tgindex
"ቃለ እግዚአብሔር "

"ቃለ እግዚአብሔር "

Статистика

"ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው።" ምሳ 16 "ሥጋችን ምግብ ሲያጣ እንደሚደክም ሁሉ ነፍስም ምግቧን የእግዚአብሔርን ቃል ስታጣ ትደክማለች።" - ብጹዕ አቡነ ሽኖዳ በመንፈሳዊ ህይወት ዙሪያ ጥያቄ ካላችሁ ለመምህራችን በ @henokasrat3 መላክ ትችላላቹ።

Последний пост
7 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
6 936
−5 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 887
21 постов
Вовлечённость
27,2%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
888
1/48двое суток
1 017
1/72трое суток
1 097

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 7 авг.806103

    без подписи

  • 7 авг.830167

    ‹‹ፍልሰታ›› የሚለው ቃል «ፈለሰ» ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን በጥሬ ትርጉሙ መለየት፣ ማረግ እና ወደላይ መውጣት ማለት ነው። የእመቤታችን ዕረፍት፦ እመቤታችን ድንግል ማርያም ያረፈችው በጥር 21 ቀን ነው። ሐዋርያት ሊቀብሯት ሲሄዱ አይሁድ በምቀኝነት ስለተቃወሟቸው መላእክት አስከሬኗን ነጥቀው በገነት አኖሩት። የሐዋርያት ሱባዔና ቀብር፦ ሐዋርያት ከነሐሴ 1-14 ሱባዔ ገብተው በጸሎት ከጌታችን ተቀብለው በክብር ቀበሯት። የቅዱስ ቶማስ ምስክርነት፦ ሐዋርያው ቶማስ በወቅቱ ባለመኖሩ በሦስተኛው ቀን እመቤታችን ስታርግ በደመና ላይ አያት። እርሷም ማጽናኛ እና ምስክር እንዲሆን ሰበኗን ሰጠችው። የሐዋርያት በረከት፦ ቶማስ ሰበኗን ለአካፈላቸው በኋላ፣ ሐዋርያትም የእመቤታችንን ትንሣኤና ዕርገት ለማየት በዓመቱ ከነሐሴ 1 ጀምረው ሱባዔ ገቡ። በነሐሴ 16 ቀን ጌታችን ከመላእክት ጋር መጥቶ እመቤታችንን አስነሥቶ አሳይቷቸዋል። ዛሬም ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሐዋርያትን ምሳሌ ተከተላ ከሰባቱ አጸዋማት አንዱ በማድረግ ይህንን ጾም እንድንጾም አዝዛናለች። የጾሙና የእመቤታችን የትንሣኤዋና የዕርገቷ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን! 🙏

  • 29 июл.1 346174

    "ነገ ሐምሌ 22 መልአከ ብርሃናት ቅዱስ ዑራኤል ቅዳሴ ቤቱ ተከብሮ ይውላል ብርሃኑን ያብራልን🙏 ✥ቅዱስ ዑራኤል ከሊቀ መላእክት አንዱ ነው። መላእክት በስማቸው ቅጥያ ኤል የሚል ቃል አለ ይኸውም እግዚአብሔር ማለት ነው። "ዑር" ማለት ብርሃን፤ "ኤል" ማለትም እግዚአብሔር ማለት ነው።ዑራኤል ማለት የብርሀን ጌታ፣ የብርሀን አምላክ ማለት ነው። ✥ የሰማይን ሚስጥር ለሄኖክ እውቀትን የገለጸለት መልአክ ነው። የፀሐይን የጨረቃን የከዋክብትንና የሰማይ ሰራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለሄኖክ ነግሮታል። መ.ሄኖክ 28፥13 ✔️በብርሃናት ሁሉ ሊቀ ብርሃናት ሆኖ የተሾመው ቅዱስ ዑራኤል ነው። ✔️ቅዱስ ዑራኤል በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ ስለሆነ እርሱም መባርቅትን ለጥጋብና ለበረከት እንዲሁም ነጎድጓድን ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል። መ.ሄኖክ ፮፥፪ ➕ ምስጢረ ሰማይና እውቀትንም ሁሉ ለሄኖክ የገለጸለት የፀሐይን የጨረቃን የከዋክብትንና የሰማይ ሰራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለሄኖክ ነግሮታል። ✥ቅዱስ ዑራኤል ልቡናን የሚያበራ እውቀትን የሚገልጽ ርሑሩህ መልአክ ነው። ቅዱስ ዑራኤል ለነብዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋአ ልቡናን አጠጥቶት ሰማያዊ ሚስጥራትን ገልፆለታል። ነብዩ እጅግ ብዙ ቁጥር ያላቸውን መጻሕፍት ደርሷል። በሰዓታቱም "ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ምስለ ኤልያስ ወኤልሳዕ ነቢያተ እስራኤል ወምስለ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋዓ ልቡና ዘአስተዮ ዑርኤል፡፡" "ነይ ወደ እኛ ድንግል ሆይ ከእስራኤል ነብያት ከኤልያስና ከኤልሳ እንዲሁም ዑራኤል ጽዋ ልቡናን ካጠጣው ከእዝራ ሱቱኤል ጋር።" ✥ሌላኛው ቅዱስ ዑራኤል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእጸ መስቀል ላይ በቀራንዮ በአምስቱ ቅንዋት (ሳዶር፣አላዶር፣ዳናት፣አዴራ፣ሮዳስ) ሲቸነከር ይህ ብርሃናዊ መልአክ ነው ከጎኑ የክርስቶስን ደም በጽዋ ቀድቶ በዓለም ሁሉ የረጨው። ✥እመቤታችን ወደ ግብፅ በተሰደደች ጊዜ በዚህ የጭንቅ ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን እየተራዳ መንገድን እየመራት በብርሃን ወደ ሀገረ ግብፅ ቀጥሎም ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም አስራት ወደ ሆነቻት ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ እየመራት መጥቷል። ማቴ 2÷13-15 ✥ሌላው የእውቀትን ብርሃን የገለጸላቸው የእውቀትን ጽዋ ያጠጣቸው ለሊቁ አባታችን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነው። እኚም አባታችን በመልአኩ ተራዳኢነት ብዙ ድርሰቶችን ደርሰዋል። እመቤታችንም በምልጃዋ ቅዱስ ዑራኤል የእውቀትን ጽዋ ያጠጣቸው ዘንድ አድርጋለች። አባ ጊዮርጊስ እመቤታችንን ይወዷት ስለነበረ አርጋኖን ሌሎችንም ደርሰዋል። የሊቀ ብርሃናት ቅዱስ ዑራኤል በረከት ተራዳኢነት አይለየን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር 🙏

  • 29 июл.1 0021

    без подписи

  • 29 июл.1 0022

    без подписи

  • 14 июл.1 9099

    без подписи

  • 14 июл.1 90779

    без подписи

  • 14 июл.1 647117

    ‹‹ሐምሌ 7›› አጋዕዝተ ዓለም ስላሴ በአብርሃም ቤት ተገኝተው ቤቱን የባረኩበት የአንድነታቸውንና ሶስትነታቸው ሚስጢር የገለጹበት ታላቅ በዓል ነው። በዚችም ቀን ልዩ የሆኑ ሦስቱ አካላት /ቅድስት ሥላሴ/ በኦሪት መጽሐፍ እንደ ተጻፈ ወደ አብርሃም ቤት ገቡ ያቀረበላቸውንም ተመገቡ፡፡ የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት ለመረዳት በሥላሴ ፈቃድ መጻሕፍት እንዳስተማሩ ሊቃውንት እንደተረጉሙልን እንጂ ማንም በገዛ ፈቃዱ ተመራምሮ አይደርስበትም፡፡ የሐምሌ 7 ቀንም ሥላሴ በአብርሃም ቤት ገብተው ቸርነታቸውና ፍቅራቸውን የገለጹበት፣ ስለሆነ በዓሉን ስናዘክር ሥላሴን እናመሰግናለን፡፡ በአጠቃላይ በዚህ ዕለት በአብርሃም ቤት እግዚአብሔር የተስተናገደበት፣ አንድነቱና ሦስትነቱ የተገለጠበት፣ አብርሃም እና ሣራ ካረጁ በኋላ ልጅ እንደሚወልዱ የተበሠረበት፣ ይሰሐቅንም እንደሚወልድ የተነገረበት ዕለት ነወ። ለአብርሃም ምሥጢሩን የገለጠ እግዘአብሔር ለሁላችን ይግለጥልን🙏

  • 11 июл.1 74476

    без подписи

  • 11 июл.1 43044

    +++ ብርሃናተ ዓለም +++ "ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ምንም ብታውቁ በእናንተም ዘንድ ባለ እውነት ምንም ብትጸኑ፥ ስለ እነዚህ ዘወትር እንዳሳስባችሁ ቸል አልልም። ሁልጊዜም በዚህ ማደሪያ ሳለሁ በማሳሰቤ ላነቃችሁ የሚገባኝ ይመስለኛል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳመለከተኝ ከዚህ ማደሪያዬ መለየቴ ፈጥኖ እንዲሆን አውቃለሁና። ከመውጣቴም በኋላ እነዚህን ነገሮች እንድታስቡ በየጊዜው ትችሉ ዘንድ እተጋለሁ።" ቅዱስ ጴጥሮስ (2ጴጥ 1:12-15) "መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፥ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም።" ቅዱስ ጳውሎስ (2ጢሞ 4:7) ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ጳውሎስ ለቤተክርስቲያን ብዙ የተጋደሉ ለምዕመናን በቀለም ብቻ ሳይሆን በደማቸው ጽፈው ለትውልድ አሻራቸውን ያስቀመጡ ክርስቶስ ምዕመናንን አደራ ያስጠበቃቸው ስለተሰጡት አደራ ብለው አንገታቸውን የሰጡ ሐምሌ አምስት ቀን ቅዱስ ጴጥሮስ ተዘቅዝቆ የተሰቀለበት ቅዱስ ጳውሎስ በሰይፍ አንገቱ የተቆረጠበት እለት ነው ። የሐዋርያቱ የቅዱስ ጴጥሮስ እና የጳውሎስ በረከት አይለየን አሜን !

  • 10 июл.1 259256

    "ሰው መሆንህን ለድካምህ እንደ ምክንያት አታቅርብ፤ በትዕግሥት መልአክ መሆን ትችላለህና፤ ጌታችን ለሚወዱትና ፈቃዱን ለሚፈጽሙት እንደመላእክት ይሆኑ ዘንድ ተስፋ አስደርጓቸዋልና።" ምክረ አረጋዊ

  • 8 июл.1 623115

    "ኢየሱስም እንዲህ አለ፦ “..ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራምም።" የዮሐንስ ወንጌል ምእራፍ - 14 1: ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ። 2: በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤ 3: ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ። 4: ወደምሄድበትም ታውቃላችሁ፥ መንገዱንም ታውቃላችሁ። 5: ቶማስም፦ “ጌታ ሆይ፥ ወደምትሄድበት አናውቅም፤ እንዴትስ መንገዱን እናውቃለን?” አለው። 6: ኢየሱስም አለው፦ “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። 7: እኔንስ ብታውቁኝ አባቴን ደግሞ ባወቃችሁ ነበር። ከአሁንም ጀምራችሁ ታውቁታላችሁ አይታችሁትማል።” 8: ፊልጶስ፦ “ጌታ ሆይ፥ አብን አሳየንና ይበቃናል፡” አለው። 9: ኢየሱስም አለው፦ “አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ፦ ‘አብን አሳየን፡’ ትላለህ? 10: እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? እኔ የምነግራችሁን ቃል ከራሴ አልናገረውም፤ ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሠራል። 11: እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ባይሆንስ ስለ ራሱ ስለ ሥራው እመኑኝ። 12: እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል፥ 13: እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና፤ አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ። 14: ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።” 15-16: “ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ* ይሰጣችኋል፤ (* አጽናኝ ማለት በግሪክ ቋንቋ ጰራቅሊጦስ ማለት ነው) 17: እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ። 18: ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ። 19: ገና ጥቂት ዘመን አለ ከዚህም በኋላ ዓለም አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ እኔ ሕያው ነኝና እናንተ ደግሞ ሕያዋን ትሆናላችሁ። 20: እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ። 21: ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ።” 22: የአስቆሮቱ ያይደለ ይሁዳ፦ “ጌታ ሆይ፥ ለዓለም ሳይሆን ራስህን ለእኛ ልትገልጥ ያለህ እንዴት ነው?” አለው። 23: ኢየሱስም መለሰ፡ አለውም፦ “የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል፡ ወደ እርሱም እንመጣለን፡ በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን። 24: የማይወደኝ ቃሌን አይጠብቅም፤ የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም። 25: ከእናንተ ዘንድ ስኖር ይህን ነግሬአችኋለሁ፤ 26: አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል። 27: ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም። 28: እኔ እሄዳለሁ ወደ እናንተም እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ። የምትወዱኝስ ብትሆኑ ከእኔ አብ ይበልጣልና ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር። 29: ከሆነም በኋላ ታምኑ ዘንድ አሁን አስቀድሞ ሳይሆን፥ ነግሬአችኋለሁ። 30: ከእንግዲህ ወዲህ ከእናንተ ጋር ብዙ አልናገርም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ይመጣልና፤ በእኔ ላይም አንዳች የለውም፤ 31: ነገር ግን አብን እንድወድ ዓለም ሊያውቅ፥ አብም እንዳዘዘኝ፥ እንዲሁ አደርጋለሁ። ተነሡ፤ ከዚህ እንሂድ።”

  • 6 июл.1 5145

    ​እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በዓለ ልደት አደረሰን ሰኔ 30 ጉዞዋችን እንዳይረሳ። የሸንኮራ መጥምቁ ዮሐንስ ሐኪማችን!!! የሸንኮራ ዮሐንስን ተአምር ለዓለም ያስተዋወቀችው ነፍሰ ኄር ፍቅርተ ሥላሴን ወ/ሮ ሳባ ሐብቶምን ከሸንኮራ ዮሐንስ ለይቶ ማየት እንዴት ይቻላል የብዙዎቻችን መዳን ምክንያት ናት እህታችን። ይህን ታላቅ ቦታ ዓለም እንዲያውቀው የተጨነቁ እንዲፈወሱ እንዲድኑ በዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ በልሳነ ተዋሕዶ መጽሔት በየቤተክርስቲያኑ አውደ ምሕረት ምስክርነት በመስጠት ብዙዎች ወደ ሸንኮራ እንዲመጡ ምክንያት ነበረች። መጥምቁ ከጡት ካንሰር በሽታ የፈወሳት እግዚአብሔር የፈቀደላትን ዘመን ኖራ በሞት የተለየችን ወ/ሮ ሳባ ሐብቶም ስመ ጥምቀታ ፍቅርተ ሥላሴ ትጉኅ አገልጋይ አንደበተ መልካም ዳግማዊት አቢጊያ 116 ሰዎች በሷ ምክንያት በጥምቀት ከኛ ወገን ያልነበሩ ክርስትና ተነስተው ሐብተ ውልድና ስመ ክርስትና ተቀብለዋል ይህ ስውር ገድሏ ነው። የድሆች እናትም ነበረች ተነግሮ የማያልቀው የሸንኮራ ዮሐንስ ጸበል ድንቅ ተአምር!!! በመጥምቁ ዮሐንስ ጸበል ከጡት ካንሰር ድና ለምስክርነት የበቃች እህታችን ሳባ ሐብቶም። አንዳንድ አፈር ዘሪዎች በጸበል የዳነ ሰው ተረፈ ደዌ አለበት መልሶ ህመሙ ያገረሽበታል ይላሉ እምነት የጎደላቸው እህታችን ሳባ ከህመሟ ድና ከ20አመት በላይ ኖራለች 20ቀን አትቆይም ከጡትሽ አልፎ በመላ ሰውነትሽ ካንሰሩ ተሰራጭቷል ተብላ እግዚአብሔር በወዳጁና በአገልጋዮ መጥምቁ ዮሐንስ ጸበል እንድትድን ብቻ ሳይሆን በአደባባይ ቆማ የእግዚአብሔር ቸርነት የመጥምቁን አማላጅነት ለመመስከር በቅታለች። ህክምናዋን በወቅቱ በጥቁር አንበሳ በባልቻ ሆስፒታል በቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል በብሩክ ክሊኒክ ትከታተል ነበር። በተለይ ኘሮፌሰር ታዬ በልዮ ሁኔታ ህክምናውን ትወስድ ነበር የሞት አዋጅ ታወጀባት ስነቅዋን ቋጥራ የመግነዝ ጨርቋን አሰፍታ እደጁ ልቀበር ብላ ወደ ሸንኮራ ዮሐንስ መጣች ገና ደጁን እንደረገጠች ያ የሚዘገንን ለዓይን የሚያስፈራ ጡትዋ ፈንድቶ ማስታጠቢያ ሙሉ ደምና መግል ፈሰሰ ሳይሆን ዘነበ ጸንታ ታግሳ ጸበልዋን ያን ገደል ከነቁስልዋ እየወረደች ስትጠመቅ ቆየች ስቃይዋ ተነግሮ አያልቅም ግን እግዚአብሔር ምክንያት አለው ለውጥ ማምጣት ጀመረች ከወራት ቆይታ በኋላ አዲስ አበባ መጥታ አዲስ ካርድ አስወጥታ ተመረመረች ነጻ ናት ያለፈ የሕክምና ታሪኬ አለ አውጡት ብላ አስወጣች ቀድሞ የሚያውቃት በህመምዋ ኢ አማኒ የሆነ ዶክተር ደነገጠ ቀድሞ ሞት የታወጀበት አሁን ጤና ሕይወት የተገለጠበት የህክምና ውጤት ወረቀት በእጁ እያየ። እነ ኘሮፌሰር ታዬ ከዛ ቀን ጀምሮ ዶክተር ዮሐንስ የሚባል ቅዱስ አለ በጸበሉ የሚፈውስ እያሉ በርካታ ህሙማንን የሳባን ስልክ እየሰጡ ብዙዎች በሸንኮራ ዮሐንስ ጸበል ድነዋል። ሳባ በየሆስፒታሉ እየሆደች የማታውቃቸውን በሽተኞች በተለይ በካንሰር የተያዙ ሕሙማንን ነርሶችን እየጠየቀች የመጎብኘት ልማድ አላት ታድያ የመጥምቁ ጸበል ይህውላችሁ ቃለ አዋዲ መጥምቅ የመግነዙን ጨርቅ የዝክሩ ምጣድ ማሰሻ አደርገው የእንባ አድርቅ ለእዝን ንፍሮ ሊቀቀል የተዘጋጀው ስንዴ የዝክሩ ድፎ ዳቦ ሆነ አምላከ ዮሐንስ ይመስገን። ወይዘሮ ሳባ ሐብቶም የደብራችን ብስራተ ገብርኤል አጥቢያ ነዋሪና የብዙ አገልጋዮች እናት ናት መቼም የመጥምቁን ዝክር ሳባ ቤት መጥቶ ያልቀመሰ አብሮዋት በደስታ ያላነባ ዘማሪ ሰባኪ የለም። "መንክር እግዚአብሔር በላዕለ ቅዱሳኒሁ።" የዘረኝነት ቁስል የተመታችው ኢትዮጵያን የፍቅር ረሐብ ያጎሳቆላት ኢትዮጵያን በዛር መንፈስ ልጆችዋ የሚጋልቡባት ኢትዮጵያን ቃለ አዋዲ መጥምቁ አራሚው ሰማዕት ነብዮ ካህኑ ሐዋሪያው ነብዮ ካህኑ የሙሽራው ወዳጅ ባሕታዊ ቅዱስ ዮሐንስ በምልጃ ጸሎቱ ያስባት በቃልኪዳኑ ይጠብቃት የእህታችንን ነፍስ በአብርሃም እቅፍ ያኑርልን አሜን አሜን አሜን

  • 30 июн.1 83277

    ....በምትጸልይበት ጊዜ ከከሰስህ ራስህን ክሰስ፡፡ ምላስህን ብትስልና ብታሾል በገዛ ኃጢአቶችህ ላይ ይኹን፡፡ አንተ ራስህ በገዛ ራስህ ላይ ያደረግኸውን እንጂ ሌላው በአንተ ላይ ያደረገብህን ክፉ ነገር አትናገር። እጅግ የሚከፋው ጉዳት አንተ ራስህ በራስህ ላይ የምታደርሰው ጉዳት ነውና፡፡ አንተ ራስህ ራስህን ካልጎዳኸው በቀር ሌላው አንተን ሊጎዳህ አይችልምና። ስለዚህ የሚበድሉህን ትበቀላቸው ዘንድ ብትሻ፥ መጀመሪያ በራስህ ላይ ተነሣሣ፤ ያን ጊዜም ማንም የሚደበቅ የለም። ሌላውን ለመክሰስ ብለህ ፍርድ ላይ ብትቀመጥ በአንተ ላይ ትልቁን ጉዳት ያደረስኸው አንተው ራስህ መኾንህ ተፈርዶብህ ትመለሳለህና፡፡ እንደው እስኪ ንገረኝ! እገሌ “በድሎኛል'' ብለህ መጥቀስ የምትችለው በደል ምንድን ነው? ያ እገሌ ያልኸው ሰው እንደ ሰደበህ፣ እንደ ቀማህ፣ ብዙ የብዙ ብዙ በኾኑ ሥጋቶችም እንደ ከበበህ ነው የምትጠቅስውን? ተው ይህ በደልን መቀበል አይደለም:: እኛ በመጠን ብንኖር ትልቁን ጥቅም የምናገኘው እኛው ነን፡፡ የሚጎ'ዳው እንዲህ ያደረሰው ሰው ነው እንጂ እንዲህ የተቀበለው ሰው አይደለም። ተጎጂውና ጎጂው ማን እንደ ኾነ ለይቶ ፍጹም አለማወቅ ደግሞ ለክፋታችን ኹሉ መንሥኤ ከኾኑ ነገሮች ኹሉ ቀዳሚው ነው። ይህንን በደንብ ብናውቀው ኖሮ ራሳችንን ባልጎዳነው ነበር፤ ሌላውን ሰው ልንጎዳው እንደማንችል ዐውቀን ያ ሌላው ሰው እንዲጎ'ዳ ብለን ባልጸለይን ነበር:: በደል ዕዳ የሚኾንብን ሌላው ሰው ሲበድለን ሳይኾን እኛ ሌላ ስውን ስንበድል ነውና። ስለዚህ ሌላውን በድለህ እንደ ኾነ ራስህን መርምር፤ ተበድለህ እንደ ኾነ ግን ከኹሉ የሚበልጠውን በጎ ነገርን አድርጎልሃልና ለበደለህ ሰው ጸልይለት፡፡ ምንም እንኳን የበዳዩ ሕሊና እንደዚያ ያልነበረ ቢኾንም፥ አንተ ግን በአኰቴት የታገሥኸው እንደ ኾነ ከኹሉ የሚበልጠውን ረብ ጥቅም ታገኛለህ፡፡ የበደለህን ስው ጻድቃን ሰዎችም ሕግጋተ እግዚአብሔርም ክፉ ግብሩን ይመሰክሩበታል የተበደልከው አንተን ግን አክሊል ያጎናጽፉሃል፤ ከፍ ከፍ አድርገውም ያመሰግኑሃል። አንድ በንዳድ የታመመ ሰው፥ ውኃ የያዘ ዕቃውን ሌላ ሰው መጥቶ በኃይል ቢነጥቀውና ጽኑ ጥሙን ቢያረካ፥ የተነጠቀው እና በንዳድ የታመመው ሰው ተበድሏል አንልም:: የተጎዳው የነጠቀው ሰው ነው ግን እንላለን፡፡ ምክንያቱም የታማሚውን ንዳድ አባብሶበታል፤ ሕመሙ እንዲጸናበትም አድርጎታል:: በዚህ መንገድ በሀብትና በገንዘብ ፍቅር የተያዘ ሰውም እነግርሃለሁ እንዲሁ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ሰውም ከድኻው ሀብትንና ንብረትን በመቀማት ከዚያኛው በሰውነት ትኩሳት ከታመመው በላይ በራሱ ላይ ነደ እሳት እንዲንቀለቀል አድርጓልና:: ዳግመኛም አንድ አእምሮውን ያጣ ሰው ከሌላ ሰው ሰይፍ ነጥቆ ራሱን ቢገድል ተጎጂው ማን ነው? የተነጠቀው ነው ወይስ ቀማኛው? ቀማኛው እንደ ኾነ ግልፅ ነው፡፡ መልካም! በኃይል ንብረት በመውሰድ ጉዳይ ላይም ተመሳሳይ የኾነ ነገር እናድርግ፡፡ አእምሮውን ያጣ ሰው ስለት እንደሚይዝ፥ ለስስታም ሰው ደግሞ ገንዘብ እንደዚያ ነው:: እንዲያውም ከዚያም የከፋ ነው:: አእምሮውን ያጣው ሰው ስለት ቢያነሣና በዚያ ራሱን ቢወጋ ያን ጊዜ አእምሮውን ከማጣት ይድናል፤ ድጋሚም ራሱን በዚያ መንገድ አይጎዳም:: ፍቅረ ንዋይ የጸናበት ሰው ግን ከዚያኛው ሰው ይልቅ ከደዌውም ሳይድን ይባስኑም ሕመሙን ጽኑ እንዲኾን በማድረግ ዕለት ዕለት ቍጥር የሌላቸው ቁስሎች ያገኙታል፡፡ በቆሰለ መጠንም ሌሎችን ቁስሎችን በራሱ ላይ በመጨመር ደዌውን ያባብሰዋል:: እንግዲያውስ እነዚህን ነገሮች እያሰብን ከዚህ ስለት እንራቅ፤ ከዚህ ዕብደት እንሽሽ:: የቱንም ያህል ብንዘገይም ራሳችንን የምንገዛ (ልከኞች) እንኹን፡፡ ይህ ምግባርንም በሰው ኹሉ ዘንድ እንደዚያ ከሚባለው ጋር እኩል ራስን መግዛት መባል ይገባናዋልና፡፡ አንድ ፍትወት በእኛ ላይ ቢሠለጥን እርሱን ከእኛ እናርቅ ዘንድ ልንጋደል የተገባ ከኾነ፥ ይህን የተጋደልን እንደ ኾነም የብዙና የልዩ ልዩ ፍትወታትን ጌታ ተጋደልን ማለት ነው፡፡ አዎን፥ የገንዘብ ባሪያ ከኾነ በላይ ሌላ ሰነፍ ሰው የለምና፡፡ ድል የተደረገ ኾኖ ሳለ ድል እንዳደረገ ያስባልና፡፡ ባሪያ ሊኾን ጌታ እንደ ኾነ ያስባልና፡፡ ራሱን በሰንሰለት አስሮ ደስ ይሰኛልና፡፡ አውሬውን እያበረታው እርሱ ደስ ይለዋልና:: ምርኮኛ ኾኖ ሳለ ይመካልና፤ በደስታም ይዘላልና፡፡ ይህን ዕብድና ነፍሱን ሊነክስ የሚሯሯጠውን ውሻ ሊያስረውና በረሃብ ሊያዳክመው ሲገባው ይባስኑ ጉልበት አግኝቶ በእርሱ ላይ ይዘልበት ዘንድ ብዙ ምግብ በርግጥ ያቀርብለታልና፤ እንዲበረታታበትም ያደርጋልና፡፡ እንኪያስ እነዚህን ኹሉ ነገሮች በማሰብ ከእስራታችን እንፈታ፤ ጭራቁን እንግደለው፤ ደዌውን እናርቀው፤ ይህን ዕብደት ከእኛ እናስወጣው:: ይህን ያደረግን እንደ ኾነም የተረጋጋንና ንጹሕ ጤንነትን እናገኛለን፡፡ በሐሴት ተሞልተንም ጸጥታን ወደ ተሞላች ወደብ እንጓዛለን፤ እነዚያን ዘለዓለማዊ በረከቶችንም እንወርሳን፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቸርነቱና ለሰው ባለው ፍቅር ኹላችንንም ለዚህ ያብቃን፤ ለእርሱ ክብርና ኃይል ዛሬም ዘወትርም እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን! (የማቴዎስ ወንጌል ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው ቅጽ ፫ ገጽ 25-27 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)

  • 24 июн.2 375205

    "አጠገብ ያለ ጸበል ልጥ መንከሪያ ይሆናል" ይላሉ አባቶቻችን ሲተርቱ ። አጠገባችሁ (አጥቢያችሁ) ባለ ቤተ ክርስቲያን ያለውን ጸበል ትታችሁ በየቦታው "አጥማቂ መጣ" ስትባሉ ግርርር ብላችሁ የምትሄዱ ሰዎች አጠገባችሁ ያለ ጸበል አያድንም ወይ !? ። "እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም" የሚለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል እግዚአብሔር በየትኛውም ጊዜ እና ወቅት ቦታም ጭምር ሲያድን እንደማይለዋወጥ ነው ። ለምሳሌ የሆኑ አንድ "አጥማቂ ሰውዬ" በጸበል አድናለው ብለው ሕዝብ ከሚያንከራትቱበት ቦታ ሄጄ ከምወናበድ አጠገቤ ያለው የቅዱስ ራጉኤል ጸበል እንደሚያድን አምኜ ብጠመቅ እድናለሁ ። እናንተም ይኸንን አስተሳሰብ ብትይዙ ከብዙ ስህተት ትድናላችሁ ። እንደሚታወቀው የትኛውም በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያናችን መሠረት ክህነት የተቀበለ ካህን የማጥመቅ ጸጋ ተሰቶታል ። የማጥመቅ ጸጋ ለብቻው የሚሰጠው ካህን የለም ። ካህን የሆነ በሙሉ ማጥምቅ ማቁረብ ማስተማር ጸጋው ነው ። ወይም ከክህነቱ አገልግሎቱ አንዱ ነው ። መጠመቅ ግዴታ ከሆነብህ አጥቢያ ባለ የመጠመቂያ ሥፍራ ተጠመቅ ። ይኸም ካልሆነልኸ የንስሐ አባትህን ጠርተኸ ከቧንቧ ውሃ ቀድትህ እንዲጸልዩበት አድርገኸ ያጥምቁኸ ። ውሃን ወደ ጸበል የመቀየር ሥልጣን የሁሉም ካህን ጸጋ ነው ። እንደ አመንዝራ ትውልድ ካህን እያማረጥክ መንፈሳዊ ትሩፋት አገኛለው ብለኸ ካሰብክ መጀመሪያም መጨረሻም ጸብኸ ክህነትን ከሰራው ከእግዚአብሔር ጋር ነው ። ሲቀጥል ሁሉንም መንፈሳዊ ችግር በጸበል ብቻ ለመፍታት ከመሞከር ታቀብ ። ማስቀደስ ጸሎት ንስሐ ቅዱስ ቁርባን ምጽዋት መስገድ በጎ ሥራ ቱሩፋት አስራት በኩራት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ባሉ መዋቅር ውስጥ ገብቶ ማገልገል (ሰበካ ጉባኤ ሰንበት ት/ቤት ማሕበራት ...) እነዚህም እኮ ላወቀባቸው ሰዎች መንፈሳዊ ሕይወትን ለማሻሻል ፍቱን መድኃኒት ናቸው ። የፎቶውን ነገር ግን ተዉኝ እስቲ ... ሰዉ ከሥርዓት ቤተ ክርስቲያን ከራቀ የማንም መጫወቻ ነው የሚሆነው ። Zekaryas Kiros

  • 24 июн.1 8444

    без подписи

  • https://www.facebook.com/share/r/1BKrBXCHFF/

  • 14 июн.2 966186

    “እምነት አለኝ” ብሎ ምግባር የሌለው ሰውና፥ “ምግባር አለኝ” ብሎ እምነት የሌለው ሰው እኩል ናቸው፤ ኹለቱም መንግሥተ ሰማያት አይገቡም፡፡ ስለዚህ “እምነት አለን” ብለን ልል ዘሊላን አንኹን ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ይላልና፡- “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም” (ማቴ.7፡21)፡፡ ስለዚህ እምነት እንደሌላቸው ሰዎች ከመንግሥተ ሰማያት ውፁአን እንዳንኾን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ነቅተን እንሥራ፡፡ ምግባር ትሩፋትን ተግተን እንሥራ፡፡ አምነን ልጅነትን ከተቀበልን በኋላ ልጅነታችንን አጽንተን የምንጠብቀው፣ ርስቱንና መንግሥቱንም የምንወርሰው ይህን ያደረግን እንደ ኾነ ነውና ነቅተን እንሥራ፡፡ እኛ ሥራ ሠርተን አንበቃምና ጽዋ ተርታችን ዕድል ፈንታችን ይህ ይኾን ዘንድ ከባሕርይ አባቱ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ጌትነቱ፣ ኃይሉና ክብሩ አንድ የሚኾን ጌታችንና መድኃኒታችን በቸርነቱና ሰውን በመውደዱ ይርዳን፤ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ አሜን!!! (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

  • 25 апр.4 36794

    без подписи

  • 25 апр.3 702145

    ብዙ ጊዜ የምታዘበው በተለይም እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ስሄድ ትዝ የሚለኝ ነገር አለ እርሱም የእቅፍ አበባ ስዕለት የሚያስገቡ ምዕመናን ናቸው የሚያመጡት ስለሚሳሉ ነው ግን አንደኛ እንዲህ አይነት ስዕለት በቤተ ክርስቲያን ያልተለመደና ሰዎችን ሁሉ በሚያስደስታቸው ነገር ልክ ለእግዚአብሔርና ለቅዱሳንም እንደሚያስደስታቸው በማሰባችን እንጂ ይህ መባ በቤተ ክርስቲያን የተለመደ አይደለም አበባ በብዙ ነገር የሚተረጎም ቢሆንም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ግን አበባ የሚታዘዝበትና አገልግሎት የሚሰጥበት ነገር የለም ብንጠቀመው እንኳን እንደ ወርሐ ጽጌ ባለ ወቅት የክርስቶስንና የእመቤታችንን ምሳሌ ለመግለጽ ብንይዘው እንጂ ያን ያህል የአበባ አያያዝ መመሪያ ወጥቶ አይደለም እርሱም እንዳለ ቢቀጥል ችግር የለውም ግን የእቅፍ አበባ ዓውደ ምሕረት ላይ መሰብሰብ ግን ምንም አይነት የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮትን የተከተለ አይደለም ሁለተኛ በየትኛውም አገልግሎት ውስጥ ቦታ ሰጥተነው የሚጠቅም ነገር አይደለም ምዕመናን በውድ ዋጋ ወስደው ያስገቡታል የተራበ አይበላው ለአገልግሎት አይውል እንደ ንብረት አይቆጠር ጊዜው ሲያልፍ ይጣላል ሦስተኛ መደበኛውን ስዕለትና ስጦታ እንድንዘነጋ ያደርጋል ብዙ ሰው ሰዎች የሚያደርጉትን አይቶ በበጎ ነገር ብቻ ተርጉሞ ስለሚያደርግ መደበኛ መባዎችን ያዘነጋናል አራተኛ የቤተ ክርስቲያንን ገጽታ ከመንፈሳዊነት ይልቅ ወደ ሌላ ገጽታ የሚቀይር ስለሆነ በዚህ ዙሪያ ሁለት መፍትሔዎች ቢደረጉ መልካም ነው እነርሱም አንደኛ በዚህ ዙሪያ ማስተማር ቢቻልና ምዕመናን ይህንን ተረድተው የሚያመጡት አበባ ምንም አገልግሎት እንደማይሰጥ አውቀው ሌላ ለአገልግሎት የሚውል ስዕለት እንዲሳሉ ግንዛቤ መስጠት ሁለተኛ በእየ ዓውደ ምሕረቱ ላይ የሚሰበሰቡ አበቦች ሥርዓት ባለው መንገድ ቢቀመጡና አበባም ካስፈለገ በጥቂቱ አስቀምጦ ሌላውን ከጸሎትና ከትምሕት ቦታ ገለል በማድረግ አበባ የሚያመጡ ሰዎችንም እየመዘገቡ ከአቅማቸው በላይ በሆነ ዋጋ የእቅፍ አበባ የሚያመጡትን ጧፍና እጣን እንዲያመጡ መምከና በተረፋቸው ብር ነዳያንን እንዲመጸውቱበት ማበረታታት መልካም ይመስለኛል! በቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎት ለማይሰጥ ነገር የምዕመናን ገንዘብ መውጣቱ መልካም አይደለም።