tgindex
ጋሜል Media

ጋሜል Media

Статистика
@Gamel_Mediaанглийский

✍️ "ጋሜል" ማለት "እግዚአብሔር ሊመረመር የማይቻል ግሩም ድንቅ ነው።" ማለት ነው። ✍️ ✍️ "ጋሜል ብሂል ግሩም እግዚአብሔር።" ✍️ ✍️ "Gamel" means "God is wonderful beyond measure." ✍️ መዝሙረ ዳዊት (Psalm) 118÷7 Youtube - https://www.youtube.com/channel/UCHxwszkxLPFCFKAOf1WtaDw

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
3
Всего постов
24
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
4 181
−8 за 3 дн.
Сутки
−3
−0,07%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
812
21 постов
Вовлечённость
19,4%
к подписчикам
Постов в день
0,4
всего 24
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
231
1/48двое суток
264
1/72трое суток
285

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 6 авг.5021212из Mar_Yisihak

    1. ሱባኤ ምን ማለት ነው? «ሱባኤ» የሚለው ቃል «ሰብአ» (ሰባት አደረገ) ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ሰባት ወይም የሰባት ቁጥር ስብስብ ማለት ነው። በኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ሕይወት ደግሞ ሱባኤ ማለት አንድ ክርስቲያን ከዕለት ተዕለት የዓለም ሥራ እና ረብሻ ተለይቶ በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት እና በብቸኝነት ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኝበት ልዩ የመንፈሳዊ ተጋድሎና የጸሎት ጊዜ ነው። 2. አንድ ሱባኤ ስንት ቀን ነው? አንድ ሱባኤ መሠረታዊ ቁጥሩ 7 ቀን ነው። ሆኖም እንደ ተጋዳላዩ መንፈሳዊ ጥንካሬ ፍላጎትና እንደ አስፈላጊነቱ በሰባት ቁጥር እየተባዛ ይያዛል፦ ☝️ አንድ ሱባኤ፦ 7 ቀን ✌️ ሱባኤ፦ 14 ቀን (ለምሳሌ፡ የፍልሰታ ጾም ሱባኤ) 🖖 ሦስት ሱባኤ፦ 21 ቀን 👉 ሰባት ሱባኤ፦ 49 ቀን (እንደ አርባ ጾም ያሉ ረጅም የሱባኤ ጊዜያት) 3. ሱባኤን ማን ጀመረው? የሱባኤ የመጀመሪያው ጀማሪ እግዚአብሔር አምላክራሱ ነው፤ ዓለምን በ6 ቀን ፈጥሮ በ7ኛው ቀን ከሥራው ሁሉ አርፏልና (ዘፍጥረት 2፡1-3)። በሰው ልጅ ታሪክ ደግሞ፦ 👉 አዳም እና ሔዋን፦ ከገነት ከተባረሩ በኋላ ይቅርታንና ምሕረትን ለማግኘት የመጀመሪያውን ሱባኤ ይዘዋል። 👉 አበው ነቢያት፦ አብርሃም፣ ሙሴ (በሲና ተራራ 40 ቀን የተቀመጠበት)፣ ኤልያስና ዳንኤል (3 ሱባኤ/21 ቀን የጾመው - ዳን. 10፡2-3) የሱባኤን ሕግ ፈጽመዋል። 👉 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፦ በገዳመ ቆረንቶስ 40 መዓልትና 40 ሌሊት በመጾምና በመጸለይ ለሱባኤ ፍጹም አርዓያ ሆኖናል (ማቴ. 4፡1-11)። 👉 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና ቅዱሳን ሐዋርያት፦ የሐዋርያት ሱባኤና የፍልሰታ ሱባኤን በመያዝ አርአያ ሆነውልናል። 4. ሱባኤ የምንገባበት ዓላማ ምንድን ነው? 👉 የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ፦ በሕይወታችን ውሳኔ በሚያስፈልጋቸው ነገሮች ላይ አምላካዊ መሪነትን ለመጠየቅ። 👉 ንሥሐ ለመግባትና ስርየተ ኃጢአትን ለማግኘት፦ ከኃጢአት ለመጠበቅና ከመንፈሳዊ ድክመት ለመፈወስ። 👉 ከእግዚአብሔር ጋር ለመቀራረብ፦ ከዓለም ረብሻ ርቆ መንፈሳዊ ሕይወትን ለማደስና እፎይታን ለማግኘት። 👉 በረከተ ሥጋን እና በረከተ ነፍስን ለመቀበል፦ በችግር፣ በበሽታ ወይም በፈተና ወቅት የእግዚአብሔርን እርዳታ ለመጠየቅ። 👉 ምስጋና ለማቅረብ፦ እግዚአብሔር ስላደረገልን ቸርነት ሁሉ በብቸኝነት የምስጋና መሥዋዕት ለማቅረብ። 5. በሱባኤያችን ወቅት ልናደርጋቸው የሚገቡ ነገሮች ምንድን ናቸው? 👉 ጸሎትና ስግደት አብዝቶ ማከናወን፦ የሰዓታት፣ የውዳሴ ማርያም፣ የመዝሙረ ዳዊትና የጸሎት መጻሕፍትን ማብዛት። 👉 ጾምና አንደበትን መግታት፦ ሆድን ከመብል ማቆጠብ ብቻ ሳይሆን ከከንቱ ጨዋታ፣ ከሐሜት፣ ከክርክርና ከቁጣ መቆጠብ። 👉 ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ፦ አእምሮን በቃለ እግዚአብሔር መገንባት። 👉 ንሥሐ መግባትና ቅዱስ ቁርባን መቀበል፦ ከነፍስ አባት ጋር በመካከር የቻለ ከሱባኤው አስቀድሞ ቀኖናን መጨረስ፤ ያልቻለ ሱባኤውን በንሥሐ መጀመርና መቁረብ። 👉 ምጽዋት መስጠት፦ ለችግረኞችና ለተራቡ ሰዎች መልካም ማድረግ። 👉 ከዓለማዊ መዝናኛዎችና ቴክኖሎጂ መራቅ፦ ስልክ፣ ማኅበራዊ ሚዲያ፣ ቴሌቪዥን እና አሳሳቢ የዓለም ነገሮችን ለጊዜው ሙሉ በሙሉ ማቆም ወይም መቀነስ። 👉 ፍቅር እና ይቅርታ ማድረግ፦ በልብ ውስጥ የተቀመጠ ቂምና በቀል ካለ ይቅር ብሎ በንጹሕ ልብ ወደ አምላክ መቅረብ። መልካም የፍልሰታ ጾም ይሁንልን! @Mar_Yisihak

  • 6 авг.1 297510

    ​​​​​​ ፍልሰታ ምን ማለት ነው? ✍️ "ፍልሰታ" ማለት ፈለሰ /ተሰደደ/ ከሚለው ግስ የወጣ ነው። 👉 ‹ፍልሰት› ማለት ደግሞ የተለያየ ትርጕም ቢሰጠውም ‹ፍልሰታ  ለማርያም› ተብሎ ሲገለጽ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሚያልፈው  ዓለም ወደ ማያልፈው ዓለም ከመቃብር የወጣችበት (የተነሣችበት) ቀን ማለት ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ ከሥጋዊው ዓለም ወደ መንፈሳዊው ዓለም የተሸጋገረችበት ማለት ነው፡፡ #ፍልሰት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መሔድን (መፍለስን) ያመለክታል፡፡ ✍️ ይህ ጾም እመቤታችን ካረፈች በኋላ የሥጋዋን መፍለስ አስመልክቶ ሐዋርያት የእመቤታችን ሥጋ የት እንደ ተቀበረ አላወቁም ነበርና እግዚአብሔር የእመቤታችንን ሥጋ እንዲገልጥላቸው የጾሙት ጾም ነው፡፡ 👉 ሐዋርያት ሁለት ሱባዔ ጾመው ኢየሱስ ክርስቶስ የእመቤታችንን ሥጋዋን ሰጥቷቸው  ትንሣኤዋንና ዕርገቷን በማየት በረከት ያገኙበት ጾም ነው፡፡ ✍️ ስለኾነም ምእመናን ፍልሰታ ለማርያምን ከልጅ እስከ አዋቂው በጾም በጸሎትና በመቍረብ በጋራ በፍቅር፣ በሰላም ያሳልፉታል፡፡ የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው? 👉 ኢትዮጵያ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የዐስራት ሀገር በመሆኗ እና ሕዝበ ክርስትያኑ ለእመቤታችን ልዩ ፍቅር ስላላቸው መሬት ላይ እየተኙ፣ ጥሬ እየበሉ በሰላም በፍቅር ይጾሙታል፡፡ ምእመናን ፍልሰታን ከሌሎች አጽዋማት በተለየ መልኩ መሬት ላይ እየተኙ ይጾሙታል፡፡ ይህ ደግሞ የእመቤታችን ፍቅር ስለሳባቸው ነው። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ! @Gamel_Media

  • ​​​​​​የጾም ዓይነቶች ጾም የግል (የንስሐ)፣ የዐዋጅ (የሕግ) እና የፈቃድ ጾም በመባል በሦስት ይከፈላል፡፡ የዐዋጅ (የሕግ) አጽዋማት ሰባት ናቸው፡፡ እነዚህም :- 1⃣ ዐቢይ ጾም 2⃣ ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም) 3⃣ ጾመ ነቢያት (የገና ጾም) 4⃣ ጾመ ገሃድ 5⃣ ጾመ ነነዌ 6⃣ ጾመ ድኅነት (ረቡዕ እና ዓርብ) እና 7⃣ ጾመ ፍልሰታ ናቸው፡፡ @Gamel_Media

  • አንገትህን ለሰይፍ እንደማትሰጥ ሁሉ፣ ጆሮህንም ለሐሜተኛው አታበድር። ሐሜተኛው ሰው በአንድ ጊዜ ሦስት ሰዎችን ይገድላል 👉 ራሱን በክፉ ምላሱ፣ 👉 የሰሚውን ሕሊና በመርዙ፣ 👉 የጉዳዩን ባለቤት ደግሞ በሐሰት። ሐሜት እንደ እሳት ነው፤ አንዴ ከቀጣጠለ የትኛውንም ሰላማዊ ማህበረሰብ አመድ አድርጎ ይቀየረዋል።" (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ) @Gamel_Media

  • #ሐምሌ_22 ይህች ዕለት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ቅዳሴ ቤቱ የሚከበርበት እና ለነቢዩ ቅዱስ ዕዝራ የእውቀትን ጽዋ ያጠጣበት ዕለት የሚታሰብበት ዓመታዊ ክብረ በዓል ነው። #ዑራኤል ማለት የብርሃን ጌታ የብርሃን አምላክ ማለት ነው። ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነው። #ቅዱስ_ዑራኤል መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሠላም እንዲሆን ያሰማራል። ምሥጢረ ሰማይንና ሰማያዊውን ዕውቀት ሁሉ ለሄኖክ የገለፀለት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው። #ቅዱስ_ዑራኤል የፀሐይን፣ የጨረቃን፣ የከዋክብትንና የሠማይ ሠራዊትን ብርሃንን የሚመራ ገናና መልአክ ነው ።  ሔኖ28፥13 #ቅዱስ_ዑራኤል መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ ሆኖ በተሰቀለ ጊዜ ክቡር ደሙን በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ በብርሃነ መነሳንስ በዓለም ላይ የረጨ ገናና መልአክ ነው። #ቅዱስ_ዑራኤል ለነቢዩ ዕዝራ ጽዋ ጥበብን አጠጥቶ ሰማያዊውን ምስጢር የገለፀለት መልአክ ነው። #ቅዱስ_ዑራኤል እውቀት ተሰውሮበት ለነበረው ኢትዮጵያዊው ሊቅ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በእመቤታችን በድንግል ማርያም ትዕዛዝ ጽዋ ጥበብን አጠጥቶ ሰማያዊውን ጥበብ የገለጠለት መልአክ ነው። #ቅዱስ_ዑራኤል ለሊቁ ለአባ ጊዮርጊስ ጽዋ ሕይወትን ካጠጣቸው በኋላ እጅግ ብዙ ድርሰቶችን የደረሱት በመልአኩ በቅዱስ ዑራኤል ተራዳኢነት ነው። #በቅዱስ_ዑራኤል መሪነት በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ የተመሠረቱ አብዛኞቹ ቅዱሳት ገዳማት አሉ ለዚህም ምስክራችን ( ማጣቀሻችን ) የቅዱስ ዑራኤል ድርሳኑ ነው በድርሳኑ ላይ የማይጠቅሳቸው በሀገራችን የከበሩ ቅዱሳት ገዳማትና ቅዱሳን ነገስታት የሉምና ። #ቅዱስ_ዑራኤል ወላዲተ አምላክን ከነልጇ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ስትሰደድ መንገድ እየመራ ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ የመጣችው እና ወደ ግብፅ የሄደችው በቅዱስ ዑራኤል መሪነት ነው ። #ቅዱስ_ዑራኤል እመቤታችንን ከተወደደ ልጇ ጋር በደመና ጭኖ መላ ኢትዮጵያን ያስጎበኘ መልአክ ነው። በኋላም ቅድስት ሀገራችንን ለእመቤታችን የዐሥራት አገር ሆና ተሰታለች ። #ሐምሌ 21 እና 22 ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ነው። በጸሎቱ ለተማጸነ ከእግዚአብሔር አምላክ በረከትን፣ ምህረትን የሚያሰጥ አዛኝ ጠባቂ እና የዋህ መልአክ ነው። በተለይም ህጻናትን የሚጠብቅ የሚለምኑትን ሁሉ የሚሰማ፣ ኃጢአተኞች ካሉበት ቦታ እኔን ላከኝ እያለ አምላኩን የሚማጸን አዛኝ የዋህ መልአክ ነው። የሊቀ መላእክት የቅዱስ ዑራኤል ምልጃ ሀገራችንን እና ሕዝቦቿን ይጠብቅ ክፉውን ያርቅልን አሜን ።🙏 ሐምሌ 22 2018 ዓ.ም @Gamel_Media

  • ለሥልጣነ ክህነቱ የማይገ'ባ ካህን ብትመለከት በደፈናው ክህነትን አትንቀፍ፡፡ ደገኛ የኾነውን የክህነት ሥልጣን ይዞ ያልተገባ ሥራን ሲሠራ በማየቱ ምክንያት፥ ከዚህ ተነሥቶ ሥልጣነ ክህነትን የሚነቅፍ አንድ ሰውስ እንኳን አይኑር፡፡ የአስቆሮቱ ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ ይሁዳ እንዲህ በማድረጉ ግን ሐዋርያነት የሚነቀፍ አይደለም፤ የይሁዳ የገዛ ነጻ ፈቃድ ችግር ነው እንጂ፡፡ የሚተቸውም ክህነቱ አይደለም፤ ጠማማው ነጻ ፈቃዱ ነው እንጂ፡፡ ስለዚህ አንተም ክህነትን አትንቀፍ፤ ክህነቱን ላልተገባ ሥራ የሚያውለውን ካህኑን እንጂ፡፡ ሐኪም ሳይኾኑ ሐኪም ነን ያሉት ስንት ናቸው? በዚሁ ምክንያት በመድኃኒት ፈንታ መርዝ የሰጡትስ ስንት ናቸው? እየነቀፍኩ ያለሁት ሙያውን አይደለም፤ ሙያውን በአግባቡ የማይተገብሩትን ነው እንጂ፡፡ መርከቦች እንዲሰምጡ ያደረጉ መርከበኞችስ ስንት ናቸው? ነገር ግን ችግሩ የባሕር ላይ ጉዞ አይደለም፤ ሙያውን እንደሚገባ የማይተገብሩት ሰዎች ላይ ነው እንጂ፡፡ ስለዚህ አንተም አንድ ክፉ ክርስቲያን ብትመለከት በደፈናው የክርስትና ትምህርትን ወይም ሥልጣነ ክህነትን አትንቀፍ፤ ደገኛውን ሥልጣን ላልተገባ ሥራ የሚያውለውን ሰው ንቀፍ እንጂ፡፡ ©ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ @Gamel_Media

  • ❖ሐምሌ 19 ዕለት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል "አምላካቸውን ክርስቶስን አንክድም" በማለታቸው የፈላ ውኃ ያለበት ጋን ውስጥ የተወረወሩት ቅዱስ ቂርቆስና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣ ተራድቶ ያዳነበት በዓል ነው። ይኸውም የቅድስት ኢየሉጣን ልጅ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስን ከሐዲው መኰንን ይዞ “ስምኽ ማነው?” ብሎ በጠየቀው ጊዜ “ከንጹሕ ዐዘቅትና ከማይለወጥ ከማይጠፋ ውኃ የተገኘ ስሜ ክርስቲያን ነው! ሞክሼ ስም ከፈለግኽ ደግሞ እናቴ የሠየመችኝ ቂርቆስ ነው።" በማለት ክርስትናው መመኪያው የኾነለት ይኽ ቅዱስ ሕፃን መለሰለት፡፡ መኰንኑም ለአማልክት ከሠዋህ ስታድግ እሾምኻለኊ ክርስቶስን ካድ ቢለው ቅዱስ ቂርቆስ ግን “የሰይጣን መልእክተኛ ለእውነትም ጠላቷ የኾንኽ ከእኔ ራቅ” አለው፡፡ መኰንኑም ይህንን ሰምቶ በመቈጣት የቅዱስ ቂርቆስ ደሙ እንደ ውኃ እስኪፈስስ ድረስ እንዲጨምቁት እና ጨውና ሰናፍጭ በኹለቱ የአፍንጮቹ ቀዳዳዎች እንዲጨመሩ ቢያደርግበት፤ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የጠነከረው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን “ትእዛዝኽ ለጒረሮዬ ጣፋጭ ኾነ ከማርና ከሥኳርም ለአፌ ጣመኝ” እያለ አምላኩ ክርስቶስን አመሰገነ፡፡ ❖ መኰንኑ በዚኽ ሳያበቃ እናትና ልጇ በክፉ አሟሟት እንዲሞቱ በማሰብ የረዘሙና የተሳሉ በእሳትም እንደ ፍም የጋሉ ዐሥራ አራት የብረት ችንካሮች እንዲመጡ አስደርጎ ሰባቱ በእናቱ አካላት፤ ሰባቱ በሕፃኑ ሰውነት ላይ እንዲሰካ ቢያስደርግም በጌታችን ትእዛዝ ግለቱ ጠፍቶ እንደ በረዶ በመቀዝቀዝ ምንም ምን ጒዳት ሳያደርስባቸው ቀረ፡፡ ❖ ከዚያም ወደ ወኅኒ ቤት እንዲገቡና እንዲዘጋባቸው አደረገ፤ ከዚያም ሕፃኑና እናቱ የሚሠቃዩበት ታላቅ መንኰራኲር ለ፵ ቀናት ተሠርቶ ካለቀ በኋላ ኹለቱንም በደረቁ ራሳቸውን ላጭተው የእሳት ፍሕምን በላያቸው ላይ ቢያደርጉም የእግዚአብሔር መልአክ ሥቃዮቹን ኹሉ ከእነርሱ አራቀላቸው፡፡ ❖ የሕፃኑ ምላስ እንዲቈረጥ አዝዞ ቢያስቈርጠውም ጌታችን ምላሱን መልሶለታል፡፡ ከዚህ በኋላ በታላቅ ጋን ውኃ አፍልተው ሕፃኑንና እናቱን እንዲጨምሯቸው ሲያዝዝ ከሚፍለቀለቀው ውኃ ድምፅ የተነሣ ለጊዜው እናቱ ፍርሀት ሥጋዊ ቢያገኛትም ልጇም ወደ ጌታችን በጸለየላት ጊዜ ፍርሃቱ ርቆላት ከልጇ ጋር ስትገባ መልአከ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ውኃውን አቀዝቅዞ ሐምሌ ፲፱ አውጥቷቸዋል፡፡ ❖ በመጨረሻም የሰማዕትነትን አክሊል የሚያገኝባት ጊዜ ሲደርስ ጌታችን ተገልጾለት ስሙን ለሚጠራ ኹሉ ቃል ኪዳንን ከሰጠው በኋላ ሥጋኽን በኤልያስ ሠረገላ ላይ አኖርልኻለኊ አለው፤ ይኽንን በሰማ ጊዜ በእጅጉ ተደሰተ፤ ከዚኽም በኋላ ጥር ፲፭ በሌሊቱ እኲሌታ ከእናቱ ጋር አንገቱ ተቈረጠ የሰማዕትነትን ክብር ተቀዳጅተዋል። ❖ ጥር ፲፮ ደግሞ የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበር የኾኑ 15,503 ሰዎች በሰማዕትነት ዐልፈዋል፡፡ ✔ እግዚአብሔር ረድኤቱን ለታናሽነትኽ ጠባቂን አስቀመጠ፤ ብልኅ የሚያደርግ ምስክርነቱንም፤ ምግባርኽ ያማረ በጎነትኽ ከከርቤ ይልቅ የሚሸት ቂርቆስ፤ በመከራ የተቸገረ በግርፊያ የቈሰለ ለኾነ ሰውነትኽ ሰላም እላለሁ። ❖ በልደተ ሥጋ ታናሽ በመንፈስ ጐልማሳ፤ እንደ ዕጣን ንጹሕ እንደ ወይንም አስደሳች ለኾነ ለቂርቆስ ሰላምታ ይገባል። የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት የቅዱስ ቂርቆስ፣ የእናቱ የቅድስት ኢየሉጣ፤ ስለአምላካቸው ስለ ክርስቶስ ፍቅር አንገታቸው በሰይፍ የተቆረጡት የሰማዕታት በረከት ይደርብን፨ ©መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ @Gamel_Media

  • 15 июл.1 47796

    #እባክህን_ከእሳቱ_ላይ_አትውረድ?!    አንድ ወንድም አባ ጴሜንን "ምከረኝ?" ብሎ ጠየቀው። አባ ጴሜንም "ድስት በእሳት ላይ እያለ ምንም አይነት ተባይ ሊቀርበውና ሊያበላሸው አይችልም፤ ከእሳት ወጥቶ ሲቀዘቅዝ ግን ነፍሳት ሁሉ ለመግባትና ለማበላሸት ይቻላቸዋል። ክርስቲያንም ከመንፈሳዊ ተግባር ካልራቀ ጠላት የሚጥልበት ምክንያት አያገኝበትም" አለው። ወዳጄ ሆይ ሕይወት ቀዝቅዛብሃለችን? ከእሳቱ ወደ መሬት ወርደህ በርደሃልን? የሕያውነትህ ሙቀት እሳት በማጣት ተንዘፍዝፏልን? ድስት የተባለ ሰውነትህ ክረምት የሚያህል ጉድን ተሸክሟልን? ዙሪያ ገባህ ፀሐይ እንደማትወጣበት ምዕራብ ጨለማን የሚጠራ ሆኗልን? ማንነትህ እሳት እንዳጣ ምግብ ጥቃቅን ነፍሳት በተባሉ ኃጢአቶች (ቁጣ፣ ቸልተኛነት፣ ስስት፣ አልታዘዝ ባይነት፣ ጭንቀት፣ ሁሉን የመናቅ ስሜት፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ...) ተወርሮ፣ መዓዛ ቅድስና ተለይቶት እጅ እጅ ብሏልን? ሞቅ የሚያደርገው አጥቶ በዓለማዊነት ሻግቷልን? የተባዮች መጫወቻ፣ የተውሳኮች መቀለጃ ሆኗልን? ✍️ እንግዲያውስ በቶሎ ወደ እሳቱ ውጣ! ወዳጄ ሆይ ሃይማኖት በተባለችና ከሰማይ በወረደች ልዩ እሳት (ሉቃ.12፥49) ላይ ተቀምጠህ የድስትነትህን ሙቀት መልስ፡፡ እምነት፣ ተስፋና ፍቅር (1ቆሮ.13፥13) በተባሉ ሦስት ጉልቻዎች ላይ በምቾት ተጥደህ የሕይወትህን የኃጢአት ብርድ አስወግድ፡፡ ንስሐ በተባለች ነበልባል ውበትነት የክረምትህን ጽልመት በምሥራቃዊ በጋነት ድል ንሳው፡፡ በሥጋ ወደሙ ፍምነት ድስት የተባለ ሰውነትህን በከዊነ እሳትነት ቀድስ፡፡ እባክህን በቶሎ ወደ እሳቱ ውጣ! ✍️ ሃይማኖት የተባለ እሳትን ተባይ አይቀርበውም፡፡ ✍️ እምነት፣ ተስፋ እና ፍቅር የተሰኙ ጉልቻዎችን ተውሳኮች ሽቅብ አይወጡአቸውም፡፡ ✍️ የንስሐን ነበልባል ነፍሳተ ጽልመት (የጨለማው ነፍሳት) መቋቋም አይችሉም! ✍️ ስለዚህ በእሳቱ ላይ እስካለህ ድረስ (በመንፈሳዊ ተግባራት፣ እስከጠነከርክ ድረስ) አንተ ሁሌም ከተባይና ከነፍሳት ብልሽት (ከአጋንንት) የራቅክ ነህ፡፡ 👉 ወዳጄ እባክህን ከእሳቱ ላይ አትውረድ! እሳቱ በደንብ ይነድ ዘንድ ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት የተባሉ እንጨቶችንና ምጽዋት የተባለ ጋዝን መጨመርህን እንዳትዘነጋ፡፡ እንዲህ ከሆነ ዘንዳ ድስትነትህ ሁሌም የሞቀ ይሆናል፡፡ እጅ እጅ ከማለት፣ ከመሻገትና የተባይ መጫወቻ ከመሆን ትድናለህ፡፡ ወዳጄ ሆይ እባክህን ከእሳቱ ላይ አይትውረድ! በኃጢአት "እጅ እጅ '' ከማለትና በበደል ከመሻገት እግዚአብሔር ይሠውረን! አሜን! ©ሕሊና በለጠ ዘኆኅተብርሃን @Gamel_Media

  • #ሐምሌ_7 #ቅድስት_ሥላሴ ሐምሌ ሰባት በዚች ቀን ሥሉስ ቅዱስ በአብርሃም ቤት የተገለጡበት ነው፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሦስትነት በባሕርይ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ተገኙ፣ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና፡፡ ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እንላቸዋለን፡፡ የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም፡፡ የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል፣ በቤቱም መጥተው ያድራሉ፡፡ ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም፡፡ አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል፡፡ አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኳናቸው አስተናገዱ፡፡ አብርሃም እግራቸውን አጠበ፡፡ በጀርባውም አዘላቸው፡፡ ምሳቸውንም አቀረበላቸው፡፡ እነርሱም እንደሚበሉ ሆኑለት፡፡ በዚያው ዕለትም የይስሃቅን መወለድ አበሠሩት፡፡ አብርሃም ከደግነቱና እንግዳ ከመውደዱ የተነሣ በተመሳቀለ ጎዳና ላይ ድንኳን ሠርቶ የወጣ የመረደውን፣ የመጣ የሄደውን ሁሉ እየተቀበለ እግዚአብሔርን እያገለገለ የሚኖር ጻድቅ ነበር፡፡ ለዚህም ነው አብርሃም በወይራ ግራር (በመምሬ) ዛፍ ሥር ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር አንድነቱን ሦስትነቱን የገለጠለት፡፡ ዘፍ 18፡1-25፣ ሮሜ 4፡-3፡፡ ቀትር ሰዓት ላይ በድንኳኑ ደጅ ተቀምጦ እንግዳ ሲጠብቅ እግዚአብሔር ታየው ተነጋገረው፡፡ አንገቱን ቀና አድርጎ ዐይኑን አራምዶ በተመለከተ ጊዜ እነሆ ሦስት ሰዎች ከበላዩ ባለ ተራራ ላይ ቆመው አያቸው፣ ወደ እርሱም ሲወርዱ አይቶ ፈጥኖ ሄዶ ከሰግደላቸው በኋላ ‹‹አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፤ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ…›› እያለ በትሕትና በመጋበዝ ወደ ድንኳኑ አስገብቶ በሚገባ ጋበዛቸው፡፡ ‹‹በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ›› ብሎ አንድነታቸውን፣ ‹‹ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ›› ብሎ የሦስትነታቸውን ምስጢር ገልጾአል፡፡ ያች ሥላሴ የገቡባት የአብርሃም ድንኳን የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡፡ ሥላሴ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደገቡ ሁሉ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም አብ ለአጽንዖ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፣ ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋዋን ለመዋሐድ የማደራቸው ምሳሌ በመሆኑ አማናዊቷ የሥላሴ ማደሪያ የአብርሃም ድንኳን እመቤታችን ናት፡፡ ሉቃ 1፡35፡፡ እግዚአብሔርም አብርሃምን የዛሬ ዓመት ልጅ እንደሚወልድ ነግሮት በዓመቱ ይስሐቅን ወልዷል፡፡ ሥሉስ ቅዱስን በምግባር በሃይማኖት ጸንተን እናገለግል ዘንድ የቅዱሳኑ ጸሎት ይርዳን! እንኳን አደረሳችሁ! https://t.me/Gamel_Media

  • 8 июл.899122

    ቅዳሴ የሚቀደሰው ለምዕመናን ነው ! በዕለተ ሰንበት ብዙ ቦታዎች ለመጠየቅ ሞክሬያለሁ በተለይ በዕለተ ሰንበት በከተማ አድባራት ቅዳሴ የሚገባው በአማካኝ ከ10:45 እስከ 11:30 ድረስ እየሆነ ነው በቅዳሴውም ላይ የዕለቱ ምንባባት በትክክል አይነበቡም ገና ሳይጀመሩ በዜማ ይለብሳሉ በጥቅሉ ሩጫ ሆኗል ሽምጥ ግልቢያ ! በዚህም ምክንያት ቆራቢዎች ለማስቀደስ ለመምጣት ገና ውድቅት ስለሚሆን ለሌባ እየተጋለጡ ነው ፤ ልጅ ማቁረብ የሚፈልጉ ልጆችን ይዘው በዚያ ሌሊት አዘጋጅቶ መምጣት አልቻሉም ፤ አረጋውያን በጨለማ ለመምጣት አቅም አይፈቅድም ዓይን ያዝ ያደርጋል። በእነዚህ ምክንያቶች ሳያስቀድሱ የሚቆርቡ ምእመናን እና ልጆቻቸውን የሚያቆርቡ ምእመናን በዝተዋል። እንደዚህ ቅዳሴው ለምንድን ነው ፈጥኖ የሚገባው ብለን ብንጠይቅ መልሱ እነሆ የሚሆነው፦ ¤ ቅዳሴው ቶሎ አልቆ ምእመናንን ገንዘብ ስጡን ብሎ በሚያሰለች ሁኔታ ለመለመን እና በበቂ ሁኔታ አንዳንዴ ከ2:00 በላይ የምዕመናንን ልባቸውን እና ኪሳቸውን ለማውለቅ ነው። ¤ ብዙ ጊዜ የደብር አለቆች ቶሎ ቶሎ በሉ ምእመናን ይቸኩላሉ ብለው ሲናገሩ ይደመጣል ግን ነገሩን ለማጣራት ስንሞክር የሚቸኩሉት ምዕመናኑ ሳይሆኑ ራሳቸው አለቆቹ ናቸው። ¤ ለወንጌል ነው የሚሉ ደግሞ አሉ በዕለተ ሰንበት ከበዛ 30 ደቂቃ ነው ስለዚህ በወንጌል አታሳቡ ደግሞ መጥታችሁ 1 ሰዓት የምታደክሙን ዕረፉ ። ልዩ ማሳሳቢያ፦ 1.ቅዳሴው 12:00 አሐዱ ቢባል እስከ 2:30 በበቂ ሁኔታ ሳይፈጠን በጣምም ዝግ ሳይባል ያልቃል ትምህርቱ 30 ደቂቃ ቢሰጥ 3:00 ሰዓት ሁሉም አገልግሎቶች በተሳካ ሁኔታ ያበቃል። 2.ቢቸግር ነው እንጂ ከቅዳሴው በኋላ በመካከሉ ለረጅም ሰዓት ትምህርት አይሰጥም ትምህርቱ ወንጌሉ ከተነበበ በኋላ ካህኑ በልዑል ቃል በዕለቱ የተነበበውን ወንጌል ለምእመናን ማስረዳት አለበት ነገር ግን ይሄ እንዳይከናወን ምዕመናን አያስቀድሱም በዚህ ምክንያት ይሄን ለማድረግ አልተቻለም አሁንም ቢሆን ወደዚህ ሥርዐት ለመመለስ ምዕመናንን ሁሉ አስቀዳሽ እና ቆራቢ ከሆኑ ትምህርቱን በሰዓቱ ማስተማር ይቻላል። ©መ/ር ነቢይ ኤልያስ @Gamel_Media

  • 📚ሰኔ 30 ✨✨✨የነቢይ፣ ሰማዕትና ሐዋርያ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ልደት✨✨✨ ፦ ይህም በእናቱ ማኅፀን ውስጥ ሳለ ለእግዚአብሔር ልጅ የሰገደው ነው። ይህም በመድኅን ዓለም ክርስቶስ ራስ ላይ እጁን ጭኖ በውኃ ያጠምቀው ዘንድ የተገባው ነው። https://t.me/Gamel_Media በቅዱስ ወንጌል እንደ ተነገረ ወንድ ልጅን ትወልድ ዘንድ የኤልሳቤጥ የፅንሷ ወራት በተፈጸመ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች። ዘመዶቿና ጎረቤቶቿ እግዚአብሔር ቸርነቱን እንዳበዛላት በሰሙ ጊዜ ስለርስዋ ደስ አላቸው። በስምንተኛውም ቀን ሊገዝሩት መጡ በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ጠሩት። እናቱ ግን "አይሆንም ዮሐንስ ይባል" አለች። "ከዘመዶችሽ ስሙ እንዲህ የሚባል የለም" አሏት። https://t.me/Gamel_Media አባቱንም ጠቅሰው "ማን ሊባል ትወዳለህ" አሉት። እርሱም ብራና ለምኖ ስሙ "ዮሐንስ ይባል" ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ። ያን ጊዜም አንደበቱ ከድዳነት ተፈትቶለት ተናገረ እግዚአብሔርንም ፈጽሞ አመሰገነው። ስለ ልጁና ስለ መድኃኒታችን መምጣት ልጁ ዮሐንስም የልዑል ነቢይ እንደሚባልና በእግዚአብሔርም ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተናገረ። https://t.me/Gamel_Media ሰብአ ሰገልም መጥተው ከሔዱ በኋላ ሄሮድስ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ስለ ሕፃኑ ዮሐንስ ለሄሮድስ ነገሩት እንዲገድሉትም ጭፍሮችን ላከ ጭፍሮችም ወደ አባቱ ዘካርያስ መጡ ሕፃኑንም ባጡት ጊዜ ጭፍሮቹ አባቱ ዘካርያስን ገደሉት። ሕፃኑ ግን አድጎ ለእስራኤል እስከተገለጠበት ጊዜ ድረስ በበረሀ ውስጥ ኖረ። https://t.me/Gamel_Media "የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ ጥርጊያውንም አስተካክሉ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ የዐዋጅ ነጋሪ ድምጽ እነሆ" ብሎ ኢያሳያስ የተናገረለት ይህ ነው። ሚልክያስም ስለእርሱ እንዲህ አለ "በፊትህ ጎዳናዬን አስተካክሎ የሚጠርግ መልአክተኛዬን እኔ እሰዳለሁ"። https://t.me/Gamel_Media ራሱ መድኃኒታችንም ስለእርሱ ሲናገር "ሴቶች ከወለዷቸው መጥምቁ ዮሐንስን የሚበልጠው የለም" ብሏል። ይህ የእግዚአብሔር ልጅ በአጠመቀውና የማትዳሠሥ ራሱን በዳሠሠው ጊዜ "የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት" የሚል የአብን ቃል ሰምቷልና። https://t.me/Gamel_Media ዳግመኛም ክብር ይግባውና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ራስ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ሲቀመጥ አየ። እኛንም መድኃኒታችን እንዲምረንና ይቅር እንዲለን በአማላጅነቱ እያመን መታሰቢያውን እናድርግ የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ በረከቱም እኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። https://t.me/Gamel_Media

  • 5 июл.2 7751029

    🌴መልመድ ያሉብን 7 ወሳኝ ተግባሮች..🖊☕️👇 1. "አይ" ማለትን መልመድ፡ ✅ ሁሉንም ሰው ለማስደሰት መሞከር ራስን ማጣት ነው። ✍️ ልምምዱ፦ 🌴 ከመንፈሳዊ ሕይወታችን፣ ከዓላማችንና ከጤናችን ጋር የማይሄዱ ነገሮች ሲመጡ በጨዋነትና በቆራጥነት "አይ" ማለትን መልመድ። ይህ ለራሳችን የምንሰጠው ክብር ነው። 2. ምስጋናን መልመድ (Gratitude)🌱 ✅ ሁልጊዜ የሌለንን ነገር ከማሰብ ይልቅ ያለንን ማየት መልመድ አለብን። ✍️ ልምምዱ፦  🌴 በየቀኑ ጠዋት ስንነሳ ወይም ማታ ስንተኛ ቢያንስ ሦስት እግዚአብሔር ያደረገልንን መልካም ነገሮች ለይቶ ማመስገን። ምስጋና በራሱ ለበረከት በር ይከፍታል። 3. ዝምታን መልመድ (The Power of Silence)🌱 ✅ ከመናገራችን በፊት ማሰብንና በዝምታ ውስጥ ራስን ማዳመጥን መልመድ ትልቅ ጥበብ ነው። ✍️ ልምምዱ፦  🌴 በጩኸትና በወሬ ውስጥ ከመሳተፍ ይልቅ፣ በቀን ውስጥ ቢያንስ ለ15 ደቂቃ በዝምታ ሆነን ከራሳችንና ከፈጣሪያችን ጋር ማውራት። "ዝምታ ወርቅ ነው" እንደሚባለው፣ ብዙ ስህተቶች የሚቀነሱት በዝምታ ነው። 4. ይቅርታን መልመድ: ✅ ቂም መያዝ ሌላው ሰው ላይ የምንወረውረው ድንጋይ ሳይሆን እኛኑ የሚያቃጥል እሳት ነው። ✍️ ልምምዱ፦ 🌴 ሰዎች ሲበድሉን ወዲያውኑ መልቀቅን (Letting go) መልመድ። ይቅርታ የምናደርገው ለሌላው ሰው ብቻ ሳይሆን ለራሳችን ሰላም ስንል እንደሆነ ማመን አለብን። 5. ንባብንና ትምህርትን መልመድ: ✅ አእምሮ ካልተመገበ ይደርቃል። ✍️ ልምምዱ፦ 🌴 በቀን ጥቂት ገጾችን እንኳ ቢሆን መንፈሳዊ ወይም ዕውቀት የሚጨምሩ መጻሕፍትን ማንበብ። አዳዲስ ነገሮችን ለመማር ራስን ሁልጊዜ ዝግጁ ማድረግ። 6. በሰዎች ስኬት መደሰትን መልመድ: ✅ ምቀኝነት የነፍስ ደዌ ነው። ✍️ልምምዱ፦  🌴 ጓደኞቻችን ወይም ዘመዶቻችን መልካም ነገር ሲገጥማቸው ከልብ ደስ መሰኘትን መልመድ። የሌላው ስኬት የእኛን ዕድል እንደማይቀንስብን ማወቅ አለብን። 7. ራስን መመርመርን መልመድ: ✅ የሌላውን ሰው ስህተት ከመቁጠር ይልቅ የራሳችንን ድካም ማየት። ✍️ ልምምዱ፦ 🌴 "ዛሬ ምን አጠፋሁ? ምንስ መልካም ነገር አደረግኩ?" ብሎ በየቀኑ መጨረሻ ራስን መጠየቅ። ይህ ለንስሐና ለዕድገት ትልቅ መንገድ ነው። 🌾 @Gamel_Media

  • ደምጸ እገሪሁ ለዝናም የዝናም ኮቴው ተሰማ ከሰኔ 26 - መስከረም 25 ዘመነ ክረምት ይባላል። እግዚአብሔር እነዚህን 3 ወራት የልምላሜ እና የመልካም ፍሬ  ወራት ያድርግልን! @Gamel_Media

  • 1 июл.8682из Mitin_kimem

    አንድ አባት እንዲህ ብለው መከሩ ''ልጄ፦ የአንተን የእንጀራ በር እከፍታለሁ ብለህ የሰው የእንጀራ በር አትዝጋ። የሰውን የእንጀራ በር በመዝጋት የአንተን እንጀራ አታገኘውም። እንዲያውም ይህን ባደረክ ጊዜ የእንጀራ በርህን አጥብቀህ ትዘጋዋለህ። ስለዚህ ልጄ የሰው ምቀኛ አትሁን።'' @Mitin_Kimem

  • 👉 መዳን በሌላ  በማንም የለም። 👈 ክፍል 2 ታዲያ አብረውት ለሶስት አመት ከሶስት ወር የተመላለሱት ቅዱሳን ሃዋርያት ጥላቸውና የልብሳቸው ዘርፍ ካዳነ በማህፀኗ ያደረባት ፡ ከስጋዋ ስጋን ከነፍሷ ነፍስን የነሳባት ፡ በክንዶቿ እቅፍ ያረፈባት ፡ ጡቶቿን ጠብቶ ያደገባት ፡ በጀርባዋ ታዝሎ በበረሃ የተሰደደባት ፡ እናቱ ፡ እናቱ ፡ እናቱ ድንግል ማርያምማ እንደምን ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ አታድን??? !!! ከእግዚአብሔር ከተሰጡት ጸጋዎች ከእመቤታችን የሚጎድልባት የትኛው ነው፡፡ የራማው ልዑል ቅዱስ ገብርኤል ይመሰክራ ፡ ሀሰት በአንደበቱ ያልተገኘበት በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው መልአኩ ገብርኤል ይመሰክራ፦ ዓለም ከጽድቅ በተራቆተበት ዘመን፡ ከጸጋው ተገፎ ራቁቱን በሆነ ሰዓት እመቤታችንን መልአኩ ገብርኤል ምን አላት?!፦ "ፀጋ የሞላብሽ" ፡፡ ስንት ፀጋ? ከፍጥረታት ወገን የእመቤታችንን ፀጋ የሚቆጥር ካለ እርሱ ይነሳ። አሁን መቁጠር ይጀምር እና በዚህ ግሩፕ ያሳውቀን። ከየት ጀምሮ የት? መቼ ጀምሮ መቼ ሊጨርስ!? ኦ እመቤታችን ሆይ በእኛ በክርስቲያኖች ዘንድ የመወደድ ፡ የመፈቀር ፤ በአጋንንትና በክፉው ሰራዊቶች ዘንድ የመፈራት ግርማ ያለሽ እናታችን ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡  ሰይጣን ከፍጥረታት ወገን ሁሉ አንቺን እጅግ ይጠላል ብሎ አባታችን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንደነገረን የባላጋራችን ልጆች እንዳሻቸው ቢናገሩ ምንም አንገረምም፡፡ የተመደቡበት ስራቸው ነውና፡፡ የጠላታችን ተንኮልን አስገራሚ የሚያደርገው ነፍሳትን ለማሳሳት እና ከእውነተኛዋ መንገድ ለማስወጣት መለያ መፈክር አድርጎ የሚጠቀመው የድንግል ማርያምን ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም መሆኑ ነው፡፡ የክርስቶስን የባህርይ አምላክነት ፡ ፈራጅነትና ተማላጅነት ፡ ይቅር ባይነትን ለማስካድ በራሱ በክርስቶስ ስም ሲመጣ ከአዕምሯችን የሚመጣው ትምህርት ያኔ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም መጨረሻ ምልክቶች ያሳሰበን አባታዊ ትምህርቱና ማስጠንቀቂያው ናት፡፡ እንዳንጠፋበት ያለን እንዲህ ነበር፦ "ማንም አያስታችሁ፡፡ ብዙዎች ሀሰተኞች በስሜ ይመጣሉ።" ቅዱስ ጳውሎስ "መዳን በሌላ በማንም የለም ከሰማይ በታች እንድንበት ዘንድ የተሰጠን ስም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡" ብሎ ያስተማረን ትምህርት ከላይ ባየነው አገባብ በጥቂቱ የሚፈታ ነው፡፡ ጥያቄው ቀድሞ የቀረብ ከአይሁድ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስና ቅዱስ ጴጥሮስ ወደ መቅደስ ሲሄዱ ከመቅደስ በር ወድቆ ያገኙትን ምስኪን ሽባን ከፈወሱት በኃላ የተነሳ የአይሁድ የምቀኝነት ተቃውሞን ተከትሎ አይሁድ በማን ስምና በምን ሃይል ይህንን አደረጋችሁ? ብለው ለጠየቁት ጥያቄ አባቶቻችን ቅዱሳን የመለሱት ምላሽ ነበር፡፡ /ሐዋ 3፥1/በጣም የሚደንቀው ክፉ የተባሉት አይሁድ በአሁን ዘመን ካሉት መናፍቃን በዚህ ጥያቄ እንደሚሻሉ ማስተዋል እንችላለን፡፡ ምክንያቱም አይሁድ አባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያትን ልጁን አላዳናችሁትም ወደሚል ጉንጭ አልፋ ክርክር አልገቡም፡፡ ልጁን ሐዋርያት እንዳዳኑት በዓይን የሚታይ በመሆኑ ነው፡፡ የነሱ ጥያቄ የነበረው፦ አዎ ልጁን አድናችሁታል ፡ እኛም ተመልክተናል፡፡ ግን በማን ስም ፡ በምን ሃይል ይህንን አደረጋችሁት? ብለው ነው የጠየቋቸው/ሐዋ 4፥7/፡፡ በእኛ ዘንድ ከቅዱሳን የማዳን ስልጣን ጀርባ ከክርስቶስ ውጪ ፡ ከስላሴ ውጪ ሌላ የምንጠረጥረው አካል ከቶ የለምና አባቶቻችን ቅዱሳን ሃዋርያት እንዳሉት በቤተክርስቲያናችን ከሚደረገው ድኀነት ጀርባ ያለው ሃይል እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን፡ ፦ የባህርይ አምላክነቱን ፡ ፈራጅነቱን ፡ ተማላጅነቱን በማያምኑ ፡ እንዲሁ በስሙ ነፍሳትን በሚያስቱ መናፍቃን ፊት ሆነን እንዲህ እንላለን፡፡ "መዳን በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ ከሰማይ በታች የተሰጠን ስም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡" እንላለን፡፡ ¥ የኛ ልዩ ነውና፡ ¥ የኛ ወልድ ዋህድ ነውና ፡ ¥ የኛ የባህርይ አምላክ ነውና ፡ ¥ የኛ ፈራጅና ተማላጅ ነውና ፡ ¥ የኛ ይቅርባይ የነገስታት ንጉስ ነውና ፡ ¥ የኛ መሃሪ የጌቶች ጌታ ነውና፡፡ ¥ የኛ የሚመስለው የሚተካከለው የለምና፡፡ ¥ የኛ የቅዱሳን አምላክ ነውና፡፡ ¥ የኛ የድንግል ልጅ ነውና፡፡ ¥ የኛ በሦስትነቱ የሚሰለስ የሚቀደስ ነውና፡፡ ጠለቅ ያለውን ትምህርት በጥቂቱ ስናነሳ ደግሞ "መዳን በሌላ በማንም የለም" የሚለው ሲመሳጠር፦ ከዋናው የውርስ ሃጢአት ፡ ከዘላለማዊው ሞት ከዲያብሎስ የ5500 የባርነት አገዛዝ ፡ ከመንፀፈ ደይን ካለ እግዚአብሔር ሰው መሆን ፡ ካለ እግዚአብሔር ከሰማየ ሰማያት መውረድ ፡ ካለ እግዚአብሔር ወልድ ከእመቤታችን ከስጋዋ ስጋን ከነፍሷ ነፍስን ከመንሳት ሌላ ፡ ካለ ክርስቶስ መከራን መቀበል ፡ መከሰስ ፡ መገረፍ ፡ በመስቀል ላይ ለህማም እጆቹን መዘርጋት በቀር ፡ በስጋው ሞትን ከተቀበለ ከእግዚአብሔር በቀር ፡ ሙስና መቃብርን በስልጣኑ አጥፍቶ ፡ መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በትንሳኤው ህያው ካደረገን ከክርስቶስ በቀር መዳን በማንም የለም ብላ ከአዳም ውድቀት እስከ ተስፋው ቃል ኪዳን ፡ ሰማዮችን ቀደህ ውረድ የሚለውን የአባቶቻችንን የነቢያት ተማፅኖና የትንቢት ቃልን ፡ ከኦሪት ምሳሌና ህብረ አምሳል እስከ መድኃኒታችን መወለድ ድረስ ያለውን እናታችን ቤተክርስቲያን አምልታና አስፍታ ታስተምረናለች፡፡ አብ ፡ ወልድ ፡ መንፈስ ቅዱስ በባህሪና በስልጣናቸው ያድናሉ፡፡ ማዳን የእግዚአብሔር ነውና፡፡ ወላዲተ አምላክ ድንግል፡ ቅዱሳን ፃድቃን ሰማእታት ፡ ቅዱሳን መላእክት እንደየ ክብራቸውና ስልጣናቸው ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ ያድኑናል፡፡ መስቀሉ፡ ፀበሉ፡ እምነቱ፡ የቅድስት ቤተክርስቲያን ትቢያው አፈሩ ሁሉ ያድናል፡፡ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን፡፡    ❤️ወስብሃት ለእግዚአብሔር፡❤️        ❤️ወለወላዲቱ ድንግል፡❤️         ❤️ወለመስቀሉ ክቡር፡፡❤️ @Gamel_Media

  • ✝"መዳን በሌላ በማንም የለም"✝ ✞Share ያድርጉና ለሌሎችም ያካፍሉ✞ "መዳን በሌላ በማንም የለም" የሚለውን የቅዱስ መፅሀፍን ቃል ለምንፍቅናና ለጥርጥር ትምህርት በማዋል የእመቤታችንና የቅዱሳንን ማዳን በይፋና በስውር ለሚቃወሙ የተሀድሶ መናፍቃን የተሰጠች አጭር ምላሽ፡፡ እንዲህ በክፋትና በተንኮል አጥማጅና አሰናካይ ርኩሰታዊ ፈተና ሊጥለን ዛሬም የሚታገለን አስቀድሞ በገነት ዛፎች መካከል በእባብ ገላ ተሰውሮ ከአምላካችንና ከአባታችን የለየን ድያብሎስ ነው፡፡ እርሱን የምታገኙት በነዚህ በመናፍቃን ልቡና ተሰውሮ ነውና፡፡ ሰይጣን በተንኮሉ ሄዋንን እንዳሳታት በጣም የዋሃን የሆንነውን፡ መንፈሳዊ ጥበብንና መዳን የሚገኝበትን ትምህርት ከአባቶቻችን እግር ስር ተቀምጠን ያልተማርነውን ብዙዎቻችንን እንዳያቆሽሸን ፡ እምነታችንንና ለክርስቶስ ማደሪያ የሚሆን ልቡናችንን እንዳያረክስብን በብርቱ መጠንቀቅ ይገባል፡፡ እንግዲህ ወደ ባላጋራችን የማጥመጃ ሀሳብ እንመለስ ፡ ጠላት ወጥመድን እንደሚያጠምድ ፡ ቢቻለው ብዙዎችን ለመያዝና ከህይወት ለመለየት እንቅልፍ የሌለው መሆኑን ቅዱሳት መፃህፍት ያስረዳሉ፡፡ እኛ የምናምነውን መጠየቅ ያለብን እኛው ነን፡፡ እራሳቸው ለራሳቸው ስለኛ እምነት ተናጋሪዎች ፡ ወሳኞች ፡ ተቺዎችና ነቃፊዎች ሆነው በሚነሳው ግርግር እንደለመዱት ነብሳትን ለመዝረፍ የሚያደርጉት ክፋት ግን የበለጠ የሰይጣን አገልጋይ መሆናቸውን ይገልጥባቸዋል፡፡ እስቲ ጥቂት ሰይጣን ከላይ ያነሳውን የተንኮል ሀሳብን የሚያሳፍር አጭር ምላሽ እንናገር፡፡ ለዚህ ርካሽ ሀሳብ መቼም ሊቃውንት መጠራት አለባቸው አንልም፡፡ እንደ አንድ ምዕመን ይህቺን እንበል፡፡ በቅድስት ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሰረት እግዚአብሔር በባህርይው አዳኝ ነው፡፡ በባህርይው አዳኝ ነው ስንል፦ ማዳንን ከማንም ያልተዋሰው ያልተቀበለው ፡ በራሱ ለራሱ ያለው ፡ ለወደደው ፡ ለፈቀደው በስጦታ የሚሰጠው ማለታችን ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ማዳን ለኢየሱስ ክርስቶስ ማዳን ሌላ ምንጭ የለውም፡፡ ለማንም ማዳን ግን ምንጩ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ስለዚህም ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል ስንልና ቅዱሳን ያድናሉ ስንል ከዚህ ከአለት ከሚፀና እምነትን መሰረት አድርገን ነው፡፡ ይህንን አባቶቻችን በምሳሌ ሲያስረዱ እሳት በባህሪው ያቃጥላል እሳት የሚያቃጥለው ማቃጠልን ከሌላ ነገር ወስዶ አይደለም፡፡ መቼም የማያቃጥል እሳት የለም፡፡ እሳት ከሆነ እርሱ ያቃጥላል፡፡ ማቃጠል የግል ገንዘቡ ነው በራሱ ያቃጥላልና፡፡ ብረትና እንጨት ደግሞ በተፈጥሮ አያቃጥሉም፡፡ ነገር ግን እንዲያቃጥሉ ማድረግ ይቻላል፡፡ እንዴት? ብረቱን ወስደን : እንጨቱን ወስደን ከእሳት ውስጥ ብንጨምረው ፍም ሆኖ ይግልና ከዛ ያቃጥላል፡፡ መቼም እሳት ውስጥ ገብቶ የማያቃጥል ብረትም ሆነ እንጨት አለ የሚል እምነት ያለው ሰው አለ የሚል እምነት የለኝም፡፡ እሳት ውስጥ ገብቶ ብረቱ ወይም እንጨቱ ካላቃጠለ አለማቃጠሉ ችግሩ የብረቱ ወይም የእንጨቱ ችግር አይደለም፡፡ እሳቱ ራሱ አያቃጥልም ማለት ነው፡፡ አሁን ከመናፍቃን በቀር ስለምን እያወራን እንዳለ ሁሉም የክርስቶስ ቤተሰብ ይረዳል የሚል እምነት አለኝ፡፡ የድንግል ልጅ ወልድ ዋህድ ክርስቶስ በባህሪው አዳኝ ነው፡፡ ቅዱሳን ደግሞ ወዷቸው ፡ መርጧቸው ፡ ለይቷቸው ፡ ሾሟቸው በፀጋ ያድናሉ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር አንድነቱ የተጠበቀ የእግዚአብሔር ቅዱስ ፡ ፃድቅና ሰማዕት የማያድንበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ካላዳነ ግን አለማዳኑ የፃድቁ ወይም የቅዱሱ ሰው ሳይሆን እግዚአብሔር ራሱ ማዳን ትቷል ማለት ነው፡፡ ወይም ያ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር አንድነትና ህብረት የለውም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ቅዱሳን ፃድቃን ሰማዕታ ሁሉ ያድናሉ፡፡ ይሁዳ ግን አያድንም፡፡ ሐዋርያ ነበር ከግንዱ ከክርስቶስ ተቆርጦ ወደቀ፡፡ ሰይጣንም አያድንም ለራሱም አይድንም፡፡ መልአክ ነበር ከምንጩ ከክርስቶስ ተቆርጦ ወደቀ፡፡ ነገር ግን አለምን የካዱ ፡ የአለምን ነገር ስለ ክርስቶስ የሰቀሉ ፡ በተጋድሎ የፅድቅ ፍሬን ያፈሩ ቅዱሳን ፡ ፃድቃን ፡ ሰማዕታት ግን ያድናሉ፡፡ መፅሀፍ ቅዱስ ይናገር ካልን ደግሞ በድን የሆነ የፊደል ችርቻሮን ከሚነግዱትና ቅዱሱን ቃል በከንቱ ተሸክመውት ከሚዞሩ መናፍቃን በቀር ሁሉም ክርስቲያን እንደሚያስተውለው በሐዋርያት ገድል ላይ ተመስርቶ የተፃፈው የሐዋርያት ሥራ እንደሚያስተምረን በቅዱሳን እጅ ድንቅ ተዓምር እንደሚደረግ እናስተውላለን፡፡ አባታችን ቅዱስ ጴጥሮስ በጥላው ሙት እንዳስነሳ ፡ ለምፅ እንዳነፃ ፡ ድውይ እንደፈወሰ ፡ ሽባ እንደተረተረ ፡ አጋንንትን እንዳሳደደ ፡ አባታችን ቅዱስ ጳውሎስም በጥላው ብዙዎችን እንደፈወሰ ተመዝግቧል። /ሐዋ 5፥15, ሐዋ 19፥11/ የአባቶቻችን ቅድስናና ስልጣን ከነሱ አልፎ ለልብሳቸው ዘርፍና ለጥላቸው ፡ ለረገጡት አፈር ሁሉ መትረፉን ቅዱስ መፅሀፍ ያስተምረናል፡፡ እኛም የክርስቶስ ልጆች የድንግል ማርያም ወዳጆች በእውነት እናምናለን፡፡ ብዙ ድንቅ ነገርም ተደርጎልናል፡፡ በመጨረሻው ቀንም የክርስቶስ ቅዱሳንን የሚያሳድዱና በቅዱሳን ደም በሰከሩ በመናፍቃን ላይ ቃሉ ይፈርዳል፡፡ በንስሀ እስካልተመለሱ፡፡ አባቶቻችን ቅዱሳን በብርሃን ከተማ ከክርስቶስ ጋር ለመኖር ከሄዱ በኃላም የረገጡት አፈር ፡ የፀለዩበት በዓታቸው ፡ የሰገዱበት ስፍራ ፡ ያረፋበት መቃብራቸው እኛ የሥላሴ ልጆችን ያድናል፡፡ ለኛ የተደረገልንን ትተነው የሉተር ልጆች በከንቱ ተሸክመውት ከሚሄዱት በአዳራሽም ሽለላና ቀረርቶ ከሚያሰሙበት ከመፅሃፍ ቅዱስ ከመፅሃፈ ነገስት ላይ አባታችን ኤልሳ ከተቀበረበት መቃብር አፈር ላይ የወደቀ አንድ የሞተ ሰው አፈፍ ብሎ መነሳቱን እንዲያነቡት እንጋብዛቸዋለን። /2ነገ 13፥31/፡፡ ለማስተዋልና ለማመን የሚያስችላቸውን የእምነት ብኩርናን በምስር ወጥ አስወስደው ዛሬ የቀደመች እምነታቸውን ለመሳደብ ፡ ለመራገም ፡ በእርሷ ላይ ለመሳለቅ ተፈረደባቸው እንጂ፡፡ እግዚአብሔር ይምራቸው ዘንድ ቤተ ክርስቲያናችን ሁሌ ወደ እግዚአብሔር ትማልዳለች፡፡ ሌላም ካሻቸው ፀበል እንደሚያድን ሶርያዊው ንዕማን በፍርድ ቀን ይመሰክራል፡፡ መስቀሉ እንደሚያድንና የእሳት ባህርን እንደሚያሻግር ፡ አጋንንትንም ከጥልቁ እንደሚያወርድ ቅዱሳኑ ሁሉ በአለም ላይ ይመሰክሩበታል፡፡ ታዲያ አብረውት ለሶስት አመት ከሶስት ወር የተመላለሱት ቅዱሳን ሃዋርያት ጥላቸውና የልብሳቸው ዘርፍ ካዳነ በማህፀኗ ያደረባት ፡ ከስጋዋ ስጋን ከነብሷ ነብስን የነሳባት ፡ በክንዶቿ እቅፍ ያረፈባት ፡ ጡቶቿን ጠብቶ ያደገባት ፡ በጀርባዋ ታዝሎ በበረሃ የተሰደደባት ፡ እናቱ ፡ እናቱ ፡ እናቱ ድንግል ማርያምማ እንደምን ከመከራ ስጋ ከመከራ ነብስ አታድን??!! ከእግዚአብሔር ከተሰጡት ፀጋዎች ከእመቤታችን የሚጎድልባት የትኛው ነው፡፡ የራማው ልዑል ቅዱስ ገብርኤል ይመስክራ ፡ ሀሰት በአንደበቱ ያልተገኘበት በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው መልአኩ ገብርኤል ይመስክራ። ይቀጥላል። @Gamel_Media

  • https://t.me/Mitin_kimem/539