tgindex
የለተሞ መንጋን በመረጃ ማፈራረስ

የለተሞ መንጋን በመረጃ ማፈራረስ

Статистика

የለተሞ መንጋን ማፈራረስ ሲባል የተፈራረሰውን ግልፅ ማድረግን ነው የተፈለገበት በአሏህ ፍቃድ የመንሀጅ ስህተቶቻቸውን በመረጃ ግልፅ እናደርጋለን በአላህ ፍቃድ።

Последний пост
10 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
4 677
−3 за 4 дн.
Сутки
+2
+0,04%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
4 262
20 постов
Вовлечённость
91,1%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
4
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1 970
1/48двое суток
2 257
1/72трое суток
2 434

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 10 авг.1 226249

    👁

  • 7 авг.2 5926723

    የለተሞ ጀመዓዎች "የሲም ካርድ" ደሩራ እና የሚሊዮኖች ሐራም! ዛሬ ደግሞ የለተሞ ጀመዓዎችን አስቂኝ "ሚዛን" እና ድርብ ማንነት የሚያሳይ አንድ ገራሚ ገጠመኝ ላካፍላችሁ። ታሪኩ እንዲህ ነው፡- አንዱ አክራሪ የለተሞ ጀመዓ ባለበት ወረዳ የመጅሊስ አባል ሆኖ ያገለግላል። በዚያውም በአንዲት የገጠር መስጂድ ውስጥ የኮሚቴ አባል ነው። ለራሱ መተዳደሪያ ደግሞ ስልክ ቤት አለው፤ ሲም ካርድም ይቸረችራል። ጉዱ የሚጀምረው እዚህ ጋር ነው፦ አንዳንድ በጎ አድራጊዎች (አህለል ኸይሮች) መጥተው "ይህችን ደሳሳ መስጂድ በዘመናዊ መልኩ እንገንባላችሁ፤ ነገር ግን ያስገነባው አካል መስጂዱ መገንባቱን የሚያሳይ የፎቶ ወይም የቪዲዮ መረጃ ይፈልጋል" አሏቸው። የእኛ "አክራሪ" ኮሚቴ ግን ምን ቢል ጥሩ ነው? "ኧረ ሱራ (ፎቶ) ሐራም ነው! በፍጹም አይቻልም!" ብሎ ሚሊዮኖች የሚፈጅባትን መስጂድ ግንባታ አገደ። 🤦‍♂️ የሚገርመው ግን ይህ "ሐራም ነው" ባይ ጎበዝ፣ ቀኑን ሙሉ በስልክ ቤቱ ወንድ ሴት ሳይል ፎቶ እያነሳ ሲም ካርድ ሲቸርችር ይውላል! "ምነው ሐራም አይደለም እንዴ?" ሲባል ደግሞ መልሱ ዝግጁ ናት፦ "ይህ እኮ ደሩራ (አስገዳጅ ሁኔታ) ነው!" ይላችኋል። ለመሆኑ የለተሞ ጀመዓዎች ሚዛን እንዲህ ነው እንዴ? - አንዲት ሲም ካርድ በ15 ብር ትርፍ ለመሸጥ ፎቶ መነሳቱ "ደሩራ" ይሆናል? - በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ወጥቶበት የሙስሊሙ ማህበረሰብ የሚገለገልበት መስጂድ ግንባታ ግን "ሐራም" ይሆናል? ለካስ "ደሩራ" ማለት ለራሳቸው ኪስ ሲሆን ብቻ ነው! ኪሳቸው ሲነካ ሐራሙ "ደሩራ" ይሆናል፤ የህዝብ ጥቅም ሲመጣ ግን ሐራሙ "ተቅዋ" ይለብሳል። https://t.me/Menhaje_Selef/

  • 7 авг.2 2224030

    በአዲስ አበባ በተለይም በስልጤ ሰፈር የፉርቃን መስጂድ አካባቢ የነበሩ የሸይኽ የሕያ አል-ሃጁሪይ ተከታዮችን ታሪክ ለሚያስታውስ ሰው፣ የዛሬው የለተሞ ጀመዓዎች ጉዞ የት እንደሚያበቃ ለመረዳት አያዳግተውም። ጽንፈኝነትና ማክረር መጨረሻው መላላትና ወደ ነበሩበት መመለስ መሆኑን እነዚህ ሁለት ጀመዓዎች ትልቅ ማሳያ ናቸው። የሃጁሪይ ጀመዓዎች ትላንት ምን ይመስሉ ነበር? 1. ሱሪ የለበሰን ሁሉ "ጀምዕይ" ብለው ይፈርጁ ነበር። 2. ከእነሱ ጋር የማይማርንና የማያውቁትን ሰው ሁሉ በጀምዕይነት ያጥላሉ ነበር። 3. ልጆችን አካዳሚክ ትምህርት ማስተማር እንደ ትልቅ ጥፋት (ጀምዕይነት) ይታይ ነበር። 4. በመስጂድ ውስጥ የሶፍ መስመር ማስመር አይቻልም ብለው ይከራከሩ ነበር። 5. "ጀምዕይ" ለሚሉት ሰው ሰላምታ ማቅረብም ሆነ የቀረበላቸውን ሰላምታ በስርዓቱ መመለስ አይፈቅዱም ነበር። 6. ልዩ መለያቸው የየመናውያን ጥምጣም መጠምጠም እና ከጀለቢያ ስር ሸርጥ ማሰር ነበር። 7. በሄዱበት ሁሉ የስለፊያ ስም በስድብና ሰዎችን በማነወር ያጠለሹ ነበር። 8. ከአፋቸው "ጀምዕይ" እና "ሒዝብይ" የሚሉ ቃላት አይጠፉም ነበር። 9. አረማመዳቸው መንጠር ያለበት፣ ቁመናቸው ኮስታራና ድንፋታም፣ ንግግራቸው ደግሞ ስርዓተ-ቢስነት የሚታይበት ነበር። ዛሬ ግን ምን ላይ ደረሱ? ጊዜ ሁሉንም ነገር አስተካክሎታል። ያ ሁሉ ጩኸትና ማክረር ዛሬ የለም። አሁን ላይ ሱሪ መልበስ ችግር የለውም፤ የጀምዕይ ፍረጃው ቀንሷል፤ ልጆቻቸውን በKG እና በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ለማስመዝገብ ሲጋፉ ይታያሉ፤ በፉርቃን መስጂድ የሶፍ መስመር አስምረዋል፤ ለሁሉም ሙስሊም ሞቅ ያለ ሰላምታ ያቀርባሉ፤ ያ የጥምጣምና የሸርጥ መለያቸውም እየጠፋ መጥቷል፤ በአጭሩ ያንን ሁሉ ማክረር ትተው ወደ መረጋጋትና ወደ መስተካከል ተመልሰዋል። የዛሬው የለተሞ ጀመዓዎችስ? ዛሬ በለተሞ ጀመዓዎች ዘንድ የሚታየው ድንፋታ፣ ጉራ፣ ውሸት፣ ስድብና የተብዲዕ ፍረጃ (ሰውን ከዲን ማውጣት) የትላንቱ የሃጁሪዮች ግልባጭ ነው። ከእነሱ ያልሆነን ሁሉ በ"ሙመይዕነት" መፈረጅና ማግለል የጊዜ ጉዳይ እንጂ እንደ ቀደሞቹ ይበርድላቸዋል። ታላቁ ነቢያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- لن يشاد الدين أحد إلا غلبه "ማንም ዲኑን አያከርም (አያጠብቅም)፤ ዲኑ ቢያሸንፈው እንጂ።" ይህ የነቢዩ ﷺ ንግግር ትልቅ ትምህርት አለው። ዲን በባህሪው መካከለኛነትን እንጂ ማክረርን አይቀበልም። በትላንቱ የሃጁሪይ ጀመዓዎች ላይ የታየው ለውጥ ዛሬ በሚያክሩት የለተሞ ጀመዓዎች ላይ መከሰቱ የማይቀር ነው። ዋናው ቁምነገር ግን ከታሪክ መማርና ከመጀመሪያውኑ በመካከለኛው መንገድ (ወሰጥያህ) ላይ መጓዝ ነው። አላህ ቀጥተኛውን መንገድ ይምራን። https://t.me/Menhaje_Selef/

  • 7 авг.2 2765618

    የለተሞ ጀመዓዎች ሰለፊዮች ጋር ሲመጡ አይናቸው ይቀላል እንጂ ለራሳቸው ጥቅም ሲሆን ፦ 1/ ማንነቱ ደብቆ ሙብተዲዕ በሚለው ሠው ደሞዝ እየተከፈለው በየገጠሩ በኡስታዝነት ገብቶ ያገለግላል። ወይም መርከዝ ከፍቶ ቡድኑ ያስለጥናል። 2/ ለራሱ በርካታ ወረዳዎች ላይ መጅሊስ ውስጥ ገብቶ ያገለግላል። ሌላው ከገባ ....... ። 3/ ለራሱ ባንክ ተቀጥሮ ይሰራል ለሌላው ከሆነ ግን ..... 4/ በህግ ሙያ ተመርቆ ፍርድ ቤት ላይ በጠበቃነት ወይም አቃቢ ህግ ሆኖ ያገለግላል ለሌላው ከሆነ ግን ...... 5/ ከነሱ ውስጥ ለብልፅግና ምርጫ ቅስቀሳ ሁላ ሲያደርግ የነበር አለ ሌላው ቢሆን ግን ...... ለማንኛውም እውነትም " የሚጮሁትን የማይኖሩ ጉዶች " ናቸው ።

  • 7 авг.1 616505

    የለተሞ ጀመዓ ጊዜያዊ ግርግርና እልህ ብዙም አይድነቃችሁ ! እስከሚበርድላቸው ነው። ድንበር አላፊነት በባህሪው ትጋት አለው ። እንኳን እነሱ አዲስ አበባ ያሉት የሸይህ የህያ አል-ሃጁሪይ ተማሪዎችም ዛሬ ከ 20 አመት በኋላ በርዶላቸዋል ።

  • 7 авг.1 979367

    የለተሞ ጀመዓ የሚጠቀምብህ ከሆነ ከአህባሽ ጋር እንኳን ቢሆን ይሰራሉ።

  • 3 авг.4 8933530

    ✅ ሸይኽ የሕያ & ሸይኽ ዓብዱ! ዛሬ ሸይኽ ዓብዱል ሐሚድ አል'ለተሚይ - هداه الله - ይዞት የመጣው "በኢጅቲሃጃዊ ነጥብ የተቃረነውን አካል ኢልዛም" የማድረግ አዲስ ቢድዓ ትላንት የሕያ አልሐጁሪይ -هداه الله- ተብዲዕ ከተደረገባቸው ቢድዓዎች ውስጥ አንዱና ዋነኛው ነው። ያያዝኩት የድምፅ ፋይል ታላቁ ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዓብዲልወሃብ አል'ወሷቢይ -رحمه الله- ስለ የሕያ አል'ሐጁሪያ ተጠይቀው የመለሱበት ነው። ከንግግራቸው ውስጥ የሚከተውን ትኩረት ሰጥታቹህ አንብቡት አድምጡትም ባረከላሁ ፊኩም። 01:23 ➡️ 03:50 "فهُو ابتدعَ في الدِّين بدعًا كثيرة؛ ومنها على سبيل المثال وليس الحصر: إذا اختلف مع شخص في مسألةٍ اجتهاديّةٍ في مثل الشّيخ عبد الرّحمن العدني هل هُو حزبيّ أم لا؟! هُو يقول بأنّه حزبيّ! وبقيّة المشايخ من أهل السُّنّة والجماعة قالوا: بل هُو سُنِّي وليس بِحِزْبي، فانظُروا ماذا فعل مع المشايخ بدّع وضلّل وفسّق وقاطع وهَجَر وأمر طُلاّبه بالهجر وأنزلُوا الملازِمَ الكثيرة والأشرطة الكثيرة؛ نقول له: يا هذا هذه مسألة اجتهاديّة ما هي نصيّة، ما في وحي ينزل لنا فُلان حزبِي! أنتَ اجتهدتَّ هذا إذا أُحْسِنَ بك الظّنّ أنّك قُلت هذا عن اجتهادٍ! إن لم تُكن قُلتَه عن هوى! لِنفرض أنّك اجتهدتَّ وغيرُك اجتهد قال: ما هُو حزبي، المسائل الاجتهاديّة ما يجوز التّضليل فيها والتّبديع والتّحزيب والتّفسيق والتّفجير أنّهُم فَجَرَة أنّهُم فَسَقَة وأنّهُم مَكَرة وأنّهُم خونة... مسألة اجتهاديّة وسِّع بالَك، فهُو شرّع هذه البدعة الخبيثة الهجر والمُقاطعة والمُدابرة وعدم السّلام والكلام ولو كان لِسنين طويلة من أجل مسألة اجتهاديّة!  عليهِ أن يتُوبَ إلى الله عزّ وجلّ من هذه البِدعة التي هِي بدعة ضلالة وتُعتَبر من الكبائر أنّه ضلّل؛ لو فَعَل هذا العُلماء! لو فعل هذا السّلف الصّالح! لو فعل هذا الأئمّة الأربعة ما بَقِيَ مودّة بين مُسْلِمَيْن؛ هذا يرى كذا وهذا يرى خلاف ذلك ومُقاطعة ومُهاجرة؛ لم تبقى مودّة بين اثنين! لهذا قُلنا: بأنّها بدعة" 📝 ትርጉም፦ "እርሱ (የሕያ አልሐጁሪይ) በዲን ውስጥ ብዙ ቢድዓዎችን ፈብርኳል። ከእነዚህም መካከል ለምሳሌ እንጂ ሁሉን ለመዘርዘር ሳይሆን፦ በአንድ ኢጅቲሃዳዊ ጉዳይ ላይ ከሌላ ሰው ጋር ሲለያይ፣ ለምሳሌ፦ "ሸይኽ ዐብዱረሕማን አልዐደኒ ሒዝቢይ ናቸው ወይስ አይደሉም?" በሚለው ጉዳይ፤ እርሱ "ሒዝቢይ ናቸው" አለ፤ ሌሎች የሱና መሻኢኾች ደግሞ "አይደሉም፤ ሱንይ ናቸው" አሉ። እንግዲህ ከዚያ በኋላ ከመሻኢኾች ጋር ያደረገውን ተመልከቱ፤ አንዳንዶቹን ሙብተዲዕ አላቸው፣ አንዳንዶቹን ጠማማ አላቸው፣ ሌሎችን ፋሲቅ አላቸው፣ ከእነርሱም ራሱን አራቀ፣ ተማሪዎቹንም እንዲርቋቸው አዘዘ፤ ብዙ ኢልዛማቶችን አወረዱ፣ ብዙ የድምፅ ቅጂዎችም ተለቀቁ። እኛ ግን እንለዋለን፦ "አንተ! ይህ ኢጅቲሃዳዊ ጉዳይ ነው፤ በቁርጥ ነስ (ግልጽ የቁርኣንና የሐዲስ ማስረጃ) የመጣበት አይደለም። ከሰማይ ወሕይ ወርዶ "እገሌ ሒዝቢይ ነው" ብሎ አይነግረንም። አንተ በኢጅቲሃድህ እንዲህ አልክ፤ - ይህም ስለ አንተ መልካም ግምት ብናደርግና በስሜት ሳይሆን በኢጅቲሃድ ብቻ ተናግረሃል ብለን ካልን ነው -  ሌላው ደግሞ በኢጅቲሃዱ "ሒዝቢይ አይደለም" አለ።" እንደዚህ ባሉ ኢጅቲሃዳዊ ጉዳዮች ሰዎችን ማጥመም፣ የቢድዓ ባለቤት ማለት፣ ሒዝቢይ ማለት፣ ፋሲቅ ማለት፣ "ፋጅር ናቸው፣ ሴሬኞች ናቸው፣ ከዳተኞች ናቸው፣ አታላዮች ናቸው…" እያሉ መፍረድ አይፈቀድም። ኢጅቲሃዳዊ ጉዳይ ነው። ልብህን ሰፋ አድርገው። ይህ (የሕያ አልሐጁሪይ) ይህችን ፀያፍ ቢድዓ መንገድ አደረገ። ማኩረፍ፣ መቋረጥ፣ ጀርባ መሰጣጠት፣ ለብዙ ዓመታት እንኳ ሰላም አለመባባል፣ ንግግርን መተውንና ግንኙነትን ማቋረጥን እንደ ሃይማኖታዊ መርህ አድርጓል። ከዚች ቢድዓ ወደ አላህ ሊመለስና ሊጸጸት ይገባዋል፤ ምክንያቱም ይህ ጥመት ቢድዓ ሲሆን፣ ሰዎችን ያለ ትክክለኛ ማስረጃ ማጥመም ከታላላቅ ኃጢአቶችም አንዱ ነው። በእርግጥ ዑለማዎች፣ መልካም ቀደምቶች፣ አራቱ የፊቅህ ኢማሞች እንዲህ ቢያደርጉ ኖሮ፣ በሁለት ሙስሊሞች መካከል ፍቅርና ወንድማማችነት ባልቀረ ነበር። ይህ አንድን አቋም ይይዛል፣ ያ ደግሞ በተቃራኒው ይላል፤ ከዚያም መቋረጥና መራራቅ ይጀምራል፤ በመጨረሻም በሁለት ሰዎች መካከል ፍቅር አይቀጥልም ነበር። ለዚያም ነው ይህችን ቢድዓ ነች ያልነው።" ✅ ጥያቄ ለለተሞ ተከታዮች፦ ✈️ በተወሳው ነጥብ ሸይኽ የሕያ አልሐጁሪይ እና ሸይኽ ዓብዱ ልሐሚድ አልለተሚይ ልዩነታቸው ምንድነው? ሸይኽ የሕያ ሸይኽ ዓብዱረሕማንን ተብዲዕ በማድረግ ኢልዛም እንዳደረገው ሁሉ ሸይኽ ዓብዱ ልሐሚድም ሸይኽ ኢልያስንና መሰል ሰዎችን ተብዲዕ በማድረግ ኢልዛም ያደርጋል። እና የሰዎች መለያየት የነገሩን ቢድዓነት ያስወግዳልን? ✈️ ሸይኽ ዓብዱል ሐሚድ የተብዲዕ ጉዳይ ኢጅቲሃጅን አያስተናግድም የሚል አቋም እንዳላቸው ይታወቃል። ዑለማኡ ሱና ደግሞ ከእርሱ በተቃራኒ ናቸው። t.me/Abu_lmran_Alaseriy/3616 እና በዚህ ነጥብ ማነው መንገድ የሳተው ሸይኻቹህ ወይስ እነዚህ ታላላቅ የሱና ዑለማኦች? ✈️ የዚህ አይነት ፍንትው ያለ ጉዳይ ሲደርሳቹህ ቆም ብላቹህ ከማሰብና ማስረጃን ከመመልከት ይልቅ "በምን መልኩ መልስ ልስጠው?" ብላቹህ መጨነቅና መጠበብ ቢቀርባቹህ አይሻል ወይ? ለመሆኑ እስከመቸ ነው ይህ የለተሞ ሸይኽ በጎተታቹህ እየተጎተታቹህ ከማስረጃ ተጣልታቹህ ከሱና ዑለማእ ተቃርናቹህ የምትቀጥሉት? ብሽሽቅና ነቆራውን ትታቹህ ሳይመሽባቹህ ወደ ሩሽዳቹህ ብትመለሱ፣ ከእንቅልፋቹህ ብትነቁ አይሻልም? ብዥታስ ካለ በውይይት መፍታትና ሐቅ ወዳለበት ሁኖ በእውነት ላይ መሰባሰብ አይሻልም? ተው ልብ ግዙ ወንድሞቸ! አላህ ልቦና ይስጣቹህ ይስጠን። = የቴሌግራም ቻናል t.me/Abu_lmran_Alaseriy t.me/Abu_lmran_Alaseriy

  • 30 июн.4 9932614

    https://youtu.be/PI0OY5xf-i8?si=hTqAq6876GWIZHB_

  • 30 июн.5 3749

    без подписи

  • 30 июн.5 320309

    የለተሞ አቋም እና የዑለማኦች ምስክርነት፡ ማን እንስማ? የለተሞ ሼህ በታላቁ ዓሊም በሸይኽ ዶ/ር ኢብራሂም አር-ሩሐይሊ ላይ የስድብ እና የተብዲዕ ዘመቻ ሲከፍቱ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሳሊሕ አስ-ሱሐይሚ (አላህ ይጠብቃቸው) አብረዋቸው ፕሮግራም ላይ በመገኘት እሳቸውን በአድናቆት ይገልጻሉ። ሸይኽ ሳሊሕ አስ-ሱሐይሚ በወቅቱ የሰጡት ምስክርነት ይህን ይመስላል፡- > "ወንድሜ ሸይኽ ዶ/ር ኢብራሂም ቢን ዓሚር አር-ሩሐይሊን በዚህ ጠቃሚና መልካም ትምህርት (ሙሓደራ) አላህ ምንዳውን ይክፈለው። ወንድሜን አላህ ይወፍቀውና ለዚህ የተባረከ ዝግጅት መልካም ምንዳውን ይክፈለው። እንደዚሁም ለዚህ የተባረከ፣ ደስ የሚል እና ጥሩ አቀራረብ አላህ መልካሙን ምንዳ ይክፈለው። ይሄን ሃሳብ ወደ ኪታብ (መጽሐፍ) እንዲያሰፋው እጠይቃለሁ፤ ኢንሻ አላህ ወደፊት የዕውቀት ፈላጊዎች ይጠቀሙበታል። እንደለመድነውም በሌሎች መጽሐፎቻቸው ላይ እንደምናየው ማለት ነው። ይህ የተባረከ ሥራ ነው፤ የዕውቀት ፈላጊዎች እና በመላው ዓለም ያሉ ሙስሊሞች እንዲጠቀሙበት ታትሞ መውጣት የሚገባው ነው።" መደምደሚያ፡ እንግዲህ አንዱ ዓሊም "የዕውቀት ፈላጊዎች ይጠቀሙበት" ብለው መጽሐፍ እንዲሆን ሲመክሩ፣ ሌላው ደግሞ በስድብ እና በተብዲዕ ሲያግዱ እናያለን። በዚህ መሃል ተጠያቂው ማነው? የለተሞን የጥላቻ ንግግር እንስማ ወይስ የዑለማኦችን የዕውቀት ምስክርነት? አንድ ጥንታዊ ብሂል እንደሚለው፡ "ተናጋሪው ቢያብድ አድማጭ ጤናማ መሆን አለበት።"

  • 29 июн.4 166299

    የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ مَن قال في مؤمنٍ ما ليس فيهِ؛ أسكنَهُ اللهُ رَدغةَ الخَبالِ، حتى يخرُجَ ممَّا قالَ "በሙዕሚን ላይ የሌለበትን የተናገረበት ሰው፤ ከተናገረው ነገር እስካልወጣ ድረስ አላህ ከጀሃነም ሰዎች አካል በሚወጣ የእዥና የመ^ግል አረንቋ ውስጥ ያኖረዋል።" [ሶሒሑ ተርጊብ፡ 2845] = የቴሌግራም ቻናል :- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

  • 28 июн.4 0885760

    በድምፅ በነገራችን ላይ ለተሞ የሚመጥነው ከሙስጠፉ ጋር ሲጠዛጠዙ ነው ። የለተሞ አቻ ተሳዳቢ ሙስጠፋ መሆኑን አድምጡ ። ___ ልብ በሉ እያነፃፀርን ያለነው የስድብ ብቃታቸው ብቻ ነው :: ሌላ ጉዳያቸው ዑለማኦች የሚፈርዱ ይሆናል ።

  • 28 июн.4 3973737

    በነገራችን ላይ ለተሞ የሚመጥነው ከሙስጠፉ ጋር ሲጠዛጠዙ ነው ። የለተሞ አቻ ተሳዳቢ ሙስጠፋ መሆኑን አድምጡ ።

  • 27 июн.4 7301773

    በነገራችን ላይ ለተሞ የሚመጥነው ከሙስጠፉ ጋር ሲጠዛጠዙ ነው ። የለተሞ አቻ ተሳዳቢ ሙስጠፋ መሆኑን ላስደምጣችሁ ?

  • 26 июн.5 5659745

    "ለተሞ" (የለተሞ ሼህ) አሊም ነው ለምትሉ :- በአቋማቸው ላይ ትችት ሲቀርብ "ዓሊም እኮ ነው" የምትሉ ወገኖች የሚከተሉትን ነጥቦች በገለልተኝነት እንድትመረምሩ እንጋብዛለን፦ 1. የዓሊምነት ማረጋገጫ፡ የዚህ ግለሰብን የዓሊምነት ደረጃ የመሰከረላቸው ታዋቂ ዑለማኦች ማን ናቸው? ስማቸውን እና ምስክርነታቸውን ማቅረብ ትችላላችሁ? 2. የኢብኑ ዑሰይሚን ተማሪነት፡ እውነትም የሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን ተማሪ ከሆኑ፣ ከሸይኹ የተሰጠ ኢጃዛ፣ ተዝኪያ፣ ወይም ቢያንስ አብረዋቸው ሲቀሩ የነበሩ የሸይኹ ሌሎች ተማሪዎች ስለ እሳቸው የሰጡትን ምስክርነት ማቅረብ ይቻላል? 3. የኢኽዋንነት ታሪክ፡ ከኢብኑ ዑሰይሚን ዘንድ ተምረው ከተመለሱ በኋላ ለምን በቀጥታ ከኢኽዋኖች ጋር ተቀላቀሉ? ኢብኑ ዑሰይሚን ያስተማሯቸው የኢኽዋንነት መንገድ ነበር ወይስ በሂደት ነው የተለወጡት? 4. ከስህተት መከላከል፡ እንደምትሉት ዓሊምነት ከስህተት የሚጠብቅ ከሆነ፣ ትላንት በኢኽዋንነት መንገድ ላይ በነበሩበት ጊዜ፣ ያኔ ኢኽዋን ሲሆኑ ዓሊም አልነበሩም ወይ? 5. የመማር ቅደም ተከተል፡ ከኢኽዋንነት ወደ ሰለፊይነት ከተመለሱ በኋላ፣ የዳዕዋ መድረኮችን በመቆጣጠር እና የዳዕዋውን ሂደት በማወክ ፈንታ፤ በመጀመሪያ ሰለፊይነትን ቁጭ ብሎ መማር እና እውቀትን መገበይ አልነበረበትም? 6. የአደብ ጥያቄ፡ ከኢኽዋን የቢድዓ አረንቋ ለማውጣት የሰለፊይ ወንድሞች ከፍተኛ ዋጋ ከፍለው ነበር። ታዲያ ዛሬ ይህንን ሁሉ ጥረት ካደረጉ ወንድሞች ጋር መመካከር ሲገባ፣ እነሱኑ "ሙብተዲዕ" በማለት ማውገዝ ምን የሚሉት የሞራል ግድፈት ነው? ስለ እናንተ የሚነገረውና የሚወራው በከንቱ አይደለም፤ እባካችሁ ወደ ትክክለኛው መንገድ ተመለሱ። https://t.me/Menhaje_Selef/

  • 26 июн.7 3425223

    ለተሚዮች እነዚህ ቡድኖች የሚያራምዱት አካሄድ ለዳዕዋው አውዳሚ ነው። በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የሚገኙ ዑለማኦችን ሳይቀር በጅምላ በመፈረጅ እና በማጥላላት ይታወቃሉ። ከሀገር ውጪ ያሉት ዑለማኦች: የየመን መርከዞች እና የሀገሪቱ ዑለማኦች፣ እንዲሁም እንደ ሸይኽ አብዱረዛቅ በድር፣ ሸይኽ ሱለይማን አርሩሃይሊ፣ ሸይኽ አብዱልዓዚዝ አርረይስ፣ ሸይኽ አብዱልመሊክ አርረመዷኒ እና ሌሎች ታላላቅ ዑለማኦች ሳይቀሩ ከእነዚህ ቡድኖች ወቀሳ እና ዘመቻ አላመለጡም። በሀገር ውስጥ ያለው ሁኔታ: በሀገር ውስጥም የነሱን አስተሳሰብ የማይከተል እና አድናቂ ያልሆነ ማንኛውም ሰው፣ የዕውቀት ደረጃው ምንም ይሁን ምን "ሙብተዲዕ" ተብሎ ይፈረጃል። በየገጠሩ፣ የተውሂድ እና የሱና መሰረታዊ ነገሮችን በማስተማር ላይ ባሉ መስጂዶች እና መድረሳዎች በመሄድ፣ ስድብ እና የተብዲዕ ዘመቻ በመክፈት ብዙዎችን ከመስጂድ እንዲርቁ አድርገዋል። በስንት ትግል የተገነቡ የዳዕዋ ማዕከላትን እና ስብስቦችን በመበተን ለትልቅ የዳዕዋ ትርምስ ምክንያት ሆነዋል። https://t.me/Menhaje_Selef/

  • 26 июн.3 9885020

    የ"ለተሚዮች" (ለተሞ) ጀመዓ ምንነት ከዑለማኦች ጋር በቅርበት ስትውል ይበልጥ ግልጽ ይሆንልሃል። ወደ ሀገራችን የሚመጡ ታላላቅ ዑለማኦች ይህንን ቡድን በተመለከተ በአብዛኛው የሚሰጡት ምክር "ከነሱ ተቆጠቡ፣ በእነሱ ላይ ጊዜያችሁን አታባክኑ" የሚል ነው። ከእነዚህም መካከል፡- ሸይኽ ባሙሳ ሸይኽ ረሻድ ሸይኽ ኢብራሂም ሸይኽ ሱሃይሚ ሸይኽ ዓሊይ አርራዚሒ እና ሌሎችም የአለማችን የዕውቀት እንቁዎች የሆኑ ዑለማኦች፣ ወደ ሀገራችን በመጡበት ወቅት ስለዚህ ቡድን ተጠይቀው ሲመልሱ፤ "ተውዋቸው፣ እንደነሱ እንዳትሆኑ " በማለት ይመክራሉ። https://t.me/Menhaje_Selef/

  • 20 июн.4 619571

    በቅርቡ በወሎ ኮምቦልቻ በተካሄደው ደውራ ላይ እጅግ በርካታ መሻይኾች እና የተለያዩ የሸሪዐ እውቀትን በመማር ላይ የተሰማሩ ደረሶች ተሰባስበው ነበር። ለኔ ከተሰጠው ትምህርት በላይ ስብስቡ በጣም ደስ ብሎኛል። የነሱም ደስታ ከፊታቸው የሚነበብ ነበር። ቁርጠኝነቱ ከቀጠለ በአሁኑ ሰዓት በየአካባቢው የምናየውን ከፍተኛ የአስተማሪ እጥረት በሆነ መጠን የሚቀርፍ ግዙፍ የዒልም ሰራዊት እየመጣ እንደሆነ ይሰማኛል፣ ኢንሻአላህ። አላህ ከክፉ ጠብቆ ለሃገር፣ ለወገን የሚጠቅሙ ያድርጋቸው። እንዲህ አይነት ፕሮግራሞች በየተወሰነ ጊዜ ቢደጋገሙ ጥሩ መነቃቃት ይፈጥራሉ። ጠንካራ ትስስር እንዲኖርም ያግዛሉ። = የቴሌግራም ቻናል :- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

  • 17 июн.7 8934348

    ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር የኢኽዋኖች የአንድነት ጥሪ በጥቃቅን ጉዳዮች አንለያይ!

  • 17 июн.5 9673115

    без подписи