tgindex
EthioNews

For latest news

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
8
Всего постов
33
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
275
−1 за 3 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
23
33 постов
Вовлечённость
8,4%
к подписчикам
Постов в день
1,1
всего 33
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
14
1/48двое суток
16
1/72трое суток
17

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • без подписи

  • без подписи

  • ፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉን ክርስቲያን ታደለንና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባሉ ዮሃንስ ቧያለውን ጨምሮ 30 የሽብር ተከሳሾች መንግሥት ያቀረበውን በቅድመ ሁኔታ የታሠረ ይቅርታ ውድቅ አደረጉ። ተከሳሾቹ፣ ወንጀለኞች መሆናቸውን አምነው ከፈረሙ ከእስር እፈታቸዋለሁ በማለት መንግሥት ያቀረበውን የይቅርታ ሠነድ 'አንፈርምም' ማለታቸውን ዋዜማ ተከሳሾቹ ከጻፉት ደብዳቤ ላይ ተመልክታለች። የይቅርታ ሠነዱ፣ ተከሳሾቹ ከእስር ለመፈታት በአማራ ክልል ለተፈጠረው ቀውስ፣ በቀውሱ ሕይወታቸውን ላጡና ለቆሰሉ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎችና ለወደመው በቢሊዮኖች የሚገመት ንብረት ኃላፊነት እንዲወስዱ የሚጠይቅ ነው። ኾኖም ተከሳሾቹ፣ በሕግ ነጻ ሆኖ የመታየትና ራሳቸውን የመከላከል መብታቸውን አሳልፈው እንደማይሠጡ ገልጸዋል።

  • ይሄ ጭፍጨፋ የተፈጸመው በግልገል በለስ መናኸሪያ ውስጥ ነው

  • ይሄ ጭፍጨፋ የተፈጸመው በግልገል በለስ መናኸሪያ ውስጥ ነው

  • ከ300 በላይ የሽብር ተከሳሾች የቀረበላቸው የይቅርታ ሰነድ ምን ይዟል ? ከአማራ ክልል ቀውስ ጋር በተያያዘ በሽብር የተከሰሱ ከ300 በላይ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና ሌሎች ግለሰቦች በይቅርታ ከእስር እንዲለቀቁ ሂደት መጀመሩን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። የይቅርታ ሂደቱ እንዴት ጀመረ ? እንደ ዘገባው ከሦስት ዓመት እና ከዚያ በላይ በእስር ላይ የሚገኙት ተከሳሾች የይቅርታ ጥያቄ እንዲያቀርቡ የሚጠይቀው ሰነድ የደረሳቸው በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አማካኝነት ነው። የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ ከሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለአንድ ወር ያህል በተከሳሾቹና በመንግሥት መካከል የማሸማገል ሥራ ሲያከናውኑ ከቆዩ በኋላ፣ ተከሳሾቹ ይቅርታ የሚጠይቁበትና የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎችን የያዘ ሰነድ ለየግላቸው ደርሷቸዋል። የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ ከተከሳሾቹ ጋር በፊትም ተገናኝተው ነበር። በታኅሣሥ ወር ከኢሰመኮ ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ወደ ፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ቂሊንጦ የጊዜ ቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል ሄደው ተከሳሾቹን ጎብኝተው ነበር። በዚያም ስለሰብዓዊ መብት አያያዝና ሌሎች ጉዳዮች ከተከሳሾቹ ጋር ተወያይተዋል። ከዚህ ጉብኝት ከስድስት ወራት በኋላ ነው ኮሚሽነሩ በድጋሚ ከተከሳሾቹ ጋር በመገናኘት የማደራደር ሥራ የጀመሩት። ሰነዱ ተከሳሾች ምን እንዲያምኑ ይጠይቃል ? ሰነዱ ተከሳሾቹ በየክስ መዝገባቸው የቀረበባቸውን ወንጀል እንደፈጸሙ አምነው ኃላፊነት እንዲወስዱ ይጠይቃል። ሰነዱ በተለይ ፦ - በአማራ ክልል ለተፈጠረው ቀውስ ኃላፊነት እንዲወስዱ፤ - በግጭቱ ለሞቱና ለቆሰሉ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ኃላፊነት እንደሚወስዱ እንዲያምኑ፤ - በቢሊዮኖች የሚገመተውን የንብረት ውድመት እንደፈጸሙ እንዲያምኑ፤ - በየክስ መዝገባቸው የተጠቀሱትን የሽብር ወንጀሎች እንደፈጸሙ እንዲቀበሉ፤ - ወደፊት በተመሳሳይ ድርጊት እንደማይሳተፉ ቃል እንዲገቡ፤ ቃላቸውን ካፈረሱ መንግሥት አስፈላጊውን ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስድባቸው እንደሚስማሙ እንዲገልጹ ይጠይቃል። ከፖለቲካዊ አቋማቸው ጋር የተያያዙ ምን ጉዳዮች ተካተዋል ? ሰነዱ ላይ "አንፈርምም" ካሉ ተከሳሾች በተገኘው ምላሽ ከወንጀል ክሶች በተጨማሪ ከፖለቲካዊ አቋሞቻቸው ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በሰነዱ ላይ ሰፍሯል። በተለይ፦ 1. "አገሪቱ በአማራ ትውፊቶችና እሳቤ መመራት አለባት" የሚል አቋም ማራመዳቸው ወንጀል መሆኑን እንዲያምኑ፤ 2. "ያለአግባብ የተወሰዱ የአማራ ርስቶች መመለስ አለባቸው" የሚል አቋም መያዛቸውም ወንጀል መሆኑን እንዲቀበሉ፤ 3. በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ "ጽንፈኛ ኃይሎች" ተብለው የተጠቀሱ ታጣቂዎችን እንዲያወግዙ ቅድመ ሁኔታ ተቀምጧል። ስንቶቹ ፈረሙ ? ስንቶቹ አልፈረሙም ? በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙት ከ300 በላይ ተከሳሾች ሰነዱን እንዲፈርሙ ቀርቦላቸዋል። አብዛኛዎቹ ፈርመዋል፤ ነገር ግን 30 የሚያህሉ ተከሳሾች ቅድመ ሁኔታዎቹን በመቃወም እንዳልፈረሙ ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቅርብ ቤተሰባቸው ባገኘው መረጃ  " አንፈርምም " ያሉት 30 ተከሳሾች የሚከተሉት ናቸው። 1. አቶ ዮሐንስ ቧያለው 2. ዶ/ር ወንድወሰን አሰፉ 3. ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው 4. ዶ/ር መሰረት ቀለምወርቅ 5. ዶ/ር ቴውድሮስ ሀ/ማርያም 6. ጋዜጠኛ ጐበዜ ሲሳይ 7. ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው 8. ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ 9. ጋዜጠኛ መስከረም አበራ 10. ጋዜጠኛ ገነት አስማማው 11. አቶ አለልኝ ምህረቱ 12. አቶ መንበር አለሙ 13. አቶ ማይክ መላክ 14. አቶ እስክንድር ሽፈራው 15. አቶ ደሳለኝ እጅጉ 16. አቶ አሳምነው ታደሰ 17. አቶ መሰለ ቸሩ 18. አቶ እሱባለው በለጠ 19. ዶ/ር ዘሪሁን በሀራው 20. ኢ/ር ፍርዱ ተፈራ 21. ወ/ሪት ሀሊማ መሐመድ 22. ወ/ሪት ህይወት አላምረው 23. አቶ ጫኔ ዘገየ 24. አቶ ሲሳይ መልካሙ 25. አቶ ማረው ስለሺ 26. አቶ ታደሰ ወልድነው 27. አቶ ያሬድ ግርማ 28. አቶ ሰለሞን ተፈራ 29. አቶ ሙሉቀን ተስፉ 30. አቶ በላይ ሲሳይ እነዚህ 30 ተከሳሾች ፥ በፍርድ ቤት የተከሰሱበትን ወንጀል እየተከራከሩ እያለ "ወንጀለኛ ነን" ብለው መፈረም እንደማይችሉ ገልጸዋል። " ወንጀለኛ ነን ብለን አንፈርምም፤ ይህ በሕግም፣ በሞራልም፣ በፖለቲካም ተቀባይነት የለውም " የሚል አቋም ይዘዋል። " የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎችም ሕጋዊ ናቸው ብለን እናምናለን " ሲሉም አክለዋል። 30ዎቹተከሳሾቹ ምን ይፈልጋሉ ? እነዚህ ተከሳሾች ከሦስት ዓመት በላይ ያለ ፍርድ በእስር መቆየታቸውን በመጥቀስ፣ ጉዳዩ በምህረት እንዲፈታ ይፈልጋሉ። ቤተሰቦቻቸው ለተለያዩ ችግሮች መጋለጣቸውን የሚገልፁት ተከሳሾች፣ መንግሥት " ክሱን አቋርጦ በፖለቲካዊ መንገድ በምህረት ይፍታን " የሚል አቋም አላቸው። የሕግ ጥያቄውስ ? ለቢቢሲ ቃላቸውን የሰጡ የሕግ ባለሙያ አቶ ኤርሚያስ ጥላሁን፣ በኢትዮጵያ የይቅርታ ሂደት ላይ የመጨረሻ የፍርድ ውሳኔ መኖሩ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 229 እና በይቅርታ አዋጅ 840/2006 አንቀጽ 15 መሠረት፣ የይቅርታ ጥያቄ በወንጀል ጥፋተኛ ተብሎ የመጨረሻ ቅጣት በተወሰነበት ሰው ላይ እንደሚቀርብ አቶ ኤርሚያስ አብራርተዋል። በዚህ ጉዳይ ግን ተከሳሾቹ ገና ፍርድ ያላገኙ ሲሆን፣ ክሳቸውም በተለያየ የሕግ ሂደት ላይ ይገኛል። ስለዚህ የቀረበው ሂደት ከመደበኛው የይቅርታ አሠራር ጋር እንዴት እንደሚጣጣም የሕግ ጥያቄ አስነስቷል። ኢሰመኮ ምን አለ ? ቢቢሲ ስለ ድርድሩ ኢሰመኮን ለማነጋገር ሞክሯል። የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ ግን በጉዳዩ ላይ መረጃ እንደሌላቸው ተናግረዋል። ነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ/ም

  • без подписи

  • без подписи

  • በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ሶስት ወጣቶች 'ፋኖ ናችሁ' ተብለው ከመኪና እንዲወርዱ ከተደረጉ በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ መረሸናቸው ታወቀ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ኢሰብአዊ እና ዘግናኝ ድርጊት መፈጸሙ ተሰምቷል። ተመስገን ጌታቸው፣ ይታገሱ አሰግደው እና ግዛው ግርማዬ የተባሉ ሶስት የአማራ ክልል ተወላጆች ከተሳፈሩበት የሕዝብ ማጓጓዣ መኪና ላይ “ፋኖ ናችሁ” በሚል ውንጀላ ተገደው እንዲወርዱ ከተደረጉ በኋላ በግፍ መገደላቸውን የአካባቢው ምንጮች ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል። ድርጊቱ የተፈጸመው አገና በተባለችው ልዩ ቦታ ሲሆን ወንጀሉን የፈጸሙት የመንግስት ኃይሎች ከአካባቢው የአበሽጌ አገና ፖሊስ እና ሚሊሻ አባላት ጋር በመተባበር እንደሆነ ተጠቅሷል። ንጹሐኑ ዜጎች ከተሳፈሩበት መኪና ከወረዱ በኋላ እጃቸውን ወደኋላ በገመድ በማሰር አሰቃቂ እንግልት እንደፈጸሙባቸው እና በመጨረሻም ጭንቅላታቸውን በጥይት በመምታት በግፍ እንደረሸኗቸው ታውቋል። የግፉ አፈጻጸም በዚህ ብቻ አላበቃም። "ገዳዮቹ የሟቾቹን አስከሬን ወደ ትውልድ ቀያቸው ናቻ ቀሊት ቀበሌ ወስደው በመጣል ማንም ሰው አስከሬናቸውን እንዳያነሳና እንዳይቀብር ጥብቅ ክልከላ ጥለው ነበር" ብለው ለሚድያችን ቃላቸውን የሰጡት አንድ የአካባቢው ነዋሪ ናቸው። "በዚህም ምክንያት የተገደሉት ሰዎች እጃቸው እንኳን ሳይፈታ ለሦስት ሙሉ ቀናት ክፍት ቦታ ላይ ተጥለው በእንስሳ እንዲበሉ እዛው እንዲቆዩ ተደርጓል" በማለት ሁኔታውን አስረድተዋል። አስከሬኖቹ በተለይም ጭንቅላታቸው አካባቢ በተመቱበት የጥይት ምት ምክንያት ሙሉ በሙሉ በመጎዳቱ ገጽታቸውን ለማየት እና ለመለየት ጭምር የሚያስቸግር እና አሰቃቂ እንደነበር ተሰምቷል። በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የመድረክ ውይይቶችና የምክክር ሂደቶች ስለ ሰላም ቢወራም ከጀርባ ግን የዜጎች ህይወት በዚህ መልኩ በስውር ማለቁና ኢሰብአዊ ጥቃት መፈጸሙ ማህበረሰቡን ለከፍተኛ ሀዘንና ስጋት ዳርጎታል። Via መሠረት ሚድያ|

  • без подписи

  • በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ሶስት ወጣቶች 'ፋኖ ናችሁ' ተብለው ከመኪና እንዲወርዱ ከተደረጉ በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ መረሸናቸው ታወቀ ተመስገን ጌታቸው፣ ይታገሱ አሰግደው እና ግዛው ግርማዬ የተባሉ ሶስት የአማራ ክልል ተወላጆች ከተሳፈሩበት የሕዝብ ማጓጓዣ መኪና ላይ “ፋኖ ናችሁ” በሚል ውንጀላ ተገደው እንዲወርዱ ከተደረጉ በኋላ በግፍ መገደላቸውን የአካባቢው ምንጮች ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.meseretmedia.org/p/346

  • ለታሪካዊው ኢትዮጵያ ሆቴል ዘመናዊ ህንጻ ሊፈርስ ነው አዲስ አበባ ብሔራዊ ቴአትር አካባቢ የሚገኘው አንጋፋው የኢትዮጵያ ሆቴል ሊፈርርስ መሆኑ ተሰማ። ከዚህ ቀደም የሆቴሉ ጀርባ ያለው የስብሰባ አዳራሽ መፍረስ የጀመረ ሲሆን፣ ዋናው ሕንፃም በቅርቡ ሙሉ በሙሉ እንደሚፈርስ ተገልጿል። በቅጥር ግቢው ውስጥ የነበሩ ሰባት የንግድ ሱቆችም አስቀድመው ተነስተዋል። ይህንን ባለ አምስት ፎቅ ሆቴል ባለሃብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ በ2002 ዓ.ም በ94 ሚሊዮን ብር ገዝተውት ነበር። አሁን ላይ በቦታው ላይ ዘመናዊ ሕንፃ ለመገንባት ታቅዷል። ሆቴሉ ሲፈርስ 140 ሠራተኞች ሥራቸውን እንደማያጡና በባለቤቱ ሌሎች ኩባንያዎች ውስጥ እንደሚዛወሩ ተነግሯል። Fortune-

  • #Update በ'ፊንቴክ ኢንቨስትመንት' የማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ አርቲስቶች የዋስትና መብታቸው ተነስቶ ጉዳያቸውን በእስር ላይ ሆነው እንዲከታተሉ አቃቢ ህግ አቅርቦት የነበረው አቤቱታ ውድቅ እንዲደረግ እና በከባድ ማስጠንቀቂያ እንዲታለፉ ብይን ተሰጠ። አቃቢ ህግ በከፍተኛ የኢንቨስትመንት ማጭበርበር ወንጀል ተከሰው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙ ተከሳሾች እና ጠበቃቸው፣ የተከሰሱበት የክስ መዝገቡ በክርክር ሂደት ላይ የሚገኝ እና በችሎት ውሳኔ ያልተሰጠበት ሆኖ እያለ በሚዲያ ላይ በመቅረብ ከክሱ አውድ ውጪ የሆነ ማብራሪያ በመስጠታቸው የፍትሕ ሂደቱን ተጽዕኖ ውስጥ ለመክተት እና ምስክሮችን ላይ ተጽዕኖ ለማድረግ ሞክረዋል በሚል የዋስትና መብታቸው ተነስቶ ከማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ የሚል አቤቱታ አቅርቦ ነበር። በተጨማሪም ዘገባው የተጫነበት ሚዲያ ይቅርታ እንዲጠይቅ እና ቪዲዮውን እንዲያወርድ ፣ በወንጀል ህግ አንቀጽ 457 ስር በቀጥታ እንዲቀጡ እንዲወሰን የሚሉ አቤቱታዎችንም አቃቢ ህግ አካቷል። ፍ/ቤቱ ድርጊቱን በቀጥታ መቅጣት የማይችል ከሆነ ደግሞ አቃቢ ህግ የወንጀል ምርመራ የማድረግ እና ክስ የማቅረብ ስልጣኑን ተጠቅሞ ምርመራ የሚጀምር እና ተከሳሾችን በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጎ ክስ የሚያቀርብ መሆኑንም አስረድቷል። ዛሬ ጠዋት በዋለው ችሎት የአቃቢ ህግ አቤቱታን እና የተከሳሾችን ምላሽ መርምሮ ብያኔ ለመስጠት ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው ችሎቱ ተከሳሾቹ የዋስትና መብታቸው እንዲነሳ የቀረበውን አቤቱታ ውድቅ አድርጎታል። ችሎቱ በዋስትና ላይ የቀረበውን አቤቱታ ውድቅ ያደረገው በጥቃቅን ስህተቶች የዋስትና መብታቸውን መከልክል አግባብነት ያለው ባለመሆኑ አልተቀበልነውም በሚል ነው። እንዲሁም አቃቢ ህግ ፍ/ቤቱ ድርጊቱን በቀጥታ መቅጣት የማይችል ከሆነ አቃቢ ህግ የወንጀል ምርመራ የማድረግ እና ክስ የማቅረብ ስልጣኑን ተጠቅሞ ምርመራ የሚጀምር እና ተከሳሾችን በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጎ ክስ የሚያቀርብ መሆኑን ያሳወቀበትን አቤቱታን በተመለከትም በመደበኛ ምርመራ ተጣርቶ የመከራከር መብታቸውም ተከብሮ የሚታይ ነው በሚል አልተቀበለውም። የተላለፈውን ዘገባ ይዘት በተመለከተ ግን ህጉን ያልተከተለ አሳሳች ዘገባ ነው ያለው ሲሆን ከተጫነበት ሚዲያ ላይ እንዲወርድ እና ሚዲያውም ይቅርታ እንዲጠይቅ ትዕዛዝ ተሰጥቷል። አርቲስቶቹን በተመለከተ በከባድ ማስጠንቀቂያ እንዲታለፉ ችሎቱ ብይን የሰጠ ሲሆን በመዝገቡ ላይ ለ ጥቅምት 2/2019 ዓም የተያዘው ቀጠሮ እንደተጠበቀ ነው በማለት ብይን ተሰጥቷል። ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ/ም

  • без подписи

  • без подписи

  • የግብር ገዳይ‼️ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ፤ አነስተኛ ንግዶችን ለመደገፍ የግብር ሥርዓት ማሻሻያ እየተደረገ ነው አለ። የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አነስተኛ ነጋዴዎችን ለማበረታታት፣ የግብር ጫናን ለመቀነስና ትርፋማነታቸውን ለማሳደግ የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎችን እየተገበረ መሆኑን ገለጸ። ቢሮው ባለፉት ሁለት ዓመታት ፍትሃዊ የግብር አሰባሰብ ሥርዓት ለመዘርጋት፣ የመልካም አስተዳደር ክፍተቶችን ለመቅረፍና ብልሹ አሠራሮችን ለማስወገድ ሰፊ ሥራዎች መሠራታቸውን አስታውቋል። በከተማዋ በተለያዩ የንግድ ዘርፎች፣ በኪራይና በራይድ ትራንስፖርት የተሰማሩ 456 ሺህ 433 የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች የሚገኙ ሲሆን፣ ከእነዚህ 9.2 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን ገልጿል። ቢሮው አነስተኛ ነጋዴዎች በግብር ጫና ሳይጎዱ ወደ ትልቅ የንግድ ደረጃ እንዲያድጉ የድጋፍ ሥርዓቶችን እያጠናከረ መሆኑንም አመልክቷል። በ2018 የግብር ዘመን አብዛኞቹ ግብር ከፋዮች በተዘረጋው የኦንላይን ክፍያ ሥርዓት ግዴታቸውን እየተወጡ ሲሆን፣ ቅሬታ ያላቸው ግብር ከፋዮች ደግሞ በወረዳና በክፍለ ከተማ ደረጃ በተዘረጋው የቅሬታ ማስተካከያ ሥርዓት መፍትሔ እንዲያገኙ መደረጉን አስታውቋል። በቀጣዩ 2019 በጀት ዓመት የአዲስ አበባ ከተማ 502.27 ቢሊዮን ብር፣ የገቢዎች ቢሮ ደግሞ 380 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገልጿል። =

  • በትግራይ ክልል ግጭት በማገርሸቱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ያለው ስጋት ዳግም አሳሳቢ መሆኑን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ‼️ በሀገር የመከላከያ ሠራዊት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል አዲስ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ የክልሉ ነዋሪዎች ዳግም ለከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት የመጋለጥ ስጋት እንደደገነባቸው አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ቲገሬ ቻጉታህ  እንደገለጹት ማህበረሰቡ ቀደም ሲል ከደረሱበት አሰቃቂ ጥቃቶች ሳያገግምና ተጠያቂነት ሳይረጋገጥ አዲስ ግጭት ውስጥ መግባቱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ስጋቱን ይበልጥ ከፍ እንዲል አድርጎታል ብለዋል። በትግራይ ክልል ያገረሸው ግጭት ከአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ውጊያዎች ጋር ተደማምሮ በሀገሪቱ ከፍተኛ የመብት ጥሰቶች እየደረሰ መሆኑን የገለጸው አምነስቲ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብቶች መርማሪ አካላትን ሥራ በአስቸኳይ መመለስ እንደሚገባ  አሳስበዋል። ከዚህ ቀደም በነበረው ጦርነት፤ የጦር ወንጀል እና በሰብአዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎችን ጨምሮ በርካታ ጥሰቶች መመዝገባቸውን ያስታወሰው ተቋሙ በጥፋተኞች ላይ ምርመራ እና ክስ ያለማቅረብ አካሄድ ልማዳዊ ሊሆን አይገባም ብሏል። የፌደራል መንግሥት እና የትግራይ ባለስልጣናት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን እንዲያከብሩ፣ ሰላማዊ ሰዎችን እንዲጠብቁ፣ እንዲሁም ለነጻ የሰብአዊ መብት ተከታታዮች፣ ለሰብአዊ እርዳታ አቅራቢዎች እና ለገለልተኛ መገናኛ ብዙሃን ያልተገደበ እንቅስቃሴ ፈቃድ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርቧል።

  • ከ23 ሰዓታት በኋላ ተኩሱ ቆሟል‼️ #በሱዳን ድንበር ሸረሪና በትናንትናው ዕለት ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም #በመከላከያ ሰራዊት እና #በህወሓት አርሚ 70 ኃይሎች መካከል የነበረው ወታደራዊ ግጭት መቆሙ ታውቋል። ያሉ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት በትግራይ #ከሱዳን ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው ሸረሪና አካባቢ የተካሄደው ግጭት፣ በህወሓት ሥር ከሚንቀሳቀሰው «ክፍለ ጦር 70» (መቀመጫውን በሱዳን በኩል አድርጓል ከሚባለው) እና በተከዜ ጠባቂ ኃይሎች በተደገፉት የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሠራዊት (መከላከያ) ክፍሎች መካከል የተደረገ ዉጊያ ነው። ውጊያው ከ23 ሰዓታት በኋላ የቆመ ቢሆንም በሁለቱም ወገኖች በኩል በአካባቢው የሠራዊት እንቅስቃሴ እና ስምሪት እየተካሄደ ይገኛል። 🕊🕊🕊🕊🕊🕊

  • በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች እና የሚያስተምሩ መምህራን ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ እንዲዘዋወሩ ጥያቄ ማቅረባቸው ተሰማ። በትግራይ በሚገኙ አራት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ የተወሰኑ ተማሪዎች እና መምህራን በክልሉ ባለው የጸጥታ ስጋት ምክንያት ወደ ሌሎች የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲዛወሩ ጥያቄ እያቀረቡ እንደሚገኝ ተሰምቷል። በመቐለ፣ አክሱም፣ ዓዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች እና የሚያስተምሩ መምህራን ጥያቄያቸውን ለመንግሥት እያቀረቡ ነው። ተማሪዎች እና መምህራን በክልሉ በሚታየው የጸጥታ ስጋት ምክንያት የቅሬታ ጥያቄ እያስገቡ ሲሆን፤ እስካሁን ከትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠ የዝውውር ውሳኔም ሆነ የተገባ ቃል አለመኖሩን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ኅብረት ፕሬዝዳንት ሓየሎም ስዩም ገልፀዋል።

  • አሳዛኝ ነው‼️ በሸረሪና አቅጣጫ የህወሓት አርሚ 70 በመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ተከትሎ መከላከያ ሰራዊት በሜካናይዝድ ጦር የአፀፋ ምላሽ እየሰጠ ይገኛል። አንድ የአርሚ 70 አባል 'ኑ ቁስለኛ እናንሳ' ሲል ይሰማል። ጦርነት ይብቃ🕊🕊🕊