ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU
Статистикаየ ያሲን ኑሩ ሐዲሶች Yasin Nuru "ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራውን ሰው ያህል አጅር ያገኛል" ረሱል (ﷺ) "የበጎ ስራ ምላሹ በጎ እንጂ ሌላ አይደለም " የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሰራ ሰው ያገኘዋል :>> { አል -ዘልዘለህ 7} UNOFFICIAL ለአስተያየት👇👇 @Hasabbbbot ሀዲሶችን ከፈለጋችሁ👇👇 @yasin_nuru_hadis
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 4
- Всего постов
- 34
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 4 433
- 1/48двое суток
- 5 080
- 1/72трое суток
- 5 479
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ከአሽረፈል ኸልቅ ﷺ አስደናቂ ባህሪያት መካከል "እዝነታቸው" ይገዝፍብኛል ይላል ኡስታዝ በድሩ ሑሴን። አልተሳሳተም። በሁለንተናዊ ህይወታቸው ውስጥ እዝነት ጎልቶ ይታያል። ኡስታዙ አራት ክስተቶችን ያነሳል። ➤ የመጀመሪያው ፈትህ መካ ነው። ድል አድርገው መካ ሲገቡ ያሳደዷቸው ፣ ባልደረቦቻቸውን የገደሉባቸው ፣ ንብረታቸውን የዘረፉባቸው ፣ ጧኢፍን ለመሰለ አስከፊ ክስተት የዳረጓቸውን የቁረይሽ ከሃዲያንን እንዴት አስተናገዷቸው? ሳዐድ ኢብኑ ኡባዳን በምን መልኩ ገሰጹት? ➤ የኛ ነቢይ ﷺ የልጆችን ዋይታ ሰምተው ሰላትን አሳጥረዋል። በአንድ ወቅት እየሰገዱ እያለ ሀሰንና ሁሴን እላያቸው ላይ ሲጫወቱ እነሱን ላለመረበሽ ብለው ሱጁድ አስረዝመዋል 🥺 ➤ የነጅራን ክርስቲያኖች ነቢዩ (ሰዐወ) ጋር ለመወያየት መስጅድ ይመጣሉ። እየተወያዩ የጸሎት ሰዓታቸው ደረሰ። መስጅድ ውስጥ ጸሎት ለማድረስ ሲነሱ ሰሐቦቹ ምን አሉ? የእሳቸው ምላሽስ ምን ነበር? ➤ በምርኮ ሳቢያ ያኮረፉ አንሷሮችን በምን መልኩ ሰዋዊ ስሜታቸውን treat አደረጉ? አንድ መሪ ለድል ያበቃውን ማኅበራዊ መሠረት (social constituency) የሚያናግርበት መንገድ ትልቅ ጥበብ ይፈልጋል። ነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) እንዴት ተወጡት? የራሳቸውንም የነሱንም ውለታ መጥቀሳቸው ምን ይነግረናል? የኡስታዝ በድሩ ሁሴን አንደበት ማራኪ ነው። የፍጥረታት አይነታ የሆኑት ነቢይ ﷺ በእርግጥም ሲራቸው ያስቆዝማል። እዝነታቸው በሰዎች ልብ ውስጥ ስትት ብሎ የሚገባ ነው። የአድማጭ አይን እንባው ቅርር ቢል አይገርም። ሲራቸው የፈገግታ እንባን ያመነጫል። አላህም እንዲህ ብሏል :- وَمَا أَرْسَلْنَاكَ إِلَّا رَحْمَةً لِّلْعَالَمِينَ “አንተንም ለዓለማት እዝነት እንጂ አልላክንህም።” [አንቢያ : 107 ] የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! የአላህ በረከትና እዝነት ባንቱ ላይ ይስፈን 💚 @Abisha_Bori @yasin_nuru @yasin_nuru
የተባረከ ጁምዓ ይሁንልን! . #ኡስታዝ_ያሲን_ኑሩ #Ustaz_Yasin_Nuru ሰሉ አለ ነቢ @yasin_nuru @yasin_nuru
"ስትቀርበው ለራቀህ አትጨነቅ ምክኒያቱም 'ውድ ነገር " ያለቦታው እርካሽ ነው እና" "ስታምነው ለከዳህ አትጨነቅ ምክኒያቱም " ታማኝ "በመሆንህ አሸንፈሃል እና" "ስትፈልገው ባጣኸው ነገር አትጨነቅ" ምክኒያቱም" እርሱ አንተን ሲፈልግ ታገኘዋለህ እና" "ስትወደው ለጠላህ አትጨነቅ ምክኒያቱም" ስንት ምርጥ ሰወች አንተን እሚወዱ አሉና" "ስላልሆነው ነገር አትጨነቅ ምክኒያቱም" ገና ከዚህ በኅላ እሚሆን ብዙ ነገር አሉና" " አጣዋለሁ ብለህ ያላሰብከውን ብታጣ አትጨነቅ ምክኒያቱም" አገኘዋለሁ ብለህ ያላሰብከውን ታገኛ ለህ እና " "ያሰብከው ሳይሆን ቢቀር አትጨነቅ ምክኒያቱም" አሏህዬ ያላሰብከውን ይሰጥሃል እና" "እናልህ ወዳጆ አትጨነቅ እንተ ለሁሉም ተፈጠርክ እንጅ ሁሉም ለአንተ አልተፈጠረም" "አሏህዬ ለአንተ እሚያስፈልግህን ያውቃል" ያሰብከውን አስጥሎህ ያላሰብከውን ይሰጥሀል እና " "ስላለፈው ብዙ አታሰላስል ' ስለወደ ፊቱ አብዝተህ አትጨነቅ ከዚህ ይልቅ ዛሬን ጠበቅ አድርግ" አትጨነቅ!! ("እችም ቀን ታልፍ እና ድሮ ትባላለች ስአቷ ታልፍ እና ታሪክ ትባላለች") በደስታ "እለፋት ነገም ሌላቀን ነው "ህይወትህ ተስፋ አላት....... @yasin_nuru @yasin_nuru
ያ ሼኽ፦ ባሌ ያለ ምንም ሰበብ ሁለተኛሚስት አገባብሻለሁ አለኝ ስራ የምሰራዉ እኔ ነኝ እሱ ስራ የለዉም ምን ላድርግ ?? ሼኽ፦ ሁለት ቤት ማስተዳደር አልችልም በይዉ. 🙆♂😎 @yasin_nuru
➲ *የሶሀባ* *ሚስቶች* *ለባላቸው* *የነበራቸው* *ልዩ* *ፍቅር* ➧ከእለታት አንድ ቀን አቡ ደርዳዕ ከሚስት ኡሙ ደርዳእ ጋር አብረው ተቀምጠው ሳሉ ኡሙ ደርዳእ እንዲህ አለች ➜ጌታዬ አላህ ሆይ ! ባለቤቴ አቡ ደርዳእ እዚህ ዱንያ ላይ እርሱ እኔን ለትዳር ጠይቆኝ አግብቶኛል ፡ እኔ ደግሞ እርሱኑ ጀነት ላይ _እንድትድረኝ_ እለምንሃለሁ አለች፡ ➧ከዛም አቡ ደርዳእ ይሄን ስትል እየሰማት ነበርና እንዲህ አላት ➻እሱ እንዲሳካልሽ የምትፈልጊ ከሆነ ምናልባት እኔ ካንቺ በፊት ከሞትኩ "አንቺ እስክትሞች ድረስ ፈፅሞ ሌላ ባል እንዳታገቢ አደራ" አላት ➺ከዚያም ከግዜያት ቡሀላ አቡ ደርዳእ ሞተ ➲ኡሙ ደርዳእ በጣም ውብና ቆንጆ ነበረችና ከአቡ ደርዳእ ሞት ቡሀላ ሙዓዊያ ኢብኑ አቢ ሱፍያን ለትዳር ሊጠይቃት ወደርሱዋ ይመጣል ➫አስቡት ሙዓዊያ በጊዜው የሙስሊሞች መሪ አስተዳደር ወይንም መንግስት ነበር፡ ➺ከዛም ሙዓዊያ የትዳር ጥያቄ ሲያቀርብላት እንዲህ ብላ መለሰችለት ➧በፍፁም ወላሂ ዱንያ ላይ ከአቡ ደርዳእ ቡሀላ ማንም ወንድ ቢመጣልኝ አላገባም፡ አላህ በርሱ ፈቃድ ጀነት ላይ አቡ ደርዳእን እስኪድረኝ ድረስ እዚች ዱንያ ላይ ባል ሚባል በፍፁም አላገባም አለችው። @yasin_nuru @yasin_nuru
📌 የልብ እርጋታ እና የዱንያ እውነተኛ ገጽታ በዚህች ምድር ላይ ስትኖር ሁልጊዜ ደስታን ብቻ አትጠብቅ። ዱንያ የፈተና እንጂ የማረፊያ አገር አይደለችም። ብዙ ጊዜ ልባችን የሚጨነቀውና ሰላም የሚያጣው፣ የማይቀረውን የፈጣሪን ውሳኔ (ቀድር) በደስታ ለመቀበል ስንቸገር ነው። ታላቁ ሊቅ ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ "አላህ አንድን ባሪያውን በችግርና በፈተና ሲከበው፣ ሊያጠፋው ፈልጎ አይደለም። ነገር ግን በትዕግስቱና በኢማኑ አማካኝነት ወደ እሱ ይበልጥ እንዲቃረብና እውነተኛ ተገዢነቱን እንዲያሳይ ስለሚፈልግ ነው።" 1. ፈተና የውዴታ ምልክት ነው ነብዩ ሙሐመድ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ ለአንድ ሕዝብ መልካምን ነገር ሲሻላቸው ይፈትናቸዋል።" (ቲርሚዚ)። ስለዚህ ያጋጠመህ ፈተና አላህ እንደረሳህ ወይም እንደጠላህ ማሳያ አይደለም። ይልቁኑ አንተን ካሉበት የወንጀል እድፍ አጥሮ ወደ ጀነት ማዕረግህ ከፍ ሊያደርግህ የፈለገበት መንገድ ሊሆን ይችላል። 2. መፍትሔውና ቁልፉ የት ነው? ተውበት (እስቲግፋር)፦ ብዙ ጊዜ በረካ የሚርቀንና ጭንቀት የሚበዛብን በራሳችን ጥፋትና ወንጀል ሳቢያ ነው። በቀን ውስጥ ቢያንስ 100 ጊዜ "አስtagፊሩላህ" ማለትን የዕለት ተዕለት ልምድህ አድርገው። ዱዓእ (ጸሎት)፦ አላህ ባሪያዎቹን እንዲህ ይላቸዋል፦ "ለምኑኝ፤ እቀበላችኋለሁ።" (ሱረቱ ጋፊር፡ 60)። በሰዎች ደጅ ከመንኳኳት ይልቅ፣ ማንም በማያይህ በሌሊት የመጨረሻ ክፍለ ጊዜ ተነስተህ ስብስብ ብለህ ፈጣሪህን ለምነው። ሰላት፦ ሰላት የልብ ብርሃን እና የጭንቀት ማራገፊያ ነው። ልብህ ሲጠበብ ነብዩ (ﷺ) እንደሚያደርጉት ወደ ሰላት ሩጥ። 3. የነፍስህን ሂሳብ አሁን አውርድ ነገ፣ ከነገ ወዲያ እያልክ የተውበት ቀጠሮ አታራዝም። መቼ እንደምትሞት አታውቅም። ዛሬ በህይወት እያለህ፣ መተንፈስ እየቻልክ ወደ አላህ ተመለስ። የሰው ልጅ የቱንም ያህል ሀብት፣ ስምና ዝና ቢኖረው ወደ ቀብር የሚሄደው በነጭ ጨርቅ (ከፈን) ብቻ ተጠቅልሎ ነው። አብሮህ የሚቀበረውና የሚጠቅምህ መልካም ሥራህ ብቻ ነው። ማጠቃለያ፦ ውድ ወንድሜ/እህቴ! አላህ ላንተ ካሰበልህ ውጪ ምንም ነገር አይደርስብህም። ስለዚህ በነገው ሕይወትህ ላይ አትጨነቅ። ዛሬህን በአላህ ታዛዥነት ላይ አሳልፍ። አላህ ልባችንን በኢማን ያርጋልን፤ መጨረሻችንንም ያሳምርልን። @yasin_nuru @yasin_nuru
የተባረከ ጁምዓ ይሁንልን . #ኡስታዝ_ያሲን_ኑሩ #Ustaz_Yasin_Nuru @YaSiN_NuRu @YaSiN_NuRu
❝ዛሬ ላይ ብዙ ሰዎች ሁለተኛ ሴት ማግባትን ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን የፍትሕንና የኃላፊነትን ትርጉም አያውቁትም። ተአዱድ(ከ አንድ በላይ ማግባት) ለሁሉም ሰው በሩ የተከፈተ አይደለም። አንድ ሰው አካላዊ፣ ፋይናንሳዊና አእምሮአዊ ብቃት ሳይኖረው፣ የሁለተኛዋንና የመጀመሪያዋን ሀቅ ሳይጠብቅ አገባለሁ ማለቱ ወደ አደጋና ወደ ወንጀል መግባት ነው።❞ ✅ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሷሊሕ አል-ዑሠይሚን (ረሒመሁልላህ) @yasin_nuru @yasin_nuru
без подписи
Morning Dua in Full أذكار الصباح كاملة بدقة عالية بصوت عمر هشام العربي 👤 Omar Hisham Al Arabi #የጠዋት_አዝካር
🌹 በባልሽ ዘንድ ተወዳጅና የተከበርሽ ለመሆን ከፈለግሽ ⁉️ በባልሽ ዘንድ ሁልጊዜም ተወዳጅ፣ የተከበርሽና የልቡ ንግሥት ሆነሽ መኖር ትፈልጊያለሽ? እንግዲያውስ ይህንን ትልቅ የትዳር ሚስጥር በተግባር አሳይው። 🌹 ባልሽን መከባከብና እሱን ማስደሰት እንዲሁ ተራ ተግባር ሳይሆን፣ አላህ ዘንድ ትልቅ ምንዳ የሚያስገኝ "ዒባዳ" መሆኑን እወቂ። 🌹 ባልሽን እንደ ባል አክብሪው አላህ ለወንዶች የሰጠውን የኃላፊነት ቦታ (ቀዋሚነት) እወቂለት። እሱን ማክበርሽ አንቺን ዝቅ አያደርግሽም፤ ይልቁንም በዓይኑ ላይ ትልቅ ያደርግሻል። አላህን በማመፅ እስካላዘዘሽ ድረስ የታዛዥነትሽን ልብ ስጪው። 🌹 የቤትሽ "ሰከን" (መረጋገጫ) ሁኚለት ከውጭ በስራና በኑሮ ደክሞት ሲመጣ፣ ቤትሽ የሰላም ወደብ ይሁንለት። ንጭንጭንና ጭቅጭቅን አስወግጂ። በለሰለሰ ንግግርና በፈገግታ ተቀበዪው። ነቢዩ (ﷺ) እንደተናገሩት፦ "ምርጥ ሴት ማለት ስትመለከታት ደስ የምታሰኝህ ናት ብለዋልና።" 🌹 እልክና ፉክክርን ተዪ ትዳር የሁለት ተፋቃሪዎች መርከብ እንጂ የፉክክር ሜዳ አይደለም።ከባልሽ ጋር እልህ ውስጥ አትግቢ፣ ለባልሽ ንቀት አታሳይ። ስህተቱ የሱ ቢሆንም እንኳ በትህትናና በጥበብ ለማሳመን ሞክሪ እንጂ በባልሽ ላይ ድምፅሽን ከፍ አታድርጊ። 🌹 የትዳር ሀቁን ጠብቂለት የባልሽን ስሜት መጠበቅና በሐላል ደስተኛ እንዲሆን ማድረግ የአንቺ ትልቁ ኃላፊነት ነው። በዚህ ረገድ አትዘንጊ፣ አትለግሚ። እሱ ካንቺ ዘንድ እርካታን ካገኘ፣ ልቡ ሙሉ በሙሉ የአንቺ ይሆናል። 🌹 ቤትሽንና ራስሽን ጠብቂ፦ ቤቱን በንጽህና ያዢ፣ ለአንቺም እንዲመቸው አድርጊው። ለባልሽ በሚያምር ሁኔታ ተዘጋጂ። ይህ ማድረግሽ ለሱ ያለሽን ፍቅርና ክብር መግለጫ ነው። 🌹 ይህንን ሁሉ ስታደርጊ ለዱንያ ጥቅም ብቻ ሳይሆን የአላህን ውዴታ ፍለጋ ይሁን። "ባሌን ካስደሰትኩ አላህ ይወደኛል" ብለሽ ነይቺ። ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ "አንዲት ሴት አምስት ወቅት ሶላቷን ሰግዳ፣ የረመዳንን ወር ጾማ፣ ብልቷን ጠብቃና ባሏን ታዛ ከሞተች፤ ከፈለግሽበት የጀነት በር ግቢ ትባላለች።" (ኢማም አሕመድ ዘግበውታል) እህቴ ሆይ! ባልሽን ለአላህ ብለሽ ካከበርሽው፣ አላህ በእሱ ልብ ውስጥ ያንቺን ፍቅርና ክብር ይዘራዋል። ትዳርሽን በኢማንና በጥሩ ስነ-ምግባር አድምቂው። ያንችው ወንድም አቡ ሒበቲላህ @yasin_nuru @yasin_nuru
የሱቄ በር ላይ መጥቶ ሲቆም ገዢ መስሎኝ ነበር:: ለዛውም ፀዴ ገዢ ዘጭ አድርጎ የሚገዛ... ሰውነቱ ደንደን ያለ አለባበሱ የሚያምር ነገር ነው :: ዝም ብሎ ሲያየኝ ከተቀመጥኩበት ሳልነሳ " ምን ላሳይህ ወንድሜ? " አልኩት ቃል ሳይተነፍስ በዝምታ ማየቱን ቀጠለ " እብድ ነው ? " እንዳልል አይመስልም " የኔ ቢጤ ነው? " በጭራሽ አይመስልም ምንም ሳይናገር ቆሞ ሲያፈጥብኝ " ምን ፈልገህ ነው? " አልኩት ቆጣ ብዬ " እባክሽ 50 ብር ላስቸግርሽ " አለና አንገቱን አቀረቀረ ... ጆሮዬን ማመን አልቻልኩም:: ማርያምን እንባዬ መጣ 50 ብር? 🥺... ይቺን ለመጠየቅ ምን ያህል እንደተሳቀቀ ቀና ማለት ያቃተው ገፁ ይናገራል:: የገመትኩት ሌላ ሆኖ ያገኘሁት ሌላ!!! ሲታይ 50 ብር የቸገረው አይመስልምኮ ለካ ሰውን በማየት ብቻ መገመት ከባድ ነው:: የጠየቃት ብር ምን ልትጠቅመው? እንዴት አንጀቴን እንደበላው 😥 እንዳፈረ ስለገባኝ ምንም መጠየቅ አልፈለኩም :: ብቻ ቦርሳዬ ውስጥ ያገኘሁትን ብር አውጥቼ ሳስጨብጠው እንባ ባቀረሩ አይኖቹ ቀና ብሎ አየኝና ፈገግ ለማለት እየሞከረ... " አሏህ ይስጥሽ " ብሎኝ ሲሄድ የተጨነቀው ፊቱ ለተወሰነ ደቂቃ ከውስጤ ሊጠፋልኝ አልቻለም ነበር:: ማጣት💔💔 Lulit tadese @yasin_nuru @yasin_nuru
⛔ #ልጆቻቹሁን_አትራገሙ‼ ◾ከጭንቅላቱ በስተቀር መላ አካሉ ፓራላይዝድ የ ነበር ህይወቱን ሙሉ ወደ አላህ የተጣራ ዳኢ ነበር። ◾#ዳኢ/ሼኽ #አብደላህ_ባኒእማ እንዲህ ይላል፡- " አንድ ቀን አባቴ ድንገት ልብሴ ላይ የሲጋራ ሽታ ሸተተው.. በወቅቱ እኔ በድብቅ አጨስ ነበር ገና የ17 አመት ልጅ ነበርኩ.. አባቴም እንደማጨስ ጠየቀኝ እኔም ማጨሴን ካድኩ ... አባቴ ተናዶ ስለነበር እንዲህ አለ: (ካጨስክ አላህ አንገትህን ይሰብረው) .. በዛው ቀን.. ከወንድሞቼ ና ከዘመዶቼ ጋር ወደ መዋኛ ቦታ ሄድኩ.. ለመዋኘት ወደ ገንዳው ለመግባት ዘለልኩ በአጋጣሚ ስህተት አዘላለል ነበርና ጭንቅላቴ መሬት አረፈ አንገቴ ላይ ያለ አከርካሪዬ ተሰበረ.. 💔💔💔 ህይወቴ ሙሉ #ሽባ ሆኜ ቀረሁ።💔😞 #የአባቴ_ዱአ_በትክክለኛው_ጊዜ_መልስ_ያገኘ_ይመስል_ነበር።" 💔😞 ◾ሼኹ ገና በወጣትነቱ ቁርኣንን ሀፍዞ ህይወቱን ሙሉ የአላህን ዲን በማገልገል (ለ31 አመታት) አሳልፏል። ◾ሼኹ የዛሬ ሁለት አመት ወደ አኼራ ሄደዋል በራሳቸው የህይወት ታሪክ ምክንያት ለብዙ ወጣቶች የሂዳያ ሰበብ ሆነዋል አላህ ይዘንላቸው #ልጆቻችሁን_አትራገሙ ‼ምናልባት ያቺ ሰአት ዱአ ተቀባይነት ሚገኝበት ሰአት ይሆናልና ከመራገም አላህ እንዲያስተካክላቸው ዱአ አድርጉ Hijra Tube @yasin_nuru @yasin_nuru
የንጉሱ ጣት እና የአላህ ጥበብ" — አስተማሪ ታሪክ 📖 በጥንት ዘመን አንድ ንጉስና ጥበበኛ አማካሪ ነበሩ። አማካሪው ሁል ጊዜ ምንም አይነት ነገር ቢፈጠር "አላህ ያደረገው ሁሉ መልካም ነው" የማለት ልማድ ነበረው። አንድ ቀን ንጉሱ በስህተት ጣቱን ይቆረጣል። በጣም ተናዶ አማካሪውን "ጣትህ ተቆርጦ ምን መልካም ነገር አለው?" ብሎ ጠየቀው። አማካሪው ግን አሁንም "ንጉስ ሆይ! አላህ ያደረገው ሁሉ መልካም ነው" አለው። ንጉሱ በቁጣ አማካሪው ወደ ወህኒ ቤት እንዲጣል አደረገ። አማካሪው ወደ ወህኒ ሲገባም "አላህ ያደረገው ሁሉ መልካም ነው" ማለቱን አልተወም። ከጥቂት ቀናት በኋላ ንጉሱ ከጥበቃዎቹ ጋር ወደ ጫካ ለአደን ይወጣል። እዚያም ሰዎችን ለጣዖት የሚሰዉ የጫካ አረመኔዎች እጅ ላይ ይወድቃል። አረመኔዎቹ ንጉሱን ለመሰዋት ሲያዘጋጁት፣ አንድ ትልቅ እንከን አዩበት፤ ጣቱ ተቆርጧል! የእነሱ እምነት ደግሞ አካሉ የጎደለ ሰውን መሰዋት ይከለክላል። ስለዚህ ንጉሱን ለቀቁት። ንጉሱ በደስታ ወደ ቤተመንግስቱ ተመልሶ አማካሪውን ከወህኒ አስወጣው። "እውነትህን ነው! ጣቴ መቆረጡ ህይወቴን አትርፎልኛል። ግን አንተ ወደ ወህኒ መግባትህ ምን መልካም ነገር አለው?" ሲል ጠየቀው። አማካሪው ፈገግ ብሎ እንዲህ አለው፦ "ንጉስ ሆይ! እኔ ወህኒ ባልገባ ኖሮ ከአንተ ጋር ወደ አደን እወጣ ነበር። አረመኔዎቹ አንተን አካልህ ስለጎደለ ሲለቁህ፣ እኔን ሙሉ ስለሆንኩ በአንተ ምትክ ይሰዉኝ ነበር። ስለዚህ እኔ ወህኒ መግባቴ ህይወቴ የተረፈበት የአላህ መልካም እቅድ ነው!" @yasin_nuru @yasin_nuru
1. ኑዐይማን ኢብኑ አምር (ረ.ዐ) እና የአንበሳው ስጋ ኑዐይማን የተባለው ሶሃባ በመቀለድና ሰዎችን በማሳቅ በጣም የታወቀ ነበር። አንድ ቀን አንድ ገጠርያዊ (በደዊ) ሶሃባ ግመሉን ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መስጂድ ውጭ አስሮ ወደ ውስጥ ይገባል። ሌሎች ሶሃባዎች ኑዐይማንን አይተው፦ "ረሃብ አድክሞናል፤ የዚህን ግመል ስጋ ብናገኘው ምንኛ ጥሩ ነበር! ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) ዋጋውን ይከፍሉለት ነበር" አሉት። ኑዐይማንም ወዲያው ሄዶ ግመሏን አረዳት። ባለቤቱ ከመስጂድ ወጥቶ ግመሉ ታርዶ ሲያይ "ዋይ ግመሌ! ሙሐመድ ሆይ ግመሌን አረዱት!" እያለ ጮኸ። ነብያችንም (ሰ.ዐ.ወ) ወጥተው "ማነው ይህንን ያደረገው?" አሉ። ሶሃባዎቹም "ኑዐይማን ነው" አሉ። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ኑዐይማንን ፍለጋ ሲሄዱ፣ አንዲት ሴት ቤት ውስጥ መሬት ተቆፍሮ በተዘጋጀ ጉድጓድ ውስጥ ተደብቆ በቅጠል ተሸፍኖ አገኙት። ነብያችንም (ሰ.ዐ.ወ) እየሳቁ ከጉድጓዱ አወጡትና "ለምን ይህንን አደረግክ?" አሉት። እርሱም "ያ አላህ መልዕክተኛ! መቼም እኔ ያለሁበትን የጠቆሙህ ሰዎች ራሳቸው ናቸው እንዲያ እንድ አደርግ የገፋፉኝ" አላቸው። ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) በንግግሩ በጣም ሳቁ፤ ከፊታቸው ላይ የነበረው አቧራም እየጠረጉለት ለባለቤቱ የባለግመሉን ዋጋ ከፈሉለት። @yasin_nuru @yasin_nuru
💙#ትዳር #በነብዩ ሰ.ዐ.ወ ሱና💙 😎 #ያገቡ #ሰዎች› እና ‹ያላገቡ ሰዎች› በእነዚህ ሰዎች መካከል የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት አለ ቢባል አይከብድም፡፡ ✍ #የእነዚህ ሰዎችን ልዩነት በአንድ ርእስ ብቻ መግለፅ ቢከብድም አጠር ባለ መልኩ ኢን ሻ አላህ ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡ 💟 (ሰ.ዐ.ወ) ፈለግ ሲከተል ያላገባ ሰው ትልቅ የሆነውን ሱና ተነፍጓል፡- ከመጀመሪያው ቀጥሎ ትልቁ ልዩነታቸው፦ ☞ #ያገባ #ሰው ትልቅ ሱናን ሲከተል ያላገባ ሰው ደግሞ ትልቁ ሱና አምልጦታል፡፡ ☞ ሰይዱል ሙስጠፋ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “…የእኔን ሱና የማይከተል ከእኛ አይደለም፡፡›› 💟 #ያገቡ #ሰዎች ከብዙ ሀራም ሲጠበቁ ያላገቡ ሰዎች ሀራም ላይ የመውደቅ እድላቸው ይሰፋል፡- ☞ያገቡ ሰዎች አይናቸው ይሰበራል፣ ☞ብልታቸው ከዝሙት ይጠበቃል፣ ☞ቀልባቸው ይረጋጋል፡፡ ☞ያላገቡ ግን ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ ተጠቃሚ አይሆኑም፡፡ 💐#ታላቁ #ነብይ(ሰ.ዐ.ወ) ‹በሁለት እግሮቹና በሁለት ከንፈሮቹ መሀል ያሉትን ስጋዎቹን የጠበቀ እኔም ጀነትን ቃል እገባለታለሁ፡፡› ብለዋል፡፡ ☞#ያገባ ሰው ከሁለቱ ነገሮች የመጠበቅ እድሉ የሰፋ ነው፡፡ ያላገባ ግን…. 💟 #ያገባ #ሰው ዘሩን ሲቀጥል ያላገባ ግን ዘሩን የመቀጠል እድል የለውም፡- ☞ #ዘር #በኢስላም ትልቅ ቦታ አለው፡፡ ‹ብዙ ተባዙ፡፡ ☞ነገ የውመል ቂያማ ከሌላው ነብይ የእኔ ኡመቶች በዝተው እንዲታዩ› ብለው ነግረውናል ታላቁ ነብይ፡፡ እናም ልጆችን የምንወልደውና የልጆችን ደስታ የምናገኘው በትዳር ውስጥ ነው፡፡ ☞ ያላገባ ሰው ይህን ኒዕማ ማግኘት አይችልም፡፡ 💟 #ያገባ #ሰው ሪዝቁ ይሰፋል፣ የልብ መረጋጋትን ያገኛል ☞ያላገባ ሰው ግን ይህን ነገር አያገኝም፡- ‹ሪዝቁ እንዲሰፋለት የፈለገ ሰው ያግባ› ሲሉ ሰለፎች ይመክሩናል፡፡ ☞ያገባ ሰው ልቡ መረጋጋትን ያገኛል፣ ቀልቡ ማረፊያን ታገኛለች፡፡ ☞ያላገባ ሰው ግን እንደተጨናነቀ ነው እድሜውን የሚጨርሰው፡ 💐💐💐 እስኪ ላገባችሁ ይህ ሁሉ ኒእማ ላይ ስለሆናችሁ ዱአ አርጉልን🌿🌿 ❤️ #አላህ ላላገባን የሚበጀንን የትዳር አጋር ይወፍቀን ✔️ #እስኪ ላላገቡት ጓደኛችሁ ሼር ያድርጉት አይታወቅም ጀምሮ ከሆነ ይህን ኒእማ ሲያነብ እስከ አሁን ተጎድቻለሁ ወይ ብሎ 😉 አባወራ ሊሆን ይችላል😉 @yasin_nuru @yasin_nuru
الإمام أبو حنيفة ኢማም ኢብኑ ሃኒፋህ አን-ኑዕማን #የጁምዓ_ኹጥባ 17-11-18 @yasin_nuru @yasin_nuru
አራት ነገሮች ሴቶችን ያጠፋሉ። የትዳር ህይወትን ያበላሻሉ ። በዱንያና በአኼራ ደስታን ያርቃሉ። 4──────⊱◈◈◈⊰────── 1#ምላስ #ማስረዘም. የሴት ልጅ ውበት ዝምታው አደቧ ሀያእዋ ነው። በተለይ ባል ላይ ከፍ ከፍ ማለት እኔ አውቃለሁ ማለት የትዳርንም የዱንያንም የአኼራንም ህይወት ያበላሻል።እንዳውም ይሄ ከምእራባውያን የመጣ የፌሚኒስት ሴቶች ባህሪ ነው። ──────⊱◈◈◈⊰────── 2#ስሞታ #ማብዛት ለትዳር ከማይበጁ ሴቶች ባህሪ ውስጥ──────⊱◈◈◈⊰────── አንዱ ባህሪ ስሞታ ማብዛት ምስጋና ቢስ መሆን በትልቅ በትንሹ መጨቃጨቅ ነው። ስግብግብ ሁሉ አማረሽ ያየችው ሁሉ የሚያምራት የምትፈልገውን ካላገኘች ወቀሳዋ ለሽማግሌ የሚያስቸግር ሴት ናት። ──────⊱◈◈◈⊰────── 3#ውለታን #መካድ ስንት አመት የተንክባከባትን ባልዋን አንድ ቀን ጥፋት ስታይ ምን አደረክልኝ ? ከአንተ ኸይር አይቸ አላውቅም የምትል ሴት ቤቷን ማፍረስ የፈለገች ሴት ናት። አኼራም ላይ እሳት የመግቢያ ሰበብ እንደሆነም ተንግሯል። ──────⊱◈◈◈⊰────── 4 ከአጋሯ ውጭ ለሆኑ ወንዶች የምትገላለጥ እዩኝ እዩኝ የምትል እና ወጣ ገባ የምታበዛ ያለባሏ ፍቃድ የምትጓዝ ውጭ ላይ ውበትን የምታሳይ እቤት ውስጥ ዝርክርክ የሆነች ሴት ነብዩ እንዳሉት አኺር ዘመን ላይ የሚመጡ መጥፎ ሴቶች እንደሆኑ ተናግረዋል፡ ──────⊱◈◈◈⊰────── ሴቶች ሆይ ይሄን እና ሌሎች መጥፎ ባህሪያቶች ተጠንቀቁ?! አላህ ሆይ እህቶቻችንን አስተካክልልን አሚንንንን @yasin_nuru @yasin_nuru
በደሴ ከተማ በስህተት የገባላቸውን ብር ለባለቤቱ በታማኝነት የመለሱት ግለሰብ! • ሀሩን ሚዲያ | ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ል በደሴ ከተማ አስተዳደር ነዋሪ የሆኑት የሬስቶራንት ባለቤት አቶ ኡመር እሸቴ፤ በስህተት ወደ የባንክ አካውንታቸው ገብቶ የነበረውን 300 ሺህ (ሦስት መቶ ሺህ) ብር ለትክክለኛው ባለቤት ለአቶ ሁሴን አህመድ በታማኝነት መመለሳቸው ተገለጸ። አቶ ኡመር ይህንን አርአያነት ያለው ተግባር የፈጸሙት በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መናፈሻ ቅርንጫፍ በአካል በመገኘት ገንዘቡን ለባለቤቱ ገቢ በማድረግ ነው። ግለሰቡ ያሳዩት ይህ ተግባር በማኅበረሰቡ ዘንድ የታማኝነትና የቅንነት እሴትን የሚያጎላ እና ለሌሎችም ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ በጎ ተግባር መሆኑ ተነግሯል። ለዚህ አርአያነት ላለው መልካም ተግባራቸውም ከፍተኛ ምስጋና እንደሚገባቸው የደሴ ፋና ኤፍ ኤም በዘገባው አስታውቋል። 📅 ሰፈር 11 ቀን 1448 ዓ.ሂ @yasin_nuru @yasin_nuru
የተባረከ ጁምዓ ይሁንልን . #ኡስታዝ_ያሲን_ኑሩ #Ustaz_Yasin_Nuru @YaSiN_NuRu @YaSiN_NuRu