tgindex
ዝክረ ቅዱሳን

ዝክረ ቅዱሳን

Статистика

ይህ የቴሌግራም ቻናል ከአምላካችን ከእግዚአብሔር እና ካከበራቸው ቅዱሳኑ ከቃል-ኪዳናቸው የምንካፈልበትና ዝክራቸውን የምናስብበት አገልግሎት ነው። "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

Последний пост
12 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Видео (по похожим)
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
1 554
мало замеров
Замеров пока мало
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
215
20 постов
Вовлечённость
13,8%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
57
1/48двое суток
65
1/72трое суток
70

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 12 авг.65из Fewus_Menfesawi

    https://youtu.be/OnPI7IQxZTo?si=JnMeDfWYF57WH2hi

  • 7 авг.1361из Fewus_Menfesawi

    https://youtu.be/-qoDOnasIwg?si=8Q-yvkrH4zvKyQyp

  • https://www.youtube.com/live/26mF4fgOfsI?si=AluAGPgQJk4LJC-x

  • 3 авг.190из AbaGebrekida

    https://youtu.be/I4MNakuh-Es?si=ULQWilmzFsyRABEH

  • 31 июл.197из AbaGebrekida

    https://youtu.be/LRL5uz6h46M?si=I0HeQOV-1V8cuTxu

  • 28 июл.194из Fewus_Menfesawi

    https://youtu.be/3bMB_3N_5QI?si=WKkmqX30293KiYJN

  • 25 июл.211из Fewus_Menfesawi

    https://www.youtube.com/live/ezAOtDd5bjw?si=DCXucEb0Mgm6Wu0e 🔴 ሥርዓተ ማኅሌት ከርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም | ቀጥታ ስርጭት | ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ | Aba Gebrekidan

  • 21 июл.258из Fewus_Menfesawi

    https://youtu.be/pGGvBWEte6I?si=tIk18aBvWxvsmQUV

  • 16 июл.264из Fewus_Menfesawi

    https://youtu.be/1mJi5cimtmE?si=541pzbnC0htmC7Lo

  • 14 июл.254из Fewus_Menfesawi

    https://youtu.be/PMN66MAF1fg?si=Yi225uwO635On43o

  • 4 июл.288из AbaGebrekida

    https://www.youtube.com/live/yGdscZuI3SI?si=pXkiZO18AV4ZnRhG

  • 2 июл.307из AbaGebrekida

    ይህንን ዓላማ ለመፈጸም ለምንገነባው ሆስፒታል በቂ ቦታ ለማግኘት የረዳንን እግዘብሔርን እርሱም ያከበራቸው ቅዱሳንን እያመሰገንን በእውነተኛው መድኃኒታችን በመድኃኔዓለም ቀን የሆስፒታላችን የመሠረት ድንጋይ ልናስቀምጥ መሆናችን ደግሞ ደስታችንን ዕጥፍ ድርብ ያደርገዋል። ከዚህም የደረስነው ነገም የምንደርሰው በማይናወጸው መሠረት በእርሱ ላይ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቁመን ነውና። ከመስቀሉ ሥር እናቱን “እናት ትሁናችሁ” ብሎ ባይሰጠንስ ቋጠሮ ሲጸናብን ማን ለእርሱ ነግሮ ያስፈታልን ነበር? ልጅ እያለን ወደ ወላጅ እናታችን እናለቅስ ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ከመድኃኔዓለም እናት እያለቀስን የወደድነውን የምንቀበልባት እናት ድንግል ማርያምን ስለሰጠንም እናመሰግነዋለን ። ውድ ኦርቶዶክሳውያን ይህንን መሬት እንድናገኝ የረዱንን ሁሉ የጉባኤ አምላክ ይስጥልን በሰማይ ቦታ ይስጣችሁ እያላችሁ እንድትመርቁልን እየጠየቅን፤ ቀዳሚት ፳፯-፲-፳፲፰ ዓም ከጧቱ 3:00 ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በተገኙበት በባሕርዳር የመሠረት ድንጋዩን ስለምናስቀምጥ እንኳን አደረሳችሁ፣እንኳን ደስ አላችሁ፣ አብራችሁን ለቆማችሁ ሁለ መድኃኔዓለም ከእናንተ ጋር ይሁን። እግዚአብሔር ገባሬ ኩሉ ወጣኔ ኩሉ ወፈጻሜ ኩሉ አኃዜ ኩሉ ወጸባጤ ኩሉ ሁሉን የጀመርህ ሁለን የምትፈጽም ሁሉን የያዝህ ሁሉን የወሰንህ መድኃኔዓለም ሆይ ከአንተው ተጠግተን የጀመርነውን እንደምትፈጽምልን ፈጽመን እናምናለን ። ለአንተ ለባሕርይ አባትህ ለአብ ለማሕየዊ መንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን ! አባ ገብረ ኪዳን ግርማ የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶች እና የእናቶች አንድነት ገዳም የ ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር መምህር

  • 2 июл.201из AbaGebrekida

    ፫. ሁለንተናዊ ፈውስ ለመስጠት ቤተ ጉባኤያችን የወንጌል ቤተ ጉባኤ እንደመሆኑ ወንጌል ደግሞ የፈውስ ሕግ ናት፣ ስለሆነም ቤተ ጉባኤያችን ኃጢአትን በንስሐ ፣ አለማወቅን በማስተማር እንደሚፈውስ ሁሉ የታመሙትን ደግሞ በማኅበር ጸሎት፣ በጸበል እንዲሁም እግዚአብሔር እጁ ሰፊ ነውና በሕክምና አገልግሎትና በሰብአዊነት ተግባር ለሰዎች ፈውስ ለመስጠት ይህንን ሆስፒታል ሊገነባ ዝግጅቱን እየፈጸመ ነው። ፬. ወንጌል የተስፋ ሕግ ናት። ከአበው አንዱ መከራን ምን ያቀለዋል ቢሉት “ እስመ ተስፋ ያቀልሎ ለምንዳቤ - መከራን የሚያቀለው ተስፋ ነው ብሏል። በመሆኑም ተስፋችሁ አልቋል የተባሉ ወገኖቻችንን ሁሉ በመንከባከብ ልቡናቸው በሰላም እንዲያርፍና በተስፋ ምርኩዝነት ዘመናቸውን በዕረፍት እንዲፈጽሙ ማድረግ። ፭.ሰው መሥራት ፦ በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አረዳድ መሠረት የሰው ልጅ የፍጥረታት ዘውድ ነው። እግዚአብሔርን መስሎ የተፈጠረ እርሱ ነው፣ ከሰማይ በታች ያሉ ፍጥረታትን እንዲያስተዳደር ሥልጣን የተሰጠው ሰው ነው፣ ክርስቶስ የሞተለት የዘለዓለም ተስፋ የተሰጠውም ሰው ነው። በመሆኑም ቤተ ጉባኤያችን ክቡሩን የሰው ልጅ የቅድመ ጋብቻ ትምህርት በመስጠት፣ የባለትዳሮች እና የልጅ አስተዳደግ ሥልጠና በመስጠት፣ በሱስ የተጎዱ ወንድሞቻችንን በመንከባከብና እንደገና አዲስ ሰውንት እንዲያገኙ በማድረግ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ሆነ ለሀገራችን በጎና ባለ አእምሮ ትውልድ ለመፍጠር ይህንን ሆሰፒታል ልንገነባ እየተፋጠንን ነው።

  • 2 июл.170из AbaGebrekida

    እግዚአብሔር ያለው ነገር እርሱ በወደደው ትክክለኛው ሰዓት ይፈጽማልና ፕሮጀክቱን ይፋ ባደረግን በዓመቱ በዚያው ቀን በወላዲተ አምላክና በቅዱሳን ጸሎት፣ ቅን ልቡና ባላቸው ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን ጥረት ሆስፒታሉን ለመገንባት የሚያስችል 30,000 ካሬ ቦታ በባሕር ዳር ከተማ ሰኔ ፲፱-፳፲፰ ዓም በጉባኤ ቤታችን ምሥረታ ቀን ስለተቀበልን አምላከ ቅዱስ ገብርኤልን እናመሰግነዋለን ። ሆስፒታሉን የምንገነባባቸው ዓላማዎቻችንም፦ ፩. ፍጥረትን ሁለ በእግዚአብሔር መንገድ ለማገልገል፦ እግዚአብሔር አምላካችን ለክፉዎችና ለደጎች፣ለኃጥአና ለጻድቃን ዝናምን እንደሚያዘንብ ፣ፀሐይን እንደሚያወጣ የሆስፒታላችን ዓላማም ለሁሉም በምሕረት፡ እምነትን፣ ዘርንና ማንነትን ሳይለይ፣ ለሰው ልጅ ሁሉ የሚታዘንበት የምሕረት ማረፊያ መሆን ነው። ፪.ለጥበብና ለሳይንስ፦ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በሀገራችን የነበራትን የጥበብ ታሪክ በዘመናዊ የምርምር ዐቅም ማስቀጠል።

  • без подписи

  • без подписи

  • 2 июл.188из AbaGebrekida

    እንኳን ደስ አላችሁ ! “ እግዚአብሔር ገባሬ ኩሉ ወጣኔ ኩሉ ወፈጻሜ ኩሉ አኃዜ ኩሉ ወጸባጤ ኩሉ - ሁሉን የጀመረ ሁሉን የፈጸመ ሁሉን የያዘ ሁሉን የወሰነ እግዚአብሔር ” ለመላው ኦርቶዶክሳውያን ፣ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ሁሉን የምትችል የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችን ጋር ትሁን እንደምን ሰነበታችሁ? እኛ አምላከ አበው እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን ደኅና ነን። የተወደዳችሁ የቤተ ጉባኤያችን ቤተሰቦች፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት የሚገኘው የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ትርጓሜ ምስክር ት/ቤት፣ ቀድሞ ጌታ ከመወለዱ ዘጠኝ መቶ ዓመት በፊት መጻሕፍተ ነቢያት ሲተረጎሙበት፣ ኋላም ቅዱስ ያሬድ ሲያስተምሩበት፣ መምህር ኤስድሮስ ምሥጢር ያገመሩበት ገዳም እንደመሆኑ ሰኔ ፲፱-፳፲፬ ዓም የቀደመ ታሪኩን ለመመለስ ቤተ ጉባኤው እንደገና ተመሥርቷል። በመሆኑም በነዚህ ያለፉት አራት ዓመታት ውስጥ ፷፬ ደቀ መዛሙርትን ተቀብሎ አራቱን ጉባኤያት እያስተማረ ይገኛል። በተጨማሪም ለምእመናን በፈውስ መንፈሳዊ ሚዲያ ወንጌልን በአበው ቅዱሳን ሊቃውንት አስተምህሮ በማዳረስ ላይ ነው። በዓመት ውስጥ ለመነኮሳት ሥርዓተ ምንኩስናን በሚመለከት፣ለካህናት ኦርቶዶክሳዊ ኖላዊነትን በሚመለከት፣ ለምእመናን ስለ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብእና ስለ ልጅ አስተዳደግ ሥልጠናዎችን ይሰጣል። ከዚህም ጋር ደግሞ በሚከተሉት ወርቃማ ምክንያቶች ጠቅላላ ሆስፒታል በባሕር ዳር ከተማ ለመገንባት ፕሮጀክቱን ይፋ ካደረግንበት ከሰኔ ፲፱- ፳፲፯ ጀምሮ ለአንድ ዓመት ያክል በሀገረ ስብከታችንና በጠቅላይ ቤተ ክህነት ፈቃድ እንቅስቃሴ ስናደርግ ከርመናል።

  • 30 июн.270из Fewus_Menfesawi

    https://youtu.be/mdFklvUVw90?si=wyT4hAZBJezwH7bQ

  • https://www.youtube.com/live/bQL2kgh8RZs?si=cP40Gm4rcBV2fayg

  • 23 июн.264из Fewus_Menfesawi

    https://youtu.be/J-xKd4dsSuM?si=MgqSeu90dfkFXq87