የቃሉ ገበታ /Word Chart [በአገልጋይ ቃለአብ ካሳዬ]
Статистика“እንኪያስ ምግባቸውን በጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተ ሰዎች ላይ የሾመው ታማኝና ልባም ባሪያ ማን ነው?”— ( ማቴ 24፥45 )
- Последний пост
- 12 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 92
- 1/48двое суток
- 105
- 1/72трое суток
- 113
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
https://youtu.be/JYkNbBJEHhM?si=4jrOQSCGED5HOw3D 👌🙏🤲🤲🤲🙏
የተገባቸው ቀርተው ፣ ያልተገባቸው በሉ። ኢየሱስ “ መንግሥተ ሰማያት ለልጁ ሠርግ ያደረገ ንጉሥን ትመስላለች ” በማለት በምሳሌ አስተምሯል። ( ማቴ 22 ፥ 2) ንጉሡ ታዳሚዎችን ወደ ሠርጉ ይጠሩ ዘንድ ባሮቹን ላከ ። የጥሪ ካርድ ደረሳቸው። እነርሱ ግን ሊመጡ አልወደዱም። እንኳን ንጉሥ ፣ ወዳጅ ሲጠራ “ጠሪ አክባሪ” ብሎ መሄድ ወግ ነው ። ንጉሡ ትኩረቱ የልጁ ሠርግ ላይ ነው። የአባት ፍቅር ለልጅ የሚገለጥበት ፣ ልጁን ቆሞ የሚድርበት ነው። ልጅም በአባቱ ፊት የሚደምቅበት ፣ በታዳሚዎች ዘንድ የሚከብርበት ነው። ስለዚህ ድግሱን ደገሠ ፣ ኮርማዎችና የሰቡት ከብቶች ለዚህ ቀን ወጥተው ታረዱ። ይሁን እንጂ ታዳሚዎች ሳይበሉ ጠገቡ ። ድግሱንም ረግጠው ቀሩ። አንዱ ወደ እርሻው ሌላውም ወደ ንግዱ ሄደ ። ይባስ ብለው የጥሪ ወረቀቱን ሊያደርሱ የሄዱትን አንገላቱ ። ሲያልፍም አንዳንዶችን ገደሉ። የንጉሥ መልእክተኛ በንጉሥ ክብር እንደሚወጣ ረስተዋልና እነዚህ ሰዎች የንጉሡ ቁጣ ወረደባቸው። አጠፋቸው፣ ከተማቸውንም አቃጠለ። ( የኢየሩሳሌም ጥፋት ፣ 70 ዓ.ም ሆነ) ንጉሡም የልጄ የሠርግ ቀን ፣ በመንገድ ለተገኙት ለክፉዎችም ለበጎዎችም ይሆናል አለ። የተገባቸው ቀርተው ያልተገባቸው በሉ። የንጉሡ ልጅ ሠርግ የጸጋ ሆነ። ንጉሥ ታዳሚ ቀረ ብሎ ሠርግ አይሠርዝም። ከክፉዎች ዓመፅ የልጁ ፍቅር በልጦበታል። የልጁ ሠርግ የተገባቸው “ያልተገባቸው” የተባሉት ፣ የልጁ ሠርግ ያልተገባቸው “ይገባቸዋል” የተባሉት ሆኑ። እስራኤል የንጉሡ ልጅ ሠርግ አለፋት። አሕዛብ የነበርነው ግን በምሕረት ተጠርተን ገባን። የቤት ልጆች ቀሩ ፣ የመንገድ ልጆች ገባን ። ባለቤቶች ቀሩ፣ እንግዶች ገባን። ነገር ግን አንመካም። ለእኛ ምሕረት በዝቷል። ለእነርሱም ተስፋ ቀርቷል። “ ወንድሞች ሆይ፥ ልባሞች የሆናችሁ እንዳይመስላችሁ ይህን ምሥጢር ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፤ የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ ድንዛዜ በእስራኤል በአንዳንድ በኩል ሆነባቸው፤እንደዚሁም እስራኤል ሁሉ ይድናል፤ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፦ መድኃኒት ከጽዮን ይወጣል ከያዕቆብም ኃጢአተኛነትን ያስወግዳል። ኃጢአታቸውንም ስወስድላቸው ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው። ” ( ሮሜ 11 ፥ 25 -27) ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን ! አገልጋይ ቃለአብ ካሳዬ https://t.me/yekalugebeta
“የሕዝብ ማኅበር ሁላችሁ፥ በእርሱ ታመኑ፥ ልባችሁንም በፊቱ አፍስሱ፤ እግዚአብሔር ረዳታችን ነው።” ( መዝ.62፥8) ግለሰብ ይቅርና ሕዝብ ቢታመንበት የማያሳፍር ፣ ልባችንን በፊቱ ብናፈስስ የማያከስር ፣ በፈጣን ረዳትነቱ ፣ በማይነጥፍ መልካምነቱ ሕይወትን የሚያሳምር -የእኛ አምላክ እግዚአብሔር ይባላል ።🙏🙈
ውኃው ፣ ደሙ እና መንፈሱ “ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው። ኢየሱስም የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ከሚያምን በቀር ዓለምን የሚያሸንፍ ማን ነው ? በውኃና በደም የመጣ ይህ ነው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ፤ በውኃውና በደሙ እንጂ በውኃው ብቻ አይደለም። መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው።የሚመሰክሩት መንፈሱና ውኃው ደሙም ሦስት ናቸውና፤ ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ። የሰውን ምስክር ብንቀበል የእግዚአብሔር ምስክር ከእርሱ ይልቅ ይበልጣል፤ ” (1ኛ ዮሐ .5፥ 4 -9) ከቁ .4 እስከ 8 ድረስ የምናገኘው ጥልቅ አሳብ ስለኀብረቱ ምስክሮች ነው። ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋል። ዓለም ማለት የሥጋ ምኞት ፣ የዓይን አምሮት እና ስለገንዘብ መመካት መሆኑን አይተናል ( ዮሐ. 2፥16) በእምነት በኩል ፣ በዳግም ልደት ከእግዚአብሔር በመወለዳችን ከመለኮቱ ባሕርይ በመካፈል ክፉ ከሆነው ዓለም ድነናል። (ገላ. 1፥4 ፤ 2ኛ. ዼጥ.1፥4) በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን በጸጋ መዳናችን ከኃጢአት በላይ እንጂ ከኃጢአት በታች እንዳንኖር ስላደረገን በድል የመመላለስ አቅምን እንደተቀበልን የአዲስ ኪዳን እውነታ ነው። ዓለምን የሚያሸንፈው እምነታችን ነው። “ኃጢአት አይገዛችሁምና፤ ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና።” ( ሮሜ .6 ፥14 ) አማኝ፦የጸጋውን መዳን በእምነት ተቀብሏል ( ኤፌ 2፥8) በዚሁ እምነትም ይኖራል ( ዕን ፣ ሮሜ 1፥17 ፤ ገላ 3፥11 ፤ ዕብ 10፥38) ። ዛሬ ከእግዚአብሔር የተወለዱ በዓለም ሲሸነፉ እናያለን። ይሁን እንጂ ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ የእግዚአብሔር ቃልና መንፈስ በውስጡ ስለሚኖር ዓለምን ማሸነፍ እንደሚችል ግልጽ ነው። በመወለድ ባሕሪውን ስንካፈል ከዓለም እንደተለየን እንዲሁ በአስተሳሰባችንና በአኗኗራችንም ከዓለም ልንለይ ይገባናል። ቁ. 5 ላይ: - “ኢየሱስም የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ከሚያምን በቀር ዓለምን የሚያሸንፍ ማን ነው? ” በማለት ሐዋርያው እምነታችን የቆመበትን መሠረት ይነግረናል። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ከሚያምን በቀር ዓለምን የሚያሸንፍስ ማነው? በማለት ይጠይቃል። ይህን ያለበት ምክንያት በዘመኑ የነበሩት የኖስቲስ የስህተት ትምህርት “አስተማሪዎች” በሥጋ የመጣው ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን የማያምኑ ስለነበሩ ነው ። ዓለምንና በዓለም ያሉትን በማሸነፍ ድልን የመቀዳጀት ምስጢር በራሳችን ላይ ባለን እምነት ሳይሆን በክርስቶስ ላይ በሚኖረን እምነት ነው። እርሱም፥ “በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ ” ስላለ የእርሱን ድል ለመካፈል በእርሱ ማመን ትክክለኛው ውሳኔ ነው ። ( ዮሐ. 16 ፥33 ) ሐዋርያው በእርሱ ያለን እምነት እና ከእርሱ ጋር ያለን ኀብረት ምስክሮች እንዳሉት ከቁ .6-8 እንዲህ በማለት ይገልጽልናል:- “በውኃና በደም የመጣ ይህ ነው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ፤ በውኃውና በደሙ እንጂ በውኃው ብቻ አይደለም።መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው። የሚመሰክሩት መንፈሱና ውኃው ደሙም ሦስት ናቸውና፤ ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ። ” በዚህ ክፍለ ምንባብ ደግሞ፦ በውኃ እና በደሙ እንደመጣ ፣ በሦስቱም ማለትም በውኃውና በደሙ በመንፈሱም እንደተመሰከረለት ይነግረናል ። ብሉይ ኪዳን ሁለት ወይም ሦስት ምስክር እንደሚጠይቅ ይታወቃል ( ዘዳ. 17፥ 6 ፤ 19 ፥15 ፤ 1ኛ. ጢሞ .5፥19 ) ☞ የመጀመርያው ምስክር ፦ውኃው - ኢየሱስ የመጣው በውኃ እና በደም ነው። ውኃው በዮርዳኖስ ወንዝ የተፈጸመውን የእርሱን ጥምቀት ያመለክታል። በዚህም ጊዜ አብ ከሰማይ ድምፅ አሰምቶ፦ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው ”ብሏል። ( ማቴ 3፥ 13-17) በተመሳሳይ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ እንደ ርግብ ወርዶ በራሱ ላይ አርፏል። ይህ በአገልግሎቱ መጀመርያ አብ ስለልጁ የሰጠው ምስክርነት ነበር ። ☞ ሁለተኛው ምስክር ፦ደሙ - ኢየሱስ የሚሞትበት ጊዜ እየቀረበ ሲመጣ አብ ተጨማሪ ምስክርነት ሰጥቷል። ልጁ:- “አባት ሆይ፥ ስምህን አክብረው ” ባለው ጊዜ አባት ከሰማይም ድምፅን አሰምቶ፦“ ስለዚህም፦ አከበርሁት ደግሞም አከብረዋለሁ የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ።” ( ዮሐ.12፥28) እንዲሁም ኢየሱስ መስቀል ላይ በነበረ ጊዜ አብ በተአምራታዊ ኃይል መስክሯል ፣ ይህም ጨለማ ፣ የምድር መንቀጥቀጥ ፣ የመቅደስ መጋረጃ መቀደድ ፣ የሙታን መነሣት የሆነበት ክስተት ነበር። ( ማቴ. 27፥45 ፣ 50 - 53)ስለሆነም ፣ በአካባቢው የነበረው መቶ አለቃ፦“ ይህ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ ”ብሎ መጮኹ የሚያስደንቅ አይሆንም ( ማቴ 27፥ 54) ☞ ሦስተኛው ምስክር፦ መንፈሱ - መንፈስ ቅዱስ የመጣበት አንዱና ዋና ዓላማ ስለክርስቶስ እንዲመሰክር ነው። ( ዮሐ. 15፥26 ፤16፥14) መንፈስ ቅዱስ የእውነት መንፈስ ስለሆነ ምስክርነቱን ልናምን እንችላለን ። እኛ ኢየሱስ ሲጠመቅ ወይም ሲሞት አልነበርንም ።ይሁን እንጂ በወንጌል እውነት የሰማነውን መንፈስ ቅዱስ ለልባችን ስለመሰከረልን አምነን የዘላለምን ሕይወት አግኝተናል። ውኃውና ጥምቀቱ የኢየሱስ ክርስቶስን በምድር የነበረውን አገልግሎት ሙሉ ምስል ያሳዮናል። አገልግሎቱን በጥምቀት እንደጀመረ በመስቀል ፈጽሞታልና። ሐዋርያው ዮሐንስ፦ኢየሱስ በውኃውም ( በጥምቀቱም) በደሙም ( በስቅለቱም ) ከአብ ዘንድ ምስክርነት እንዳገኘ መጻፍ ለምን አስፈለገው ? ስንል ፦ ኖስቲሶች፦ “ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ክርስቶስ፥ የሰው ልጅ በሆነው ኢየሱስ ላይ የወረደበት በጥምቀቱ ጊዜ ሲሆን ፣ በመስቀል ከመሰቀሉ በፊት ትቶት ሄዷል ” ብለው ያስተምሩ ስለነበር ነው። ሐዋርያው በውኃውና በደሙ ስለነበረው ስለአብ ምስክር ብቻ ሳይሆን ስለመንፈስ ቅዱስ ምስክርነትም ሲናገር፦“ መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው።”( ቁ.7) ሲል አስረግጧል። በመቀጠልም በቁ .9 ላይ፥“የሰውን ምስክር ብንቀበል የእግዚአብሔር ምስክር ከእርሱ ይልቅ ይበልጣል፤ ስለ ልጁ የመሰከረው የእግዚአብሔር ምስክር ይህ ነውና።” ይላል ሐዋርያው እየተናገረ ያለው ግልጽ ነው። ስለክርስቶስ ከሰው ምስክርነት መቀበል ይቻላል። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ስለልጁ የመሰከረው ከሁሉ ይበልጣል። ወዳጆቼ በዚህ እውነተኛ ምስክርነት ሁላችንንም ያጽናን ። ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን አገልጋይ ቃለአብ ካሳዬ https://t.me/yekalugebeta
без подписи
без подписи
https://youtu.be/Zsv9qvJzWTw?si=dW93yKb-qV8mNyo6
“በድክመትህ ወቅት ጠንካራ ሁን ፣ በጥንካሬህ ወቅት ደካማ ሁን !”
ለክርስቶስ መኖር ( ክፍል -2) ☞ ጌታንና ሰዎችን እንውደድ ኢየሱስ እግዚአብሔርንና ሰዎችን መውደድ ፍጹም ትእዛዛት መሆናቸውን አስተምሯል ።() ይህም ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር የምንገልጠው ለሰዎች በምንገልጠው መልካምነት ፣ ቅንነት እና ርኅራኄ መሆኑን ያመለክታል።የጌታ መሆናችን የሚታወቀው በምንጠራበት የእምነት ተቋም ( Denominations)ሳይሆን በእውነተኛ ፍቅራችን ነው ።( ዮሐ .13፥35 ፤ 1ኛ. ዮሐ. 3፥18) ☞ለኃጢአት ባለን ወጥ አቋም አማኝ በክርስቶስ በማመን ከኃጢአት እና ከሞት አምልጦ የእግዚአብሔርን ጽድቅ እና ቅድስናን ወርሷል ። (1ኛ ቆሮ .1፥31) ስለዚህ በማንነት እና በአቋም ደረጃ ከኃጢአት ጋር ጠላት ነው ። ስለዚህ በእግዚአብሔር ቃል እና ታላቅ ጸጋ፥ “ዓለማዊ ምኞትንና ኃጢአተኝነትን ” እየካደ ይኖራል ። ይሁን እንጂ በደካማ ( ባልተዋጀ) ሥጋ ፣ በወደቀ ዓለም እና በመንፈሳዊ ውጊያ መኻል ስለሚኖር ሊበድልና ኃጢአትን ሊሠራ ይችላል ። በዚህ ጊዜ ለኃጢአት ለዘብተኛ የሚሆን ሳይሆን፥ በጌታ ፊት ኃጢአቱን የሚናዘዝ እና በደሙ የሚነጻ መሆን አለበት ።(1ኛ. ዮሐ 1፥8) ለክርስቶስ መኖር ፣ ክርስቶስ ለኃጢአት ባለው ጭከና ላይ የተመሠረተ ነው ። ለክርስቶስ ለመኖር ከኃጢአት አርነት(ነጻነት) እንጂ በኃጢአት ባርነት አይደለም ። ☞ በቤተክርስትያን ከቅዱሳን ጋር ኅብረት እናድርግ በቅዱሳን ኅብረት መካከል፦አምልኮ ፥ ትምህርት ፣ጸሎት እና የጌታን ራት መካፈል በመንፈሳዊ እድገት ለክርስቶስ ለመኖር በጣም ጠቃሚ ነገሮች ናቸው ።( ሐዋ .2፥42) የመዳን ጥሪ በግል ደርሶን ይሆናል እንጂ በግል እና ለግል የምንኖረው የክርስትና ሕይወት ግን የለንም ።( ማቴ 18፥20) በቅዱሳን ኅብረት መካከል ፦በየዋህነት ፣ በገርነት ፣ በትዕግስትና በማስተዋል በመኖር ክርስቶስን ለሌሎች ማንጸባረቅ አለብን ። (ኤፌ 4፥2-4) የእግዚአብሔር ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን ! አገልጋይ ቃለአብ ካሳዬ https://t.me/yekalugebeta
በክርስትና በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ በመንፈስ መሆን ማለት ❝ በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር ❞ መሆን ማለት ነው ። ልትቆጣጠሩት በማትችሉት ነገር መኻል እናንተንም ሆነ ጉዳያችሁን የመቆጣጠር አቅም የመንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው ። እኔ እንዲህ ልባርካችሁ ዘመናችሁ እና ሁኔታችሁ ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር ይኑርላችሁ ። እርሱ ከማረጋጋት ባለፈ በሰላም የሚያጥለቀልቅ መንፈስ ነው ! ደስ ብሏችሁ ዋሉ 🤝
без подписи
ሰላም ቤተሰብ ቀጣዩን ማስታወቂያ ሰምታችሁ ከወንድማችን አገልጋይ ያሬድ ዮሐንስ አገልግሎት እንድትጠቀሙ አበረታታለሁ ።👇👇👇
https://t.me/lera_koinonia
የቃሉ ገበታ ቤተሰቦቼ ፤ እስቲ ሌላ አንድ የቴሌግራም መንፈሳዊ ቻናል ላስተዋውቃችሁ ።ጸሐፊው ወዳጄ ወንድም ሆነልኝ ሲሆን ፣ ቻናሉ ደግሞ “ ቅዱስ ማኅበር ” ይባላል ። ጸሐፊው “ለመንፈሳዊ ሕንጸት ” የሚጠቅሙ ግልጽነት ያላቸውን መንፈሳዊ ጽሑፎች ያቀርባል ። የመንፈሳዊ ሕይወት እውነታዎችን በፍቅርም በቁጣም በግልጽ ቋንቋ ይሞግታል። አጠገባችሁ ሆኖ የሚያወራችሁ ይመስላችኋል ። ከፈለጋችሁም እዚሁ ቴሌግራሙ ላይም ላይቭ ጸሎትና ምክክርም ፕሮግራም አለው ። በሉ ሊንኩ ከታች አለ እናንተ ። የምትወዱኝ ሁሉ ተቀላቀሉት ። እያየሁዋችሁ ነው !😊 👇👇👇
без подписи
ለክርስቶስ መኖር ( ክፍል 1) ለክርስቶስ መኖር ትግል ( Hardship) አይደለም። ለክርስቶስ መኖር ፦እርሱን ማወቅ ፥ በእርሱ መታመንና ወደ እርሱ መልክ ለማደግ የሚደረግ የፍቅር ጉዞ ነው። ለክርስቶስ ስለመኖር ስናስብ ቀጣዮችን መንፈሳዊ እውነታዎችን ብንለማመድ እጅግ መልካም ነው ። ☞ እምነታችንን በክርስቶስ ላይ እናጽና የእምነታችን ጀማሪው እና ፈጻሚው ክርስቶስ ነው። (ዕብ.12 ፥1-2) እንደምናውቀው በሚያናውጠን በብዙ ፈተና እና መከራ መካከል እናልፋለን።ስለዚህ ጌታን በማመን የጀመርነውን ሕይወት እስከ መጨረሻው አጽንተን ለመያዝ መወሰን አለብን። “የመጀመሪያ እምነታችንን እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ፥ የክርስቶስ ተካፋዮች ሆነናልና፤” ( ዕብ. 3፥14) ☞ መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብና በመታዘዝ እንከናወን እግዚአብሔር ፈቃድ ያለው አምላክ ብቻ ሳይሆን ፈቃዱንም የገለጠ አምላክ ነው። ፈቃዱም የተገለጠው በቃሉ ነው። ለሕይወት የኾነው እምነታችን ( ሮሜ .10፥17) እና ምልልሳችን ( ያዕ .1፥23 ) የሚለካው በቃሉ ነው። ብዙ ክርስትያኖች ፈቃዱን ማወቅ ይፈልጋሉ ፣ቃሉን ማወቅ ግን አይፈልጉም። ይሁን እንጂ በየዕለቱ ቃሉን ስናጠና የፈቃዱ ምክር እንደማለዳ ብርሃን እየደመቀልን ይመጣል።ፈቃዱን ስንረዳና ከእርሱ ጋር ፍቅር እየበዛልን ሲመጣ ደግሞ ፥ ጸጋው ለፈቃዱ የመኖርን አቅም ይሰጠንና ወደ መታዘዝ እናድጋለን። “እንደ ትእዛዛቱም እንሄድ ዘንድ ይህ ፍቅር ነው፤ ከመጀመሪያ እንደ ሰማችሁ፥ በእርስዋ ትሄዱ ዘንድ ትእዛዙ ይህች ናት።”(2ኛ ዮሐ .1፥6) ☞ ሳናቋርጥ እንጸልይ ጸሎት የሃይማኖት መመሪያ አይደለም። ጸሎት በእግዚአብሔር አባትነት እና በእኛ ልጅነት መካከል ያለ የኅብረት ሕይወት ነው።ስለዚህ ለዘወትር ልንከታተለው እንችላለን። “በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ ”(ኤፌ .6፥18 ) በዕለታዊ ሕይወታችን ደስታችንን ፣ ኅዘናችንን ፣ ፍርሃታችንን ...ለእግዚአብሔር ልናስታውቅ እንችላለን። እግዚአብሔርም በቃሉ ፣ በጸጋው እና በመንፈሱ ሊያጽናናን ፥ ሊያበረታን ፥ ሊያጸናን እና ምሪትን ሊሰጠን የታመነ ነው።ምክንያቱም ክርስትና ጌታን በመስማት እንጂ በግምት አይደለምና ። (መዝ .25 ፥9) ይቀጥላል .... ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን አገልጋይ ቃለአብ ካሳዬ https://t.me/yekalugebeta
ለራሳችሁ የምትሰጡት ትርጉም እግዚአብሔር ስለ እናንተ የሚለውን ይሁን ። እግዚአብሔር መልካም እና ትክክል ነው ! ❤
без подписи
በደጅ ( በማኅበረሰብ መኅል ፣ በሥራ ቦታ ፤ በአደባባይ ያለው የክርስትና ሕይወታችን) የክርስትና ሕይወታችን በውጭ ላሉት ( To the Out siders) ማለትም፦ለማያምኑትም ሆነ ፣ ለደካማ አማኞች ክርስቶስን የሚያሳይ መኾን አለበት ። የክርስትና ሕይወታችን በደጅ ባሉት ዘንድ መልካም መሆን የሚኖርበት ለምንድነው ? ① እግዚአብሔር እንዲከብር ☞ “ መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።” ( ማቴ ፥16) ② ዘመንን ለመዋጀት “ዘመኑን እየዋጃችሁ፥ በውጭ ባሉቱ ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ።”( ቆላስ .4፥5) ③ ለክርስቶስ ብቁ ምስክር ለመኾን በደጅ ፥ በአግባቡ የምንኖረው የተገለጠ የክርስትና ሕይወታችን ለወንጌል ምስክርነት ጠንካራ መሠረት ነው። በደጅ ያሉት እያንዳንዱ እንቅስቃሴያችንን ያስተውላሉ። “ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን። ” (1ኛ ጴጥ. 2፥12 ) ④ ሕሊናችን እንዳይፈርድብን ☞ “ ጸልዩልን፤ በነገር ሁሉ በመልካም እንድንኖር ወደን፥ መልካም ሕሊና እንዳለን ተረድተናልና።” (ዕብ. 13፥18) ☞ “በክርስቶስ ያለውን መልካሙን ኑሮአችሁን የሚሳደቡ ሰዎች ክፉን እንደምታደርጉ በሚያሙበት ነገር እንዲያፍሩ በጎ ሕሊና ይኑራችሁ።”(1ኛ. ጴጥ.3፥16 ) ☞ “ስለዚህ እኔ ደግሞ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ሁልጊዜ ነውር የሌለባት ሕሊና ትኖረኝ ዘንድ እተጋለሁ።”(ሐዋ. 24፥16) ⑤ የወንጌል ተቃዋሚ እንዲያፍር “ የሚቃወም ሰው ስለ እኛ የሚናገረውን መጥፎ ነገር ሲያጣ እንዲያፍር፥ በነገር ሁሉ መልካምን በማድረግህ ምሳሌ የሚሆን ራስህን አሳይ፤ በትምህርትህም ደኅንነትን፥ ጭምትነትን፥ ጤናማና የማይነቀፍ ንግግር ግለጥ።” ( ቲቶ .2፥7-8) ⑥ ሰዎችን ለክርስቶስ ለመማረክ “ሚስቶች ሆይ፤ እናንተም እንዲሁ ለባሎቻችሁ ተገዙ ፤ አንዳንድ ለቃሉ የማይታዘዙ ቢኖሩ ፣ ያለ ቃል በሚስቶቻቸው አኗኗር ተማርከው ይመለሳሉ፤ ይህም የሚሆነው ንጹሕና ፍጹም አክብሮት የተሞላውን ኑሮአችሁን ሲመለከቱ ነው። ( 1ኛ ጴጥ .3፥1 ዓ.መ.ት ) ቤተሰቦቼ፥ ሕይወታችን ወደ ታች ሥር ከሰደደ ( ቆላስ .2፥ 7) ፤ ወደ ላይ በእርሱ ከታነጸ ( ቆላስ .2፥7) ወደ ውስጥ ለኃጢአት የሞተው ማንነታችን ከክርስቶስ ጋር ከተሰወረ ( ቆላስ .3 ፥3) ከላይ ለተዘረዘሩት ምክንያቶች ደግሞ ወደ ውጭ መገለጥ አለበት ( ቆላስ .4 ፥5) የእግዚአብሔር ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን!
በምሕረቱ መታመን