tgindex
Endalkachew Ababu Ayele

💚💛❤️እውነትና ኢትዮጵያዊነቴ ትክ የለሽ ሀብቶቼ ናቸው።💚💛❤️

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
5
Всего постов
23
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 937
−23 за 4 дн.
Сутки
−18
−0,92%
Неделя
—
 
Месяц
—
 
Просмотров на пост
920
23 постов
Вовлечённость
47,5%
к подписчикам
Постов в день
0,7
всогО 23
УпОПинаниК
0
канаНОв
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
371
1/48двое суток
425
1/72трое суток
458

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ወላፈኑ ሸዋ 💪

  • https://youtu.be/NzmXUkkaT9I?si=N_JLU_i65qUj20Ba እለታዊ ዜናዎቹን ትከታተሉ ዘንድ ይሄው 👌

  • የምንመካከረው በብሔራዊ መግባባት አገርን ለማጽናት እንጂ የቡድን የበላይነትን ለማንበርና ሌላ አዲስ የእርስ በእርስ ጦርነት ለማዋለድ አይደለም! በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ዙሪያ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ የአቋም መግለጫ ኢትዮጵያ ሀገራችን እያለፈችበት ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመፍታት በምክክር ብሔራዊ መግባባት በመፍጠር አገር ልትጸና ይገባል በሚል ጽኑ እምነት ፓርቲያችን የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ያላሰለሰ ጥረት አድርጓል። በአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምሥረታው፣ በኮሚሽነሮች አመራረጥና በኮሚሽኑ የአሠራር ሂደት፣ የአካታችነት ችግሮች፣ እየተካሄዱ ያሉ ጦርነቶች በሚያሳድሩት አሉታዊ ተጽዕኖና መሰል አስቻይ ባልሆኑ ሁኔታዎች ላይ ጠንካራ ሀሳቦችንና የመፍትሔ ጥቆማዎችን ፓርቲያችን ሲያቀርብ መቆየቱም ይታወቃል። ፓርቲያችን በምክክሩ ሂደት እና ከምክክሩ አስቀድሞ ስኬታማ ምክክር ለማካሄድ ሊተገበሩ ይገባቸዋል ብሎ የሚያምንባቸውን ሃሳቦችና ቅድመ ሁኔታዎች በግልጽ አስቀምጦ ያለመታከት ሲያሳስብ የቆየ ቢሆንም ሰሚ ጆሮ በመጥፋቱ አገር ባለችበት ሁኔታ ወደ ምክክር እንድትገባ ተደርጓል። እናት ፓርቲ ይህን በትክክለኛው ጎዳና ተጉዞ በስኬታማ መልኩ ሊጠናቀቅ ቢችል የአገራችን መፃኢ ጉዞ ላይ ትልቅ ምዕራፍ ሊከፍት የሚችልን ሂደት ቅድመ ሁኔታዎች ስላልተሟሉ በማለት በቸልታ ሊመለከተው ያልፈለገ ሲሆን ይልቁን ሂደቱ ውስጥ በማሳተፍ ትክክለኛነቱን ካረጋገጠ ለአገር የሚበጁ ሀሳቦችን በማንሳት ለመሞገት ብሎም በተመካካሪዎች ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ በማድረግ በጎ ተጽዕኖ መፍጠርን በማሰብ በምክክሩ እየተሳተፈ ይገኛል። አገር የገባችበት ችግር ከምንጊዜውም ይልቅ በተወሳሰበበት ሁኔታ ውስጥ የምክክሩ ሂደት ከነችግሮቹ እያነከሰ ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ ያለው ሀገራዊ ምክክር ወደ መጨረሻው ምዕራፍ እየተሸጋገረ ያለ ቢሆንም በሂደቱ የጎሉ ችግሮች እየተስተዋሉበት ይገኛል። ለአብነትም በወረዳ ደረጃ ተደረጉ ከተባሉ ምክክሮች ጀምሮ የምክክር ተሳታፊዎች የገዥው ፓርቲ አባላት እና የሥርዓቱ ደጋፊዎች መሆናቸው ሲገለጽ የነበረ ሲሆን በአገር አቀፍ ደረጃ እየተደረገ ባለው በዚህ ምክክርም አብላጫውን ቁጥር የሚይዙ ተሳታፊዎች የገዥው ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች መሆናቸውን መረዳት ችለናል። በምክክሩ ሂደት ድምጾች እንዳይሰሙ መገደብ፣ የአካታችነት ችግሮች፣ የተሳታፊዎች ምርጫና ምደባ፣ የፍትሓዊነት፣ የገለልተኝነት፣ የግልጽነት ማነስ፣ በጸጥታ አካላት ታጅቦ መወያየት፣ የውይይት ተሳትፎውን ለማጥበብ ከውስጥና ከውጭ የሚደረጉ ጫናና ወከባዎች፣ የምክክሩ አጠቃላይ ወለል ወይም ቀይ መሼመር ያለመኖር እና የመሳሰሉ ጉልህ ችግሮች የተስተዋሉበትን እውነታ ታዝበናል። ምክክሩ ኢትዮጵያን ለማጽናት ሳይሆን እንዳለፈው ጊዜ ስሑት ትርክትና ሕገ መንግሥታዊ መሠረት ያለው የጨቋኝ ተጨቋኝ ትርክት ብሎም ሁሉ ለእኔ ብቻ ፍላጎት በአጠቃላይ ኢትዮጵያን አንደ ሀገር እና ዋና መገለጫ ጌጦቿን ኹሉ ለድርድር ያቀረበ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። በዚኽም የምክክሩን ፍትሓዊነትና ቅቡልነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ሆኖ አግኝተነዋል። ይኽ ደግሞ ፓርቲያችንና ሌሎች ተሳታፊዎች ከሂደቱ ራሳቸውን እንዲያገሉ እያስገደደ ይገኛል። ምክክር የቅንጦት ጊዜ ኹነት ሳይኾን የቀውስ ጊዜ መፍትሔ ማመንጫ ውጥን ነው። ቀዳሚው ዘርና ጎሳ ላይ የተመሠረተው ፌዴራሊዝም ሀገራችንን ሊያጠፋት ከጫፍ ደርሶ እያለ ይህን ያፈጠጠ አደጋ ሊያስቀር ወይም ሊያለዝብ የሚችል መፍትሔ ይጠበቅ የነበረ ቢሆንም ምልክቱ እንኳ አለመታየቱ እጅግ የሚያስቆጭ ነው። እንዲያውም ገና ምክክሩ ሳይጠናቀቅ አንዳንድ ክልሎችን በስም ተጠርተው ሌላ ክልል ለማዋለድ ምክረ ሀሳብ ሲነሳ ብቻ በደስታ ይጨበጨባል፤ ሌላው ደግሞ ማን ነክቶን እያለ በማን አለብኝነት መግለጫ ይሰጣል። ይህም በዘርና በጎሳ ላይ የተመሠረተ ፖለቲካ ለሀገር አንድነትና ሕልውና ሥጋት መሆኑን አንዱ ማሳያ ነበር። በሌላ በኩል ይህ ምክክር እየተካሄደ ባለበት በአሁኑ ወቅት ቢያንስ ሦስት ክልሎች ላይ ጦርነቶች እየተካሄዱ ነው፤ ሌላውም መጣሁ እያለ ነው። የርስ በርስ ጦርነቱን ጉዳይ ብልጽግናን ጨምሮ ሁሉም ተዋጊ ኃይሎች ወደ ድርድር እንዲመጡ እውነተኛ፣ ጥልቅ ውይይትና ደፋር ምክረ ሀሳብ ይፈልግ የነበረ ቢሆንም ሂደቱ ግን እከከኝ ልከክህ ሆኖ የአንድን ወገን ጥቅምና ፍላጎት ለማስጠበቅ ቀድሞ የተወሰነን ውሳኔ በሀገራዊ ምክክር ስም ቅቡልነት እንዲኖረው ለማድረግ እየተከናወነ ነው። የታሪክና የትርክት መፋለሶች በናኙበት በዚህ ዘመን ቢያንስ እውነት አፈላላጊ ቡድኖችን አዋቅሮ ግማሽ መንገድ እንኳን ማቀራረብ ይገባ ነበር። እነዚኽንና መሰል አንኳር ጉዳዮች እንጂ የኢትዮጵያ መሪ (ከፕሮቶኮል አንጻር ነው አመክንዮው) ጠቅላይ ሚንስትር ሳይሆን ፕሬዝዳንት መኾን ነው ያለበት ላይ አልነበረም የችግሮቹ ቋጠሮ ያለው። ዙሪያ ዙሪያዋን ሲሏት የነበረችውን አዲስ አበባ በወከባ ብዛት ለአንድ ቡድን ሆ ብሎ ለማሳቀፍና አዲስ የፀብ ግንባር ለመቀስቀስም አልነበረም ለምክክር የተቀመጥነው፡፡ ድሬዳዋ ከየት ወገን ትሑን የሚለው ሀገር ሊያፈርስ ደርሶም አልነበረም በሚሊዮን የሚቆጠር የሀገር ሀብት አባክነን ለምክክር የተቀመጥነው፡፡ በዓለም በልዩነት የምንታወቅበት ዘመን አቆጣጠር አሥሮ ይዞንም አልነበረም ምክክር ያስፈለገን፡፡ በአጠቃላይ የተጠቀሱና መሰል የተስተዋሉ ሳንካዎች ምክክሩ ከታለመለት ዓላማና በሀገሪቱ ያለውን ችግር ከሥሩ ከመፍታት ይልቅ ጠግኖ ለማስቀጠል፣ ለይምሰል የተደረገ፣ የአገዛዝ እና ቡድን(ኖች) ጠባብ ጊዜያዊ ፍላጎት ለማሳካት በሚመስል ሁኔታ እየተከናወነ እንዳለ ይሰማናል። በዚህም በመሠረታዊ የሀገር ሕልውና ጉዳዮች በዋናነት የርስ በርስ ጦርነትን በማስቆም፣ የዘርና ጎሳ ፌዴራሊዝምን ማስቀረት/ማለዘብ እንደ ዋና ግብ መያዝና መሰል የተጋረጡ ፈተናዎች በአግባቡ ተረድቶ እልባት የሚበጅበትን አቅጣጫ ሊያስቀምጥ ያልቻለ ሀገራዊ ምክክር ከመነሻው እንደከሸፈ ለመረዳት ነቢይ መሆን አይጠይቅም። እናት ፓርቲ ከዚህ በመለስ ባሉ የምክክር አጀንዳዎች እና በምክክር ስም ተላለፉ በሚባሉ ስምምነቶች ላይ ፊርማውን የማያሰፍር መሆኑን ሕዝባችን እንዲያውቅ መልእክታችንን እናስተላልፋለን፡፡ በዚህም፤ 1. ገዥው ፓርቲ በሀገራዊ ምክክሩ ስም ለማሳካት ከሚፈለግ ማንኛውም ፍላጎትና ሀገርን አስይዞ ከሚደረግ የፖለቲካ ቁማር እንዲታቀብ እናሳስባለን። 2. ተመካካሪዎች ለጊዜያዊ ጥቅምና የፖለቲካ ውሳኔዎች ሽፋን ከመስጠት እና በታሪክ ተወቃሽ ከሚያደርጉ ድርጊቶች በመቆጠብ ለሀገርና ለሕዝብ መቆምን በቀረችው አጭር ጊዜም ቢሆን በድፍረት እንዲያሳዩ በአክብሮት እንጠይቃለን። 3. ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሀገራዊ ምክክሩ የጥቂት አካላትን ፍላጎት ማስፈጸሚያና ለአዲስ ቁርሾ የሚያዘጋጅ እንዳይሆን ሂደቱን በንቃትና በትኩረት እንዲከታተል እናሳስባለን። ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! እናት ፓርቲ ነሐሴ ፎ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

  • https://youtu.be/ho46t_g9Tn0?si=CueSY-5FfZ1K05_R

  • https://youtu.be/yEewiA4AH4I

  • https://youtu.be/vQ4kqXzoZiQ?si=34SYDQakEJMSUSQl

  • https://youtu.be/_7xZB-JQd68

  • https://youtu.be/qoduKgexORM

  • ሰበር ዜና ! ከፍተኛው ውጊያ ማለዳ 12 ሰዓት ጀምሮ በከባድ መሳሪያ ቀጥሏል። በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር የተጀመረው ይህ ውጊያ እስካሁን ከታዩት ሁሉ የከፋ እንደሆነ እየተነገረ ነው። በዝርዝር እንመለስበታለን።

  • https://youtu.be/FtJ8PvX7F2I?si=NtUe3VCx4wR328hw

  • https://youtu.be/KLjfqsTsA7U ሰበር መረጃውንና የምሽግ ድልሉን ስሙት

  • የአማራ ክንድ 💪

  • https://youtu.be/gxB1_Kq6mJ4

  • “እየተመካከሩ” የሚገኙ የባለድርሻ አካላት ተወካዮች የተለያዩ “የማንነትና አስተዳደር መዋቅር” ጥያቄዎችን እያነሱ መሆናቸውን ሰምተናል። ብልጽግና ፓርቲ ባደረገው ስብሰባ፤ ለመሰል ጉዳዮች ፓርቲው ያለውን አቋም አስመልክቶ ጥያቄ ያቀረቡ የፓርቲው “አባላት”፤ ፓርቲው የማንነትና አስተዳደር መዋቅር ጥያቄዎች መነሳታቸውን “እንደሚደግፍ” የሚጠቁም ምላሽ ማግኘታቸውን ከምንጮች አረጋግጠናል።  ይህ ጉዳይም በፓርቲው አባላት መካከል “ልዩነት” የፈጠረ መሆኑን የገለጡልን ምንጮች፤ በምክክሩ የተነሱ የማንነትና አስተዳደር መዋቅር ጥያቄዎችን በጽኑ የተቃወሙ የፓርቲው አባላት መኖራቸውን ነግረውናል። ይህ ጉዳይ ፓርቲው በቀጥታ አቅጣጫ ከሰጠባቸው አጀንዳዎች መካከል ባይሆንም፤ ከፓርቲው አባላት ጉዳዩን አስመልክቶ ለቀረበው ጥያቄ መልስ የሰጡ “ከፍተኛ አመራሮች” በመሰል ጉዳዮች ዙሪያ “ተቃውሞ” እንደሌለ ማሳወቃቸውን ሰምተናል።  በማደሪያ ቦታዎች የሚደረጉ ስብሰባዎች ብልጽግና ፓርቲ እሁድ ዕለት “በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል” በሰፊው ካካሄደው ስብሰባ በተጨማሪ፤ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ለ”ተመካካሪዎች” ባዛጋጃቸው የማደሪያ ቦታዎች “አነስተኛ” ስብሰባዎች እንደሚካሄዱ ሰምተናል። በእነዚህ ስብሰባዎች በዕለታዊና “ድንገተኛ” ጉዳዮች ዙሪያ ለ”ተመካካሪዎች” ገለጻ እንደሚሰጥ የነገሩን ምንጮች፤ የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች አመራሮች በተሰጣቸው ተልዕኮ መሰረት ለተመካካሪዎች “አቅጣጫ” እንደሚሰጡ ገልጠዋል።  “ማስታወሻ” ደብተር የያዙ ተመካካሪዎች     በ”ጥቃቅን” ቡድን እንዲሁም በ”ንዑስ” ቡድን ደረጃ በተካሄዱ “ምክክሮች” በ”ማስታወሻ ደብተር” የተጻፉ ጽሑፎችን “እያነበቡ” አስተያየት የሚሰጡ “ተመካካሪዎችን” ማስተዋላቸውን የገለጡልን ምንጮች፤ በአንዳንድ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ መሰል “ዝግጅት” የተደረገባቸው “ጽሑፍ መር አቋሞች”ን መመልከታቸውን ገልጠዋል። በአጀንዳዎች ዙሪያ በተካሄዱ የ”ምክክር” ሂደቶች በተነሱ ሀሳቦች ላይ “ተመካክሬ አስተያየት እሰጣለሁ” የሚሉና “ከሻይ” እንዲሁም “ከምሳ” እረፍቶች በኋላ “የተመካከሩበትን” አስተያየት የሚሰነዝሩ መኖራቸውንም ሰምተናል። ከገዥው ብልጽግና ፓርቲ በተጨማሪ ሌሎች “የተደራጀ” እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ቡድኖች ስለመኖራቸው አክለው የነገሩን ምንጮች፤ በ“ማህበራዊ ሚዲያ” አማራጮች በተከፈቱ መወያያ “ግሩፖች” እንዲሁም በጽሑፍ በሚሰራጩ መረጃዎች አማካኝነት፤ “የተናበበ” ተሳትፎ እያደረጉ መሆናቸውን ገልጠዋል። ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን እስካሁን በመሰል እንቅስቃሴዎች ዙሪያ የሰጠው መግለጫም ሆነ ያጋራው መረጃ የለም። የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ሐምሌ 16 ቀን፤ 2018 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “በማህበራዊ ሚዲያዎች ያልተረጋገጡ መረጃዎች እየተሰራጩ ነው” ማለታቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ሌሎች የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ደግሞ “ያልተረጋገጡ” ያሏቸው መረጃዎች “ባሰራጩ” ተመካካሪዎች ላይ “እርምጃ” እንደሚወሰድ ለ”ተመካካሪዎች” ገለጻ በተሰጠባቸው መርሃግብሮች ላይ ገልጸው ነበር። ይሁንና በዋና ኮሚሽነሩም መግለጫ ሆነ በሌሎች ኮሚሽነሮች ገለጻ፤ “መደበኛ ያልሆኑትን” አደረጃጀቶች አስመልክቶ የተባለ ነገር የለም። [ዋዜማ]

  • https://youtu.be/IaqgKdnjvTk

  • 23 июл.1 310114

    "ኢትዮጵያዊነት ምንድነዉ❓" አስደናቂው የጃንሆይ ምላሽ‼️ "ኢትዮጵያዊነት ኩራትና ትህትና ነዉ" ጃንሆይ ቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ በንግስናቸዉ ወቅት ወደ ኒዉ ዮርክ ለስራ ባቀኑበት ሰአት ነበር ከአንድ የኒዉዮርክ ታይምስ ጋዜጠኛ ፈታኝ ጥያቄ የቀረበላቸዉ። ጋዜጠኛው ንጉሰ ነገስቱን አይን አይናቸዉን እያየ "ኢትዮጵያዊነት ምንድነዉ❓" ነበር ያላቸዉ። ቀዳማዊ ሀይለ ስላሴም በተረጋጋ መንፈስ "ኢትዮጵያዊነት ኩራት እና ትህትና ነዉ" የሚል ምላሽ ነበር የሰጡት። ጋዜጠኛው ግራ በመጋባት አይነት ስሜት፡ "ጃንሆይ ይቅርታ ያድርጉልኝና ይሔ ትህትና (Humbleness) እና ኩራት (Proudness) የሚባሉ የማንነት ባህሪያት እርስ በርሳቸው አይጣረሱም" በማለት ጋዜጠኛው በድጋሚ ጥያቄዉን ያስከትላል። ቀዳማዊ ሐይለስላሴ በልበ ሙሉነት እንዲህ ሲሉ ነበር ለጋዜጠኛዉ ማብራሪያቸዉን ያስከተሉት "አየህ አንድ ለፍቶ አዳሪ ኢትዮጵያዊ አርሶ አደር ቤት በእንግድነት ብትሔድ ያለዉን አብልቶ ፣ እግርህን አጥቦ ፣ ያጠበዉን እግርህን ስሞ ፣ አልጋዉን ላንተ ለቆ እርሱ ግን መሬት ላይ ይተኛል...ይሔ የትህትናዉን ጥግ ያሳያል። ነገር ግን በሚስቱ ፣ በርስቱ እና በሀገሩ ላይ ብትመጣበት ደግሞ ያለ ርህራሔ በግንባርህ ላይ ጥ*ይት ይቆጥርልሀል...ይህ ደግሞ ኩራታዊ ማንነቱን ያሳያል። ስለዚህ ኩራትና ትህትናዉ አይጋጭበትም። ነገር ግን ይሔንን ለመረዳት ኢትዮጵያዊ መሆን አለብህ" በማለት ነበር ጃንሆይ ምላሻቸዉን የሰጡት። ለእናንተስ ኢትዮጵያዊነት ምንድነዉ❓

  • https://youtu.be/XrH0GBd5vII

  • https://youtu.be/pq6YQE5Pc54?si=qZFJfpq-iCWN1GSz

  • እነሆ መቆያ ጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ የረጅሙ ሰው ረጅም ታሪክ፣ የብቁው ባለሙያ አንጋፋ ትረካዎች፣ የጎመሩ ታሪኮች በእሸት አንደበት ሲንቆረቆሩ ኖረው አሁን ደግሞ በመፅሀፍ መልክ ቀርበዋል። ጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ 🎤 እነሆ መቆያ !

  • አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የመጀመሪያ መደበኛ ጉባዔውን አካሄደ ​ሰኔ 16/2018 ዓ.ም ​በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ሁለቱ ዕዞች አንድነታቸውን እውን ካደረጉበት ቀን ጀምሮ በሸዋ ጠንካራ ድርጅታዊና ተቋማዊ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል። የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የመጀመሪያ ጉባዔውን በማካሄድ የሸዋን አንድነት በጽኑ መሠረት ላይ እያጠናከረ መጓዙን ቀጥሏል። ​ይህ ጉባዔ ከሰኔ 9/2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 15/2018 ዓ.ም ለተከታታይ ሰባት (7) ቀናት የተካሄደ ሲሆን፣ በጉባዔው ላይ የዕዙ ጠቅላላ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ተሳትፈዋል። በዚሁ ስብሰባ ላይ ድርጅቱ ከትላንት እስከ ዛሬ እንዲሁም ከዛሬ እስከ ነገ በሚከተላቸው መርሆች ላይ ጥልቅ ግምገማ በማድረግ፣ የታዩ ክፍተቶችን በመንቀስና ለቀጣይ ስኬትን ሊያጎናፅፉ የሚያስችሉ ውሳኔዎችን በማሳለፍ የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል። ​በጉባዔው የተለዩ ዋና ዋና ክፍተቶችና የተወሰዱ ማስተካከያዎች፦ ▸ቀደም ሲል የነበሩ የተናጠል ጉዞዎች ህዝብን፣ ሰራዊትንና ደጋፊዎችን ያሳፈሩ፣ ትግሉ በሚፈለገው ፍጥነት እንዳይሄድ ያደረጉና ለጠላት ጊዜ የሰጡ በመሆናቸው ወደፊት እንዳይደገሙ ተደርጓል። ▸የድርጅቱ የአሠራር ክፍተቶች ተገምግመው፣ አንድ ወጥና ሰንሰለቱን የጠበቀ አሠራር እንዲዘረጋ በሚል አቋም ተይዟል። ▸ከጉባዔው ማግስት ጀምሮ የድርጅቱ ወታደራዊና ህዝባዊ መዋቅር ሙሉ በሙሉ ወደ ሼል እንዲገባ ተወስኗል። ▸የህዝብና የሰራዊት መብቶችን ማክበር ቀዳሚ ተግባር መሆኑ ተረጋግጧል። ​ በሂደቱም ቀጣይ በትኩረት እንድሰሩ አቅጣጫ የተሰጠባቸው ጉዳዮች :- ▸ድርጅታዊ አሠራርና መርሆዎችን ሙሉ በሙሉ ተፈፃሚ ማድረግ። ▸በህዝባዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ አንድ ወጥ አሠራርን መተግበር። ▸የሰራዊቱን ብቃትና ዝግጁነት በስልጠናና ተሃድሶ ወደ መካናይዝድ በማሻሻል ለማይቀረው ድል ማዘጋጀት። ▸ህዝቡ ከትላንት ደጀንነቱ በላቀ መልኩ፣ ለነገው የድል ግስጋሴ በጠንካራና ወጥ አደረጃጀት እንዲዘጋጅ ማድረግ። አርበኛ ኢ/ር ደሳለኝ ሲያስብ (የዕዙ ዋና መሪ) እንደገለፀው :-ትግሉ ግለቱን ጠብቆ እንዳይሄድ አደናቃፊ የነበረውን ወጥመድ በጥሰነዋል። ማዕከላዊ ኮሚቴው በሰራዊቱና በህዝቡ ፍላጎት እውን የሆነውን የሸዋ አንድነት በተግባር ለመግለጽ ከመቼውም በላይ በልበ ሙሉነት ሼል መጀመሩን ገልጿል። ​አርበኛ ጠጁ ባበይ (የዕዙ ም/ል መሪ) እንደገለፀው :-ከውስጥም ከውጪም ድላችንን ለሚናፍቅና በአንድነቱ ደስ ለተሰኘው ሁሉ፣ ለምናደርገው አኩሪ የህልውና ተጋድሎ ከጎናችን ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችን ተግባራዊ ነው።አንድነታችን እውን ነው።ከዚህ ቡሀላ አንድነትን የሚጠላ ካለ ህዝባችንንና ሰራዊታችንም አይቀበልም በአንድነት ለማይቀረው ድል እንጓዛለን። ​በማጠቃለያው፣ የአገዛዙን ዕድሜ ላለማራዘም ዋጋ እየከፈሉ ላሉ ጀግኖች የድል ቀን ከመቼውም በላይ እየቀረበች ስለሆነ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ መስራት አለብን በማለት ሀሳቡን ገልጿል።። ​"ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!" "ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!" ​የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ