tgindex
አፋብን ጎጠግ በላይ ዕዝ

አፋብን ጎጠግ በላይ ዕዝ

Статистика

የአማራ ህዝብ እያደረገ ያለው የህልውና ትግል የሚዘገብበት የትግል ቻናል ነው። ለማንኛውም ጥያቄ @Heaven11111ያግኙን

Последний пост
1 июн.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
am
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
5 710
−10 за 4 дн.
Сутки
−5
−0,09%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
4 109
20 постов
Вовлечённость
72,0%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • Channel photo updated

  • Channel photo removed

  • Channel name was changed to «አፋብን ጎጠግ በላይ ዕዝ»

  • 1 июн.3 320311

    #መረጃ #ምርጫ ጭልጋ ወረዳ ቀን-ወጣ ከተማ ጣቁሳ ወረዳ ሰቢ፤ጨውድባ፣ውድብል፤ቸመራ ምዕራብ ደንቢያ ወረዳ፤ጎርጎራ፣ ሳንኪሳ፤ስምራ ሮቢት ምስራቅ ደንቢያ ወረዳ ሮቢት፣አይንባ ጎንደር ዙሪያ ወረዳ ማክሰኝት፣ ሩፋኤል፤ጉንብሪት፤አጣጥ ዙሪያ ስማዳ ፣ እስቴ ፣ ነፋስ መውጫ ፣ደብረታቦር፣አዲስ ዘመን፣ታች ጋይንት፣ወረታ፣እብናት፣ ትናት እና ዛሬ በተደረገው ትንቅንቅ ምርጫው ሙሉ በሙሉ ቁሟል፤ጠላት ከፍተኛ ኪሳራ አስተናግዷል። በጎርጎራ የጠላት ካንፕ ሙሉ በሙሉ ሲወድም ሮቢት የነበረ ሐይል በቆረጣ ሙትና ቁስለኛ ሆኖ የተረፈው ወደ ቆላድባ ፈርጧል። በደልጊ፣ጯሒትና ቆላድባ ህዝብን በማስገደድ ለማስወጣት ያደረገው ሙከራ በዙሪያው በነበረው ውጊያ ምክንያት ከሽፎበታል። በጥቅሉ ከላይ በተጠቀሱት ቦታዎች ምርጫው ከሽፏል። Fb:https://www.facebook.com/share/p/1BetNdJHgp/?mibextid=ZbWKwL

  • 30 мая3 49729

    #መረጃ ጎንደር -ደንቢያ በምስራቅና ምዕራብ ደንቢያ ወረዳዎች ለምርጫ የተንቀሳቀሰ ሐይል ተመታ። በምስራቅ ደንቢያ ሰቀልት-አይንባ ቀጠና እና በምዕራብ ደንቢያ ናርቸቻ ቀበሌ በተደረገ ውጊያ የጠላት ሐይል በከፍተኛ ውኔታ ሲመታ ውሏል። በግንባር አንድ፦ የአፋብን ጎጠግ በላይ ዕዝ አካል የሆኑት በጌምድር ክፍለጦር (አይሸሽም ብሬጌዴ) እና የታድሎ ብርሐን ክፍለጦር አሐዶች በጥምር ባደረጉት ተጋድሎ በደንቢያ-ሰቀልት አይንባ ከተማ ላይ የነበረን ምሽግ በመስበር የጠላትን ሐይል በከፍተኛ ሁኔታ የመቱት ሲሆን ለጨረባ ምረጫ የተዘጋጁ ቁሳቁሶችን ማስወገድ ተችሏል። በቦታው የነበረው ሐይል የተመታው ተሐቶ የተረፈው የስርዓቱ አገልጋይ ወደ ሰንበት ደብር ካንብ የፈረጠጠ ሲሆን ከ13 በላይ የነብስ ወከፍ መሣሪያ ገቢ ተደርጓል። በግንባር ሁለት፦ የአፋብን ጎጠግ በላይ ዕዝ በጌምድር ክፍለጦር ናደው ብርጌድ አህዶች በምዕራብ ደንቢያ ናርቸቻ ቀበሌ ከጭልጋ ወረዳ(ጫንድባ)፣ከጣቁሳ ወረዳ(ደልጊ) እና ከምዕራብ ደንቢያ ወረዳ(ጯሒት) የተውጣጣ ጥምር ሐይል ከተጠቀሱት ወረዳወች ተነስቶ እንቅስቃሴ በሚያደርግበት ሰዓት በደፈጣ እና በቆረጣ በከፍተኛ ሁኔታ የተመታ ሲሆን፤ ፅሑፉ እስከተፃፈበት ሰዓት ድረስ ውጊያው እንደቀጠለ ነው። ጠላት ከፍተኛ ኪሳራ አስተናግዷል፤ዝርዝሩን እናደርሳለን። FB:https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02mwCcgpkESGM4mDKrHvepBDouM6CyibTqwcFcRB3W4v97cZy3bPu6m7Nfzc76JMsyl&id=61588416561129&mibextid=CDWPTG

  • 25 апр.5 548562

    без подписи

  • 25 апр.5 078321

    እየተደረገ ባለው የህልውና ተጋድሎ ጀግኖች ዋጋ መክፈላቸውን ቀጥለዋል። ሚያዚያ 17/2018 ዓ/ም የአርበኛ ልባርጋቸው ሙጨን መስዕዋትነት አስመልክቶ ከአፋብን ጎጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 202ኛ ኮር የተሰጠ የሐዘን መግለጫ፦ አርበኛ ልባርጋቸው ሙጨ ከትግሉ ቀደም ብሎ ሐገሩን በመምህርነት ሲያገለግል የነበረ ባለ ትዳርና የአንዲት ሴት ልጅ አባት ነበር። አርበኛ ልባርጋቸው ሙጨ በጣቁሳ ወረዳ ከደልጊ ከተማ በቅርብ ርቀት መኮንታ ላይ ተወለደ። አርበኛው ሐገር በህውሐት ሐይል ተደፈረች በተባለበት ሰዓት ከመምህርነት ወደ አማራ ልዩ ሐይል የተቀላቀለ ሲሆን፤ በወቅቱ በነበረው ተጋድሎም የአማራነት ግዴታውን በሚገባ ተወጧል። በመቀጠል የአማራ ልዩ ሐይል በተበተነበትና የህልውና ትግሉ በተጀመረበት ወቅት ወደተወለደበት ጣቁሳ ወረዳ በመምጣት ከነ ራስ ደረጀ በላይና ከሌሎች የትግል አጋሮቹ ጋር በመቀላቀል ቀጠናውን በማደራጀትና በመምራት አይረሴ አሻራውን አሳርፏል። አርበኛ ልባርጋቸው ሙጨ ዘመናዊ ትምህርትን ከወታደራዊ ሙያ ጋር አጣምሮ የያዘ ሲሆን ደከመኝ ሰለቸኝ የማይል ታታሪ ጓድ ነበር። ከትግል አባቱ ከእራስ ደረጀ በላይ ጋር በመሆን የጣቁሳ በረሐማ አከባቢወችን ለማደረጀት ብዙ ዋጋ የከፈለ ሲሆን በበጌምድር ክፍለጦር ስር የምትመራውን ጣና ብርጌድን በማቋቋምና በመምራት ደልጊ፣መኮንታ፣አሲን፣ድኩል አርባ፣በግ መንክር ፣አሊሰፈርና መሰል ቦታዎች ላይ ከፍተኛ ተጋድሎ አድርጓል። አንጋፋው በጌምድር ክፍለጦር በወጣ በወረደባቸው እና ተጋድሎ ባደረገባቸው ቦታዎች ሁሉ የአርበኛ ልባርጋቸው ሙጨ አሻራም አለበበት። አርበኛው ከማደራጀትና ከመዋጋት በተጨማሪ በተለያዩ የሐሃፊነት ቦታወች አገልግሏል። ቀደም ሲል የበጌምድር ክፍለጦርን በገንዘብ መምሪያ ሐላፊነት ያገለገለ ሲሆን እስከተሰዋበት ሰዓት ድረስ ደግሞ ጣና ብርጌድን በዋና አዛዥነት ሲያገለግል ነበር። ይሁን እንጅ ይህ ሁሉ ተጋድሎ ሲደረግ ያልተሰዋው አርበኛ ልባርጋቸው ሙጨ በትናትናው ዕለት (16/8/2018 ዓ/ም) መንግስት ባሰማራቸው ሰርጎ ገቦች መስዕዋትነት ከፍሏል። አርበኛው መደበኛ ስራውን ሲሰራ ውሎ ከድኩል አርባ ተነስቶ ወደ አሲን በሞተር ጉዞ እያደረገ በነበረበት እና ቀጠናው ሰላም በነበረበት ሰዓት ለተልዕኮ ሰርገው በገቡ ሐይሎች በተጣለ ደፈጣ መሰዕዋትነት ሊከፍል ችሏል። አርበኛ ልባርጋቸው ሙጨ የተሰዋለትን አላማ ለማሳካት ከመቸውም ጊዜ በላይ እንተጋለን። ነብሱን ከደጋግች ጎን ያሳርፍልን! 202ኛ ኮር!

  • 13 мар.6 58651

    #መረጃ-ጎንደር ከትናት የቀጠለው ውጊያ ተጠናክሮ ቀጥሏል መጋቢት 4/2018 ዓ/ም በማዕከላዊ ጎንደር ምስራቅ ደንቢያ ወረዳ ሮቢት ከተማ እና በአጎራባች ቀበልዎች ለሁለተኛ ቀን ውጊያ ሲደረግ ውሏል። የአፋብን ጎጠግ ዕዝ 202ኛ ኮር በጌምድር ክ/ጦር አካል የሆኑት ናደው ብርጌድና ፋሲለደስ ብርጌድ ከአፄዎች ክፍለጦር ጋር በመጣም ለሁለት ተከታታይ ቀናት ውጊያ እያደረጉ ይገኛሉ። ከጎንደር ከተማ በቅርብ እርቀት ከምትገኘው ሮቢት ከተማ እየተደረገ ባለው ውጊያ ጠላት ከፍተኛ ሰባዊና ቁሳዊ ከሳራ አስተናግዷል። የአድማ ብተና አባላት በከፍተኛ ሁኔታ እየፈረሰ 202ኛ ኮርን እየቀላቀለበት የሚገኝበት ስርዓቱ በከፍተኛ ብስጭት ከቆላድባ፤ከጎንደር እና ከማክሰኝት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሐይል ወደ ቀጠናው ያስገባ ቢሆኖም የፋኖን ምት መቋቋም አቅቶት እየተገረፈ ይገኛል። የኮበለሉ የአድማ ብተና አባላትን እመልሳለሁ ብሎ የወጣው የጠላት ሐይል ከፍተኛ ቁጥር ያለው አስክሬን እየጫን ተመልሷል። በአሁኑ ሰዓት ይዟቸው የነበሩት ምሽጎች ተሰብረው የተመታው ተመቶ የተረፈው ወደ ቆላድባ ከተማ እግሬ አውጭኝ እየፈረጠጠ ይገኛል። መልሶ ለመያዝ ቋምጦባት የነበረችው የሮቢት ከተማም በአናብስቶቹ ቁጥጥር ስር ትገኛለች። ሙሉ መረጃውን ይዘን እንመለሳለን! ድል ለግፉዓን! የአፋብን ጎጠግ ዕዝ ግንኙነት መምሪያ! Fb:https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0aXZdJjia8Ly5bT413tHorFXGC3DAQMcHDJADe1s6Ny8Guya6L6bXi8uz8iUx3VsNl&id=61588416561129&mibextid=ZbWKwL

  • 6 мар.5 941285

    የቀጠለ...#የአደረጃጀት ዜና በመሆኑም ለምናደርገው የህልውና ትግል  እንደ አማራ በህይወት ለመቆየት አድረጃጀት መስራትና መዋቅርን ማዘመን በማስፈለጉ ዛሬ 27/06/2018 ዓ.ም  204ተኛ አሰቻለው ደሴ ኮር  በጠንካራ በታማኝነታቸው  በትግል ብቃታቸው አንቱ  በተባሉ አርበኛችን ከአምስቱ ክፍለጦሮች ማለትም እትጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር; ጀኔራል ፈንታ በላይ ክፍለ ጦር; መይሰው ጋፋት ክፍለ ጦር; ታዲወስ ታንቱ ክፍለ ጦር; ፋሲል ክፍለ ጦር በጋራ  የኮሩ ስራ ስፈፃሚዎችን በአዲስ አደራጅተናል:: በዚህም መሰረት 1. ዋና ወታደራዊ አዛዥ-- አርበኛ ተሾመ አበባው                            2.   ም/ወታደራዊ አዛዥ   ___ አርበኛ  ጌቴ  መሳፍንት 3.  ዘመቻ ------ አርበኛ ውባንተ ተስፋው 4. ህዝብ ግንኙነት ----- አርበኛ  ባንቴ ጌትነት 5. መረጃና ደህንነት --- ##### 6. ምልመላና ስልጠና-  አርበኛ ሁነኛው አረጋ 7. እቅድና ስትራቴጂ  ---አርበኛ  ወርቅዬ ተስፋ 8. ጽ/ቤት---- አርበኛ አስማማው  ዋለልኝ 9. ወታደራዊ አስተዳደር--- አርበኛ ገዳም ካሳ 10. ሎጅስቲስቲክ---- አርበኛ ጮራ መኳንንት 11.   ፋይናንስና ንብረት -- አርበኛ ጌታሁን ደሳለኝ 12. ቁጥጥርና ኦዲት-- መልኩ መስፍን 13. ፖለቲካ ዘርፍ ----   አርበኛ ይበልጣል ማርዬ 14. አደረጃጀት ዘርፍ -- አርበኛ ታርቆ ከበደ 15 .ሕዝብ አስተዳደር  ######## 16. ህግ ጉዳይ  ########## በማለት የስራ አሰፈፃሚ  ማሻሻያ መዋቅር የሰራን ሲሆን የኮር  መሪዎቻችን  የተሻለ ስራ በመስራት የአማራ የህልውና ትግል ከግብ  ለማድረስ የራሳቸውን አስታወፅዎ  የፀና እምነት አለን::    "እንደራጃለን፣ እንሰለጥናለን፣ እንታጠቃለን እናሸንፋለን"‼️ ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር  ህዝብ ግንኙነት ክፍል!               የካቲት 27/ 2018  ዓ.ም        👉 ስር ነቀል ለውጥ ለህልውናችን‼️ Fb: https://www.facebook.com/share/p/1DBFajdZNS/

  • 6 мар.4 5402

    без подписи

  • 6 мар.4 53092

    #የአደረጃጀት ዜና "በትዕግሥት ማለፍ እያንዳንዱ መከራ የራሱ መውጫ ጊዜ አለው:: ያ ጊዜ እስኪደርስ ድረስ በፅናት መቆም ብስለትን ያመጣል" የካቲት 27/2018 ዓ.ም ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር የስራ አስፈፃሚ የመዋቅር ለውጥ ተቋማችን 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር በግዙፉ አርበኛ አስቻለው ደሴ (ገብርየ) ስም ስንሰይም አደራውን; ግቡን; የአማራን ህዝብ ነጻነት ማረጋገጥ መሆኑን በመረዳት የእውነትም የገብርየን የትግል አደራ ዳር ያደርሳሉ ብለን ያመንባቸው እንቁ አርበኞቻችን ኮሩን እንዲመሩ ታጋዩ ሲወስን የትግሉ አሸናፊነት የሚረጋገጠው ተቋም በመገንባት; ተቋምን በማጽናት መሆኑን እናምናለን። ስለሆነም የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ የተጋረጠበትን የመጥፋት ስጋት፣ የተጋረጠብንን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ከዚህ ጨፍጫፊ ስርዓት ጋር ትንቅንቅ ከተጀመረ አመታት የተቆጠሩ መሆኑ አለም የሚያውቀው ሀቅ ነው በዚህም ወቅት በርካታ እንቁ ታጋዮቻችን አኩሪ ታሪክ ሰርተው በክብር ተሰውተዋል ። ይህንን አስከፊ ጨፍጫፊ ስርዓት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመገርሰስ ባለን የሰራዊት አቅም ማሳደግ; ተቋማትን መገንባት ; አደረጃጀትን ማዘመንና ዘመናዊ መሳሪያዎችን መላመድ እንዲሁም ማዘመን አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ።

  • 4 мар.4 438241

    የአደረጃጀት ዜና አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን ) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር የአመራር ሪፎርም ሰራ!!! የትግልን ሁለተናዊ አንድነት፣ አቅምና ጉልበት እሚሻ መሆኑን የተረዱ ብልሆች ተቋም መሰባሰቢያ መሆኑን አምነው አንድ ቤታቸውን ይቀልሳሉ። በህግ እሚመራ ተቋም ደግሞ የስራዎቹ ሁሉ ማሰርያ ፣ የግቦች ሁሉ ቁልፍ መሆኑን ተረድቶ የትግል መሰረቱ አደረጃጀት በመሆኑ እንደ ንስር ራሱን አድሶ ብቅ ያለው 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ከትናት በተሻለ የአመራር ሪፎርም ለጠላት ራስ ምታት ለወገን ደግሞ ኩራት የሆነ ተቋም ገንብቶ ብቅ ብሏል ። በአባታችን ሜጀር ጀኔራል ከፍያለው ደሴ የተሰየመው ኮራችን ባለፉት አንድ አመት በርካታ አውደ ውጊያዎችን በማድረግ በጠላት ላይ ከባድ ክንዱን ሲያሳርፍ ቆይቷል ከትናት የተሻለም የአመራርነት አቅሙ ላይ በመገኘት የቀጠናው አኩሪ ኮከብ ሆኖ ለመውጣት እንደሚከተለው የአመራር መዋቅሩን ሰርቷል ። 1. ዋና ወታደራዊ አዛዥ------ አርበኛ የቆዬ አበጀ 2.ምክትል ወታደራዊ አዛዥ----አርበኛ ኪሮስ አበባው 3. ዘመቻ ኃላፊ -----------አርበኛ ምህረቱ አንዳርጌ 4. መረጃና ደህንነት ኃላፊ----------##### 5.ወታደራዊ ምልመላና ስልጠና ኃላፊ ------አርበኛ ጌትነት ምስጋናው 6. ወታደራዊ እቅድና ስትራቴጂ ኃላፊ-----አርበኛ ሰለሞን አዳሙ 7. ጽ/ቤት ኃላፊ---------------አርበኛ ዶ/ር አድማሱ አለምነው 8. ወታደራዊ አስተዳደር ኃላፊ------አርበኛ አያና ሆነ 9. ሎጅስቲስቲክ ኃላፊ----------አርበኛ አይናለም ጥላሁን 10. ፋይናንስና ንብረት ኃላፊ ----አርበኛ ባንቲደር እውነቱ 11. ቁጥጥርና ኦዲት ኃላፊ-------አርበኛ እያዩ በዜ 12. ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ----አርበኛ ልየው ተካልኝ 13. አደረጃጀት ኃላፊ------አርበኛ ዋለ ፈንታሁን 14. ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ----አርበኛ ጋሻው ግዛት 15. ሕዝብ አስተዳደር ኃላፊ---አርበኛ ገበየሁ አማረ 16. ህግ ጉዳይ ኃላፊ---አርበኛ ኢ/ር አንዳርጌ እሸቴ ሆኖ ተደራጂቷል። ስለሆነም ኮራችን ይህን ሪፎርም ሲሰራ ከእንደዚህ ቀደሙ ጠላትን በማንበርከክ የህልውና ስጋት ውስጥ ያለውን ማህበረሰባችንን ነጻ ማውጣትና የቀጠናው አቅም እንዲሆን ጭምር ነው ። ድል ለአማራ ፋኖ!!! ድል ለአማራ ህዝብ!!! የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ!!! የካቲት 25/ 2018 ዓ.ም Fb: https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid01M4JJW6tKc7RwmBT7WDueC5taAhFPCgDkAwVy44qogDkkFdzBNxQZjNvYPpfoquql&id=61588416561129&mibextid=ZbWKwL

  • 3 мар.3 55226

    #መረጃ በለሳ-ደጎማ የስርዓቱ ወንበር ጠባቂ ተረፍርፏል። የአፋብን ጎጠግ ዕዝ ታዲዮስ ታንቱ ክ/ጦር በአካባቢው ከነበሩ የበላይ ዕዝ አህዶች ጋር በመሆን ደጎማ መሽጎ የነበረን ሐይል አፅድተዋል። በአርበኛ ታርቆ ከበደ የሚመራው ታዲዮስ ታንቱ ክ/ጦር በአደረገው አልህ አስጨራሽ ተጋድሎ ብሬን ጨምሮ ብዙ የነብስ ወከፍ መሳሪያዎችን የማረኩ ሲሆን በሰላም እጃቸውን የሰጡትን ተቀብለው የቀሩትን ሸኝተዋል። በተደረገው ተጋድሎ 40 የሚሊሻ አባላት ወደማይቀረው ሲሸኙ 27 የሚሆኑት ደግሞ በሰላም እጃቸውን ሰጥተው ከሞት ተርፈዋል። ምርጫችን ማሸነፍ ብቻ ነው! አፋብን ጎጠግ ዕዝ ግንኙነት መምሪያ! Fb:https://www.facebook.com/share/p/1CVZL1HmfE/

  • 1 мар.6 1662

    без подписи

  • 1 мар.5 7903

    без подписи

  • 1 мар.6 150313

    የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፊያለው ደሴ ኮር የአንበሳው ጋይንት ክ/ጦር አመራሮች ከጎብጎብ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል። በዚህም በወቅታዊ የአማራ ፋኖ የትግል ጉዳይ እና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ውይይት የተደረገ ሲሆን ማህበረሰቡም ትግሉን እያገዘ የቆየ መሆኑን እና በቀጣይም ከትግሉ ጎን ሆኖ የጋራ ትግል እሚያደርግባቸውን ሁለተናዊ ድጋፍ እንደሚያደርግ ጭምር አሳውቋል። ድል ለአማራ ህዝብ!! ድል ለአማራ ፋኖ!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር አንበሳው ጋይንት ክፍለ ጦር የህዝብ ግንኙነት ክፍል!!! የካቲት 22/2018 ዓ,ም Fb:https://www.facebook.com/share/p/1DYTbAtyXs/

  • 26 февр.4 200281

    ሰበር መረጃ የአገዛዙ ወታደሮች በሰላማዊ መንገድ እጅ እየሰጡ ነው!!! አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር አፄ ፋሲል ክፍለ ጦር የአገዛዙን ወታደሮች በመቀበል ላይ ነው። የክፍለ ጦሩ አዛዥ አርበኛ ዝናው አያናው ጋር በተደረገ ንግግር አንድ የሻንበል መሪውን ጨምሮ 11 የአገዛዙ አድማ ብተና አባላት ከ 1 ብሬን እና 11 የነፍስ ወከፍ ክላሽ ኮፕ ትጥቆች ጋር ክፍለ ጦራችንን በሰላም ተቀላቅለዋል። አሁንም ቢሆን ለወደቀ ስርዓት እርስ በርስ ከምንገዳደል በሰላማዊ መንገድ ትግላችንና አባላችንን እንድትቀላቀሉ እና ትግላችንን የጋራ እንድናደርግ ወንድማዊ ጥሪ እናቀርብላችኋለን። ድል ለአማራ ፋኖ!!! ድል ለአማራ ህዝብ!!! የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር ህዝብ ግንኙነት !!! የካቲት 19/ 2018 ዓ.ም Fb:https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0ERxLVizs1T1jq4Dnx8dAh4d1aGpDmsyGnj62umTStKS9iFLtu3BkL7gZafyEHjH5l&id=61588416561129&mibextid=CDWPTG

  • без подписи

  • без подписи

  • 25 февр.3 890303

    #ሰበር ዘመቻ ታድሎ ወርቄ አፋብን ጎጠግ ዕዝ 202ኛ ኮር በጌምድር ክ/ጦር እና ዞብል ጃኖ ክ/ ጦር ጣቁሳ ወረዳ ደልጊ ከተማን ተቆጣጥሯል። ጠላት በኮንክሪት የሰራቸው ምሽጎች ተሰባብረዋል። fb: https://www.facebook.com/share/p/1GKgMXSCAV/