WCU DISCIPLESHIP
Статистикаደቀ መዛሙርት ህብረት 📚 -ወንጌልን መመስከር -በቃሉ እውቀት ማደግ -ሕይወትን ሚቀይር ህብረት -ጤናማ አምልኮ ትክክለኛ ደቀ መዝሙር እውነተኛውን እየሱስን አውቆ የሚከተልና ሌሎች ክርስቶስን ተከታዮችን የሚያፈራ ነው። “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው.." ማቴ 28:19
- Последний пост
- 28 июл.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 27
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Образование (по похожим)
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 350
- 1/48двое суток
- 401
- 1/72трое суток
- 432
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ |Sola scriptura| ክፍል አምስት ቀኖና እና አዋልድ መጻሕፍት (አፖክሪፋ) ቀኖና “ቀኖና” የሚለው ቃል “ሕግ” ወይም “መመዘኛ፥ መለኪያ” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን፣ ይህም ለእምነትና ለሕይወት መለኪያ ወይም መስፈርት መሆኑን ያሳያል። አንድ መጽሐፍ ቀኖናዊ ለመባል ከሚያስፈለጉት መስፈርቶች መካከል ጽሑፉ በነቢይ፣ በሐዋርያ ወይም ከሁለቱ በአንዱ የቅርብ ባልደረባ የተጻፈ መሆን አለበት። ስለ ቀኖና ሊታወስ የሚገባው በጣም አስፈላጊው ነጥብ፦ መጻሕፍት ቀኖና አካል ተደርገው የታወቁት በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ስለተጻፉ(የእግዚአብሔር ቃል ስለሆኑ) እንጂ፣ ቀኖና አካል ስለተደረጉ የእግዚአብሔር ቃል አልሆኑም። ማለትም ቤተ ክርስቲያን ቀኖናውን እራሷ አልፈጠረችውም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት አስቀድሞ የጻፋቸውን መጻሕፍት ለይታ አወቀች (ተቀበለች) እንጂ። ቀኖናው ለክርስቲያናዊ ትምህርትና ለሕይወት ሙሉ እና የመጨረሻው ባለሥልጣን ሆኖ ያገለግላል። ሉቃስ 24:44፤ 2 ጢሞቴዎስ 3:16–17፤ ይሁዳ 3። የብሉይ ኪዳን ቀኖና የብሉይ ኪዳን ቀኖና በዕዝራ (5ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ዓ)፣ በዮሴፍስ (95 ዓ.ም)፣ በ2ኛ ዕዝራ 14 (100 ዓ.ም) እና ጃምንያ (ያምንያ) ጉባኤ (70-100 ዓ.ም) ጸድቋል። ኢየሱስም በሉቃስ 11:51 ላይ “ከአቤል ደም ጀምሮ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ” ስላለ የአይሁድን መጻሕፍት ወሰን አረጋግጧል። የአቤል ግድያ በዘፍጥረት የተመዘገበ ሲሆን፣ የዘካርያስ ግድያ ደግሞ በአይሁድ የመጻሕፍት አደረጃጀት መሠረት የመጨረሻው መጽሐፍ በሆነው በ2ኛ ዜና መዋዕል 24:20 ላይ ይገኛል። ስለዚህ ይህ የኢየሱስ አገላለጽ ለእኛ “ከዘፍጥረት እስከ ሚልክያስ” እንደማለት ነው። የፕሮቴስታንት ብሉይ ኪዳን በይዘቱ የዕብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስን የሚከተል ቢሆንም፣ የመጻሕፍቱ ቅደም ተከተል ግን ይለያያል። የሐዲስ ኪዳን ቀኖና የሐዲስ ኪዳን ቀኖና በሐዋርያት ወይም በቅርብ ባልደረቦቻቸው አማካኝነት ከ45 ዓ.ም እስከ 95 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ የተጻፉ 27 መጻሕፍትን ይዟል። የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን እነዚህን መጻሕፍት የተቀበለቻቸው ሐዋርያዊ መነሻ ያላቸው፣ በውስጣቸው ባለው ትምህርት የታመኑ፣ በምዕመናን ዘንድ በሰፊው ተቀባይነት ያገኙ እና የመንፈስ ቅዱስን ሥራ በግልጽ ያሳዩ ስለነበሩ ነው። የቤተ ክርስቲያን ጉባኤዎች ለእነዚህ መጻሕፍት ሥልጣንን አልሰጧቸውም፤ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ቃል አስቀድሞ የነበራቸውን መለኮታዊ ሥልጣን በይፋ እውቅና ሰጡ እንጂ። አዋልድ መጻሕፍት (አፖክሪፋ) አፖክሪፋ (Apocrypha) ከ300 እስከ 100 ዓ.ዓ ባለው ጊዜ ውስጥ ለተጻፉ 15 “የተሰወሩ” መጻሕፍት የተሰጠ ስም ነው። የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እ.ኤ.አ በ1546 ከተካሄደው የትሬንት ጉባኤ (Council of Trent) ጀምሮ ከእነዚህ ውስጥ 11ዱን እንደ ቅዱሳት መጽሓፍት አካል አድርጋ ትቀበላለች (ከ1ኛ እና 2ኛ ዕዝራ እንዲሁም ከምናሴ ጸሎት በስተቀር)። መጻሕፍቱ እራሳቸው በመለኮታዊ መንፈስ መመራታቸውን አይናገሩም፣ እንዲሁም ምንም ዓይነት ትንቢት አልያዙም፤ በዚህም ምክንያት በሐዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች ዘንድ ተቀባይነት አላገኙም (ምንም እንኳ ይሁዳ 14 እና ዕብራውያን 11:35 በተዘዋዋሪ ቢጠቅሷቸውም)። መጻሕፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የብሉይ ኪዳን አካል ሆነው የታዩት በሰባ ሊቃናት ትርጉም (ሴፕቱአጀንት - 3ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ዓ) ላይ ቢሆንም፣ ከ700 ዓመታት በኋላ በጄሮም ቩልጌት (Vulgate) ትርጉም ላይ እስኪካተቱ ድረስ በማንኛውም የቀኖና ዝርዝር ውስጥ አልታዩም ነበር። ጄሮም (340-420 ዓ.ም) እነዚህን መጻሕፍት ከ“ቀኖናዊ” ይልቅ እንደ “የቤተ ክርስቲያን ንባብ” (ecclesiastical) መጻሕፍት አድርጎ ፈርጇቸዋል። @wcudisciple
"መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ" |Sola scriptura | ክፍል አራት 2ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ፪:፲፭ --- ፲፭፤ እንግዲያስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፥ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ። ሁሉም “ትውፊቶች” እኩል ሚዛን የላቸውም። ጳውሎስ ራሱ ልክነት የጎደላቸውን ትውፊቶችን አውግዟል (ለምሳሌ የእግዚአብሔርን ቃል የሚያፈርሱ የሰዎችን ትእዛዛት፤ ቈላ 2፡8)። የአዲስ ኪዳን ትውፊት በሐዋርያዊ መመሪያ (ደንብ) መፈተን እንዳለበት ያመለክታል። ትውፊቱ እውነተኛና ጠቃሚ የሚሆነው ሐዋርያዊውን ቃል ሲያንጸባርቅና ሲያስተላልፍ ነው፤ ነገር ግን ልክነቱን መዛኝ የመጨረሻው ፈራጅና ወሳኙ ሥልጣን ቅዱሳት መጻሕፍት ብቻ ናቸው። ሌላው ደግሞ፣ አንድ ትውፊት ሊጠበቅ (ሊያዝ) የሚገባው መሆን አለመሆኑን ሙሉ በሙሉ የሚወሰነው በዚያ ትውፊት የየራሱ ባሕርይ ላይ ነው። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እርስ በርሳቸው የሚቃረኑ ትውፊቶች አብረው ሊጠበቁ አይችሉም፤ ስለዚህም ከተጻፈው ትውፊት (ማለትም ከቅዱሳት መጻሕፍት) ጋር የማይስማማ “በቃል የሚተላለፍ” ማናቸውም ትውፊት የተኮነነ (የተወገዘ) ይሆናል። የአንድነት ጉዳይ በካቶሊኮችም ሆነ በኦርቶዶክሶች የሚታመነው እሳቤ የፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶች መከፋፈልና አንድነት ማጣት (denominational variation) ምክንያቱ ይሄው "የመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ" ትምህርት ነው ብለው ይከሱናል። ይህ ክስ እነርሱንም መልሶ የሚነካ ክስ ቢሆንም ቅሉ። እዚህ ላይ ሁለት ነጥቦችን ላንሳ አንደኛ ተሓድሶን የአንድ ሰው (ሉተር) እንቅስቃሴ ብቻ ሳይሆን ይልቁንም በሉተር የተጀመረው ሉተራዊነት፤ በጆን ካልቪን ሲመራ የነበረው ካልቪናዊነት ፤ በዝዊንግሊ የሚመራው የዳግም መጥመቂያዊያን እንቅስቃሴ ፤ በእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን የተነሳው ተሓድሶ ማለትም አንግሊካን እንዲሁም በራሷ በካቶሊክ የተደረገው ተሓድሶም ይጠቀሳል። ገና ከጅምሩም በፕሮቴስታንት ሓዳሲያን ዘንድ በአንዳንድ ጉዳዮች የተለያየ አመለካከት ነበራቸው በሚበዙት ብስማሙም። አንድ የሚያደርጋቸውም የሮማ ካቶሊክ ስሁት ልምምድን በአንድነት መቃወማቸው ነበር። ሁለተኛ የአንድነታችን/የህብረታችን መሰረት እውነት መሆን አለበት። የክርስቶስ ቤተክርስትያን እውነትን ለዓለም እንዲትገልጥ ብርሃን የሆነች እንጂ ከሀሰት ጋር የምትስማማ አይደለችም። እውነት ላይ በተመሰረተ ህብረት የጌታ በረከት አለ። እውነት ተረግጦ አንድነት ገዳይ ነው። ይቀጥላል... @wcudisciple
"መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ" |Sola scriptura | ክፍል ሦስት ይህ የሓዳሲያን መፈክር ከመጽሐፍ ቅዱስ ስሙም መሆኑን (መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረቱን) እንቃኝ። አስቀድመን ከሁሉም ይልቅ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የቅዱሳት መጻሕፍት አጠቃቀም ትኩረት ሰጥተን ካጠናን ይህንኑ የመጽሐፍ ቅዱስን የበላይነት የምያስጠብቅ ትምህርት እናገኛለን። ጌታችን በስጋ ከአብርሃም ቤት ስለሆነ በዘመኑም ይህን የአይሁዶችን መጽሐፍ (ብሉይ ኪዳንን) ጠቅሶ ስያስተር ይስተዋላል። እንደ ምሳሌም ጌታችን በምድረ በዳ ከፈታኙ የቀረበለትን ፈተና "ተብሎ ተጽፏል" በማለት ስመልስ በእርግጥም ከሚሰማን ስሜትና ግላዊ አመክንዮ ይልቅ ለእግዚአብሔር ቃል ስፍራ መስጠቱ የመጽሐፍ ቅዱስ የበላይነትን አጉልቶ ያሳያል። ይበልጥ ቀረብ ስንል ደግሞ በጌታችን በምድር ቆይታው ወራት ከቅዱሳት መጻሕፍት ይልቅ ለሽማግሌዎች ወግና ትውፊት የላቀ ስፍራ የሰጡትን የእግዚአብሔርን ቃል የናቁትን ፈሪሳዊያንን እንዲህ ሲል ይወቅሳችኋል:- የማርቆስ ወንጌል 7:8-13 8፤ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ ጽዋን ማድጋንም እንደ ማጠብ የሰውን ወግ ትጠብቃላችሁ፥ ይህንም የመሰለ ብዙ ሌላ ነገር ታደርጋላችሁ። 9፤ እንዲህም አላቸው፦ ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እጅግ ንቃችኋል።... 13፤ ባስተላለፋችሁትም ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፤ እንደዚሁም ይህን የሚመስል ብዙ ነገር ታደርጋላችሁ። ኢየሱስም ሆነ ሐዋሪያት ትምህርታቸውን ለመጽሐፉ ማህበረሰብ(ለአይሁዶች) ለማስረዳትና እውነትነቱን ለማረጋገጥ ከሕግ፥ ከነቢያትና ከመዝሙራት ያጣቅሱ ነበር። ማቴ 2፡17,18 የሐዋ 2፡16 ሮሜ 3፡10 እንደ ምሳሌ መጥቀስ እንችላለን። ሌላው ሐዋሪያትም በዘመናቸው በጎውን ክርስቲያናዊ ወግ እንድንይዝ ብያስተምሩንም ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ስሙም ያለሆኑትን በአደባባይ እንድንቃወማቸው መክረውናል አስጠንቅቀውናል። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2፡8 "፤ እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ።" ወደ ቲቶ 1:13 ፤ ይህ ምስክር እውነተኛ ነው። ስለዚህ ምክንያት የአይሁድን ተረትና ከእውነት ፈቀቅ የሚሉትን ሰዎች ትእዛዝ ሳያዳምጡ፥ በሃይማኖት ጤናሞች እንዲሆኑ በብርቱ ውቀሳቸው። ይልቁንም ለቃሉ እውነት እጅጉን እንድንጠነቀቅና እንድንጠብቀው ይመክሩናል። 2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1:19 (NASV) ¹⁹ እንግዲያስ ትንቢታዊው ቃል ይበልጥ ተረጋግጦልናል፤ ሌሊቱ እስኪነጋና የንጋት ኮከብ በልባችሁ እስኪበራ ድረስ፣ በጨለማ ስፍራ ለሚበራ መብራት ጥንቃቄ እንደሚደረግ እናንተም ለዚህ ቃል ብትጠነቀቁ መልካም ታደርጋላችሁ። ይቀጥላል... @wcudisciple
"መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ" |Sola scriptura | ክፍል ሁለት 'መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ' ስንል ምን ማለታችን ነው? ምንስ ማለታችን አይደለም? እዚ'ጋ መሰመር ያለበት እውነት ትልቁ ጥያቄ 'ማን ይገዛናል?' ሳይሆን 'ማን የሁሉ በላይ ገዥ ነው?' የሚል ነው። በጣም ግልጥ ስናደርገው ከመጽሐፉና ከትውፊቱ/ጳጳሱ/ቤተክርስቲያን አስተዳደር/በኋላው ዘመን ከተነሱት ቅዱሳን ሀሳብያን፥ ማን የሁሉ በላይ ገዥ ነው? የሀሳብ ልዩነት ከተገኘ በሁለት እኩል ባለሥልጣናት መመራት ስለማይቻለን ። ተቃርኖ ብገኝባቸው የቱ ልታመን ይገባዋል የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀሬ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ስንል የቤተክርስቲያን ትውፊት፥ ጉባኤያት፥ የቤተክርስቲያን ስልጣን አለመቀበል፥ የተሳሳቱ ግላዊ ፍታቴን እያበረታታን ሳይሆን ነገር ግን እነዚህ ልሳሳቱ የሚችሉ ሲሆን ሁሉም በመጽሐፍ ቅዱስ መመዘን አለባቸው እያልን ነው። እንዲሁም ለስልጣኑም መገዛት አለባቸው የሚል ይሆናል። “መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ” ተሐድሶ አድራጊዎቹ፣ ከጳጳሱ የማይሳሳት ነው ከሚለው የይገባኛል ጥያቄ እና በቤተ ክርስቲያን አባቶች ጽሑፎች እንዲሁም በቃል በሚተላለፉ ትውፊቶች ውስጥ ከሚገኘው የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ሥልጣን የመጽሐፍ ቅዱስን ሥልጣን መለየታቸውን አመላካች ነበር። ቃሉም ከራሱ ከእግዚአብሔር የሚመነጭ በመሆኑ፣ ሊፈርድበት የሚችል ከእርሱ በላይ የሆነ ምንም ዓይነት ሥልጣን ወይም ሊገዛለት የሚገባው መመዘኛ የለም! እርሱ ራሱን በራሱ የሚያረጋግጥ፣የመዳን እውነትና ዕውቀት የሞላበትና ፍጹም ስህተት አልባ ነው። ሌሎቹ መመዘኛዎች ወይም ሥልጣናት ሁሉ ከቅዱሳት መጻሕፍት አንጻር ሲታዩ አንጻራዊ ናቸው (መዝ. 138:2፤ ኢሳ. 46:9-11፤ ማቴ. 24:35፤ ዕብ. 1:1-3)። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3:16 ¹⁶ የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል። ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ ቅዱሳት መጻሕፍት በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡት እንደሚችሉ ያስታውሰዋል (3:15)። እርሱም ቅዱሳት መጻሕፍት ለትምህርት፣ ለተግሣጽ (ለመውቀስ)፣ ልብን ለማቅናትና በጽድቅም ለመኮትኮት (ለመምከር) ጠቃሚ እንደሆኑ ያስተምራል (3:16)። ቅዱሳት መጻሕፍት ይህ ባሕርይ ስላላቸው፣ የእግዚአብሔር ሰው ለበጎ ሥራ ሁሉ ፍጹም ሆኖ እንዲዘጋጅ ያደርጉታል (3:17)። ለዚህ ተግባር በቂም ብቁም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በርሱ የሚስማማና የማይቃረን ነው። እርሱ የእግዚአብሔርን የእውነት ዕውቀት፣ ባሕርይና ማንነት ያንጸባርቃል። መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር መንፈስ የተነፈሰበት(inspired) ቃል ስለሆነ፣ ሥልጣን ያለው በመሆኑም የማይሳሳት ነው። ይ🀄ጥላል... @wcudisciple
መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ |Sola scriptura | ክፍል አንድ መግቢያ የሚያምነውን የማያውቅ እመን ባይ በዛ፥ የእውነትና የሀሰት ድንበር ደበዘዘ፥ በየአደባባዩ ጩኸት አዋክቦናል ታዲያ በዚህ በወከባው ዘመን ምን እንመን!? ማንንስ እንመን!? የዘመኑ ንፋስ ስለነካካን ህይወታችን(አኗኗራችን) በየጊዜው ይለዋወጣል፤ እውነተኛ ጽኑ መልክ አጥቶ መለዋወጥ መገለጫው በሆነ ትውልድ መካከል እንዴት እንኑር!? ተግባራዊ ምላሽ የሚሹ የክርስትያን ሁሉ ጥያቄ! የእግዚአብሔርን ሀሳብ የሰው ሲውጠው፤ የአምልኮ ስርዓት በሰውኛ እሳቤ ሲገዛ፤ እውነት ስፍራ ሲታጣ ሐሰት ሲነግስ፤ የእውነተኛ አምላክ አገልጋይ ቤተ ክርስቲያን ከእውነት ይልቅ ስህተት ሲሆን መገለጫዋ፤ ብርሃን ሲደበዝዝ፤ ክርስትና ሕይወት አልባ ሙት ሃይማኖት ብቻ ሲሆን፤ ሕዝቤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ደም ያገኘውን 'የኃጢአት ስርየት በኩፖን'(indulgence) ስሸጥ ያለው ለሙቱና ለሕያው ሲሸምት፤ የሌለው በኃጢአት ክስ ኩነኔ ሲዘፈቅ፤ የበላይ ገዦችና ጳጳሳት ሀብት ሲያድግ ድሃው በድህነቱ ሲማቅቅ ማን እኔ አለው ይበል? 'እኔ አልሳሳትም፥ የበላይ ገዥ ነኝ' ሚለውን የሚገዛ ስህተት አልቦ ፍጹም ገዥ ይኖር ይሆን? ለአምልኮ፥ ለአስተምህሮ ክርስትና እንዲሁም ለክልስቲያናዊ አኗኗር ማን የበላይ ገዥ ፥ መንገድ ጠቋሚ ብርሃን ነው? ቤት አስተዳዳሪው(ጳጳሱ፣ ቄሱ፣ ፓስተሩ....) ከተሳሳተ ማን ይሁን ልኩ? ማንስ ይሁን የበላይ ገዥው? ይህ የመካከለኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጥያቄ ነበር። በእርግጥም የክርስትናን እምነትና አኗኗር የሚገዛና የሚመራ የበላይ ስህተት አልባ በራሱ በቂና ብቁ የሆነ ባለሥልጣን አለ! የሚል ነበር የሓዳሲያን አቋምና መፈክር። መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ሙሉ በሙሉ እውነተኛ፣ ባለሥልጣን፣ ግልጽ፣ አስፈላጊ፣ እንዲሁም ለእምነትና ለሕይወት በቂ ነው። ክርስቲያኖች ምን ማመን እንዳለባቸው እና እንዴት መኖር እንዳለባቸው የሚወስነው የእግዚአብሔር የመጨረሻው ባለሥልጣን ቃል ነው (2 ጢሞቴዎስ 3:16–17፤ 2 ጴጥሮስ 1:20–21)። ከሁሉ የበላይ የሆነ ስልጣኑንም በምንነቱ(የእግዚአብሔር ቃል በመሆኑ)፥ ከማይሳሳት አምላክ የመነጨ ስህተት አልባ መጽሐፍ ነው። ሓዳሲያንም ይህን እውነት በማጉላት ሰውኛ ጭማሪዎችን በአደባባይ ተቃወሙ። ከቤተ ክርስቲያን መባረር፥ እንደ መናፍቅ መወገዝ ገፋ ሲል ሌላ ኃይማኖት መመስረት ዓላማቸው አልነበረም። ለእውነት ሲባል የተከፈለ መስዋዕትነት እንጂ። እንደ መፈከር በአደባባይ የተገለጠው "ጽድቅ በእምነት ብቻ" የሚል ቢሆንም ውስጥ ውስጡን ተሃድሶን ሲያጋግል የነበረው " መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ" የሚል ነበር። እንግዲህ እውነት ሲበረዝ አስተምህሮአችንን ሆነ ልምምዳችንን የምንዳኝበት የእውነት መለኪያ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሆነ በሓዳሲያን ዘንድ ይታመናል፥ ይህም እውነት በየዘመኑ የተሃድሶ ምክንያት ሆኖ አለ ይኖራል። ይ🀄ጥላል... @wcudisciple
የጌታ ሰላም እና ፀጋ ይብዛላችሁ ቤተሰብ። በዚህ channel ላይ አገልግሎታችንን እየተካፈላችሁ ስላላችሁ ደግሞም ስለምታበረታቱት እጅግ ደስተኞች ነን። በዚህ ሳምንት አድስ ተከታታይ ፁሁፎችን እናቀርብላቸዋለን። ከዚህ ቀደም "ነገረ ክርስቶስ" በምል ርዕስ አቅርበን ነበር። በዚያውኑ መልክ አሁን "መፅሐፍ ቅዱስ ብቻ" በምል ርዕስ እንማማራለን። ይህንን ማስታወቂያ ለሌሎች በማጋራት አገልግሎታችንን እንድትደግፉን በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን። @wcudisciple
ክርስቶስ ኢየሱስን ማወቅ እግዚአብሔርን ማወቅ ነው። እግዚአብሔርን ማወቅ ደግሞ ለሕይወታችን መሠረታዊና ወሳኝ መሆኑ አይታበልም። “የተሠራነው ለምንድን ነው? እግዚአብሔርን ለማወቅ። በሕይወት ውስጥ ምን ዓላማ ሊኖረን ይገባል? እግዚአብሔርን ማወቅ። ኢየሱስ የሚሰጠን የዘላለም ሕይወት ምንድን ነው? እግዚአብሔርን ማወቅ። በሕይወት ውስጥ ከሁሉ የተሻለው ምርጥ ነገር ምንድን ነው? እግዚአብሔርን ማወቅ። ከሰዎች እግዚአብሔርን የሚያስደስተው የትኛው ነገራቸው ነው? እርሱን ማወቃቸው በዚህ ምድር የምንኖርበት ዐቢይ ምክንያት እግዚአብሔርን ለማወቅ መሆኑን ስናስተውል አብዛኞቹ የሕይወት ችግሮች ቦታ ቦታቸውን ይይዛሉ።እናም እግዚአብሔርን ለማወቅ ካልፈለግን የምንጓዝበትን አቅጣጫም ሆነ የዙሪያ ገባውን ምንነት ሳናይ ዐይናችን ታስሮ በሕይወት ጐዳና ዕውር ድንብራችንን እንተራመሳለን።እግዚአብሔርን ማወቅ ግን ይቻላል፤ የሚታወቀው በክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ነው (ዮሐ 1፥14፥18)። ጳውሎስ ፍቃዱ፣"የእግዚአብሔር ልጅ" @wcudisciple
"ፀጋ ተግሣጽም እንዲሁም አስተምህሮ አዘል ነው። ከኃጢአት እርግማን የሚቤዠን ብቻ ሳይሆን ኃጢአትን እንድንተውም ያሠለጥነናል።" C.Spurgeon @wcudisciple
ሀሳብህ ከሀሳቤ አላማህ ከእቅዴ ህግህ ከመንገዴ ይሁን በዘመኔ🙏 @wcudisciple
ይህም ጸጋ በኀጢአት መኖርንና ዓለማዊ ምኞትን ክደን፣ በአሁኑ ዘመን ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ፣ በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት እንድንኖር ያስተምረናል፤ ቲቶ 2፥12 አንዳንዴ ለሀጥያት እና ለድነት ያለን ምልከታ በእግዚአብሔር ቃል ካልተፈተሸ የክርስትና ኑሮአችንን መቀንጨር ያጠቃዋል። ኃጢአት ከስህተት ወይም ከመጥፎ ልማድ በላይ ነው።ሀጢአት በድርጊት፣በአስተሳሰብ ወይም በባህርይ የሰማዩን ንጉስ ሀሳብ እና ህግ በከፍተኛ ሁኔታ መቃረን እንዲሁም የእግዚአብሔርን ሥልጣን ችላ በማለት መናቅ ነው። ከኃጢአት መዳን ማለት ደግሞ የእግዚአብሔርን ሥልጣን ችላ ብሎ ከመተው ና ከመናቅ መዳን ነው፣የራስን ፈቃድ እና ራስን ደስ የማሰኘት አካሄድን መተው ነው፣መንገዳችንን መተው ነው። ይህም ማለት ለእግዚአብሔር ስልጣን መማረክ ነው፣ ለአገዛዙ እጅ መስጠት እና በሁለንተናችን እንዲሰለጥንብን መፍቀድ ነው ። ይህንን ልያስችለን የእግዚአብሔር ፀጋ ተገልጧል። ማንም የክርስቶስን ሸክም በራሱ ላይ ለመቀበል የማይወድ ፤በ እያንዳንዱ የህይወት ምልልሱ በእውነት እና በሀሴት እግዚአብሔር ደስ ለማሰኘት የማይሻ... ነገር ግን " በክርስቶስ በተጠናቀቀ ስራ ማረፍ ሆኖልኛል" የምል እሱ በሰይጣን ተሸንግሏል። ሀጥያት የመስራታችን tendency በእግዚአብሔር ላይ መተማመናችንን እና በእርሱ ፀጋ መደገፋችንን የሚያፀባርቅ አይደለም። በእርሱ ላይ ያለንን ጠላትነታችንን እና አመፀኝነታችንን እንጂ። እውነተኛ አማኝ የእግዚአብሔርን ፍቅሩን እና ፀጋውን የኃጢአት መፈፀሚያ ፈቃድ(license) አድርጎ አይመለከተውም። ይልቁንም የእግዚአብሔርን ቸርነት እና ይቅርታውን፦ ለመንፈሳዊ እድገት ና የመቀደስ(sanctification) መንገድ አድርጎ ይመለከተዋል። ስለ ታላቅ ፍቅሩ እና ይቅር ለማለት ፈቃደኛ መሆኑን እየተገረመ፣ያለማቋረጥ የተባረከ ተስፋችን የሆነውን ይጠብቃል። ...ይህም የተባረከ ተስፋችን የሆነውን የታላቁን የአምላካችንንና የአዳኛችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ በመጠባበቅ ነው፤ ቲቶ 2፥13 @wcudisciple
🧎➡️እንጸልይ🧎♀➡️ አባት ሆይ፥ ወዳንተ ከሚስቡን ጥያቄዎች በላይ ማንነትህ ይናፍቀናል። ከጠረንህ ርቀን መቆየት አንችልምና የፍቅርህን መአዛ አትሰውርብን!!! በሁኔታዎች ለምትንገዳገደው ነፍሳችን መገኘትህን የብርታታችን ውጤት አድርገን እንድናስብ አትፍቀድልን! የበረታን ጊዜ የምናገኝህ የልፋታችን ውጤት አይደለህምና፥ ስንደክም ልታበረታን ስንበረታም ልትከብርብን በአንተ ዓለም መክረምን አለማምደን። አባት ሆይ በምድር ጥበብ ሰማይ አይደረስምና በላይኛይቱ ጥበብ ሳበን፤ በኃይልና በብርታታችን መራመድ አንችልምና መንፈስህን አብዛልን። መበርታት ባንችል እንኳን መድከምም #አንችልበትምና ለነፍሳችን ቀዳዳ በሌላ የማትተካ ሙላትዋ ሆይ ብቻህን ተገኝልን። አንተን እንደ መንገድ እየተጠቀምን ብዙ መድረሻዎችን አበጅተን ጠፍተናልና፥ አሁን የደረስንባቸውን ስኬቶቻችንና ውድቀቶቻችንን ሁሉ ተጠቅመህ ወደ እውነተኛው ደስታችን ወደ ራስህ አስጠጋን🙌 አሜን!!!
"እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።" የዮሐንስ ወንጌል 13:35 ትልቁን የእግዚአብሔርን ፍቅር የተካፈልን ነንና የፍቅር ዕዳችን ከፍ ያለ ነው። ኀጢአት በውስጣችን በዘራው ከንቱ ዘር ራስ ወዳድነትን አበቀለ። የመሲሁ በመስቀል ላይ ሞቱ ይህን ክፉ ዘር ከልባችን ነቀለ። አሁን ከራስ ያለፈ ለሌሎች የሚቆረስ ሕይወት አለን። መሲሁ በዚህ ምድር ሳለ ለደቀ መዛሙርቱ ተከታዮቹ እንደሆኑ ለዓለም ተለይተው ሚታወቁበትን የደቀ መዛሙርቱን መለዮና ታላቅ ክርስቲያናዊ ዕሴት ገልጦልናል። እርሱም ፍቅር ነው። እርስ በርስ በመዋደዳችን ፍቅር የሆነ አምላክ በምርጦቹ ፍቅር ይደሰታል ይከብራልም። ሆኖም ወደ ፍጽምና አልገባንምና የተዋረደ ስጋችን በቀድሞ ሕይወት ስርዓት መያዙ አይደንቀንም። ፍቅርን አጥቶ በፈራረሰ እንዲሁም ጥላቻን የምንተፍስበት ብኩል አየር በሞላበት ምድር ላይ ራስ ወዳድነት ይነካካናል። በምድር ላይ ለሚሆኑት ነገሮች በሙሉ ከሁለቱ የአንዱ ተጽዕኖ ምክንያት እንሆናለን- ወይ በበጎ አልያም በመጥፎ። ሰዎች ነንና በመካከላችን የሀሳብ ብዝሃነት አለን። ይህን የሀሳብ ልዩነቶች በመካከላችን ጠብን እንዳይጭሩ፤ አለመግባባትም ከተፈጠረ በእግዚአብሔር ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ቃኝተን ሀሳባችንን ለዚህ ለበላይ ገዥ አስገዝተን በፍቅር መኖር የእግዚአብሔር ሀሳብ ነው። ፍቅር ያለ እውነት ፍቅርን አምላኪነት ነው ይህም በእግዚአብሔር ዘንድ ጥዮፍ ነው፤ እውነትም ያለ ፍቅር ኢ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው። አቤቱ ጌታችን ሆይ ፍቅርን አድለን 🤲 @wcudisciple
የክርስቶስ ቃል በሙላት በልባችሁ ይኑር፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤ በመዝሙርና በውዳሴ፥ በመንፈሳዊ ዜማም እግዚአብሔርን ከልብ እያመሰገናችሁ ዘምሩ።በኢየሱስ በኩል እግዚአብሔር አብን እያመሰገናችሁ በቃልም ሆነ በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት፤ በእርሱም እግዚአብሔር አብን አመስግኑ።" ቈላስይስ 3፥16-17 ሰናይ_ሰንበት🙌 @wcudisciple
ዐላፊው ዓለም ሲያበቃ ዐላፊው ዓለም ሲያበቃ፣ የምታቃጥለው ፀሓይ ላትመለስ ጠልቃ፣ ከክርስቶስ ጋር ስንቆም በክብር፣ ያለፈውን የሕይወት ታሪክ በጥንቃቄ ስንዘክር፣ ያኔ ጌታን በሙላት ዐውቀዋለሁ፤ ማክበር እንደሚገባኝም አከብረዋለሁ፡፡ ምድር ዋጪኝ፤ ተራሮች ልትሸሽጉ በላያችን ውደቁ፣ የሚለውን የክፉዎች ጥሪ ስሰማ፤ በአስፈሪ ቊጣው ሲያልቁ፣ ሳያቸው ተጨማትረው ፊታቸው መስሎ ከሰል፣ አስፈሪው የመከራ ጐርፍ በላያቸው ሲከነበል፣ ያኔ ጌታን በሙላት ዐውቀዋለሁ፤ ማክበር እንደሚገባኝም አከብረዋለሁ፡፡ ስቆም በታላቅ ዙፋኑ ፊት፣ የከበረ ልብስ ለብሼ ተጨምሮልኝ ልዩ ውበት፣ እርሱን በታላቅ ግርማው ስመለከተው፣ ኀጢአት በሌለበት ንጹሕ ልብ ስወደው፣ ያኔ ጌታን በሙላት ዐውቀዋለሁ፤ ማክበር እንደሚገባኝም አከብረዋለሁ፡፡ የሰማያትን ምስጋና ስሰማ በሚገባ፣ እንደ ታላቅ ነጐድጓድ ድምፅ በጆሮዬ ሲያስተጋባ፣ እንደ ብዙ ወንዞች ድምፅ ያለማቋረጥ ሲተም፣ እንደ በገና ድምፅ ተቃኝቶ ወደ ሕይወት ሲገባ ሲጥም፤ ያኔ ጌታን በመሙላት ዐውቀዋለሁ፤ ማክበር እንደሚገባኝም አከብረዋለሁ፡፡ ከእኔ መልካምነት የተነሣ ያልተመረጥሁ፣ ከሚመጣው ቊጣ ለማምለጥ የተቀሰቀስሁ፣ መሆኔን ዐውቃለሁ የተሸሸግሁ በመድኀኒቴ ጕያ፤ ቀድሶኝ ያ መንፈሱ ወደር የሌለው አምሳያ፤ ጌታ ሆይ፣ አስተምረኝ በዚህ ምድር ስኖር፣ እንደማከብርህ ለመግለጽ ከልብ በሆነ ፍቅር። ደራሲው:- Robert Murray McCheyne @wcudisciple
የተፈጥሮ ብርሃን በሁሉም ላይ ጌትነትና ሉዓላዊነት ያለው እግዚአብሔር መኖሩን ያሳያል፤ እርሱ መልካም ነው፤ ለሁሉም መልካም ያደርጋል። ስለዚህ ሊፈራ፣ ሊወደድ ፣ ሊመሰገን፣ ሊጠራ፣ ሊታመንና በሙሉ ልብ፣ ነፍስና ኀይል ሊያገለግሉት ይገባል።ነገር ግን እውነተኛው አምላክ የሚመለክበት ተቀባይነት ያለው መንገድ በእርሱ የተደነገገና በተገለጸው በራሱ ፍቃድ የተወሰነ ነው። በሰዎች ግምትና ዘዴ ወይም በሰይጣን ሐሳብ ፣በማንኛውም በሚታይ ወኪል ወይም በመጽሐፍ ቅዱስ ባልተሰጠ በማንኛውም ዐይነት መንገድ ሊመለክ አይገባም። እግዚአብሔር ሙሴን ለእስራኤላውያን እንዲነግር እንዲህ ሲል አዘዘው፥ “እኔ እግዚአብሔር ከሰማይ እንዴት እንደ ተናገርኳችሁ አይታችኋል፤ እኔን ብቻ አምልኩ እንጂ፥ ከብርና ከወርቅ ጣዖቶች ሠርታችሁ አታምልኩ፤" — ዘጸአት 20:22-23 ሰናይ_ሰንበት🙌 @wcudisciple
ይቅርታ በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ ወደ ኢየሱስ ቀርቦ፣ “ጌታ ሆይ፤ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ይቅር ልበለው? እስከ ሰባት ጊዜ ነውን?” አለው። ኢየሱስም “እስከ ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ ብቻ አልልህም” አለው። ማቴዎስ 18፥21-22 በደልን መተው፣ ይቅር ማለት ፦ፍቅር : ትዕግሥት እና ቸርነት የተባሉትን የመንፈስ ፍሬ አጣምሮ ልይዝ የሚችል ፤ጥላቻ ፣ጠብ ፣ ቁጣ እና መለያየት የተባሉትን የሥጋ ሥራ እጅጉ የሚቃረን አማኞች ልኖሩት የታዘዙት ቀንበር መሳይ ልዝቡ የ ክርስቶስ ሸክም ነው። ይቅር ለማለት የሚያስችለውን የእግዚአብሔርን ሀይል የተነፈግን ይመስል ለሥጋ ሥራ ስንሸነፍ ከህብረት ሽሽት ከወንድሞች አንድነት ተነጥሎ መኖር ወይም ደግሞ በደልን ቋጥሮ መያዝ የልብሳችን ያህል ቀሎናል። በክርስትና ጉዞአችን እግዚአብሔርን እራሱን በመገለጡ ማወቅ ፤እሱን በማወቅ እኛነታችንን ከተረዳን የሸክሙን ልዝብነት መገንዘብ አይሳነንም። የእግዚአብሔርን ፍፁም ቅዱስነቱን አይተን የሀጢአታችን ክብደት እና በእኛ ላይ ይወርድ ዘንድ የተገባውን ቅዱሱን ቁጣውን እለት ብናስተውል፤ ደግሞም....ለእንዲህ አይነት መፀኞች የተገለጠውን የእግዚአብሔር ማዳን ተመልክተን የፍቅሩን ታላቅነት ሳንታክት ብናሰላስል ሸክሙን በወደድን ነበር። የመንፈስ ፍሬ እግዚአብሔር ስናውቅ...ደግሞም ለማውቅም በወደድን ቁጥር በመንፈስ ቅዱስ በውስጣችን የሚያድግ ነው ። ይህም ከአማኞች ጋር ለምናደርገው መንፈሳዊ ህብረት ፣የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ እና የሰይጣን ሀሳብ በመካከላችን ስፍራ እንዳይኖረው ለማድረግ እጅግ አስፈላጊ ነው። የበደሉንን ይቅር ማለትም የዚህን ያህል ዋጋ አለው። ✨ይቅርታ ማድረግ አንድም እኛ አመፀኞች እና ኃጢአተኞች በቅዱሱ እግዚአብሔር ይቅር የመባላችን ነፀብራቅ ነው፤ደግሞም በወንድሞች ህብረት የሰይጣን ሀሳብ መግቢያ ቀዳዳ ማሳጫ ልዩ መሳሪያም ጭምር ነው። እናንተ ይቅር የምትሉትን ሰው እኔም ይቅር እለዋለሁ፤ በርግጥ ይቅር የምለው ነገር ካለ፣ በክርስቶስ ፊት ይቅር የምለው ስለ እናንተ ስል ነው። ይህንም የምናደርገው ሰይጣን መግቢያ ቀዳዳ እንዳያገኝ ነው፤ የእርሱን ዕቅድ አንስተውምና። 2 ቆሮንቶስ 2፥10-11 @wcudisciple
የማቴዎስ ወንጌል 5:16 (AMH) •••••••••• ¹⁶ መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ። በክርስትያናዊ ርዕዮተ ዓለም በመልካም ስራ ጽድቅ አይገነባም። የትላንት በደልን ደምስሶ ለዛሬው ህይወት ጽድቅ፤ ለነገውም ደግሞ ዋስትና አይሆንም። በመልካም ስራ ባንድንም ለመልካም ስራ ድነናል። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ማዳን ከኃጢአት ነው እንጂ በኃጢአት አይደለምና። ምንም እንኳ በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት ብንሆንም ከትላንት አሮጌው ፍጥረት የቀረ ልምድና የሕይወት ስርዓት ሙሉ በሙሉ ተላቀን ፍጽምና ላይ አልደረስንም። ግና በውጊያ ሜዳ ውስጥ ነን። መጽሐፍ ቅዱሳችን ድነትን ከመልካም ስራ ጋር አያይዞ ያቀርባል። ይህም ከድነት መነሻነት ጋር አያይዞ ሳይሆን ከእውነተኛ የድነት ማረጋገጫ አድርጎ ያቀርብልናል። ይህም ማለት እውነተኛ ድነት መልካም ስራን እንደ ፍሬ ያመጣል። ፍሬ የምናፈራውም አዲሱ ፍጥረታችን ለዚህ እንዲሆን ተብሎ በክርስቶስ ስለተፈጠረ ነው። ይህን መልካም ስራ ለራስ ሙገሳና ክብር ያዋልነው እንደሆነ መስመር ስቷል ። ታሃድሶም ያሻዋል። ጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተራራው ስብከት ስለ መልካም ስራ ባስተማረበት የመልካም ስራ የመጨረሻ ግቡ የእግዚአብሔር ክብር እንደሆነ ያስተምረናል። እንደ ክርስቲያን ከመልካም ስራችን እንደ ውጤት መጠበቅ ያለብን የሰውን ጭብጨባ፤ የአደባባይ ሙገሳ፤ለsocial media ቀረርቶ ሳይሆን በሰማያት ያለው አባታችን መክበሩ ላይ ነው። "ሙያ በልብ!" አባባል አይደለም መልካም ስራ። መብራት አብርተን ከዕንቅብ በታች ማኖራችን ጥቅም ስለማይኖረው ከአለመብራት አይለየውም። መልካም ስራ በአደባባይ ለሰው ሁሉ ክርስቶስን የሚገልጥ፤ እግዚአብሔርን የሚያከብር ክርስቲያናዊ የህይወት ስርዓት ነው። @wcudisciple
እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፤ ቀርቦም ሳለ ጥሩት። ኢሳይያስ 55፥6 ሰናይ_ሰንበት🙌 @wcudisciple
ሰው ክርስቶስን ካልያዘ፣ ሰማይንና ምድርን ቢያውቅ እንኳ ጥበቡ ሞኝነት ነው። ሰማያዊው የጥበብ መዝገብ ሁሉ በክርስቶስ ውስጥ ይገኛልና። __John Calvin ሰናይ_ሰንበት🙌 @wcudisciple
ት. ኢሳ 44:24 ".... እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሁሉን የፈጠርሁ፥ ሰማያትን ለብቻዬ የዘረጋሁ ምድርንም ያጸናሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ ከእኔ ጋር ማን ነበረ?" ወደ ቆላስይስ 1:15 "...ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤" ት. ኢሳ 44:24 "ሁሉን" የፈጠረው የእስራኤል አምላክ ያህዌህ እግዚአብሔር ከሆነ... ይህን "ሁሉን" የመፍጠር ግብር መጽሐፍ ቅዱስ በቆላስይስ ለክርስቶስ ከተጠቀመው... ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ ፍጡር አይደለም ፈጣሪ ነው። ...እግዚአብሔርና ኢየሱስ አንድ መሆን አለባቸው። አንድ ስንል ምን ማለታችን ነው? " ኢየሱስ እራሱ ብቻውን አብ በፍጥረት፥ ወልድ በቤዝዎት፥ መንፈስ ቅዱስ ሆኖ በአማኝ ውስጥ በዚህ ዘመን ይኖራል" ማለታችን ነው? ዮሐ 17:5 "...አሁንም፥ አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ።" ዓለም ሳይፈጠር በፊት ክርስቶስ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ/ጋር ነበረ። ይህ ደግሞ ኢየሱስ አብ ነው እንዳንል ቀይ መስመር ያሰምርልናል። ታዲያ ሥላሴ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም ማለት እንዴት ይቻለናል? ክብር ከሰው አእምሮ ለሚልቀው ለቅዱስ ሥሉስ አምላክ ይሁን!! @wcudisciple