tgindex
Seid Al-jeylani

Seid Al-jeylani

Статистика
@Islamic_path1арабский

❤️‍🩹 وما من كاتـب إلا سـيفنى ويبقى الدهر ما كتبت يداه فلا تكتُـب بكفك غير شيء يسـرك في القيامة أن تراه ☘ . . For any comment 👇 📧 @Islamic_path_bot

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
28
Тип
открытый
Язык
арабский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
10 440
−35 за 3 дн.
Сутки
−17
−0,16%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
216
28 постов
Вовлечённость
2,1%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 28
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
42
1/48двое суток
48
1/72трое суток
51

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ኢላሂ! ከተውበተኞች አድርገህ ካኖርከኝ ይበቃኛል። ሙስሊም ሆኜ ከሞትኩም በታላቁ ችሮታህ ነው።ኢላሂ! ወዳንተ መልሰኝ።በመንገድህ ላይ አፅናኝ።

  • ሁሌም ካንተ ጋር ነኝ፣ ፈፅሞ አልለይህም ለሚሏችሁ ...ሁሌም ከኛ ጋር የሚሆነው አላህ ብቻ ነው በሏቸው። በዚህች አጭር የዱንያ ላይ ዕድሜያችን ከስንቱ ጋር ወዳጅነት ጀምረን፤ ስንትና ስንት ሰው ወደኋላ ጥለን እዚህ ደርሰናል።ሰው ይረሳል። ይረሳና ሁሉንም ነገር ይረሳል።

  • በዚህ ዘመን...ስሜትህን የሚረዳልህ፣ ብሶትህን የሚያዳምጥልህ፣ እንባህን የሚጠርግልህ፣ እጅህን ይዞ የሚያነሳ ወዳጅ ካገኘህ ብዙ ነገር አገኘህ፡፡

  • ኻሊድ ቢን በርመክ እንዲህ ይላል፦ ❝ዝሙት የክፋት ፀባዮችን በሙሉ አጠቃልሎ የያዘ ነው። አንድ ዝሙተኛ ዘንድ አላህን መፍራት፣ ቃል ኪዳን ማክበርም ሆነ ለጓደኛ ታማኝ መሆንን አታገኝም። — ከኢብኑል ጀውዚ «አኽባሩ-ኒሳእ» ኪታብ የተወሰደ

  • አላህዪ! ወዴት ልሂድ? የማንንስ በር ላንኳኳ? ከአንተ ውጪ ማን አለኝ? መጠጊያዬም፣ መሸሸጊያዬም አንተ ብቻ ነህ። የሁሉ ነገር ባለቤት ሆነህ ሳለ እንዴት ከበርህ እመለሳለሁ? የአዛኞች ሁሉ አዛኝ ሆነህ ሳለ እንዴት ተስፋ እቆርጣለሁ?

  • ከማህበራዊ ሚዲያ እብደትና ሱስ ስታገግም... በርካቶች ቀድመውህ የራቀ ጉዞ እንደተጓዙ ታያለህ። አንደኛው ቁርዓን ሲሃፍዝ፣ ሌላው መሠረታዊ የእስልምና እውቀቶችንና ልዩ ልዩ ጥበቦችን ሲቀስም አንተ ግን ስልክህ ላይ እንደተደፋህ ጊዜህ በከንቱ ያልፋል፤ ዕድሜህ ሲነጉድ እንኳ አይሰማህም። በአንተና በመቃብርህ መካከል ግን የቀረችው አንዲት እርምጃ ብቻ ልትሆን ትችላለች!

  • ጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ያለሁት ብለህ አትዘናጋ፡፡ ከጀነት የበለጠ ጥሩ ቦታ የለም፡፡ አባታችን አደም በሷ ዉስጥ ሆነው ጭምር ፈተና አግኝቷቸዋል። በዒባዳህ ብዛትም አትጃጃል፣ ኢብሊስ ከዚያ ረጅም የዒባዳ ሕይወት በኋላ ምን እንዳጋጠመው ይታወቃል፡፡

  • ከአላህ በስተቀር ሁሉም ምትክ አለው! የሰው ልጅ ላጣቸው ነገሮች ሁሉ ይብዛም ይነስ ምትክ ( አማራጭ ) ሊያገኝ ይችላል፤ አላህን ያጣ ( ከርሱ የራቀ፣ እሱን ያስቆጣ ) ሰው ግን ምንም ዓይነት ምትክና አማራጭ መቼም ማግኘት አይችልም። ስለዚህ መቼም ቢሆን፣ ለማንም ለምንም ብለህ አላህን እንዳታጣ ተጠንቀቅ

  • በርካታ የዱንያን ፈተናዎች እና ደስ የማይሉ የሚረብሹ ስሜቶችን በየቀኑ እንታገላለን ። በዚህ ሁሉ መሀል ደህና መስለን ለመታየት የምናደርገው ጥረትም ሌላው ከባድ ትግል ነው።

  • ​ያ አላህ! የልቤን መረጋጋት አትቀማኝ፤ የተስፋዬን በር አትዝጋብኝ። ከጭንቀት ይልቅ ሰኪናህን፣ ከጥርጣሬ ይልቅ የቂን በልቤ ውስጥ ሙላልኝ። ከአንተ ውጭ ሌላ ደጋፊ የለኝምና ልቤን በአንተ ውሳኔ ወዳጅ አድርገው።

  • አንዳንዶቻችንም ምንም የማይጠቅም የእርዳታ ጩኸት ይጮኻሉ። አላህ እንዲህ ይላል፦ ﴿قال رَبِّ ارْجِعُونِ لَعَلِّي أَعْمَلُ صَالِحًا فِيمَا تَرَكْتُ ۚ كَلَّا ۚ إِنَّهَا كَلِمَةٌ هُوَ قَائِلُهَا ۖ وَمِنْ وَرَائِهِمْ بَرْزَخٌ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ﴾ እንዲሁም አላህ እንዲህ ይላል፦ ﴿وَأَنْفِقُوا مِنْ مَا رَزَقْنَاكُمْ مِنْ قَبْلِ أَنْ يَأْتِيَ أَحَدَكُمُ الْمَوْتُ فَيَقُولَ رَبِّ لَوْلَا أَخَّرْتَنِي إِلَىٰ أَجَلٍ قَرِيبٍ فَأَصَّدَّقَ وَأَكُونَ مِنَ الصَّالِحِينَ﴾ እንዲሁም አላህ እንዲህ ይላል፦ ﴿يَقُولُ يَا لَيْتَنِي قَدَّمْتُ لِحَيَاتِي﴾ ስለዚህ ገና ዕድሜ እያለን ሳለ፣ እንመከር፣ እንለወጥ።

  • ያለ ስራ ምኞት ቂልነት ነው ። قال يحيى بن معاذ -رحمه الله - : أعظمُ الاغترَار: التمادِي في الذنُوبِ معَ رجَاء العَفْو مِن غير ندامَة ، وتوقّع القُرب من الله بغير طاعَة ، وانتظَار زرْع الجنّة بِبَذر النار ، وطلَبُ دَار المطيعينَ بالمعاصِي ، وانتظار الجزاء بغير عمَل ، والتمنّي علَى الله مَعَ الإفرَاط. تزكية النفوس(١١٤). 🔷  የሕያ ኢብኑ ሙዓዝ የተባሉ ታላቅ ሊቅ እንዲህ ይላሉ :- " በጣም ትልቁ መታለል በወንጀል መዘውተር ነው ። ያለ ፀፀት የአላህን ምህረት , መከጀል ትእዛዙን ሳይፈፅሙ ወደ አላህ ለመቃረብ መጠበቅ , የእሳት ዘር እየዘሩ የጀነት ፍሬ መጠባበቅ , ወንጀል እየሰሩ የአላህን ታዛዦች ሀገር መፈለግ , ያለ ሥራ ምንዳ መፈለግ , ምንም ሣይሠሩ በአላህ ላይ ተስፋ ማድረግ " ናቸው ።

  • በቢሊዮን ከሚቆጠሩ የዓለም ሕዝቦች መሃል ሙስሊም ሆኖ መገኘትን የመሰለ ታላቅ ጸጋ ይዞ ማማረር እንዴት ይሆናል? ሙሊም ከመሆን በላይስ ምን ፀጋ አለ!? ኧረ አልሐምዱ ሊላህ እንበል!

  • ወንጀል ከሰራህ በኋላ ምንም እንኳን ትንሽ ገንዘብ ቢሆን ሰደቃ ስጥ፤ ምክንያቱም ሰደቃ የኃጢአቱን መጥፎ ተጽእኖና መዘዝ በአላህ ፈቃድ ታስወግዳለች። — ሸይኽ ዐብዱስሰላም አሽ-ሹወይዒር

  • ኢላሂ...ፍጡራን ሁሉ ቢወዱኝም ሆነ ቢጠሉኝ ግድ የለኝም፤ የእኔ ትልቁ ጭንቀት በአንተ ዘንድ ያለኝ ስፍራ ብቻ ነው። ኢላሂ! ሰዎች ከሚያዩት ውጫዊ ማንነቴ ይልቅ በአንተና በእኔ መካከል ያለውን አሳምርልኝ!

  • ትልቁ ኪሳራ ማለት...ጀናዛው ላይ ሊሰገድበት ብቻ ተብሎ መስጊድ የገባ ሰው ነው። ልትቀበር ተብላ በከፈን ጊዜ ብቻ ሒጃቧን ፀጉሯን የሸፈነ ሴት ናት።ጌታዬ ሆይ በዲንህ ላይ አጽናን።መልካም መመለስን ወዳንተ መልሰን።

  • ኢማም ፉደይል ቢን ዒያድ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦ "ሙእሚን ንግግሩ ጥቂት ነው፣ ሥራው ግን ብዙ ነው። ሙናፊቅ ደግሞ ንግግሩ ብዙ ነው፣ ሥራው ግን ጥቂት ነው።" እንዲሁም እርሳቸው (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦ "ከጁምዐ እስከ ጁምዐ ድረስ የተናገረውን ቃል በጥንቃቄ የሚቆጥር ሰው አውቃለሁ።"

  • ኢላሂ! ~ ባንተ ታውቀን ባንተ ከሚያምፁት አታድርገን፣ለሰው ጠቁመን ተቃራኒውን ከሚጓዙ አታድርገን፣ በአፍ ቀርበውህ በተግባር ከሚርቁህ አታድርገን፣ በምላስ ከሚያመልኩህ በልቦና ከሚሸሹህ አታድርገን፣አለባበሣችንን እንዳሳመርክ ዉስጣችንን አሳምርልን!

  • وَلَا تُخْزِنِي يَوْمَ يُبْعَثُونَ በሚቀሰቀሱበት ቀንም አታዋርደኝ፡፡ يَوْمَ لَا يَنفَعُ مَالٌ وَلَا بَنُونَ ገንዘብም ልጆችም በማይጠቅሙበት ቀን፡፡ إِلَّا مَنْ أَتَى اللَّهَ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ ወደ አላህ በንጹህ ልብ የመጣ ሰው ቢኾን እንጅ፡፡» [سورة الشعراء]

  • ከማንም ምንም አለመጠበቅ ከአንገት እንጂ ከአንጀት የሚያወራ ቁምነገረኛ ሰው በጠፋበት በዚህ ዘመን፤ ካንተ ጋር ቃል ገብቶ ዘወር ብሎ ከሌላ ጋር የሚደራደር በሞላበት በዚህ መጣሁ ብሎ ቀረሁ እኮ ማለት እጅግ ተራ ነገር በሆነበት በዚህ ወቅት፤ ብቻ በአጠቃላይ መልካም እሴቶች እየተሸረሸሩ ባሉበት ዘመን ሕይወታችሁን ቀጥ አድርጋችሁ ለራሣችሁ ኑሩ እንጂ ወደ ሰዎች ብዙ አትመልከቱ፡፡ ማንንም አትጠብቁ፤ ከማንም አትጠብቁ። ብዙዎቻችን ወደኋላ ያስቀረን መጠበቅ ነው፡፡ መጠበቅ ያደኅያል፣ መጠበቅ ከሰው ያስከጅላል፣ መጠበቅ አላህን ያስረሳል፣ መጠበቅ ያሰንፋል፣ ልብን ያንጠለጥላል፣ ሞራልን ይሰብራል ... አንዳንድ ጊዜ መጠበቅ መልካም ቢሆንም ግና ፍፁም በሆነ መልኩ ሰው ላይ በመደገፍ መሆን የለበትም። ነብዩ ዩሱፍ ዐ.ሰ. ለአላህ አደራህን አምላኬ ማለት የነበረባቸዉን ነገርእረስተው ከእስር ለተፈታው ባልደረባቸው እንዳትረሳኝ አሉት፡፡ ግና እሱ ጉዳያቸዉን ረሳ፡፡ አላህ ግን አልረሣቸዉም። አባታችን ሊሞትልን ነው ብለው የአባታቸውን ሀብት ለመውረስ ሲጠብቁ ስንቶች ድሆች ሆነው ሞተዋል! ያገባኛል / ታገባኛለች ብለው ሲጠብቁ ስንቶች ተከዳን ብለው እሪ ብለዋል፡፡ በርግጠኝነት መጠበቅና _ በርሱ ላይ እራሣችንን ልንጥል የምንችለው አምላካችንን አላህን (ሱ.ወ.) ብቻ ነው፡፡ እሠጣለሁ ብሎ ቃሉን የማያጥፍ፣ እመጣለሁ ብሎ የማይቀር ከርሱ ወዲያ ማን አለ!!።

Seid Al-jeylani — tgindex