የታዋቂ ሰዎች ንግግር
Статистикаአለም ላይ የምናቃቸው የታላላቅ ሰዎች ንግግር ይቀርባል #share share እውነተኛ የጠቢባን ንግግር 🇪🇹😂😂😂😂😂😂🇪🇹 ♎️♊️♋️♐️♍️♒️♑️♈️🔱🔯♓️💢➗💠💡💤💨💦🕐🌟⭐️
- Последний пост
- 11 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 12 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 121
- 1/48двое суток
- 138
- 1/72трое суток
- 149
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
ከእርዕስ ውጪ!! እህታችን እንደኛ መሳቅ መራመድ መጫወት መብላት መጠጣት ሳይሆን መዳን ትፈልጋለች። ሰዎችን በትንሹ ለመርዳት ብዙ ሃተታ መፃፍ የለብንም። ሰው መሆናችን በራሱ ለእርዳታ ሊመራን ይገባል። ስለ ኤልሮኢ ያልሰማ የለም በአጥንት ካንሰር እየተሰቃየች የምትገኝ እህታችን ናት! እና በፈጣሪ ቃል እና በእኛ ርህራሄ ልንረዳት ትጠብቀናለች እና አለንልሽ እንበላት። ራሄል አረጋይ/Rahel aregay TeleBirr - 0911179293 CBE - 1000487578828 Awash Bank - 013471629151800 ✔️ በትንሹ ይሄን ፖስት የሚያይ ሰው 100ብር ቢሰጥ እና 1000 ሰው ቢመለከተው በ ቻናላችን ስም 100ሺ ብር እረዳናት ማለት ነው!! እንደማታሳፍሩኝ አቃለው!! @ETHIOIPTV1206
"በኢኮኖሚ ማደግ አቃተን" ለሚሉ ወጣት ባለትዳሮች፦ በአሁን ሰዓት፡ ትልቁ የወጣት ተጋቢዎች ፈተና፡ "በዚህ ደሞዝ ሠርተን እንለወጣለን ወይ?" የሚል ነው። ብዙ ትዳሮች የሚናጉበት አንዱ ትልቁ ምክንያት፡ በቂ የኾነ ገቢ አለማግኘትና፡ ተምሮ ወይም ለፍቶ በኑሮ መለወጥ አለመቻል ነው። በተለይ፡ ሚስት፡ ባሏ በቂ ገቢ ስለሌለው፡ በትዳሩ ላይ ፍላጎት ታጣና፡ ቁጣ ወይም ንቀት ማሳየት ትጀምራለች። ከዚያም፡ ትዳሩ ይረበሽና፡ ጭቅጭቅና ጭንቀት ቤቱን ይሞላዋል። ይኽን ዓይነት ችግር፡ በተደጋጋሚ በዙርያችን እናያለን፤ ከትዳር አማካሪዎችም ሰምቼያለሁ። እንዲሁም፡ ወጣት ተጋቢዎችም አንዳንዴ በግል ምክሬን እንድለግሣቸው በውስጥ መሥመር ይጠይቁኛል። ከማንም ምክር ወይም እርዳታ የማይጠይቁና፡ እንደአማራጭ፡ መሪጌቶች ጋር ኼደው፡ የሀብት ድግምት የሚያሠሩም ቀላል አይደሉም። እንዲህ ያለው ስኅተት፡ በቁርባን የተጋቡትን ሳይቀሩ እየጣለ ነው። ቁርባናቸውን ረስተው፡ ሀብትና ዕድገት ፍለጋ የደብተሮችንና የጠንቋዮችን ደጅ የሚረግጡ ባልና ሚስቶችን ቤት ይቁጠራቸው። ያሳዝኑኛል፤ እግዚአብሔር መውጫውን ያዘጋጅላቸው። ሰሞኑን፡ ተመሳሳይ የኢኮኖሚ ችግርና የትዳር አለመረጋጋት ለገጠመው ወጣት የጻፍኩትን ምክር ላካፍላችሁ። ለኾነ ሰው ይጠቅም ይኾናል። እናንተም ተመሳሳይ ችግር ላስጨነቃቸው ባለትዳሮች የምትለግሧቸው ምክር ካለ፡ በመወያያ ቡድኑ ጻፉላቸው። * * * "....እናንተ የምትለወጡበትንና የምታድጉበትን ነገር እግዚአብሔር ያስብላችኋል። እንደዚያ እንዲኾን ግን፡ አንድ ላይ የጸሎት ጊዜ ይኑራችሁ። ስምምነት ይኑራችሁ። ትዕግስትና ፍቅር ይኑራችሁ። ተንበርከኩና "ከራሳችንም አልፈን ሰውን የምንረዳበት፤ ልጆቻችንን የምናሳድግበት ሀብት ስጠን፤ አሳድገን፤ አስፋን፤ አብዛን" ብላችሁ ጸልዩ። እግዚአብሔር ያሰባችሁትን ኹሉ ይሰጣችኋል። ከንስሓ ሕይወትና ከቅዱስ ቁርባን አትውጡ። ለዓለማዊ ምኞትና መሻት፥ እንደሌሎች ለመኾንና ለቅንጦት ብላችሁ ገንዘብን አትመኙ። ለበረከት ሕይወት ብላችሁ ለምኑት። ለምግባር ትሩፋት ለመሥሪያ ብላችሁ ለምኑት። "መጽውተን፣ ቤተሰብ ረድተን፣ ዐሥራት በኩራት አውጥተን የምንጸድቅበት ሀብት ስጠን" በሉት፤ ይሰጣችኋል። የጠበቃችሁትን ብቻ ሳይኾን፡ ያልጠበቃችሁትንም ይሰጣችኋል። በዚህ እርግጠኛ ኹኑ። ለሚስትህም ምከራት። "በቅንነት የሚኼዱትን ከመልካም ነገር ኹሉ አያሳጣቸውም" (መዝ 84:11) "አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፤ ይኽም ኹሉ እንደ ዳረጎት ይጨመርላችኋል።" (ማቴ 6:33) "በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ፣ ከምስጋናም ጋራ ልመናችሁን በእግዚአብሔር ፊት አቅርቡ እንጂ ስለ ማንኛውም ነገር አትጨነቁ።" (ፊል 4:6) ማታ ማታ ወይም ጠዋት ጠዋት፡ አብራችሁ ባርቶስን ብትጸልዩ ጥሩ ነው፤ የዘወትሩንም የእለቱንም። ብዙዎች በረከት አግኝተውበታል። ዶ/ር መስረም ለቺሳ
በአንድ ትምህርት ቤት መምህርቷ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገበ ተማሪ ጫማ ሽልማት ለመስጠት ቃል ትገባና ፈተናው ተካሄደ ። በፈተናው ሁሉም ልጆች ተመሳሳይ ውጤት አስመዘገቡና ለሁሉም ጫማ መስጠት ስለማይቻል መምህርቷ አብሰለሰለች። ከዛም አንድ ሃሳብ መጣላት ፦ ለተማሪዎቹ ቁራጭ ወረቀት ሰጠቻቸው እና ስማቸውን በላዩ ላይ እንዲፅፉ እና በዕጣ እንዲለዩ ስማቸው የወጣለትም ጫማ እንድወስድ ወሰነች ። ሁሉም ጽፈው እንደጨረሱ መምህርቷ የሰበሰበችውን ወረቀት በኩባያ ውስጥ ነቀነቀቻቸውና በሁሉም ፊት አንድ ወረቀት መዘዘች። ወረቀቱን ስትከፍት መሎና ይላል ...ሁሉም ደስ አላቸው ። መሎናም በደስታ ተሞልታ ሽልማቱን ተቀበለች። መሎና እነዛን ጫማዎች በጣም ትፈልጋቸው ነበር ። በተቀደደው ባረጀው ጫማዋ በጣም ተሰላችታ ነበር ። አባቷ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል ...እናቷ ድሃና ረዳት የሌላት ስለነበረች ይህ ሽልማት ለሷ ትልቅ ትርጉም ነበረው። ታርኩን ይበልጥ አስገራሚ የሚያደርገው ነገር ታዲያ እዚህ ጋር ነው ያለው ፦ መምህርቷ በኩባያ ውስጥ ያሉትን ሌሎች ወረቀትን ቀስ እያለች አንድበአንድ ስትመለከት እያንዳንዱ ልጅ በወረቀት ላይ የጻፈው የመሎናን ስም ነበር ። ✅ልባችን ንጹህ ስሆን ለኔ ማለትን ትተን ለኛ ማለት እንጀምራለን ✅ልጆች ንፁህ ነጭ ወረቀት ናቸው ጥላቻን ፣ ዘረኝነት አንስበካቸው ✅ፍቅርን መተሳሰብን እንዝራባቸው፣ ያኔ አለምን የተሻለ ቦታ ማድረግ እንችላለን ። "ከቲክቶክ አለም የተወሰደ" የልጆችን አይነት ልብ ይስጠን 🙏 <<መልካም ምሽት👋>> @tebibangegr
ኢትዮጵያ ውስጥ ላይመለሱ የጠፉ ነገሮች:- ➤ ለህዝብና ለሃገር የሚያስብ ታማኝና ቅን መሪ ➤ የፈለግከው የሃገሪቱ ክፍል እንደ ልብህ ተንቀሳቅሶ መስራት ➤ ወጣቶች በሃገራቸው ላይ የነበራቸው ተስፋ ➤ በወር ደሞዝህ ሳትሳቀቅ ከወር ወር መቆየት ➤ በቀን ሶስት ግዜ መብላት ➤ ደስ የሚሉ የክረምት የልጅነት ጊዜያቶች ➤ ክረምት ት/ቤት ሲዘጋ ቤተሰብ ጋር ገጠር መሄድ ➤ በልጅነታችን የፈለግነው የሰፈራችን ቤት እየገባን ምሳና ቁርሳችንን እየበላን የምንውልበት ➤ የሰው ልጅ ዋጋ ከገንዘብ በላይ ነበር 😭😭 ➤ ተምሮ ስራ መያዝ ➤ የአውዳመት ድባብ ፣ ቡና መጠጣት 📌 የቀረ ካለ ጨምሩበት.... መልካም ጊዜ እመኝላቹሃለሁ 💚💛❤️
Download Poppo with me and input my invitation ID:82563963
Live stream finished (3 minutes)
Live stream started
Live stream finished (6 minutes)
Live stream started
ዳኛ ዑመር በጅግጅጋ ከተማ በታላቅ እና ደማቅ አቀባበል ተቀብለዋል። በአቀባበሉ ላይ የክልሉ ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት፣ ከንቲባው፣ የወጣቶች ሚኒስትር፣ የባምቤዳ ኃይል፣ የባህልና የሙዚቃ ቡድኖች እንዲሁም የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል። @tebibangegr
ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው (ሰሜ ባላገሩ) ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘገበ። ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው የተለያዩ ባህላዊ እና ሌሎች ይዘቶቸ ያሏቸው የሙዚቃ ሥራዎችን ለአድማጭ ተመልካች አበርክቷል፡፡ ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት ነበር። ሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ/ም
አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ! 🚨 ሰሞኑን በቴሌግራም ላይ እጅግ አደገኛ የሆነ የአካውንት ጠለፋ እና የማጭበርበር ድርጊት እየተፈጸመ ይገኛል። በጣም ፀያፍ የሆኑ ምስሎችን እና ቪዲዮዎችን እንደ ሽፋን በመጠቀም፣ ከስራቸው ሊንክ (Link) ያያይዛሉ።ሊንኩ የሚላክላችሁ ከማታውቁት ሰው ብቻ ሳይሆን፣ አካውንታቸው በተጠለፈ የቅርብ ጓደኞቻችሁ ወይም ዘመዶቻችሁ ስም ሊሆን ይችላል። ከዚያ ሊንኩን ልክ እንደነካችሁት የእናንተም የቴሌግራም አካውንት ወዲያውኑ በሰከንዶች ውስጥ ይጠቃል፣ ከቁጥጥራችሁ ውጪ ይሆናል። ከዚያም በእናንተ ስም ለሌሎች ሰዎች ተመሳሳይ ቫይረስ ይልካል። ⚠️ስለዚህ ከማንኛውም ሰው (የምታውቁትም ይሁን የማታውቁት) የሚላክላችሁን ማናቸውንም አይነት ሊንክ በፍጹም አትንኩ! አትክፈቱ! እባካችሁ ይህንን መረጃ ለምትወዷቸው ሰዎች ሁሉ በማጋራት ከጠላፊዎች ይታደጓቸው። SHARE @tebibangegr
#ምርጫ2018 ዛሬ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ መካሄድ ጀምሯል። @tebibangegr
አርቲስት ሰላማዊት ደስታ ከዚህ ዓለም ድካም አረፈች አርቲስት ሰላማዊት ደስታ ባደረባት ህመም ምክንያት በህክምና ስትረዳ ቆይታ ግንቦት 21/2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፋለች። የአርቲስት ሰላማዊት ደስታ የሽኝት ፕሮግራም በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ዛሬ ግንቦት 22/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ቤተሰቦቿ፣ ዘመዶቿ፣ ጓደኞቿና የሙያ አጋሮቿ በተገኙበት የሚከናወን ሲሆን የቀብር ስነስርአቱ ከቀኑ 7:00 ሰዓት በማህደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም እና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ይፈፀማል።
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖች፣ እንኳን ለኢድ አል አደሃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ኢድ ሙባረክ
የህይወት አርቲቡርቲ፥ ቅጥ ያጣ የኢኮኖሚ አለመረጋጋት፥ ሰው ሰራሽ የኑሮ ውድነት፥ የዘረኝነት እንቶፈንቶ፥ የሃይማኖት አክራሪነት ለደቆሰው ለዚህ ህዝብ ደስታውን ስለሚደሰትበት መንገድ ቅድመ-ሁኔታ አታውጡለት። ይህ ህዝብ ለአርሰናል አይደለም ማልያ በሬ ቢጥልለትም አሻሮ ከሰራው የውስጡ ብሶት ሊሸሽ ኳስ ስር ተሸሽጎ ውስጡ የሚያመነጭለትን dopamine ያጣጥምበት በህይወቱ ሲያማርር፥ ኑሮ ከተባለ የማይገፋ ቋጥኝ ጋር ጡጫ ሲጋጠም፥ የቀለብና የቤት ኪራዩን ሊያገኝ ሲንደፋደፍ ምን አግዘኸዋል?ለየትኛው ብሶቱ ለማንኛው ጭንቀቱ መፍትሄ ዘይደህለት ነው ዛሬ በፌሽታው ቀን የደስታው ኬላ የምትሆንበት? እርሙን መደሰቻ አጥቶ በግራ የማይገታ የኑሮ ሰበዝ፥ በቀኝ የተተበተበ የዘረኝነት ትብታብ፥ ከፊቱ ድንግርግሩ የወጣ መፃኢ ተስፋ፥ ከኋላው ያልተቋጨ ሃገራዊ ስንክሳር እያግተለተለ በመሆንና ባለመሆን ለሚዋዥቅ ለዚህ ምስኪን ህዝብ ለምን ለደስታው ደረሰኝ ካልቆረጥኩልህ ትላለህ??? አርሰናልን ደገፈ ማለት ለተፈናቀሉ ወገኖቹ ስሜት አልባ ነው ማለት ይሆን እንዴ? በዋንጫው ስኬት አቅሉን እስኪስት አበደ ማለት ለሃገሩ ስሜት አልባና ባንዳ ትውልድ ተፈጠረ ማለትስ ነው? አርሰናል ዋንጫ በልቷል አንተስ ቁርስህን በላህ?🙄🙄🙄 ላም ጥያቄ😏😏😏 ህይወት እስከ ምግብ መኖር እስከ እህል ድረስ ብቻ የሚመስላቸው አጋሰሶች ሃሳብ ነው። ይሄ ህዝብ ደስታውን በዊድም ባገኘ🤲🤲🤲 በመከራው መመከሩ ሳያንስ፥ በስቃዩ መሳቀቁ ሳይጎድለው፥ በችጋር መከትከቱ፥ በአሳር መንከራተቱ ዕጣፈንታው እኮ አይደለም። በቃ ኢትዮጵያዊ by hook or by crook ይሳቅልኝ ከጋራ ድል ይልቅ ለጋራ ሀዘን የታጨ፥ ከጋራ ስኬት ይልቅ ለወል ውድቀት ተላልፎ የተሰጠ ህዝቤ ለሳቅና ፌሽታው አርሰናል ምክንያት ከሆነ ከ"ያርግለት" በቀር ምንስ ሊባል🙏🙏🙏 አጉል ጥራዝ አትንጠቁ፥ ከልክ በላይ አትወቁ፥ ጦርነቱን ያልጀመረ ህዝብ የውጭ ኳስ ላይ ለምን ፈነጠዘ ተብሎ ሙሾ አይደረደርለትም። የኑሮ ውድነቱን የፈጠረው በኢትዮጵያ የሚገኝ የአርሰናል ደጋፊ ይመስል በሰው ደስታ ተዝካር አትፍጠሩ። አርሰናልን ስንከተል ያለፍነውን ስርጓጉጥ፥ የተሻገርነውን የሰቀቀን ድልድይ፥ የተጫነብንን ቋጥኝ፥ የተፎገርነውን ፉገራ እኛው ባለቤቶቹ በዘመናት ቁጥር ስር የሆንነውን ስለምናውቅ የሆንነው ላይ ያልነበራችሁ የደስታችን ትራፊኮች ተዉን እንለፍበት🤲🤲🤲 የሰው ልጅ passion የሚባል ነገር አለው የኔ passion ኳስ መመልከት ነው ያንተን passion የመተቸት መብት የለኝም፤ እኔ የሚመቸኝ የግድ እንዲመችህ አላስገድድህም። ብዙ የተባልንበት፥ ልጅነቴን የተዋደቅኩለት፥ ከእኩዮቼ የተሟገትኩለት፥ እራቴን ያልበላሁለት፥ ጅማቴ እስኪገተር የጮህኩለት የኔው አርሰናል ዋንጫውን በክብር አንስቷል የፈረንጅ ሃገር ኳስ፥ ነጫጭባ ለሚራገጠው፥ አርሰናል ቁርስ አይገዛልህም ጂኒ ጃንካችሁን ተዉትና ሰዉን ለምርጫው ተዉት። የውጭ ሙዚቃን ሆነ ፊልም ስታሳድዱ ልክ የውጭ ኳስ ስንደግፍ ስህተት🤣🤣🤣🤣 ሄችሄችሄችሄች "ለመደሰት ምክንያት ባይኖረን እንኳን ሰበብ እየፈጠርን እንደሰትበት" ፍሊስ...ፍሊስ🤲🤲
ትዳርን የምገድሉ 18 ነገሮችን እኔሆ 1. ስንፍና ትዳርን ያፈርሳል። 2. ጥርጣሬ ትዳርን ያፈርሳል። 3. እምነት ማጣት ትዳርን ያፈርሳል። 4. እርስ በርስ አለመከባበር ትዳርን ያፈርሳል። 5. ይቅር አለማለት፣ ቂም፣ ጥላቻ፣ ክፋትና ቁጣ ትዳርን ያፈርሳሉ። 6.አላስፈላጊ ክርክር ትዳርን ያፈርሳል። 7. ከትዳር አጋርህ ምስጢር መደበቅ ትዳርን ያፈርሳል። 8. ማንኛውም ዓይነት ክህደት (በገንዘብ፣ በስሜት፣ በሥነ-ልቦና ወይም በሌላ) ትዳርን ያፈርሳል። 9. ውሸት ትዳርን በቀላሉ ያፈርሳል፤ በሁሉም ነገር ለትዳር አጋርህ ቅን ሁን። 10. ከትዳር አጋርህ ይልቅ ከወላጆችህ/ቤተሰብህ ጋር ብዙ መቀራረብ ትዳርን ያፈርሳል። 11. የግብረ ሥጋ ግንኙነት እጥረት፣ ወይም አለመደሰት ትዳርን ያፈርሳል። 12. ብዙ እና ጥንቃቄ የሌለው ንግግር ትዳርን ያፈርሳል። 13. ከትዳር አጋርህ ጋር ትንሽ ጊዜ ማሳለፍ ትዳርን ያፈርሳል። 14. ገንዘብ፣ ያለ እቅድ ግዢና የገንዘብ ዲሲፕሊን ማጣት ትዳርን ያፈርሳል። 15. የትዳር አጋርህን ድክመት ለወላጆች ወይም ለእህት ወንድሞች ማጋለጥ ትዳርን ያፈርሳል። 16. በመንፈሳዊ ሕይወት ጽኑ አለመሆንና አብሮ አለመጸለይ ትዳርን ብቻ ሳይሆን ሕይወትንም ይጎዳል። 17. ማማረር ፣ ተግሣጽና እና እርማት አለመቀበል ትዳርን ያፈርሳል። 18. የእግዚአብሔርን ቃል አለማወቅና አለመታዘዝ ትዳርን ያፈርሳል።
видео или голосовое, без подписи
ጧት ------ ራሱን ጎዝጉዞ ራሱን አንጥፎ ራሱ ላይ አድሮ ሰው በጧት ይነቃል ተስፋና ብልቱን አንድ ላይ ገትሮ ----------- የመፀሀፍ ርዕስ: የቀንድ አውጣ ኑሮ! ይስማዕከ ወርቁ