❤የፍቅር እውነታ❤
Статистика❤️ የፍቅር ግጥሞች ❤️የፍቅር ጥቅሶች ❤️ የፍቅር ደብዳቤዎች ❤️ የፍቅር መልእክቶች ፍቅርን💓 የመሰለ ምን አለ! 🚩 አስተማሪ እና አዝናኝ ገጠመኝ እዚ ይገኛል 🔴 የፍቅር ጉዋደኛ ፣ ❣ወርቃማ የሆኑ የፍቅር አባባሎች ✅ @yefkl_eweneta Contact 👇👇 @BAMII213 @ferid69 . . . . . . . . @AFEKARIWE
- Последний пост
- 8 сент. 2024 г.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
እንባ እንባ ይለኛል ይተናነቀኛል እንባ ግን የታባቱ ደርቇል ከረጡቱ ሳቅ ሳቅም ይለኛል ስቆ ሳይስቅ ጥርሴ ስቃ እየነደደች መከረኛ ነፍሴ ✍✍✍ 👑BAMII👑
🌿ህይወት ቀጥላለች እዚህ ሰአት ላይ ደርሳለች በእያንዳንዱ ሰከንድ መንቀሳቀስ ደሞ ወደ ሞታችን እየቀረብን ነው ። እናም በሞታችን ስራችንን እንድናስቀጥል በእያንዳንዱ ሰከንድ ልክ መንቀሳቀስ አለብን ተማሪ ከሆንክ ጥናት ሰራተኛ ከሆንክ ስራህን ምክንያቱም ያንተ እረፍት ስራህ እንዲሆን ሁሌ መሞከር አለብህና ያለፈውን ስህተትህን መልሰህ ማስተካከል ትችላለህ ግን ያለፈህን ጊዜ መመለስ አትችል። 💫 መልካም ቀን ይሁንላችሁ።
🌿#6ቱ_የቅናት_ምልክቶች #አንድ አንተን የማክበር ወይም ላንተ እገዛ የማሳየት ጊዜ ሲሆን ጊዜ የለንም ይላሉ። #ሁለት አንተን ወይም እንቅስቃሴህን ይኮርጃሉ #ሶስት የምታደርገውን ሁሉ ያያሉ ግን አንተ እንድታይ አይፈልጉም። #አራት ራሳቸውን እንደ ጓደኛ ወይም እንደ ቤተሰብ ይቆጥራሉ። ድርጊታቸው ግን ያን አያሳይም። #አምስት እነሱን የሚጠቅም ሲሆን ብቻ ይፈልጉሃል። #ስድስት ትልልቅ ስኬቶችህን እንደ ትንሽ ይቆጥራሉ።
አታድርጉት! • ገንዘብን ለማግኘት ብላችሁ ጤንነታችሁን አትሰው! • ሰዎችን ላለማጣት ብላችሁ ከራሳችሁ ጋር አትለያዩ! • ስልጣንን ለመጨበጥ ብላችሁ ከሕብረተሰብ ጋር አትጣሉ! • አጉል ልማዳችሁን ላለመልቀቅ ብላችሁ ከሕይወት መስመር አትውጡ! • ላለመሸነፍ ብላችሁ ቤተሰባችሁን አታፈራርሱ! ይቅርባችሁ!
/// " አበጀው በያቸው " /// አንቺ አትሳቀቂ ሀቁን ንገሪያቸው እውነት ነወይ? ሲሉሽ እውነት ነው በያቸው በአንቺ ፍቅር ያጣሁ ማግኘት ያልታደልኩኝ ትህምርቴን አቁሜ እብድት ያጠናሁኝ ውበትና ፍቅር አቅሌን አስጥለውኝ እብደት በሚል ማዕረግ ሰውነት ያጣሁኝ እኔ ያንቺ ምርኮ የፍቅርሽ ቁስለኛ እብድ ነኝ ለሰዎች ያልሆንኩ ወረተኛ እናም ሲጠይቁሽ ሳትሸማቀቂ በአንቺ መወፈፌን ለሁሉ አሳውቂ ልብሴን አሶልቆ በሰፊ ጎዳና የሚያንከራትቱኝ ያው ፍቅርሽ ነውና ለሚጠይቁሽም እንዲህ ንገሪያቸው የአበደው በእኔ ነው አበጀው በያቸው። ✍በአምላክ
▪️ዜና ልጅ ሳለች ትምህርት ቤት ወላጅ አምጪ ትባላለች። ስብሐት ተከትሏት ይሄዳል። መምህሩ በስብሐት ፊት ዜና (ልጁ) ያጠፋችውን ይዘከዝክ ጀመር። አጠገቧ ቁጭ ብላ ከምትማር ልጅ ገንዘብ ወስዳለች በመባሏ ነበር ወላጅ እንድታመጣ የታዘዘችው። ስብሐት ኮስተር ብሎ... "እኔ ልጄን አውቃታለሁ" ይላል "ልጄን ጠንቅቄ አውቃታለሁ፤ ገንዘብ ካስፈለጋት እኔን አባቷን በግልፅ ትጠይቀኛለች። እንደማልከለክላት ታውቃለች። ደግሞ ሌብነት መጥፎ መሆኑን ልጄ ስለምታውቅ አትሰርቅም። ሌላ ጣጣ ሳናበዛ የጠፋውን ብር መጠን ንገሩኝና እኔ እተካለሁ" አለ። ይሄንን ያለው ለምን እንደሆነ ሲተነትን... "አንደኛ ዜና በአባቷ ልትኮራ ይገባታል። ገንዘቡን ልትሰርቅም፣ ላትስርቅም ትችላለች። እኔ አባቷ በፊቷ እንደዛ ተማምኜ ስለተናገርኩ፣ የሰረቀች ከሆነ ከዚያ በኋላ አትደግመውም። ገንዘብ ትጠይቀኛለች እንጂ" አለ ©️ ሕይወትና ክህሎት [በአለማየሁ ገላጋይ] *
❤የፍቅር እውነታ❤ pinned «ዛሬን እማ በቡሄ ቀኑ አንቺን ብቻ ያሳልመኝ ፈጣሪ ከወደደኝ አንቺን ያሳየኝ አንቺን ሳገኝ ደስታ ስለሚሰማኝ ብቻ አንቺን ብዬ ባከንኩኝ»
መፅናኛ __ ዛሬ ነገ እያልሁ የመውደዴን ፅናት የፍቅሬን ከፍታ ፥ ልነግራት ስጓጓ ጊዜ ብፈጅባት ነገ ልትሞሸር ፥ ተደገሰ ሰርጓ። ግዴላትም ይሁን ፥ በዚህ እኔ ኣልባባም ወደድኳት ኣልሁ እንጂ ፥ እሷን ኣላገባም!።
"የጉንዳኖች ፍልስፍና" ጉንዳኖች ሲጓዙ መንገድ ብትዘጋባቸው ከጉዟቸው አይገቱም፤ሌላ መንገድ ፈልገው ጉዟቸውን ይቀጥላሉ፡፡ ከተስፋ መቁረጥ ጋር ፈጽሞ አይተዋወቁም፡፡ ጉንዳኖች ለመጪው ጊዜ ይዘጋጃሉ፡፡ በበጋ ወቅት ለክረምት ጊዜ የሚሆናቸውን ቀለብ ያከማቻሉ፡፡ በዝናብ ወቅት ወደ ውጭ ሳይወጡ ክረምቱን ለማሳለፍ የቻሉትን ያህል ዝግጅት ያደርጋሉ፡፡ በክረምት ወቅት ነገ በጋ እንደሚመጣ ወይም ብራ እንደሚሆን እርግጠኞች ናቸው፡፡ ክረምቱ ለረዥም ጊዜ እንደማይዘልቅ ያውቃሉ፡፡ በጋውን በብሩህ ተስፋ ይጠብቃሉ፡፡ ጸሃይዋ ብጭ ስትልም ተግተልትለው ይወጣሉ፡፡ ጉንዳኖች ከአካላቸው ክብደት 20 እጥፍ የሚልቅ ነገር መሸከም ይችላሉ፡፡ ፈጣንም ናቸው፡፡ ሁልጊዜ በሥራ ተጠምደው ነው የሚታዩት፤ ምንጊዜም በእንቅስቃሴ ላይ ናቸው፡፡ መሰራት ያለበትን ሁሉ በትጋት ይሰራሉ፡፡ ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለነጋቸውም ያስባሉ - መኖሪያቸውን ይገነባሉ፤ቀለባቸውን ይሰንቃሉ፡፡ የሰው ልጅ ታዲያ ከጉንዳኖች ህይወት ምን ይማራል? በአሜሪካ የሞቲቬሽናል አባት የሚባለው ጂም ሮን፣ ከጉንዳኖች ለህይወት ስኬት የሚጠቅሙ አራት መመሪያዎችን መቅሰም እንችላለን፤ ይላል፡፡ "የጉንዳኖች ፍልስፍና" ሲልም ሰይሞታል፡፡ አራቱ የስኬት መመሪያዎች የሚከተሉት ናቸው፡- • ምንጊዜም ተስፋ አትቁረጡ • ሁልጊዜም ለነገ ወይም ለወደፊቱ አስቡ • አዎንታዊ ብሩህ ተስፋ ይኑራችሁ • የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ
እውነተኛ ደስታ ! ትክክለኛ ሰላምን ለማግኘት ትፈልጋለህ? እንግዲያውስ ወደ ፈጣሪህ ቅረብ አጥብቀህ ፈልገው ትዕዛዛቶቹንም ጠብቅ ፣ በመንገዱ ሂድ ያኔ ገንዘብ የማይገዛው ዝና የማይሰጠው ጥልቅ ደስታ እና ሰላም በቤትህ ወለል ብሎ ይገባል ! የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
🌿 አንተን ሁለት ነገሮች ይገልፁሀል ፡፡ የመጀመሪያው ምንም የሌለህ ጊዜ የምታሳየው ትዕግስት ሲሆን ሁለተኛው ሁሉም ሲሟላልህ የምታሳየው ጠባይ ነው ፡፡ --ኢማምአሊ
🌿 ያለህ አሁን ነው… አንድ ቀን ለዘላለም ዝም ትላለህ…አንድ ቀን ለዘላለም ትሄዳለህ…አንድ ቀን እስከወዲያኛው ትረስተህ ትዝታ ትሆናለህ…ፎቶህ ቤትህ ግድግዳ ላይ ተሰቅሎ ነበር ብቻ ትሆናለህ…አንድ ቀን ደግመኛ እድል አይሰጥህም…ያለህ አሁን ነው…የናፈቀህ ጋር ደውለህ አውራው…ያስቀየምከውን ይቅርታ ጠይቅ…🖤
በህይወቴ ከተማርኩት ነገር ውስጥ አንደኛው ለሰዎች #መልካም ነገር ብታደርግ ለመልካምነትህ ከሰዎች ዘንድ ምላሽ መጠበቅ ሊጎዳ እንደሚችል ነው። አንዳንዱ መልካም ስታደርግ ሞኝ እንደሆንክ ሊቆጥርህ ይችላል። አንዳንዱ ደግሞ ከእሱ የሆነ ነገር ፈልገህ የምታደርግለት ይመስለዋል። ሌላኛው ደግሞ ከምስጋና ይልቅ ጠላትህ ሊሆን ይችላል። እናም እልሀለሁ #ለመልካምነትህ ከሰዎች ምላሽን አትጠብቅ! ባገኘኸው አጋጣሚ ሁሉ ምላሹ ምንም ይሁን ምን #መልካምነት አብሮህ ይሁን! ፈጣሪ ይከፍልሀልና!!!
ግን የተከፈልልንን ዋጋ እናውቃለን? ምን ያህል አምላካችን እንደሚወድን እንረዳለን:: የክርስቶስ ለእኛ ያለው ፍቅር ከአእምሮ በላይ ነው::
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ቤተሰቦቻችን እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! ✝ መልካም የፋሲካ በአል ✝
ብዙዎች ስኬትን ተኝተው ያልማሉ ጥቂቶች ከአልጋቸው ተነስተው በተግባር ያሳኩታል። ወዳጄ ተነሳ የነገው የሚሳካው ዛሬን ከሮጥክ ነው ሰላም እደሩልኝ
እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታች ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልካም በዓል 🙏ከመርጌታ ንጉስ🙏🌹❤🐓🐓🐑🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
1. ምስጋና አመስጋኝ የሆኑ ሰዎች ምስጋና ቢስ ከሆኑ ሰዎች የበለጠ ደስተኛ ናቸው፡፡ “ተመስገን” በሉ ሲባሉ “ምን ምስጋና የሚገባው ነገር አለና” የሚሉ አሉ፡፡ ግን ብዙ “ተመስገን የሚያስብሉ ብዙ ነገሮች እንዳሉ ቆም ብለን ብናስብ በዙሪያችን ሞልተዋል፡፡ 2. ቀና ማሰብ ቀና አሳባዎች ቀና ከማያስቡ ሰዎች የበለጠ ደስተኛ ናቸው፡፡ ደስተኛ መሆን ከፈለግን “ይሆናል፤ ይቻላል፤ ይሳካል፤ ለበጎ ነው ወዘተ” ማለትን እንለማመድ፡፡ የእውነት እንደዚያ ካደረግን ለውጡን እናየዋለን፡፡ 3. ከልክ በላይ ማሰብ እና ራስን ከሌሎች ጋር ማወዳደር ማቆም “ከልኩ አያልፍ” ትል ነበር አያቴ፤ ሃሳብ ከልክ በላይ እንደገባት ወይንም አጠገቧ ያለ ሰው ከልክ በላይ እንደተጨነቀ ሲሰማት፡፡ ሺህ ዓመት አይኖርም፡፡ ሁሉም የሚያጭደው የዘራውን ነው፡፡ ራስን ከሌሎች ጋር ማወዳደር የተረጋገጠ ራስን የማሰቃያ መንገድ ነው፡፡ ሰው እንደቤቱ እንጂ እንደጎረቤቱ ሊኖር አይገባም፡፡ 4. ደግነት ደግ መሆን ይቅርና ሰዎች ደግ ስራ ሲሰሩ መመልከት እንኳን ደስተኛ እንደሚያደርግ ሳይኮሎጂስቶች አረጋግጠዋል፡፡ ደስታ ከህይወታችን እንደ ራቀ ሲሰማን አንዱ መልሶ ማቅረቢያ ስልት መልካም ስራ መስራት ነው፡፡ በርካታ የግብረ ሰናይ ድርጅቶች አሉ፡፡ ወደዚያ ጎራ ብሎ አንድ መልካም ነገር አድርጎ መመለስ ደስታን አጭዶ መመለስ ነው፡፡ 5. መልካም ማኅበራዊ ግንኙነት “ለሰው መድኃኒቱ ሰው ነው” ብለው አበው ጨርሰውታል፡፡ የልባችንን የምናዋየው የልብ ወዳጅ ዘመድ አንዱ የደስታ ምንጭ ነው፡፡ የሚያሳስበንን ነገር ከውስጣችን አውጥተን መናገር ጭንቀትን ይቀንሳል፡፡ 6. ይቅርታ “ቂም መቋጠር ማለት መርዝ ጠጥቶ ሌላኛው ሰው እንደሚሞት ማሰብ ነው” ይባላል፡፡ ይቅርታ የምናደርገው ከሁሉ በፊት ለገዛ ራሳችን ደህንነት ነው፡፡ ማህተመ ጋንዲ “ደካማ ሰው ይቅር ብያለሁ ማለት አይችልም፡፡ ይቅርታ የጠንካራ ሰው መገለጫ ነው” ይላሉ፡፡ ይቅር ብያለሁ ማለት በመንፈስ የበላይ መሆን ነው፤ መብለጥ ነው፤ ገናና የሞራል ከፍታ ላይ መውጣት ነው፤ ይህ ብቻ ሳይሆን ደስታን ወደ ህይወታችን የምንጋብዝበት መጥሪያ ካርድ ነው፡፡ 7. የምንወደውን ነገር ማድረግ 8. ያቀድነውን ዕቅድ እውን ለማድረግ የምንችለውን ሁሉ ማድረግ ያሰቡትን ማሳካት በራሱ ትልቅ ደስታን ይፈጥራል፡፡ ሁልጊዜ ሩቅ አሳቢ ቅርብ አዳሪ ከሆንን ግን ደስታ ውስጣችን አይለመልምም፡፡ የጀመርነውን ነገር ዳር የማድረስ ልምዱ ይኑረን፡፡ የምንኖረው የአማራጮች ዓለም ውስጥ ነው፡፡ ብዙ የማይቻሉ የሚመስሉ ነገሮች ተችለው የምንመለከትበ ዓለም፡፡ 10. ሃይማኖት እና መንፈሳዊነት ከሲኦል ቢያድነንም ባያድነንም ወደ ቤተ-እምነት መቅረባችን ደስታን ይገዛልናል እንጂ ደስታችንን አይነጥቀንም፡፡ ሃይማኖት እና መንፈሳዊነት ደስተኛ እንደሚያደርጉ በጥናት ጭምር ተረጋግጧል፡፡ 11. ሰውነታችንን መንከባከብ አእምሮአችን ከአካላችን ጋር በእጅጉ የተሳሰረ ነው፡፡ ጤናማ የሆነ ብቻ ሳይሆን የተዋበ ሰውነት እንዲኖረን የተመጣጠነ ምግብ በመመገብ፣ ስፖርት መስራትና በተለያየ መንገድ ጥረት ማረግ አለብን፡፡
1. ችግር ሲገጥምህ ሁልጊዜ ሊኖርህ የሚገባው አንዱ መርህ ፈጽሞ አለማቆም ነው። ተስፋ ስትቆርጥ በሕይወትህ ውስጥ የሽንፈት’ አስተሳሰብን ትጋብዛለህ። ይልቁንም ችግሩን ለመፍታት የተለያዩ መንገዶችን ፈልግ እና ችግሩን እስክታሸንፍ ድረስ ስልቶችህን መቀየርህን ቀጥል። 2. የሚመጣውን ማንኛውንም ችግር መቋቋም እችላለሁ ብለህ ካሰብክ የማትፈታው ችግር አይኖርም። እያንዳንዱ ችግር የራሱ የሆነ የመፍትሔ ዘር ይዟል። ይህ ማለት በአንተ ላይ የሚመጣ ችግር ሁሉ የራሱን መፍትሄ ይዞ ይመጣል ማለት ነው። ሰለዚህ የሚመጣውን ማንኛውንም ችግር መቋቋም እችላለሁ ብለህ ካሰብክ የማትፈታው ችግር አይኖርም። 3. በራስህ ማመንህን ቀጥል፣ በራስ መተማመን ይኑርህ በራስ መተማመን ችግሮችህን እና ዓለምን በድፍረት ለመጋፈጥ መቻልህን ያረጋግጣል። ሕይወትን ለመጋፈጥ በውስጥህ የሚያስፈልግህ ነገር ሁሉ እንዳለህ እመን። 4. ፍርሃትን ስታስወግድ ስኬት ወደ አንተ ይመጣል ፍርሃት በተለይም ውድቀትን መፍራት ብዙ ሰዎች በልበ ሙሉነት ችግራቸውን ለመፍታት እንዳይችሉ የሚያደርጋቸው መሰናክል ነው። ፍርሃት ችግሮች ሲያጋጥሙህ ከሚያጋጥምህ ውጤት ይልቅ አሁን ያለው ሁኔታ የተሻለ እንደሆነ እንድታስብ ያደርግሃል። ፍርሃት በአንተ እና በስኬት መካከል ያለ እንቅፋት ወይም መሰናክል ነው። ስለዚህ ፍርሃትን ስታስወግድ ስኬት ወደ አንተ ይመጣል። 5. ተአምርን ጠብቅ አንዳንድ ጊዜ ተአምራት እንደሚፈጸሙ ማወቅ እና ማመን በጣም አስፈላጊ ነው። ሆኖም፣ ተአምራት በህይወትህ ውስጥ የሚከሰቱት አንተ ድርሻህን ስትወጣ ብቻ ነው። ማድረግ ያለብህን ሁሉ አድርግ፣ እናም ተአምራት በአንተ ላይ ይከሰታሉ። 6. አእምሮህ አንተ ከምታስበው በላይ ሊሠራ የሚችል ታላቅ ሃብት ነው። ስኬታማ ሰው ለመሆን የሚያስፈልጉህ ግብዓቶች በሙሉ በአእምሮህ ውስጥ ናቸው - ታላቅነትን ለማግኘት እና ያሉብህን ችግሮች ለመፍታት የሚያስፈልግህ ነገር ሁሉ በአእምሮህ ውስጥ ነው። መፍትሄዎችን እንዳታይ የሚያደርጉህን እና ትኩረትህን የሚከፋፍሉ ነገሮችን በሙሉ ስታስወግድ፣ ያኔ ነገሮች ቀላል ይሆናሉ።
ራስን መቀየር! "ዛፍ ለመቁረጥ 6 ደቂቃ ብቻ ቢሰጠኝ አራቱን ደቂቃ መጥረቢያውን እየሳልኩ አጠፋዋለው" ብሎ ነበር አንድ የማከብረው የሀገር መሪ። አንተም ጊዜ ማጥፋት ያለብህ ራስህን ለመቀየር ነው እንጂ ስራው፣ ገንዘቡ፣ የፍቅር ግንኙነቱን ማሳመር ቀላል ነው። ወዳጄ መጀመሪያ አንተ በአመለካከትና በስብዕና ከፍ በል እንጂ ሌላውን መቀየር ማገዶ አይፈጅም! @Inspire_Ethiopia2 የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!