tgindex
ሱናህ

ወንድማዊ ማስታወሻዎች።

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
798
−1 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
194
21 постов
Вовлечённость
24,3%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
20
1/48двое суток
22
1/72трое суток
24

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • 8 авг.80из abuhaddaf1

    видео или голосовое, без подписи

  • ኢማሙ አቡ ሐኒፋ ኑማን ኢብን ሳቢት በታላቋ የኢራቅ ከተማ ኩፋ ውስጥ የተወለዱት በሂጅራ አቆጣጠር በ80 ሒ. (በኡመውያው ኸሊፋ ዐብዱልማሊክ ኢብን መርዋን ዘመነ መንግሥት) ነው። ​የዕድሜያቸው የተወሰነ ክፍል ከሶሐባዎች (ከነቢዩ መሐመድ ሰ.ዐ.ወ  ባልደረቦች) ዘመን ጋር የተገናኘ ሲሆን፣ ታላቁን ሶሐቢ አነስ ኢብን ማሊክን (ረዲየላሁ ዐንሁ) በግዳድ አግኝተዋቸዋል፤ ከእርሳቸውም  ሐዲሶችን ሰምተዋል። ይህ ልዩ ዕድል ከታቢዒዎች አንጋፋ ሊቅ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል። ​ የአቡ ሐኒፋ መዝሀብ በአንድ ቀን ወይም በአንድ ሌሊት በድንገት የተፈጠረ አይደለም፤ በሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሂጅራ አጋማሽ ላይ በኩፋ እና በበግዳድ የምሁራን ሸንጎ ውስጥ ሥር የሰደደ የዕውቀት ማዕበል ነው። ኢማሙ አቡ ሐኒፋ የራሳቸውን ሐሳብ በብቸኝነት የጫኑ ሰው አይደሉም። ከሰላሳ በላይ ከሚሆኑ እጅግ ብቁ ተማሪዎቻቸው ጋር (እንደ አቡ ዩሱፍ፣ ሙሐመድ ኢብን አል-ሐሰን አሸይባኒ፣ ዙፈር እና ሌሎችም) አንድን የፊቅህ ጉዳይ (مسألة) ጠረጴዛ ላይ አቅርበው፣ ክርክር በማድረግ፣ ቁርአንንና ሐዲስን መሠረት በማድረግ፣ እንዲሁም የሰውን ልጅ አእምሮና ኑሮ ሁኔታ በማመዛዘን በጋራ ውሳኔ ላይ ይደርሱ ነበር። ጥያቄዎች ሲቀርቡ መጀመሪያ ከቁርአን፣ ካልተገኘ ከሰሂህ ሐዲስ፣ ከዚያም ከሶሐባዎች አባባል፣ በመጨረሻም የሕዝብን ጥቅም (ኢስቲሕሳን) እና ፍትሕን መሠረት አድርገው ህጎችን በዝርዝር ትንተና አደራጁ። ይህ  (የቡድን የዕውቀት ውቅያኖስ) በጊዜ ሂደት "የሐነፊ መዝሀብ" ተብሎ በዓለም ዙሪያ ተስፋፋ። ኢማሙ አቡ ሐኒፋ ዕዉቀታቸዉን በዋናነት ያስተላለፉት በትምህርት፣ በንግግር እና በተማሪዎቻቸው አማካይነት ቢሆንም፣ በብዕር የሠፈሩ ውድ ኪታቦችንም አበርክተዋል። ከእነዚህም መካከል፡ ​አል-ፊቅሁ አል-አክበር (الفقه الأكبر): በእስልምና እምነት (ዐቂዳ) እና በመሠረታዊ የተውሒድ ሐሳቦች ላይ ያተኮረ እጅግ ጥልቅ መጽሐፍ። ​አል-ዓሊም ወል-ሙተዐሊም (العالم والمتعلم): በዕውቀት ፈላጊና አስተማሪ መካከል በሚደረግ ጥልቅ ውይይት መልክ የተጻፈ። ​ (رسالة إلى البصري): በወቅቱ በነበሩ የሃይማኖት ፖለቲካዊ ውዝግቦች ዙሪያ የተጻፈ ደብዳቤ። ​ሙስነድ አቡ ሐኒፋ (مسند أبي حنيفة): ኢማሙ ከሰበሰቧቸው እና ካስተላለፏቸው የሐዲድ ስብስቦች የተወሰዱ ኪታቦች (በተማሪዎቻቸው የተጠናቀሩ)። ታላላቅ ሊቃውንት ስለ ኢማም አቡ ሐኒፋ የነበራቸው ምልከታ የዕውቀታቸውን ማማ በግልጽ ያሳያል። ​"ሰዎች በፊቅህ (በእስልምና ሕግ) ረገድ አቡ ሐኒፋን የተመረኮዙ (ጥገኛ) ናቸው።" "በፊቅህ ጥልቀት ከአቡ ሐኒፋ በላይ የተሰጠው ማንም የለም" ©ኢማም አል-ሻፊዒ (ረ) ​"አቡ ሐኒፋ በዘመኑ የምድር ሁሉ እጅግ አዋቂ ሰው ነበሩ። ከእርሳቸው በላይ የዕውቀት ጽዋን የተጎነጨ አላየሁም።" ©ዐብዱላህ ኢብን ሙባረክ ​ ​ኢማም ማሊክ የኢማም አቡ ሐኒፋን የዕውቀት ደረጃ እና ተናግሮ የማሳመን አቅም ሲገልጹ " አቡ ሀኒፍ ይህንን ምሰሶ  'ይህ እንጨት ወርቅ ነው' ቢልህ፣ በማስረጃና በምክንያት ሊያሳምንህ የሚችል አእምሮ ባለቤት ነው" ​አቡ ሐኒፋ ኑማን ኢብን ሳቢት (ረ) ሕይወታቸውን የጀመሩት በንግድ  ነበር። አባታቸው የሐር ንግድ ነጋዴ ነበሩ። ወጣቱ ኑማን የአባታቸውን ዱካ በመከተል በገበያ አደባባዮች ሲመላለስ፣ ንግዱን እንደ ገንዘብ ማግኛ ብቻ ሳይሆን እንደ ታማኝነት እና ፍትሕ መለኪያ አድርጎ ይመለከተው ነበር። ​በንግዱ ዓለም ውስጥ ታማኝነቱ፣ ፍትሐዊነቱ እና ሰብአዊነቱ ከወርቅ በላይ አብረቅራቂ ነበር። ለሽያጭ የሚያወጡትን ዕቃ ጉድለት ለገዢው ሳይደብቁ የሚገልጡ፣ የሚያሳዩት ቸርነት በዘመኑ የንግድ ማኅበረሰብ ውስጥ ተምሳሌት ሆኖ አለፈ። ንግድ ልባቸውን ግን አላረከሰውም፤ ​​ዕድሜው እየገፋ ሲሄድ የኑዕማን ልብ ወደ ታላቁ  የፊቅህ (የእስልምና ሕግጋት) ውቅያኖስ ገሰገሰ። በኩፋ መስጊዶች ውስጥ ተቀምጦ የእስልምናን መሠረቶች እየቀዳ፣ በዘመኑ የነበሩ ታላላቅ ሰሃቦችና ታቢዒዎች (ተከታዮች) ፊት ተንበርክኮ ተማረ። ​በልዩ የማስተዋል ችሎታቸው (ዘካዕ) እና  (ጥልቅ ማሰላሰል) ይታወቁ ነበር። የሐማድ ኢብን አቢ ሱለይማን የተባለውን ታላቅ ሊቅ  ሀለቃ ለረጅም ዓመታት አብረውት አሳለፉ። የሐማድ ከሞቱ በኋላም የኩፋ ሕዝብ በአንድ ድምፅ "የዚህች ከተማ የዕውቀት ሐኪም እና መሪ አንተ ነህ" ብሎ ማዕረጋቸውን ሰጣቸው። ​ኢማሙ አቡ ሐኒፋ የሰውን ልጅ አእምሮ በቁርዓንና በሐዲስ ማዕቀፍ ውስጥ በማስተሳሰር ረገድ ልዩ ምዕራፍ ከፈቱ። ጥያቄዎች ሲመጡባቸው በፍጥነት ከመፍረድ ይልቅ፣ የጉዳዩን ፍሬ ነገር፣ ዓላማ (መቃሲድ) እና ማኅበራዊ ዐውድ በጥልቀት ይመለከቱ ነበር። ​እርሳቸው የመሠረቱት የዕውቀት ትምህርት ቤት (አል-ረእይ እና አል-ቂያስ) በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን አፈራ። ከእነዚህም መካከል እንደ ኢማሙ አቡ ዩሱፍ እና ሙሐመድ ኢብን አል-ሐሰን አል-ሸይባኒ ያሉ ግዙፍ ምሁራን ወጥተው የኢማሙን አስተምህሮ ወደ አራቱ መዓዘን አዳረሱት። ዛሬም ድረስ በምድር ላይ ካሉት ሙስሊሞች ትልቁ ድርሻ የሚከተለው የሳቸዉን ፊቅህ መዝሀብ ነዉ:: ​እውነተኛ ሊቅ ለሥልጣንና ለቁሳቁስ አይንበረከክም፤ የኢማም አቡ ሐኒፋ ሕይወት የዚህ ፍጹም ማሳያ ነበረ። በወቅቱ በነበረው የዓባስዮች መንግሥት ዘመን፣ ከሊፋ አል-መንሱር "የቃዲዎች (የዳኞች) አለቃ ሁን" የሚለውን ታላቅ የመንግሥት ሹመት አቀረበላቸው። ​ነገር ግን ኢማሙ በታላቅ ጽናት "ለዚህ ቦታ ብቁ አይደለሁም" በማለት ፈቃደኛ አልሆኑም። ከሊፋው "ውሸቱን ነው" ሲል፣ ኢማሙ "እውነት እላለሁ፤ ውሸታም ከሆንኩ ደግሞ ውሸተኛ ሰው ዳኛ ለመሆን እንዴት ብቁ ይሆናል?" የሚል ጥልቅና የማይበገር መልስ ሰጡ። በዚህም ምክንያት በግፍ ተገርፈዋል፣ ከወህኒም ወህኒ ተወርውረዋል። ነገር ግን የኢማሙ እጅ ለእውነት ብቻ የተዘረጋ እንጂ ለአገዛዝ ጫና አልተንበረከከም። ​በዕድሜያቸው ማገባደጃ ላይ በባግዳድ እስር ቤት ውስጥ እያሉ፣ 150 (ዓ.ሒ) ለአላህ ያላቸው ፍቅርና ውበት ሳይቀንስ በሶላት ላይ እንዳሉ ነፍሳቸው ወደ  ተመለሰች።​ኢማም አቡ ሐኒፋ ዛሬ በአካል የሉም፤ ነገር ግን የሠሩት ስራ  እና ያወረሱት ጥልቅ ማስተዋል እንደ ፀሐይ በታሪክ አድማስ ላይ አሁንም ያበራል። ​"እውቀት ተምሮ ዝም ያለ ብርሃን ነው፤ አስተምሮ ሕዝብን የጠነከረ ምሰሶ ያደረገ ደግሞ የዘላለም ሕያው ነው።" ​እርሳቸው የኡማው የፊት መብራት፣ የዕውቀት አባት፣ የፍቅርና የፍትሕ አርማ ሆነው በታሪክ ማኅደር ውስጥ ለዘላለም ይኖራሉ።

  • 📜 ተቀርቶ የተጠናቀቀ የዳሩል ኢልም ኢስላማዊ ተቋም የአረብኛ ቋንቋ (ነህው) ሞጁል-1 ደርስ ስብስብ 🎙 በዑስታዝ ሀሰን ዳውድ 📖የኪታቡን PDF File ለማግኘት https://t.me/c/3777943155/4/21?single https://t.me/c/3777943155/4/21?single ክፍል አንድ https://t.me/c/3777943155/1/28 https://t.me/c/3777943155/1/28 ክፍል ሁለት https://t.me/c/3777943155/4/38 https://t.me/c/3777943155/4/38 ክፍል ሶስት https://t.me/c/3777943155/4/46?single https://t.me/c/3777943155/4/46?single ክፍል አራት https://t.me/c/3777943155/4/91 https://t.me/c/3777943155/4/91 ክፍል አምስት https://t.me/c/3777943155/4/113 https://t.me/c/3777943155/4/113 ክፍል ስድስት https://t.me/c/3777943155/4/126 https://t.me/c/3777943155/4/126 ክፍል ሰባት https://t.me/c/3777943155/4/164 https://t.me/c/3777943155/4/164 ክፍል ስምንት https://t.me/c/3777943155/4/182 https://t.me/c/3777943155/4/182 ክፍል ዘጠኝ https://t.me/c/3777943155/4/197 https://t.me/c/3777943155/4/197 ክፍል አስር https://t.me/c/3777943155/4/206 https://t.me/c/3777943155/4/206 ክፍል አስራአንድ https://t.me/c/3777943155/4/224 https://t.me/c/3777943155/4/224 ክፍል አስራሁለት https://t.me/c/3777943155/4/245 https://t.me/c/3777943155/4/245 ክፍል አስራሶስት https://t.me/c/3777943155/4/266 https://t.me/c/3777943155/4/266 ክፍል አስራአራት https://t.me/c/3777943155/4/269 https://t.me/c/3777943155/4/269 ክፍል አስራአምስት https://t.me/c/3777943155/4/280 https://t.me/c/3777943155/4/280 ክፍል አስራስድስት https://t.me/c/3777943155/4/297 https://t.me/c/3777943155/4/297 🕌 አምቢያእ መስጅድ

  • “ዕውቀትን ለሁሉም፣ በየትኛውም ቦታ!” የዳሩል ኢልም ኢስላማዊ ተቋም የ2 ዓመት የሸሪዓ ዲፕሎማ ፕሮግራም ምዝገባ በይፋ መጀመሩን ስናበስርዎ በታላቅ ደስታ ነው! 📚 የምናስተምራቸው 6 ዋና ዋና ኮርሶች (Courses)፦ 📌 ዓቂዳ (የእምነት መሠረቶች) — ትክክለኛውንና ጥልቅ የሆነውን የእስልምና አስተምህሮ የሚጨብጡበት። 📌 ፊቅህ (የእስልምና ህግጋት) — የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎንና ኢባዳዎን በዕውቀት የሚመሩበት። 📌 ሀዲስ — የነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ፈለግና አስተማሪ ንግግሮች የሚረዱበት። 📌 ተርቢያ (ስነ-ምግባርና ስብዕና ግንባታ) — የእስልምናን ውብ ስነ-ምግባር በህይወትዎ ላይ የሚተገብሩበትና ማንነትዎን የሚያንጹበት። 📌 የነብያት ታሪክና ሲራ — ከታላላቅ መሪዎች ህይወት ተሞክሮ የሚቀስሙበት። 📌 የአረብኛ ቋንቋ — ለዲን ዕውቀት ቁልፍ የሆነውን ቋንቋ ደረጃ በደረጃ የሚያጠኑበት። 🕒 ለእርስዎ የተመቹ የትምህርት አማራጮች፦ 🏢 በአካል (Weekend)፦ ቅዳሜና እሁድ ብቻ በተቋማችን በመገኘት። 💻 በኦንላይን (Online)፦ ባሉበት ሆነው በኢንተርኔት አማካኝነት ምቹ በሆነ ሰዓት። 🚨  አሁኑኑ ፈጥነው ይመዝገቡ! 📍 የምዝገባ ቦታ፦ ጎሮ አምቢያእ መስጅድ 📞 ለበለጠ መረጃ፦ +251 974 47 09 57 / +251 914 64 53 77 “ዳሩል ኢልም — ዲኑን የሚኻድም ትውልድ እንፍጠር!”

  • видео или голосовое, без подписи

  • ሐሰን ኢብን ያሲር የተወለደው በዑመር ኢብን አል-ኸጣብ ዘመን በ21 ሒጅራ በመዲና ነው። አባትና እናቱ ሁለቱም ባሮች ነበሩ። አባቱ ሙስሊሞች በኢራቅ በበስራ እና በዋሲጥ መካከል የምትገኘውን ሚሳን የተባለች ቦታ ሲቆጣጠሩ ተማርኮ ወደ መዲና መጣ። አባቱ የሰሃባው የየዚድ ኢብን ሳቢት አገልጋይ በመሆን እስልምናን ተቀብሎ በመዲና መኖር ጀመረ። በኋላም ኸይሪያህ የተባለች የነቢዩ ﷺ ባለቤት የዑሙ-ሰለማን አገልጋይ አገባና ሐሰን ተወለደ። ዑሙ-ሰለማም ሐሰን ሲወለድ ኸይሪያህን ነፃ አወጣቻት። እንደሚባለው አንድ ቀንም እናቱ ወደ ገበያ ስትሄድ ሐሰን ማልቀስ ሲጀምር ዑሙ-ሰለማ አጠባችው። በዚህም የጡት ልጇ ሆነ። ሐሰን ያደገው በነቢዩ ﷺ ቤተሰቦች መካከል ሲሆን ዑሙ-ሰለማ ወደተለያዩ ሰሃባዎች በመውሰድ ዱዓዕ ታስደርግለት ነበር። ዱዓዕ ካደረጉለት አንዱ ዑመር ኢብን አል-ኸጣብ ሲሆኑ ❝አላህ ሆይ! የኢስላም አዋቂና በሰዎች ዘንድ የሚወደድ አድርገው።❞ ብለው አላህን ለምነውለታል። ሐሰን ብለው ስም ያወጡለትም ዑመር እንደሆኑ ይነገራል። ሐሰን በልጅነቱ ቁርኣንን ሐፈዘ። ከዚያም በነቢዩ ﷺ መስጂድ በመቀማመጥ ከበርካታ አንጋፋ ሰሃባዎች ስር ተማረ። ከእነሱም መካከል ዑስማን ኢብን ዐፋን፣ ዐሊይ ኢብን አቡ-ጣሊብ፣ አቡ-ሙሳ አል-አሽዓሪ፣ አቡ-ሑረይራህ፣ ዐነስ ኢብን ማሊክ፣ ዐብደላህ ኢብን ዐባስ፣ ዐብዱላህ ኢብን ዑመር እና ሌሎችም ይጠቀሳሉ። በ36 ሒጅራ በዐሊይ ዘመን ሐሰን የ15 ዓመት ልጅ ሳለ ቤተሰቦቹ ወደ ኢራቅ በስራ በመሄድ ከተሙ። በዚያ የተነሳም ❝ሐሰን-አል በስሪ❞ የሚል ስያሜ ተሰጠው። ሐሰን በወቅቱ በበስራ ይኖሩ በነበሩ በርካታ ሶሃቦች እጅ ፊቅህን፣ ሐዲስን እና ነህውን የተማረ ሲሆን የቁርኣን መምህሩ ሐጣን ኢብን ዐብዱላህ አር-ረቃሺይ፥ የቋንቋ መምህሩ ደግሞ ገጣሚው ኢብን ሱረይ አት-ተሚሚይ ነበሩ። ሐሰን ሰማያዊ ዐይን ያለው መልከመልካም ሲሆን ኢብን ቀዪም ሲናገሩ ❝ሴቶች ለዒድ ቀን ወጥተው ሲመለሱ ከኻጢቡ የበለጠ መልከኛ አላየንም ይሉ ነበር። እሱም ሐሰን አል-በስሪይ ነው።❞ ብለዋል። ሐሰን ከጥልቀቱ ብዛት በባህር የሚመሰለውን እውቀቱን ከሰበሰበ በኋላ በዚያው በበስራ ማስተማር ጀመረ። በባህሪው ይህንን ዓለም የናቀ ዛሂድ፣ አብዛኛውን ቀን የሚፆም፣ ሌሊቱን በተሐጁድ የሚያሳልፍ፣ ቁርኣን ሲያነብ የሚያለቅስ፣ ብዙም ሳቅ የሌለው፣ ንግግር አዋቂ፣ ለስላሳ፣ የተግባር ሰው፣ ትምህርቱ በማስረጃ የዳበረና ቀጥተኛ በመሆኑ ተቀባይነቱ ከሁሉም ከፍ አለ። በወቅቱ የነበሩ ብዙ ተራኪዎች ነገሮችን የማጋነን ዝንባሌ ስለነበራቸው ከሐሰን በቀር ሁሉም መስጊድ ውስጥ እንዳይተርኩ እስከመታገድ ደረሱ። በበስራ ይኖሩ የነበሩት ሰሃባው ዐነስ ኢብን ማሊክ የሐሰንን የእውቀት ደረጃ በማየት ሰዎች ሲጠይቋቸው ❝ሐሰንን ጠይቁት። እሱ እኛ የረሳነው የሚያውቀው ይኖራል።❞ ይሉ ነበር። የሐሰን ዕድሜ አብዛኛው በፊትና ያለፈ ነው። አጥፊ መሪዎችን ፊትለፊት የሚጋፈጥ በመሆኑ ምክንያት በበኑ-ዑመያዎች ዘመን ብዙ መከራና መሳደድ ደርሶበታል። ሙዓዊያህ ሞቶ ልጁ የዚድ በተተካ ጊዜ የየዚድን አካሄድ በግልፅ ከተቃወሙት አንዱ ሐሰን አል-በስሪይ ነው። ለበስራ ሰዎችም ከእርስበርስ ውጊያ እንዲታቀቡ ጥሪ አቅርቦላቸው ነበር። በበስራ የተወከለው አል-ሙሐለብ ኢብን አቢ-ሱፍራህ ❝ይሄ ጠማማ ሸይኽ ሰዎች በአላህ መንገድ እንዳይጋደሉ እያገደ ነውና ከተግባሩ የማይታቀብ ከሆነ የሚገባውን እሰጠዋለሁ።❞ እስከማለት ደረሰ። በኋላም የቁም እስረኛ ተደረገ። (ዙህድ አል-ሐሰን አል-በስሪ 77) ሐሰን ከአዋቂነቱ ባለፈ ጂሐድን የሚወድ በጣም ጀግና በመሆኑ በብዙ ውጊያዎች ተሳትፏል። አል-ሙሐለብ ኢብን አቢ-ሱፍራም ይህንን ስለሚያውቅ ሐሰንን ከፊት መስመር ያሰልፈው ነበር። በዐብዱልመልክ ኢብን መርዋን ዘመን ሐጃጅ በኢራቅ እንደተሾመ በሚሰራው ግፍ ከሐሰን ጋር ግጭት ውስጥ ገባ። ሐጃጅም ሊገድለው ይፈልግ ስለነበረ ሐሰን ብዙ ዘመኑን ከቦታ ቦታ በመዘዋወርና በመደበቅ አሳለፈ። በኋላም ሐጃጅ ሊሞት ሲል የህመሙ ስቃይ ሲበረታበት ሐሰንን ጠርቶ ዱዓዕ እንዲያደርግለት ጠየቀው። ሐሰንም ❝ሰዎችን አታሰቃይ ብዬ አልነገርኩህም ነበርን?❞ አለው። ሐጃጅም ❝እኔ ከአላህ ምህረትን እንድትለምንልኝ አልጠራሁህም። ሞቴን አፍጥኖ ከስቃዩ እንዲገላግለኝ ብቻ ጠይቅልኝ።❞ አለው። ሰዎችም ይህንን ሲሰሙ አለቀሱለት። ከሱለይማን ኢብን ዐብዱልመሊክ በኋላ ዑመር ኢብን ዐብዱልዓዚዝ እንደተተካ ሐሰንን ዋና አማካሪ አደረገው። ሐሰንም በበስራ ቃዲ በመሆን ካለክፍያ ማገልገል አገለገለ። (ሲየር አዕላም 4/588) ዑመር ከሞተ በኋላ ሐሰን ኸሊፋዎቹ መንገድ እንዳይስቱና ህዝቡም እንዳይጠፋ በመምከርና በመገሰፅ የሚችለውን ሁሉ አደረገ። ከሐሰን ታሪክ ጋር አብሮ ከሚነሳው አንዱ የሙዕተዚላዎች ጉዳይ ሲሆን መስራቹ ዋሲል ኢብን አጣዕ የሐሰን ተማሪ ነበረ። ከዚያም አንድ ቀን ሐሰንን ❝ወንጀል የሰራ ሰው አማኝ ነው ከሃዲ?❞ በማለት ጠየቀቸው። ሐሰንም ❝በወንጀሉ ይጠየቃል። ነገርግን ሙስሊም ነው።❞ አለው። ዋሲልም ❝ወንጀል የሰራ ሰው አማኝም ከሃዲም ሊባል አይችልም።❞ በማለት ተሟገተና ትቷቸው ወጣ። በዚህ ጊዜ ሐሰን ❝ዋሲል ከእኛ የወጣ ነው።❞ አለ። ከዚያ በኋላም የዋሲል ተከታዮች ❝ሙዕተዚላዎች❞ ወይም ❝የወጡ❞ ተባሉ። (አል-ፈርቅ በይን አል-ፉሩቅ 118) ሐሰን አል-በስሪይ በዚህ ሁኔታ ዘመኑን ካሳለፈ በኋላ በረጀብ ወር 110 ሒጅራ በጁሙዓ ዕለት በ86 ዓመቱ ይህንን ዓለም ተሰናበተ። ቀብሩም በዚያው በበስራ የተፈፀመ ሲሆን ህዝቡ ለሽኝት ወጥቶ ስለነበረ ከተማዋ ባዶ ሆኖ አሳለፈች። ስለ ሐሰን አል-በስሪይ ልቅና በዘመኑ የነበሩትም በኋላ የመጡትም የኢስላም ዑለማዎች መስክረውለታል። ለአብነት ኢብኑ ሰዕድ ❝አጥ-ጠባቃት❞ በተሰኘው ዝነኛ መጽሐፋቸው ❝ሐሰን አል-በስሪይ እውቀቱ ሰፊ፣ ዐቢድ፣ ግልጽ ተናጋሪ፣ መልከመልካምና በጣም ጀግና ነው። ነቢይ ቢሆን እንጅ እርሱን የሚመስል የለም።❞ ብለዋል። ኢብን ቡርዳህ ❝ከነቢዩ ሶሐቦች ጋር እንደ እርሱ የሚመሳሰል አላየንም።❞ ሲሉ ተናግረዋል። በተመሳሳይ አቡ-ቀታዳህ ❝እንደ አል-ሐሰን አመለካከቱ የዑመር ኢብን አል-ኸጣብን የሚመስል ሰው አላየሁም።❞ ብለዋል። በአንድ ወቅት አጧዕ ኢብን አቢ-ረባህ ለሞተ ሰው ቁርኣን ስለመቅራት ሲጠየቅ ❝ለሟች እንደሚቀራ አልተማርንም ወይም አልሰማንም።❞ አለ። ጠያቂውም ❝አል-ሐሰን ግን መቅራት አለብን ይላል።❞ ሲለው ❝እንግዲያውስ ይህንኑ ተከተል። ምክንያቱም አል-ሐሰን ታላቅ ዐሊም ነውና።❞ በማለት መልሶለታል። ኻሊድ ኢብኑ ሰፍዋን የአል-ሐሰን አል-በስሪ የቅርብ ጎረቤት ነበር። በአንድ ወቅት ስለ ሐሰን ሲናገር ❝እንደ እርሱ ያለ ሰው አይቼ አላውቅም። ውጫዊ ገጽታው ከውስጣዊ ማንነቱ ጋር አንድ ነው። ንግግሩም ከተግባሩ ጋር ይገጥማል። መልካም ነገርን ካዘዘ ቀድሞ የሚተገብረው እርሱ ነው። ከመጥፎ ነገር ሲከለክልም ከሁሉ በላይ እርሱ ይርቃል። ከሌሎች ሰዎች ምንም ፍላጎት የለውም። ነገር ግን ሰዎች ወደ እርሱ ፈላጊዎች ነበሩ።❞ ብሏል። የሐሰንንና የዑመርን የተዋዱዕ ሰላት ያየው የዚድ ኢብን ሐውሻብ ደግሞ ❝ሐሰን አል-በስሪይ እና ዑመር ኢብን ዐብዱልዓዚዝን ሲሰግዱ ላያቸው ጀሃነም ከእነሱ በቀር ለሌላ የተፈጠረች አይመስለውም።❞ ሲል ተናግሯል። (ሲፋቱ ሰፍዋህ 1/156)

  • видео или голосовое, без подписи

  • 🔖ስለ ነፍስህ|ስለ ራስህ ማወቅ ከፈለግክ፡       ~  ~ قال ابن الجوزي رحمه الله፡ إنْ أردت أنْ تنظر إلى نفسك فخُذ كفًا من تُراب فإنك منه خلقت وفيه تعود ومنه تخرج 📚 التذكرة (١٦٩/١) ✔️እፍኝ አፈርን ዘግነህ ተመልከታት፡ 👉ከሷው ተፈጥረሀል፡ 👉ወደ'ሷም ትመለሳለል፡ 👉ከሷም ትወጣለህ! ስለዚህ እራስህን አታካብድ፡ ቀለል አድርግ፡ ጋሽ አፈር! ከአፈር ተፈጥሮ ወደ አፈር የሚመለስ የሰው ልጅ ማለት ደካማ ፍጡር መሆኑን ሳስብ ሁሌም ደስ ይለኛን ያለ በለዚያ ከባድ ነበር ነገሩ ይህንን ደካማ ፍጡር ለፈጠርከው አላህየ ምስጋና ለአንተ ይሁን

  • - قال الإمام ابن حِبَّان رحمه الله : لا ينبغي للعاقل أن يحزن ، لأنّ الحزن لا يـرد المُصيبة ، ودوام الحزن ينقص العقل. - روضة العقلاء (٣٨) #آثار_السّلف

  • ‏عن سعد بن أبي وقاص رضي الله عنه قال: قال رسول الله ﷺ : " أيعجز أحدكم أن يكسب كل يوم ألف حسنة ؟ " فسأله سائل من جلسائه : كيف يكسب أحدنا ألف حسنة ؟ قال : " يسبح مائة تسبيحة، فيكتب له ألف حسنة، أو يحط عنه ألف خطيئة ". 📚رواه مسلم 2698

  • ሱናህ: ኢብኑ አልቀይም -ረሒመሁላህ- ዛድ አልመዓድ ላይ ስለ ሐቢባችን -ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም- ልግስና ከተናገሩት:- «መስጠት እና ልግስና እርሳቸው ዘንድ በጣም የተወደዱ ነበሩ:: በመስጠታቸው የሚያንፀባርቁት ደስታ ተቀባዩ ሲሰጠው ከሚደሰተው በላይ ነበር!።» اللهم صلي على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد 📌አቡ ረቢዓህ አል-ፈቂህ ሚስቱ በሞተች ጊዜ ቀበራትና እጆቹን አራግፎ ወደ ቤቱ ተመልሶ لا حول ولا قوة إلا بالله إنا لله وإنا إليه راجعون አለና አለቀሰ። ከዚያም ራሱን እያናገረ እንዲህ አለ "የኻሊድ አባት ሆይ! ቤቱም ጭምር ሞቷል። ግንባታ (ቤት) ህያው የሚሆነው ውስጡን ህያው በምታደርገው ሴት መኖር ነው  አለ።     🌷አላህ ሴቶቻችንን ይጠብቅልን🤲

  • ባሁን ወቅት የምንፅናናበትና አልለን የምንለው አንጡራ ሀብታችን ተውሂድና ሱና ናቸው። ይህንን ውዱ ሀብታችን ሊያስጥሉን የሚፈልጉ ብዙ ሌቦች አልሉና ከምንም ነገር በላይ አጥብቀን እንያዛቸው።

  • ንግዳቸው ትርፋማ የሆነላቸው አባት! ────⊱◈◈◈⊰──── ሸይኽ ሙሀመድ ኢብን ሳዐድ አሽ'ወይዒር ይባላሉ! በዘመናችን ፊቅህ ክንፏን ዝቅ ያደረገችለት እውቁ የመዲናው ፈቂህ "ሸይኽ ዐብድሰላም አሽ'ወይዒር" ወላጅ አባት ናቸው። እኚህ ወላጅ አባት ለታላቁ ኢማም ኢብን ባዝ ረሂመሁሏህ እጅግ የቅርብ አማካሪ ወዳጅና ፀሀፊ የነበሩ  ሰው ናቸው።  ሸይኽ ኢብን ባዝ (ረ.ሂ) ለ30 አመታት "ኑሩን ዓለ ደርብ" በተሰኘው በካሴት ይተላለፍ በነበረውን የፈታዋ ፕሮግራም ላይ የተሰጡትን ከ11,300 በላይ የድምፅ ትምህርቶችና ፈታዋዎች ወደ ፅሁፍ በመቀየር (مجموع فتاوى ومقالات متنوعة) በሚል ርዕስ በ30 ሙጀለድ አዘጋጅተው በቀላሉ ለኡማው እንዲደርስ የአንበሳውን ድርሻ የተወጡ ከባድ ሰው ናቸው ከዛም በተጨማሪ በተለያዩ አጋጣሚዎች የተበታተኑ የሸይኽ ኢብን ባዝን ጽሁፎችና መጣጥፎችን በማደራጀትና ለኪታቦቹም ማውጫና ርዕስ በማዘጋጀት በአጠቃላይ ከሰዎች እይታ በስተጀርባ ለሸይኽ ኢብን ባዝ ዳዕዋ ሰፊውን እጅ ወስደው የራሳቸውን አሻራ ያሳረፉ ቁልፍ ሰው ነበሩ። ከዚህም ስራቸው ጎን ለጎን የአላህም ተውፊቅ ታክሎበት ለልጃቸው ሸይኽ ዐብድሰላም አሽ'ወይዒር እዚህ መድረስ ትልቁን የአባትነት ትግልና አስተዋፅኦ አበርክተዋል። አላህ ይዘንላቸው የዛሬ 4 አመት ሻዕባን ወር ላይ ወደማይቀረው አኺራ ሄደዋል። አላህ መልካም ስራቸውን ሁሉ ይቀበላቸው ቀብራቸውንም በብርሃን የተሞላ የጀነት ጨፌ ያድርግላቸው። እዚህ ድረስ ከመጣችሁ አይቀር የልጃቸውን ሸይኽ ዐብድሰላም አሽ'ወይዒር ወርቅ የሆኑ ትምህርቶችና ማስታወሻዎችን የምታገኙበት link comment ላይ አስቀምጥላችኋለሁ። ልጃቸው ከሚሰጠው ትምህርት አንዲትን እውቀትም ትሁን ማስታወሻ ያገኛችሁ እንደሆን ለእኚህ አባት ዱዐ ማድረጋችሁን አንዘንጉ! "የእርሳቸው ትርፋማው ንግድ ይህ ነውና።" ✨@Abuhatim7

  • Channel photo updated

  • Messages in this channel will no longer be automatically deleted

  • Messages in this channel will be automatically deleted after 1 month

  • Channel name was changed to «ሱናህ»

  • Channel photo updated

  • 📢  የዕውቀት ብርሃን በ“ዛድ አካዳሚ” (Zad Academy) 🌟የዱንያም የአኺራም ስኬት መክፈቻ የዲን ዕውቀት ነው! አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፦      "እነዚያ የሚያውቁና እነዚያ የማያውቁ እኩል ይሆናሉን?" (አዝ-ዙመር፡ 9) የአላህ መልእክተኛም (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦      "ዕውቀትን ፍለጋ መንገድን የጀመረ ሰው፣ አላህ ወደ ጀነት የምትወስደውን መንገድ ያቀልለታል።" (ሙስሊም) 🌟የአምቢያ (ጎሮ) መስጂድ ልዩ የሸሪዓ ትምህርት መርሃ-ግብር የእስልምና እውቀትን በትክክለኛ ምንጩ፣ በዘመናዊ አቀራረብ እና በታመኑ መምህራን መቅሰም ይፈልጋሉ? “ዛድ አካዳሚ” የቂርዓት መርሃ-ግብር ይዞላችሁ ቀርቧል። ትምህርቱ በዓይነቱ ልዩ በሆነ መልኩ በአካል (Face-to-Face) በአምቢያ መስጂድ እና በየትኛውም ቦታ ሆነው መከታተል በሚያስችል በኢንተርኔት (Online) አማራጮች ተዘጋጅቷል። 📚 ለምን ዛድ አካዳሚን ይመርጣሉ? * ደረጃውን የጠበቀ ካሪኩለም፦ በ7 ዋና ዋና የትምህርት ዘርፎች ላይ ያተኮሩ፣ በሞጁል የተዘጋጁ ስልታዊ ትምህርቶች። * ተደራሽነት፦ በሥራ ወይም በሌላ ጉዳይ ለተወጠሩ ተማሪዎች ምቹ የሆነ የጊዜ ሰሌዳ። * ትክክለኛ ምንጭ፦ በቁርአንና በነቢዩ ሱና ላይ የተመሠረተ፣ ጥራቱን የጠበቀ የሸሪዓ ዕውቀት። 📖 ለአሁን የሚጀመሩት የትምህርት ዘርፎች * ፊቅህ (የእስልምና ሕግጋት) * ሉጋህ (አረብኛ ቋንቋ - ነሁና ሶርፍ) ⏰ ትምህርቱ የሚሰጠው እሁድ ጠዋት ከ2:30 - 6:00 "ዕውቀት ለሰው ልጅ እንደ አየርና ውሃ አስፈላጊው ነው።" ኢማም አሕመድ እንዳሉት አሁኑኑ ይመዝገቡ! ለተጨማሪ መረጃ እና ለመመዝገብ @Hubo_1