Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠
СтатистикаSupport channel for mental health awareness in Ethiopia. We post facts about psychology and psychological phenomenon. ''There's no health without mental health.'' Contact፡ @FikrConsultSupportbot Buy ads፡ https://telega.io/c/melkam_enaseb
- Последний пост
- 8 авг.
- Последнее чтение
- 00:45
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 34
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 686
- 1/48двое суток
- 1 932
- 1/72трое суток
- 2 083
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በዓይነቱ ልዩ የሆነ የአእምሮ ጤና እና የስነ-ልቦና ድጋፍ መርሃ-ግብር! በእርስዎ፣ በወዳጅዎ ወይም በቤተሰብዎ ላይ የደረሰ የአእምሮ ህመም አለ? የተንከባካቢዎች (Caregivers) ድካም እና የስነ-ልቦና ጫና አሳስቦዎታል? ከታዋቂ የስነ-አእምሮ ህክምና እና የስነ-ልቦና ባለሙያዎች ጋር የሚደረገውን ይህን ታላቅ መርሃ-ግብር አይለፉ! 👨⚕️ የባለሙያዎቻችን ስብስብ፦ • ዶ/ር ዳዊት አሰፋ — ሳይኪያትሪ ስፔሻሊስት • ዶ/ር እስቲፋኖስ እንዳለማው — ሳይኪያትሪ ስፔሻሊስት • ታመነ ግርማ — ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት (Clinical Psychologist) • ትዝታ አየለ — የስነ-ልቦና ባለሙያ (Psychologist) 🌟 ከልምድ አጋሪዎች (Lived Experience) ጋር የሚደረግ ድንቅ ውይይት! 📅 ቀን፦ ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም (August 18, 2026) 📍 ቦታዎን አሁኑኑ ያስይዙ፦ 📞 ደውሉልን፦ 0912778174 @melkam_enaseb
የትኩረት ኃይል 📌 በዲጂታል ትርምስ ውስጥ ውጤታማ የመሆን ጥበብ (Deep Work) በዘመናችን ትልቁ የሰው ልጅ ብቃት፣ ትኩረትን ሳይከፋፍሉ በአንድ ትልቅ ነገር ላይ የማሳረፍ ችሎታ ነው ! - Cal Newport በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ውስጥ ስንት ጊዜ ነው በሥራ ላይ እያለን፣ ስልካችን ላይ የሚመጣ የኖቲፊኬሽን (Notification) ድምፅ ትኩረታችንን የሰረቀው? ስንት ጊዜ ነው በአንድ ተግባር ላይ እያለን በአንድ በኩል ኢሜይል፣ በሌላ በኩል የማህበራዊ ሚዲያ መልእክት ሰላም የነሳን? የምንኖረው በቴክኖሎጂ በተጥለቀለቀ ዓለም ውስጥ ነው። ይህ ዓለም ትኩረታችንን በየሴኮንዱ ለመቀማት የተዋቀረ ነው። እውነታው ግን፤ ትኩረታችንን በየቦታው መበተን፣ በአእምሯችን ላይ ከፍተኛ ድካም (Cognitive Fatigue) ከመፍጠሩ ባሻገር፣ ምርታማነታችንን ወደ ዜሮ ዝቅ እያደረገው ነው። 💠 ጥልቅ ሥራ (Deep Work) ምንድነው? ጥልቅ ሥራ ማለት በአእምሮአዊ ጥረት የተሞላ፣ ምንም አይነት የውጭ መስተጓጎል (Distraction) ሳይኖር፣ በአንድ ቁምነገር ያለው ተግባር ላይ ብቻ የምንጠመቅበት የሥራ ዘይቤ ነው። ይህ ሁኔታ እኛን ወደ "Flow state" ወይም በሥራችን ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ወደመዋጥ (አእምሮአዊ መረጋጋት) ያደርሰናል። ይህ ማለት ዝም ብሎ በቢሮ መቀመጥ ሳይሆን፣ ትርጉም ባለው ነገር ላይ አእምሮን አሳርፎ ውጤታማ መሆን ነው። 💠 ትኩረትን መበተን በአእምሯችን ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ትኩረትን በየቦታው መበተን (Context Switching) አእምሯችንን ልክ እንደ ኮምፒውተር ፕሮሰሰር ያደክመዋል። → የአእምሮ መዛል (Attention Residue)፦ ከአንድ ተግባር ወደ ሌላ ተግባር ስንዘል፣ አእምሯችን የቀድሞው ተግባር ስሜት ውስጥ ይቀራል። ይህ ለውጥ በተደጋጋሚ ሲፈጠር የፈጠራ ችሎታችን ይገደባል። → ውሳኔ የመስጠት አቅም መዳከም (Decision Fatigue)፦ ትናንሽ ትኩረትን የሚሰርቁ ነገሮች አእምሯችንን ያደክሙታል። ቀኑ መጨረሻ ላይ ለትልቅ ሥራ የሚሆን ጉልበት አይኖረንም። → የጭንቀት ስሜት መብዛት፦ በአንድ ጊዜ ብዙ ነገር ለመሥራት መሞከር (Multitasking) በሰውነታችን ውስጥ የኮርቲሶል (የጭንቀት ሆርሞን) መጠን እንዲጨምር ያደርጋል። → የረዥም ጊዜ የትኩረት አቅም መዳከም፦ የፈለግነውን ያህል ጊዜ በአንድ ነገር ላይ ማተኮር የማንችልበት ደረጃ ላይ መድረስ። 💠 ትኩረትን ለመጠበቅ ተግባራዊ መፍትሔዎች 1. "ጥልቅ ሥራ" የሚሰሩበትን ጊዜ መለየት፡ ቀኑን ሙሉ በስልክና በኢሜይል መወጠርን ይተዉ። በቀን ቢያንስ ለአራት ሰዓታት ምንም አይነት ዲጂታል መስተጓጎል የሌለበት "ጥልቅ ሥራ" የሚሰሩበት ጊዜ ይፍጠሩ። 2. ዲጂታል ዝምታን መለማመድ (Digital Detox)፡ ስልክዎን ከማንኛውም ኖቲፊኬሽን ነፃ ያድርጉ። አስፈላጊ ባልሆኑ ጊዜያት ስልክዎን ከእይታዎ ውጭ ያድርጉት። ትኩረት የሚሰርቅ ነገር ካላዩ፣ የመጠቀም ፍላጎትዎ ይቀንሳል። 3. ማረፍን እንደ ሥራ መውደድ፡ አእምሮ በተከታታይ ሊሠራ አይችልም። ጥልቅ ሥራ ሲሠሩ አእምሮዎ ሲደክም፣ እረፍት ያድርጉ። እረፍት ማለት ስልክ መያዝ ሳይሆን፣ ከአእምሯዊ እንቅስቃሴ መራቅ ነው። 4. "ምን መተው አለብኝ?" ብሎ መጠየቅ፡ በጣም ብዙ ነገር ለመሥራት መሞከር ትልቅ ስህተት ነው። በየቀኑ ከሚሰሩት ስራ ውስጥ የትኛው ነው ትልቅ ዋጋ ያለው? ያንን ብቻ ይለዩና ሌላውን መተው ይለማመዱ። 5. አእምሯዊ ጥንካሬን መገንባት (Monotasking)፡ በአንድ ጊዜ አንድ ነገር ብቻ የመሥራት ልምድን ያዳብሩ። ስትበሉ ብቻ ብሉ፣ ስትጽፉ ብቻ ጻፉ። ይህ ልማድ የትኩረት አቅምዎን ቀስ በቀስ ይገነባል። ማስታወሻ፡ በቴክኖሎጂ ዓለም ውስጥ ትኩረታችሁን መጠበቅ እንደ መዋኘት ነው። ተቃራኒ ሞገድ ቢኖርም፣ የራስዎን አቅጣጫ መምራት ይችላሉ። 1. ትኩረት የእርስዎ ንብረት ነው፦ በማንኛውም አፕሊኬሽን ወይም ሰው ትኩረትዎ እንዲወሰድ አይፍቀዱ። 2. ጀምሩና አትቁረጡ፦ ትልቅ ሥራ የሚጠይቀው ሰዓትን ብቻ ሳይሆን፣ ጥራት ያለው ትኩረትን ነው። 3. የአእምሮ ሰላም ቅድሚያ አለው፦ በተበታተነ አእምሮ ከመሥራት፣ በተረጋጋ አእምሮ ጥቂት መሥራት ይሻላል። የአእምሮአችን ትኩረት፣ የሥራችን ውጤት መለኪያ ነው! ✍ Solomon M., Mind Whisper @melkam_enaseb
⤵️
🧠 Understanding Major Depression Join Mental Health Addis for an interactive session exploring major depression, featuring expert dialogue and a group Reflective Writing activity. 🗣 Speakers: • Yohanan Zerihun (Psychiatry Professional, Psychotherapist) • Rehoboth Masresha (Psychiatry Professional, Moderator) 🗓 Date: Saturday, Aug 1, 2026 ⏰ Time: 2:30 PM (8:30 Local Time) 📍 Location: Modern Art Museum: Gebrekiristos Desta Center (6 Kilo) ✨ All are welcome to join and participate in this safe, supportive space. #MentalHealthAddis #AddisAbaba #EventsInAddis @melkam_enaseb
Remember: የአእምሮ ሰላምህን እያጣህ በሕይወት ውስጥ ማሸነፍ ፍጹም አትችልም። ለምንም ነገር ከመሯሯጧቹህ በፊት ለአእምሮ ጤናችህ ቅድሚያ ስጡ፤ ራሳችሁ በአግባቡ ተንከባከቡ (take care of yourself)! ውጫዊ ስኬት ለማሳደድ ሌት ተቀን ስትደክሙ... ውስጣዊ ሰላማችሁን (Mental peace) እየገደላችሁት እንዳልሆነ እርግጠኛ ሁኑ! በዚህ ዘመን ሁሉም ሰው ስኬታማ፣ ባለገንዘብና 'ደርሻለሁ' ባይ ለመሆን ይሮጣል። ነገር ግን በትልቁ የምትሳሳቱት እዚህ ጋ ነው፤ አእምሮአችሁ እየፈረሰ፣ ውስጣችሁ በጭንቀትና በባዶነት እየተቆረቆረ የምታመጡት ስኬት ትርጉም የለውም። ባንክ ቤት ውስጥ የሞላ ገንዘብ ኖሯችሁ...በአእምሮአችሁ ውስጥ ግን ሰላም ከሌለ፣ እናንተ አሁንም ተሸናፊ ናችሁ። ለሰዎች ስትሉ ራሳችሁን አሳልፋችሁ እየሰጣችሁ... የራሳችሁን ስብዕና (Self-care) የምትረሱ ከሆነ፣ መጨረሻችሁ ባዶነት ብቻ ነው። ዓለምን ለማሸነፍ ከመነሳታችሁ በፊት መጀመሪያ ራሳችሁን አሸንፉ። ለሰዎች ስትሉ ወይም ስራ ለማሳካት ብላችሁ የአእምሮ ጤናችሁን (Mental health) አሳልፋችሁ አትስጡ። You matter first! ራሳችሁን ጠብቁ፤ ሰላማችሁን የሚነካ ማንኛውንም ነገር ደግሞ 'NO' ማለት ልመዱ። You can replace a job, you can find new connections, and you can rebuild your finances. But you can never buy back a mind that you allowed to break. Protect your peace at all costs. ይምላቹህ ነገር ቢኖር ውጫዊ ኑሯችሁን ለማሳመር ውስጣችሁን አታፍርሱ። የአእምሮ ሰላማችሁን (Mental health) መስዋዕት አድርጋችሁ የምታመጡት ምንም ዓይነት ስኬት 'ማሸነፍ' ተብሎ አይጠራም። Your peace of mind is your greatest wealth. Take care of yourself. በርቱ! Fetia Yusuf (Psychiatrist) @melkam_enaseb
⤵️
📌 የሐሳብ እስረኝነት (The Prison of Overthinking) አእምሮአችን በትክክል ከተጠቀምንበት እጅግ ድንቅ መሣሪያ ነው፤ ካልሆነ ግን ከፍተኛ ጥፋት የሚያስከትል አጥፊ ይሆንብናል! - Eckhart Tolle በገዛ አእምሯችን እስር ቤት ውስጥ ታስረን እናውቃለን? ትናንት በፈጸምነው ስህተት መጸጸት፣ ዛሬ ለምንወስነው ትንሽ ውሳኔ ከመጠን በላይ መጨነቅ፣ እና ገና ስላልመጣው ነገ በመስጋት ማለቂያ በሌለው የሐሳብ አዙሪት (Rumination) ውስጥ መሽከርከር የብዙዎቻችን የዕለት ተዕለት ፈተና ነው። ይህ ሁኔታ አእምሯችንን ብቻ ሳይሆን መላ አካላችንን የሚያዝል የሐሳብ እስረኝነት (Overthinking) ይባላል። 💠 የሐሳብ እስረኝነት (Overthinking) ምንድነው? ይህ ሁኔታ እንዲሁ ዝም ብሎ ማሰብ አይደለም። የሐሳብ እስረኝነት ማለት በአንድ ጉዳይ ላይ ከመጠን በላይ ተደጋጋሚ እና አሉታዊ ሐሳቦችን በማመንጨት፣ መፍትሔ ወደሌለው ጭንቀት የመግባት ሂደት ነው። አእምሯችን አንድን ችግር ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ፣ በችግሩ ዙሪያ ብቻ ደጋግሞ በመሽከርከር ራሱን ሲያደክም የሚፈጠር ስነ-ልቦናዊ ጫና ነው። 💠 ከመጠን በላይ ማሰብ በአእምሯችን እና በአካላችን ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ የሰውነታችንና የአእምሯችን ትስስር እጅግ የጠበቀ በመሆኑ፣ ከመጠን በላይ ስናስብ የሚከተሉት አካላዊና አእምሯዊ ቀውሶች ይፈጠሩብናል፦ → የማያቋርጥ የአእምሮ ድካም (Mental Fatigue)፦ ምንም እንኳ አካላዊ ስራ ባንሰራም፣ አእምሯችን በአንድ ሐሳብ ላይ ደጋግሞ በመሽከርከሩ ብቻ ከፍተኛ ግሉኮስና ኦክስጅን ስለሚጠቀም ከፍተኛ የድካም ስሜት ይሰማናል። → የእንቅልፍ መዛባት (Insomnia)፦ ማታ ለመተኛት በምንሞክርበት ወቅት አእምሯችን ንቁ ሆኖ ሐሳቦችን ማውጠንጠን ይጀምራል። በዚህም ምክንያት የሰውነት እንቅልፍ ሆርሞን (Melatonin) መመንጨቱን አቁሞ የጭንቀት ሆርሞን (Cortisol) ይተካል። → የጡንቻ ውጥረት እና ህመም (Muscle Tension)፦ ከመጠን በላይ መጨነቅ በሰውነታችን ውስጥ የጡንቻ መኮማተርን ይፈጥራል። በተለይም በትከሻ፣ በጀርባ እና በአንገት አካባቢ የሚሰማ የማያቋርጥ ህመም ዋነኛው ምልክታችን ነው። → የምግብ መፈጨት ስርዓት መታወክ፦ አንጎላችን እና ጨጓራችን ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው። በሐሳብ ስንወጠር የጨጓራ ህመም፣ የመጮህ ስሜት ወይም የምግብ ፍላጎት መለዋወጥ ሊከሰትብን ይችላል። እነዚህ ሁኔታዎች በሙሉ በደማችን ውስጥ የኮርቲሶል (Cortisol) መጠን እንዲጨምር በማድረግ የሰውነታችንን የበሽታ መከላከያ አቅም (Immune System) ያዳክማሉ። 💠 ከሐሳብ እስረኝነት ለመውጣት ተግባራዊ መፍትሔዎች፦ 1. ሐሳቦችን በምክንያታዊነት መፈተሽ (Cognitive Reframing)፡ አስጨናቂ ሐሳቦች ሲመጡብን እንደ እውነት አንቀበላቸው። ይልቁንም ቆም ብለን ሐሳቡን እንመርምረው። "ይህ የምፈራው ነገር ለመከሰቱ ማስረጃ አለኝ?" ወይም "ይህ ሐሳብ አሁን እየጠቀመኝ ነው ወይስ እያዳከመኝ?" ብለን ራሳችንን እንጠይቅ። ሐሳብን በጥያቄ ስንሞግተው የማስጨነቅ አቅሙ ይቀንሳል። 2. የሐሳብ መዝገብ መያዝ (Brain Dumping)፡ አእምሯችን መረጃዎችን ለማመንጨት እንጂ ሁሉንም ጭንቀቶች ለማከማቸት አልተሰራም። የሚያስጨንቁንን ነገሮች በሙሉ ሳንመርጥ በወረቀት ላይ እንጻፋቸው። ሐሳብ ከአእምሮ ወጥቶ ወረቀት ላይ ሲሰፍር፣ ጭንቅላታችን ክፍት እንደሆነና እንደቀለለን ይሰማናል። 3. የጭንቀት ጊዜ መመደብ (Scheduled Worry Time)፡ ጭንቀት ቀኑን ሙሉ እንዲረብሸን አንፍቀድለት። በቀን ውስጥ 15 ደቂቃ ብቻ (ለምሳሌ ከቀኑ 11:00 ሰዓት እስከ 11:15) ለጭንቀት እንመድብ። በሌላ ሰዓት ጭንቀት ሲመጣብን "ጊዜው ሲደርስ አስባለሁ" በማለት ወደ ስራችን እንመለስ። ይህ አእምሯችን ጭንቀትን እንዲቆጣጠር ያሰለጥነዋል። 4. ከ "ለምን" ወደ "እንዴት" መሸጋገር (Action-Oriented Thinking)፡ "ለምን እንዲህ ሆነ?" ብለን ደጋግመን ማሰባችን መፍትሔ አያመጣም። ጥያቄያችንን እንቀይር። "ለምን ይሄ ደረሰብኝ?" ከማለት ይልቅ "ነገሮች እንዲስተካከሉ አሁን ምን አንድ ትንሽ እርምጃ መውሰድ እችላለሁ?" ወደሚል የመፍትሔ ሐሳብ እንሸጋገር። 5. የ 5 ሰከንድ ህግ (The 5-Second Rule)፡ ከመጠን በላይ ማሰብ ውስጥ ስንገባ ወዲያውኑ ድርጊት ላይ እንድናተኩር ይረዳናል። አንድ ነገር ለማድረግ አስበን ማቅማማትና ማሰብ ስንጀምር፣ ከ 5 ወደ 1 ወደ ኋላ እንቁጠር (5-4-3-2-1) እና ወዲያውኑ ወደ ስራ እንግባ። ይህ ቆጠራ አእምሯችን ሐሳብ እንዲያባዛ የሚሰጠውን ጊዜ ይቆርጥበታል። 6. አእምሮን በሌላ ስራ መጠመድ (Engagement/Flow)፡ አእምሯችን በአንድ ጊዜ ሁለት ተቃራኒ ነገሮችን ማሰብ አይችልም። በጣም ማሰብ ስንጀምር አእምሯችንን ሙሉ ትኩረት በሚፈልግ ሌላ ስራ እንጠምደው። ለምሳሌ፦ መጽሐፍ ማንበብ፣ ስፖርት መስራት፣ ምግብ ማብሰል ወይም የቤት ስራዎችን ማከናወን። ድርጊት ላይ ስንሆን ጭንቀት ቦታ ያጣል። 7. ለራስ ርህራሄ ማሳየት (Self-Compassion)፡ ብዙ ጊዜ የምንጨነቀው በራሳችን ላይ በምናሳየው ወቀሳ ምክንያት ነው። ስህተት ስንሰራ ራሳችንን ከመውቀስ ይልቅ፣ ለምናዝንለት ጓደኛችን እንደምናደርገው ርህራሄ ለራሳችን እናሳይ። "ሰው ነንና እንሳሳታለን፣ አሁን ግን ካለንበት መውጣት እንችላለን" ብለን ራሳችንን እናበረታታ። ማስታወሻ፡ የሐሳብ እስረኝነት (Overthinking) አእምሯችንን የሚቆልፍ የአስተሳሰብ ልማድ እንጂ፣ የማይለወጥ ማንነታችን አይደለም። ከዚህ እስር ቤት ለመውጣት ቁልፉ ያለው በእጃችን ነው። የአእምሯችን ሰላም፣ የሕይወታችን ውበት ነው ! ✍️ Solomon M., Mind Whisper @melkam_enaseb
⤵️
ትኩረት የማጣት እና የመረጋጋት ችግር (Attention Deficit hyperactivity Disorder) - ADHD ADHD ልጆች ላይ ሊከሰት የሚችል የእድገት እክል ነው። አንዳንድ ወላጆች ልጆቻቸውን ከሌሎች በተለየ ትዕግስት የለሽ፣ ቀዥቃዣና አስቸጋሪ ሆነውባቸው መፍትሔ ሲፈልጉ ይታያሉ፡፡ እነዚህ ህፃናት የሚይዙት የሚጨብጡት የሚጠፋባቸው፣ አንድ ነገር ጀምረው አፍታም ሳይቆዩ ሌላ የሚያምራቸው፣ ለመናገርና ለመጠበቅ ትዕግስት የማይኖራቸውና ችኩል ናቸው፡፡ ይህ አይነት የስነባህሪና የስነአእምሮ ችግር ያለባቸው ህፃናት ትኩረት ያጡ፣ ትዕግስት የለሽ ቀዥቃዣነት (ADHD) ህመም ተጠቂዎች ናቸው፡፡ የእነዚህ ህፃናት መሰረታዊ መገለጫዎች፦ - አንድ ነገር ጀምረው በቀላሉ ወደ ሌላ የሚሳቡና አንድን ነገር ጀምሮ ለመጨረስ ትኩረት የሌላቸው - በትምህርት ቤት ግዴለሽነት የሚታይባቸውና ቀላል ስህተቶችን በፈተና ላይ በተደጋጋሚ የሚሰሩ - የማያዳምጡና የተባሉትን የማያደርጉ - የክፍልና የቤት ስራን ጀምሮ ለመጨረስ እንኳን ትዕግስት የሌላቸው - በተሰጣቸው ስራ ላይ ሀሳባቸውን መሰብሰብ የማይችሉ - ዝንጉነት በእጅጉ የሚታይባቸው - በየአቅጣጫው የሚሮጡና እረፍት የሌላቸው፣ ዛፍም ሆነ ደረጃ ላይ ለመውጣት የሚታገሉ - እጅና እግራቸው የሚቅበጠበጥና አደብ የሌላቸው - ከጓደኞቻቸው ጋር እየተጫወቱ ተራቸው አስኪደርስ መጠበቅ ሞት የሚመስላቸው - በቀላሉ የሚበሳጩና የሚናደዱ ናቸው፡፡ ስለዚህም ይህ ትኩረት የለሽነታቸውና ትዕግስት አልባነታቸው የትምህርት አቀባበልና አረዳዳቸውን በእጅጉ ይጎዳዋል። ለዚህ ህመም እንዲህ ነው የሚባል ምክንያት ባይኖርም በእርግዝና ጊዜ አልኮልና ሲጋራ መጠቀም እንደ አጋላጭነት ይጠቀሳሉ፡፡ ዓለም አቀፍ ጥናት እንደሚያሳየው ከሆነ ለትምህርት ከደረሱ ህፃናት መካከል ከ5-10 በመቶ የሚሆኑት ህፃናት ይህ ችግር ሊታይባቸው ይችላል፡፡ አብዛኛው ትኩረት የለሽ ህፃናት በስነ-ልቦና ህክምና፣ በአማራጭ ትምህርት (Special Education) እና በመድሀኒቶች በመታገዝ የሚስተካከሉና መሻሻል ሊያሳዩ ይችላሉ፡፡ ሆኖም አንዳንዶች የጎላ ችግር ያለባቸው ካደጉ በኋላም ራስን ዝቅ ማድረግና ከማህበራዊ ግንኙነቶች ማፈግፈግ ሊታይባቸው ይችላል፡፡ ወላጆች እንዲህ አይነት ባህሪ ያላቸውን ህፃናት በአግባቡ በማሳከምና በቤት ውስጥ ድጋፍና አንክብካቤ በማድረግ ችግራቸውንና የትምህርት አቀባበላቸውን ቀስ በቀስ ማስተካከል ይችላሉ፡፡ በዶ/ር ሄኖክ ዘውዱ (የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስትና የልጅ በእድሉ አይደግ መፅሀፍ ደራሲ) @melkam_enaseb
⤵️
ሰኔ (June) የዓለም አቀፍ የወንዶች የአእምሮ ጤና ወር (Men's Mental Health Month) ነው! ሰኔ በዓለም አቀፍ ደረጃ የወንዶች የአእምሮ ጤና ግንዛቤ የሚፈጠርበት ወር ነው። ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ይህንን ወሳኝ ጽሑፍ ልናጋራችሁ ወደድን። ብዙ ጊዜ ወንዶች የአእምሮ ጭንቀታቸውን፣ ፍርሃታቸውንና ድካማቸውን ደብቀው "ሁልጊዜ ጠንካራ" ለመምሰል ትልቅ ትግል ውስጥ ይገባሉ። ከጥንካሬ ጭንብል ጀርባ (Behind the Mask) "ወንድ ልጅ አያለቅስም!"፣ "ወንድነትህን አሳይ!"፣ "ወንድ አይደለህ እንዴ ምን ያልፈሰፍስሀል?" እነዚህ አረፍተ ነገሮች በማህበረሰባችን ውስጥ ለዘመናት ሲደጋገሙ የኖሩና የወንድ ልጅን ማንነት ከልጅነቱ ጀምሮ የሚቀርጹ ትዕዛዞች ናቸው። ወንድ ልጅ ስሜቱን እንዲደብቅ እና ሁልጊዜም "ጠንካራ" ሆኖ እንዲታይ ሲገፋፋ በሂደት "የጥንካሬ ጭንብል" (The Mask of Strength) ያጠልቃል። ነገር ግን ከዚህ ጭንብል ጀርባ ብዙ ያልታዩ ቁስሎችና የታፈኑ ስሜቶች አሉ። የ"ጥንካሬ ጭንብል" ምንድነው? → በስነ-ልቦና እይታ፤ ወንዶች ማህበራዊ ተቀባይነትን ለማግኘት ሲሉ ድክመቶቻቸውን፣ ፍራቻዎቻቸውንና ስሜታዊ ፍላጎቶቻቸውን የሚደብቁበት ሂደት ነው። ይህም ወንዶች ሰው የመሆን ተፈጥሯዊ ባህሪ የሆነውን ስሜትን የመግለጽ መብታቸውን ይነጥቃቸዋል። ⛔️ ስሜትን አፍኖ መያዝ የሚያስከትለው ስነ-ልቦናዊ ጉዳት (Psychological Impact) 1. የስሜት መታፈን (Emotional Suppression): ስሜቶች ስለታፈኑ አይጠፉም፤ ይልቁንም ቅርጻቸውን ቀይረው በቁጣ(aggression)፣ በከባድ ጭንቀት (Anxiety) ወይም በድብርት (Depression) መልክ ይገለጣሉ። 2. የብቸኝነት ስሜት: ስሜቱን የማይገልጽ ወንድ በሰው መካከል ሆነው "ማንም አይረዳኝም" የሚል ጥልቅ የብቸኝነት ስሜት ያጠቃዋል። 3. የአካል ጤና መታወክ (Psychosomatic Symptoms): የአእምሮ ጤና ችግሮች አካላዊ ቅርጽ ይዘው እንደ ራስ ምታት፣ የልብ ምት መጨመር እና የምግብ ፍላጎት መቀነስን ሊያስከትሉ ይችላሉ። 4. ራስን የመጉዳት አደጋ: ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ወንዶች እርዳታ የመጠየቅ ልምዳቸው ዝቅተኛ በመሆኑ፣ ለከፋ የአእምሮ ቀውስና ለራስ ማጥፋት (Suicide) የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው። ✅ እውነተኛ ጥንካሬ ምንድነው? እውነተኛ ጥንካሬ ማለት ስሜትን መደበቅ ወይም በብዙ ጫናዎች ውስጥ ሆኖ እንደ ጠንካራ መታየት አይደለም። ይልቁንም፦ → የራስን ስሜት በሚገባ መረዳት (Self-awareness) → ህመምንና ድክመትን አምኖ መቀበል → እርዳታ በሚያስፈልግበት ጊዜ ያለ ፍርሃት "እርዳታ እፈልጋለሁ" ብሎ መጠየቅ እውነተኛ ጥንካሬ ነው። 🌱 ማስታወሻ ለራስህ ቃል ግባ፦ ከዛሬ ጀምሮ "ወንድ ልጅ አይለቅስም" የሚለውን የተሳሳተ አስተሳሰብ ሰብረህ፣ ስሜትህን በነጻነት የምትገልጽበት እና ራስህን የምትጠብቅበት ጅማሮ ይሁን። ሌሎችን አበረታታ፦ በዙሪያህ ያሉ ወንዶችን (ጓደኞችህን፣ ቤተሰቦችህን) "እንዴት ነህ? ምን እየተሰማህ ነው?" ብለህ ለመጠየቅ አትዘግይ። አንዳንድ ጊዜ አንድ ጥያቄ የሰው ህይወትን ሊታደግ ይችላል። አንድ ላይ እንሁን፦ የአእምሮ ጤና ለሁላችንም ነው። ጤናማ ወንድ ማለት ስሜቱን የሚደብቅ ሳይሆን፣ ስሜቱን ተረድቶ ራሱን የሚንከባከብ ነው። ወንዶች ሆይ! ስሜታችሁን መግለጻችሁ ወንድነታችሁን አያጎድለውም። ይልቁንም ለራሳችሁ ያላችሁን ክብርና ፍቅር ያሳያል። ህብረተሰባችንም ወንዶች ስሜታቸውን ያለ ፍርሃት የሚገልጹበትን ደህንነቱ የተጠበቀ ምህዳር መፍጠር ይኖርበታል። ማልቀስ፣ ማዘን፣ እና እርዳታ መጠየቅ ሰው የመሆንህ መገለጫዎች እንጂ የድክመትህ ምልክቶች አይደሉም። ✍️ Solomon M., Mind Whisper @melkam_enaseb
⤵️
አዕምሯችንም ይደክማል! ብዙዎቻችን የአካላችንን ድካም በቀላሉ እንረዳዋለን ለምሳሌ እግራችን ሲደክም እንቀመጣለን፣ ትከሻችን ሲዝል ደግሞ ጋደም ብለን ለማረፍ እንሞክራለን። ነገር ግን አዕምሯችን የሰውነታችን ሁሉ መሪ ሆኖ 24 ሰዓት ያለ እረፍት እንዲሠራ እናስገድደዋለን። አዕምሮ ልክ እንደ አካላችን ካልተንከባከብነውና ተገቢውን እረፍት ካልሰጠነው መድከሙ የማይቀር ነው። በየቀኑ በኑሮና በሥራ ሩጫ ውስጥ ስንሆን አዕምሯችን "ደክሞኛል፣ እረፍት እፈልጋለሁ!" እያለ በተለያየ መንገድ ድካሙን ይገልፃል። አንዳንዴ በእንቅልፍ ማጣት፣ አንዳንዴ የማተኮር አቅም በማጣት፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ያለምክንያት ቶሎ በመበሳጨትና በስሜት መለዋወጥ ሊገለፅ ይችላል። ታዲያ እነዚህን ምልክቶች እንደ ቀላል አይቶ ችላ ማለት ለከፍተኛ የአዕምሮ ችግር ሊያጋልጥ ይችላል። የአዕምሮ ጤናን መጠበቅ የሚጀምረው ራስን ከማድመጥና ለራስ ጊዜ በመስጠት ነው። ለአዕምሯችን ጊዜ መስጠትና ማሳረፍ ስንል ምን ማለታችን ነው? - በቂ እንቅልፍ ወስደን አዕምሯችን ራሱን እንዲያድስ እድል በመስጠትና ከመተኛታችን በፊት ከስልክና ሶሻል ሚዲያ በመራቅ አዕምሮ በአግባቡ እንዲያርፍ ማድረግ። - ብቻችንን ከመብሰልሰል ከሰዎች ጋር ተገናኝቶ የውስጥን ጫና እና ጭንቀት ማውራት፤ ስሜትን ለምናምነው የቅርብ ሰው ወይም ለባለሙያ በማጋራት የአዕምሮን ሸክም ማውረድ። - ከዕለት ተዕለት ጩኸት ራቅ ብሎ በንጹህ አየር እና በተፈጥሮ መካከል ጥቂት ደቂቃዎችን በማሳለፍ እንዲሁም ከአደንዛዥ እፆች፣ ከጫት እንዲሁም ከአልኮል ጊዜያዊ መጠለያነት በመራቅ የአዕምሮን ጤና መጠበቅ እና መንከባከብ እንችላለን። (በዶ/ር ኃይለልዑል መኮንን -የአዕምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት) @melkam_enaseb
#የአዕምሮ_ጤና_ግንዛቤ_ወር የሕፃናት አዕምሮ ጤና ! ብዙዎቻችን የአዕምሮ ህመም ትልቅ ሰዎችን ብቻ የሚያጠቃ ይመስለናል። ነገር ግን ልክ እንደ አዋቂዎች ሁሉ የሕፃናትም አዕምሮ ይጨነቃል፣ ይቆስላል፣ ይታመማልም። ባደጉት ሀገራት እንኳ ከ7 ሕፃናት ውስጥ አንዱ ቢያንስ በአንድ የአዕምሮ ጤና እክል ውስጥ እንደሚያልፍ መረጃዎች ያሳያሉ። በሀገራችን ደግሞ ይህ ቁጥር በተለያዩ ማህበራዊ ጫናዎች ምክንያት ከዚህ ሊበልጥ ይችላል። የሕፃናት አዕምሮ ሕክምና ላይ ትልቁ ፈተና ሕፃናት እንደ አዋቂዎች ስሜታቸውን በቃላት መግለጽ አለመቻላቸው ነው። የውስጣቸውን ስሜት እና ህመም የሚገልጹት በባህሪያቸው ነው። ነገር ግን ወላጆችና መምህራን አብዛኛዉን ጊዜ ይህንን የባህሪ መለዋወጥ " ያልተቀጣ ፣ ምግባር የጎደለዉ፣ እልኸኛ ወይም ሰነፍ " እንደሆኑ አድርጎ የመቁጠር ዝንባሌ ይስተዋላል። ነገር ግን ይህ ባህሪ የሕፃኑ አዕምሮ የዉስጡን ህመም የሚገልፅበት መንገድ ሊሆን ይችላል። በሕፃናት ላይ በተደጋጋሚ የሚታዩ ዋና ዋና የአዕምሮ ጤና እክሎች ምንድን ናቸው ? (ለግንዛቤ ያክል የተወሰኑትን እንመልከት) 1. የትኩረት ማጣትና ከመጠን በላይ መቅበጥበጥ (ADHD) ፦ በአንድ ቦታ ረግቶ መቀመጥ ያቅታቸዋል። ወንበር ላይ እያሉ እጅና እግራቸውን ማንቀሳቀስ፣ መጠማዘዝ ወይም ያለ ቦታው መሮጥና መውጣት ያዘወትራሉ። ጥያቄ ተጠይቆ ሳያልቅ መልስ ለመስጠት መቸኮል፣ የሌሎችን ጨዋታ ወይም ወሬ ጣልቃ እየገቡ ማቋረጥ እና ፍላጎታቸው ወዲያውኑ ካልተሟላ ከፍተኛ መበሳጨት ማሳየት። መምህራን ወይም ወላጆች ሲያናግሯቸው በቀጥታ የማይሰሙ ይመስላሉ። ትንንሽ የሆነ የቤት ስራዎችን እና መመሪያዎችን ጨርሶ ከመፈጸም በፊት ቶሎ ይረሳሉ ወይም ይዘናጋሉ። 2. የጭንቀት ህመም (Anxiety Disorders) ፦ ከወላጅ መለየትን አጥብቆ መፍራት፣ አዳዲስ ቦታዎች ላይ ከመጠን በላይ መደንገጥ ወይም ያለምክንያት የሆድ እና የራስ ምታት ማዘውተር። 3. የድባቴ ህመም (Depression) ፦ ከወትሮዉ የተለየ ብስጭት እና ንዴት ወይም ማልቀስ፣ ቀድሞ ይጫወቱባቸው ከነበሩ ነገሮች መራቅ እና ከሰዎች መገለል እንዲሁም በትምህርታቸው ላይ የነበራቸው ፍላጎትና ውጤት በአጭር ጊዜ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆል። 4. ኦቲዝም (Autism Spectrum Disorder) ፦ ከሰዎች ጋር የዓይን ለአይን ግንኙነት አለማድረግ፣ በዕድሜያቸው ልክ መናገር አለመቻል፣ የተደጋገሙ ድርጊቶችን ማዘውተር እና የእለት ተዕለት ልምዳቸው ትንሽ እንኳ ሲቀየርባቸው ከፍተኛ መረበሽ ማሳየት ዋና ምልክቶች ናቸዉ። እነዚህ ምልክቶች በአንድ ሕፃን ላይ ለተከታታይ ሳምንታት ሲታዩ እና የልጁን የትምህርት ፣ የቤት ውስጥ እንዲሁም የማህበራዊ ህይወት #ሲያስተጓጉሉ የሕክምና እርዳታ የሚያስፈልገው የአዕምሮ ጤና ጉዳይ መሆኑን ተረድተን ወደ ባለሙያ በመውሰድ በጊዜ ህክምና ማድረግ አስፈላጊ ነዉ። #የአዕምሮ_ጤና_ግንዛቤ_ወር #የሕፃናት_አዕምሮ_ጤና #MentalHealthAwarenessMonth (በዶ/ር ኃይለልዑል መኮንን - የአዕምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት) @melkam_enaseb
⤵️
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖች፣ እንኳን ለኢድ አል አደሃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ኢድ ሙባረክ! @melkam_enaseb
📌 የአእምሮ እና የአካል ትስስር (Mind-Body Connection) ያለ አእምሮ ጤና፣ የተሟላ ጤና የለም! አካላዊ ጤንነታችን ከአእምሮ ሰላማችን ይጀምራል። ሁላችንም ስለ ጤና ስናስብ አብዛኛውን ጊዜ ትኩረት የምናደርገው በአካላዊ ሕመም ላይ ነው። ነገር ግን አእምሯችንና አካላችን የማይነጣጠሉና ሁልጊዜም የሚገናኙ መሆናቸውን እናስተውል ይሆን? የአእምሯችን ሰላም ለአካላችን ጥንካሬ፣ የአካላችን ደህንነት ደግሞ ለአእምሯችን መረጋጋት ወሳኝ መሠረት ነው። 💠 ጤና ምንድን ነው? የዓለም የጤና ድርጅት (WHO) ጤናን እንዲህ ሲል ይተረጉመዋል፦ > ጤና ማለት ከበሽታ ወይም ከደካማነት ነፃ መሆን ብቻ ሳይሆን፣ የተሟላ አካላዊ፣ አእምሯዊ እና ማህበራዊ ደህንነት ነው (Health is a state of complete physical, mental and social well-being and not merely the absence of disease or infirmity.) 💠 የአእምሮ እና የአካል ትስስር በምሳሌ አእምሯችን የሚሰማው ማንኛውም ስሜት በአካላችን ላይ ቀጥተኛ ለውጥ ያመጣል። ለምሳሌ፦ → ውጥረት (Stress): ስንጨነቅ የልብ ትርታችን ይጨምራል፣ የጡንቻ መወጠር ይፈጠራል እንዲሁም ለራስ ምታት ይዳርገናል። → የበሽታ መከላከል አቅም: ከፍተኛ የሐዘን ወይም የጭንቀት ስሜት የሰውነታችንን በሽታ የመከላከል አቅም (Immune System) ሊያዳክም ይችላል። → የምግብ መፈጨት: ጭንቀትና ፍርሃት በሆድ አካባቢ መረበሽና የምግብ መፈጨት ሥርዓት መዛባትን ያስከትላል። → የኃይል መጠን: የአእምሮ ድካም አካላዊ ድካም እንዲሰማንና የሥራ ተነሳሽነታችን እንዲቀንስ ያደርጋል። አካላዊ ሁኔታችንም በአእምሮአችን ላይ ተፅዕኖ ይፈጥራል። ለምሳሌ፦ → የአንጀትና አእምሮ ትስስር፡ አንጀታችን ውስጥ የሚገኙ ባክቴሪያዎች ለደስታ ስሜት የሚረዳውን Serotonin የተባለ ኬሚካል 90% ያመርታሉ። → የአቋቋም ስነ-ልቦና (Posture) ትከሻችንን ሰብስበንና አንገታችንን ደፍተን ስንቀመጥ አእምሮአችን የጭንቀትና የዝቅተኝነት ስሜት ይላካል። → አካላዊ እንቅስቃሴ፡ ስፖርት ስናደርግ አካላችን እንደ Endorphins እና Dopamine ያሉ "የደስታ ኬሚካሎችን" ያመነጫል። በተጨማሪም አካላዊ እንቅስቃሴ የአንጎል ሴሎችን የሚጠግንና አዳዲስ የነርቭ ግንኙነቶችን የሚፈጥር BDNF የተባለ ፕሮቲን እንዲመረት ያደርጋል። ይህ የማስታወስ ችሎታንና የመማር ብቃትን ይጨምራል። 💠 5 ልምዶች ለተሻለ የአእምሮ እና አካል ትስስር ለተሟላ ጤና እነዚህን ቀላል ግን ውጤታማ ልምዶች በየቀኑ እንተግብር፦ 1. በትኩረት መተንፈስ (Mindful Breathing): በቀን ውስጥ ጥቂት ደቂቃዎችን ወስዶ በጥልቀት መተንፈስ የነርቭ ስርዓታችንን በማረጋጋት ጭንቀትን ይቀንሳል። 2. አካላዊ እንቅስቃሴ: አዘውትሮ መራመድ ወይም ስፖርት መሥራት አእምሯችን "ኤንዶርፊን" (Endorphins) የተባሉ የደስታ ስሜት የሚፈጥሩ ኬሚካሎችን እንዲያመነጭ ይረዳል። 3. የተመጣጠነ ምግብ: የምንመገበው ምግብ ለአንጎላችን ነዳጅ ነው። ጤናማ አመጋገብ የአስተሳሰብ ጥራትን እና የስሜት መረጋጋትን ይጨምራል። 4. ጥራት ያለው እንቅልፍ: በቂ እንቅልፍ አእምሯችን ራሱን የሚጠግንበት እና ሰውነታችን ኃይል የሚያገኝበት ወሳኝ ጊዜ ነው። 5. ስሜትን መረዳት: የሚሰማንን ስሜት (ጭንቀት፣ ደስታ፣ ንዴት) አውቆ መቀበልና በጤናማ መንገድ መግለጽ ለአካላዊ ጤንነታችን ትልቅ መድኃኒት ነው። ማስታወሻ አካላዊ ጤንነታችንን ለመጠበቅ የምናደርገውን ጥረት ያህል፣ ለአእምሯችንም ትኩረት መስጠት የጤናማ ህይወት ቁልፍ ነው፦ → ሰውነታችንን እናዳምጥ፦ ራስ ምታት ወይም የጡንቻ መወጠር ሲሰማን "አእምሮዬ በውጥረት ምክንያት መልዕክት እየላከኝ ይሆን?" ብለን እንጠይቅ። → ለራሳችን ጊዜ እንስጥ፦ ከሥራና ከዲጂታል ዓለም ወጣ ብለን አእምሮአችንን የምናሳርፍበት ጊዜ ይኑረን። ባለሙያዎችን ማማከር፡ አካላዊ ሕመም ሲሰማን ወደ ሕክምና እንደምንሄደው ሁሉ፣ አእምሯዊ ጫናዎች ከአቅማችን በላይ ሲሆኑ የባለሙያ ድጋፍ መፈለግ የጥንካሬ ምልክት ነው። የስነ-ልቦና ምክክር ከአካላዊ ሕመም እንድንጠበቅና የተሟላ ጤና እንዲኖረን ይረዳናል። ለአእምሯችን የሚገባውን እረፍት እንስጠው፤ የጤና ባለቤት እንሁን! Solomon M., Mind Whisper @melkam_enaseb
⤵️
Virtuous/ communal Narcissist (ደግ መሳይ ራስ ወዳዶች) አንዳንድ ናርሲሲስቶች - ደግ መስለው ለመታየት ይሞክራሉ - መካሪዎች እና አነቃቂዎች ናቸው - በበጎ ስራዎች ላይ ይሳተፋሉ - ሃይማኖተኞች እና ሰው አክባሪዎች መስለው ይኖራሉ (በነገራችን ላይ የሃይማኖት ተቋማት ለ Narcissistic ሰዎች ምቹ ናቸው.. ጥቅስ እያጣቀሱ እና hypnotize እያደረጉ ምዕመኑን ሰጥ ለጥ አድርገው እንዲታዘዛቸው ማድረግ ስለሚያስችሏቸው) ግን.. ይህ ሁሉ ከልባቸው አይደለም፤ የማስመሰል እንጂ! እንዲህ የሚያደርጉት ደግ ስለሆኑ ሳይሆን የሰዎችን ቅቡልነት ለማግኘት ሲሉ ነው። ሰውን መልካም በመምሰል ደልለው የውስጣቸውን መሻት ለመፈጸም። That is Their way of manipulation. (እዚህ ጋር አንድ ወሳኝ ጥያቄ መጠየቅ ይኖርብናል.. Altruistic (ምግባረ ሰናይነት) ከምን ይመነጫል? የምር ሰዎች የሚያገኙት ጥቅም ሳይኖር ሌሎችን እንዲሁ ሊረዱ የሚችሉበት አግባብ ይኖርን? መጠኑ ይለያያል እንጂ ሁላችንም ስንረዳ መልካም ለመባል አይደለምን?.. የ virtuous narcissism ትንሽ ለየት ይላል..) ደግሞም...አያንዳንዷን የበጎ አድራጎት ስራዎቻቸውን በደምብ ያስወራሉ። እጃቸውም ሆነ ልባቸው የሚፈታው በካሜራ ፊት ሲሆኑ ነው። ውለታ ይቆጥራሉ። የተበደሉ ወይንም የተገለሉ ሲመስላቸው እንዲህ አድርጌላችሁ.. ብለው ማልጎምጎም እና መገሰጻቸው የማይቀር ነው። የበጎነት ስራዎቻቸውን ኋላ ላይ ቆጥረው ይረከቧችኋል.. 'በጎነታቸው' አላማው የሰዎችን ቅቡልነት ማግኘች፣ 'ጥሩ ናቸው' ተብለው መወደስ ነውና። ይህ External validation ውስጣዊ ባዶነታቸውን በተወሰነ መልኩ ይሞላላቸዋል። እውነት እና ንጋት እያደር ይጠራል እንደሚባል ሁሉ.. ከጊዜያት በኋላ የተደበቀው ማንነታቸው መገለጥ ይጀምራል.. እብሪት እና ከኔ ወዲያ ላሳር ማለት ይጀምራሉ። አንዳንድ ሰዎች የቀደመ 'መልካም መሳይ' ባህሪያቸውን አስበው ሊከራከሩላቸው ይሞክራሉ.. እነሱም እነዚህን የሚከራከሩላቸውን ሰዎች አደላድለው ይይዟቸዋል..እንዲያ ነው እንግዲህ ነገሩ። መውጫ: ያው እነዚህ ሰዎች Narcissistic ለመሆን አቅደው እና አልመው አይደለም የሆኑት..አንድም ይህ ባህሪያቸው የስነልቦና ችግራቸውን ለማስታገስ የሚጠቀሙት defense እንደሆነ ይታመናል.. የስነልቦና ህክምና ማግኘታቸው አንድም ይህን ስም ያልሆነ ራስን የማግዘፍ እና ሌሎችን የማናናቅ ባህሪያቸውን እንዲያጤኑት፣ ሲልም እንዲያስተካክሉት ይረዳቸዋል። ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው (የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት) @melkam_enaseb
⤵️