- Последний пост
- 11 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 508
- 1/48двое суток
- 582
- 1/72трое суток
- 627
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ወልድያ እና ደሴ አካባቢ ለሚሰራ ስራ ኪራይ ከ20_25 የሚሆን ሲኖትራክ ይፈለጋል።ያላችሁ ደውሉ። 0990909037
የመካው የሶስትዮሽ ታሪካዊ ስምምነት ''በአንዳችን ላይ የሚሰርስ ጥቃት የሁላችንም ጥቃት ነው'' ሳኡዲ አረቢያ፣ቱርክ እና ፓኪስታን መካ ውስጥ ባደረጉት የሶስቲዮሽ ስምምነት ላይ ያሰተላለፉት መልእክት ነው። ሳኡዲ ገንዘብ አላት።ፓኪስታን ኒኩሊየር ታጥቃለች።ቱርክ የኔቶ አባል ናት። ይህ ስምምነት እስራኤልን ያቁነጠንጣል። 57ቱን የእስላማዊ ትብብር አባል አገራት (OIC) ያጠናክራል።የሳኡዲን ተሰሚነት ዳግም ይመልሳል።የቱርክን ዲፕሎማሲያዊ ሚና ያልቃል። የፓኪስታንን ወታደራዊ ምጥቀት እጥቅም ላይ ያውላል። ውጤቱ በሒደት የሚገመገም ነው። ልብ ያለው ልብ ይበል!
ስፔን 100 ፍልስጤማውያንን ለህክምና ከጋዛ አስወጣች #Ethiopia | ስፔን በአካባቢው በነበረው አስቸጋሪ ሁኔታ ምክንያት በሀገራቸው አስፈላጊውን ህክምና ማግኘት ያልቻሉ 100 ፍልስጤማውያንን ከጋዛ በማስወጣት ሌላ ትልቅ የሰብአዊ ድጋፍ ተልእኮ ማካሄዷ ተገለጸ። ወደ ሀገሪቱ ከገቡት ታካሚዎች መካከል 20 ህጻናት የሚገኙበት ሲሆን፣ ሁሉም በሀገሪቱ በሚገኙ ልዩ የህክምና ማዕከላት አስፈላጊውን አስቸኳይ ህክምና የሚያገኙ ይሆናል። የስፔን ባለስልጣናት ይህንን መሰል የህክምና ትራንስፖርት ማመቻቸት እና የሰብአዊ ድጋፍ ማቅረብ ታላቅ ሰብአዊ ኃላፊነት መሆኑን ገልጸዋል። ይህ ድንበር ተሻጋሪ ጥረት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ተጎጂ ቤተሰቦችን ከተሻሉ የህክምና ተቋማት ጋር በማገናኘት የህይወት አድን አገልግሎት እንዲያገኙ ያስቻለ ሌላው የስፔን የበጎ አድራጎት እርምጃ ሆኖ ተመዝግቧል። በያፌት ገ/ህይወት
~ ትዕግስትን የተካነ ሰው ህይወት አትሰብረውም... የፍቅርን ዋጋ የሚያውቅ ሰው ደግሞ መስዋዕትነት ቀላል ይሆንለታል... ደስታን ከሌሎች ጋር የሚያካፍል ሰው የሰው ልጅ ዋጋ ይሰማዋል።
✨ የጋብቻ ናፍቆታችሁ የማይመጥናችሁን ሰው እንድትቀበሉ አይገፋፋችሁ! ✨ የተሳሳተ ምርጫ ከነፍሳችሁ፣ ከአእምሮ ሰላማችሁ፣ ከውበታችሁ፣ ከጤናችሁ፣ ከዕድሜያችሁ፣ ከሥነ-ልቦናችሁ እና ከወጣትነታችሁ ውድ ዋጋ ያስከፍላል። 💔 ስንት የተጣደፉ ሰዎች ውድ ዋጋ ከፍለዋል መሰላችሁ! 🤲 እስቲኻራህ ስገዱ፤ ጌታችሁን አማክሩ፤ ከዚያም (ሰዎችን) አማክሩ፤ ጠይቁ፣ ጠይቁ፣ ጠይቁ! እነዚህ በሸሪዓው የታዘዝንባቸው አስፈላጊ እርምጃዎችና ምክንያቶች ናቸው። 🌱 ልክ አስያ በፈርዖን፣ ሉጥም በባለቤቱ እንደተፈተኑት ሁሉ፤ አንዳንድ ጊዜ እስቲኻራህ ሰግደን፣ ሰዎችን አማክረንና ጠይቀን የተቻለውን ሁሉ ጥረት ካደረግን በኋላ እንኳ፣ በሥነ-ምግባር፣ በአስተዳደግ፣ በቤተሰብ፣ በፍቅርም ሆነ በቅንነት በፍጹም የማይመስለንን ሰው ልናገኝ እንችላለን። ይህም በትዳር ውስጥ የሚገጥም ትልቅ «ፈተና» ነው። 🛑 በዚህ ጊዜ በሙሉ እውነተኛነት ነገሮችን ለማስተካከል፣ ለማደስና ለማከም ጥረት፣ ጥረት፣ ጥረት አድርጉ። ትዕግሥት፣ ከዚያም ትዕግሥት፣ ከዚያም ትዕግሥት ያስፈልጋል—በተለይም በመካከላችሁ ልጅ ካለ። ⚖️ ሆኖም አብሮ መኖር ከተሳነ ፣ ምንም ዓይነት በጎ ለውጥ ካልመጣና አብሮ መቀጠሉ በሥነ-ልቦናችሁ ወይም በልጆቻችሁ ላይ ጉዳት የሚያስከትል ከሆነ፣ በክብር መለያየት ጥበብ የተሞላበት መፍትሔ ነው። 📖 «ቢለያዩ እንኳ አላህ እያንዳንዳቸውን ከስፋቱ ያበቃቸዋል፤ አላህ ሰፊ፣ ጥበበኛ ነውና።» ከዚያም ተስፉ አትቁረጡ ተሞክሮቹ ለዕድሜ ልክ የሚጠቅም ትምህርት ይሆናል። 💡 ወዳጆች ሆይ! ጋብቻ ውድድር ወይም የደስታ ብቸኛ መለኪያ አይደለም፤ በትክክለኛው ጊዜ ከትክክለኛው ሰው ጋር ይሳካል አትቸኩሉ ። አሁን ግን ዋናው ቅድሚያ ለአእምሮ ሰላማችሁና ለተረጋጋ ሕይወታችሁ ይሁን! 🌿🌸
🚢መዳኛ መርከባችንን የምንገነባው ከውሃ ሙላት በፊት ነው!። (የሱረቱ ሁድ አስተምሕሮዎች) የነብዩላህ ኑሕ(ዐ.ሰ) ታሪክ የሚያስተምረን በሕይወታችን ላይ የሆነ አደጋ ከመድረሱ በፊት ዝግጅት እንደሚያስፈልግ ነው። መርከብ ምድር ከጠፋች በኋላ እንደማይሰራው ሁሉ ኢማንም የጥፋት ማዕበል ሲመጣ አይገነባም። የድነት መርከብ የምትግገነባው በሰላም ቀናት ውስጥ ነው። -እንደቀላል ሰግድሀት በልብህ ውስጥ የኢማንን ጠብታ ባሳረፈች ሶላት ውስጥ የመዳን መርከብህን ገንብተሀል። -በራስህ ላይ የፈረድካት ወይም ለሕሊናህ ስትል ያወጣሀት የእውነት ቃል የነፍስህን ሚዛን እንዳትሸጥ ትምሕርት ሰጥታህ ባለፈች ጊዜ የመዳኛ መርከብህን ገንብተሀል። -ተቸግረህ ሳለህ የተውከው የሐራም ገንዘብ ከአላህ ዘንድ የሚቀረው የተሻለ መሆኑን እምነት ባሳደረብህ ጊዜ የመዳኛ መርከብህ ተገንብቷል። -የመበቀል አቅም እያለህ ይቅር ማለትህ የስልጣን፣ የገንዘብ፣ የጉልበት፣ የዕውቀትም ይሁን ሌላ ኃይል በውስጥህ ወደ «ዓድ»ነት እንዳይቀየር በገደበልህ ጊዜ የመድህን መርከብህን ገንብተሀል። -በተሳሳትክ ጊዜ የጠየቅከው ይቅርታ በውስጥህ ሊያቆጠቁጥ የፈለገውን ትንሽ «ፊርዓውን»ነት በሰበረበት ጊዜ የመዳኛ መርከብህ ተገንብቷል። -በኢስላም ጥላ ስር መኖር በራሱ የድነት መርከብ ነው!። መርከቡ የሚገነባው በኢስላማዊ ተግባርህ ነው። የአላህን(ሱ.ወ)ና ነብዩን(ሰ.ዐ.ወ) ትዕዛዝ መፈጸም ሁሉ ሳንቃ ነው። ሁሉም የኽይር ትግል(ሙጃሃዳህ) ሚስማር ነው። ሁሉም ውዳሴ (ዚክር) እንጨቱን ከውሃ ዝገት የሚጠብቅ ቀለም ነው። ወሳጅ ጎርፍ ያለው የውሃ ሙላት በጣ ጊዜ በድብቅ ስትሰራውና ስትገነባው የነበረው መርከብ ተሸክሞ ያድንሀል። ሙእሚን ትንንሽ ስራዎቹን አይንቅም። በሌሊት ጨለማ ውስጥ የተሰገዱ ሁለት ረከዓዎች በፈተና ቀን ልቡን የሚያጸኑት ሊሆኑ ይችላሉ። አሁን ውጤቷን ያላየሃት መልካም ጓደኝነትህ በማግኘትህ ወቅት ወደ ኩራት ተራራ ላይ ልትቀርብ ስትል ለአላህ ስትል ወደ መተናነስ ጠርታ ኢማንህን ትጠብቅልሀለች። ማንነታችን በመከራ ጊዜ አይገነባም። ከመከራ በፊት የገነባነውን ማንነት ግን በመከራ ጊዜ ይገለጣል። Hamudi Hamudi ይቀጥላል... #facebookviral #facebookreels #facebookpost #facebookreelsviral #FacebookPage #facebookvideo #islam #Quran
✔️በዚህ ክረምት ነፃ የቋንቋ እድል የምታገኙበት ቻሌጅ ልጠቁማችሁ 1️⃣ኛ ለወጣ ነፃ የቋንቋ ስልጠና እና ብር 1500 2️⃣ኛ ለወጣ ነፃ የቋንቋ ስልጠና እና ብር 1000 3️⃣ኛ ለወጣ ነፃ የቋንቋ ስልጠና እና ብር 500 🏪ቻሌንጁ ለመሳተፍ ሙሉ ማብራሪያ🔣 https://t.me/Ihsan_language/315 https://t.me/Ihsan_language/315
🌖🌗🌗🌘🌑 ﴿ فَلا يحُزنك قّولهُم ﴾ ~••{ ንግግራቸውም አያሳዝንህ፡፡} አትበሳጭ/አትዘን በንግግራቸው... የሰው ልጅ ባልዋልክበት ቢያውልህ ያልሆንከውን ቢልህ አትስብ አላህ (ሱ.ወ) ከአንተ ጋር እንደሆነ ፣ ሁኔታህን እንደሚያውቅና ስሜትህን እንደሚያይልህ እንደማይረሳህ ለልብህ የሚሆን የመጽናኛ ንግግሩን አስትውስ ።" https://t.me/Golden_Speech https://t.me/Golden_Speech
"‘እኔ ከአንተ ጋር ነኝ ላሉን ሁሉ ምስጋና ይድረሳቸውው..!! የምንሸከመውን የህይወት ሸክም ግማሽ ድካም የምታቃልለው ያች አፅናኝ ዓረፍተ ነገር..፣ ..በእውነትና ከልቡ ሳያስመስል ላለን ሁሉ ምስጋና ይድረሰሳቸው ንግግሮቻችን ወይም ስሜታችን ጥሩ ባልሆነበት ጊዜ እንኳ አብሮነታችን ውብ እንደሆነ ለሚያስቡ ሁሉ ምስጋና ይድረሳቸው.. መጥፎ ጎናችንን በጥሩ ፣ እንከኖቻችንንም በበጎ የሚያርመን አይቶ ስህተቶቻችንን ላለፈ ሁሉ ላስተማረን ፣ ግንኙነታችንን በቆረጥነው ቁጥር የፍቅር ድልድይ ዘርግቶ ላገናኘን ሁሉ ምስጋና ይድረሰው።" https://t.me/Golden_Speech https://t.me/Golden_Speech
የአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎችን ወደ ጦር ግንባር ! ሌሎች እምነት ተከታይ ተማሪዎችን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና እንድወስዱ ወደ መቀለ ዩኒቨርሲቲ ! ✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅ በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ዛሬ እና ነገ ወደ መቀለ ዩኒቨርሲቲ እየገቡ ይገኛሉ። በአፖርታይዷ ከተማ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች እንዳይማሩ ፈተና ወስደው ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ እንዳይሸጋገሩ ህይዎታቸውን አጨልመው ዛሬ ላይ ለግዳጅ ጦርነት ከፊት እያሰለፏቸው ይገኛሉ። 📌ለጦርነት ሲሆን ሂጃብ አውልቂ ሂጃብ ከለበሽ ጦሩ ይሸነፋል አይሏትም። የሀይል ሚዛንን በመጠቀም በክልልሉ የአንድ እምነት ባህልና ወግን ለማስጠበቅ ሲባል ሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ እየደረሰ ያለው በደል ታሪክ ይቅር የማይለው ነው። ከሂጃብ የፀዳ ሙስሊም እንፈጥራለን የሚለው ትግል እንኳን ያረጀ ያፈጀ ትግል ነው። አትችሉም ! ሴት ልጅ በህጉ መሰረት ተጨማሪ የሞራል ስብዕና እንድሁም ቅድሚያ ለሴት የሚለው ቀርቶባት ሰብአዊ እና ድሞክራሲያዊ መብቷ ተነፍጎ ህገ ወጥ ትጥቅ በያዙ አካላት ተጨቁና በትግራይ ክልል ተመልክተናል። አንረሳውም ! ከእስልምና እምነት ውጭ ያሉ ማንኛውም ሴት ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ጣቢያ መቀለ ዩኒቨርስቲ ዛሬና ነገ በመግባት ላይ ይገኛሉ።ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ግን መማርም ሆነ ፈተና መውሰድም ወንጀል ነው ! ግንባር ገብተው እንድዋጉ ግን መስፈርት አልጣላቸውም። አሰልፈዋቸዋል !
"ክርስቲያኖች ተሰደው ሲመጡ ተቀበልናቸው" 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 በአሕመዲን ጀበል ✅✅✅✅✅ እኛ ኢትዮጵያውያን ከጥንት ጀምሮ የተለያዩ እምነት ተከታዮች ነበርን።ከመካከለኛ ምስራቅ በቅድሚያ የአይሁድ እምነት ተከታዮች ተሰደው ወደኛ ሲመጡ በእንግድነት ተቀበልናቸው።እነርሱም እምነቱን መስበክ ጀመሩ። ከኛ ዉስጥ ጥቂቶች እምነቱን ተቀበሉ። ቀጥሎም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ330 ፍሪምናጦስ በተባለ ወጣት መሪነት ጥቂት የሶሪያ ክርስቲያኖች በስደት ወደ አክሱም መጡ። በእንግድነት ተቀበልናቸው። እምነታቸውን እንዲሰብኩ ፈቀድንላቸው።ክርስትናን መስበክ ጀመሩ። የአክሱሙ ንጉሥ ኢዛናን ጨምሮ ከኛ ዉስጥ ጥቂቶች ክርስትናን ተቀበሉ። ወጣት ፍሪምናጦስ ጳጳስ ፍለጋ ወደ ግብጽ አመራ። ንጉሡ ኢዛና ክርስትናን እንዲቀበል እንዳደረገ ገለጸ። ንጉሡን ክርስትና ማስነሳት ከቻልክ አንተኑ ጳጳስ እናድርግህ ብለው "አባ ሰላማ" ብለው ቀቡት። ክርስትናን የተቀበሉት ኢትዮጵያውያን ደግሞ "ከሳቴ ብርሃን" ብለው ሰየሙት። ክርስትና ከ330 እስከ 451 ድረስ የአክሱም ቤተ መንግስት ሃይማኖት እንጂ የአጠቃላዩ ሕዝብ ሃይማኖት መሆን አልቻለም ነበር። በአምስተኛው ክፍለ ዘመን በሰሜን ኢትዮጵያ ክርስትናን ለሕዝቡ የሰበኩትና ‹‹ዘጠኙ ቅዱሳን›› በሚል የሚታወቁት የሃይማኖት አባቶች ሁሉም መጤና የመካከለኛ ምስራቅ ስደተኞች ናቸው። እነዚህ ስደተኞች ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ተሰደው የመጡት እ.ኤ.አ በ451 ከተካሄደው ‹‹ቻልኬዶን ጉባዔ›› በኋላ ነበር። ስደተኞቹ የሃይማኖት አባቶች አባ አፍጼ፣ አባ አሌፍ፣ አባ ገሪማ፣ አባ ጉባ፣ አባ ሊቃኖስ፣ አባ ጴንጤሌዎን፣ አባ ጻሕማ፣ አባ የማታ፣ እና አባ ዘሚካኤል ዓረጋዊ ናቸው። (The Dictionary of Ethiopian Biography, Vol.1, From Early times to the End of the Zagwe Dynasty C.1270 AD, Institute of Ethiopian studies, Addis Ababa University, 1975, Pp. 209-210) ቀጥሎም በ615 ከመካ የኢስላም እምነት ተከታይ ሰሀቦች ተሰደው መጡ። ነጻነት በመስጠት የጥገኝነት ጥያቄያቸውን በመቀበል በሀገራችን እንዲኖሩ ፈቀድንላቸው። እምነቱን ሰበኩ። ከኛ ዉስጥም ጥቂቶችም ኢስላምን እንደ እምነት ተቀብለው ሙስሊም ሆኑ። በኢትዮጵያ ቆይታቸውም ጥቂት ስደተኞች በዚሁ ሞተው በትግራይ ተቀበሩ። የተቀሩት ከ15 ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ። ክርስትና እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ330 ወደ አክሱም ሲገባ ኢስላም ደግሞ ክርስትና ወደ አክሱም ከገባ ከ285(ከሁለት መቶ ሰማንያ አምስት) ዓመታት በኋላ ማለት በ615 ነበር የገባው። ከዚያ በኋላ እኛ ኢትዮጵያውያን በተለያየ ጊዜ በተቀበልናቸው ሃይማኖቶች ምክንያት እምነታችን የተለያየ ሆነ። ከፊሉ አይሁድ፥ ከፊሉ ክርስቲያን፥ ከፊሉ ሙስሊም ሆነ። ቀጥሎም በ16ኛ ክፈለ ዘመን ካቶሊኮች ወደ ሀገራችን ተሰደው መጡ።ተቀበልናቸው። እምነታቸውን መስበክ ጀመሩ። ከኛ መካከል ከፊሎች የካቶሊክ እምነትን ተቀበሉ። ቀጥሎም በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ወደ ኢትዮጵያ መጡ።ተቀበልናቸው።እምነታቸውን እንዲሰብኩ እኛ ኢትዮጵያውያን ፈቀድንላቸው። በዚህ ሁኔታ እኛ ኢትዮጵያውያን እምነታችንን እየቀያየርን ቀጠልን። ከፊላችን ኦርቶዶክስ፣ ሙስሊም፣ ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንት፣ወዘተ እየሆንን ቀጠልን። ከላይ በተጠቀሰው መልኩ በመጤ ስደተኞች የተሰበከውን እምነት እየተከተልን ዘለቅን።ነገር ከኛ መካከል በመጤ ስደተኞች የተሰበከው የአንዱ እምነት ከፊል ሰባኪዎች "ሌሎች እንጂ እኛ መጤ አይደለንም።" የሚል እይታ ያዙ።በእርግጥ መጤዎቹ እምነቱን ያመጡልን እንጂ እኛ የተቀበልነው ኢትዮጵያውያን አይደለንም። ከእምነቶቹ መምጣት በፊት ሀገርና ህዝብ ነበር።ዛሬም ሀገራችን የሁላችንም ስለሆነች ሁላችንን በምትመስልና እኩል በምትወክል መልኩ እንገንባት የሚል ጥያቄ ሲነሳ "እኛ ነባር እናንተ መጤ" የሚል የድንቁርና ጫወታ መጫወት ያማራቸውን ታዘብን። እኔም ሀገራችን የሁላችንም ናትና መስተካከል ያለባቸው ነገሮች እንዲስተካከል ሀሳብ ሳነሳ አፍ በማዘጋት ዝም ለማሰኘት ጥቂቶች ተረባረቡ። አክራሪ፣አይ፣ ኤስ፣ወሃቢያ፣ የእጌሌ ተላላኪ፣ ኢስላማዊ መንግስት ሊመሰርቱ አቅደዋል፣ሌላም ሌላም። ያሻችውን ይበሉ እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ተሰደው ሲመጡ በመቀበላችን እንደምንኮራው ክርስቲያን ስደተኞችን በመቀበላችን እንኮራከን። ቸር እንሰንብት! ኡዝታዝ አህመዲን ጀበል
😵🤔🙁😝😤☹️🙁☹️ 🛜የመጀመሪያው ፕሮግራማችን ▶️ 🙁☹️😭🙁😭🙁☹️🙁 🎤ስለ ሒጃብ ግዴታነት ተ🎁 ጀ▶️ መ ▶️ ረ▶️ ➡️አቡ ሂበቲላህ ሁሰይን ✅ ገባ ገባ በሉ ባረከሏሁ ፊኩም! ‼ ➘ ➘ ➘ ➘➘ ➘ ➘ ➘ ➘ ➘ ➘ t.me/tdarna_islam?livestream t.me/tdarna_islam?livestream
ባንክ ውስጥ የሙስሊሙ ገንዘብ የተቀመጠው የት ነው⁉️ ================================== (ለነማንስ በብድር መልክ እየቀረበ ነው⁉️) || ✍️ "ከወለድ ነፃ ባንክ (Interest-Free Banking - IFB)" የሚለው ስያሜ በሀገራችን በስፋት መነገሩ እና በተለያዩ ባንኮች በኩል መስኮቶች መከፈታቸው ይታወቃል። ነገር ግን፣ እኛ የራሳችንን ሃብት እያጠራቀምን ነው ብለን የምናስበው ገንዘባችን በትክክል የት ነው ያለው? ለነማንስ የኢኮኖሚ ጉልበት እየሆነ ነው? 🔗እስኪ እስከ ባለፈ December 31, 2025 ባለው ይፋዊ መረጃ መሠረት እውነታውን በቁጥርና በፐርሰንት እንገምግመው 📊🫴 1⃣) የገንዘባችን ክምችት የት ነው ያለው? ➡️ በሀገራችን ባሉ ሁሉም ባንኮች ከወለድ ነፃ (IFB) ተብሎ የተቀመጠው አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ (Deposit) 498.8 ቢሊዮን ብር (ወደ ግማሽ ትሪሊዮን ብር ገደማ) ደርሷል። ይህ እጅግ ግዙፍ አቅም ነው! ነገር ግን ይህ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ገንዘብ የተቀመጠው የት ነው? ▫️ የአራቱ ሙሉ በሙሉ ኢስላማዊ ባንኮች ድምር (ዘምዘም፣ ሒጅራ፣ ራሚስ እና ሸበሌ)፦ በአንድ ላይ የያዙት ተቀማጭ ገንዘብ 36.52 ቢሊዮን ብር ብቻ ነው! ▫️ የወለድ ባንኮች የመስኮት (IFB Windows) ክምችት፦ ቀሪውን 462.3 ቢሊዮን ብር ይዘዋል። ይህ ምን ማለት ነው▫️⁉️ ▫️ ከጠቅላላው የሙስሊሙ ከወለድ ነፃ ገንዘብ ውስጥ ወደ እውነተኛዎቹና ሙሉ በሙሉ ኢስላማዊ ወደሆኑት አራቱ ባንኮቻችን የገባው 7.3% ብቻ ነው! ▫️ ቀሪው 92.7% የሚሆነው የሙስሊሙ ማህበረሰብ ገንዘብ ዛሬም የተቀመጠው በወለድ ባንኮች መስኮቶች ውስጥ ነው። 2⃣) ይህንን ክፍተት ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ ጥቂት ንፅፅሮችን እንመልከት፦ ➡️ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) የወለድ ነፃ መስኮት ብቻውን 256.3 ቢሊዮን ብር የሙስሊሙን ገንዘብ ሰብስቦ ይዟል። ይህ ማለት የCBE መስኮት ብቻውን አራቱንም ሙሉ ኢስላማዊ ባንኮች በጋራ ከያዙት ተቀማጭ ገንዘብ (36.52 ቢሊዮን ብር) 7 እጥፍ በላይ ይበልጣል! ➡️ የአዋሽ ባንክ መስኮት ብቻውን 53.1 ቢሊዮን ብር ይዟል። (ከአራቱ ኢስላማዊ ባንኮች ድምር ይበልጣል!) ➡️ የአቢሲኒያ ባንክ መስኮት ብቻውን 42.8 ቢሊዮን ብር ይዟል። (ይህም ከአራቱ እስላማዊ ባንኮች ድምር ይበልጣል!) ከዚያ ላንተ ከዚህ ላይ ዘካ ማውጣቱን ትቶ ለቤተ ክርስቲያን ግን የአስራት ይከፍላል። 📣 በአገልግሎት ምቹነትና በቅርንጫፍ ብዛት ሰበብ፣ 92.7% የሚሆነውን አቅማችንን በፈቃደኝነት ለሌሎች አሳልፈን ሰጥተናል። 3⃣ ይህ ገንዘብ ለማን ነው ፋይናንስ እየሆነ ያለው⁉️ ▫️ በወለድ ባንኮች ውስጥ የሚቀመጠው ከወለድ ነፃ ተብዬ ገንዘብ፣ ምንም እንኳን በሒሳብ መዝገብ ላይ ተለይቶ ቢቀመጥም፣ የባንኮቹን አጠቃላይ የፈሳሽነት (Liquidity) አቅም በእጅጉ ያጎለብታል። 🔸 አጠቃላይ የባንክ ኢንዱስትሪው የግልና የCBE ተቀማጭ ገንዘብ 4.2 ትሪሊዮን ብር ደርሷል። በነገራችን ላይ ከላይ ያየነው ከወለድ ነፃ በሚባለው መስኮት የተቀመጠውን እንጂ በወለድ መስኮት «ሁሉም ያው ነው» ብለው የሚያስቀምጡ ጥቂት የማይባሉ ግዙፍ ሙስሊም ባለሃብቶች እንዳሉ ልብ ይሏል። 🔸 የወለድ ባንኮች ይህንን ገንዘብ ተጠቅመው ለተለያዩ ታላላቅ የወለድ (ሪባ) የንግድ ዘርፎች፣ ለግዙፍ አስመጪና ላኪዎች በመቶ ቢሊዮኖች የሚቆጠር ብድር ያቀርባሉ። 🔸 በአንፃሩ አራቱ ኢስላማዊ ባንኮቻችን ለህብረተሰቡ ያቀረቡት ጠቅላላ የፋይናንስ መጠን (Financing) 25.3 ቢሊዮን ብር ብቻ ነው። ምክንያቱም አቅማቸውን አላዳበርነውም! 🔸 ገንዘባችንን በሌሎች ባንኮች መስኮት ላይ እያስቀመጥን፣ እነዚያ ባንኮች የእኛን ፈሳሽነት ተጠቅመው የሪባን ግንብ ሲያጠናክሩበት ይውላሉ። የገዛ ባንኮቻችንን ግን በአቅርቦት ማነስና በቅርንጫፍ ጥበት በጥቃቅን ነገሮች አኩርፈን እንተዋቸዋለን። የነርሱ ስግጥና ሲጨመርበት ደግሞ ችግሩ የከፋ ይሆናል። 4⃣ መፍትሄው ምንድን ነው⁉️ 🎀 የተከበረው ሙስሊሙ ማህበረሰባችን የኢኮኖሚ ጥገኝነትን ሰብሮ መውጣት ካለበት፣ ከስሜት ባለፈ በስሌትና በቁጥር መመራት ይኖርበታል። 1️⃣ ገንዘብን ወደ እውነተኛ ኢስላማዊ ባንኮች ማዞር፦ ሒጅራ ባንክ ባለው አነስተኛ አቅም 10 ሚሊዮን ብር ለአካባቢው ማህበረሰብ ዘካና ወቅፍ ማውጣት ከቻለ፣ ያ በሌሎች መስኮቶች የፈሰሰው 462 ቢሊዮን ብር ወደ ራሳችን ተቋማት ቢዞር ኖሮ ማህበረሰባችን ውስጥ ምን ያህል የኑሮ ለውጥ ማምጣት ይቻል ነበር? 2️⃣ አስተማማኝና ዘመናዊ የኢንቨስትመንት ሥርዓት (System) መገንባት፦ ⬅️ ሰሞኑን ያነሳሁትን የ4.9 ቢሊዮን ብር የጋራ ጥሬ ካፒታል ሃሳብ አስታውሱት። እርስ በእርስ ከመጠራጠር ወጥተን፣ ሰውን ሳይሆን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታጠረን ግልጽ ሥርዓት (Transparent System) አምነን በጋራ ከተነሳን፣ የራሳችንን ግዙፍ የፋይናንስና የኢንቨስትመንት ተቋማት መገንባት እንችላለን። «የገዛ ቤቱን በጭልፋ እያጠጣ፣ የጎረቤቱን ግንብ በባሊ የሚሞላ ሕዝብ፣ መጨረሻ ላይ 'ቤቴ ፈረሰ' ብሎ ሲያለቅስ ጥፋተኛው ማን ነው?» 🔸 አስተሳሰባችንን እናስተካክል፣ ገንዘባችን የት እንደሚቀመጥና ለማን ጥቅም እንደሚውል እንወቅ። አቅማችንን በጋራ አስተባብረን የኢኮኖሚ ነፃነታችንን የምናረጋግጥበት ጊዜ አሁን ነው! ሀሳባችሁን በኮመንት አጋሩኝ👇💬 ሃሳቤን ገና አልጨረስኩም፤ በሌላ ክፍል እመለሳለሁ። || t.me/MuradTadesse
🙁🙁🙁🙁🙁🙁☹️🥳 😃ታላቅ የደዕዋና የቁርአን ኸትሚያ ፕሮግራም ⭐️ ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 🌿 የእህታችን ኡሙ አብዱል ወሃብ የቁርአን ኽትሚያ በማስመልከት የተዘጋጄ ደማቅ የደዕዋ ፕሮግራም ⭐️ የሚጋበዙ ኡስታዞቻችን ⭐️ ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ✅ ሸይኽ ሁሴን አቡ ሀኒፋ (ሀፊዘሁሏህ ✅ ሸይኽ አቡ ፋጢማ(ሀፊዘሁሏህ ✅ ኡስታዝ አቡ ሀኒፋ ሀፊዘሁሏህ ✅ ኡስታዝ አቡ ሻኪራ ሀፊዘሁሏህ ✅ ኡስታዝ አቡ ኸውላ ሀፊዘሁሏህ ✅ ኡስታዝ አቡ ሙሀመድ ሀፊዘሁሏህ ✅ወንድም አቡ ሂበቲላህ ሀፊዘሁሏህ ✅ወንድም አቡ ሹራ ሀፊዘሁሏህ ✅ወንድም ኑረዲን አቡፋሩቅ ሀፊዘሁሏህ 📖 የቁርአን ቲላዋ የሚጋብዙን ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ⭐️ ወንድም አቡ ኢምራን ሀፊዘሁሏህ ⭐️ ወንድም አቡ አፍናን ሀፊዘሁሏህ ⭐️ ወንድም ሙሀመድ ሲራጅ ሀፊዘሁሏህ 🔧 የፕሮግራሙ መሪ ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ✅ ወንድማችን አቡ ማሒ ሀፊዘሁሏህ 🗺 ቀን እና ሰአት፦ የፊታችን ሰኞ ማታ ከምሽቱ 3:00 ሰአት ጀምሮ ❤️ ፕሮግራሙ የሚተላለፍበት ቻናል 🔗 https://t.me/tdarna_islam 🔗https://t.me/tdarna_islam
አምላኬ ሆይ፣ ከዋክብት ጠፍተዋል፣ ዓይኖችም በእንቅልፍ ተዘግተዋል፣ አንተ ግን ሕያው ነህ፣ ራስህን የምትጠብቅ ነህ፣ እንቅልፍም ሆነ እንግልዣ አያገኝህም። አልህ ሆይ፣ ጸጸትን የሚያመጣ፣ ጸጸትን የሚያስከትል፣ ሲሳይን የሚከለክል እና ጸሎቶችን የሚከለክል ኃጢአት ሁሉ ይቅርታህን እጠይቃለሁ። ጌታ ሆይ፣ ከበርህ በስተቀር ሁሉም በሮች ተዘግተዋል፣ ወደ አንተ የሚመሩትን በስተቀር ሁሉም መንገዶች ተቆርጠዋል። በአንተ ውስጥ ካልሆነ በስተቀር ኃይልም ሆነ ኃይል የለም። አምላኬ፣ ታዛዦችን ብቻ የምትምር ከሆነ፣ እማይታዘዙትን ማን ይምራል? የትጉዎችንም ሥራ ብቻ የምትቀበል ከሆነ፣ ቸልተኞችን ማን ይምራል? ጌታየ ጌታዬ ሆይ፣ በዚህ ዓለም ውስጥ ብቸኝነቴን፣ በሞት ጊዜ የሚሰማኝን ስቃይ እና በመቃብር ውስጥ ያለኝን ጥፋት ማረኝ።አሚን ያረበል አለሚን።
ኢላሂ…🤲 ያየህብኝን ፥ አታሳይብኝ፣ እኔ እና አንተ የምናውቀውን ፥ አትንገርብኝ። እያየኸኝ ነው ፥ የወንጀል ሸክም አደካክሞኛል፣ የተውከኝ ዕለት… ያበቃልኛል። ቆሸሽክ ብለህ፥ አልገፋኸኝም ከንፁህ ደጅህ፣ ሰተርከኝ አይደል?… በዛውም ማረኝ ፥ በነካው እጅህ።🤲
ቱርክ እና ግብፅ የግብረ-ሰዶማውያን መንገደኞችን የጫነች የሽርሽር መርከብ ወደ ወደቦቻቸው እንዳትገባ ከለከሉ! • ሀሩን ሚዲያ | ሐምሌ 4 ቀን 2018 ዓ.ል የቱርክ እና የግብፅ ባለሥልጣናት በሺዎች የሚቆጠሩ የግብረ-ሰዶማውያን መንገደኞችን የጫነችው "ስካርሌት ሌዲ" የተሰኘች የሽርሽር መርከብ ወደ ወደቦቻቸው እንዳትጠጋ ክልከላ ጣሉባት። የቱርክ ባለሥልጣናት 1,900 ያህል መንገደኞችን ያሳፈረችው ይህች መርከብ በኩሻዳሲ እና ኢስታንቡል ወደቦች እንዳትቆም የከለከሉ ሲሆን፤ ለውሳኔያቸውም "የሞራል እሴቶችን" በምክንያትነት አንስተዋል። በተመሳሳይ ሁኔታ ይቺው መርከብ በግብፅ ባለሥልጣናት በኩል ያልተጠበቀ ክልከላ ገጥሟታል። የግብፅ ባለሥልጣናት ምንም ዓይነት ይፋዊ ምክንያት ሳያቀርቡ በመጨረሻው ሰዓት መርከቧ ወደ ሀገሪቱ እንዳትገባ ማገዳቸው ተገልጿል። ክልከላውን ተከትሎም መንገደኞቹ ሌሊት ላይ መረጃው እንዲደርሳቸው የተደረገ ሲሆን፣ መርከቧም የጉዞ አቅጣጫዋን ለመቀየር ተገደዳለች። የጉብኝቱ አዘጋጆች ተመሳሳይ የጉዞ መርሃ-ግብር ባለፈው ዓመት ያለምንም ችግር በስኬት ተጠናቆ እንደነበር በማስታወስ በዘንድሮው ክልከላ መገረማቸውን ገልጸዋል። በመሆኑም አሁን ላይ መርከቧ አቅጣጫዋን በመቀየር ወደ ክሬት (ግሪክ) እና ሞንቴኔግሮ እንደምታቀና ዘ ጋርዲያን በዘገባው አስነብቧል። 📅 ሐምሌ 4 ቀን 2018 ዓ.ል © ሀሩን ሚዲያ
ከ1400 ዓመታት በፊት የተነገረው አስደናቂው የ"ዲ ኤን ኤ" (DNA) እና የትንሣኤ ምስጢር! የሰው ልጅ አካል በሙሉ በስብሶ፣ አፈር ሆኖ ከቀረ በኋላ እንዴት መልሶ ሊቀሰቀስ ይችላል? ለሚለው ጥያቄ ዘመናዊው የፅንስ ሳይንስ (Embryology) እና ጄኔቲክስ በአጉሊ መነጽር ያረጋገጡትን እውነታ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ገና በሰባተኛው ክፍለ ዘመን በምድር ላይ ላብራቶሪም ሆነ ሳይንሳዊ መሣሪያ በሌለበት ዘመን በግልጽ አስቀምጠውልናል። ይህንን ድንቅ ተዓምር አብረን እንመልከት 👇 📜 ታላቁ የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲስ የአላህ መልክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ "የሰው ልጅ (አካል) ሁሉ በስብሶ ያልቃል፤ የአጅቡዝ-ዘነብ (የጀርባ ወይም የጅራት መጨረሻ ቅንጣት አጥንት) ሲቀር፤ ከእርሷ ተፈጠረ፤ በትንሣኤ ቀንም በእርሷ ላይ መልሶ ይገነባል።" > 📖 (ሶሒሕ ሙስሊም፡ 2955) 🔬 ዘመናዊው ሳይንስ ምን ይላል? (ሳይንሳዊው እውነታ) 1️⃣ ፕሪሚቲቭ ስትሪክ (Primitive Streak) እና የሕይወት መጀመሪያ፦ በፅንስ ሳይንስ ጥናት መሠረት፣ ፅንሱ በተፈጠረ በ14ኛው ቀን አካባቢ በጀርባው የታችኛው ክፍል ላይ Primitive Streak የሚባል ጥቃቅን የሴሎች ስብስብ ይፈጠራል። ይህ ስብስብ የሰውነታችን የነርቭ ሥርዓት፣ አጥንት፣ አንጎልና ሌሎች አካላት በሙሉ እንዲቀረጹ መሠረት የሚጥል “የሕንጻ ፕላን” ነው። ፅንሱ ሙሉ አካል አውጥቶ ሲያድግ ይህ መሠረት እየጠበበ ሄዶ በጀርባችን አጥንት መጨረሻ (Coccyx/Tailbone) ላይ እንደ አንዲት ቅንጣት አጥንት ሆኖ ይቀመጣል። ይህም ሐዲሱ "ከእርሷ ተፈጠረ" ካለው እውነታ ጋር 100% ይገጥማል። 2️⃣ የማይጠፋው "የመረጃ ቋት" (The Indestructible Bone): በተለያዩ አገራት (ለምሳሌ በጀርመንና በየመን ሳይንቲስቶች) በዚህች የጅራት መጨረሻ አጥንት ላይ ከፍተኛ የምርምር ሙከራዎች ተደርገዋል። አጥንቷን በከፍተኛ ሙቀት (እስከ 1000 ዲግሪ ሴንቲግሬድ) አቃጥለዋታል፣ በጠንካራ አሲዶች ውስጥ ዘፍቀዋታል፣ እንዲሁም በከፍተኛ መዶሻ ቀጥቅጠዋታል። ነገር ግን የተገኘው ውጤት አስገራሚ ነበር—ውስጥ ያለው የዘረመል መረጃ (DNA) እና ዋናው የሴል መዋቅር ሊጠፋ አልቻለም! 3️⃣ የትንሣኤ ቀን ዳግም ምስረታ፦ ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ከሆነ ይህች አጥንት ልክ እንደ ኮምፒውተር "Hard Drive" የሰውን ልጅ ሙሉ የሰውነት መረጃ (Genetic Code) ይዛ ትቆያለች። በትንሣኤ ቀን አላህ (ሱ.ወ) ዝናብ በሚያዘንብበት ወቅት፣ የሰው ልጅ አካል ከዚችው ቅንጣት አጥንት ላይ ልክ እንደ ተክል ዘር መልሶ እንደሚበቅል ሐዲሱ ያስረዳናል። 💡 ይህ የዛሬ 14 ክፍለ ዘመን የሳይንስ ሊቃውንት ጨርሶ የማይገምቱት፣ በአጉሊ መነጽር በዘመኑ ቴክኖሎጂ ብቻ ሊደረስበት የቻለ ጥልቅ ምስጢር ነው። ታዲያ ይህንን ሚስጥር ለነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ማን ነገራቸው? ፈጣሪያችን አላህ በቁርአኑ ላይ እንዲህ ብሏል፦ "እርሱ (ነቢዩ) ከልብ ወለዱ አይናገርም፤ እርሱ (የሚናገረው) የሚወርድለት ራዕይ እንጂ ሌላ አይደለም።" (አን-ናጅም፡ 3-4) ሱብሓነላህ! ለሌሎች እንዲደርስ ሼር (Share) በማድረግ የበኩልዎን ያድርጉ! 💚 የነቢዩ ሰ አ ወ ሰሂህ ሃዲሶች #MiraclesOfIslam #ScienceInHadith #IslamicFact #FaithAndScience #Coccyx✍️
በባህርዳር መግሪብ ሰግዶ ሲወጣ ወንድማችንን ሊወስዱ የመጡ አሸባሪው ፋኖ ቡድን አልሄድም ሲላቸው በጥይት መተውት ሄድዋል። አሁን ሆስፒታል ተኝቶ ነው ያለው።
በማታስታውሰው ቅፅበት ህይወትህ ጀመራለች። አሁንም… ልታውቀው በማትችለው ቅፅበት ውስጥ ህይወትህ ታበቃለች። መለወጥ በማትችለው "ትናንት" ውስጥ ኖረሃል… በማታምነው "ነገ" ውስጥም ትብሰለሰላለህ። … እመነኝ ደካማ ነህ…… ጌታህን ያዝ! ዱባይም ኢትዮም ያላችሁ እዘዙኝ ማንኛውንም የምትፈልጉትነገር ታገኛላችሁ።