tgindex
CHRISTIAN BROTHER HOOD የክርስቲያን ወንድማማቾች ህብረት

CHRISTIAN BROTHER HOOD የክርስቲያን ወንድማማቾች ህብረት

Статистика

ይህ ቻናል የተከፈተበት ዋና አላማ ክርስቲያኖች በእምነታቸው ምክንያት የሚደርስባቸውን ጥቃት ለዓለም ለማሳየትና ሊደርስባቸው የሚችለውን ጥቃት አስቀድሞ ለማሳወቅ እና ነቅተው ረሳቸውን እንዲጠብቁ ለማስቻል ነው ።በተጨማሪም እርስ በራስ መረጃን ለመለዋወጥና ወንድማማችነትን ለማጎልበት ነው።https://www.facebook.com/eotci1/

Последний пост
9 июн.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
470
0 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
417
20 постов
Вовлечённость
88,7%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ክርስቲያናዊን ወደዚህ ይጋብዙ @Christianbrotherhood መልእክቶቻችሁን በ  @Christianbrothershood

  • ክርስቲያናዊን ወደዚህ ይጋብዙ @Christianbrotherhood መልእክቶቻችሁን በ  @Christianbrothershood

  • без подписи

  • #EOTC የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች መገደላቸው ተገለጸ። በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በመኀል ሳይንት ወረዳ በተተኮሰ ከባድ መሣሪያ 5 የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች መገደላቸው ተገለጸ። በአደጋው 26 ኦርቶዶክሳውያን ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸውም ተነግሯል። ቅዳሜ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በመኀል ሳይንት ወረዳ በምትገኘው ርእሰ አድባራት ወታዕካ ነገሥት አትሮንሰ ማርያም ገዳም በዕለቱ  ቅዳሴው እንደተጠናቀቀ ከደቂቃዎች በኋላ የዕለቱን ቅዳሴ የመሩ መነኮሳትና ዲያቆናት ወደ ደጀ  ሰላም ቢያመሩም በተተኮሰው  ከባድ  መሣሪያ ከአንድ ወር በፊት የአስተዳዳሪነት  ቦታቸው የለቀቁ  የቀድሞ  የገዳሙ  አስተዳዳሪ፣ 3 ዲያቆናትና አንዲት አቃቢ መገደላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቴሌቪዥን ዘግቧል። በተተኮሰው ከባድ መሣሪያ በሰዓቱ በገዳሟ ቅጥር ጊቢ የነበሩ 26 ሰዎችም ከባድ  የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተጠቁሟል። ከሞቱት አገልጋዮች መካከል ዛሬ የካቲት 29 ቀን 2018 ዓ.ም 3ቱ በገዳሙ ሲቀበሩ 2ቱ  ደግሞ አስክሬናቸው ወደ ቤተሰባቸው  ተሸኝቷል። በአካባቢው በተደጋጋሚ በተፈፀመው የከባድ መሣሪያ ድብደባ በገዳሙ የነበሩ ከ60 በላይ የአብነት ተማሪዎችና ከሞት የተረፉት አገልጋዮች አካባቢውን ለቀው መሸሻቸው ተገልጿል። በአሁኑ ሰዓት በመኀል ሳይንት ወረዳ ታዕካ ነገሥት አትሮንሰ ማርያም ገዳም አቅራቢያ የሚኖሩ ነዋሪዎችና ገዳማውያኑ በከፍተኛ ስጋት ውስጥ መሆናቸው ተጠቅሷል። ርእሰ አድባራት ወታዕካ ነገሥት አትሮንሰ ማርያም ገዳም በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ካሉ ዕድሜ ጠገብና የኦሪት መሥዋዕት   ከተሠዋባቸው ገዳማት መካከል አንዷ ናት። መረጃው የEOTC TV ነው። @Christianbrotherhood @Christianbrothershood

  • без подписи

  • #ሰበር " ለበርካታ ዓመታት ከገጠር እስከ ከተማ ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ሀገራት ቅዱሱን ሕያው ወንጌል በታማኝነትና በትጋት ያለዕረፍት ያገለገሉት መምህር ዘለዓለም ወንድሙ በዛሬው ዕለት ከድካመ ሥጋ ዐርፈዋል " - የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዲስ አበባ የካቲት 28 ቀን 2018 ክርስቲያናዊን ወደዚህ ይጋብዙ @Christianbrotherhood መልእክቶቻችሁን በ  @Christianbrothershood

  • ማርያምን አስለቀሰኝ🥹 እናቱን ገደሉበት እሱ ደግሞ እግሩን እንዲቆረጥ በህክምና ተወሰነ ተቆረጠም🥹 5 ኪሎ ያሉ ጳጳሳት ስልጣን ሽሚያ ላይ ናቸው! ክርስቲያናዊን ወደዚህ ይጋብዙ @Christianbrotherhood መልእክቶቻችሁን በ  @Christianbrothershood

  • በአርሲ ሀገረ ስብከት በኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚኖሩ 14 ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ። ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም በአርሲ ሀገረ ስብከት ጉና ወረዳ በሚገኘ ኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያን መገዳላቸውን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያሳያል። በደረሰን መረጃ መሠረት በቀበሌው የሚኖሩ 14 ኦርቶዶክሳውያን ከለሊቱ 6:00 ሰዓት አካባቢ በዕለተ ረቡዕ ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ለ14 አጥቢያ ከተኙበት ከቤታቸው አስወጥተው የታጠቁ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሲሆን ስድስቱ ከመገደላቸው ከአንድ ቀን በፈት ቀድመው ታፍነው ተወስደው ነበር ተብሏል። የተገደሉት ምእመናን የዕድሜ ክልላቸው ከ2 ዓመት ጀምሮ እስከ 76 ዓመት አዛውንት እንደሚገኙበት መረጃው ይገልጻል። በተጨማሪም ሁለት ሰዎች በጥቃቱ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ለተሻለ ሕክምና ወደ አቦምሳ ከተማ ሪፈር መሄዳቸውን በመረጃው ተያይዞ ተነግሯል፡፡ ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ በቀበሌው ውስጥ የሚኖሩ 8 ኦርቶዶክሳውያን ሌሊት ላይ ከቤታቸው አስወጥተው የታጠቁ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸውን በደረሰን መረጃ ለማወቅ ችለናል። ከተገደሉት ምእመናን ውስጥ 6ቱ በገገሌ በዓለወልድ ቤተ ክርስቲያን፣አንድ ደግሞ በሞዬ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን እና ቀሪ ሟቾች ባሉበት አካባቢያቸው ሥርዓተ ቀብራቸው መፈጸሙ ተገልጿል። በመረጃው እንደተመላከተው በቀበሌው ባለ ከፍተኛ ስጋት በቀጣይ የባሰ ችግር እንዳይፈጠር በሀገረ ስብከት ደረጃ ከመንግሥት ጋር በጋራ መሥራት ይገባል ተብሏል። በአሁኑ ሰዓት በአካባቢው ሁኔታዎችን ለማረረጋት የሀገር መከላከያ በስፍራው እንደሚገኝ በመረጃው ተጠቅሷል። ክርስቲያናዊን ወደዚህ ይጋብዙ @Christianbrotherhood መልእክቶቻችሁን  @Christianbrothershood

  • без подписи

  • መስቀሉን ወረረው ትቋቁር አሞራ: እንደ ጥንቱ መስሎኝ የዛሬው ደመራ! የመስቀል ወፍ መጥታ ችቦው እስኪበራ: ወፊቱን ስጠብቅ እስክትመጣ በርራ: በመስቀል ወፍ ፈንታ ሌላ ጉድ ተሠራ: መስቀሉን ወረረው ትቋቁር አሞራ: ዛሬአችን ሥቃይ ነው ነጋችን መከራ: ብርሃን የሌለበት ይኽው ደመራ: ያ የደመቅንበት ኢትዮጵያን ያኮራው ከዐድዋ ጀምሮ ጠላት የሚፈራው በእዮሐ አበባዬ የት አለ ባንዴራው? ክርስቲያናዊን ወደዚህ ይጋብዙ @Christianbrotherhood መልእክቶቻችሁን  @Christianbrothershood

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • በምሥራቅ አርሲ ሮቤ ወረዳ ኦርቶዶክሳውያን ተገደሉ። መስከረም 7 ቀን 2018 ዓ.ም በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በሮቤ ወረዳ በእንደቶ 01 ቀበሌ መስከረም 05 ቀን 2018 ዓ.ም ሰኞ ከለሊቱ 5፡00 ለማክሰኞ አጥቢያ ሁለት ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂ ኃይሎች ተገድለዋል። አቶ ከበደ ማሞ እሸቱ የተባሉ የ65 ዓመት አዛዉንትና የ6 ልጆች አባት እንዲሁም ወ/ሮ አበሬ ስዩም የተባሉ የሁለት ልጆች እናት በጥይት መገደላቸውን ከአካባቢው ነዋሪዎች የደረሰን መረጃ ያመላክታል። በተጨማሪም የወ/ሮ አበሬ ስዩም የ 15 ዓመት ወንድ ልጅ ተማሪ እሱባለዉ ስዩም በታጣቂዎቹ በጥይት ተመትቶ በሕክምና ላይ ይገኛል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን አሳውቀዋል። በሮቤ ወረዳ በተደጋጋሚ በምእመናን ላይ ጥቃት፣ ሞት ፣ ዘረፋ እና ስደት እየደረሰ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል ። በተለይም የሮቤ እንደቶ 01 ቀበሌ ከሮቤ ከተማ 60 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ መሆኑን ተከትሎ ምእመናን ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኙም ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን በተደጋጋሚ ተናግረዋል፡፡ ክርስቲያናዊን ወደዚህ ይጋብዙ @Christianbrotherhood መልእክቶቻችሁን  @Christianbrothershood

  • без подписи

  • በሐዲያ ዞን የጊንበቾ ከተማ ኦርቶዶክሳውያን በዓለ ጥምቀትን ጥቁር በመልብሰ አሳልፈዋል። ክርስቲያናዊን ወደዚህ ይጋብዙ @Christianbrotherhood መልእክቶቻችሁን  @Christianbrothershood

  • без подписи

  • без подписи

  • በምእራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በነንሰቦ ወረዳ ገረምባሞ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ የጥምቀት በዓል ተከበሯል። ክርስቲያናዊን ወደዚህ ይጋብዙ @Christianbrotherhood መልእክቶቻችሁን  @Christianbrothershood

  • የመጀመሪያው "የጥምቀት ኤክስፖ " በይፋ ተከፈተ የተዋህዶ ኤክስፖ ሁለተኛ ክፍል የሆነው የጥምቀት ኤክስፖ  2017  በአዲስ አበባ ኤግዚብሽን  ማዕከል ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል። ማርኮናል ኢቨንት ኦርጋናይዘር ከጠቅላይ ቤተ ክህነት እና  ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጋር በመተባበር ያዘጋጀዉ ይህ ኤክስፖ  ዛሬ ጥር 3/2017 ዓ / ም በኤግዚቢሽን ማእከል የመክፈቻ ስነስርዓቱ ተከናውኗል። ይህ በአይነቱ መጀመሪያ የሆነው የጥምቀት ኤክስፖ  ከጥር 3 ጀምሮ እስከ ጥር 9 ድረስ የሚቆይ ይሆናል። በዚህ የጥምቀት ኤክስፖ መፅሀፍትን ጨምሮ የተለያዩ የኪችን እቃዎችን እንዲሁም ሀይማኖታዊ ልብሶች እና እቃዎች እንደሚገኙም ተነግሯል። እስከ ጥር 9 ድረስ በሚቆየው በዚህ የጥምቀት ኤክስፖ  ከ10 ሰዓት  በኋላ የተለያዩ መዘምራን በተገኙበት ሀይማኖታዊ መርሀ ግብር እንደሚካሄድም ሰምተናል። ክርስቲያናዊን ወደዚህ ይጋብዙ @Christianbrotherhood መልእክቶቻችሁን  @Christianbrothershood