Wolkite University Muslim students jeme'a official channel
Статистикаይህ ቻናል ትክክለኛው የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሲሆን፣ በቻናሉም፦ ➲ ሙስሊም ተማሪዎችን የተመለከቱ መረጃዎች ➲ በዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች መስጂድ ስለሚደረጉ ሀይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች ለምሳሌ ➩ የዳዕዋ ፕሮግራም ➪ የቂርአት እንቅስቃሴ ➪ ሌሎችም ዝግጅቶች ሲኖሩ የሚለቀቁ ይሆናል በአላህ ፍቃድ። @Wku_ibnuabbas_bot https://t.me/Wku_ms_Official_Channel
- Последний пост
- 2 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 549
- 1/48двое суток
- 629
- 1/72трое суток
- 678
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
✔️በዚህ ክረምት ነፃ የቋንቋ እድል የምታገኙበት ቻሌጅ ልጠቁማችሁ 1️⃣ኛ ለወጣ ነፃ የቋንቋ ስልጠና እና ብር 1500 2️⃣ኛ ለወጣ ነፃ የቋንቋ ስልጠና እና ብር 1000 3️⃣ኛ ለወጣ ነፃ የቋንቋ ስልጠና እና ብር 500 🏪ቻሌንጁ ለመሳተፍ ሙሉ ማብራሪያ🔣 https://t.me/Ihsan_language/315 https://t.me/Ihsan_language/315
"የ19 ዓመት የዩንቨርስቲ ተማሪ ወደ ህክምና ማዕከል በሄደችበት ማደንዘዣ በመውጋት አስገድዶ መድፈር የፈፀመው ዶ/ር በ21 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ" የሚል ዜና አየሁኝ። "በሃኪም እንዴት ይሄ ይፈጸማል?" ማለት ሞኝነት ነው። በሃኪም ቀርቶ በሃይማኖት አስተማሪም ይፈጸማል። መፍትሄው አጭርና ቀላል ነው። ማንኛዋም ሴት ከባዳ ወንድ ጋር ተገልላ ልትገኝ አይገባትም። ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ لا يخلوَنَّ رجلٌ بامرأةٍ فإنَّ الشيطانَ ثالثُهما "አንድ ወንድ ከባዕድ ሴት ጋር ብቻውን አይነጠል፤ ምክንያቱም ሶስተኛቸው ሸይ^ጧን ነውና።" [ቲርሚዚይ፡ 2165] "ሶስተኛቸው ሸይ^ጧን ነው" የሚለው አጉል መልካም እምነት እንዳያዘናጋን ጥብቅ ማሳሰቢያ ነው። ስለዚህ ያልታሰበ ከባድ ጥፋት የመድረስ እድሉ ከፍተኛ ነው ማለት ነው። ህክምናን በተመለከተ ሴቶች አማራጭ ካለ በሴቶች ታከሙ። አስገዳጅ ሁኔታ ከገጠመ ከቤተሰብ ጋር እንጂ ብቻችሁን ወንድ ሃኪም ዘንድ አትግቡ። ወይም ሴቶች ነርሶች ካጠገባችሁ እንዲሆኑ አናግሩ። እዚህ ላይ "ውጭ ቆዩ" የሚሉ ሃኪሞች ይኖራሉ። (መግቢያየ ላይ የጠቀስኩትም ክስተት በዚህ መልኩ የተፈፀመ ነው።) እንዲህ አይነት ሃኪም ሲገጥመን ቢቻል ማስረዳት፣ ካልሆነ መጋፈጥ ይገባል። ፈቃደኛ የማይሆኑ ሃኪሞችና ሃኪም ቤቶች ዘንድ አትሂዱ። ቆራጥ ከሆንን ለራሳቸው ሲሉ ያስተካክላሉ። ለሃኪሞች ማሳሰቢያ፦ ከባዳ ሴት ጋር ተገልሎ መቆየት እንደማይቻል አትዘንጉ። ስለዚህ ስታክሙ ቤተሰብ በቅርብ እንዲኖር አድርጉ። ወይም ረዳቶች ባቅራቢያችሁ ይኑሩ። አስገዳጅ ሁኔታ ከገጠማችሁ የምትሰሩበትን ክፍል በሩን ክፍት አድርጉት። በነገራችን ላይ እንኳን ባዳ የሆነ አካል በቤተሰብ መሀል ራሱ መጥፎ ነገር ሊከሰት ይችላል። ለዚያም ነው ኢስላም በዚህ ጉዳይ ላይ ጥብቅ መመሪያ ያስቀመጠው። ነብያችን ﷺ ልጆችን አስር አመት ሲሆናቸው መኝታቸውን ለያዩዋቸው ብለዋል። ለአስር ዓመት ልጆች! ስለዚህ ቤተሰብ አላህ ባገራለት ልክ መኝታቸውን ሊለያያቸው ይገባል። ሁሉም አንድ ክፍል ውስጥ የሚተኙ ከሆነ ሴቶችን አንድ ጥግ፣ ወንዶችን ደግሞ ሌላ ጥግ ማድረግ ይገባል። በቂ ክፍሎች ካሉ ሴቶችን የብቻ አንድ ክፍል፣ ወንዶችን የብቻ ሌላ ክፍል ማድረግ ይገባል። ከተቻለ ወንዶችን ከወንዶች፣ ሴቶችንም ከሴቶች ፍራሻቸው ቢለያይ ጥሩ ነው። አጉል መልካም ግምት ሊያዘናጋን አይገባም። "የዘመድ ልጅ ነው"፣ "ቤተሰብ ነው"፣ "ሸይኽ/ ኡስታዝ ነው"፣ "የጎረቤት ልጅ ነው"፣ "እንግዳ ነው"፣ "ስርአት ያለው ጨዋ ልጅ ነው"፣ "ትልቅ ሰው ነው"፣ የመሳሰሉ የዋህ ድምዳሜዎች ከባድ ዋጋ ያስከፍላሉ። እንኳን ሴቶችን ከወንድ፣ ወንዶችን ከወንድም መኝታቸውን መለየት ይገባል። ሌላው ቀርቶ አባት ወይም ወንድም ቢሆኑ እንኳ ጥሩ ያልሆነ አዝማሚያ የሚያሳዩ ከሆነ የሚቻለውን ሁሉ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿إنَّ مِن أفضَلِ أيّامِكم يومَ الجُمعةِ، فأكْثِروا عليَّ الصلاةَ فيه؛ فإنَّ صلاتَكم مَعروضةٌ عليَّ.﴾ “ከቀናችሁ ሁሉ በላጩ የጁምዓ ቀን ነው። በዚህ ቀን በኔ ላይ ሰለዋት ማውረድ አብዙ። ሰለዋታችሁ ለኔ ይቀርብልኛልና።” አቡ ዳውድ ሶሂህ ብለውታል: 1531 የሰለዋቱ ሁኔታ «اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ
ነሕውን ከዘዋጅ ጋር የሚያያይዝ አባባል፦ "present form of a verb በመርፉዕነት፣በመንሱብነት እና በመጅዙምነት መካከል በነፃነት እና ያለ ገደብ እድሜውን ያሳልፋል(ላጤ)::አንስታይ ፆታ አመልካች 'ن' እስክትቀጠልበት:(ስትቀጠልበት)በስኩን ይገነባል"-ይረጋጋል። አንዱ ይህንን አባባል ሲሰማ "አላህ ሆይ፥ይህችን 'ن' ከጎኔ አድርግልኝ"ብሎ ዱዓ አድርጓል።
🎉الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي بِنِعْمَتِهِ تَتِمُّ الصَّالِحَاتُ ✨አልሃምዱሊላህ! ✨አልሃምዱሊላህ! ✨አልሃምዱሊላህ! «ድብቁ ገዳይ እና የተስፋው ጋሻ»! ~ ተለቀቀ~ ሰው ነኝና ከስህተት ከጥፋት አልጠራም እርምት እና አስተያየት ካላችሁ በዚህ ንገሩኝ @Abu_Hulud22 ሚስኪኑ ወንድማችሁ ⎛አቡ ሑሉድ.⎫
ﻗَﺎﻝَ ﺷَﻴْﺦُ ﺍﻹﺳْﻼَﻡِ ﺍﺑﻦُ ﺗَﻴْﻤِﻴَّﺔَ، ﺭَﺣِﻤَﻪُ ﺍﻟﻠﻪُ ﺗَﻌَﺎﻟَﻰ : " ﻣَﻦْ ﺗَﺪَﺑَّﺮَ ﺍﻟْﻘُﺮْﺁﻥَ ﻃَﺎﻟِﺒًﺎ ﻟِﻠْﻬُﺪَﻯ ﻣِﻨْﻪُ، ﺗَﺒَﻴَّﻦَ ﻟَﻪُ ﻃَﺮِﻳﻖُ ﺍﻟْﺤَﻖِّ ." [ﻣﺠﻤﻮﻉ ﺍﻟﻔﺘﺎﻭﻯ ( ١٣٧ /٣ ) ] ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ﺭَﺣِﻤَﻪُ ﺍﻟﻠﻪُ ﺗَﻌَﺎﻟَﻰ እንዲህ ይላሉ ፦"ቁርአንን ለመመራት ብሎ ያስተነተነ ሰው የሐቁ መንገድ ግልፅ ይሆንለታል" 📚 መጅሙዑል ፈታዋ (3/137) አላህ ቁርአንን እያስተነተኑ ከሚቀሩ ሰዎች ያድርገን
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ስለ ክረምት ደርሳችን የመጨረሻ ማስታወሻዎች: 1,መደበኛ ምዝገባ የተጠናቀቀ ቢሆንም ቂርኣቱን መከታተል ለሚፈልግ ምዝገባው ለ1 ሳምንት ያህል ይቀጥላል። 2,በፕሮግራማችን መሠረት በአላህ ፈቃድ የመጀመርያ ደርሳችን የሚሆነው الأصول من علم الأصول ዛሬ(ሰኞ) አመሻሽ11:45 ላይ ይሆናል። 3,ለደርሱ በጊዜ መገኘት፣ሙጣለዓ ማድረግ እና live መከታተል ያልቻለ ሪከርዶችን በተገቢው ሁኔታ መከታተል ዋና ዋና አዳቦች ናቸውና ባትዘናጉ።ያለ በቂ ምክንያት ላለማቋረጥ ቆራጥ ሁኑ።አላህ ይርዳን!!። 4,ከዚህ በኋላ አስገዳጅ ካልሆነ በስተቀር ስለ ደርሱ እዚህ ቻነል ላይ ምንም ነገር አይለቀቅም።የደርሱ channel link፦ https://t.me/mibnabas
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ስለ ኮርሶቹ ጥቂት ማስታወሻዎች: በመጀመርያ ወኔ እና ቆራጥነታችሁ እጅግ በጣም አስደስቶኛል:ፍፁም ከጠበኩት በላይ ነው።አላህ ያስደስታችሁ ያስደስተን ፅናቱንም ይወፍቀን።በመቀጠል የናንተንም አስተያየት ከግምት በማስገባት የሚከተሉት ውሳኔዎች ላይ ደርሰናል።እነዚህም፦ 1,ኪታቦቹ A,ሙስጦለሑል ሐዲስ(የሸይኽ ኢብኑ ዑثይሚን) B,ኧልኡሱሉ ሚን ዒልሚል ኡሱል(በተመሳሳይ የሸይኽ ኢብኑ ዑثይሚን رحمه الله) እና C,ከሶርፍ ደግሞ መትኑል ቢናእ(ሸይኽ አቡ ዚያድ ሙሀመድ ቢን ሀሰን)...ለጀማሪ ከነሕው ይልቅ ሶርፍ ቀለል ስለሚል እና ነሕው በቅርብ ስለቀራን ነው ሶርፍ የተመረጠው። *pdf የቂርኣቱ ግሩፕ ላይ ተለቋል። *ኪታቦቹን በhardcopy ይዛችሁ ብትከታተሉ በላጭ ነው።ምናልባት ቢናእ ለብቻው ላይኖር ስለሚችል مجموعة الصرف ሚል መጠነኛ ጥቅል ኪታብ መግዛት ትችላላችሁ። 2,ምዝገባ ሚደረገው ዛሬ(ቅዳሜ)እና ነገ ስለሆነ ወንዶች በዚ username- @zidni1 እህቶች ደግሞ በዚኛው- @Umuayan2 መመዝገብ ይኖርባችኋል።attendance ክትትል ይደረጋል እና እንዳትዘናጉ። 3,ሁሌም ላይመቻችሁ ስለሚችል record ተደርጎ ይለቀቃል። 4,የቂርኣቱ ግሩፕ link፦ https://t.me/mibnabas ነው እናም ከዚ ሰዓት ጀምራችሁ join ማድረግ ትችላላችሁ።
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ያ ጀማዐተል ኸይር እንዴት ናችሁ;የረፍት ቀናት ጅማሮ እና ቤተሰብ ሁሉ ሰላም?... الحمد لله(على كل حال) ይነበብ፡ባረከሏሁ ፊኩም!(ሙሉ ብታነቡት) የክረምት ኮርስ በኢብኑ ዐባስ!! አንድ ነገር ላዋያችሁ ነበር...ይሀውም ለቀጣይ 2ወራት የሚቆይ የonline ኮርስ ለማዘጋጀት በኔ በኩል ፈቃደኛ እና ደስተኛ ነኝ።ተሳክቶ ብናስኬደው እኔም እናንተም ቢያንስ አራት ዋና ዋና ጥቅሞች ስለምናገኝበት ነው። 1,ሸሪዓዊ እውቀትን እና በዒባዳ አጅር ማግኘት። 2,የውመል ቂያማ ከምንጠየቅባቸው ነገሮች መካከል እድሜያችን:ወጣትነታችንን እና ገንዘባችንን አላህ በሚፈልግብን ሁኔታ ማዋል። 3,ጊዜያችን በሚጠቅመን ነገር ስናውል ጥፋት እና ወንጀል ላይ ከመውደቅ በአላህ ፈቃድ ስለምንጠበቅ። 4,ከዚ በፊት በየአመቱ ወይም በየአጋጣሚው ክፍት ጊዜ ሲኖረኝ እጠቀምበታለሁ እያልን ላመለጡን እድሎች ማካካሻ እና ለቀጣይ ክፍት ጊዜያትም ጥሩ ትዝታን ማኖር ነው። የኮርሶቹ ይዘት;ብዙ ቦታ ላይ እድሉን ማናገኝባቸውን መርጫለሁ።እነዚህም፦ 1,ኡሱሉል-ፊቅህ 2,ሙስጦለሑል ሐዲث 3,ሶርፍ(probably ነሕውም ሊሆን ይችላል) ፈተና እና ሰርተፊኬት ይኖራቸዋል። ቀን እና ሰዓት:ከቅዳሜ እስከ ሐሙስ አመሻሽ 11:45-12:30 ማስታወሻ: 1,ብዙዎች በዚህ ወቅት በአካል መስጅድ በመገኘት ወይም በኦንላይን ለመቅራት ፕሮግራም ይዛችሁ ሊሆን ስለሚችል ሀሳቡ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊሉ ሊቀየር ይችላል። 2,ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ በዚህ username- @zidni1 ብታቀርቡ። 3,መጀመር ላይ ከወሰንን ነገ እና ከነገ ወድያ ምዝገባ አድርገን ከ2ቀናት በኋላ ሰኞ የምንጀምር ይሆናል።(ክፍያ የለውም)
🎉الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي بِنِعْمَتِهِ تَتِمُّ الصَّالِحَاتُ ✨አልሃምዱሊላህ! ✨አልሃምዱሊላህ! ✨አልሃምዱሊላህ! «ድብቁ ገዳይ እና የተስፋው ጋሻ»! ~ ተለቀቀ~ ሰው ነኝና ከስህተት ከጥፋት አልጠራም እርምት እና አስተያየት ካላችሁ በዚህ ንገሩኝ @Abu_Hulud22 ሚስኪኑ ወንድማችሁ ⎛አቡ ሑሉድ.⎫
без подписи
"aselamu aleykum werahmetulahi weberekatuhu ustaz endet neh 1 neger laschegrk neber yehone masreja liteyikh Yehonu lijochin film atiyu biye simekrachew le haraminetu masreja amta alugn ine demo ke gudatu antsar endemaychal new yesemahut so masrejawn ke kuran weyim ke hadith bitsetegn" ከቁርኣን... 1,{قُل لِّلْمُؤْمِنِينَ يَغُضُّوا مِنْ أَبْصَارِهِمْ وَيَحْفَظُوا فُرُوجَهُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَزْكَىٰ لَهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا يَصْنَعُونَ(٣٠){وَقُل لِلمُؤْمِنَات يَغْضُضْنَ مِنْ أَبْصَارِهِنَّ ويَحفظْن فروجَهن...(٣١)سورة النور} 2,{...وَلَا تَقْرَبُوا الزِّنَا ۖ إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَسَاءَ سَبِيلًا }(32 :الإسراء) "And do not go near adultery" 3,"{...وَلَا تَقْرَبُوا الْفَوَاحِشَ...}" "And do not approach shameful deeds"(الأنعام:151) ከሐዲث... 4,"لاَ ينظرُ الرَّجلُ إلى عورةِ الرَّجلِ ولاَ تنظرُ المرأةُ إلى عورةِ المرأةِ..."أخرجه مسلم وغيره 5,"فالعينانِ تَزنيانِ وزناهُما النَّظرُ، والأذنانِ تَزنيانِ وزناهُما الاستِماعُ، واللِّسانُ يَزني وزناهُ الكَلامُ، واليدُ تَزني وزناها البَطشُ، والرِّجلُ تَزني وزناها الخُطا، والقلبُ يهوَى ويَتمنَّى، ويُصدِّقُ ذلِكَ الفرجُ أو يُكَذِّبُهُ"...متفق عليه 6,سمعت رسول الله ﷺ يقول: «وَيْلٌ لِلَّذِي يُحَدِّثُ بِالحَدِيثِ لِيُضْحِكَ بِهِ القَوْمَ فَيَكْذِبُ، وَيْلٌ لَهُ! وَيْلٌ لَهُ!» (رواه الترمذي) 7,"مَنْ أَشارَ إلى أخِيهِ بحَدِيدَةٍ، فإنَّ المَلائِكَةَ تَلْعَنُهُ، حتَّى يَدَعَهُ، وإنْ كانَ أخاهُ لأَبِيهِ وأُمِّهِ" 8,"مَن رأى منكم منكراً فليغيِّره بيده، فإن لم يستطع فبلسانه، فإن لم يستطع فبقلبه، وذلك أضعف الإيمان" Watching movies excessively can lead to a sedentary lifestyle, social isolation, and sleep disruptions. It often fosters unrealistic expectations about relationships and life, and wastes valuable time that could be spent on productive, creative, or physical activities. Physical & Mental Health Drawbacks Sedentary Lifestyle: Prolonged sitting increases the risk of obesity, cardiovascular issues, and poor posture. Sleep Disruption: Watching movies right before bed exposes the brain to blue light and emotional stimulation, which ruins sleep quality. Desensitization to Violence: Frequent exposure to on-screen violence can desensitize viewers and potentially increase aggressive behavior, particularly in younger audiences
Congratulations ለግቢያችን ሙስሊም ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ...እንኳን ደስ አላቹ!!! የዘንድሮው ደግሞ በዓሹራእ-አላህ ነብዩሏሂ ሙሳን ከፊርዐውን እና ከግብረ አበሮቹ ግፍ ነፃ ባወጣበት ቀን ነው እናንተንም ነፃ ያወጣቹ። እራሳችሁን እና መላ ሙስሊሙን አላህ በሚወደው መልኩ የምትጠቅሙ ያድርጋችሁ።የዱንያ ጀነት የሆነ የዘዋጅ ህይወትንም አላህ ይወፍቃቹ።....በድጋሚ እንኳን ደስ አላቹ!!!
የዐሹራእን ፆም የሚመለከቱ ጥቂት ነጥቦች ~ ያለንበት ወር የሙሐረም ወር ነው፡፡ ሙሐረም በሂጅራው አቆጣጠር የአመቱ መጀመሪያ ወር ነው፡፡ በዚህ ወር ውስጥ የሚገኘውን የዓሹራእን ቀን የሚመለከቱ ኢስላማዊ ስርኣቶች አሉና ጥቂት እንተዋወስ 1. በመጀመሪያ ወሩ ታላቅና የተከበረ ወር ነው ነው፡፡ [ተውባህ፡ 36] ነብዩም ﷺ እንዲህ ብለዋል፡ “አንድ አመት 12 ወር ነው፡፡ ከነዚህ ውስጥ አራቱ የተከበሩ ናቸው፡፡ (ከተከበሩት ውስጥ) ሶስቱ ተከታታይ ናቸው፡፡ ዙልቀዕዳህ፣ ዙልሒጃህ፣ ሙሐረም እና በጁማዳ እና በሸዕባን መካከል ያለው የሙደር ረጀብ ነው፡፡" [ቡኻሪ፡ 2958] 2. ሙሐረም ወርን መፆም እጅግ የላቀ ዋጋ አለው፡፡ ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡ “ከረመዳን ቀጥሎ ከሁሉም በላጩ ፆም የአላህ ወር የሆነው ሙሐረም ነው፡፡” [ሙስሊም፡ 1163] ልብ በሉ! ሁሉም ወሮች የአላህ ሆነው ሳለ ነብዩ ﷺ ሙሐረምን “የአላህ ወር” ሲሉ መጥራታቸው ወሩ ያለውን ልዩ ደረጃ ያመላክታል፡፡ ልክ ሁሉም መስጂዶች የአላህ ቤቶች ሆነው ሳለ ከዕባ ለየት ባለ መልኩ “የአላህ ቤት” እንደሚባለው ማለት ነው፡፡ 3. በዚህ ወር ውስጥ ታላቅ ቀን አለ፡፡ እሱም ሙሐረም 10 ነው፡፡ “ዓሹራእ” በመባል ይታወቃል፡፡ የአላህ መልእክተኛ ﷺ ከመካ ወደ መዲና ሲገቡ የሁዶች ዓሹራእን ይፆሙ ነበርና “ምንድን ነው ይሄ የምትፆሙት ቀን?” ሲሉ ጠየቋቸው፡፡ እነሱም “ይሄ አላህ ሙሳንና ህዝቦቹን አትርፎ ፊርዐውንና ህዝቦቹን ያሰመጠበት ታላቅ ቀን ነው፡፡ ሙሳ አላህን ለማመስገን ሲሉ ፆመውታል፡፡ እና እኛም እንፆመዋለን” አሉ፡፡ ነብያችን ﷺ ይህን ጊዜ “ከናንተ ይልቅ እኛ ለሙሳ የተገባን ነን” በማለት ፆሙት፡፡ እንዲፆምም አዘዙ፡፡ [ቡኻሪ፡ 2004] [ሙስሊም፡ 1130] 4. ይህን ቀን፣ ማለትም ሙሐረም አስርን መፆም እጅግ የላቀ ዋጋ አለው፡፡ ያለፈውን አንድ አመት ወንጀል እንደሚያሚያሳብስ ነብያችን ﷺ ተናግረዋል፡፡ [ሙስሊም] 5. ይህን ቀን (ሙሐረም አስርን) ለመፆም ከወሰንን ዘጠነኛውንም ጨምረን ብንፆም የተወደደ ነው፡፡ ምክንያቱም ነብዩ ﷺ “ለቀጣይ (አመት) ከቆየሁ በርግጥም ዘጠነኛውንም እፆማለሁ” ብለዋልና። [ሙስሊም፡ 1134] 6. በነገራችን ላይ ዓሹራእን የመካ ሙሽሪኮችም ይፆሙት ነበር፡፡ ነብያችንም ﷺ ገና ወደ መዲና ሳይሰደዱ በፊት መካ እያሉ ይፆሙት ነበር፡፡ የረመዳን ፆም ከመደንገጉ በፊት ዓሹራእን መፆም በሙስሊሞች ላይ ግዴታ ነበር፡፡ እነኚህን እውነታዎች የሚያመላክተው እናታችን ዓኢሻህ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ስትል የተናገረችው ነው፡- “ዓሹራእ ቁረይሾች በዘመነ ጃሂሊያ (በጨለማው ዘመን) ይፆሙት የነበረ ቀን ነው፡፡ ነብዩም ﷺ ይፆሙት ነበር፡፡ መዲና በመጡ ጊዜ እሳቸውም ፆሙት ሰዎችም እንዲፆሙት አዘዙ፡፡ የወርሃ ረመዳን ግዴታ በወረደ ጊዜ ግን ረመዳንን ሆነ (በግዴታነት) የሚፆሙት፡፡ ዓሹራእን እንዲፆም (ማዘዙን) ተውት፡፡ እናም የፈለገ ይፆመዋል የፈለገ ደግሞ ይቶወዋል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] 7. ዓሹራእን እለቱን መፆም እንጂ በምንም መልኩ በዓል አድርጎ ማክበር አይፈቀድም፡፡ አቡ ሙሳ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዳስተላለፉት ዓሹራእን የሁዶች ይፆሙት ነበር፡፡ እንደ ዒድ ይቆጥሩት ነበር፡፡ ሴቶቻቸውንም ጌጦቻቸውንና ጥሩ ጥሩ ልብሶቻቸውን ያለብሷቸውም ነበር፡፡ ነብዩ ﷺ ግን “እናንተ ፁሙት” በማለት መፆም እንጂ እንደ ዒድ እንዳይታሰብ ጥቆማ ሰጥተዋል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] ማሳሰቢያ፦ ሙሐረም 9 እና 10 ነገ ረቡዕ እና ሃሙስ መሆኑን አውቀን ብንፆም እና ሰዎች እንዲፆሙት ብናስታውስ መልካም ነው። = (ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 17/2007) የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor
አላህ ባሪያውን በቂ አይደለምን? 📘 ቁርአን ሱረቱ አዝ-ዙመር 39፡36
без подписи
без подписи
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته Urgent notice for all jeme'a members... 1,ዛሬ(ሰኔ 12) በኢብኑ ዐባስ የጁሙዐ ሶላት በexit ፈተና ተፈታኞች ምክንያት ቀደም ተብሎ ስለሚጀመር በጊዜ ለመገኘት ብትሞክሩ። 2,የአመቱ የስንብት እና የውጤት ካርድ መስጫ ፕሮግራም በአላህ ፈቃድ ነገ(ቅዳሜ) ከ4:30-7:00 ስለሚሆን programኣቹን ይህንን ታሳቢ በማድረግ adjust እንድታደርጉ።ከፕሮግራሙ በፊት የግድ መውጣት ያለበት ካለ ዛሬ ማታ የውጤት ካርዱን አስቀድሞ አሳውቆ መውሰድ ይችላል። 3,ውጤቶቻችሁ እና ተያያዥ መረጃዎችን በተገቢው መልኩ ያልጨረሳቹ ዛሬ መስጅድ በመገኘት ብትጨርሱ:ባረከሏሁ ፊኩም።
без подписи
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته በዝናብ ምክንያት የዛሬው(እሮብ ጠዋት)የተንቢሀት ደርስ ወደ ነገ ተቀይሯል።