tgindex
🔥 እናት መረጃ ዜና

🔥 እናት መረጃ ዜና

Статистика

ትኩስ ዜናዎችን፤መረጃዎች ፤ ክስተቶችን ፤ወንጀሎችን እና አለማቀፍ ሁነቶችን ክሽን ባለ አቀራረብ ወደናንተ የሚያደርስ ቻናል ነው ። ቻናሉን ተቀላቀሉ🙏https://t.me/EnatMerejaa #tiktok _Enatmereja የተለዪዩ የህይወት ሳይኮሎጂዎችን ለማግኘት👇 https://t.me/adviceeeeee

Последний пост
31 июл.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
45
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
4 732
−11 за 3 дн.
Сутки
−4
−0,08%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 616
40 постов
Вовлечённость
34,2%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 45
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1 303
1/48двое суток
1 493
1/72трое суток
1 610

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • 31 июл.1 220101

    በአንድ ወጣት ካሜራ አማካኝነት በገጠር ተቀርጻ በማህበራዊ ሚዲያ ከተጋራች በኋላ በመላው ኢትዮጵያ የበርካታ ሰዎችን ትኩረት ስባ የነበረችው ታዳጊ ኤልሳቤት ደስታ፣ አሁን ላይ የህይወት ምዕራፏ በከፍተኛ ሁኔታ መቀየሩ ተበሰሯል። ተፈጥሯዊ ውበቷና ማራኪ ገጽታዋ በዲጂታል ገጾች ላይ በስፋት ከተሰራጨ በኋላ ከፍተኛ ተቀባይነትን አግኝታ የነበረችው ኤልሳቤት፣ አሁን ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የሞዴሊንግና የፎቶሹት ሙያዊ ስልጠናዎችን መውሰድ ጀምራለች። ወደ ዋና ከተማዋ ከመጣች በኋላ በታወቀችው የሜክአፕ አርቲስት «Touch by Marzel» የተደረገላት የውበት እንክብካቤና የሞዴሊንግ ዝግጅት ድምቅ ያደረጋት ሲሆን፣ ይህ አጋጣሚም ወደ ዓለም አቀፍ የሞዴሊንግ ስራዎችና መድረኮች እንድትቀላቀል መንገድ ከፍቶላታል። በአጭር ጊዜ ውስጥ ከገጠር አካባቢ ተነስታ እስከ ዓለም አቀፍ የሞዴሊንግ እድሎች ድረስ መድረሷ በብዙዎች ዘንድ አነቃቂ አጋጣሚ ሆኖ የተቆጠረ ሲሆን፣ ትክክለኛ አጋጣሚና ድጋፍ ሲገኝ ህይወት በአንድ አፍታ እንዴት ሊቀየር እንደሚችል ያሳየ ክስተት እንደሆነ በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ይነገራል። ነገር ግን አንዳንዶች የሜካፑን ገፅታ እምብዛም አልተቀበሉት እናንተስ የትኛው በተሻለ ተመለከታቹት / ሳባቹ ? EnatMerejaa🤱 https://t.me/EnatMerejaa

  • 27 июл.1 83182

    የችሎት ዜና በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከአንድ ዓመት በላይ ሲታይ የቆየው የቀድሞ የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ እና የቀድሞው የሲዳማ ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ ሽመልስ ቶማስ የክስ መዝገብ በመጨረሻ ውሳኔ ተቋጨ። ፍርድ ቤቱ ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ ጥፋተኛ በተባሉባቸው ወንጀሎች የ10 ዓመት ከ5 ወር ፅኑ እስራት እና የ4,000 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል። በተመሳሳይ መዝገብ የተከሰሱት የቀድሞው ኮሚሽነር አቶ ሽመልስ ቶማስ ላይ ደግሞ የ1 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት ፍርድ ተላልፎባቸዋል። EnatMerejaa🤱 https://t.me/EnatMerejaa

  • 27 июл.1 4691

    без подписи

  • 20 июл.2 2171

    без подписи

  • 20 июл.2 1961

    без подписи

  • 20 июл.2 0041

    без подписи

  • 20 июл.2 0051

    без подписи

  • 20 июл.1 8301

    без подписи

  • 20 июл.2 190121

    #WorldCup : ስፔን የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ሆነች። በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ከአርጀንቲና ጋር የተፋለመችው ስፔን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫው ባለቤት ሆናለች። የጨዋታው መደበኛው 90 ደቂቃ አልቆ በተጨማሪው 30 ደቂቃ ላይ ነው አንድ ጎል አስቆጥራ ያሸነፈችው። በሙሉ ጨዋታው ስፔን ከፍተኛ ብልጫ ወስዳ ነበር። ሊዮኔል ሜሲ ተከታታይ የዓለም ዋንጫ የሚያሳካበት እድል ሳይሰምር ቀርቷል። EnatMerejaa🤱 https://t.me/EnatMerejaa

  • без подписи

  • 19 июл.1 8977

    አሳዛኝ አደጋ:-  የ12 ሰዎች ሕይወት አለፈ‼ በሶማሌ ክልል ቀብሪበያህ ወረዳ ጉዮው ቀበሌ ዛሬ ንጋት ላይ በደረሰ ከባድ የትራፊክ አደጋ የ12 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ፣ በ3 ሰዎች ላይ ደግሞ የመቁሰል አደጋ ደርሷል። አደጋው የተከሰተው በአንድ ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) እና በአይሱዙ ጭነት መኪና መካከል በተፈጠረ ግጭት መሆኑን የሶማሌ ክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አስታውቋል። የአደጋው መንስኤ በአሁኑ ወቅት በፖሊስ እየተጣራ ይገኛል። የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሐመድ በአደጋው ሕይወታቸውን ባጡ ወገኖች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን የገለጹ ሲሆን፣ ለተጎጂ ቤተሰቦችም መጽናናት ተመኝተዋል። EnatMerejaa🤱 https://t.me/EnatMerejaa

  • 19 июл.1 25821

    አዲሱ የዩኒቨርስቲ የፕሬዝዳንትነት መመርያ EnatMerejaa🤱 https://t.me/EnatMerejaa

  • 18 июл.1 6125

    " ህወሓት ከሻዕቢያ ጋር በመተባበር ወጣቶችን ለሞትና ለስደት እንደዳረገ ነው " - አቶ ጌታቸው ረዳ በትግራይ የሰላምና የለውጥ ምክር ቤት አዘጋጅነት "አፈሳ ይቁም፣ ሰላም ይስፈን" በሚል መሪ ቃል በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል። ሰልፉ በክልሉ የሚታየው የውጥረት ሁኔታ እንዲያበቃና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ጥሪ ያቀረበ ነበር። ሰልፈ ላይ የተገኙት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ፣ የፕሪቶሪያ ስምምነት እንዲተገበር የነበረው ጥረት በ "ሙሉ ስልጣንን ለመቆጣጠር በሚፈልግ ቡድን" መሰናከሉን ተናግረዋል። እንደ ገለጻቸው፣ ስምምነቱ ሳይተገበር "ፈርሷል" የሚል ትርክት በመፍጠር ከሻዕቢያ ጋር መቀናጀት እንደተመረጠ ገልጸዋል። አቶ ጌታቸው በንግግራቸው፣ ህወሓት ከሻዕቢያ ጋር በመተባበር በትግራይ ውስጥ ሁከት እንዳባባሰ፣ ወጣቶችን ለሞትና ለስደት እንደዳረገ እና ክልሉን ለአለመረጋጋት እንዳጋለጠ ተናግረዋል። በተጨማሪም ወጣቶች ለውጭ ኃይሎች እየተሸጡ መሆናቸውንና የቡድኑን ድርጊት የተቃወሙ ወጣቶችም መታሰራቸውን በመጥቀስ፣ ለዚህ ሁኔታ ተጠያቂነት ሊኖር እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በተጨማሪም፣ ለክልሉ የተመደበው በጀት ለህዝብ አገልግሎት ከማዋል ይልቅ በማባከን ተጠምዶ ቆይቶ ይህንንም ከህዝብ በመደበቅ በፌደራል መንግስት ላይ ተደጋጋሚ ወቀሳ ሲቀርብ እንደነበር ተናግረዋል። የትግራይ ችግር መፍትሄ በሰላምና በውይይት ብቻ ሊገኝ እንደሚችል ያስገነዘቡት አቶ ጌታቸው፣ ማንኛውም መፍትሄ ህዝቡን ማዕከል ያደረገ ሊሆን እንደሚገባ ገልጸዋል። የፌደራል መንግስትም ህዝቡን ለመጠበቅ ያለበትን ህገ-መንግስታዊ ሀላፊነት እንዲወጣ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም በጉዳዩ ላይ ተገቢውን ጫና እንዲያሳድር ጠይቀዋል። በሌላ በኩል በሰልፉ ላይ ፦ - " በህወሓት ቡድን የተጣለው አፋኝ አዋጅ በአስቸኳይ ይነሳ! " - " ጦርነት ይብቃ፤ ሰላም የትግራይ ህዝብ ምርጫ ነው " - " ወጣቶች ለጦርነት ዓላማ በኃይል እየታፈሱ መወሰዳቸው ይቁም! " - " ጦርነት ይበቃ፣ ስደት ይበቃናል! " - " ሰላም የትግራይ ህዝብ ምርጫ ነው! " - " የፕሪቶሪያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ ይከበር! EnatMerejaa🤱 https://t.me/EnatMerejaa

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи