መዝሙረ ማኅሌት ቁ፪
Статистика@zemarian የቀደመው ቻናል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤት የሚከናወኑ ተግባራቶች አስመልክቶ ቆየት ያሉ ያሬዳዊ ዝማሬ በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ፣የሰንበት ት/ቤታችን ወቅታዊ ትምህርቶና የቤተክርስቲያን ወቅተዊ ጉዳዮችን ለማግኘትና ለመማማር @zemariann ይቀላቀሉን፡፡ ለማንኛውም አስተያየት ..@zemariiii_bot
- Последний пост
- 11 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- am
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 274
- 1/48двое суток
- 314
- 1/72трое суток
- 338
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
https://youtu.be/WUpN3lCNHiw?si=q35CF0fRHhq8R_0a
https://youtu.be/WUpN3lCNHiw
https://youtu.be/5fwxp9FqXms
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ከዚህ በኋላ ባለ ጠጋው ከሄደበት በተመለሰ ጊዜ በደስታ የሆነውን የመሰንቆና የእንዚራ ድምፅ ሰምቶ ‹‹ይህ የምሰማው ምንድነው›› ብሎ ጠየቀ፡፡ እነርሱም ‹‹ስሙ ባሕራን ለተባለ የአንተን ደብዳቤ ላመጣ ጐልማሳ ሰው ልጅህ ዕገሊትን አጋቡት፡፡ እነሆ ዓርባ ቀናት በሰርግ ላይ ነው፡፡ ገንዘብህንና ጥሪትህን ሁሉ ወንዶችና ሴቶች ባሮችህን አንተ እንዳዘዝህ ሰጥተውታል›› አሉት፡፡ ይህንም በሰማ ጊዜ ደንግጦ ከፈረሱ ላይ ወደቀ በድንገትም ሞተ፡፡ ባሕራንም ከዚህ በኋላ የቅዱስ ሚካኤልን ዝክር በሚገባ እየዘከረና ለቤተ ክርስቲያኑም እየታዘዘ የሚያገለግል ሆነ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዓሉን በሚገባ አክብረን በረከት እንድንቀበል ይርዳን፤ የቅዱስ ሚካኤል የረድኤቱ ኀይል በሀገራችን በሃይማኖታቸው ምክንያት ከተሠውት የክርስቲያን ወገኖች ጋር ይሁን፤ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ ምንጭ፡– ድርሳነ ቅዱስ ሚካኤል፣ ስንክሳር ዘወርኃ ሰኔ
ሚካኤል ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ ሚ-መኑ፣ካ-ከመ፣ኤል-አምላክ መኑ ከማከ አምላክ? እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው? ማለት ነው።(ኪ.ወ.ክ)። ቅዱስ ሚካኤል ዲያብሎስ በትዕቢቱ ፈጣሪነትን ሽቶ በዓለመ መላእክት ሁከት ባስነሣ ጊዜ የቅዱሳን መላእክት ፊታውራሪ ሆኖ ዲያብሎስን የተዋጋ ጽኑዕ መልአክ ነው። "በሰማይም ሰልፍ ሆነ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉት፣ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ አልቻላቸውም። ከዚያም ወዲያ በሰማይ ሥፍራ አልተገኘላቸውም።"(ራእይ ፳፪:፯) ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ነው። ይሁዳ በመልእክቱ "የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በማለት ሊቀ መላእክትነቱን ገልጾአል። (ይሁዳ ፱) ይህችውም ቅሩበ መንበር ተደርጎ የተፈጠረው ዲያብሎስ የተዋት ክብሩ ናት። ቅዱስ ሚካኤል ይቅር የሚል ከመዓት የራቀ ነው።(ሄኖ፥፲፥፩፪) ለሰው ባደረገው በጎነት ለሕዝቡ ሁሉ ታዛዥ ነው። የቅዱስ ሚካኤል ሹመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይ ጭምር ነው፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል፣ ለእኛ ለሰዎች አማላጅ ሲሆን ለቅዱሳ ጻድቃንና ሰማዕታት ደግሞ አጋዣቸው ነው፤ በሕይወታቸውና በተጋድሏቸውም እስከ መጨረሻው ይረዳቸዋል፡፡ ይህንንም በቤተ ክርስቲያናችን በመጽሐፈ ስንክሳር እና በድርሳነ ሚካኤል ሰኔ ፲፪ ቀን ተጽፎ እናገኘዋለን። ይህም ቀን መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ተከብሮ የሚውልበት ታላቅ ዕለት ነው፡፡ በእስክንድርያ ከተማ ክላወባጥራ የተባለች ንግሥት የበጥሊሙስ ልጅ ዙሐል በሚባል ኮከብ ስም ያሠራችው ታላቅ ምኲራብ ነበር፤ ሕዝቡም ሰኔ በገባ በዐሥራ ሁለት የዚህን ጣዖት በዓል ያከብሩ ነበር። ይህንንም ግብራቸውን እንዲተው አባታችን እለ እስክንድሮስ ቢነግራቸው አይሆንም አሉት። በኋላም ጻድቅ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ሲነግሥ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኃዋ ወአብያተ ጣዖታት ይትአጸዋ የሚል አዋጅ ስለወጣ በዚህ ምቹ ጊዜም የጣዖት አምልኮ እንደምን ያለ ክፉ ግብር እንደሆነና በጎ ዋጋም እንደሌለው ነግሮ እንዲተዉ ቢጠይቃቸው እኛስ ይህን አንተውም አሉት። እርሱም በጥበብ እንዲህ አላቸው፤ ‹‹ይህን ግብር ብትተው በዚህች ቦታ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን። መሥዋዕታችሁንም በዚያ ለቅዱስ እግዚአብሔር ታቀርባላችሁ አላቸው።›› በዚህ ተደስተው ተመለሱና ያንን የጣዖት ቤት አፍርሰው እጅግ ያማረች ቤተ ክርስቲያንን በመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ስም ሠሩ። የመልአኩንም በዓለ ንግሥ በዚህች ዕለት አከበሯት። ከዚያን ጊዜም ጀምሮ የከበረ የመላእክት አለቃ የመልአኩ የሚካኤል የመታሰቢያውን በዓል በሰኔ ዐሥራ ሁለት ቀን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይከበራል፡፡ዳግመኛም ንዑድ ክቡር የሚሆን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ባሕራንን በሰኔ ዐሥራ ሁለት ቀን ያዳነበት ድንቅ ተአምርም ይህ ነው። አንድ ደግ ሰው በዚያች ሀገር ይኖር ነበር። ክፉ ጎረቤትም ነበረው። ይህም ደግ ሰው ነዳያንን እጅግ የሚወድ የቅዱስ ሚካኤልንም ዝክር ሳያስታጉል የሚዘክር ሰው ነው። በዚህ ሥራው ግን ይህ ክፉ ጎረቤቱ ይዘብትበት ነበር። በኋላም ያ ደግ ሰው የሚሞትበት ቀን ሲደርስ ሚስቱን ዝክረ ሚካኤልን እንዳታቋርጥና ነዳያንን እንዳትዘነጋ ነግሯት ያርፋል። እርሷም ፀንሳ ነበርና እርሱ ከሞተ በኋላ የመውለጃዋ ጊዜ ደረሰ። ምጥም ቢጠናባት ወደ መልአኩ ጮኸች፤ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልም ተራዳትና መልከ መልካም የሆነ ወንድ ልጅ ወለደች። መልአኩም እንዲህ አላት። ‹‹ልጅሽ የዚህ የጎረቤትሽን ሀብት ይወርሳል።›› መልአኩም ለጎረቤታቸው ጆሮውም ከፍቶለት ነበርና ይህን ነገር ሰማ። በዚህም ‹‹በምን ምክንያት ወስጄ ላጥፋው›› ብሎ ሲያስብ ሴቲቱ ልጅዋን ብቻዋን ለማሳደግ ተቸገረች፤ ‹‹ላሳድግልሽ፤ ለአንቺም ይኸው ገንዘብ እሰጥሻለሁ›› ብሎ ብዙ ወርቅ ሰጣት። እርሱም ‹‹ከእንግዲህ አርፋለሁ›› ብሎ ልጁን መጣያ ሳጥን ያዘጋጅና ወደ ባሕር ቢጥለው ባሕሩም ሩቅ ሀገር ወስዶት ከዳር ይጥለዋል። ከዚህም በኋላ አንድ በጎቹን ያሠማራ ሰው ያገኘዋል። ያንንም ሳጥን ወስዶ ከቤት ያኖረዋል፤ በምን መክፈት እንደሚችል ሲያስብ ዳግመኛ ወደ ባሕሩ እንዲሄድ እግዚአብሔር ሐሳብ ያሳድርበትና ተነሥቶ ይሄዳል። ሲሄድም ዓሣ አጥማጅ ያገኝና ዓሣ ለእርሱና ለቤተሰቡ እንዲያጠምድለት ይነግረዋል። ያም ዓሣ አጥማጅ ሲያጠምድ ታላቅ ዓሣ አገኘና ሰጠው። ዋጋውን ሰጥቶም ወደ ቤት ተመለሰና ሆዱን ቢሰነጥቀው ቁልፉን በዚያ አገኘው። በዚያም ሳጥኑን ቢከፍት መልከ መልካም ልጅ አገኘ። ልጅም ስላልነበረው እጅጉን ተደሰተ። ባሕራን ብሎም ሰየመው። ከብዙ ጊዜያት በኋላ ያ ክፉ ሰው ከንግድ ተመልሶ በዚያ መንገድ ሲያልፍ መሸበትና ከዚህ ሰው ቤት አደረ። ባሕራንንም ተመለከተውና ሰውየውን ልጁ እንደሆነ ለማወቅ ታሪኩን ጠየቀው፤ ሰውየውም የሆነውን ሁሉ ነገረው። ክፉ ሰውየውም ልጁ እንዳልሞተ ባወቀ ጊዜ ደነገጠና መልእክት ሊልከው ስለሚፈልግ የባሕራንን አባት ልጁን እንዲሰጠው ጠየቀው። እርሱም ተስማምቶ ሰጠው። በክፋትም ተነሣሥቶ ባሕራንን እንዳገኘው እንዲገድለው ለአገልጋዩ ደብዳቤ ጽፎ አገልጋዩና እርሱ ብቻ የሚያውቁትን ማኅተም አድርጎ ሰጠው። ‹‹ይቺን ደብዳቤ በምታነባት ጊዜ ደብዳቤዋን ይዞ የመጣውን ገድለህ በጉድጓድ ውስጥ ጣለው፡፡ ማንም እንዳያውቅ›› ለባሕራንም ለመንገዱ የሚሆነውን ስንቅ ሰጠው፡፡ የራሱን የሞት ደብዳቤ እንደያዘ ሳያውቅ ባሕራን ወደ ታዘዘበት ሥፍራ ተጓዘ፤ ከዚያ ሰው ቤት ለመድረስ ሲቀርብ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በነጭ ፈረስ ላይ ተቀምጦ ‹‹አንተ ጐልማሳ የያዝኸው ምንድነው›› አለው፡፡ ‹‹ወደ ዕገሌ ሀገር ወደ ቤቱ ለማድረስ ከአንድ ባለ ጠጋ የተጻፈች መልእክት ናት›› አለው፡፡ ‹‹ያቺን ደብዳቤ አሳየኝ›› አለው፤ እርሱም ስለ ፈራ ሰጠው፡፡ የሞቱን ደብዳቤ ያቺን የሞት መልእክት ደምስሶ በሕይወት ቀየረለት። በእርሱም ፈንታ በንፍሐት ለውጦ እንዲህ ብሎ ጻፈ፤ ‹‹ይቺን ደብዳቤ ይዞ ለመጣ ባሕራን ለሚባል ሰው ይቺ ደብዳቤ ደርሳ በምትነበብበት ጊዜ ልጄ ዕገሊትን አጋቡት፡፡ በውስጥና በውጭ ያለ ንብረቴንና ጥሪቴን፣ ወንዶችና ሴቶች ባሮቼን፣ ጠቅላላ ንብረቴንም አውርሼዋለሁና የፈለገውንም ሊያደርግ ሥልጣን ሰጥቼዋለሁና እኔን አትጠብቁኝ፡፡ እኔ ብዙ እዘገያለሁ የኔ ሹም እገሌ ሆይ! በእኔና በአንተ መካከል ይቺ ምልክት እነኋት፡፡›› አሽጐ ለባሕራን ሰጠውና ‹‹ወደ ባለ ጠጋው ቤት ሂደህ ይቺን ደብዳቤ ለሹሙ ስጠው፡፡ በጎዳናም እኔ እንደ ተገናኘሁህ አትንገረው፡፡ እንዳይገድልህም ይህን የሞት ደብዳቤ ለውጬልሃለሁ›› አለው፡፡ ባሕራንም ‹‹እሺ ጌታዬ ያዘዝኸኝን ሁሉ አደርጋለሁ›› አለ፡፡ ባሕራንም ወደ ባለ ጠጋው ቤት በደረሰ ጊዜ ያቺን ደብዳቤ ለሹሙ ሰጠው፡፡ ካነበባት በኋላም በመካከላቸው ያለውን ምልክት አገኘ፡፡ አስተውሎም እርግጠኛ እንደ ሆነ ዐወቀ፡፡ ለባሕራን ሰርግ አዘጋጅቶ እንደሚገባ በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት በተክሊል የባለ ጠጋውን ልጅ አጋቡት፡፡ ዓርባ ቀን ያህልም ደስታና ሐሴት እያደረጉ ኖሩ፡፡ ሀብቱንም ሁሉ አወረሱት።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! ‘’ከመላእክት አለቆች አንዱ የሆነው ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ።’’ (ት.ዳን. ፲ ፥፱) እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ‼️ በዓል “አብዐለ” አከበረ÷ አበለጠ÷ ዕለትን በዓል አደረገ ከሚለው ግስ የወጣ ስም ነው። ይህም የደስታ፥የዕረፍት ቀን ፥በዓመት በወርና በሳምንት የሚከበር፥ ያለፈ ድርጊት የሚታወስበትና ምእመናን የበዓሉን ምሥጢር እያሰቡ ሐሴት የሚያደርጉበት ማለት ነው:: ዕለቱም ምእመናን መደበኛ ሥራቸውን ትተው ለበዓሉ ይገባዋል የሚሉትን ተግባር የሚፈጽሙበት የበዓሉን ባለቤት እግዚአብሔርንና የበዓሉን ምክንያት እያሰቡና እያመሰገኑ ደስ የሚሰኙበት ነው። ቅዱስ ዳዊት “….በዓልን የሚያደርጉ ሰዎች በምስጋናና በደስታ ቃል ሲያመሰግኑ ተሰሙ:: ”(መዝ ፵፩፥፬፡፡) እንዳለው። በዓላት የዕረፍት ቀናት ናቸው ማለት ከሥጋዊ ወይም ምድራዊ (ዓለማዊ) ሥራዎች የሚያርፉባቸው ናቸው ለማለት ነው። በአንጻሩ ግን መንፈሳዊ ሥራዎች ሁሉ እንደየችሎታ የሚከናወንባቸው መሆናቸው መረሳት የለበትም፡፡ እነዚህ ዕለታት እግዚአብሔር በራሱ ወይም በቅዱሳኑ አድሮ ለሠራቸው ድንቅ ሥራዎች (ተአምራት) መታሰቢያዎች ናቸው። (መዝ፻፲፥፬)፡፡ ፻፲፩፥፮፡፡ ሉቃ፳፪፥፲፱፡፡) በበዓሉ ዋዜማ ለዕለቱ የተሠራውን የምስጋና ቃል እየመሩ፣ እየተመሩ፣ እያነሡ፣ እየዘመሙ፣ መስተብቁዕ እየደገሙ፣ እያመረገዱ፣ እያመለጠኑ፣ እየጸፉ ሊቃውንቱ እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ። በዚህ መልኩ ከሚከበሩ ዐበይት በዓላትም አንዱ በዓለ ቅዱስ ሚካኤል ነው።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ በስመ ኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሓዱ አምላክ አሜን! ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ፤ ብፁዕ ኣቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፤ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን ኣበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ በአጠቃላይ በዚህ ዓመታዊ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የተገኛችሁ በሙሉ፦ ማሕየዊት በምትሆን ሞቱ ሰማያውያንና ምድራውያንን ያስታረቀ፣ በቅድስት ትንሣኤውም የሙታንን ሕይወት በተስፋ ያለመለመ ጌታችን፣ አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እንኳን ለዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አደረሰን አደረሳችሁ! “እስመ ተዋለጠ እግዚአብሔር ዓለመ በክርስቶስ ኣናኅስዮ ኃጢኣቶሙ ወኢነጺሮ ጌጋዮሙ፤ ወረሰየ ላዕሌነ ቃለ ሥምረቱ፤ ወወሃበነ መልእክተ ሣህሉ፡- እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና በደላቸውን ኣይቈጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል ኣኖረ” (2ቆሮ. 5፥19)። የእግዚአብሔርም ልጅ፣ የሰውም ልጅ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም በሰብእነት ሲገለጽ ግልጽ የሆነ ዓላማና ግብ እንደነበረው ቅዱስ መጽሓፍ ይነግረናል፤ እሱም በሰማይም፣ በምድርም ያሉትን በሙሉ ማስታረቅ፣ ማገናኘትና ኣንድ ማድረግ ነበረ፤ ጌታችን ይህንን ሲያደርግ ሰማያውያኑንና ምድራውያኑን የለያየው ምክንያት በማስወገድ ነው፤ የመለያየቱ ምክንያት ክፉ ኅሊና ኣምጦ የወለደው በደልና እሱን ተከትሎ የተከሠተው ኃጢኣት ነበረ፤ በኃጢኣት ምክንያት የገባው ሞት ደግሞ የቅጣቱ ማሳያ ፍርድ ነበረ። የመጀመሪያዎቹ ሰዎች በፈጸሙት ስሕተት መነሻነት ምድርንና ምድራውያንን ለከባድ ቅጣትና መርገም የዳረገው ይህ መለያየት ለሰማያውያኑም ተርፎኣል፤ ምክንያቱም መለያየቱ በእግዚአብሔርና በሰው፣ በመላእክትና በሰው፣ በሰውና በሰው፣ በነፍስና በሥጋ ጭምር የጥል ግድግዳን ገንብቶ እስከ ክርስቶስ ዕለተ ስቅለት መዝለቁን በቅዱስ መጽሓፍ የምናውቀው ስለሆነ ማለት ነው። ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ ኣባላት! ቀዳማዊና ዘላለማዊ የሆነው ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ሰብእናችንን ተዋሕዶ በዚህ ዓለም የተገለጸው ሰማያውያንንና ምድራውያንን የለያየው የጥል ግድግዳን ለማፈራረስ ነው፤ ለመለያየት ምክንያት የሆነችውን ኃጢኣት በሰውነቱ በመቅጣት የሕግን ትእዛዝ ከፈጸመ በኋላ የዕርቁን ተግባር በወሳኝ መልኩ ኣከናውኖታል፤ በክርስቶስ ቤዛነት የሆነው ይህ ዕርቅ በእግዚአብሔር ዘንድ እጅግ የተወደደ ነበረና እሱ ራሱ በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ኣስታረቀ፤ ለዚህም ነው ተበዳይ እሱ፣ ቤዛዊ መሥዋዕት ሆኖ የቀረበው እሱ፣ ኣስታራቂ እሱ፣ ታራቂ እሱ ሆኖ የምናገኘው፤ ለሱ የሚሳነው ነገር የለምና ለኛ ግር የሚል ቢመስልም ለሱ ቀላል ነበረ። በዚህ የዕርቅ ተግባር ሰውና እግዚአብሔር፣ ሰውና መላእክት፣ ሰውና ሰው፣ ነፍስና ሥጋ ታርቀው በይፋ ተገናኙ፤ በኅብረትና በኣንድነትም መኖር ቻሉ፤ በቀኙ ለተሰቀለው ሽፍታ “ዛሬውኑ ከኔ ጋር በገነት ትኖራለህ” የሚለው ቃለ ምሕረትና “ኣባት ሆይ፥ ነፍሴን በእጅህ ኣደራ እሰጣለሁ” የሚለው ቃለ አማሕፅኖ የዕርቁ፣ የግንኙነቱና የኣንድነቱ ማሳያ ኣስረጅ ናቸው። ስቅለተ ክርስቶስ ነፍሶቻችን ወደ ግዞት ቤት ሳይሆን ወደ ገነት እንዲገቡ፣ የሚቀበላቸውም ራሱ እግዚአብሔር እንዲሆን ያስቻለ ታላቅ መለኮታዊ ፍጻሜ ነው፤ እኛ “ክርስቶስ መድኃኒታችን ነው፤ አድኖናል” ብለን በልበ ሙሉነት የምንመሰክረው፣ እሱም “ሰላሜን ሰጠኋችሁ” ብሎ የሚያረጋጋን በመሰቀሉ ይህንን ውጤት ስላስገኘልን ነው። ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ ኣባላት! የድኅነታችንና የሰላማችን መሠረት የሆኑትን የክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ለዓለም ማኅበረ ሰብ የማብሰርና የማሥረጽ ተግባር የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቍጥር አንድ ተልእኮ ነው፤ ነገረ ሞቱና ነገረ ትንሣኤው በአስተውሎት፣ በጥልቀትና በተመሥጦ ስናስተምር በውስጡ የምናገኘው የዕርቅ፣ የሰላምና የአንድነት ምስጢር ነው፤ እንደ እውነቱ ከሆነ እኛ የክርስቶስ መልእክተኞች እንደ ቃሉ ራሳችንን ክደን በሚጠበቀው መጠን ተልእኮኣችንን መወጣት ብንችል ኖሮ፣ አሁን በዓለማችን የተፈጠረው መለያየትና ግጭት ኣይኖርም ነበር፤ ችግሩን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት ባንችልም በእጅጉ መቀነስና ዓቅሙን ማዳከም እንችል ነበር፤ ነገር ግን ተልእኮኣችንን በኣግባቡ ኣለመወጣት ኣንድ ነገር ሆኖ የዓለሙ መሳሪያ ሆነን መገኘታችን “በዕንቅርት ላይ…” ሆኖ ይስተዋላል። ይሁንና ኣሁንም ሕዝቡን ወደ ኣንድነት፣ ወደ ፍቅር፣ ወደ ሰላም፣ ወደ ዘላቂ የጋራ ጥቅምና ወደ ፈሪሐ እግዚአብሔር ማምጣት የጉባኤያችን ዓቢይ ተግባር ሊሆን ይገባል፤ እነዚህ ካሉ የምናጣውም ሆነ የሚያመልጠን የለምና ነው፤ ሃገርን በኃላፊነት ተረክባችሁ በላዕላዊ፣ በማእከላዊና በታሕታዊ መዋቅር የምትገኙ፣ እንደዚሁም ኣማራጭ ሓሳብ ኣለን ብላችሁ የምትንቀሳቀሱ ልኂቃነ ሃገር ፣ ሁላችሁም እግዚአብሔርን ከሚያውቅ፣ ከሚያመልክና ከሚፈራ ሕዝብ የተገኛችሁ ናችሁና በልባችሁ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ድምፁንም ስሙ፤ የሱ ገንዘብ በሆኑ ፍጡራንም ኣትጨክኑ፤ ሰውን መያዝ የሚቻለው ኅሊናን በመርታት እንጂ በሌላ ኣይደለምና፣ የሕዝቡን ፍላጎትና የልብ ትርታ በሚገባ ኣዳምጡ፤ ሕዝቡ የሚፈልገው በኣንድነትና በእኩልነት መኖር፣ በሰላም ወጥቶ መግባት፣ ፍትሕን ማስፈን፣ ለኑሮው የሚበቃ ምጣኔ ሃብትን ማግኘት፣ የእምነት ነጻነትና እኩልነት መረጋገጥ የመሳሰሉት ናቸው። ሕዝቡ እነዚህ ከተሟሉለት ተደመጠ ማለት ነው፤ ከተደመጠ ደግሞ እሱም በበኩሉ ያደምጣል፤ ይከተላልም፤ ስለሆነም ለሁሉም ልጆቻችንና ወገኖቻችን የምናስተላልፈው ወቅታዊ ጥሪ ሁሉንም ችግሮቻችን በሰላምና በሰላም ብቻ ለመፍታት ተባበሩ የሚል ነው፤ ከዚህ ውጭ የሚደረገው ኣማራጭ ሁሉ ለዘላቂ ሰላማችን አይበጅም እንላለን። በመጨረሻም፦ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ከበዓለ ትንሣኤ በኋላ በሃያ አምስተኛው ቀን የሚካሄደው ዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት የተጀመረ መሆኑን ለሕዝበ ክርስቲያኑና ለመላው ኢትዮጵያውያን እናበስራለን!!! እግዚአብሔር ጉባኤያችንን ይባርክ! እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ! ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ አሜን!!! አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘኣኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፤ ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ ኣበባ - ኢትዮጵያ