላትና ጎኗን ታሳርፈዋለች። ጃል! ይቺ የኑሮ ምስቅልቅል የውጣ ውረድ ሕይወት ፊቷን ያገረጣት፣ ያከሳት፣ ያለዘባት፤ ጥላሸቱም፣ ሊጡም፣ አፈሩም በብጫቂ ቀሚሷ የወዛባት፤ የፊትዋ ፈገግታና ብርሃን ግን ከውስጧ ለእኛ የፈካላት ዘንካታዋ የገጠሯ ብርቱ ሴት የእኔ፣ የአንተ፣ የአንቺ እና የሁላችንም ኢትዮጵያውያን እናት ነች። እናት የሁሉ መሠረት ናት። በእውነት ለእናት እኮ ውለታዋ ተከፍሎ አያልቅም። እናቶቻችንን ፈጣሪ ይባርክልን፣ ሺህ ዓመታትን ያኑርልን አሜን 🤱🤰🙏 አወ፥ እናቴ ይህቺ ናት፤ ሁላችሁም እናታችሁን የምትወዱ እንኳን ለእናቶች/ለእናቶቻችን ቀን አደረሳችሁ አደረሰን🙏❤🤰🤱 የኪነጥበብ ቤተሰብ ይሁኑ ! @sundayschoolstudents የሰንበት ት/ቤት ኪነጥበብ ክፍል !
++ እናቴ ይህቺ ናት 🤰🤱 ! ፍቅር እንደ እንጀራ ተጎዝጉዞ በሚበላበት የገጠሩ አካባቢዎች ኢትዮጵያዊ ለዛና ወዟን ጠብቃ የበቀለችው እናቴ፤ በጠዋት ማልዳ ወፍ ተንጫጭቶ ሳያበቃ ከመኝታዋ ትነሳና ፊትዋን ተታጥባ ወደምድጃዋ ታመራለች፡፡ ብዙዎቹ እርሷን መሰል አርሶአደር ሴቶች የሚያጠቡት ልጅ አያጡም፡፡ እናም ልጅዋ አግቶ ያደረ ጡትዋን ፍለጋ እየተነጫነጨ፣ እንደማልቀስም እያደረገው ከምድጃው ሳለች የውጥር ይይዛታል፡፡ ማታ አዳፍና ያሳደረችውን እሳት ከማዳፈኛው አመድ ውስጥ ገላልጣ ካወጣች በሁዋላ ከምዳጃዋ ጠፍቶ ከማይጠፋው ኩበት ሰበር አድርጋ ከፍሙ ላይ ትፈረፍርበታለች፡፡ ከፍሙ ላይ ያረፈው ስብርባሪ ኩበት መጨስ ይጀምራል፡፡ ትንሽ ጭራሮ ቢጤ ሰባብራ በሚጨሰው ኩበት ላይ ታደርጋለች፡፡ በስብርባሪው ጭራሮ ላይ ጠና ጠና ያለ እንጨት፣ ከተገኘም ፍልጥ ብጤ ታኖርና እሳቱ ሲጫጫስ ድስትዋን ትጥዳለች፤ ያደረውን ወጥ አሙቃ ለባልዋና ለልጆችዋ ቁርስ ብጤ ለማቃመስ በማሰብ፡፡ ወጡ እስከሚሞቅ ድረስ ወደዛ የውጥር ይዞአት ጡት ካላመጣሽ ብሎ ወደሚያለቃቅሰው ልጅዋ ፊትዋን ታዞራለች፡፡ ጡት እያጠባች ባንድ እጇ ወጡ እንዳይጎረና ታማስላለች፡፡ ይህን ሁሉ እንዲህ ከውና ብድግ ስትል ያ ጊዜ አይሰጤ ጡት ያልጣለ ልጇ አብሮዋት ብድግ ይላል፡፡ ትታው ከሄደች ሊያለቅስ ነው፡፡ ስለዚህ ብድግ አድርጋ ከጎኗ ላይ ይዛው ወደ ጓዳዋ ትሄዳለች፡፡ ከሞሰብ ያለውን እንጀራ ከቤቷ ባላት ትሪም ይሁን ሌማት፣ እርቦም ይሁን ሳህን ላይ አኑራ ከሞቀው ዶኬ፣ እሱም ካለ ነው፣ አሊያም ከማሳ ተቀጥፎ በሰፊው ከተቀቀለው የጎመን ወጥ አውጥታ የባልዋን ከውጪ መመለስ ትጠብቃለች፡፡ ባለቤትዋም ልክ እሷ ከእንቅልፍዋ እንደተነሳች እሱም ተነስቶ ለከብቶቹ ገለባ ካለ በየ ግርግማቸው አድርጎና ከግርግሙ አጠገብ ካለ ችንካር አስሮአቸው ሲያበቃ ወደአረም ከመሄዱ በፊት አፉን ለማሟሸት ይመጣል፡፡ ለመስክ ስራ የደረሱ ልጆች ካሉዋቸው ከአባታቸው ጋር አፋቸውን ያሟሻሉ፡፡ በርግጥ አሁን አሁን ከበጋው የከብቶች ቀለብነት ተርፎ ለክረምት የሚበቃ ገለባ ያለው ገበሬ በጣት የሚቆጠር ነው፡፡ ይቺ ብርቱ እናትም ያንን ከስዋ የማለየውን ልጅዋን ወይ አዝላ አሊያም በጎንዋ ይዛ ለሌሎች ልጆችዋ፣ ከባለቤትዋ የተረፈ ካለ እሱን እንደሚሆን እንደሚሆን አድርጋ ለቁርስ ትሰጣቸዋለች፡፡ ያ ከሌለ ደግሞ ምናልባት ከማታ ተርፎ ያደረ ንፍሮ ካለ እሱን ብረት ምጣድ ጥዳ ታሞቅና፣ ትንሽ ጨው በላዩ ነስነስ አድርጋ በእጅ በእጃቸው ትሰጥና ከብቶች በጎችና ፍየሎች ካሉዋቸው እነሱን እንዲጠብቁ ታሰማራቸዋለች፡፡ በመቀጠል ቤት ትጠርጋለች፣ ደጁንም ታጸዳለች፡፡ የደጁ ጽዳት የከብቶቹን እበት ማንሳት፣ የበጎቹንና የፍየሎቹን ጉረኖ መጥረግን ያካትታል፡፡ ይህ እንግዲህ ከብቶች ካሉዋቸው ማለት ነው፡፡ ዛሬ ዛሬ ከስንት አርሶአደር ቤት አንድ ወይ ሁለቱ አንድና ከአንድ በሬ በላይ ቢኖራቸው ነው፡፡ ገበሬ ሆነህ አንድ በሬ እንኩዋን ስታጣ ምን ማለት እንደሁ ይታይህ፡፡ መራር ሀቅ ነው፡፡ ገበሬው በየእለቱ የሚጋተረው እንቆቆ ተግዳሮት ነው፡፡ አንድ በሬ ካላቸው በእኚ እያጣመዱ፣ ምንም በሬ ከሌላቸው በሮች ላሉዋቸው ሰዎች አንድ ቀን ለነሱ አንድ ቀን ለራሳቸው በማረስ ነው ይቺን በክረምት ወራት የሚያርሙዋትን ሰብል ማብቀል የሚችሉት፡፡ ወደ መንታላዋ እናት ስመለስ፤ ማለዳ ተነስታ ያ ልጅዋም ሳይለያት እንዲሁ ጎንበስ ቀና እንዳለች ይረፋፍዳል፡፡ ውሃ ካለበት በዛ መከረኛ ቢጫ ጄሪካን ቀድታ ባንድ እጅዋ እሱን በሌላኛው እጅዋ ልጅዋን ከጎንዋ ይዛ ትመለሳለች፡፡ ጤዛ ሳይረግፍ አረም ማልደው ለሄዱት ቤተሰቦችዋ ከመስክ የሚጠበቅ በግ፣ ፍየልና ከብት ካለ እረኝነት ለሄዱትም ሆነ፣ የሚጠበቅ ምንም ነገር ከሌላት ደግሞ ከቤት ሆነው አይን አይንዋን የተራቡ አይኖቻቸውን እያንከራተቱ ለሚጠብቁዋት ልጆችዋ ምሳ ለማዘጋጀት ደፋ ቀና ማለትን ትያያዘዋለች። እኩልቀን ላይ ከቤት ላሉም ሆነ ወይም በእረኝነት ለዋሉት ልጆችዋ ምሳ ሰጥታ ስታበቃ እያረሙ ላሉት ቤተሰቦቸዋ ምሳ ባገልግል ወይም በሌማት አድርጋ፣ ያንን ልጅዋን ወይ ከጀርባዋ አሊያም ከጎንዋ ይዛ ወደማሳ ትሄዳለች፡፡ ምሳውን ከሰጠች በሁዋላ ቁጭ አትልም፣ ወይም አብራ አትበላም፡፡ የሁሉም ግምት እቤት ሳለች በልታ ነው የመጣችው የሚል ነው፡፡ እስካሁን እህል ባፍዋ ይዙር አይዙር እስዋና አንድ እግዚአብሄር ብቻ ናቸው የሚያውቁት፡፡ አለመብላትዋን በሆነ አጋጣሚ ያወቀ ሌላ ሰው ቢኖር እንኩዋን እህሉ በጅዋ ማን አትብዪ አላት? የሚልን አኞ አኞ ያለ፣ ካስፓልት የደደረ፣ ከጎማ የገነተረ አስተያያየት አይሉት ጥያቄን ማትረፍ ብቻ ነው ትርፏ፡፡ አረም የዋሉት ቤተሰቦችዋ ምሳቸውን ሲበሉም ሆነ በልተው ካበቁ በሁዋላ እስዋ ቁጢጥ ብላ ታርማለች፡፡ አረም ሲታረም ዝርፍጥ ተብሎ ተቀምጦ አይደለም፡፡ አንድም በሁለት እግር ቆሞና ከወገብ አጎንብሶ፣ አንድም ቁጢጥ ተብሎ ነው አረም የሚታረመው፡፡ አለበለዚያ በውልድ ወይም በአንጉዋ ደረጃ ያለው ቡቃያ ድምጥማጡ ይጠፋል፡፡ ስለዚህ ነው እግር የሚያርፍበት ክፍት ቦታ በጥንቃቄ እየተፈለገ በቁጢጥታ ወይም ወገብን አጉብጦ የሚታረመው፡፡ ያቺ ቀጭን እናት ልጅዋ ጡት እያለ በየመሃሉ ሲያስቸግራት ለሱ ጡትዋን በምታጎርስበት ጊዜ ከምትኖራት ፋታ በተቀር ለተጨማሪ ሁለትና ሶስት ሰአት ቁጢጥ ብላ ወይም አጎንብሳ ታርማለች፡፡ ያቺ ጠልጣላ አርሶአደር እናት ችግርዋን ሊረዳላት በማይችልበት እድሜ ላይ ያለ ልጅዋ የማያቁዋርጥ ጥያቄና መነጫነጭ ሳትበሳጭ ለሰአታት ምናልባትም በባዶ አፍዋ ቁጢጥ ብላ ስታርም ትውላለች፡፡ ይቺ እናት ወይም እህት ከማሳ ያሉትን ቤተሰቦችዋን ምሳ አብላታ ለሰአታት አብራ ስታርም ከዋለች በኋላ፤ ጀንበር ዘቅዘቅ ስትል በሉ እንግዲህ እራት ላዘገጃጅ ብላ ቤተሰቦችዋን ከማሳው ትታ ያንን ህልውናዊ ኮኤፊሸንቷን በጎንዋ ይዛ ወደቤት ትመለሳለች፡፡ እግረመንገድዋንም አታርፍም፡፡ ለእራት ማዘገጃጃ ጭራሮ ብጤ እየለቃቀመች ነው የምትሄደው፡፡ እራት አዘገጃጅታ ስታበቃ ከአረም ማሳ ያሉት፣ ጠዋት ጤዛ ሳይረግፍ የጀመሩትን አረም ማታ ጤዛ ሲጥል ያቆሙና ወደቤት ይመለሳሉ፡፡ በምሳ ሰአት እህል አፋቸው ሲያደርጉ ከሚያገኙዋት ፋታ በስተቀር፣ ቀን ሙሉ በቁጢጥታ ወይም በጉንባሶ ከአረም ዘር ጋር ሲታገሉ ውለው ነው ወደቤት የሚመለሱት፡፡ ጀንበር ስትወጣ ጀምረው ጀምበር ስትገባ ነው ከአረም የሚገላገሉት፡፡ ዘንካታዋ እናት ደግሞ ከማሳ ለዋሉት እግር መታጠቢያ ውሃ አሙቃ ከበር ነው የምትቀበላቸው፡፡ ሁለትም ትሁን ሶስት ፍሬ ቡና በሁለትና ሶስት እፍኝ ቅሽር ታጅባ የተፈላው ቡና በንፍሮ ወይ በቆሎ ቡና-ቁርስነት ይጠጣል፡፡ ድሮ ድሮ ቡና ቢያንስ በቀን ሁለቴ ይፈላል፡፡ አሁን አሁን እጅ እያጠራቸው በርካታ የአርሶአደር ቤተሰቦች ወይ ጠዋት አሊያም ማታ ብቻ ቡና ያፈላሉ፡፡ እሱም ሲዳላ ነው፡፡ በሶስትና አራት ቀን አንዴ የሚያፈሉም አሉ፡፡ ድህነት ምን የማይሰራን ስራና ያልዋለብን ግፍ አለ፣ ምን ያልነጠቀን የህይወት ገጽ አለ። ድሮ ድሮ ግን ኮልኮሌ ምሁራን፣ የኢትዮጵያ ሰው ቡና ላይ ተጎልቶ ወሬውን ሲቀድ ነው ወደ ኋላ የቀረው፣ እያሉ አለሳሙና ራሳቸውን ሲያጥቡብን ነበር፡፡ ዛሬ ሰለጠንኩ የሚለው ዓለም ወጣቶች ሆኑ ህጻናት፣ አዛውንቱም ሳይቀሩ ፌስቡክ ላይ ተጥደው አይደለም እንዴ የሚውሉትና የሚያድሩት?!
++ ዕድሜ መስታወት ነው ብዙ ያስተምራል !! አንዲት ቆንጆ ናት 18 ዓመቷ ነው። ጎረምሶች ሲያይዋት ዓይናቸው ይመኛታል። ሴቶች በቅናት እንደ ሽንኩርት ይልጧታል። አንድ ቀን እንዲህ ስል ጠየቅኳት። "ማግባት የምትፈልጊው ባል ምን መስፈርት እንዲያሟላ ትፈልጊያለሽ?" በፍጥነት መለሰችልኝ የተማረ መሆን አለበት፤ ማስተርስ ያለው ይመረጣል። ከተቻለ የግል ቢዝነስ የሚሠራ፤ ኢንቨስተር ቢሆን አሪፍ ነው። ካልሆነ ግን አሪፍ ደሞዝ ሊኖረው ግድ ነው። መኖሪያ ቤቱ G+2 ቢሆን ደስ ይለኛል፤ ከG+1 በታች ግን አልፈልግም። መኪና በጣም ነው የምወደው። አሪፍ መኪኖች ቢኖሩት ደስ ይላል፥ ካልሆነም ከተጋባን በኋላ እኔ እንዲገዛ አደርገዋለሁ። ሙድ የገባውና ጨዋታ የሚያውቅ ሁሌ የሚያስቀኝ፣ ቁመቱ በጣም እንዲረዝም አልፈልግም። እኔ አጠር ስለምል በጣም እንዳይበልጠኝ። ቦርጭ የሚባል ደግሞ እንዲኖረው አልፈልግም። ፀጉሩ ፍሪዝ ቢሆን ደስ ይለኛል፤ ድሬድ ቢሆን ደግሞ ነፍስ ነው። ዐይኑ የሚያምር፤ መልኩ ጠይም መሆን አለበት በጣም ቀይ ወንድ አልወድም። አለባበሱ ዘናጭ መሆን አለበት። የሚወደኝ፤ የሚንከባከበኝ፤ በሳምንት ቢያንስ ሁለቴ የሻማ እራት ያለበት ሆቴል የሚጋብዘኝ፤ ቢያንስ በወር ሁለቴ ጭፈራ ቤት የሚወስደኝ፤ ከበዓላት እና ከልደቴ ቀን በተጨማሪ ስጦታ እያመጣ ሰርፕራይዝ የሚያደርገኝ፤ ፍቅር የሚያውቅ፤ በተለያየ ቁልምጫ ስም የሚጠራኝ እና ታማኝ ከእኔ ውጪ አንዲት ሴት የማያይ ..." ብላ ልትቀጥል ስትል እየገረመኝ "ይበቃል" አልኳት እንደማታቆም ስለገባኝ። እንዲህ ዓይነት ወንድ ኢትዮጵያ ውስጥ ቀርቶ ዘፋኞቹ ዐይኑ፣ ቁመቱ፣ ወንዳወንድነቱ እያሉ የጣኦት አምልኮ እስከሚሆን ድረስ በሚዘፍኑት ዘፈን ውስጥ እንኳን አይገኝም አልኩ በውስጤ። ለሷ ግን አልነገርኳትም። መቼም ታውቃላችሁ ጊዜው ይበራል! አቤት ፍጥነቱ። ከአራት ዓመት በኋላ ሳገኛት 22 ዓመቷ ነበር። አላገባችም። ትምህርት ጨርሳለች ሥራም ይዛለች። ጥቂት ቦይ ፍሬንዶች ይዛ ለቃለች። ያው ናት! አሁንም ታምራለች። እንደ ድሮው ግን የሰው ሁሉ ዐይን ማረፊያ አይደለችም። መልሼ ያንኑ ጥያቄ ጠየቅኳት። "ማግባት የምትፈልጊው ባል ምን ዓይነት ነገሮች ማሟላት አለበት?" የማፈቅረው ሰው መሆን አለበት፤ ፍቅር ከሌለ ላገባው አልችልም። ከማልወደው ሰው ጋር አንድ ቀን ላድር አልችልም። ታማኝ እንዲሆን እፈልጋለሁ። እንዲያከብረኝ እፈልጋለሁ። ጥሩ ሥራ ቢኖረው፤ ማንበብ የሚወድና በሐሳብ የምንግባባ ቢሆን ደስ ይለኛል። ቆንጆና ሃብታም ከሆነ ጥሩ ነው፤ ካልሆነም ግን አብረን ሠርተን መለወጥ እንችላለን። ዋናው መግባባት ነው። በተረፈ ቤተሰቡን የሚወድ እና የማይዋሽ መሆን አለበት። ወንዱ ሁሉ የማይታመን ሆነብን እኮ። ዋናው የሚታመን ከሆነ ሌላው ችግር የለውም።" አለችን። አቤት..! ጊዜው ሲሮጥ! ደግሞ በተመሳሳይ ጊዜ ከአምስት ዓመት በኋላ ስንገናኝ አላገባችም። 27 ዓመት እያለፋት ነበር። ደግሜ ያንኑ ጥያቄ ጠይቅኳት። "ማግባት የምትፈልጊው ባል ምን ዓይነት ነገሮች ማሟላት አለበት?" ትንሽ አሰብ አደረገችና "የምግባባው ሰው ከሆነ ሌላው ችግር የለውም" አለችኝ። "መልኩ፤ ፀጉሩ፤ ሃብቱ፤ እውቀቱስ" አልኳት። "ወንድ ልጅ ደግሞ መልክ ምን ያደርግለታል? ጠባዩ ብቻ አስቀያሚ እንዳይሆን እንጂ ሌላው ችግር የለውም" አለች እየሳቀች። ከሦስት ዓመት በኋላ ሳገኛት አግብታ ልጅ ወልዳ ነበር። ባሏ አጭር፣ ጥቁር፣ መላጣ፣ የከባዳ መኪና ሾፌር ዓይነት ቦርጭ ያለው፣ ሱሪውን ቦርጩ መሃከል ላይ የሚታጠቅ፣ በቀላሉ የሚነጋገርና የሚግባባ የማይመስል ነገር ነው። "እንዴት ነው ትወጂዋለሽ?" አልኳት፤ "ምን ማለትህ ነው ትዳር አይደል?" አለችኝ። "እሱማ ልክ ነሽ፥ ማለቴ ድሮ የነገርሽኝ ዓይነት ሰው አይደለም ብዬ ነው?" አልኳት እየገረመኝ። "ያኔማ አየር ላይ ነበርኩ፤ ዕድሜ መስታወት ነው፤ ብዙ ያስተምራል፤ አሁን ተምረን ልብ ገዝተን ነው።" አለች ተከዝ ብላ። "ሁሌ የማይቀያየር አንድ መስፈርት ነበረሽ፤ ታማኝ መሆን አለበት ትይኝ ነበር። ባልሽ ታማኝ ነው?" አልካት እያመነታሁ፤ "ታማኝ እግዜር ብቻ ነው፤ በቃ ግን ትዳር ስለሆነ ከማይታመን ሰው ጋር መኖር ትለምዳለህ፤ አየህ አሁን የገባኝ ነገር ትዳር ማለት እንደ ፖለቲካ ነው። ፖለቲከኞች ውሸት እየነገሩን አብረን እንደምንኖር ትዳር ውስጥም ይሄ ያጋጥማል።" አለችኝ። በውስጤ "ትዳር እንደ ፖለቲካ ነው እንዴ? ስለዚህ እኔና ትዳር ሆድና ጀርባ እንሆናለና! እኔም አልፈልገው እሱም አይቅረበኝ፤" አልኩኝ በውስጤ የተዘበራረቀ ስሜት እየተሰማኝ። "በትዳርሽ ደስተኛ ነሽ?" አልኳት እያዘንኩ። "አይ አንተ ደስታ አንጻራዊ ነው፤ በልጆቼ ደስ ይለኛል፤ ትዳሬን አከብራለሁ። በተረፈ ግን እየኖርኩ ነው" አለች ፈገግ ብላ። በዛች ቅጽበታዊ ፈገግታ ውስጥ የጊዜን ኃይለኝነት አየሁ። አይ ጊዜ ኃያል! ምን ታሳየኝ ይሆን? ምንስ ታሰማኝ ይሆን? መቼም ሁሉም አንተጋር ነው ያለው፤ አልኩ በውስጤ እያሰላሰልኩ። ለካ "ጊዜ ነው እንጂ ቁምነገራም ባላባትነት አያኮራም" የተባለው ለእንደዚህ ዓይነት ነው አልኩ። ለማንኛውም በዚህ ታሪክ ውስጥ ለማስተላለፍ የፈለግነው መልእክት "ዕድሜ መምህር ነውና ከቻልን ከዕድሜያችን አለፍ ብለን በብልህነት እናስብ። ካልቻልን በዕድሜያችን በማስተዋል መንገድ እንጓዝ ለማለት ያህል ነው። የኪነጥበብ ቤተሰብ ይሁኑ ! @sundayschoolstudents የሰንበት ት/ቤት ኪነጥበብ ክፍል !
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ ! ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ዓልፋና ኦሜጋ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ሊይዘው አልቻለምና የተገነዘበትን ልብስ ትቶ ልብሰ መንግስቱን ለብሶ ተነሳ፤ በተወለደ ጊዜ የእናቱን መኃተመ-ድንግልና እንዳልለወጠ ሁሉ፥ በትንሳኤውም መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በብርሃን መላእክት ታጅቦ እነሆ በክብር ተነሳ። ዛሬም እግዚአብሔርን የሚያምንና የሚወድ ቢኖር እርሱ በዚህ አንፀባራቂና የደስታ በዓል ደስ ይበለው፡፡ እኛ ህዝበ ክርስቲያኖችም “ትንሳኤከ ለእለ አመነ ብርሃነ ከፈኑ ዲቤነ” (ትንሳኤህን ለምናምንህ ለእኛ ብርሃንን ላክልን ወደ እኛ) እያልን ስለተገለጸልን ምስጢረ ትንሳኤ እንዘምር። በመኾኑም የጌታ ትንሣኤ ለእኛ ለክርስቲያኖች የድል፣ የሰላም፣ የደስታ፣ የሕይወት፣ የማሸነፍ በዓል ነውና ይኽ ሰላምታ ይድረሳችሁ ፤ ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን አሠሮ ለሰይጣን አግዓዞ ለአዳም ሰላም እምይዕዜሰ ኮነ ፍሥሐ ወሰላም ! ! የተወደዳችሁ የኪነጥበብ ቤተሰቦች ፥ እንኳን ለ2018 የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዐለ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን !! መልካም የትንሳኤ በዓል ይሁንልን ! ! ! ትንሳኤ በዓል 2018 ዓ.ም 💚💛❤️ የኪነጥበብ ቤተሰብ ይሁኑ ! @sundayschoolstudents የሰንበት ት/ቤት ኪነጥበብ ክፍል !
የሰሙነ ሕማማት ትረካ ርዕስ - ሕማማተ መስቀል ይኽ የጌታችን ሕማማት ከወንጌል አንጻር የተተረከ ትረካ ነው ። እህታችን ቃለሕይወት ያሰማልን፣ ጸጋውን ያብዛልሽ ። የኪነጥበብ ቤተሰብ ይሁኑ ! @sundayschoolstudents የሰንበት ት/ቤት ኪነጥበብ ክፍል !
++ ሥነጽሑፍ - የዐብይ ጾም ግጥሞች ! ( ርዕስ - ሆሳዕና/ ስምንተኛ ሳምንት ) ሆሳዕና በአርያም - ሆሳዕና በአርያም - - - ሆሳዕና በአርያም - - - ሆሳዕና በአርያም የዳዊት ልጅ መድኃኔዓለም፤ በኪሩቤል ግርማ የሚቀመጥ አልፋና ዖሜጋ በቀስተ ደመና ላይ ዙፋኑን የዘረጋ፤ በእሳት መድረክ ላይ የሚመላለስ በሱራፌል የሚቀደስ - - - የሚወደስ፤ ሰባት መቅረዝ በፊቱ የሚያበራ መንጦላይትህ ብርሃን ማደሪያህ የሚያስፈራ፤ በልዩ ልዩ ቅኔ በመለከተ ድምጽ በመብረቅና ነጎድጓድ የምትገስጽ፤ ዓይኖችህ እንደ እሳት የሚያበሩ እግሮችህ ንጥረ ነሀስ የመሰሉ፤ የልብስህ ዘርፍ ቤተ-መቅደሱን የሞላ የኃያላን ኃያል ባለብዙ ሺህ ሠረገላ፤ በማደሪያህ በጸባኦት ባይቻለን አንተን ማየት ልትባርከን በበረከት ልትፈውሰን በምህረት፤ የአዳም ልጅ - - - የእግዚአብሔር ልጅ - - - ልትጨበጥ - - - ልትዳሰስ በአህያ ላይ ተቀምጠህ አገኘንህ ቤተ-መቅደስ፡፡ ሆሰዕና በአርያም - - - በጌታ ስም የሚመጣ ከምርኮ አገር ከባርነት የሚያወጣ፤ ብሩክ - ቅዱስ የአበው ተስፋ የመርገም ጨርቅ ባንተ ጠፋ፤ የነቢያት ትንቢት የጽድቃቸው ዜና የህይወት እንጀራ የእስራኤል መና፤ ቃል ከሥጋ ጋራ በተዋህዶ ጸና በሰማያት የተከለልክ የተጋረድክ በደመና በምድር ላይ ተመላለስክ ታየህልን በጎዳና፤ አላዋቂ - በማስተዋሉ ተደገፈ - በጥበቡ አመነ የዚህ ዓለም እውቀት ግን ፍጹም ከንቱ ሆነ፤ በማኅበር በጉባኤ መካከል ላይ ተገለጠ የዋህ ሆኖ የጽዮን ልጅ በአህያ ላይ ተቀመጠ፤ ከሚጠቡ ህፃናት አፍ ምስጋናህን አዘጋጀህ አንደበትን ለምስጋና - ለዝማሬ አንተ ከፈትክ፤ እኛም ልጆችህ ይዘን ዝንጣፊ ዘንባባ በሀሴት ተመልተን አሸብርቀን በአበባ፤ የሠላም ንጉሥ መድኃኔዓለም ስለስምህ ተቀኝተናል - - - ሆሳዕና በአርያም፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን !!! ( የዐብይ ጾም ሳምንታት ግጥሞች ) +++ ተፈጸመ ++++ የኪነጥበብ ቤተሰብ ይሁኑ ! @sundayschoolstudents የሰንበት ት/ቤት ኪነጥበብ ክፍል !
💐 *አብርሃም*🧔🏽እትዬ አለሜ ይቅር በይኝ ሳላዉቅ በስህተት እያወኩ በድፍረት የበደልኩሽን ሁሉ ይቅር ካላልሽኝ ከእግርሽ አልነሳም 💐 *እናት አለሜ*👳🏼♀እረ ጉድ አቶ አብርሃም የይቅር ለእግዚአብሔር ተነስ እንዴ እረ እንደዚህም አያስፈልግም እቤት ድአስ መምጣትህ ራሱ ትልቅ ይቅርታ ነው 💐 *አብርሃም*🧔🏽እግዚአብሔር ያክብርልኝ ሁላችሁም እወዳችኋለሁ ለፍቅራችን መግለጫ አብረን ምሳ እንብላ ቢላሆ ስጡኝ 💐 *ትግስት*👧🏽 አቶ አብርሃም በእዉነት እግዚአብሔር ያክብርልን እናመሰግናለን ወገኖቼ ምሳ እስኪደስ ድረስ ትንሳኤ ምን እንደሆነ እንወያይ 💐 *ሐረግ*👩🏽🦱 ትጂዬ እኔ 🤚🏽🤚🏽 ምንም ነገር አላዉቅም 💐 *ቅድስት*👩🏽 እኔም አላዉቅም ፀጋዉ የበዛላችሁ አሳዉቁን ከምታዉቁት 💐 *ፍሪ*👩🏽🦳 መልካም እህቶቼ ትንሳኤ ማለት ተንሰአ ካለዉ የግዕዝ ግስ የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙ መነሳት አነሳስ ማለት ነው እስራኤል ዘስጋ ያከበሩት የነበረው በዐል ፋሲካ ከባርነት ቀንበር ወደ ነፃነት የተላለፉበት ከሃዘን ወደ ደስታ የተሸጋገሩበት በአል ነው 💐 *ትግስት*👧🏽የክርስቶስ ትንሳኤ እግዚአብሔር እኛን ምን ያህል እንደወደደን የምናስተዉልበት የፍቅሩ ጥልቀት የቸርነቱ ስፋት የምናደንቅበት የነፍሳችን የዕረፍት ቀን ነው 💐 *እናት እቴቱ*👵🏽የክርስቶስ ትንሳኤ ላመኑ ክርስቲያኖች ሁሉ ትንሳኤ ነው ክርስቶስ ለሙታን ሁሉ በኩር ሆኖ ተነስቷል የሙታን ሁሉ መነሳት የሚያረጋግጥልን ትንሳኤ ነው የክርስቶስም ትንሳኤ መርገመ ስጋ መርገመ ነፍ ሞተ ስጋ ሞተ ነፍስ የተሻረበት ርደተ ገሃነም ጠፍቶ በአዳም የተፈረደዉ ፍርድ ሁሉ ተደምስሶ ፍፁም ነፃነት የማይለወጥ ደስታ የተገኘበት ስለሆነ ፋሲጋ ይባላል 💐 *ፍሪ*👩🏽🦳የሐዲስ ኪዳን በአል ትንሳኤ ግን እስራኤል ዘነፍስ ወደ ከኃጢአት ፅድቅ የተመለሰበት ከሐሳር ወደ ክብር ከአሮጌው ወደ አዲስ ህይወት የተሸጋገርንበት መንፈሳዊ የነጻነት በአል ነው 💐 *ሐረግ*👩🏽🦱 ለሁላችሁም ቃለ ህይወት ያሰማልን ፀጋዉን ያብዛላችሁ 💐 *ቅድስት*👩🏽 ለሁላችሁም ቃለ ህይወት ያሰማልን እህቶቼ ግን ለምን ዳግም ትንሳኤ ተባለ⁉️ 💐 *ትግስት*👧🏽 ጥሩ ጥያቄ ነው ዳግም ትንሳኤ የተባለበት ምክንያት በአከባበር በስርዓት የመጀመሪያዉን ትንሳኤ ስለሚባል ነው የትንሳኤዉ ለት የሚባለው ቃል እግዚአብሔር ሳይለወጥ በሙሉ በዚህ ቀን ይደገማል ከዚህም የተለየ ሁለት መጠሪያ ስያሜ ስሞች አሉት እነዚህም *ፈፀምነ አግአተ ግብር* ይባላሉ 💐 *እናት እቴቱ*👵🏽ፈፀምነ የተባለበት የሰሞነ ትንሳኤ በአል አክብረን ፈፀምን ማለት ሲሆን አግብአተ ግብር የተባለው ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባ ወአቡየ ግብር ዘወሀብከኒ ፈጸምኩ እኔ ልሰራዉ የሰጠኸኝን ስራ ፈጽሜ በምድር ላይ አከበርኩህ ያለው ከቅዳሴ በኃላ ሊቃዉንት በዚህ ቀን የሚዘምሩት ነው 💐 *እናት አለሜ*👳🏼♀በሉ ግቡ ከቤት በረክ በረክ በሉ ምሳ ደርሷል ኑ እንብላ እሰይ እንዲህ አሰባስበን ምን ይሳነዋል እግዚአብሔር 💐 *አብርሃም*🧔🏽በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን አምላካችን ሆይ ከፊለፊታችን ያቀረበዉን ማዕድ ባርክልን ቀድስልን እኛ የበላነዉን የጠጣነዉን ምግብ መጠጥ ለተራቡት ወገኖቻችን አድልልን አሜን በሉ ብሉ 💐 *ሐረግ*👩🏽🦱እረ ደስ ስትሉ ስንል አብረን እንኑር ለእነ ቅድስቴም አባዬ አባታቸው ይሆናል እዉነት ደስ አይላችሁም 💐 *ቅድስት*👩🏽ዉድ እህታችን ስለ መልካም አስተሳሰብሽ ሁሉ እናመሰግናለን ከእናንተ ይቅር ለእግዚአብሔር ተባባልን ማለት ቤተሰብ ሆንን ማለት ነው 💐 *አብርሃም*🧔🏽ተመስገን እግዚአብሔር ሆይ ይቺን ያበላኸን ያጠጣኸን አምላክ ተመስገን እግዚአብሔር ይስጥልን እትዬ አለሜ እድሜ ና ጤና አብዝቶ ይስጥልን እንዳከርሽን ድንግል ከእነ ልጇ ታክብርሽ *አቡነ ዘበሰማያት* 💐 *ተፈፀመ ወስብሐት ለእግዚአብሔር*🕯️ *አዘጋጅ አጸደ ማርያም* ለብርሃነ ትንሳኤው በሠላም ያድርሰን !!! የኪነጥበብ ቤተሰብ ይሁኑ ! @sundayschoolstudents የሰንበት ት/ቤት ኪነጥበብ ክፍል !
++ ኪነጥበብ - መንፈሳዊ የትንሳኤ ጭዉዉት ! ( ርዕስ - ሃብታም እና ደሃ ) 💐 *እናት አለሜ*👳🏼♀ ስብሐት ለአብ ስብሃት ለወልድ ስብሃት ለመንፈስ ቅዱስ እሰይ አምላኬ ምን ይሳንሃል ለአንተ የአብይ ፆምን በሰላም በፍቅር አሳልፈህ ለብርሃነ ትንሳኤ ያደረስከን እንዉ በትንሳኤዉም በፆም ከበደሉ ከተበዳደሉም ይቅር ለእግዚአብሔር ተባባሉ ይላል እግዚአብሔር አይ የእኔ ጉድ እንደዉ ከጎረቤቶቼ ጋር ሳልስማማ አሁን እሔዳለሁ ምንም ይበሉኝ ልጆች ተኝተዋል እንዴ ቅድስቴ ቅድስት 💐 *ትግስት*👧🏽እማዬ ሰላም አደርሽ እንዴ ቅድስቴ እስካሁን አልተነሳችም እንዴ እኔ እኮ የሌሊት ኪዳን ጨርሼ መጣዉ 💐 *እናት አለሜ*👳🏼♀እሰይ የእኔ ልጅ ጎብዘሻል እኔም አስቤ ነው አልተሳካልንም ከዚህ ወኜ ፀሎቴን አድርሻለሁ 💐 *ቅድስት*👩🏽ማነው የሚጣራው አያስተኙ ትናትና ምሽት ነበረብኝ ለትንሳኤ በተን ብዬ ከጓደኞቼ ጋር አቤት እማ 💐 *እናት አለሜ*👳🏼♀በይ ቅድስቴ ቶሎ በይና ፊትሽን ታጠቢ ልብስሽን ቀይሪና ፆም ፍቱ ትንሽ እንቁላል ሰርቻለሁ 💐 *ቅድስት*👩🏽እረ እማ ሁለት ወር ሁሉ ፆሜ ፆሜ በእንቁላል ልፈታ ነው እንዴ እማ ሼም ነገር የለም 💐 *ትግስት*👧🏽ቅድስቴ ረጋ በይ ቤት ያፈራውን ነው የምንቀምሰዉ እማዬ እኮ ብቻዋን ነች አታዛዝንሽም ደግሞ እኮ ስጋ በላን አልበላን ምንም የምናመጣው ለዉጥ የለም 💐 *ቅድስት*👩🏽እረ ትጂዬ አካበድሽ እና አመት በአመት ልደጋግም ነው እስኪ ጎረቤታችን እይ እንዴ አንዴ በሬዉ፥በጉን፥ፍየሉን ዶሮዉን የምግብ አቢታይቴን ከፈቱት እኮ በሽታ 💐 *እናት አለሜ*👳🏼♀የእኔ ልጅ ድሃ እንደቤቱ እንጂ እንደ ጎረቤቱ አያድርም አይዉልም ቤት ያፈራውን ቅመሱ አይ አምላኬ ምን በደልኩህ አመት በአመት ጭቅጭቅ 💐 *ትግስት*👧🏽እማ አምላክን አታማሪዉ ፈጣሪ ይመስገን ምን አጣን ይበቃል እሔ እኛ የምንበላው ለጥጋብ ነው እንዴ የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ምግብ ና መጠጥ ነው ተመስገን አምላኬ ለዚህ ያበቃኸኝ 💐 *ቅድስት*👩🏽አንቺ ልጅ ማካበድ ትወጃለሽ መሰለኝ 💐 *ትግስት*👧🏽እነሆ ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው የሆድም ፍሬ የእርሱ ዋጋ ነው አለ ልበ አምላክ መዝሙረ ዳዊት በመዝሙር 127፥3 አንቢ መፃህፍት ቅመም ልጨምርልሽ በሆድ ሳልሰራህ አዉቄሃለሁ ከማህፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ ለአህዛብም ነብይ አድርጌሃለሁ ትንቢቸ ኤርሚያስ 1፥5 💐 *ቅድስት*👩🏽 በቃሽ ቲቸር ትግስት በሉ ልተኛ ኦፍፍፍፍፍፍ 💐 *አባት አብርሃም*🧔🏽እሰይ እሰይ ልጆቼ ብሉሉኝ ጠጡልኝ ምን ይቅረብ ቢራ ቁርጥ ጥብስ ንገሩኝ 💐 *ሐረግ*👩🏽🦱 አባዬ ሁሉም ፉል ነው ደስ የሚልል የትንሳኤ ቀን ነው ፍሪ ምነው አኮረፍሽ 💐 *ፍሪ*👩🏽🦳 ምን ደስታ አለ ቆይ ግን እዚህ ቤት ብርሃነ ትንሳኤ በአል የምናሳልፈው በስጋና በመጠጥ ነው እንዴ እስቲ ለጎረቤቶቻችን እናስብ ምንም የላቸውም እግዚአብሔር ባርኮ ከሰጣቸው በስተቀር ታዉቃላችሁ አታዉቁምእንጂ እግዚአብሔር ካለህ ለሌለው አካፍል ይላል ስለዚህ እኛ በልተን እንብርታችን ከሚገለበጥ ለወገኖቻችን እናቅምሳቸዉ 💐 *አብርሃም*🧔🏽ምን አልሽ እኔ ለፍቺ የምሰራ ለጎረቤት ነው እንዴ ለእናንተ ብዬ ነው እነሱም መስራት ይችላሉ ለመለወጥ 💐 *እናት እቴቱ*👵🏽ምን ሆናችሁ ነው ፊታችዉ አመድ ለበሰ እንደዉ 💐 *ፍሪ*👩🏽🦳እማ ካለንላይ ለሌላቸው ብናካፍል ለተቸገረ ብንሰጥ ምን ይጎድልብናል በፀጋ ላይ ፀጋ በረከት እናገኛለን እንጂ 💐 *እናት እቴቱ*👵🏽ልክ ብለሻል የእኔ ልጅ እኔ ኮ ከሁሉም እያደራረኩ ይዘን እንድንሔድ አስቤ ነበር 💐 *አብርሃም*🧔🏽ለማነዉ የምታደራርጊዉ ለወይዘሮ አለሜ ነው አይሆንም ከእርሷ ጋር ብዙ በቀል አለኝ ገና 💐 *እናት እቴቱ*👵🏽በቀልከእኛ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ነው ደግሞም አንተ ነህ አባታቸውን በቅናት የገደልክባቸዉ እነሱ ግን ሁሉም ትተዉን ጎረቤት አድርገዉናል ለምን አተዉ እንደው ወይ ዘንድሮ ምን ጉድ ነው እደዉ 💐 *ፍሪ*👩🏽🦳 አባዬ የጨካኞች ቁጣ እስትንፋስ ቅጥርን እንደሚመታ ዐዉሎ ነፋስ በሆነ ጊዜ ለድሃው መጠጊያ ለችግረኛው በጭንቁ ጊዜ መጠጊያ ከዉሽፍር መሸሸጊያ ከሙቀት ጥላ ሆነሃል ይላል በትንቢተ ኢሳያስ ምዕ 25፥4 ስለዚህ አባ ሁሉንም መተዉ አለብህ 💐 *እናት እቴቱ*👵🏽ምን እሔ ብቻ በኦሪት ዘሌዋውያን ምዕ 19፥18 አትበቀልም በህዝብም ልጆች ቂምአትያዝ ነገር ግን ባልንጀራህን እንደራስህ ዉደድ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ይላል ተመለከት አብርሃም በቀል ከአንድ ፈጣሪ የመጣል ይቺቀን ደግሞ ይቅር ለእግዚአብሔር የምንባባልባት ቀን ነች 💐 *ሐረግ*👩🏽🦱 እረ ቤቱን የስብከት ቤት አደረጋችሁት በቃ ኑ ብሉ 💐 *ፍሪ*👩🏽🦳አንቺ ዝም ብለሽ ሆድሽን አስቢ አባዬ አዳምጥ በመፅሐፈ ኢዮብ ምዕ 11፥18-19 ተስፋ ስላለህ ተዘልለህ ትቀመጣለህ በዙሪያህም ትመለከታለህ በደህንነትም ታርፋለህ ከሞላ ጎደልመፅሐፈ መክብብ 5፥12// 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10፥31 ይበልጥ ያስተምራል አባ 💐 *ሐረግ*👩🏽🦱እማዬ ፊሪ ዝም በሉ እኛ ያልቅብናል ሆሆሆሆ ደግሞ መስጠት 💐ስንሰጥ ይበልጥ ይሰጠናል ልጄ ኦሪት ዘዳግ ምዕ 15፥11 ድሆች ከምድሪቱ ላይ አያልቁምና ስለዚህ እኔ በአገር ዉስጥ ላለው ድሃ ለተቸገረዉም ወንድምህ እጅህን ትከፍታለህ ብዬ አዝዝሃለሁ አየሽ ልጅ ከእግዚአብሔር የተሰጠን ቃል ነው በመፅሐፈ ምሳሌ ምዕ 3፥27// 11፥24-25ም በደንብ ያስተምራል 💐 *ፍሪ*👩🏽🦳 ቃለ ህይወት ያሰማልን እማ ቅዱስ ያዕቆብ በመልክቱ እንዳስተማረን በያዕቆብ በምዕ 2፥15-17 እንዲሁም የሉቃስ ወንጌል ምዕ 6፥38 ስጡ ይሰጣችኋል በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኃል የተጨቁንና የተነቃነቀ የተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ በእቅፋችሁ ይሰጣችኋል 💐 *አብርሃ*🧔🏽ለሁላችሁም ቃለ ህይወት ያሰማልን በሉ እንግዲህ በግ ይዘን አብረን እንሒድ 💐 *ሐረግ*👩🏽🦱 አዎ በእዉነት እኔም ተማርኩ ወይ አለማወቅ ለካ ጠይቁ ይመለስላችኋል የሚባለው ትክክለኛ ነው 💐 *ትግስት*👧🏽 እኔ እኮ እንደዛ ያልኩ እንድታለቅሺ አይደለም እማ አታዛዝንም ስላለቅስ ለእኛ ብላ እንደ እናትም አባታትም ሆና እንጀራ ሸጣ የሰው ልብስ አጥባ ወይ የእናት መከራ እንቺ መፅሐፍ ቅዱስ መዝሙረ ዳዊት 9፥9-10 // መዝሙረ ዳዊት 37፥18-19// መዝሙረ ዳዊት 9፥2 እይዉ እስቲ በዚህ እንመን ችግርን የምናመጣው እኛ ብቻ ነን አሁን ተነሽና እማዬን ይቅርታ ጠይቃት 💐 *ቅድስት*👩🏽 */እያለቀሰች* እማዬ ይቅርታ አስጨነኩሽ አይደል 💐 *እናት አለሜ*👳🏼♀ እናት አያኮርፍም ልጄ እንደዉ አይሟላልኝ ብሎ ነው እንጂ ሁሌም አስባለሁ 💐 *ቅድስት*👩🏽እማ እኔ ነኝ ግራ ያጋባሁሽ 💐 *እናት አለሜ*👳🏼♀ፅዮንም ሆይ ለአምላክሽ እልል በይ የደጆችሽን መወርወሪያ አፅንቷልና ልጆችም በዉስጥ ባርኳቸዋልና እሰይ ልጄ ተባረኪልኝ 💐 *ትግስት*👧🏽እማዬደስ ስትሉ ፍቅር ሞላው ቤታችን 💐 *እናት አለሜ*👳🏼♀እንዴ አቶ አብርሃም መጡ ምን ፈልገዉ ይሆን ምን ቀራቸው በእግዚአብሔር እኛንም ሊጨርስ ነው የቀረነዉን ልጆቼ ግቡ ወደ ዉስጥ 💐 *ቅድስት*👩🏽 እማ ሞት አይፈራም ይግደለን ሁላችንም ደግሞ በግ ይዟል ዛሬ ቀኑ ትንሳኤ ስለሆነ ይቅር ሊጠይቅ መቶ ሊሆን ይችላል
#ምኒልክ_ያችን_ሰዓት 🙏 የካቲት 23/ 1888 ማለዳ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት እምዬ ዳግማዊ አጤ ምኒልክ አድዋ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ያረጉት ፀሎት ስብሐት ለእግዚአብሔር- ኅያው በመንበሩ ሰላም ለዛቲ -ሃገሪትነ ቅድስት ወሰላም ለህዝብየ- ዘይሔሉ ለምድሩ ዘይመውት -ለክብሩ ፡፡ ምስጋና ለሕያው አግዚአብሔር ሰላም ለዚህች -አንድ ቅድስት አገር ሰላም ለደጉ ህዝቤ-አፈሬን ብሎ ለሚኖር ክብር ላንተ-ሰማዕቱ የእናት የአባቴ ታቦት ጊዮርጊስ መመኪያዬ-እንግዴህ ከፊቴ ዝመት መንገድ ጥረግ ፈረሰኛው -ቀዳማዊው ሰራዊት ተማርኩ ያለ አገር ሊዘርፍ-ውል አዛንፎ በለበጣ የነገር ፈሩን ስንጨብጥ -ለሴራው ብልሐት ሲያጣ ለጦር ልቡ ሸፍቶ -ዳር ድንበር ጥሶ ከመጣ ፈርሐ-እግዜር የሌለው ጣሊያን -ህዝቤን በጅምላ ሲወር በህዝቤ ተደምስሶ -አደዋ አረህ ውስጥ ሲቀር በሟጥሽ ስር ተበትኖ -በአጋም ስራስር ሲሰባበር እለቱ በደም ታፍኖ-ሰልስቱን በአሞራ ሲያከብር ኪደነ-ምህረት ገሰሶ-ምንድብድብ ሸዊቶ ሜዳ እማርክ ብሎ የመጣ -ሞቱ በአፍታ ቢረዳ እኔ ክፉ እማይደለሁ -ልቤን ቅር እንዳይለው ነገር መቼም ነፍሰ-እግዚሃር ነውና… ክብር ለሃያሉ አምላክ -ቃሌን ቀድሜ ልናገር ፡፡ ቴወድሮስ ይሙት! ቃሌ ነው!! እኔ ምኒልህ … አይኑን ለጨፈነ ጠላት -እዝኑን ለደፈነ ጦረኛ መልህቅ ቢያነሳ ብዬ እንጂ -ይሔ ነጭ ነውረኛ አወድመው እንደሳት ሰደድ -እመታው እንደመጋኛ፡፡ እንዴት አይነት ጥጋብ ነው ? እንዴት አይነት መወፍነን? ምኒልክን ለባርነት- ኢትዮጵያን ለቅኝ ግዛት አሳብ ጠንስሶ መጅመንመን? እንዴት አይነት ንቀት ነው -ምን የሚሉት ሰማይ ማከክ? ጣሊያን ሱሪ የለበሰው ሐበሻን ለማንበርከክ? ...... አዬ ያገሬ ጀግና አንጀተ ፅኑው ገበሬ በማርያም መማፀኔን -ያገር አዋጄን ሰምቶ ከመናገሻ እስከ ሀረር በጌምድር ተጠራርቶ የአራት ማዕዘን -ጀግና ድፍን ኢትዮጵያ ተነስቶ በሮቹን ባለህ ባይ ሳይኖር -ዝሪቱን ለተባይ ትቶ ወንጭፉን ከማማ ሰቅሎ -ጦርና ጋሻ አንግቶ ምኒልህ ጠራኝ ብሎ -በጭብጦ ተሸኝቶ በእፍኝ ጥሬ-ከቤት ወጥቶ ላመል ታህል በኮዳ ውሃ-ከምንጭ በቅል ጠጥቶ ለእግሩ ከለላ ሳይኖረው -አሜኮላውን ጥሶ ጫካውን በግር በፈረስ -ዥው አርጎት እንደኮሶ ላገር ሟቹ ቃል ጠባቂው ይሔው አደዋ ከተመ ለነፃነቱ እልፍ ሆኖ -ለክብሩ በአንድ ተመመ የአብሮነት ቃልኪዳኑን -በባንዲራው ስም አተመ፡፡ እና ከዚህ በላይ -ምን ደስታ አለ? ከህዝብና ከክብሩ- ሰው ካገሩ ከዋለ እምነትና ጀብዱን ታጥቆ -አገሩን ብሎ ለመጣ ሰው እስከ አፅናፍ የሚነገር -ድል ነው ፀዲቅ የሚቆርሰው፡፡ እንደ ቤተ-መቅደሱ -እንደ ሞገሩ ሽታ እንደ ነጋሪቱ ድምፅ -መለከትና እምቢልታ ተመስገን ያባቴ አምላክ -ልቤ ሃሴት ተሞልቷል ሰማዕቱ በእለተ ቀንህ -ክንዴ እልፍ ጦር አንግቷል ህዝቤ -አፎቱን ከፍቷል ብቻ ህልም አየሁ በሰመመን… አንጎለላ ኪዳነምህረት -ከደጅሽ የወይራ አፀድ በቀስተዳመና ተከቦ- አንዱ ክንፍ ተቆርጦ ሲወርድ ይሔ ሃሞተ መራር-ይሔ ልበ ተራራ የሰው ምክር ግድ የለው-ትንሽ ለነፍሱ አይፈራ ቀኝ እጄን እንዳላጣው- ክንዴን ገበየሁን አደራ:: ክብር ለአያቶቼ ኢትዮጵያን ከነ-ስሟ -ከነ ክብሯ ላኖሯት ጣሊያን ጉድጓዱ ይገባል -ዛሬም ማንም አይደፍራት። የካሳ እልፍኝ ይታዘበኝ -ጦር ሰልጥኜ ያደኩበት ልበ-ባህሩ ሸዋ -አባ መቻል-አባ መስጠት ስም አልጠራም አባባ ብዬ -አይወልደኝም ሀይለመለኮት እኔ ዳኘው ምኒልህ -ወገኔን ካሳፈርኩት !! በቀዳማዊ ምኒልክ -በሳህለ ሥላሴ መንፈስ በአያቴ ወንበር ዘውድ ስጭን -በጥንቶቹ አልጋ ስነግስ እንዴት ተብሎ ቃል ቢዛነፍ-ጫፏ ይነካል አገሬ አፍር ይሆናል እንጂ-ጠላት ይገባል መረሬ!! እውነት ኪዳነ-ምህረት -በቀንሽ ቅጠል ሳልበጥስ ዳዊት ከደጅሽ ደግሜ -ፀበል ጠጥቼ ሳልሰልስ ቆመ-ብዕሴሽን ታሽቼ-ገራገራሽን ተሳልሜ የኖርኩት የከበርኩት -ባንች እማዶለ አለሜ ! ፈገግተዋ የሚያጠግበኝ-የመኖር ውሃ ሙላቴ እንግዲህ አንቺ ከልያት-ከፊት ቀድማለች ጣይቴ ፡፡ አሔሔ! ኢትዮጵያዊነት ሥሙ -ሀይሉ ካድማስ የሚርቀው የወገኔ እንኳን ጦሩ-ድምጡ ጠላት የሚንደው ከወረይሉ እስከ ሶሎዳ - እየፎከረ የተመመው እምቢ ብሎ እንደመጣ -የድል ጀንበር ሊያሳልፍ ነው፡፡ እንግዴህ ይህ ነው ፀሎቴ ... ይህ ቀን -ታላቅ ነውና - የኢትዮጵያ ሐያልነት በአደባባይ ይወሳ ወራሪ አጥንቱ ደቆ- ከደሃ ላይ እጁን ያንሳ አንበሳ አንበሳ ነውና- እንደትላንቱ ዛሬም ያግሳ ጥቁርና የጥቁር ምድር- አንገቱ ቀና ይበል የሐበሻን ጠንካራ ክንድ -አውሮጳም አምኖ ይቀበል ። እኔ ምኒልህ አይኑን ለጨፈነ ጠላት -እዝኑን ለደፈነ ጦረኛ ልቦና ቢገዛ ብየ-እንጂ -ይሔ ነጭ ነውረኛ አወድመው እንደሳት ሰደድ -እመታው እንደመጋኛ፡፡ ብቻ ህልም አየሁ በሰመመን… አንጎለላ ኪዳነምህረት -ከደጅሽ የወይራ አፀድ በቀስተዳመና ተከቦ -አንዱ ክንፍ ተቆርጦ ሲወርድ ይሔ ሃሞተ መራር-ይሔ ልበ ተራራ የሰው ምክር ግድ የለው-ትንሽ ለነፍሱ አይፈራ ቀኝ እጄን እንዳላጣው ክንዴን ገበየሁን አደራ፡፡ የኪነጥበብ ቤተሰብ ይሁኑ ! @sundayschoolstudents የሰንበት ት/ቤት ኪነጥበብ ክፍል !
ዋ!... ያቺ አድዋ ዋ!... ዓድዋ ሩቅዋ የዓለት ምሰሶ ጥግዋ ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ ዓድዋ… ባንቺ ህልውና በትዝታሽ ብጽዕና በመሥዋዕት ክንድሽ ዜና አበው ታደሙ እንደገና… ዋ! ዓድዋ የዘር ዐፅመ ርስትዋ የደም ትቢያ መቀነትዋ በሞት ከባርነት ሥርየት በደም ለነፃነት ስለት አበው የተሰዉብሽ ለት፤ ዓድዋ የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ የኢትዮጵያነት ምስክርዋ ዓድዋ የኩሩ ደም ባንቺ ጽዋ ታድማ በመዘንበልዋ ዐፅምሽ በትንሣኤ ነፋስ ደምሽ በነፃነት ሕዋስ ሲቀሰቀስ ትንሳኤዋ ተግ ሲል ሲንር ትቢያዋ ብር ትር ሲል ጥሪዋ ድው-እልም ሲል ጋሻዋ ሲያስተጋባ ከበሮዋ ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ ያባ መቻል ያባ ዳኘው ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው ያባ በለው በለው ሲለው በለው-በለው-በለው-በለው! ዋ!... ዓድዋ… ያንቺን ጽዋ ያንቺን አይጣል ማስቻል ያለው አባ መቻል በዳኘው ልብ በአባ መላው በገበየሁ በአባ ጎራው በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው በለው ብሎ በለው፣ በለው- በለው! ዋ! … ዓድዋ … ዓድዋ የትላንትናዋ ይኸው ባንቺ ህልውና በትዝታሽ ብፅዕና በመሥዋዕት ክንድሽ ዝና በነፃነት ቅርስሽ ዜና አበው ተነሡ እደገና፡፡ … ዋ! … ያቺ ዓድዋ ዓድዋ ሩቅዋ የዐለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ ዓድዋ… ( ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ) የኪነጥበብ ቤተሰብ ይሁኑ ! @sundayschoolstudents የሰንበት ት/ቤት ኪነጥበብ ክፍል !
++ ኪነጥበብ - መንፈሳዊ ሙግት ! (ርዕስ - የነፍስና የስጋ ሙግት ) ነፍስና ስጋ ቅዳሜ ማታ ለእሁድ አጥቢያ በቤት ተቀምጠው ሲጨዋወቱ ነፍስ "ነገ እሁድ በጧት ተነስቼ ለፀሎት ወደ ቤተ ክርስቲያን እሄዳለው" አለች፤ ስጋ ደግሞ እኔም መክፈልት ለመብላት አብሬሽ እሄዳለው አለቻት፤ በማግስቱም እሁድ ጧት ነፍስ ለፀሎት ስጋ ለመክፈልት ወደ ቤተክርስቲያን ሄደው እንደቆሙ አንድ የሐዲስ መምህር ምን እንበላለን ብላችሁ አታስቡ፤ የማይዘሩ የማይሰበስቡ አእዋፍን አብነት አድርጉ እነርሱ እግዚአብሔር ይመግባቸዋል እንጂ አይዘሩም፣ አይሰበስቡም የሚለውን እያነበበ ለምእመናኑ ሲያስተምር ሰምተው በሚመለሱበት ጊዜ ነፍስና ስጋ እየተሟገቱ እየተጨቃጨቁ ወደ ቤታቼው ገቡ። መክፈልት ሲሹ መቅሰፍት እንደሚባለው ወይ እግር አለማረፍ እንግዲያው እኔ ካላሰብሁ ማን አስቦ ሊያሳድረኝ ነው እያለች ስጋ ነፍስን ትወዘግባት ነበር፤ ነፍስ ግን ሁሉንም ከጉዳይ ሳትቆጥረው በየሳምንቱ ወደ ቤተ ክርስቲያን ስትገሰግስ ስጋም መክፈልትን ለምዳ ተከትላ መሄዷን አላቋረጠችም ነበር፤ አንድ ቀንም ሰባኪው በተለመደው ስብከቱ ስጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘላለም ህይወት አለው የሚለውን ቃል ሲያስተምር ሰምታ ምን እበላ ምን እጠጣ እያልኩ እንዳላስብ ከዚህ መብልና መጠጥ ማን በሰጠኝ በማለት አስባ ለንስሐ አባቷ ነገረቻቼው። እርሳቸውም እኔን ምን ከፋኝ በጣም ደስ ይለኛል አሁንም ባልሽን ጥሪና እሰጣችዋለው አሏት፤ ስጋም ከአሳብ ለመዳን ጓጉታ ነበርና ወዲያው በፍጥነት ባሏን ጠርታ አምጥታ ከህይወት መብል በልተው ከህይወትመጠጥ ጠጥተው ደስ እያላቸው ወደ ቤታቼው ተመለሱ። ከዚያች ሌሊት ነፍስ ዘለአለማዊ ስንቋን አስገኘች ከስጋ ተለይታ ወደማይቀሩባት አዲስ አለም ወደ ገነት ከመላእክት ጋር አረገች። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን ! የነፍስና የሥጋን ሙግት መጨረሻውን እንዴት አያችሁት ? ይኸን ዓይነት የኪነጥበብ ሥራዎችን በምስጢሬን ላካፍላችሁ ፕሮግራሞች መጠቀም ትችላላችሁ ! የኪነጥበብ ቤተሰብ ይሁኑ ! @sundayschoolstudents የሰንበት ት/ቤት ኪነጥበብ ክፍል !
++ ሥነጽሑፍ - የነነዌ ግጥም ! (ርዕስ - ምነው ተኝተሀል? ) ባለማመን ደዌ ፥ ሀገር ስትማቅቅ በክህደት ማዕበል ፥ የህዝብ ልብ ሲወድቅ በኃጢአት ትኩሳት ፥ ምድር ስትጨነቅ መርከብ - "የሰው ልጅ ነፍስ" በኃጢአት ስትማስን - ከሰውነት ስታንስ ቁሳዊነትና ዝንጀሮነት ሲነግስ ክፉ አሳብ ፥ ክፉ ምኞት ክፉ ግብር ፥ ርኩሰት ... መርከብ "የነነዌ ምድርን" ሲንጥ ጎርፍና ማዕበል ፥ መርከቧን ሲያናውጥ መቅሰፍት በዙርያዋ ሲያንዣብብ የእግዚአብሔር ቁጣ በዙሪያዋ ሲረብ ... አንተ የእግዚአብሔር ነብይ ፥ ወደ የት ሄደሃል ? የታወከን ትውልድ ፥ መስበክ መገሰፅህ ፥ ጨውነትህ የታል? የቀደመ ቸልታህ ፥ የዝምታህ መብዛት የትውልድን ስብራት ፥ ቸል ብለህ ማዬት ፅኑ እንቅልፍና አዚም ፥ ከእንቅልፍ አለመንቃት... እሱን ሁሉ ታወው ፥ እርሱን አላነሳም አሁን ስትቀሰቀስ ግን ፥ ለምን አትነቃም? ወደ ነነዌ ምድር ገስግሰህ እንድትወጣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ አንተ ሲመጣ እንድትሰብክ እንድትገስፅ የእግዚአብሔርን ቁጣ ለህዝብ እንድትገልፅ ከእግዚአብሔር ተለያችሁ ከአምላክ ራቃችሁ ህጉንና ስርዓቱን በርግጥም ሻራችሁ ስለ ክፉ ስራ ከአምላክ ሸሻችሁ ብለክ እንድትሰብክ ከአምላክ ብትላክ በራህ ፈቃድ ፥ ዋጋንና ገንዘብን ከፍለህ ከአምላክ ትኮበልል ፥ ከአምላክ ትሸሻለህ ! ወይ ዮናስ የዋኅ ሰው ልብህን ምን ነካው .. አልሰማህም ይሆን ነብዩ ዳዊትን ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ ከአንተስ ወዴት እሸሻለሁ ወደ ሰማይ ብሄድ አንተ በዚያ አለህ ወደ ባህር ብጠልቅ በዚያ ትገኛለህ የሚል ተደምሞውን ውዳሴ መዝሙሩን.... መልእክተኛው ዮናስ.. እግዚአብሔር ቀስቅሶህ ፥ እንዲያ አለመንቃትህ አለመታዘዝህ ፥ እንዲያ ማጉረምረምህ ይሄ ጸጸት ሆኖ ፥ እንቅልፍን ሳይነሳህ በማዕበልና ሞገድ ፥ መርከብህ ስትናጥ አህዛብ ለጸሎት ሲተጉ ፥ ባህር ስትናወጥ እግዚኦታና ዋይታ ጩኸት ሲበረታ ስላንተ አለመታዘዝ ባሕር ስትናዘዝ አንተ ግን ... መርከብ ላይም ወጥተህ ማዕበል እያማታህ ፥ በጩኸት ተከበህ ቢጠሩህ አትሰማም ፥ ብርቱ እንቅልፍ ላይ ነህ ! ይገርመኛል ዮናስ ! ሂድ ለጸሎት ቀስቅስ ፤ ተብለህ ብትታዘዝ ፥ ተብለህ ብትነገር በአህዛብ አንደበት ፥ ተነሥና ጸልይ ፤ ተብለህ መገሰፅህ ፥ ምንኛ ያሳፍር? ደግሞስ ! በነቢይነት ክብር ከመገኜት ብትሸሽ ፥ ነነዌ ባትሄድ ስለ አመፀኛነትህ በአህዛብ ፥ ስትጣል ወደ ባህር ስትወርድ ... ምን አይነት መራቆት ፥ ምን አይነትስ ጉድ በፈቃድ መጎስቆል ከከፍታ መውረድ እያልኩ አስባለሁ ሀሳብ አወጣለሁ ሀሳብ አወርዳለሁ በስከመጨረሻም የስካሁኑ ዮናስ እኔ ነኝ እላለሁ። ያንተ ታሪክ ግን አሁንም ይቀጥላል ከብርቱ አዚም ኋላ መንቃትህ ተገልጧል ለመርከቢቱ መናወጥ ፥ ምክንያት እኔ ነኝ ልሞት ይገባኛል ፥ ወደ ባሕር ጣሉኝ ብለህ በራስህ ላይ ስትፈርድ ንስሓን ስታውጅ ፥ ራስህን ስታዋርድ የልቦናህ መሰበር ፥ የፀፀትህ ጥልቀት ሆኖልህ መታደስ /መፈወስ ፥ ክብርና ሹመት ዳግም መልሶሃል ፥ ወደ ቀደመ ማዕረግህ ፥ ወደ ነብይነት አንተን ሳስብ ዮናስ ! የንስሓን በረከት ፥ ፈፅሜ አደንቃለሁ ዕፁብ ድንቅ እያልኩኝ ፥ በአግራሞት እቆማለሁ በተፀፀትክበት አፍታ ፥ በዓይን ጥቅሻ ፍጥነት ወዲያውኑ በቅፅበት ማዕበል ከሚያናውጣት የዓሣ አንበሪ ከሚገለብጣት ረዓድና ፍርሃት ፥ በርሷ ዘንድ ካሉባት ሰው ሰራሽ መርከብ ወጥተህ ያለምንም ስጋት የምትጓዝበት መገልበጥ ማዕበል ፥ ስጋት የሌለበት አድነኝም ያይደል ፥ አዳንከኝ ለማለት ፥ ለመሆን ምስክር "ደህንነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው"፤ ብለህ ለመዘመር ወደ ባህር ሰርጓጅ ፥ መርከብ ለመግባትህ በዓሣ አንባሪ መርከብነት ፥ ለመፈናጠጥህ... ከአመፀኛነት ነጥቆ በነቢይነት ክብር ዳግም የሚያስፅፍህ አሁንም ወደ ነነዌ ለመሄድህ ሞገስ ያስገኜልህ ክብር የሆነልህ የእግዚአብሔር ቸርነት የንስሓህ በረከት ምንኛ ድንቅ ነው ? ምንኛ ግሩም ነው ? ከፍጡር ከፈጣሪ እንድትታረቅ ፥ በእውነት ሸምጋይ ነው ! ስለ መመለሰህ የንስሓ ጉዞህ በዚህ ብደሰትም አንተን አልዋሽህም እንዲህ ስል አምቼሀለሁ አንተን ታዝቤያለሁ... ይህንን ሁሉ ተዓምር ፥ በዓይኖችህ እያየህ አንድ ነፍስ አንተ ፥ በድለህም እንኳን ፥ እንዲህ ሲፈልግህ ማዕበልና ሞገድ ፥ ባሕር ውስጥ ሲሻህ ዓሣ አንባሪ ሆድ ፥ ውስጥ በዚያ ሲጠብቅህ ለሰው ታለውን ፍቅር ፥ በስራው እያዬህ ይህንን ከመረዳት ፥ ስለምን ታካች ሆንህ? ይልቁንም አንተ ያልተከልካት ፥ ያላበቀልካት የአንዲት ቅል መቆረጥ ፥ በትል መበላት ያንተ በነፋስ መጠውለግ ፥ በፀሐይ መመታት የሚከነክንህ ፥ የሚያስመኝህ ለሞት እንዲያ ሆነህ ሳለ ... ሲሆን እንደ ሙሴ ፥ እንደ ደጉ አባት ከመጽሐፍ ደምስሰኝ ፥ ስለእነርሱ ልሙት ማለትህን ስንጠብቅ ፥ ስለህዝብ መቅናት ከህዝብ መዳን ይልቅ ፥ ንግግርህ ገዶህ ያዙኝ ልቀቁኝ ባይ ፥ ነብይን መሆንህ 120ሺን ተነሳሂ ፤ የእግዚአብሔር ፍጥረታት የነነዌን ከተማ መገልበጥ ፤ ከምድረ ገፅ መጥፋት አሁን ካልሆነ እያልክ ማላዘንህ ፤ በብርቱው መቆጣት ምኑ ይሉት ጭካኔ ፥ ምን ይሉትስ ክፋት ... ! እያልኩ ሀሳብ አወጣለሁ ፥ ሀሳብ አወርዳለሁ በአንተና በነነዌ አንፃር ፤ የእግዚአብሔርን ፍቅር ፈፅሜ አደንቃለሁ ! በስከመጨረሻም እርሱ ማለት እኔ ነነዌም ወገኔ ስል እታዘባለሁ ራሴን አያለሁ ! በእንቅልፍ ብዛት የከበዱ ዓይኖቼን ከአምላክ ስለመሼሽ የሚተጉ እግሮቼን ከአንተ ለመራቅ ፥ ዋጋ የሚከፍሉ ጉስቁል እጆቼን ከሌሎች መዳን ይልቅ ፥ ክብርን የሚሻ የዕቡይ ልቦናዬን ፥ የእኔን መጨረሻ አሁንም ቅድምም ፥ አወጣ አወርዳለሁ በአንተ መስታውትነት ፥ ራሴን አያለሁ ፥ ውስጤን አደምጣለሁ ! በስተመጨረሻም ፥ እኔ ሆይ ! " ምነው ተኝተሃል" ስል እጠይቃለሁ ! ======///========== የነነዌ ህዝብን በምህረቱ የጎበኘ እግዚአብሔር ለሀገራችንም ለህዝባችንም ምህረትና ቸርነቱን ያብዛልን፤ ፆሙን የበረከት ፆም ያድርግልን አሜን ፫ 🙏 የኪነጥበብ ቤተሰብ ይሁኑ ! @sundayschoolstudents የሰንበት ት/ቤት ኪነጥበብ ክፍል !
++ ኪነጥበብ - የሠርግ ግጥም ! ( ርዕስ - ሕይወት ሲተረጎም ) አምላክ ቀዳማዊ ፍጥረትን ሲፈጥር ሁሉን በየዘሩ። እንስሳት ሲሮጡ አዕዋፍ ሲበሩ። አሣት በበሕር ውስጥ አራዊት በዱሩ። በክብር ላይ ክብር አዳምና ሔዋን እንደ አምላክ ሲያምሩ። መልኩን መልክ ነሥተው ግብሩን እንደ ግብሩ። ይህን ተገንዝበው መላእክት ዘመሩ። አዳም ተለይቶ ከሁሉም ፍጥረታት ግብር እምግብር ሲፈጠር ከውሃ ከመሬት ከነፋስ ከእሳት ከአራቱ ባሕርያት ብቻውን እንዳይሆን እንዲተካ ፍጥረት ሔዋንን ከጎኑ አምላክ አስገኘለት። በዚህ ዓለም ሲኖር ብቻውን ይሆን ዘንድ ሰው አግባብ አይደለም እንዳሉ ሥላሴ ከአዳም ተነሥቶ በአበው ተተክቶ ሰው ሰውን ሲተካ ከሰው ተገኝቶ። የቻለ ሲመንን የልቻለ ሲወሰን በሕግ ተመሥርቶ። አምላክ ሰውን ሆኖ ሠርግ ቤት ተገኝቶ። ቃና ዘገሊላን ከባረከ ወዲህ በቤተክርስቲያን ሥርዓት ተሰራ በደንግልናቸው ጸንተው ለሚኖሩ በሥርዓተ ቁርባን በተክሊል ሲከብሩ። ለተክሊል ያልበቁ በቁርባን ሲዳሩ። የቴዎብስታና የኤርምያስ ተራ ሲወርድ ሲዋረድ ዛሬውኑ ደርሶ በተክሊል ተዳሩ ድግስ ተደግሶ። የቴዎብታማ እጅጉን ይደንቃል የእድሏ ነገር ከሌላው ይበልጣል በድንግልናዋ ጸንታ ስለኖረች ኤርምያስ ዲያቆኑን መምህሩን ታደለች። ይቺ ቴዎብስታ እጅግ አመሮባታል ፍጹም ተውባለች። በተክሊል አጊጣ ካባ ደርባለች። መርዓት ቴዎብስታ ጀሮ ጌጥ አታርጊ አልቦም አያሻሽም ድሪም አታጠልቂ አባርሽን አውልቂ ስንድድም እንደዛው። ክብርሽ ድንግልናሽ ውበትሽ ተክሊል ነው። እርሱ ይበቃሻል ኤርምያስ የገዛው። መርዓት ቴዎብስታ የነቢይ ኤርምያስ ፍቅሩ ልብሽ አድሮ። ለጸሎት ስትቆሚ አንደበትሽ ሠምሮ። ጸሎትሽን ሰምቶ እግዚአብሔር ዘንድሮ። ለክብር አብቅቶሻል በሚካኤል አድሮ። ከነቢያት ሁሉ ማንን ትወጃለች ቴዎብስታን ደንገት ብየ ስጠይቃት ድምጿን ከፍ አድርጋ በፍጥነት መለሰች ከዐበይት ነቢያት ኤርምያስን አለች። ድሮ ቴዎብስታን ብቸኝነት ሕመም ቢያማተይ በጠና በፍጹም እምነቷ ቁማ ተቀምጣ አምላከ ነቢያት አምላከ ኤርምያስ እያለች ተማጽና ከብቸኝነቷ ከሕመሟ ዳነች ፍጹም ሆነች ደኅና። የሰንበት ተማሪ ይቺ ቴዎብስታ። ማንበብ ትወዳለች መጻፍ ጠዋት ማታ። እንዲሁም ዘወትር ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል። የኤርምያስ ትንቢት እጂግ ደስ ይላታል። ዘመኑ ሲፈጸም የኤርምያስ ቃሉ ራዕይ ትንቢቱ ከባቢሎን ምርኮ የብቸኝነቱ። ሰቆቃው አለፈ ሰላም ገባ ቤቱ። ለነቢይ ኤርምያስ ሚካኤል ሲነግረው በራዕይ ተገልጦ። ቴዎብስታን አያት አንጂባ ተቀምጦ። መምህር ኤርምያስ ወረብ እያዜመ ልዕልት ቴዎብስታ ድንገት ብትሰማ። ልቧ ተመሰጠ በኤርምያስ ዜማ። በፍቅሩ ወደቀች እጂግ ታማ ታማ። ድርሳነ ሚካኤል በሚያነብ ጊዜ መምህር ኤርምያስ። እጂግ ይደነቃል በነቴዎብስታ በነዱራታኦስ። የቴዎብስታችን ጸሎቷ ተሰማ። ስለሚጠብቋት ኤርምያስ በምድር ሚካኤል / ገብርኤል በራማ። ጸንታ ትኖራለች በዝች ከተማ። የቴዎብስታን ገጽ ዐይኗን ዐይኗን ብታይ ኤርምያስ አበበ የለብህም ከልካይ። ለዲያቆን ኤርምያስ እጂግ በዝቶልሀል የእግዚአብሔር ጸጋ። ስለመታዘዝህ ለክብርህ መለያ። ቴዎብስታን ሰጠህ የሴቶችን ላቂያ። ስለ ፍቅር ብለህ ያም ለማያረጅ። ኤርምያስ መጽናትህ ቴዎብስታ ደጅ። መልአክ አይደለህም ልክ እንደ ቦሰና በተፈጥሮ ጉዳይ ሰውብትሆን ነው እንጂ። ሰኔ ሀምሌ ግንቦት ዝናብ በዘነበ። በበር የበቀለው የሮማን አበባ ኤርምያስ አበበ ፍሬሕይወት ሆነ ፍሬው ተቀመ። ይቺ ቴዎብስታ በፍጹም ውበቷ ያለም ወርቅ የሆነች ለኔስ ለሕይወቴ ኤርምያስ ኤርምያስ አለልኝ ትላለች። የቴዎብስታን መልክ ዐይኗን እንድታየው። ወንድሜ ኤርምያስ ፎቶ ስታነሳ ካሜራህን አስፋው። የዲያቆን ኤርምያስ የቀና ምኞቱ። የሠመረ መሆን እንደ አቤል መሥዋቱ። አንደ አባታችን አብርሃም እምነቱ። ስለማይቋረጥ የዳዊት ጸሎቱ። መርአዊ ኤርምያስ የሕይወቱን ፍሬ በስብሐት ፈንታውን አግኝቶ እጂግ ደስ ብሎታል በያሬድ ምስጋና ፍጹም ተደስቶ። ኤርምያስ መርአዊ የአለባበሱ ያለው የደስደስ እጂጉን አጊጧል ተመስሎ ንጉሥ። የመዳሪያው ጊዜ ፋንታው በመድረሱ የተክሊሉ ሥርዓት በቃሉ ሲፈጸም ደርሰው ሲመሉ እልል በሉለት እናጅብ ተነሱ ኤርምያስ ዛሬ ቀን ደስ ብሎት ዋለ፡ ዓለሙንም ገዛው እልል እያስባለ። መርአዊ ኤርምያስ በፍጹም ተመልቷል ፊቱ በፈገግታ። ጥርሶቹም አምረዋል በሳቅ በጨዋታ። አንደበቱም ቀንቷል በደስታ ገጽታ። የደስታው መፍሰሻ መጥታ ቴዎብስታ። መምህር ኤርምያስ ሰለ ተክሊል ሰብኮ። ቴዎብስታን ነሣ በካህን ተባርኮ። ኤርምያስ መርአዊ መርዓት ቴዎብስታ። አንተ እንደ አብርሃም አንቺም እንደሳራ። ዘመናችሁ ይስመር ቤታችሁ ይሰራ። ውለዱ ክበዱ ስማችሁ ይጠራ። 🧖♀️🧖♂️ 💞 በቅኔው ውስጥ የተካተቱ የሙሽራውና የሙሽሪት የቤተሰቦቻቸው ስሞች ፦ አበበ : ላቂያ ፣ አስፋው ፣ ያለምወርቅ ፣ ፍሬ ሕይወት ፣ሰውብትሆን ቦሰና ፣ በሪሁን፣ አቤል ፣ አብርሃም ፣ ዳዊት ፣ ያሬድ ፣ ፍሬ ሕብሐት ፣ ዋለ ፣ ገዛው ፣ ፋንታሁን ፣ ንጉሤ ፣ ዓለሙ። ( የሠርግ ግጥም : ለዲ/ን ኤርምያስ እና ቴዎብስታ ) በማኅቶት እሸቴ ፥ ክብረት ይስጥልን 🙏🤴 የኪነጥበብ ቤተሰብ ይሁኑ ! @sundayschoolstudents የሰንበት ት/ቤት ኪነጥበብ ክፍል !
++ ኪነጥበብ - መነባንብ ! ( ርዕስ - ባህረ ዮርዳኖስ ) አንቺ ሰፊ ባህር ዮርዳኖስ መስክሪ የተጠመቀብሽ የአለም ፈጣሪ ትንቢት መነገሩ በዳዊት ነብይ ድምፅ በውኖች ነው ብሎ መመስከሩ በውኖች ይታያል ብሎ መዘከሩ በዩርዳኖስ መሸሽ ትልቁ ሚስጥር የዩርዳኖስ ባህር አምላኩን ማክበሩ በጥልቅ ውሃዎች ላይ ስልጣን አለው ሲሉ አምላክን ማክበሩ ፈርቶ መንቀጥቀጡ ሰዎች ሳይረዱ ወንዙ መረዳቱ የዳዊት ትንቢት ትውልድ መዘንጋቱ ምን ይባላል አሁን እውነትን መሣቱ ሰው መዳኑን ንቆ እንዲህ መቅበዝበዙ ዳዊት ለምን ሸሸ ብሎ የጠየቀሽ ባህረ ዮርዳኖስ ፈጣሪሽን አወቅሽ ኧረ አንቺ ዮርዳኖስ ኢያሱየከፈለሽ ሕዝበ እስራኤን በአንቺ ያሻገረብሽ ከዕለቱ ክርስቶስ ውሃ ያጠጣብሽ ኤልሳና ኤልያስ ደግሞ የቆሙብሽ ለመጎናፀፍያ ከፍለው ያለፉብሽ ንዕማር ሲጠመቅ ከለምጹየነፃብሽ ሰው የሆነ ንጉስ ባንቺ ሲታይብሽ ይህ ሁሉ ሲደረግ ትግሉ ሲሰምርብሽ ዩሐንስ ሲያጠምቅ መድህን ሲመጣብሽ እራሱን አዋርዶ ባንቺ ሲታይብሽ ወልድ አምላክ በክብር ሲጠመቅ በውስጥሽ እርጥበትሽ ሳይደርቅ እሳቱ ሳይፈጅሽ ዮርዳኖስ ድንቅ ነው ጸንተሽ መገኘትሽ ይመሰክር ጀመር ዩሐንስ ተረድቶ የእግዚአብሔር በግ መጣ ይኽው ብሎ እኔ አላውቀውም ጥንትም ነበር ደግም አለ መስከር እውነት ተናገር በእሳት የሚያጠምቅ ይመጣል እያለ ታዲያ እንዲህ ሰዎች ሲጠመቁ መድሐኒት ብቅ አለ ከወደ ጥምቀቱ በዮሐንስ እጆች ሊጠመቅ ፈልጎ ዩሐንስ አዘነ እጅግ ተፀፀተ አምላከ ሰማይን እንዴት ላጥምቅ ብሎ ፅድቅን ለመፈፀም ወዲህ መጣሁኝ ብሎ ሲያስተምረው መድሐኒዓለም ያጠምቀው ጀመረ በእሽታ መንፈስ እየሱስ ሲጠመቅ በዮሐንስ እጅ ሰማያት ተከፍተው ቃል ሲመጣለት መንፈስ ቅዱስ መጥቶ በራሱ ላይ ሲያርፍ የምወደው ልጄ ይህ ነው ስሙት ተብሎ ሲነገር ከእግዚአብሔር አብ የስላሴ ምስጢር በዮርዳኖስ ባህር ተገልጾ ነበር የአንድነት ምስጢር አንድነት ሶስትነት ያለመከፋፈል ሰዎች ሲጠመቁ በስላሴ ስም የእግዚአብሔር ልጅነት ያገኙ ነበር ታዲያ ምን ይባላል የአሁኑ ትዕቢት ስላሴ ምንድ ነው ብሎ መደንፋት ኢየሱስ አንድ አካል ፍጡር ነው ማለት ልበ ቆሻሻዎች የክርስቶስ ጠር ጆረአቸው ተደፎኖ ልባቸው ቢዝል በዮርዳኖስ ታይቷል የአንድነት ምስጢር የወደደ ይምጣ የጠላ ይመለስ አይከለስ እንደው የዮርዳኖስ እውነት ከባህሮች ተመርጠሽ ዮርዳኖስ የታደልሽ ምስጢር ስላሴ የተገለፀብሽ አንቺ ሰፊ ምድር ዮርዳኖስ መስክሪ የተጠመቀብሽ የዓለም ፈጣሪ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ! ! ጥምቀተ ባሕር ዮርዳኖስ ነያ /2/ ሀሌ ሉያ /4/ እልል በይ ዮርዳኖስ የጥምቀት መገኛ የጽድቅ መሰላል የድኅነታችን መገኛ ቀላያት አብርህት ብዙዎች እያሉ እንደምን ተመረጥሽ ዮርዳኖስ ከሁሉ ? የተወደዳችሁ የኪነጥበብ ቤተሰቦች፥ እንኳን ለጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ጥምቀቱ በሠላም በፍቅር አደረሰን አደረሳችሁ 🙏 የኪነጥበብ ቤተሰብ ይሁኑ ! @sundayschoolstudents የሰንበት ት/ቤት ኪነጥበብ ክፍል !
++ ኪነጥበብ - መንፈሳዊ ዜና ! ( መንፈሳዊ አስደሳች ዜና ) ለ5500 ዘመናት በሰው ልጆች እና በዲያብሎስ መካከል የቆይው የትግል ውድድር በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ ምክንያት ትግሉ በሰው ልጆች አሸናፊነት ተጠናቀቀ። ይህም የሆነው ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ንጽሕት ከሆነች ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለ ወንድ ዘር በዳዊት ከተማ በቤተልሔም ዘይሁዳ በከብቶች ግርግም በመወልዱ ነው። በዚህም የነገስታት ንጉስ ኢየሱስ ክርስቶስ ለ5500 ዘመን በዲያብሎስ ቁጥጥር ስር የነበረውን ሪከርድ ሙሉ በሙሉ ሰባብሮ አዲስ ሪከርድ በትህትናው፣ በሃያል ፍቅሩ እና በቸርነቱ አስመዝግቧል። ይህም በመሆኑ የሰው ልጆች እና መላዕክት ጌታችን በተወለደበት ግርግም በአንድነት በደስታ የዘመሩ እና ያመሰግኑ ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ ዲያብሎስ እና ዘረማንዘሮቹ በሙሉ በጥልቁ ሲኦል ሃዘን ተቀምጠዋል። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን ! ! " ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና ደስ ይበላችሁ!! " (ሉቃ 2፥11) ውድ የኪነጥበብ ተከታታዮች እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሠላም አደረሳችሁ አደረሰን እያልን ለበዓሉ ይኸን አስደሳች ዘበር ዜና ለወዳጅ ዘመድዎ የተዋህዶ ልጆች ሸር በማድረግ የገና ስጦታን ያበረክቱ !! እንኳን ለ2018ኛው የጌታችን ልደት አደረሳችሁ አደረሰን !! መልካም የገና በዓል ይሁንላችሁ 🙏 የኪነጥበብ ቤተሰብ ይሁኑ ! @sundayschoolstudents የሰንበት ት/ቤት ኪነጥበብ ክፍል !