tgindex
ďż˝

𝗔𝗕𝗖 𝗡𝗘𝗪𝗦 𝗔𝗠𝗛𝗔𝗥𝗜𝗖

Статистика
@ABCNEWSAMHARICангНиКскиК

This public channel features all aspects of life in # Ethiopia, # News # Zena # News #Reviews

Последний пост
17 авг.
Последнее чтение
ещё не заходили
Постов за неделю
6
Всего постов
528
Тип
открытый
Язык
ангНиКскиК
В каталоге с
12 авг.
Подписчики
759
0 Са 5 дн.
Сутки
−2
−0,26%
Неделя
—
 
Месяц
—
 
Просмотров на пост
124
40 постов
Вовлечённость
16,3%
к подписчикам
Постов в день
0,9
всогО 528
УпОПинаниК
0
канаНОв
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
69
1/48двое суток
79
1/72трое суток
85

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • " በስራችን በርካታ ቤተሰብ አለብን፤ አዳምጡን! " - የታይዋን የገበያ አዳራሽ ነጋዴዎች 👉 " የታሸጉት 30 ሱቆች ናቸው፤ ነጋዴዎቹ የ2018 ዓ.ም ዕዳቸውን ከፍለው ወደ ሾል እንዲመለሱ እንፈልጋለን " - የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን በድሬዳዋ ከተማ ታሪካዊው 'ታይዋን' የገበያ አዳራሽ በልብስ ችርቻሮ ንግድ የተሰማሩ ነጋዴዎች፣ የከተማዋ ገቢዎች ቢሮ "በጅምላ ቫት (VAT) ካልገባችሁ" በማለት ሱቆቻቸውን ከሰኔ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ አሽጎባቸው ከስራ ውጪ መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ። " 120 ይሆናል የታሸጉት ሱቆች " ያሉት ነጋዴዎቹ ቅሬታቸውን ይዘው የሄዱባቸው የተለያዩ የመንግስት ቢሮዎች ምላሽ እንደነፈጓቸው ጠቅሰዋል። የፌደራል እና የከተማው አስተዳደር ጉዳዩን ትኩረት ሰጥቶ የታሸጉ ሱቆቻቸው እንዲከፈቱ፣ ገቢያቸውን ያገናዘበ ህጋዊ ግብር እየከፈሉ ወደ ስራቸው እንዲመለሱ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ጠይቀዋል። ነጋዴዎቹ በዝርዝር ምን አሉ ? " የከተማዋ ገቢዎች ቢሮ ያሸገብን ' ሁላችሁም ቫት መግባት አለባችሁ ' ብሎ ነው። ቫት ለመግባት አዋጁ አንድ ነጋዴ ቢያንስ አመታዊ ገቢው ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል። ቢሮው አጠናሁት ባለው መሰረት ገቢያችን ከ1.5 ሚሊዮን በታች ነው። ለምን ሱቃችን ይታሸጋል ስንል ' ገቢያችሁ ከሁለት ሚሊዮን አልፏል፣ ስለዚህ ሁላችሁም በጅምላ ቫት መግባት አለባችሁ ' ነው የሚሉን። እኛ ደግሞ በሰራነው መጠን ግብር እየከፈልን ነው፣ ያለአግባብ እኛን የሚያከስር እና ከስራ ውጭ የሚያደርገንን ግብር እንድንከፍል ልንጠየቅ አይገባም። ከህግ ውጭ 'በግዳጅ ቫት ካልገባችሁ' ተብሎ ሱቆቻችንን ማሸግ ይቁምልን ብንልም፣ ከወራት በላይ በየቢሮው ብንመላለስም መፍትሄ ሊሰጠን የሚችል አንድም አካል ልናገኝ አልቻልንም። በአዲሱ የግብር አከፋፈል አዋጅ ቁጥር 1395/2017 መሠረት እስከ 2 ሚሊዮን ብር ድረስ የንግድ እንቅስቃሴ ያላቸው 9% ይክፈሉ ቢልም፣ የኛ መረጃ በእጃቸው እያለ 'ሁላችሁም በጅምላ ቫት ካልገባችሁ በስተቀር አንሰማችሁም' በማለት ከስራችን በማፈናቀል ሱቆቻችንን አሽገውብን ይገኛሉ። ቫት መግባት የእኛ አቅማችን አይችልም፣ ችርቻሮ ነው የምንሰራው፤ በዛ ላይ ማወራረጃ ሪሲት አናገኝም፣ ስለዚህ በምን እናወራርዳለን ? ሁለተኛ ነገር ደግሞ በጅምላ እንዴት ይገባል ? የአንዱ ቤት ካፒታል ትንሽ ነው፣ የአንዱ ቤት ደግሞ ትልቅ ነው፤ እንዴት በጅምላ ይሆናል? እዩልን ስንል እናንተ ራሳችሁ ይቻላል የምትሉትን ነጋዴ ለይታችሁ ስጡን አሉ። እናንተ እጃችሁ ላይ ዶክመንት አለ፣ በዛ መሰረት ቫት ይቻላል የምትሉትን ነጋዴ አስገቡ እንጂ እኛ መርጠን አንሰጥም። ምክንያቱም በምንም ማወቅ አንችልም አልን። ' ትገባላችሁ ትገባላችሁ ' ነው መልሳቸው። የሚመለከተው የከተማውም ሆነ የፌደራል ተቋም ይህን አሳሳቢ ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶ ፍትሃዊ ምላሽ እንዲሰጠን፣ የታሸጉ ሱቆቻችን እንዲከፈቱልን እና ወደ ስራችን እንድንመለስ ይደረግልን። ስራችንን እንስራ፤ ተገቢና ገቢያችንን ያማከለ ህጋዊ ግብር እንክፈል። አዳምጡን፣ በስራችን በርካታ ቤተሰብ አለብን " ብለዋል። አንድ ስሟ እንዲጠቀስ ያልፈለገች ነጋዴ " እኔ በበኩሌ ቫት ለመግባት አቅሙ የለኝም፣ ዕቃዬም ቢታይ አይሆንም። 7 ቤተሰብ አስተዳዳሪ ነኝ፣ ከወር በላይ ሾል ማቆም ማለት ከባድ ነው። ሾል ቦታም መኖሪያዬም ተከራይቼ ነው። ያሉሁበት ሁኔታ በጣም ከባድ ነው። ለልጆቼ ዳቦ መግዣ እስከማጣት ደርሻለሁ። መድኃኒት ሊቋረጥባቸው የማይገቡ ቤተሰቦች አሉን፣ ስለዚህ መንግስት እኛ ነጋዴዎች እየራበን እና ኑሮ እንደከበደን አውቆ መፍትሔ ይስጠን " ስትል ትጠይቃለች። የከተማው ገቢዎች ባለስልጣን ምን መለሰ ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሾለ ጉዳዩ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር ዶ/ር አብዱሰላም መሀመድን አነጋግሯል። " ' 120 ሱቆች ታሽገዋል ' የተባለው ውሸት ነው 30 አካባቢ የሚሆኑት ናቸው የታሸጉት፣ የታሸጉትም ለአቅመ ቫት የደረሱ ስለሆነ ወደ ቫት መግባት ስላለባቸው ነው " ሲሉ ከነጋዴዎች ለተነሱት ቅሬታዎች ምላሽ ሰጥተዋል። አክለውም " የአንድ ነጋዴ የቀን ሽያጩ ከ3000 በላይ ከሆነ ቫት መመዝገብ እንዳለበት ህጉ ያዛል። አንዳንዶቹ የታሸገባቸው ነጋዴዎች በቫት ብቻ ሳይሆን የ2018 ዓ.ም የገቢ ግብር ያልከፈሉ ናቸው። ያ ማለት ዕዳ አለባቸው " ብለዋል። " መጀመሪያ አካባቢ ከ100 በላይ ሱቆች ታሽገው ነበር። ወዲያውኑ ተነጋግረን ቫት ለመመዝገብ ፍቃደኛ የሆኑት ከ15 ቀን በፊት ተከፍቶላቸው እየሰሩ ነው " ሲሉ ገልጸዋል። " እንደቢሮ ጥናት አጥንተን ነው እየሰራን ያለነው። ሱቆች እንዲታሸጉ አንፈልግም። ነጋዴዎቹ እየመሰላቸው ያለው ሁለት ሚሊዮን ሲባል ተቀማጭ ገንዘብ ነው። እውነታው ግን አመታዊ ትራንዛክሽን ነው። በነጋዴዎች ላይ የግንዛቤ እጥረት ስለተፈጠረ ነው እዚህ የደረስነው " ሲሉ አስረድተዋል። " ከነጋዴዎች ጋር አሁን መግባባት ላይ እየተደረሰ ነው " የሚሉት ዶ/ር አብዱሰላም መሀመድ " ሃሳባችን ህጋዊ ግብይት እንዲኖር ነው፣ በታይዋን ገበያ አዳራሽ አካባቢ ኮንትሮባንድ ንግዶች ተንሰራፍተዋል፣ ስለዚህ ለሚሸጡት እቃ ደረሰኝ መስጠት አለባቸው ነው " ያሉት። " አሁን ላይ ሱቃቸው የታሸገባቸው ነጋዴዎችንም አወያይተናል። ቅሬታ ካላቸው ቅሬታ ሰሚ አለ፣ ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ፣ ሱቆች ሲዘጉ ነጋዴዎች ብቻም ሳይሆኑ መንግስትም ተጎጅ ነው። እኛ የምንፈልገው ነጋዴዎቹ ወደስራ እንድመለሱ ነው " ብለዋል። " እንዳይሰሩ ማድረግ የገቢ ግብር አዋጁ መርህ አይደለም። አዋጁን ተገንዝበው ያለባቸውን ዕዳ ከፍለው ወደ ሾል መግባት አለባቸው " ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia

  • йоС пОдписи

  • ‎" አሁን ላይ ከዋና ዋና ከተሞች ርቀው በሚገኙ አከባቢዎች ከሚደረግ የቡድን ዝርፊያ በበስተቀር የሳምንቱ ሐሙስ የነበረው ሰልፍም ቀርቷል " - አቶ ዮሐንስ ሀቢቢ ‎ ‎ላለፉት ወራት በደቡብ አፍሪካ በስፋት ሲስተዋል የነበረው " የስደተኞች ይውጡልን " እንቅስቃሴ በሀገሪቱ የምርጫ ወቅት እየተቃረበ ቢመጣም ከዚህ ቀደም ከነበረው በተቃራኒ ከፍተኛ መሻሻል ማሳየቱን በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ‎ ‎ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡት በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ወካይ ዮሐንስ ሀቢቢ " የፀረ ስደተኞች እንቅስቃሴ እንደተፈራው አይደለም "ሲሉ ገልፀዋል። ‎ ‎አሁን ላይ ከሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች ወጣ ባሉ አከባቢዎች በቡድን ከሚፈፀም ንጥቂያ እና ዘረፋ በስተቀር የ " ይወጡልን " ሰልፍ መቀዛቀዙን አስረድተዋል። ‎ ‎" የነበረው ከፍተኛ ስጋት የተነሳ ለወራት በስራ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ አሳድሮብን ነበር " ያሉ ሌላ በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ነጋዴ " አሁን ላይ ያለው አንፃራዊ መረጋጋት ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነቱ ዘመቻ ባልነበረባቸው የአከባቢ ምርጫ ወቅቶች ጭምር ከነበረው የተሻለ ነው " ሲሉ ገልፀዋል። ‎ ‎ይህ በእንዲህ እንዳለ ደቡብ አፍሪካ ከ80,000 በላይ ያልተመዘገቡ ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው ለመመለሾ እና ለማጓጓዝ ከአቪዬሽን፣ የትራንስፖርት እና የቆይታ ወጪዎች ጋር ተያይዞ 18 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ወጪ ማድረጓን በመግለፅ የካሳ ጥያቄ (ወጪ እንዲሸፍኑ) ኢትዮጵያን ጨምሮ እነ ማላዊና ናይጄሪያን መጠየቋን አሶሺየትድ ፕረስ እና አፍሪካ ዶት ኮም ዘግበዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia ‎

  • йоС пОдписи

  • የውጭ ሀገር ዜጎች በኢትዮጵያ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሚሆኑበትን አሰራር የሚወስን አዲስ መመሪያ ወጣ • በመመሪያው ድንጋጌ መሰረት የውጭ ሃገር ዜጎች በመንግስት ቀጥተኛ ድጎማ የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም)  ባለቤት መሆን አይችሉም። የከተማና መሰረተ-ልማት ሚኒስቴር የውጭ ሀገር ዜጎች በኢትዮጵያ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሚሆኑበትን ዝርዝር ሁኔታ የሚወስን "መመሪያ ቁጥር 1147/2018" አውጥቷል። መመሪያው የወጣው የውጭ ሀገር ዜጎች የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሚሆኑበትን አግባብ ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1388/2017 በጥቅሉ የተቀመጡ ጉዳዮችን በመለየት፣ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን የሚፈልጉ የውጭ ሀገር ዜጎች ማሟላት የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች፣ ገደቦች እና ክልከላዎች በዝርዝር ለመደንገግ ነው። የውጭ አገር ዜጋ ማለት ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆነ የውጭ ዜጋን ሳይጨምር ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሌለው ወይም የሌላ አገር ዜግነት ያለው ማንኛውም ሰው ማለት መሆኑን የመመሪያው ትርጓሜ ያስረዳል። በመመሪያው መሰረት፣ ማንኛውም የውጭ ሀገር ዜጋ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን የሚያስችል ፈቃድ ከሚኒስቴሩ ለማግኘት የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለበት፡- • የጸና ፓስፖርት እና የጉዞ ሰነድ ማቅረብ፤ • የጸና የመግቢያ ቪዛ ወይም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ከሆነ የጸና ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ፤ • ከሚኖርበት ሀገር የሚሰጥ ከወንጀል ነፃ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ፤ • ለቤት ግዥ የሚውል ዝቅተኛ የገንዘብ መጠን በባንክ ገቢ ማድረጉን የሚያሳይ ማስረጃ፤ • የውጭ ባለሀብት ከሆነ ደግሞ በኢንቨስትመንት ውስጥ ቢያንስ 150,000 የአሜሪካ ዶላር ድርሻ ያለው መሆኑን የሚገልጽ የኢንቨስትመንት ፈቃድ እና የጽሁፍ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርበታል። መመሪያው እንደ አካባቢው ለቤት ባለቤትነት የሚያስፈልገውና የውጭ ሃገር ዜጋው ማቅረብ የሚጠበቅበት ዝቅተኛ የገንዘብ መጠን በዝርዝር አስቀምጧል። • በአዲስ አበባ እና በሸገር ከተማ አስተዳደሮች የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን ቢያንስ 150,000 የአሜሪካ ዶላር • በኦሮሚያ(ሸገርን ሳይጨምር) ፣ አማራ፣ ትግራይ፣ ሲዳማ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ሶማሌ፣ ሐረሪ ክልሎች እና ድሬዳዋ አስተዳደር 120,000 የአሜሪካ ዶላር፤ • በአፋር፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ወይም ጋምቤላ ክልሎች ደግሞ ቢያንስ 100,000 የአሜሪካ ዶላር ማቅረብ ይኖርበታል። በተጨማሪም ማንኛውም የውጭ ሀገር ዜጋ በኢትዮጵያ ውስጥ ሊኖረው የሚችለው ከፍተኛ የቤት ብዛት አንድ ብቻ እንደሆነ ተደንግጓል። ማንኛውም የውጭ ሀገር ዜጋ ለመኖሪያ ቤት የሚሆን የውጭ ምንዛሬ በመረጠው ባንክ ገቢ ለማድረግ በመጀመሪያ ከሚኒስቴሩ የፈቃድ ደብዳቤ ማግኘት የሚኖርበት ሲሆን ባንኩም የቀረበለትን ምንዛሬ በዕለቱ ተመን ወደ ብር በመቀየር በዜጋው ስም በተከፈተ ዝግ የባንክ ሂሳብ ውስጥ ያስቀምጣል። በዝግ ሂሳብ የተቀመጠው ገንዘብ የሚለቀቀው ግለሰቡ ቤት ሲገዛ ወይም በሊዝ ጨረታ መሬት ሲያገኝ ብቻ ይሆናል ይህም የሚከናወነው ሚኒስቴሩ ገንዘቡ እንዲለቀቅ የሚገልጽ የፈቃድ ደብዳቤ ለባንኩ ሲያቀርብ ባንኩ በአሰራሩ መሰረት ገንዘቡን እንዲለቀቅ ሲያደርግ ነው። በሽብር ወንጀል፣ በሰው መነገድ፣ በአደገኛ ዕጽ ዝውውር፣ በገንዘብ ማጠብ፣ በከባድ ሙስና፣ በሳይበር ወንጀል እና በሌሎች ከባድ ወንጀሎች የተጠረጠረ ወይም ጥፋተኛ የተባለ ሰው የመኖሪያ ቤት ባለቤት መሆን አይችልም። በተጨማሪም በመንግስት ቀጥተኛ ድጎማ የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም)፤ ከትርፍ ውጭ ለሆነ ዓላማ በመንግስት ወይም ከህዝብ በተሰበሰበ ገንዘብ የተገነቡ ቤቶች፤ በመንግስት፣ በባለሀብት ወይም በመንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍ የተገነቡ ቤቶች፤ በህብረት ሾል ማህበራት የተገነቡ ቤቶች የውጭ ሀገር ዜጎች በባለቤትነት ሊይዟቸው አይችሉም። ለባለቤትነት ፈቃድ ለማውጣት 50 የአሜሪካ ዶላር በዕለቱ ምንዛሬ መከፈል እንዳለበት መመሪያው ይደነግጋል። የሚሰጠው ፈቃድ ለአንድ ዓመት ብቻ የሚያገለግል ሲሆን፣ ግለሰቡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ቤት መግዛት ወይም መስራት ካልቻለና ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ካጋጠመው ለተጨማሪ አንድ ዓመት ሊታደስለት ይችላል። ፈቃዱን ካልተጠቀመበት ግን ለሚኒስቴሩ መመለሾ ይኖርበታል። የመኖሪያ ቤቱን ላልተፈቀደ ወይም ለህገ-ወጥ ዓላማ የተጠቀመ የውጭ ሃገር ዜጋ ከ1,000 እስከ 3,000፣ ያለ ፈቃድ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ሆኖ የተገኘ ከ2,000 እስከ 5,000 ዶላር እንዲሁም ህገ-ወጥ መሆኑን እያወቀ የረዳ ወይም የተባበረ ማንኛውም ሰው ከ30,000 እስከ 50,000 የኢትዮጵያ ብር መቀጮ እንደሚጣልበት መመሪያው ያመለክታል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

  • йоС пОдписи

  • йоС пОдписи

  • "በችኮላና በጥድፊያ" የሚዘጋጁ ህጎች፣ በህግ አወጣጥ ስርዓቱ ላይ አለመረጋጋት እየፈጠሩ መሆኑን በጥናት ተመላክቷል። 👉 አንዳንድ መመሪያና ደንቦች ከመውጣታቸው በፊት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው የማይገመገሙ መሆኑ ደግሞ ችግሩን አባብሶታል ተብሏል። 👉 ህጎች በወጡ በሳምንት እና በአመታቸው ማሻሻያ የተደረገባቸውም እንዳሉም ተገልጿል። (ቲክቫህ ኢትዮጵያ) በኢትዮጵያ የህግ አወጣጥ ሂደት ውስጥ ተደጋጋሚ ማሻሻያዎች፣ የአዋጅ መሻሮችና መጣረሶች እየታዩ መሆኑን፣ ይህንንም መረጋጋት ለማምጣት የሚያስችል ሁሉን አቀፍ ፖሊሲም ሆነ ወጥ የህግ ማዕቀፍ በሀገሪቱ አለመኖሩን ፌደራል የህግ እና ፍትህ ኢንስቲትዩት ያካሄደው ጥናት አመለከተ። ጥናቱ "የህግ አወጣጥ ስርዓት መረጋጋት በኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ የተካሄደ ሲሆን፣ ዓላማውም በሀገሪቱ ያለውን የፖሊሲና የህግ ማዕቀፍ እንዲሁም የአተገባበር ስርዓት ከረጅምና ከአጭር ጊዜ እቅዶች እንዲሁም ከቦትስዋና፣ ከጋናና ከደቡብ አፍሪካ ተሞክሮዎች አንጻር በመመርመር የመፍትሄ ሀሳብ ማቅረብ ነው። ህግ የማህበረሰብንና የመንግስትን መስተጋብር የሚመራ መሳሪያ እንደመሆኑ ተለዋዋጭነት ባህሪው ቢሆንም፣ የሚወጡ ህጎች ጥራት፣ ግልጽነት፣ ወጥነት፣ ተገማችነትና ቀጣይነት ሊኖራቸው እንደሚገባ ጥናቱ ያስቀምጣል። ከ2010 ዓ.ም ወዲህ የተካሄደው የመንግስት ለውጥ ተከትሎ በርካታ ህጎች የመውጣታቸውን ያህል፣ በችኮላና በጥድፊያ የሚወጡ ህጎች የህግ አወጣጥ ስርዓቱ የተረጋጋ እንዳይሆን፣ በህዝብና በባለሙያዎች ያልተመከረበት እንዲሆን እንዳደረጉት ጥናቱ ጠቁሟል። ይህም ባለሀብቶች የረጅም ጊዜ የኢንቨስትመንት ውሳኔ እንዳይወስኑ፣ ዜጎችም ሾለ መብትና ግዴታቸው ያላቸው ግንዛቤ አናሳ እንዲሆን አስተዋጽኦ እንዳደረገ ተመላክቷል። ጥናቱ ከ2010 እስከ 2018 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጡ አዋጆችን ሙሉ በሙሉ መመርመሩን ገልጿል። ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮ በመነሳት፣ የህግ አወጣጥ ስርዓት መረጋጋት በስድስት ተያያዥ ተቋማዊ ምሶሶዎች ላይ የተመሰረተ መሆኑን የለየው ጥናቱ እነሱም የህገ መንግስት የበላይነት በተግባር መረጋገጥ፣ ውጤታማ የስልጣን ክፍፍልና ሚዛን፣ ጠንካራ የፓርላማ ኮሚቴ ስርዓት፣ በሙያ የታገዘ የረቂቅ ዝግጅት ተቋም፣ ትርጉም ያለው የህዝብ ተሳትፎ፣ እና ገለልተኛ የዳኝነት ቁጥጥር ናቸው። ኢትዮጵያን በተመለከተ ግን ሀገሪቱ የህግ አወጣጥ ስርዓት መረጋጋትን የተመለከተ ፖሊሲ እንደሌላት፤ ጠቅላላ የህግ አወጣጥ ስርዓትን የሚመራ ፖሊሲም እንደሌለ፤ የሚወጡ ህጎችም በአብዛኛው በጸደቁ ፖሊሲዎች ላይ ከመመስረት ይልቅ የአስፈጻሚውን ጊዜያዊ ፍላጎት የሚያንጸባርቁ ሆነው መገኘታቸውን ለይቷል። በህግ ማዕቀፍ ረገድም ኢፌዲሪ ህገ መንግስት፣ ደንብ ቁጥር 6/2008፣ አዋጅ ቁጥር 1263/2014 እና ሌሎች ሰነዶች ቢኖሩም፣ ከማርቀቅ እስከ አፈጻጸምና ክትትል ድረስ ያለውን ሂደት በአንድ ወጥነት የሚገዛ ማዕቀፍ አለመኖሩ ተጠቁሟል፤ ያለው አሰራርም በተበታተኑና በተበጣጠሱ መመሪያዎች ላይ የተመሰረተ ነው። በአተገባበር ደረጃም ከተለዩ ክፍተቶችም ውስጥ :- - ተደጋጋሚ የአዋጅ ማሻሻያዎች (ለምሳሌ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትና የኤክሳይዝ ታክስ አዋጆች በወጡ በአመታቸው ማሻሻያ የተደረገባቸው መሆኑ) ፣ - ሰፊ የአዋጅ መሻሮች (ለምሳሌ አዋጅ ቁጥር 1263/2014 ብቻውን 18 አዋጆችንና 35 ደንቦችን መምሊ)፣ - ተደራሽ ያልሆኑ መመሪያዎች ፣ - ተቃራኒ ይዘት ያላቸው አዋጆች መውጣት፣ - ከበላይ ህጎችና ከህገ መንግስቱ ጋር የሚጋጩ ድንጋጌዎች መኖር (በህገ ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብ ህጋዊ ማስመሰልን በተመለከተ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የያዘ ድንጋጌ በመሆኑ ማክሰኞ ወጥቶ በሳምንቱ ማክሰኞ ማሻሻያ የተደረገበት ሂደት መኖሩ) - የበታች ህጎች ያለ ተገቢ ግምገማ መውጣት ( በተለይ ታክስ አካባቢ ይሄ ችግር በአደገኛ ሁኔታ መስተዋሉ) - አዋጆች በተግባር ያለመፈጸም ይገኙበታል። ከጥንካሬ አኳያም የተለያዩ ግኝቶችን ያስቀመጠው ጥናቱ ባለ ሶስት ደረጃ የምርመራና የንባብ ሂደት፣ የፍትህ ሚኒስቴር ማጣራት ሚና፣ የህግ ማዕከልና አማካሪዎች መኖር፣ እንዲሁም በቅርቡ የተቋቋመው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ ማሻሻያና ቁጥጥር መሪ ሾል አስፈጻሚ እንደ አዎንታዊ እርምጃዎች ተጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የባለሙያ እጥረት፣ የተቋማት አለመናበብ፣ የአመራር ትኩረት ማነስ እና ወጥ የህግ ይረቀቅልኝ ስርዓት አለመኖር እንደ ዋና ዋና ድክመቶች ተለይተዋል። ጥናቱ ከጋና፣ ከደቡብ አፍሪካና ከቦትስዋና ተሞክሮ በመነሳት ፦ ° ፍርድ ቤቶች ግልጽ የህገ መንግስት ተጣጣሚነት የመተርጎም ስልጣን እንዲኖራቸው ማድረግ፣ ° የፓርላማ ኮሚቴ ስርዓትን ማጠናከር፣ ° ሙያዊ የረቂቅ ዝግጅት አቅምን ማጎልበት፣ ° የህዝብና የባህል እንዲሁም የሃይማኖት ተወካዮች ተሳትፎን ተቋማዊ ማድረግ፣ ° ህግ ማውጣትን ከፖለቲካ ፍጥጫ ነጻ ማድረግ፣ ° የተጠቃለለ ፖሊሲና ሁሉን አቀፍ ህግ ማዘጋጀት፣ ° ገለልተኛ የህግ ኮሚሽን ማቋቋም፣ ° በዩኒቨርሲቲዎች የሌጂስሌቲቭ ድራፍቲንግ ስልጠናና ካሪኩለም ማዘጋጀት፣ ° የህግ አወጣጥ ሉዓላዊነትን ከውጭ ተጽእኖ መጠበቅ፣ እንዲሁም የበታች ህጎችን ከአዋጅ ጋር ተጣጥመው መውጣታቸውን የሚከታተል ስርዓት መዘርጋት የሚሉ ምክረሃሳቦችን አቅርቧል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

  • йоС пОдписи

  • #ችሎት የፌደራል ፖሊስ በኢህአፓ አባላት አቶ አበበ አካሉ፣ አቶ ይስሀቅ ወልዳይ እና በፓርቲው ጠበቃ አቶ አበራ ንጉስ ላይ " የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ተንቀሳቅሰዋል " ሲል ወንጅሏል። ተጠርጣሪዎች ዛሬ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበዋል። ፖሊስ ለፍርድ ቤት እንደገለጸው፣ ተጠርጣሪዎቹ ከህወሓት፣ "ጽምዶ" እና ከሌሎች "ጸረ ሰላም ኃይሎች" ጋር በመቀናጀት ፦ - በአዲስ አበባ አባላትን በመመልመልና በማደራጀት፣ - የጸጥታ ኃይሎችን እንቅስቃሴ በመሰለል፣ - ለ "ፅምዶ" ቡድን መረጃ በማቀበል እንዲሁም የፖለቲካ፣ የወታደራዊ እና የሚዲያ ፕሮፖጋንዳ ክንፎችን በማደራጀት ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ ሲንቀሳቀሱ ነበር ሲል ወንጅሏቸዋል። በተጨማሪም ፖሊስ፣ ተጠርጣሪዎቹ የብሔርና የሃይማኖት ግጭት ለመፍጠር በማሰብ በውጭ ሀገር በሚገኙ መገናኛ ብዙኃን የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ሲያሰራጩ ነበር በማለት ወንጅሏቸዋል። በፖሊስ ማመልከቻ በስም የተጠቀሱት መገናኛ ብዙኃን አንከር ሚዲያ፣ ኢትዮ ፎረም እና ኢትዮ 360 ናቸው። ግለሰቦቹ "ስልጣን ላይ ያለውን መንግስት ‘በኃይልም ቢሆን ማስወገድ አለብን’፣ ‘በየትኛውም አካባቢ የሚደረግ የትጥቅ ትግል አግባብ ነው’ በማለት"፣  "ለህዝቡ የትጥቅ ትግል የመጨረሻ አማራጭ መሆን እንዳለበት" መናገራቸውን ፖሊስ በማመልከቻው ላይ ጠቅሷል። ሶስቱ ተጠርጣሪዎች በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ሾር የዋሉት፤ በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች ላይ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ተቋማት እና በመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ላይ "የሽብር ጥቃት ለመፈጸም በእንቅስቃሴ ላይ እያሉ " እንደሆነ ፖሊስ ለፍርድ ቤት ገልጿል።  የተጠረጠሩበት የሽብር ወንጀል ጉዳይ " ውስብስብ " እና " ሰፊ ጊዜ " የሚፈልግ በመሆኑ የምርመራ ሾል ለማካሄድ 14 ቀን ጠይቋል። ተጠርጣሪዎቹ በበኩላቸው ሁሉንም ውንጀላ በመካድ፣ “በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እናምናለን፤ መንግስትን በኃይል የመገልበጥ ዓላማ የለንም " ብለዋል። አቶ አበበ፥ " መንግስት እንዲስተካከል የሚጥሩ " መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል። " ሀገር አለኝ፣ ልጆች አሉኝ። በሰላማዊ ትግል ነው የምናምነው " ብለዋል። ችሎቱ፣ ፖሊስ ግለሰቦቹን በሽብርተኝነት የጠረጠረበትን በመገናኛ ብዙሃን የተላለፉ መልዕክቶች የሽብር ክስ እንደሚያቋቁም ለመረዳት እና በዋስትናው ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ተጨማሪ መረጃ ማግኘት እንደሚያስፈልገው ገልጿል።  በዚህም መሰረት ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ በመገናኛ ብዙሃን አድርገውታል የተባለውን ንግግር በማስረጃነት ይዞ ለነገ ሐሙስ ሐምሌ 30፤ 2018 እንዲቀርብ አዝዟል።  ማስረጃዎቹን መርምሮ በዋስትና ጥያቄው ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለአርብ ነሐሴ 1 ጠዋት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።  ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ነው። ሃምሌ 29 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

  • йоС пОдписи

  • ፍካሬ_ ⛔️  የአለማሁ ዋሴ እሸቴን ዘመን የማይሽራቸዉን መጻሕፍት ✅እመጓ ✅ዝጎራ ✅ሚትራሊዮን ✅መርበብት ✅ችቦ ✅ፍካሬ ሁሉንም በአንድ ላይ በ PDF  ✉️@QIMEMEBOOKS ✉️@QIMEMEBOOKS

  • . ⛔️ችቦ በዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ (ዶ/ር)

  • . ⛔️ሚተራሊዮን በዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ (ዶ/ር

  • .⛔️ሰበዝ በዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ (ዶ/ር)

  • .⛔️መርበብት በዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ (ዶ/ር)

  • .⛔️ዝጎራ በዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ (ዶ/ር)

  • .⛔️እመጓ በዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ (ዶ/ር)

  • የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሼል አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም የሕንድ ሁለተኛው ትልቁ አየር መንገድ ዋና ሼል አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ። በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ10 ዓመታት በላይ በመሪነት በማገልገል ተቋሙን ወደ አፍሪካ ቀዳሚ አየር መንገድ ለማሳደግ ቁልፍ ሚና የተጫወቱት አቶ ተወልደ፣ አሁን የሕንድ ሁለተኛው ትልቁ አየር መንገድ የሆነውን ኤር ኢንዲያን ይመራሉ። ኤር ኢንዲያ በቅርብ ጊዜ ከደረሰበት የአውሮፕላን አደጋ እና ከሌሎች የሥራ ተግዳሮቶች በኋላ አዲስ አመራር እየፈለገ ሲሆን፣ አቶ ተወልደ በቀድሞ የአመራር ልምዳቸው እና በአቪዬሽን ዘርፍ ባላቸው ስኬት ተመርጠዋል። አቶ ተወልደ ገብረማሪያም ከ20 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለያዩ ኃላፊነቶች ያገለገሉ ሲሆን፣ በ2014 ዓ.ም. በጤና ምክንያት ከዋና ሼል አስፈጻሚነት ለቀው የነበሩት። ሃምሌ 29 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

  • йоС пОдписи