- Последний пост
- 5 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 25
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 529
- 1/48двое суток
- 606
- 1/72трое суток
- 653
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
Summer Tutorial
ለትምህርት ቤታችን አዲስ ገቢና ነባር ተማሪዎች በሙሉ የ2019ዓ.ም ትምህርት ዘመን ምዝገባ ከነሀሴ 1/2018ዓ.ም ሰለሚጀመር ከወዲሁ አፈላጊውን zegjit እንድታደረጉ እያሳሰብን በተባለው መሰረት ካድ ተሰርቶ ስላለቀ ነገ መወሰድ የምትችሉ ሲሆን ለመውሰድ ስትመጡ ክሊራን ይዛችሁ መምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡
ለት/ቤታችን ተማሪዎች በሙሉ ካርድ ሐሙስ ማለትም በ23/11/18ዓ.ም እንድትወስዱ መልዕት ቢተላለፍም ብዙ ተማሪዎች በተለያየ ምክንያት ኢንኮምፕሊት እንዲሁም ያልተሞላ ውጤት በማጣራት ላይ የቆየን ሲሆን ካርድ በኦንላይን የተሰራና ወደ ወረቀት ፕሪንት አድረጎ ለመጨረስ የተወሰነ ጊዜ ይፈልጋል ስለሆነም ነገ የተባለው ቀን በ30/11/18ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 መጥታችሁ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ለተፈጠረው ቀን መቀየርና ለአንዳንድ ጉዳዮች ይቅርታ እየጠየቅን ተማሪዎች ካርድ ለመውሰድ መጥተው እንዳይለፍ መረጃውን እንድታደርሱ ይሁን፡፡ ት/ቤቱ
без подписи
без подписи
ማስታወቂያ ለት/ቤታችን ከ10ኛ ወደ 11 እንዲሁም ከ11ኛ ወደ 12ኛ ክፍል በጥሩ ውጤት ላለፋችሁ ተማሪዎች በሙሉ ት/ቤቱ ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት ስላዘጋጀ ተማሪዎች መጥታችሁ እንድትማሩ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
ሰበር ዜና ከቀለም ሜዳ ቴክኖሎጂስ! ሐምሌ 18/2018 ዓ.ም. የሲዳማ ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም. የ8ኛ ክልልአቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ ! በቀለም ሜዳ ቴክኖሎጂስ የበለጸገው ዘርፈ ብዙ የፈተና እርማት እና ማስተዳደሪያ ሲስተም (EMaCS Ministry) በመጠቀም ከተማሪዎች ምዝገባ እስከ ውጤት መግለጫ ሰርቲፊኬት ዝግጅት ድረስ ያለው ሂደት በዚሁ ዘመናዊ የዲጂታል አገልግሎት እየተከናወነ ይገኛል። ስለሆነም ተፈታኝ ተማሪዎች በኮምፒውተር ወይም በስልካቸው የድር መፈለጊያ (Web browser) በመጠቀም፡- 👉 ለ8ኛ ክፍል https://sidama.ministry.et/#/result የሚለውን አድራሻ በመክፈት፣ 👉 ፊት ለፊት በሚታየው ቅጽ (form) ላይ የተማሪውን መለያ ቁጥር (Registration Number) እና የመጀመሪያ ስም በማስገባት “ውጤት ይመልከቱ (Check Your Result)” የሚለውን ቁልፍ በመጫን ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ። በቴሌግራም ቦት አማካኝነት በቀላሉ ለማየት የሚከተሉትን ሂደቶችን ይከተሉ፦ 👉ወደ @MinistryResultQMTBOT በመሄድ ቦቱን ያስጀምሩ። 👉ቦቱን ከከፈቱ በኋላ /start የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ። 👉ክፍልዎን ይምረጡ፡ የሚሰጡትን አማራጮች በመጠቀም “Grade 8” የሚለውን ይምረጡ። 👉የሰባት ዲጂት (7-digit) የምዝገባ ቁጥርዎን ያስገቡ። 👉የመጀመሪያ ስምን (First Name) በትክክል በመጻፍ ውጤታሁን ማየት ትችላላችሁ። 🎯 ማስታወሻ፡ በቅድሚያ ቪፒኤን (VPN) ማጥፋት ይኖርባችኋል። Telegram: https://t.me/qelemmedatechnologies LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/78350212/admin/notifications/all/ YouTube: youtube.com/@qelemmedatechnologies 🌐 www.qelemmeda.com 📨 qelemmeda@gmail.com
ማስታወቂያ ሰላም ለሁላችሁ ይሁን። በትምህርት ቤታችን የንብረት ቆጠራ (Inventory) ሥራ ስለተጀመረ፣ በእጃችሁ ያለ ማንኛውም የትምህርት ቤቱ ንብረት በኢንቨንተሪ መመዝገብ ስለሚያስፈልግ፣ እስከ ነገ 15/11/2018 ዓ.ም. ብቻ ለንብረት ክፍል ገቢ በማድረግ ክሊራንስዎን እንድትወስዱ በአክብሮት እናሳስባለን። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ክሊራንስ ያልወሰዱ ሠራተኞች የሐምሌ ወር ደመወዛቸው ሊታገድ እንደሚችል ከወዲሁ እናሳውቃለን። እባካችሁ ቀነ-ገደቡን በማክበር አስፈላጊውን ሂደት በወቅቱ ያጠናቅቁ። ት/ቤቱ አስተዳደር
ማስታወቂያ ለትምህርት ቤታችን ከRound 1 እስከ Round 5 ድረስ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማትሪክ ፈተናን የወሰዳችሁ ውድ ተማሪዎቻችን፣ ፈተናችሁን በሰላም፣ ያለ ምንም እንከን በማጠናቀቃችሁ ከልብ እጅግ ደስ ብሎናል። በፈተና ወቅት ያሳያችሁትን ትዕግሥት፣ ጥረት፣ ሥነ-ምግባር እና ትጋት እናደንቃለን። እንኳን ደስ አላችሁ! የደከማችሁበትን ፍሬ በሚያስደስት ውጤት እንድታገኙ ከልብ እንመኛለን። ውጤታችሁ ለእናንተ፣ ለቤተሰቦቻችሁ፣ ለትምህርት ቤታችን እና ለአገራችን የደስታ ምንጭ እንዲሆን እንጸልያለን። ከፈተናው በኋላ የሚኖራችሁን የዕረፍት ጊዜ በጤና፣ በደስታ እና በጥንቃቄ እንድታሳልፉ እንመኛለን። መልካም ውጤት! መልካም ዕረፍት! መልካም ቀጣይ የትምህርት ጉዞ! የትምህርት ቤታችሁ አስተዳደር
ማስታወቂያ ለRound 5 የ12ኛ ክፍል ማትሪክ ተፈታኞች በሙሉ፦ ነገ በቀን 13/11/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ልክ 12፡00 ሰዓት በቱላ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግቢ በመገኘት በተዘጋጀው መርሃ ግብር መሠረት ወደ ፈተና መዕከላችሁ እንድትሄዱ ትምህርት ቤቱ ያሳውቃል። ማሳሰቢያ: ሁሉም ተፈታኞች በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በወቅቱ በመገኘት አስፈላጊ የፈተና ሰነዶቻችሁን ይዛችሁ እንድትቀርቡ በጥብቅ ይጠየቃል። ትምህርት ቤቱ
ማስታወቂያ ከዚህ በታች በስም ዝርዝር የተጠቀሳችሁ የትምህርት ቤታችን መምህራን ለ2018 ዓ.ም የክረምት ቱቶሪያል ትምህርት እንድታስተምሩ የተመደባችሁ በመሆኑ፣ ነገ በ13/11/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ልክ 2፡00 ሰዓት ለትምህርት ቤቱ በመቅረብ ሪፖርት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን። የተመደቡ መምህራን መ/ር አቦነህ አበራ መ/ር ዳንኤል ሀ/መስቀል መ/ር ዳንኤል ፈንዳሞ መ/ር አለማየሁ ናና መ/ር ታጠቅ ተሾመ መ/ር አክልሉ ቡንጌ መ/ር መሠረት ዬኔነህ ማሳሰቢያ: ሁሉም የተመደቡ መምህራን በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በወቅቱ ተገኝተው ሪፖርት እንዲያደርጉ ይጠየቃሉ። ትምህርት ቤቱ
ማስታወቂያ ለትምህርት ቤታችን በ2018 ዓ.ም ከ11ኛ ክፍል ወደ 12ኛ ክፍል ላለፋችሁ ተማሪዎች በሙሉ፦ ትምህርት ቤታችን ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የቱቶሪያል ትምህርት አዘጋጅቷል። በመሆኑም ከነገ ጀምሮ ማለትም 13/11/2018 ዓ.ም በተያዘላችሁ መርሃ ግብር መሠረት በሰዓታችሁ በመገኘት ትምህርቱን በመደበኛነት እንድትከታተሉ ትምህርት ቤቱ በጥብቅ ያሳስባል። ማሳሰቢያ: የቱቶሪያል ትምህርቱ ለ2019ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ትምህርትና ለብሔራዊ ፈተና ዝግጅት ከፍተኛ ጠቀሜታ ስላለው ሁሉም ተማሪዎች ያለምንም መቅረት እንዲገኙ ይጠበቃል። ትምህርት ቤቱ
ማስታወቂያ ለትምህርት ቤታችን መምህራን በሙሉ በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ሰምስተር ውጤት በተለያዩ ምክንያቶች Incomplete ሆኖ የቀረ የተማሪዎች ውጤት በ11/11/2018 ዓ.ም ብቻ የሚስተካከል መሆኑን እናሳስባለን። ስለሆነም፦ በተማሪዎች እጅ ያለውን ሪፖርት እና የማርክ ሊስት በጥንቃቄ በማመሳከር የIncomplete ውጤቶችን በዕለቱ እንዲያስተካክሉ። ተማሪዎች ያልወሰዱት ፈተና ካለ፣ ዳግም (ተለዋጭ) ፈተና እንደሚሰጣቸው በማወቅ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ። ከ11/11/2018 ዓ.ም በኋላ የIncomplete ውጤት ማስተካከል ስለማይቻል፣ ሁሉም መምህራን ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በተቀመጠው ቀን ውስጥ ማጠናቀቃቸውን ትምህርት ቤቱ በጥብቅ ያሳስባል።
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи