tgindex
ፍሬ ሃይማኖት

ፍሬ ሃይማኖት

Статистика

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአ/አ ሐገረ ሥብከት የመ/ደ/ገ/ቅዱስ ሚካኤል ካ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እና ሥርዓት የጠበቁ መዝሙሮች እና ወረቦች ግጥማቸው ከነዜማ የሚገኝበት ቻናል ነው፡፡ ® ለማናኛውም ሃሳብ አስተያየት ጥያቄና ጥቆማ @Frehaymanoteebot

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
5
Всего постов
24
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 848
−2 за 2 дн.
Сутки
−1
−0,05%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
386
24 постов
Вовлечённость
20,9%
к подписчикам
Постов в день
0,7
всего 24
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
188
1/48двое суток
215
1/72трое суток
232

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ✝️ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምሣሌዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ✝️       ፩. ገራኅተ ሠሉስ (የማክሰኞ እርሻ) "እግዚአብሔርም ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድርም  ላይ እንደ ወገኑ  ዘሩ  ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል አለ።እንዲሁም ሆነ።" ዘፍ. ምዕ.።1፥11-13።  "አንቲ  ውእቱ ገራኅት ዘኢተዘርዐ ውስቴታ ዘርዕ" "ዘር ያልወደቀባት(ያልተዘራባት)፣ገበሬ ያልጋረባት(የልደከመባት)  "ታብቅል" ባለው አምላካዊ ቃል መሠረት ከልምላሜ፣ ከአበባ፣ ከፍሬ የተገኘች የማክሰኞ እርሻ አንቺ ነሽ" (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ የማክሰኞ ውዳሴ ማርያም ቁ.4)       እንደሚታወቀው መሬት  ታርሳና ለስልሳ ዘር ካልተዘራባት በስተቀር አዝእርትንና ዕጽዋትን አብቅላ ፍሬን  (ምርትን) ልትሰጥ አትችልም።በጥንተ ፍጥረት ግን ሁሉን ማድረግ የሚቻለው፤ የሚሳነው የሌለ አምላክ በዕለተ ሠሉስ(ማክሰኞ) በቃሉ ትዕዛዝ ብቻ   በዕለተ እሁድ የተፈጠረችው ምድር ዘር ሳያስፈልጋት አዝእርትንና ዕጽዋትን አብቅላ ተገኝታለች። ፍሬንም ሰጥታለች።       እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በመጋቢት 29 ቀን መልአከ ብሥራት፣አብሳሬ ትስብዕት የሆነው ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል "ትጸንሲ + ትጸንሻለሽ" ብሎ ባበሠራት "ጊዜ ወንድ ስለማላውቅ ይህ ነገር እንደ ምንይሆንልኛል? ምድር ያለ ዘር ፍሬን፣ ሴት ያለ ወንድ ልጅን ማስገኘት እንደምን ይቻላቸዋል" ብላ ብዙ ተከራክራዋለች።     በስተመጨረሻም አርጅታና አፍጅታ የነበረችው፣ ሙቀትና ልምላሜ የተለያት አክስቷ ኤልሳቤጥ መጽነሷንና ይህም ከሆነ ስድስት ወር እንደሆነውና  ለልዑል እግዚአብሔር የሚሳነው ነገር እንደሌለ መልአኩ በነገራት ጊዜ  ክርክሯን በመተው  "ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ + እንደ ቃልህ ይሁንልኝ ይደረግልኝ።እኔ ለእግዚአብሔርባሪያው ነኝ" በማለት የምሥራቹን ቃል ተቀብላዋለች።      በዚህ ጊዜ ቃሏን ምክንያት አድርጎ ሰማይና ምድር የማይወስኑት ጌታ ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍስዋም ነፍስን በመንሳት በፍጹም ተዋሕዶ በማኅጸኗ አድሯል።      ስለዚህም የማክሰኞ ዕለት ምድር(እርሻ) ለእመቤታችን ምሣሌ ሆና በቅዱስ ኤፍሬምና መንፈስ ቅዱስ በገለጸላቸው በሌሎችም ሊቃውንት ተመስላለች።      ምክንያቱም አስቀድማ ባዶ የነበረችው ምድር  ለፍጥረታቱ ሁሉ የሚሆን ምግበ ሥጋን ዘር ሳያስፈልጋት  እንዳስገኘች ሁሉ ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያምም ዘርአ ብዕሲ(የወንድ ዘር) ሳያስፈልጋት የሕይወት(የነፍስ) ምግብ፣የጽድቅ ፀሐይ፣የዓለሙ መድኅን የሆነውን ጌታ አስገኝታልናለች። ይቀጥላል........ ጽንዕት በድንግልና ስርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን። ጣዕሟን በልቦናችን ፍቅሯን በአንደበታችን ያሳድርብን። ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን።

  • .            ✝ ጽንሰታ  ለማርያም ✝ ውድ ቤተሰቦቻችን እንደ ምን ከረማችሁ?      ዛሬ ነሐሴ ፯ ቀን እመ አምላክ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተጸነሰችባት ልዩ ዕለት ናት።       እመቤታችን ሠላሳ ሶስት የተቀደሱ በዓላት ሲኖሯት ቀዳሚው በአሏ በዛሬው ዕለት በቅድስት ቤተክርስቲያናችን በታላቅ መንፈሳዊ ስነ-ሥርዓት የሚከበረው  በአለ ጽንሰቷ ነው። የእመቤታችን ጽንሰቷ እንዴት ነው???       የእመቤታችን ቅድመ አያቶቿ ቴክታና በጥሪቃ ይባላሉ። ይህ  ቀራቸው የማይባሉ ባዕለ ጸጎች ነበሩ።ከዕለታት በአንደኛው ቀን ከግምጃ  ቤት ገብቶ፣ የገንዘባቸውን (የሃብት ንብረታቸውን) ብዛት ተመልክቶ ቴክታ "እኔ መካን አንቺ መካን ይህ ሁሉ ገንዘብ(ሃብትና ንብረት)  ለማን ይሆናል?" አላት።          እሷም "እግዚአብሔር ከእኔ ልጅ ባይሰጥህ ከሌላ ሊሰጥህ ይችላልና ሌላ ሴት አግብተህ አትወልድምን?"  አለችው። እርሱም" ይህንን እንደማላደርገው አምላከ እሥራኤል ያውቃል" አላት።         በዚህ ጊዜ አዘኑ።ወዲያው ራዕይ አይተዋል። ነጭ እንቦሳ እየወለደች እስከ ስድስት ስትደርስ ስድስተኛይቱ ጨረቃን ጨረቃ ፀሐይን ስትወልድ አይተው በአገራቸው ህልምን ፈቺ  ሰው አለና ሄደው ነገሩት።      ህልም ፈቺው ሰውም "ልጅ ትወልዳላችሁ። ጨረቃይቱም  ከፍጡራን  በላይ የምትሆን ልጅ ትወልዳላችሁ። የፀሐይ ነገር ግን አልተገለጠልኝም እንደ ነቢይ እንደ ንጉሥ ያለ ይሆናል" አላቸው።እነርሱም  "ጊዜ ይተርጉመው" ብለውት ሄዱ።       ከዚህ በኋላ ቴክታ ጸነሰች ወለደችም።ስሟን ሄኤሜን አለቻት። "ስዕለቴን፣ ምኞቴን፣ የልቤንም መሻት አገኘሁ" ማለት ነው። ሄኤሜን ዴርዴን፣ ዴርዴ ቶናን፣ ቶና ሲካርን፣ ሲካር ሄርሜላን፣ ሄርሜላ ሐናን ወለደች።      ሐና ለአካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ ይሁዳ ለተወለደ ኢያቄም ለሚባል ደግ ሰው አጋቧት። ምክነት(አለመውለድ) ወርዶ(ተላልፎ) እርሷም እንደ አያቶቿ ሆናለች። ሃብትና ንብረታቸው  ግን እንደ አያቶቿ ሳይሆን የእነርሱ በመጠን ሆኗል።      ከጎረቤቷ በዝሙት የምትተዳደር አንዲት ሴት ነበረች። በአንደኛው ቀን ሐና ጎረቤቷን  "ቤተ መቅደስ እስማለሁ ብዬ ነበር። ነገር ግን የምለብሰው ልብስ የለኝም አለቻት"።       ጎረቤቷም  "የእኔ ልብስ ከአንድም ሁለት ሶስት አለልሽ አይደለምን? ልስጥሽና  ለብሰሽ ሂጂ" አለቻት። ሐናም "ያንቺ ልብስ የተሰበሰበው በኃጢአት(ዝሙት) በተገኘ ዋጋ(ገንዘብ) ነው። እግዚአብሔር ደግሞ ንጹሐ ባሕርይ ነውና ንጹሕ ነገር ይወዳል። ይህንን ለብሼ ብለምነው አይሰማኝም ብዬ ነው" አለቻት።      ጎረቤቷም  "ሐናን በምን ምክንያት ልጅ ነሳት እያልሁ ሳዝንልሽ እኖር ነበር። ለካ እንደ ድንጋይ አድርቆ ያስቀረሽ ይህ ክፋትሽ ነው" አለቻት።በዚህም ሐና  አዝናለች።      አንድም ሐናና ኢያቄም መስዋዕት እናቀርባለን ብለው ከቤተ መቅደስ ሄዱ።ሊቀ ካሕናቱ ሮቤል ይባላል። "እናንተማ ብዙ ተባዙ ብሎ ለአዳም የሰጠውን ጸጋ ያስቀረባችሁ ርጉሞች ብትሆኑ  አይደለምን? ቢጠላችሁ ነው እንጂ ቢወዳችሁማ ኑሮ ልጅ ይሰጣችሁ ነበር። መስዋዕታችሁን አልቀበልም" ብሏቸዋል። በዚህም ምክንያት እያዘኑ ተመልሰዋል።      እያዘኑ ሲመለሱ ከዛፍ ስር ተቀምጠው ሳሉ ርግቦች ከልጆቻቸው ጋር ሲጫወቱ፣ ዕፅዋትም  አብበው አፍርተው አይታ ርግቦችን በባሕርያቸው እንዲራቡ(ራ ይጠብቃል) ዕፅዋትን እንዲያብቡ እንዲያፈሩ የምታደርግ፤ የእኔ ተፈጥሮዬ ከድንጋይ ይሆን? ልጅ የነሳኸኝ"። ብላ አዘነች።      ከቤታቸው ሄደው "ወንድ ልጅ ብንወልድ ወጥቶ ወርዶ፣ አርሶ ቆፍሮ ይርዳን አንልም። ለቤተ እግዚአብሔር አንጣፊ፣ ጋራጅ(መጋረጃን የሚጋርድ) ሆኖ ይኖራል።ሴት ልጅ ብንወልድ ደግሞ እንጨት ሰብራ ውኃ ቀድታ ትርዳን አንልም ለቤተ እግዚአብሔር መሶበ ወርቅ ሰፍታ፣ መጋረጃ ፈትላ ትኑር" ብለው ብፅዓት ገብተዋል(ስዕለት ተስለዋል)።      ሐምሌ ሰላሳ ዕለት እርሷ ለእርሱ "ፀምር ሲያስታጥቁህ መቋሚያህ አፍርታ ፍጥረት ሁሉ ሲመገባት አየሁ"። ብላ ነገረችው። እርሱ ለእርሷ "ነጭ ርግብ ሰባቱን ሰማያት ሰንጥቃ መጥታ በራስሽ ላይ ስታርፍ፣ በቀኝ ጆሮሽ ገብታ በማኅጸንሽ ስታድር አየሁ" ብሏት በራዕይ ያዩትን ተጨዋውተዋል።       በአገራቸው ህልምን ፈቺ ሰው ነበረና ሄደው ነገሩት። "ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ" አላቸው። እነርሱም "አንተስ አልፈታኸውም ጊዜ ይፍታው" ብለው ተመልሰዋል።         ይህ በሆነ በሰባተኛው ቀን(ነሐሴ ፯) ቀን  መልአከ እግዚአብሔር መጥቶ "ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው በዚያኑ ቀን እመቤታችን በመልአኩ አብሳሪነትና በልዑል እግዚኘብሔር ፈቃድ ተጸነሰች።     በተጸነሰችም ጊዜ ብዙ ተአምራት ተደርጓል።በርሴባ የምትባል አንድ ዐይና አክስት ነበረቻት። "ሐና እግዚአብሔር በረድኤት ጎበኘሽ መሰለኝ። ጡትሽ ጠቁሯል፣ ከንፈርሽ አሯል" ብላ ማኅፀኗን ዳስሳ ዐይኗን ብታሸው በርቶላታል። ይህንን አብነት አድርገው ሕሙማን ሁሉ ማኅፀኗን እየዳሰሱ የሚፈወሱ ሆነዋል።        ዳግመኛም ሳምናስ የሚባል የአጎቷ ልጅ ነበር ሞተ። ትወደው ነበርና የአልጋውን ሸንኮር ይዛ እየዞረች ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት ተነስቶ "ሰማይና ምድርን የፈጠረ  አያቱ ሆይ ሰላም ላንቺ ይሁን"  ብሎ ከሕልም ፈቺው የቀረውን ተርጉሞላታል።      ከዚህ በኋላ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና "ቀድሞ ከእነዚህ ወገን የሚሆኑ ዳዊትና ሰሎሞን አርባ አርባ ዘመን እንደ ሰም አቅልጠው፤ እንደ ገል ቀጥቅጠው ገዙን። ደግሞ ከዚች የተወለደ እንደምን ያደርገን ይሆን?" ብለው በጠላትነት ተነሱባቸው። መልአከ እግዚአብሔር ኢያቄምን ወደ ሊባኖስ ተራራ ይዘሃት ሂድ ብሎት ይዟት ሄደ። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚያ ተወልዳለች።"ከሊባኖስ ሙሽራ ትወጣለች" ተብሎ የተነገረው ለዚህ ነው። ይቆየን። ይቀጥላል.... ጽንዕት በድንግልና ስርጉት በቅድስና  እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን። ጣዕሟን በልቦናችን ፍቅሯን በአንደበታችን ያሳድርብን። ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን

  • ✝  የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የዕረፍቷና የትንሣኤዋ ነገር  ✝        እመቤታችን ቅድስት ድንግል  ማርያም  በ64 ዓመቷ ጥር 21 በ48ዓ.ም  በሰንበተ  ክርሰቲያን እሁድ አርፋለች።ሐዋርያት በአጎበር(በቃሬዛ) አድርገው ወደ ጌቴ ሴማኒ ሊቀብሩ ይዘዋት ሲሄዱ "አይሁድ ቀድሞ ልጅዋን ተነሣ አረገ እያሉ ሲያውኩን ይኖራሉ።ዛሬ ደግሞ እርሷን ተነሳች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለምን? በእሳት እናቃጥላታለን" ብለው ተነሱ።      ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ተራምዶ አጎበሩን ጨበጠው።መልአክ ሁለት እጆቹን በሰይፍ ቢቀጣው ከአጎበሩ ላይ ተንጠልጥሎ ቀረ።ከዚህ በኋላ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስን ጨምሮ በደመና ነጥቆ፣ ከገነት አግብቶ ከዕፀ ሕይወት(ከሕይወት ዛፍ) ስር  አኖራት።       ቅዱስ ዮሐንስን "እንደምን ሆነች?" አሉት። "ከገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር አለች"። አላቸው። ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ ብለው በነሐሴ መባቻ(መግቢያ) በዕለተ ሰኑይ(ሰኞ) ጾም ጀመሩ።ሁለት ሱባኤን እንደጾሙ  እሁድ ነሐሴ 14 ቀን የእመቤታችንን ትኩስ አሰከሬን አምጥቶ ሰጥቷቸው ቀብረዋታል።ማክሰኞ ነሐሴ 16 ተነስታለች። "ከመ ትንሣኤ ወልዳ  እንደ ልጅዋ ትንሣኤ" የተባለውም ለዚህ ነው።      ከአሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት አንዱ የነበረው ቅዱስ ቶማስ አብሯቸው አልነበረም።ደመና ጠቅሶ(በደመና ተጭኖ) ከአገረ ስብከቱ ሲመጣ ስታርግ አገኛት።"ቀድሞ የልጅሽን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ። አሁን ደግሞ ያንቺን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁን?" ብሎ ከደመናው ሊወድቅ ፈለገ።      እመቤታችንም "አይዞህ አትዘን እሊያ(አስራ አንዱ ደቀ መዛሙርት) ትንሣኤዬንም ዕርገቴንም አላዩም።አንተ አይተሃል።ተነሳች ዐረገች ብለህ ንገራቸው"። ብላ የያዘችውን ሰበን(የመግነዟን ጨርቅ)) ሰጥታ ሰደደችው።       ከዚህ በኋላ ቅዱስ ቶማስ ሄዶ  ወንድሞቹ ሐዋርያትን "የእመቤታች ነገር እንደምን ሆነ?" አላቸው። እነርሱም "አግኝተን ቀበርናት" አሉት። "ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር ተዉ ይህ ነገር  አይመስለኝም" አላቸው። ቅዱስ ጴጥሮስም አንተ ልማድህ ነው።አንተ ራስህ ተጠራጥረህ ብቻህን  አትቀርም ።ሰውን ሁሉ ስታጠራጥር ትኖራለህ።" አለው።      እርሱም(ቶማስ) የያዘውን ያውቃልና ዝም ብሎ ይሰማቸዋል።ከዚህ በኋላ ቅዱስ ጴጥሮስ ተቆጥቶ ሄዶ መቃብሩን ቢከፍተው አጣት። ደንግጦ ቆመ። ቅዱስ ቶማስም "አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችንስ ተነሳች ዐረገች አላቸው። የያዘውንም ሰበን  ሰጣቸው።ለበረከት ተካፍለውታል። ዛሬ አባቶቻችን የሚይዙት መስቀል ላይ የሚገኘው እራፊ ጨርቅ የዚያ ምሣሌ ነው።       ከዚህ በኋላ በዓመቱ "ቶማስ ትንሣኤሽን ዕርገትሽን አይቶ እኛ ሳናይ" ብለው መጾም ጀመሩ። በ16ተኛው ቀን እመቤታችንን መንበር አድርጎ ቅዱስ ጴጥሮስን ረዳት(ንፍቅ ቄስ) ቅዱስ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ ጌታ ራሱ ገባሬ ሠናይ ካህን ሆኖ ቀድሶ አቁርቧቸዋል።       እኛ ኦርቶዶክሳውያንም  አባቶቻችን በሠሩልን ሥርዓት ባቆዩልን ትውፊት መሠረት እነርሱን አብነት በማድረግ  በየዓመቱ በአማላጅነቷ ከልጅዋ ይቅርታን ለማግኘት የእናትነት ፍቅሯን ለመቅመስ በረከቷን ለመቋደስ ስንል እንጾማለን(ሱባዔ እንገባለን)። ይቆየን። ይቀጥላል...... ጽንዕት በድንግልና ስርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን። ጣዕሟን በልቦናችን ፍቅሯን በአንደበታችን ያሳድርብን ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን። አሜን።

  • .                       ✝ ጾመ ፍልሰታ ☦ ✍  ጾም ማለት፦ "ጾመ - ተወ፣ ታቀበ፣ ታረመ፣ ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም፦ ምግብ መተው(አለመብላት)፣ መከልከልና መጠበቅ(ጠ ይጠብቃል) ማለት ነው።በጾም ጥሉላት መባልዕትን(ምግቦችን) ፈጽሞ መተው፣ ሠውነትን አብዝቶ ከመብላትና መጠጣት እንደዚሁም ከሌላው ክፉ ነገር ሁሉ መጠበቅ፣ መግዛት፣ መቆጣጠር፣ በአጠቃላይ ፈቃደ ሥጋን ለፈቃደ ነፍስ ማስገዛት ነው።በንስሐ ታጥቦ በጸሎት ወደ ልዑል እግዚአብሔር መቅረብና እርሱንም ደጅ መጥናት ነው።   ✍ "ፍልሰታ" ማለት ምን ማለት ነው??? ፍልሰታ ማለት "ፈለሰ" ከሚለው የግዕዝ ግሥ የወጣ ሲሆን  ትርጉሙም መሰደድ፣ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መንቀሳቀስ፣ መዘዋወር ማለት ነው። ፍልሰታ ማርያም ሲባልም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሞት ተነስታ፣ ከከርሠ መቃብር ወጥታ ከሚያልፈው ዓለም ወደ ማያልፈው ዓለም ወይም ከሥጋዊው ዓለም ወደ መንፈሳዊው ዓለም የተሸጋገረችበት ነው።    ✍ እንዴት???? ታሪኩ ይቀጥላል። ፍቅሯን በአንደበታችን ጣዕሟን በልቦናችን ያሳድርብን።አሜን። ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን

  • видео или голосовое, без подписи

  • .    ታሪክ በዛሬዋ  ዕለት(ሐምሌ 26)           አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን         በደረጀ እሸቴ(ወልደ ሥላሴ) ሰላም ለኩልክሙ ኦ ውሉደ ፍሬ ሃይማኖት እንደምን ሰነበታችሁ❓ ውድ ቤተሰቦቻችን    አገራችን ኢትዮጵያ ምንም እንኳን ክርስትናን የተቀበለችው ባኮስ (አቤላክ) በተባለው የኢትዮጵያ ንግሥት የህንደኬ በጅሮንድ  አማካኝነት በአንደኛው መ/ክ/ዘ ቢሆንም እስከ አራተኛው መ/ክ/ዘ ድረስ የኤጲስ ቆጶስነት መንበር አላገኘችም ነበር።          ሩፊኖስ የተባለ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ፀሐፊ እንደጻፈው ሜሮጵሰዮስ የተባለ ጢሮሳዊ(ግሪካዊ) ነጋዴ  ፍሬምናጦስና ኢዲስዮስ የተባሉ ዘመዶቹን በማስከተል ከአገሩ ተነስቶ ወደ ሕንድ አቅጣጫ በጀልባ ጉዞውን ጀመረ።በጉዞውም ወደ አፍሪካ የባሕር ጠረፍ በመምጣት በቀይ ባሕር ወደብ ውሃ ለመጠጣትና እግረ መንገዱንም አገር ለማየት ጀልባውን ጠረፍ ላይ አቆመ።ነገር ግን እርሱ እንዳሰበው ሳይሆን በአካባቢው የነበሩ ሰዎች በጀልባቸው ላይ አደጋ ጥለው እርሱን እና የጀልባዋን ቀዛፊዎች ገድለው ሃብታቸውን ዘረፏቸው።       ባላሰቡት ሁኔታ ከሜሮጵዮስ የተለዩት ወጣቶቹ ወንድማማቾች ፍሬምናጦስና ኢዲስዮስ ቋንቋውንና ባሕሉን በማያውቁት አገር ብቻቸውን በመቅረታቸው እያዘኑና እያለቀሱ ከዛፍ ስር ተቀምጠው ይጸልዩ ጀመር።እነዚህን ወጣቶች በማየታቸው የተገረሙት መንገደኞች ከዚያ ቦታ አንስተው በወቅቱ የአክሱም ንጉሥ ለነበረው ታዜር "ይኸው ምርኮ አመጣንልህ" በማለት አስረከቧቸው።      ንጉሡም ወጣቶቹ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ያድጉ ዘንድ ፈቃዱ ሆነና ከልጆቹ አብርሃና አጽብሃ ጋር አንድ ላይ ማደግ ጀመሩ።  ከዓመታት በኋላ በአዕምሮ መብሰላቸውን በጥበብም ማደጋቸውን የተመለከተው ንጉሥ ታዜር ፍሬምናጦስን በጅሮንድ ኢዲዮስን ደግሞ ጋሻ ጃግሬው አድርጎ ሾማቸው።ወጣቶቹም ሹመቱን በመቀበል በቤተ መንግሥቱ በማገልገል ላይ እንዳሉ ንጉሡ አረፈ።በዚህ ጊዜ ግሪካውያኑ ወጣቶች ነጻ ወጣን በማለት ወደ አገራቸው ሊሄዱ ተነሡ።ነገር ግን መንግሥቱን በሞግዚትነት የተረከበችው ንግሥት አሕየዋ (ሰፊያ) ልጆቿ ኢዛናና ሳይዛና (በኋላ አብርሃና አጽብሃ) አድገው ዙፋኑን እስኪረከቧት ድረስ በአስተዳደር እንዲረዷት ለመነቻቸው።እነርሱም ጥያቄዋን ተቀብለው ጉዟቸውን በመተው በዚያው በቤተ መንግሥቱ በአማካሪነት ሲያገለግሉ ቆዩ።      ከዓመታት በኋላ ታናሽ ወንድሙ ወደ አገሩ በመሄዱ በብቸኝነት የቀረው ፍሬምናጦስ ለክርስትና እምነቱ ቀናኢ ስለነበር አስቀድሞ በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ተሰብኮ በአክሱምና በአካባቢዋ የነበረው የክርስትና እምነት የሚስፋፋበትን መንገድ ዘወትር ያስብ ነበር።ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ሃይማኖት ብቻ እንጂ ክህነት፣ቁርባን፣ወዘተ የመሳሰሉትን ምሥጢራት የሚፈጽምላቸው ካህናትን የሚሾምላቸው ኤጲስ ቆጶስ ስለሌላቸው ያዝኑ እንደነበር ተመለከተ። ይህን የሕዝቡን ሐዘን ለማቆም የበኩሉን ጥረት ለማድረግ ወስኖ ጉዳዩን የአባታቸውን መንግሥት ለተረከቡት አብርሃና አጽበሐ ማስረዳቱን ቀጠለ።       ነገሥታቱም ጉዳዩን ሙሉ በሙሉ በመቀበል ተግባራዊ የሚሆንበትን መንገድ  ሲያሰላስሉ በፍሬምናጦስ ምክር ከአንድ ውሳኔ ላይ ይደርሳሉ።እነርሱም ፍሬምናጦስን የእኛን ቋንቋና ባህል ከአንተ ሌላ የሚያውቅ የለምና አንተ ወደ እስክንድርያ ሄደህ ክህነትንና ቁርባንን አምጣልን ብለው እርሱን ወደ እስክንድርያ ሰደዱት።ፍሬምናጦስ ወደ እስክንድርያ የተላከው እንደ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ነው እንጂ የትውልድ አገሩን ወክሎ እንዳልሆነ ልብ ይሏል።        ፍሬምናጦስ እስክንድርያ የደረሠው እለ እስክንድሮስ አትናቴዎስን አስከትሎ በጉባዔ ኒቅያ ለመካፈል በሔደበት ወቅት ነበርና እስኪመለሱ ድረስ በዚያው ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን እየተማረ በትዕግስት መጠበቅ ግድ ሆነበት።      እለ እስክንድሮስ በጉባዔ ኒቅያ በአትናቴዎስ አፈ ጉባኤነት አርዮስን ረትቶ ከተመለሰ በኋላ ወዲያው ስላረፈ በመንበሩ አትናቴዎስ ተተካ።ፍሬምናጦስ የተላከበትን ዐብይ ጉዳይ ለሐዋርያዊው ቅዱስ አትናቴዎሰ አቀረበ።አትናቴዎስ ስለ ኢትዮጵያውያን ሃይማኖት በሚገባ ከተረዳ በኋላ ለፍሬምናጦስ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ አስተምሮ "ኤጲስ ቆጶስ ዘአክሱም ወዘኩላ ኢትዮጵያ"ብሎ በቅብዓትና በአንብሮተ ዕድ ሹሞ ላከው።ፍሬምናጦስ ጵጵስናውን ተቀብሎ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሰ በኋላ 👉 የወንጌልን ትምሕርት በስፋት ለሕዝቡ የሚያዳርሱ፣የሚያጠምቁና የሚያቆርቡ ካህናትንና ዲያቆናትን ሾመ። 👉 በአብርሃና በአጽብሃ አማካኝነት አያሌ አብያተ ክርስቲያናትን አሳነጸ። 👉 በዘመኑ የኢዮዮጵያ ግዛት ወደ ነበሩት ኑብያ፣ አኑኖ እና መርዌ አምስት ቆሞሳትን በመላክ ትምሕርተ ወንጌል እንዲሰበክ፤ ቤተ ክርስቲያን እንድትስፋፋ አደረገ። 👉 ቅዱሳት መጻሕፍትን ከሱርስት፣ ከዕብራይስጥና ከግሪክ ወደ ግዕዝ እንዲተረጎሙ አደረገ። 👉 የሳባውያንን የፊደል አቀማመጥ በመለወጥ ከግራ ወደ ቀኝ የመጻፍንና የማንበብን ዘዴ ያስተማረው እርሱ ነው። 👉 በዚህም መሠረት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ በ350ዓ.ም እንዲታወጅ አድርጓል።ኢትዮጵያውያን ይህንን ታላቅ አባት በሃይማኖቱና በምግባሩ ስለወደዱት "አቡነ" (አባታችን) የሚለውን መዓርግ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰጡት ለእርሱ ነው።በብርሃናዊ ሥራውም "ከሣቴ ብርሃን" (ብርሃን ገላጭ) ብለውታል።      አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን የተባለው ፍሬምናጦስ በኢትዮጵያ ክርስትና እንዲስፋፋ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ በመውጣትና በመውረድ የሚገባውን ሁሉ ከፈጸመ በኋላ ልክ በዛሬዋ ዕለት ሐምሌ 26 ቀን 352ዓ.ም አረፈ። ረድኤትና በረከቱ በሁላችንም ላይ ይደርብን። አሜን። ተጻፈ ሐምሌ 26 ቀን 2018ዓ.ም በ8:00 ሰዓት።

  • ✨በስመ አብ ወወልድ ወወልድ ወመን ፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ✨ “ እግዚአብሔርን አመስግኑ መዝሙር መልካም ነውና“ መዝ 147፥1 እንኳን ደስ አለን ለሁለተኛ ዙር በመዝሙር ክፍል ሲሰጥ የነበረው የድምጽ መዝሙር ጥናት  ምርቃት በ25/11/2018 ዓ/ም  በደማቅ ሁኔታ  የተመራቂ ወላጆች መምህራን ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከናወነ  ። እግዚአብሄር አገልግሎታችሁን ይቀበል። ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን  እናታችንን ፍሬ ሃይማኖትን በዘመናችሁ ሁሉ የምታገለግሉበት መልካም እና ጥሩ የአገልግሎት ህይወት ላይ ለመድረስ መነሻ ይሆናችሁ ዘንድ   መንፈሳዊ ምኞታችን ነው

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

ፍሬ ሃይማኖት — tgindex