tgindex
የማለዳ ፀሎት

የማለዳ ፀሎት

Статистика
@yemaledatselotанглийский

ይህ ቻናል የተከፈተው በተለይ የማለዳ ፀሎትን ለማበረታታት ነው። የእግዚአብሔርን ፊት በግል እና በጋራ በየቀኑ ከማለዳው 10-12 ሰዓት እንፈልጋለን። Come and let's Pray and seek God's face together. #Prayer #Teaching #Pentecost #Power #Holy_Spirit #ፀሎት #Worship

Последний пост
18 июл.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 670
+8 за 4 дн.
Сутки
+5
+0,30%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
951
20 постов
Вовлечённость
56,9%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 🕊የእግዚአብሔር ቃል ስለ እግዚአብሔር ጥበቃ ምን ይላል? (ክፍል 1/3) የእግዚአብሔር ቃል ጠባቂያችን ብርቱ እና አስተማማኝ ስለሆነ በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብንሆን ልንፈራ፣ ልንሸበር፣ ተስፋ ልንቆርጥ ፈጽሞ እንደማይገባን ይነግረናል። የምናመልከው አምላክ ብርቱ ነው! “የእግዚአብሔር ስም የጸና ግምብ ነው፤ ጻድቅ ወደ እርሱ ሮጦ ከፍ ከፍ ይላል።” — ምሳሌ 18፡10 “በጥፋትና በራብ ላይ ትስቃለህ፤ ከምድረ በዳ አራዊትም አትፈራም፤” — ኢዮብ 5፡22 “ተስፋም ስላለህ ተዘልለህ ትቀመጣለህ፤ በዙሪያህ ትመለከታለህ፥ በደኅንነትም ታርፋለህ። ትተኛለህ፥ የሚያስፈራህም የለም፤ ብዙ ሰዎችም ልመና ያቀርቡልሃል።” — ኢዮብ 11፡18-19 “ፀሐይ በቀን አያቃጥልህም ጨረቃም በሌሊት። እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፥ ነፍስህንም ይጠብቃታል።” — መዝሙረ ዳዊት 121፡7-8 “በተኛህ ጊዜ አትፈራም፤ ትተኛለህ፥ እንቅልፍህም የጣፈጠ ይሆንልሃል።” — ምሳሌ 3፡24 “በጎንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማን ነው?” — 1ኛ ጴጥሮስ 3፡13 🙏 የዛሬ ማለዳ የፀሎት አቅጣጫ፦ እግዚአብሔር አምላካችንን አብረነው በትህትና ከተጓዝን አብሮን ስለሚሆን፥ የደካሞችንም ጩኸት ስለሚሰማ፥ ከወደረኞቻችን እና ከጠላቶቻችን ሊታደገን ስለሚችል በእርሱ ተማምነን ተደግፈን መውጣት ስለሆነልን እናመስግነው። ታዳጊያችን ብርቱ ነው! የሚጨነቅ፥ የሚፈራ እና የሚደነግጥ ካለ በእነዚህ ቃሎች አጽናኑአቸው። 💬ተወያዩበት፦ በዚህ ጉዳይ ላይ ማካፈል የምትፈልጉት ካለ ከታች ባለው ሊንክ መጻፍ ይችላሉ። 👉 ሐሳብዎን እዚህ ያጋሩ (https://telegram.me/+VOtOuzSRe9kHdFxJ) 👈 👉 [ ✝️🀄️ላ🀄️ሉን ] 👈 🙏 @yemaledatselot 🙏 🙏 @yemaledatselot 🙏 🙏 @yemaledatselot 🙏 #Hope #Protection #Pray #Comfort

  • 🕊የእግዚአብሔር ቃል ስለሞት ምን ይላል? (ክፍል 2/2) የእግዚአብሔር ቃል ሞት ሊያስፈራን እንደማይገባ እና እግዚአብሔር በሞት ላይ ሥልጣን እንዳለው ይነግረናል። “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ለዘላለም ሞትን አያይም።” — ዮሐንስ 8፡51   “እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ።” — ዕብራውያን 2፡14-15   “ሞት ሆይ፥ መውጊያህ የት አለ? ሲኦል ሆይ፥ ድል መንሣትህ የት አለ?” — 1 ቆሮንቶስ 15፡55   “ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን።” — ሮሜ 5፡9   “ስለዚህም አንታክትም፥ ነገር ግን የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳ የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል።” — 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡16   “ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።” — ዮሐንስ 3፡14-15   “ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።” — ሮሜ 8፡38-39   “ታላቅም ድምፅ ከሰማይ፦ እነሆ፥ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው ከእነርሱም ጋር ያድራል፥ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤ እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።” — የዮሐንስ ራዕይ 21፡3-4   🙏 የዛሬ ማለዳ የፀሎት አቅጣጫ፦ዛሬ ስለወደፊቱ እና ስለሞት እየተጨነቃችሁ ካላችሁ እነዚህን ጥቅሶች አንብባችሁ አባታችን እግዚአብሔር በመንፈሱ እንዲያጽናናን እና ልባችንን እንዲያበረታን እንጠይቀዋለን። የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሆናል። በእንደዚህ አሳብ የተጨነቀ የምታውቁ ካለ ሼር አድርጓቸው። ሌሎችም ወደዚህ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ እንዲሆኑ ጋብዟቸው። 💬ተወያዩበት፦ በዚህ ጉዳይ ላይ ማካፈል የምትፈልጉት ካለ ከታች ባለው ሊንክ መጻፍ ይችላሉ።  👉 ሐሳብዎን እዚህ ያጋሩ 👈 👉 [ ✝️🀄️ላ🀄️ሉን ] 👈 🙏 @yemaledatselot 🙏 🙏 @yemaledatselot 🙏 🙏 @yemaledatselot 🙏 #Hope #Grief #Pray #Comfort

  • 🕊የእግዚአብሔር ቃል ስለሞት ምን ይላል? (ክፍል 1/2) የእግዚአብሔር ቃል ሞት ሊያስፈራን እንደማይገባና እግዚአብሔር በሞት ላይ ሥልጣን እንዳለው ይነግረናል። “ነገር ግን እግዚአብሔር ይቀበለኛልና ነፍሴን ከሲኦል እጅ ይቤዣታል።” — መዝሙረ ዳዊት 49፡15 “ሞትን ለዘላለም ይውጣል፥ ጌታ እግዚአብሔርም ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፥ የሕዝቡን ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል፤ እግዚአብሔር ተናግሮአልና።” — ትንቢተ ኢሣይያስ 25፡8 “ከሲኦል እጅ እታደጋቸዋለሁ፥ ከሞትም እቤዣቸዋለሁ፤ ሞት ሆይ፥ ቸነፈርህ ወዴት አለ? ሲኦል ሆይ፥ ማጥፋትህ ወዴት አለ? ርኅራኄ ከዓይኔ ተሰወረች።” — ትንቢተ ሆሴይ 13፡14 “በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።” — መዝሙረ ዳዊት 23፡4 “የልቤ አምላክ ሆይ፥ ልቤና ሥጋዬ አለቀ፤ እግዚአብሔር ግን ለዘላለም እድል ፈንታዬ ነው።” — መዝሙረ ዳዊት 73፡26 🙏 የዛሬ ማለዳ የፀሎት አቅጣጫ፦ዛሬ ስለወደፊቱ እና ስለሞት እየተጨነቃችሁ ካላችሁ እነዚህን ጥቅሶች አንብባችሁ አባታችን እግዚአብሔር በመንፈሱ እንዲያጽናናን እና ልባችንን እንዲያበረታን እንጠይቀዋለን። የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሆናል። ቀጣዩን ክፍል ነገ ይላካል። በእንደዚህ አሳብ እየተጨነቁ ያሉ የምታውቁ ካለ ሼር አድርጓቸው። ሌሎችም ወደዚህ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ እንዲሆኑ ጋብዟቸው። 💬ተወያዩበት፦ በዚህ ጉዳይ ላይ ማካፈል የምትፈልጉት ካለ ከታች ባለው ሊንክ መጻፍ ይችላሉ።  👉 ሐሳብዎን እዚህ ያጋሩ 👈 👉 [ ✝️🀄️ላ🀄️ሉን ] 👈 🙏 @yemaledatselot 🙏 🙏 @yemaledatselot 🙏 🙏 @yemaledatselot 🙏 #Hope #Grief #Pray #Comfort

  • መዝሙር 31 ¹አቤቱ አንተን ታመንሁ፤ ለዘላለም አልፈር፤ በጽድቅህም አድነኝ። ²ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፥ ፈጥነህም አድነኝ፤ ታድነኝ ዘንድ መታመኛ አምላክና የመጠጊያ ቤት ሁነኝ። ³አምባዬና መጠጊያዬ አንተ ነህና፡ ስለ ስምህ መንገዴን አቅና ምራኝም። ⁴አንተ መታመኛዬ ነህና፡ ከደበቁብኝ ወጥመድ አውጣኝ።

  • 6 июл.867186

    መዝሙር 124 ¹እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን፡ እስራኤል እንዲህ ይበል፦ ²“እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን፡ ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፥ ³ቍጣቸውን በላያችን በነደደ ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር፤ ⁴በዚያን ጊዜ ውኃ ባሰጠመን ነበር፥ በነፍሳችንም ላይ ፈሳሽ ባለፈ ነበር፤ ⁵በዚያን ጊዜ የጐርፍ ውኃ በነፍሳችን ላይ ባለፈ ነበር። ⁶ለጥርሳቸው ንክሻ ያላደረገን እግዚአብሔር ይባረክ። ⁷ነፍሳችን እንደ ወፍ ከአዳኞች ወጥመድ አመለጠች። ወጥመድ ተሰበረ እኛም አመለጥን። ⁸ረድኤታችን ሰማይንና ምድርን በሠራ፡ በእግዚአብሔር ስም ነው።”

  • без подписи

  • መዝሙረ ዳዊት 70 ¹አቤቱ፥ እኔን ለማዳን ተመልከት፤ አቤቱ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን። ²ነፍሴን የሚሹአት ይፈሩ ይጐስቍሉም፥ ክፉንም የሚመክሩብኝ ወደ ኋላቸው ይመለሱ ይፈሩም። ³እንኳ እንኳ የሚሉኝ አፍረው ወዲያው ወደ ኋላቸው ይመለሱ። ⁴የሚሹህ ሁሉ በአንተ ሐሤት ያድርጉ ደስ ይበላቸው፤ ማዳንህን የሚወድዱ ሁልጊዜ፦ እግዚአብሔር ታላቅ ነው ይበሉ። ⁵እኔ ችግረኛና ምስኪን ነኝ፤ አቤቱ፥ እርዳኝ፤ ረዳቴ ታዳጊዬም አንተ ነህ፤ አቤቱ፥ አትዘግይ።

  • https://youtube.com/playlist?list=PLpPSLDwJycDVgh4ZQOECOxLvngiOWK6Ml&si=YxFBorXQNWpCbjAx

  • 13 июн.1 126182

    ኤፌሶን 1 ³በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። ⁴ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን። ⁵በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን። ⁷በውድ ልጁም እንዲያው የሰጠን የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ ይህን አደረገ። ⁷በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት። ⁸ጸጋውንም በጥበብና በአእምሮ ሁሉ አበዛልን። ⁹በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤ ¹⁰በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው። ¹¹እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ፥ አስቀድመን የተወሰንን በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ተቀበልን። ¹²ይኸውም፥ በክርስቶስ አስቀድመን ተስፋ ያደረግን እኛ ለክብሩ ምስጋና እንሆን ዘንድ ነው። ¹³እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤ ¹⁴እርሱም የርስታችን መያዣ ነው፥ ለእግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እስኪዋጅ ድረስ፥ ይህም ለክብሩ ምስጋና ይሆናል።

  • 20 мая1 255284

    ኢሳ 33 ¹⁵በጽድቅ የሚራመድ፣ ቅን ነገር የሚናገር፣ በሽንገላ የሚገኝ ትርፍ የሚንቅ፣ መማለጃን ላለመቀበል እጁን የሚሰበሰብ፣ የግድያን ሤራ ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን፣ ክፋትን ላለማየት ዐይኑን የሚጨፍን፣¹⁶ይህ ሰው በከፍታ ላይ ይኖራል፤ የተራራም ምሽግ መጠጊያው ይሆናል፤ እንጀራ ይሰጠዋል፣ ውሃውም አይቋረጥበትም። በጽድቅ የሚገኝ ከፍታ መገናኘት ይሁንልን።

  • 7 мая1 471215

    መዝሙር 112 ¹እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ትእዛዙንም እጅግ የሚወድድ ሰው ምስጉን ነው። ²ዘሩ በምድር ላይ ኃያል ይሆናል፤ የቅኖች ትውልድ ትባረካለች። ³ክብርና ባለጠግነት በቤቱ ነው፥ ጽድቁም ለዘላለም ይኖራል። ⁴ለቅኖች ብርሃን በጨለማ ወጣ፤ መሓሪና ይቅር ባይ ጻድቅም ነው። ⁵ቸር ሰው ይራራል ያበድራልም፥ በፍርድም ነገሩን ይፈጽማል። ⁶ለዘላለም አይናወጥም፤ የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል። ⁷ከክፉ ነገር አይፈራም፤ በእግዚአብሔር ለመታመን ልቡ የጸና ነው። ⁸በጠላቶቹ ላይ እስኪያይ ድረስ፡ ልቡ ጽኑ ነው፥ አይፈራም። ⁹በተነ ለችግረኞችም ሰጠ፤ ጽድቁ ለዘላለም ዓለም ይኖራል፤ ቀንዱ በክብር ከፍ ከፍ ይላል። ¹⁰ኃጢአተኛም አይቶ ይቈጣል፥ ጥርሱንም ያፋጫል፥ ይቀልጣልም፤ የኃጢአተኞችም ምኞት ትጠፋለች።

  • 24 апр.1 46282

    ኤፌሶን 4 ¹⁷እንግዲህ አሕዛብ ደግሞ በአእምሮአቸው ከንቱነት እንደሚመላለሱ ከእንግዲህ ወዲህ እንዳትመላለሱ እላለሁ በጌታም ሆኜ እመሰክራለሁ። ¹⁸እነርሱ ባለማወቃቸው ጠንቅ በልባቸውም ደንዳንነት ጠንቅ ልቡናቸው ጨለመ፥ ከእግዚአብሔርም ሕይወት ራቁ፤ ¹⁹ደንዝዘውም በመመኘት ርኵሰትን ሁሉ ለማድረግ ራሳቸውን ወደ ሴሰኝነት አሳልፈው ሰጡ። ²⁰እናንተ ግን ክርስቶስን እንደዚህ አልተማራችሁም፤ ²¹በእርግጥ ሰምታችሁታልና፥ እውነትም በኢየሱስ እንዳለ በእርሱ ተምራችኋል፤ ²²ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥ ²³በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ ²⁴ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ። ²⁵ስለዚህ ውሸትን አስወግዳችሁ፥ እርስ በርሳችን ብልቶች ሆነናልና እያንዳንዳችሁ ከባልንጀሮቻችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ። ²⁶ተቆጡ ኃጢአትንም አታድርጉ፤ ²⁷በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት። ²⁸የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፥ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖርለት በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም። ²⁹ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ። ³⁰ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ። ³¹መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ። ³²እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ። የማሰላሰያ ጥያቄዎች፣፦ በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ መሠረት፦ 1. የአሮጌው ሰው እና የአዲሱ ሰው መለያቸው/ባህሪያቸው ምን ምን ናቸው? 2. አሮጌውን ሰው እንዴት እናስወግድ? አዲሱን ሰው እንዴት እንልበስ?

  • 16 апр.1 27792

    መዝሙር 54 ¹አቤቱ፥ በስምህ አድነኝ፥ በኃይልህም ፍረድልኝ። ²አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማኝ፥ የአፌንም ቃል አድምጥ፤ ³እንግዶች ቁመውብኛልና፥ ኃያላንም ነፍሴን ሽተዋታልና። እግዚአብሔርን በፊታቸው አላደረጉትም። ⁴እነሆ፥ እግዚአብሔር ይረዳኛል፥ ጌታዬም ለነፍሴ ደጋፊዋ ነው። ⁵ክፋትን ወደ ጠላቶቼ ይመልሳታል፤ በእውነትህም አጥፋቸው። ⁶ከፈቃዴ እሠዋልሃለሁ፤ አቤቱ፥ መልካም ነውና ስምህን አመሰግናለሁ፤ ⁷ከመከራ ሁሉ አድኖኛልና፥ ዓይኔም በጠላቶቼ ላይ አይታለችና።

  • 12 апр.1 33773

    ወደ ዕብራውያን 7 ²⁰-²¹እነርሱም ያለ መሐላ ካህናት ሆነዋልና፤ እርሱ ግን፦ ጌታ፦ አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ ብሎ ማለ አይጸጸትም ብሎ በተናገረለት ከመሐላ ጋር ካህን ሆኖአልና ያለ መሐላ ካህን እንዳልሆነ መጠን፥ ²²እንዲሁ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል። ²³እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለ ከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፤ ²⁴እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤ ²⁵ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል። ²⁶ቅዱስና ያለ ተንኮል ነውርም የሌለበት ከኃጢአተኞችም የተለየ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባልና፤ ²⁷እርሱም እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና። ²⁸ሕጉ ድካም ያላቸውን ሰዎች ሊቀ ካህናት አድርጎ ይሾማልና፤ ከሕግ በኋላ የመጣ የመሐላው ቃል ግን ለዘላለም ፍጹም የሆነውን ልጅ ይሾማል። ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት ተነስቷል፥ ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን። ሞት እይዘው ዘንድ አልቻለም። ዛሬ የምንኖረው ሕይወት ያኔ በመስቀል ላይ በከፈለልን ዋጋ ነው። ዛሬ ከኃጢአት ቀንበር ነፃ የሆንነው፥ በድል የምንመላለሰው፥ የማይጠፋ እና እድፈት የሌለበት ርስት ያገኘነው ክርስቶስ ኢየሱስ ከተቀበለልን መከራ የተነሳ ነው። ስለእኛ እርሱ ርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ነፃ አወጣን። ሞት ስለከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙዎች ናቸው። ሞት ግን እሱን ይይዘው ዘንድ አልቻለም። ዛሬ ደግሞ እስከ ለዘላለምም ሊያማልድልን ዘወትር በሕይወት ይኖራል። በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር ብንቀርብ ያድነናል። ስለ ታላቅ ማዳኑ እግዚአብሔርን እናመስግነው። "²የሕዝብህን ኃጢአት አስቀረህ፥ አበሳቸውንም ሁሉ ከደንህ።... ¹⁰ምሕረትና እውነት ተገናኙ፤ ጽድቅና ሰላም ተስማሙ።" እንኳን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

  • እንኳን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!! በዚህ በማለዳ ፀሎት አብረን እንድንፀልይ ከታች ባለው ሊንክ ይቀላቀሉን 👇👇 🙏 @yemaledatselot 🙏 🙏 @yemaledatselot 🙏 🙏 @yemaledatselot 🙏

  • 10 апр.1 18462

    ወዳጆች ሆይ፥ ተኝተናል? ³²ጌቴሴማኒ ወደምትባልም ስፍራ መጡ፥ ደቀ መዛሙርቱንም፦ ስጸልይ ሳለሁ፥ በዚህ ተቀመጡ አላቸው። ³³ጴጥሮስንና ያዕቆብን ዮሐንስንም ከእርሱ ጋር ወሰደ፤ ሊደነግጥም ሊተክዝም ጀመረና። ³⁴ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዘነች፤ በዚህ ቈዩ ትጉም አላቸው። ³⁵ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በምድርም ወድቆ፥ ይቻልስ ቢሆን ሰዓቲቱ ከእርሱ እንድታልፍ ጸለየና፦ ³⁶አባ አባት ሆይ፥ ሁሉ ይቻልሃል፤ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን አንተ የምትወደው እንጂ እኔ የምወደው አይሁን አለ። ³⁷መጣም ተኝተውም አገኛቸው፥ ጴጥሮስንም፦ ስምዖን ሆይ፥ ተኝተሃልን? አንዲት ሰዓት ስንኳ ልትተጋ አልቻልህምን? ³⁸ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉ ጸልዩም፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች፥ ሥጋ ግን ደካማ ነው አለው። (የማርቆስ ወንጌል 14) በዚሁ በምዕራፍ 14 ሲጀምር እንዲህ ይለናል፦ "¹ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካና የቂጣ በዓል ነበረ። የካህናት አለቆችም ጻፎችም እንዴት አድርገው በተንኰል እንደሚይዙትና እንደሚገድሉት ይፈልጉ ነበር።" ይላል። የእውነት ጠላቶች፥ የጽድቅ ጠላቶች፥ የእግዚአብሔር ጠላቶች ዋናውን እረኛውን ብንገድለው መንጋው ይበተናል (ማርቆስ 14፡27) እየተባባሉ ይዶልታሉ። ጌታ ኢየሱስ ደግሞ ይህንኑ ያውቃል። ስለዚህም ለደቀመዛሙርቱ እና ለተከታዮቹ ይጸልይላቸው ነበር። በሌላ ቦታ እንዲህ ይላል የእግዚአብሔር ቃል፦ "³¹ጌታም፦ ስምዖን ስምዖን ሆይ፥ እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤ ³²እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና አለ።" (ሉቃስ 22፡31-32) ግን ቢሆንም የሚመጣውን ስለሚያውቅ ለደቀ መዛሙርቱ "በዚህ ቈዩ ትጉም" (ቁጥር 34) ብሏቸው ሄደ። እንዚያ ደቀ መዛሙርት አላወቁም እንጂ የካህናት አለቆች እና ጻፎች ሊያርዱት፥ ለተከታዮቹም ተመሳሳይ እጣ ፈንታ ሊያጎናጽፉአቸው በተንኮል እየተመካከሩ ነበር። ደቀ መዛሙርቱ ግን እንቅልፍ ከብዶአቸው ተኝተው ነበር። ጌታ ኢየሱስ ግን ምን አላቸው? "ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉ እና ጸልዩ" ነው ያላቸው። የጠላት ዱለታ የማይቀር ነገር ነው። መከራ በዚህ ዓለም የማይቀር ነገር ነው። በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እውነተኛ የሆነ የብርሃን ሕይወት ስለምንኖር የዚህ ዓለም ገዢ ጨለማ ስለሆነም በእኛ ላይ መነሣቱ የማይቀር ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ ያስቀመጠውን ብርሃን ሰዎች ሲመለከቱ ከጨለማው መንግስት አምልጠው ወደ ብርሃን መንግስት መፍለሳቸው የማይቀር ስለሆነ ማለት ነው። ፈተናው እግዚአብሔርን መካድ ነው። በምንጨነቅበት ሰዓት፥ ሞት ፊት ለፊት ሲጋፈጠን እንደ ጴጥሮስ እራሳችንን እየተራገምን 'የምትሉትን ሰውዬ ፈጽሞ አላውቀውም' ብለን እንሸሻለን ወይስ እየመሰከርንለት ጸንተን እንቆማለን? እርግጥ ነው፥ ኢየሱስ እየማለደልን ስለሆነ ነው ከእጁ የማንወጣው እና የምንበረታው፥ ግን ጸልዩ ከተባልን ልንጸልይ ይገባናል። ብዙም ደግሞ አላከበደብንም። 'አንዲት ሰዓት አብራችሁኝ ልትጸልዩ አልቻላችሁም?' አላቸው። ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አንድ ሰዓት ማሳለፍ ይከብደን ይሆን? ከወዳጁ ጋር ተገናኝቶ ሻይ ቡና ማለት የማይፈልግ አለ? ካለ ያ ሰው እውነተኛ ወዳጅ አይደለም። ክርስቶስ የዘላለም ወዳጃችን ነው። በዛሬው ዕለት ያኔ በመስቀል ላይ ያደረገልንን ማዳን እንዘነጋው ይሆን? ጠላት ዙሪያችንን የሚዉጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ እያገሳ እየዞረን ተኝተን ይሆን? ደግሜ አሁንም ልበለው፦ እምነታችን እንዳይጠፋ ኢየሱስ ስለእኛ እየማለደ ነው። የእኛን ድርሻ እየተወጣን ነው? ወይስ ተኝተናል? ዛሬ ፋሲካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የታረደበት ቀን መታሰቢያ በዓል ነው። ያኔም የነበሩት ጠላቶቹ የዚህ ጨለማ ዓለም ገዦች እና አለቆች እንዲሁም ስልጣናት እና ጭፍሮች አሁንም በእኛ ላይ እየዶለቱ አሉ። ጌታ ስለ እኛ ይማልዳል፥ እኛ ግን ወደፈተና እዳንገባ እየጸለይን ነው? የተወደዳችሁ ወገኖች፥ አሁን መንቃት ይሁንል። በአእምሮም በመንፈስም መጸለይን ጌታ ኢየሱስ ያስተምረን። እኛ እንድንበረታ፥ ወንድሞቻችንንም እንድናበረታ፥ ቤተ ክርስቲያንን እንድናበረታ፥ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ መልካም የምስራች በኃይል እና በስልጣን እንዲሰበክ ነቅተን መጸለይ ይሁንል። "²⁰እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥ ²¹ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ። (ይሁዳ 1፡20-21) 🔥 እግዚአብሔር በመንፈሱ ይርዳን። አሜን! 🔥 በዚህ በማለዳ ፀሎት አብረን እንድንፀልይ ከታች ባለው ሊንክ ይቀላቀሉን 👇👇 🙏 @yemaledatselot 🙏 🙏 @yemaledatselot 🙏 🙏 @yemaledatselot 🙏

  • https://youtu.be/RCDbu_dTLog?si=CHMqM5GFt3fySlcR የጌታ ኢየሱስ የወንጌል መልዕክት ጥርት አድርጎ የሚናገር አዲስ የፋሲካ መዝሙር!

  • ሮሜ 5 ⁵በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም። ⁶ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቶአልና። ⁷ስለ ጻድቅ የሚሞት በጭንቅ ይገኛልና፤ ስለ ቸር ሰው ግን ሊሞት እንኳ የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል። ⁸ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። ⁹ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን። ¹⁰ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤ ¹¹ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን አሁን መታረቁን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ እንመካለን። ጌታ እግዚአብሔር በታላቅ አዳዳን አድኖን ፍቅሩን ገልጾልናል። ከዚያም አልፎ መመኪያችን ሆኗል። ክብር ለስሙ ይሁን። ዛሬ ግራ ያጋባን ነገር አለ? በልጁ ሞት ምክንያት ከእግዚአብሔር ጋር ታርቀናልና በእግዚአብሔር እንመካ።

  • 9 апр.1 13566

    ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀና ሲጸልይ፦ አባቴ፥ ቢቻልስ፥ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ፤ ነገር ግን አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን አለ። (የማቴዎስ ወንጌል 26፥39) ቢቻልስ… ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔርን አንድ ነገር ለመነው። "ቢቻልስ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ" ብሎ። የሚያልፍበትን መከራ ምን ያህል እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃል። ምን እንደሚጠብቀው ያውቃል። እኛን ለማዳን የከፈለው ዋጋ ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ ተረድተናል? ይህንን ስንረዳ ልባችን በፍቅር ቅልጥ ይላል። የእኔ ኢየሱስ እውነተኛ ወዳጄ! ብለን ከልባችን እንወደዋለን። ስለወዳጆቹ አይደለም የሞተው። ገና ኃጢአተኞች ሳለን ነው የሞተልን። ጀርባው ተተልትሎ አጥንቱ እስኪታይ ድረስ በጨካኝ የሮም ጅራፍ ገረፉት፤ አዋረዱት፤ አንገላቱት፤ እርቃኑን ሰቀሉት። ወዳጆቹ ጥለውት ሸሹ፥ የእግዚአብሔር ቁጣ በእርሱ ላይ አረፈ… ይህንን ሁሉ ስለእኛ አለፈ። ያለፈበትን መከራ ጥልቀቱ በደንብ የተረዳን እንደሆነ ሕይወታችን ይቀየራል። ውዴ ኢየሱስ! እያልን ልባችን በፍቅር ቅልጥ ይላል። ከሞትም፣ ከኃጢአትም፣ ከሰይጣንም፣ ከዓለምም በመስቀል ሥራው እሱ አድኖናልና! ቢቻልስ ብሎ አባቱን ጠየቀ። ነገር ግን ሌላ መንገድ አልነበረም። “ለሚያምን ሁሉ ይቻላል” ያለው ጌታ በዚህ መንገድ ማለፍ ነበረበት። ስለዚህም እኔን እና እናንተን እያየ መስቀሉን ተሸክሞ ሄደ። በታላቅም አዳዳን አዳነን። ክብር ለስሙ ይሁን! ዛሬ ይህንን እያሰብን እንዋል እንጸልይም። ሌላ መንገድ አልነበረም። ጽዋውን ለእኔ ሲል ተጎነጨው፥ ጨልጦትም ጠጣው። ለእኔ ሲል።

  • 1ኛ ጴጥሮስ 1 ¹¯²የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ጴጥሮስ፥ እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ እንዳወቃቸው በመንፈስም እንደሚቀደሱ፥ ይታዘዙና በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ይረጩ ዘንድ ለተመረጡት በጳንጦስና በገላትያ በቀጰዶቅያም በእስያም በቢታንያም ለተበተኑ መጻተኞች፤ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። ³¯⁵ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል። እነዚህን ጥቅሶች በሙሉ በልባችን ልንይዛቸው ይገባናል። ጌታ እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በክርስቶስ ትንሳኤ ምክንያት ያዘጋጀልን ድነት ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ፥ ርስት እንዳለንና በመታዘዝና በቅድስና የምንኖርበትን አቅም እንዴት እንደተሰጠን ያስረዱናል። በዚህ የሕማማት ሰሞን በዚያ መስቀል ላይ ሆኖ የተሰቃየው እና የሞተው፥ ከሙታንም የተነሳው ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ ያስገኘልንን እያሰብን እግዚአብሔር አብ እያመሰገንነው እና እየባረክነው እንጸልያለን።