tgindex
መንፈሳዊ ጉባኤ

መንፈሳዊ ጉባኤ

Статистика

ወዳጄ ሆይ፥ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥ነውርም የለብሽም። መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 4 : 7 @Menfesawi_Gubae ጥያቄ ካላችሁ ከታች ባለው አድራሻ መጠየቅ ትችላላችሁ። @HenokAsrat3

Последний пост
7 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 376
−3 за 5 дн.
Сутки
−1
−0,04%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
618
20 постов
Вовлечённость
26,0%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
316
1/48двое суток
362
1/72трое суток
390

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • без подписи

  • ‹‹ፍልሰታ›› የሚለው ቃል «ፈለሰ» ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን በጥሬ ትርጉሙ መለየት፣ ማረግ እና ወደላይ መውጣት ማለት ነው። የእመቤታችን ዕረፍት፦ እመቤታችን ድንግል ማርያም ያረፈችው በጥር 21 ቀን ነው። ሐዋርያት ሊቀብሯት ሲሄዱ አይሁድ በምቀኝነት ስለተቃወሟቸው መላእክት አስከሬኗን ነጥቀው በገነት አኖሩት። የሐዋርያት ሱባዔና ቀብር፦ ሐዋርያት ከነሐሴ 1-14 ሱባዔ ገብተው በጸሎት ከጌታችን ተቀብለው በክብር ቀበሯት። የቅዱስ ቶማስ ምስክርነት፦ ሐዋርያው ቶማስ በወቅቱ ባለመኖሩ በሦስተኛው ቀን እመቤታችን ስታርግ በደመና ላይ አያት። እርሷም ማጽናኛ እና ምስክር እንዲሆን ሰበኗን ሰጠችው። የሐዋርያት በረከት፦ ቶማስ ሰበኗን ለአካፈላቸው በኋላ፣ ሐዋርያትም የእመቤታችንን ትንሣኤና ዕርገት ለማየት በዓመቱ ከነሐሴ 1 ጀምረው ሱባዔ ገቡ። በነሐሴ 16 ቀን ጌታችን ከመላእክት ጋር መጥቶ እመቤታችንን አስነሥቶ አሳይቷቸዋል። ዛሬም ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሐዋርያትን ምሳሌ ተከተላ ከሰባቱ አጸዋማት አንዱ በማድረግ ይህንን ጾም እንድንጾም አዝዛናለች። የጾሙና የእመቤታችን የትንሣኤዋና የዕርገቷ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን! 🙏

  • "ነገ ሐምሌ 22 መልአከ ብርሃናት ቅዱስ ዑራኤል ቅዳሴ ቤቱ ተከብሮ ይውላል ብርሃኑን ያብራልን🙏 ✥ቅዱስ ዑራኤል ከሊቀ መላእክት አንዱ ነው። መላእክት በስማቸው ቅጥያ ኤል የሚል ቃል አለ ይኸውም እግዚአብሔር ማለት ነው። "ዑር" ማለት ብርሃን፤ "ኤል" ማለትም እግዚአብሔር ማለት ነው።ዑራኤል ማለት የብርሀን ጌታ፣ የብርሀን አምላክ ማለት ነው። ✥ የሰማይን ሚስጥር ለሄኖክ እውቀትን የገለጸለት መልአክ ነው። የፀሐይን የጨረቃን የከዋክብትንና የሰማይ ሰራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለሄኖክ ነግሮታል። መ.ሄኖክ 28፥13 ✔️በብርሃናት ሁሉ ሊቀ ብርሃናት ሆኖ የተሾመው ቅዱስ ዑራኤል ነው። ✔️ቅዱስ ዑራኤል በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ ስለሆነ እርሱም መባርቅትን ለጥጋብና ለበረከት እንዲሁም ነጎድጓድን ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል። መ.ሄኖክ ፮፥፪ ➕ ምስጢረ ሰማይና እውቀትንም ሁሉ ለሄኖክ የገለጸለት የፀሐይን የጨረቃን የከዋክብትንና የሰማይ ሰራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለሄኖክ ነግሮታል። ✥ቅዱስ ዑራኤል ልቡናን የሚያበራ እውቀትን የሚገልጽ ርሑሩህ መልአክ ነው። ቅዱስ ዑራኤል ለነብዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋአ ልቡናን አጠጥቶት ሰማያዊ ሚስጥራትን ገልፆለታል። ነብዩ እጅግ ብዙ ቁጥር ያላቸውን መጻሕፍት ደርሷል። በሰዓታቱም "ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ምስለ ኤልያስ ወኤልሳዕ ነቢያተ እስራኤል ወምስለ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋዓ ልቡና ዘአስተዮ ዑርኤል፡፡" "ነይ ወደ እኛ ድንግል ሆይ ከእስራኤል ነብያት ከኤልያስና ከኤልሳ እንዲሁም ዑራኤል ጽዋ ልቡናን ካጠጣው ከእዝራ ሱቱኤል ጋር።" ✥ሌላኛው ቅዱስ ዑራኤል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእጸ መስቀል ላይ በቀራንዮ በአምስቱ ቅንዋት (ሳዶር፣አላዶር፣ዳናት፣አዴራ፣ሮዳስ) ሲቸነከር ይህ ብርሃናዊ መልአክ ነው ከጎኑ የክርስቶስን ደም በጽዋ ቀድቶ በዓለም ሁሉ የረጨው። ✥እመቤታችን ወደ ግብፅ በተሰደደች ጊዜ በዚህ የጭንቅ ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን እየተራዳ መንገድን እየመራት በብርሃን ወደ ሀገረ ግብፅ ቀጥሎም ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም አስራት ወደ ሆነቻት ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ እየመራት መጥቷል። ማቴ 2÷13-15 ✥ሌላው የእውቀትን ብርሃን የገለጸላቸው የእውቀትን ጽዋ ያጠጣቸው ለሊቁ አባታችን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነው። እኚም አባታችን በመልአኩ ተራዳኢነት ብዙ ድርሰቶችን ደርሰዋል። እመቤታችንም በምልጃዋ ቅዱስ ዑራኤል የእውቀትን ጽዋ ያጠጣቸው ዘንድ አድርጋለች። አባ ጊዮርጊስ እመቤታችንን ይወዷት ስለነበረ አርጋኖን ሌሎችንም ደርሰዋል። የሊቀ ብርሃናት ቅዱስ ዑራኤል በረከት ተራዳኢነት አይለየን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር 🙏

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • ‹‹ሐምሌ 7›› አጋዕዝተ ዓለም ስላሴ በአብርሃም ቤት ተገኝተው ቤቱን የባረኩበት የአንድነታቸውንና ሶስትነታቸው ሚስጢር የገለጹበት ታላቅ በዓል ነው። በዚችም ቀን ልዩ የሆኑ ሦስቱ አካላት /ቅድስት ሥላሴ/ በኦሪት መጽሐፍ እንደ ተጻፈ ወደ አብርሃም ቤት ገቡ ያቀረበላቸውንም ተመገቡ፡፡ የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት ለመረዳት በሥላሴ ፈቃድ መጻሕፍት እንዳስተማሩ ሊቃውንት እንደተረጉሙልን እንጂ ማንም በገዛ ፈቃዱ ተመራምሮ አይደርስበትም፡፡ የሐምሌ 7 ቀንም ሥላሴ በአብርሃም ቤት ገብተው ቸርነታቸውና ፍቅራቸውን የገለጹበት፣ ስለሆነ በዓሉን ስናዘክር ሥላሴን እናመሰግናለን፡፡ በአጠቃላይ በዚህ ዕለት በአብርሃም ቤት እግዚአብሔር የተስተናገደበት፣ አንድነቱና ሦስትነቱ የተገለጠበት፣ አብርሃም እና ሣራ ካረጁ በኋላ ልጅ እንደሚወልዱ የተበሠረበት፣ ይሰሐቅንም እንደሚወልድ የተነገረበት ዕለት ነወ። ለአብርሃም ምሥጢሩን የገለጠ እግዘአብሔር ለሁላችን ይግለጥልን🙏

  • без подписи

  • +++ ብርሃናተ ዓለም +++ "ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ምንም ብታውቁ በእናንተም ዘንድ ባለ እውነት ምንም ብትጸኑ፥ ስለ እነዚህ ዘወትር እንዳሳስባችሁ ቸል አልልም። ሁልጊዜም በዚህ ማደሪያ ሳለሁ በማሳሰቤ ላነቃችሁ የሚገባኝ ይመስለኛል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳመለከተኝ ከዚህ ማደሪያዬ መለየቴ ፈጥኖ እንዲሆን አውቃለሁና። ከመውጣቴም በኋላ እነዚህን ነገሮች እንድታስቡ በየጊዜው ትችሉ ዘንድ እተጋለሁ።" ቅዱስ ጴጥሮስ (2ጴጥ 1:12-15) "መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፥ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም።" ቅዱስ ጳውሎስ (2ጢሞ 4:7) ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ጳውሎስ ለቤተክርስቲያን ብዙ የተጋደሉ ለምዕመናን በቀለም ብቻ ሳይሆን በደማቸው ጽፈው ለትውልድ አሻራቸውን ያስቀመጡ ክርስቶስ ምዕመናንን አደራ ያስጠበቃቸው ስለተሰጡት አደራ ብለው አንገታቸውን የሰጡ ሐምሌ አምስት ቀን ቅዱስ ጴጥሮስ ተዘቅዝቆ የተሰቀለበት ቅዱስ ጳውሎስ በሰይፍ አንገቱ የተቆረጠበት እለት ነው ። የሐዋርያቱ የቅዱስ ጴጥሮስ እና የጳውሎስ በረከት አይለየን አሜን !

  • "ሰው መሆንህን ለድካምህ እንደ ምክንያት አታቅርብ፤ በትዕግሥት መልአክ መሆን ትችላለህና፤ ጌታችን ለሚወዱትና ፈቃዱን ለሚፈጽሙት እንደመላእክት ይሆኑ ዘንድ ተስፋ አስደርጓቸዋልና።" ምክረ አረጋዊ

  • "ኢየሱስም እንዲህ አለ፦ “..ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራምም።" የዮሐንስ ወንጌል ምእራፍ - 14 1: ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ። 2: በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤ 3: ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ። 4: ወደምሄድበትም ታውቃላችሁ፥ መንገዱንም ታውቃላችሁ። 5: ቶማስም፦ “ጌታ ሆይ፥ ወደምትሄድበት አናውቅም፤ እንዴትስ መንገዱን እናውቃለን?” አለው። 6: ኢየሱስም አለው፦ “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። 7: እኔንስ ብታውቁኝ አባቴን ደግሞ ባወቃችሁ ነበር። ከአሁንም ጀምራችሁ ታውቁታላችሁ አይታችሁትማል።” 8: ፊልጶስ፦ “ጌታ ሆይ፥ አብን አሳየንና ይበቃናል፡” አለው። 9: ኢየሱስም አለው፦ “አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ፦ ‘አብን አሳየን፡’ ትላለህ? 10: እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? እኔ የምነግራችሁን ቃል ከራሴ አልናገረውም፤ ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሠራል። 11: እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ባይሆንስ ስለ ራሱ ስለ ሥራው እመኑኝ። 12: እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል፥ 13: እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና፤ አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ። 14: ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።” 15-16: “ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ* ይሰጣችኋል፤ (* አጽናኝ ማለት በግሪክ ቋንቋ ጰራቅሊጦስ ማለት ነው) 17: እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ። 18: ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ። 19: ገና ጥቂት ዘመን አለ ከዚህም በኋላ ዓለም አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ እኔ ሕያው ነኝና እናንተ ደግሞ ሕያዋን ትሆናላችሁ። 20: እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ። 21: ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ።” 22: የአስቆሮቱ ያይደለ ይሁዳ፦ “ጌታ ሆይ፥ ለዓለም ሳይሆን ራስህን ለእኛ ልትገልጥ ያለህ እንዴት ነው?” አለው። 23: ኢየሱስም መለሰ፡ አለውም፦ “የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል፡ ወደ እርሱም እንመጣለን፡ በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን። 24: የማይወደኝ ቃሌን አይጠብቅም፤ የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም። 25: ከእናንተ ዘንድ ስኖር ይህን ነግሬአችኋለሁ፤ 26: አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል። 27: ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም። 28: እኔ እሄዳለሁ ወደ እናንተም እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ። የምትወዱኝስ ብትሆኑ ከእኔ አብ ይበልጣልና ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር። 29: ከሆነም በኋላ ታምኑ ዘንድ አሁን አስቀድሞ ሳይሆን፥ ነግሬአችኋለሁ። 30: ከእንግዲህ ወዲህ ከእናንተ ጋር ብዙ አልናገርም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ይመጣልና፤ በእኔ ላይም አንዳች የለውም፤ 31: ነገር ግን አብን እንድወድ ዓለም ሊያውቅ፥ አብም እንዳዘዘኝ፥ እንዲሁ አደርጋለሁ። ተነሡ፤ ከዚህ እንሂድ።”

  • ....በምትጸልይበት ጊዜ ከከሰስህ ራስህን ክሰስ፡፡ ምላስህን ብትስልና ብታሾል በገዛ ኃጢአቶችህ ላይ ይኹን፡፡ አንተ ራስህ በገዛ ራስህ ላይ ያደረግኸውን እንጂ ሌላው በአንተ ላይ ያደረገብህን ክፉ ነገር አትናገር። እጅግ የሚከፋው ጉዳት አንተ ራስህ በራስህ ላይ የምታደርሰው ጉዳት ነውና፡፡ አንተ ራስህ ራስህን ካልጎዳኸው በቀር ሌላው አንተን ሊጎዳህ አይችልምና። ስለዚህ የሚበድሉህን ትበቀላቸው ዘንድ ብትሻ፥ መጀመሪያ በራስህ ላይ ተነሣሣ፤ ያን ጊዜም ማንም የሚደበቅ የለም። ሌላውን ለመክሰስ ብለህ ፍርድ ላይ ብትቀመጥ በአንተ ላይ ትልቁን ጉዳት ያደረስኸው አንተው ራስህ መኾንህ ተፈርዶብህ ትመለሳለህና፡፡ እንደው እስኪ ንገረኝ! እገሌ “በድሎኛል'' ብለህ መጥቀስ የምትችለው በደል ምንድን ነው? ያ እገሌ ያልኸው ሰው እንደ ሰደበህ፣ እንደ ቀማህ፣ ብዙ የብዙ ብዙ በኾኑ ሥጋቶችም እንደ ከበበህ ነው የምትጠቅስውን? ተው ይህ በደልን መቀበል አይደለም:: እኛ በመጠን ብንኖር ትልቁን ጥቅም የምናገኘው እኛው ነን፡፡ የሚጎ'ዳው እንዲህ ያደረሰው ሰው ነው እንጂ እንዲህ የተቀበለው ሰው አይደለም። ተጎጂውና ጎጂው ማን እንደ ኾነ ለይቶ ፍጹም አለማወቅ ደግሞ ለክፋታችን ኹሉ መንሥኤ ከኾኑ ነገሮች ኹሉ ቀዳሚው ነው። ይህንን በደንብ ብናውቀው ኖሮ ራሳችንን ባልጎዳነው ነበር፤ ሌላውን ሰው ልንጎዳው እንደማንችል ዐውቀን ያ ሌላው ሰው እንዲጎ'ዳ ብለን ባልጸለይን ነበር:: በደል ዕዳ የሚኾንብን ሌላው ሰው ሲበድለን ሳይኾን እኛ ሌላ ስውን ስንበድል ነውና። ስለዚህ ሌላውን በድለህ እንደ ኾነ ራስህን መርምር፤ ተበድለህ እንደ ኾነ ግን ከኹሉ የሚበልጠውን በጎ ነገርን አድርጎልሃልና ለበደለህ ሰው ጸልይለት፡፡ ምንም እንኳን የበዳዩ ሕሊና እንደዚያ ያልነበረ ቢኾንም፥ አንተ ግን በአኰቴት የታገሥኸው እንደ ኾነ ከኹሉ የሚበልጠውን ረብ ጥቅም ታገኛለህ፡፡ የበደለህን ስው ጻድቃን ሰዎችም ሕግጋተ እግዚአብሔርም ክፉ ግብሩን ይመሰክሩበታል የተበደልከው አንተን ግን አክሊል ያጎናጽፉሃል፤ ከፍ ከፍ አድርገውም ያመሰግኑሃል። አንድ በንዳድ የታመመ ሰው፥ ውኃ የያዘ ዕቃውን ሌላ ሰው መጥቶ በኃይል ቢነጥቀውና ጽኑ ጥሙን ቢያረካ፥ የተነጠቀው እና በንዳድ የታመመው ሰው ተበድሏል አንልም:: የተጎዳው የነጠቀው ሰው ነው ግን እንላለን፡፡ ምክንያቱም የታማሚውን ንዳድ አባብሶበታል፤ ሕመሙ እንዲጸናበትም አድርጎታል:: በዚህ መንገድ በሀብትና በገንዘብ ፍቅር የተያዘ ሰውም እነግርሃለሁ እንዲሁ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ሰውም ከድኻው ሀብትንና ንብረትን በመቀማት ከዚያኛው በሰውነት ትኩሳት ከታመመው በላይ በራሱ ላይ ነደ እሳት እንዲንቀለቀል አድርጓልና:: ዳግመኛም አንድ አእምሮውን ያጣ ሰው ከሌላ ሰው ሰይፍ ነጥቆ ራሱን ቢገድል ተጎጂው ማን ነው? የተነጠቀው ነው ወይስ ቀማኛው? ቀማኛው እንደ ኾነ ግልፅ ነው፡፡ መልካም! በኃይል ንብረት በመውሰድ ጉዳይ ላይም ተመሳሳይ የኾነ ነገር እናድርግ፡፡ አእምሮውን ያጣ ሰው ስለት እንደሚይዝ፥ ለስስታም ሰው ደግሞ ገንዘብ እንደዚያ ነው:: እንዲያውም ከዚያም የከፋ ነው:: አእምሮውን ያጣው ሰው ስለት ቢያነሣና በዚያ ራሱን ቢወጋ ያን ጊዜ አእምሮውን ከማጣት ይድናል፤ ድጋሚም ራሱን በዚያ መንገድ አይጎዳም:: ፍቅረ ንዋይ የጸናበት ሰው ግን ከዚያኛው ሰው ይልቅ ከደዌውም ሳይድን ይባስኑም ሕመሙን ጽኑ እንዲኾን በማድረግ ዕለት ዕለት ቍጥር የሌላቸው ቁስሎች ያገኙታል፡፡ በቆሰለ መጠንም ሌሎችን ቁስሎችን በራሱ ላይ በመጨመር ደዌውን ያባብሰዋል:: እንግዲያውስ እነዚህን ነገሮች እያሰብን ከዚህ ስለት እንራቅ፤ ከዚህ ዕብደት እንሽሽ:: የቱንም ያህል ብንዘገይም ራሳችንን የምንገዛ (ልከኞች) እንኹን፡፡ ይህ ምግባርንም በሰው ኹሉ ዘንድ እንደዚያ ከሚባለው ጋር እኩል ራስን መግዛት መባል ይገባናዋልና፡፡ አንድ ፍትወት በእኛ ላይ ቢሠለጥን እርሱን ከእኛ እናርቅ ዘንድ ልንጋደል የተገባ ከኾነ፥ ይህን የተጋደልን እንደ ኾነም የብዙና የልዩ ልዩ ፍትወታትን ጌታ ተጋደልን ማለት ነው፡፡ አዎን፥ የገንዘብ ባሪያ ከኾነ በላይ ሌላ ሰነፍ ሰው የለምና፡፡ ድል የተደረገ ኾኖ ሳለ ድል እንዳደረገ ያስባልና፡፡ ባሪያ ሊኾን ጌታ እንደ ኾነ ያስባልና፡፡ ራሱን በሰንሰለት አስሮ ደስ ይሰኛልና፡፡ አውሬውን እያበረታው እርሱ ደስ ይለዋልና:: ምርኮኛ ኾኖ ሳለ ይመካልና፤ በደስታም ይዘላልና፡፡ ይህን ዕብድና ነፍሱን ሊነክስ የሚሯሯጠውን ውሻ ሊያስረውና በረሃብ ሊያዳክመው ሲገባው ይባስኑ ጉልበት አግኝቶ በእርሱ ላይ ይዘልበት ዘንድ ብዙ ምግብ በርግጥ ያቀርብለታልና፤ እንዲበረታታበትም ያደርጋልና፡፡ እንኪያስ እነዚህን ኹሉ ነገሮች በማሰብ ከእስራታችን እንፈታ፤ ጭራቁን እንግደለው፤ ደዌውን እናርቀው፤ ይህን ዕብደት ከእኛ እናስወጣው:: ይህን ያደረግን እንደ ኾነም የተረጋጋንና ንጹሕ ጤንነትን እናገኛለን፡፡ በሐሴት ተሞልተንም ጸጥታን ወደ ተሞላች ወደብ እንጓዛለን፤ እነዚያን ዘለዓለማዊ በረከቶችንም እንወርሳን፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቸርነቱና ለሰው ባለው ፍቅር ኹላችንንም ለዚህ ያብቃን፤ ለእርሱ ክብርና ኃይል ዛሬም ዘወትርም እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን! (የማቴዎስ ወንጌል ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው ቅጽ ፫ ገጽ 25-27 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)

  • የእውነተኛ ክርስትያን መግለጫው ምንድን ነው? ፀሐይ ብርሃን ካልሰጠች ፀሐይ አትባልም፤ ብርሃን አለመስጠት ተፈጥሮዋ አይደለምና፡፡ እንስሳት ካልተነፈሱ እንስሳት አይባሉም፤ መተንፈስ ተፈጥሮአቸው ነውና፡፡ ዓሣ ከውኃ ከወጣ ሕይወት ያለው ዓሣ መኾኑ ይቀርና ይሞታል፡፡ አንድ ክርስቲያንም እውነተኛ ክርስቲያን የሚባለው፡- ሲጸልይ ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት በወልድ ውሉድ በክርስቶስ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስም መንፈሳዊ መባል ነውና፡፡ ልጅ ከኾኑ ደግሞ አባትን ማናገር ክርስቲያናዊ ተፈጥሮ ነውና፡፡ ሲያመሰግን ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት እግዚአብሔር ፈጣሬ ዓለማት ነው ብሎ ማመን ነውና፡፡ ስለዚህ ለአንድ ክርስቲያን የሰማይና የምድር ውበት እየተመለከተ እግዚአብሔርን ማመስገኑ ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነው፡፡ ሲመጸውት ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት ሀብት ኹሉ ከእግዚአብሔር እንደ ኾነ መመስከር ነውና፡፡ ስለዚህ ራስን እንደ መልእክተኛ አድርጎ በመቁጠር ያለውን ለሌላው ማካፈል ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነውና፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትን ሲያነብ ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት በመንፈስ ቅዱስ ሀብት ደስ የሚሰኝ ነውና፡፡ይህን ለማድረግ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳት መጻሕፍት በኩል ሲናገር መስማት ለአንድ ክርስቲያን ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነውና፡፡

  • “እምነት አለኝ” ብሎ ምግባር የሌለው ሰውና፥ “ምግባር አለኝ” ብሎ እምነት የሌለው ሰው እኩል ናቸው፤ ኹለቱም መንግሥተ ሰማያት አይገቡም፡፡ ስለዚህ “እምነት አለን” ብለን ልል ዘሊላን አንኹን ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ይላልና፡- “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም” (ማቴ.7፡21)፡፡ ስለዚህ እምነት እንደሌላቸው ሰዎች ከመንግሥተ ሰማያት ውፁአን እንዳንኾን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ነቅተን እንሥራ፡፡ ምግባር ትሩፋትን ተግተን እንሥራ፡፡ አምነን ልጅነትን ከተቀበልን በኋላ ልጅነታችንን አጽንተን የምንጠብቀው፣ ርስቱንና መንግሥቱንም የምንወርሰው ይህን ያደረግን እንደ ኾነ ነውና ነቅተን እንሥራ፡፡ እኛ ሥራ ሠርተን አንበቃምና ጽዋ ተርታችን ዕድል ፈንታችን ይህ ይኾን ዘንድ ከባሕርይ አባቱ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ጌትነቱ፣ ኃይሉና ክብሩ አንድ የሚኾን ጌታችንና መድኃኒታችን በቸርነቱና ሰውን በመውደዱ ይርዳን፤ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ አሜን!!! (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

  • 11 апр.1 1331

    без подписи

  • 11 апр.1 0422

    💥💥💥💥💥💦💦💦💦💦💥💥💥💥💥💦💦💦💦💦💦💥💥💥💥💥💥 #እንኳን_ለጌታችን_መድኅኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_በዓለ_ትንሳኤ_በሰላም_አደረሳችሁ   ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤       በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤            አሰሮ ለሰይጣን፤                አግዐዞ ለአዳም፤                     ሠላም፤                        እምይዕዜሰ፤                              ኮነ፤                                  ፍስሐ ወሰላም፡፡ "ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነስቷል እንጂ በዚህ የለም:: 'የሰው ልጅ በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል: በሦስተኛውም ቀን ሊነሣ ግድ ነው' እያለ ገና በገሊላ ሳለ ለእናንተ እንደተናገረ አስቡ::"  (ሉቃ. ፳፬፥፭-፰)       #_ትንሣኤ_ዘክርስቶስ_የክርስቶስ_ትንሳኤ ☞  ሦስት መዓልት እና ሦስት ሌሊት በመቃብር? ☞  ሦስት መዓልት እና ሦስት ሌሊት የሞላው እንዴት ነው? ☞  እንዴት ተነሣ? ☞  ለምን በአዲስ መቃብር ተቀበረ? ☞  እንዴት በዝግ መቃብር ተነሣ? ☞  መቃብሩን ማን ከፈተው?       ጌታችን  አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድኅነተ ዓለምን በመስቀል ላይ ከፈጸመ በኋላ በአካለ ሥጋ ወደ መቃብር ወረደ ÷ ይኸውም በመቃብር ፈርሶ በስብሶ መቅረትን ሊያስቀርልን ነው፡፡ በአካለ ነፍስ ደግሞ ወደ ሲኦል ወረደ÷ ይኸውም በሲኦል ለነበሩ ነፍሳት ነፃነትን ይሰብክላቸው ዘንድ ነው፡፡ መለኮት፥ በተዋሕዶ፥ ከሥጋም ከነፍስም ጋር ነበረ፡፡ ለዚህ ነው፥ መቃብር ሥጋን ሊያስቀረው ያልቻለው፤ ሲኦልም ነፍስን ማስቀረት አልተቻለውም፡፡ ቅዱስ ዳዊት፡- « ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተዋትም» ያለው ይኽንን ታላቅ ምሥጢር በትንቢት ቃል ሲናገር ነው፡፡ መዝ ፲፭÷፲፡፡ ሐዋርያው  ቅዱስ ጴጥሮስም፡- «ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር (ወደ አብ÷ ወደ ራሱና ወደ መንፈስ ቅዱስ) እንዲያቀርበን፥ እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት (ስለ ሰው ልጆች ኃጢአት ተላልፎ በመሰጠት) ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ (በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው ለየ)÷ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ÷ (ያን ሥጋ ነፍስ እንድተለየችው መለኰት አልተለየውም)÷ በእርሱም ደግሞ (መለኰት በተዋሐዳት ነፍስ) ሄዶ በወኅኒ ለነበሩት ነፍሳት ሰበከላቸው፤» ብሏል። ✞ #ሦስት_መዓልት_እና_ሦስት_ሌሊት_በመቃብር✞ ጌታችን በከርሰ መቃብር የቆየው ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት ነው፡፡ «ሥጋዬ ደግሞ በተስፋ ታድራለች፤» የሚለው ቃለ ትንቢት የሚያረጋግጥልን ይኽንኑ ነው፡፡ መዝ ፲፭፥፱፡፡ ምሥጢራዊ ትርጉሙም «ወደ መቃብር የወረደ ሥጋዬ በተስፋ ትንሣኤ ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት በመቃብር አደረ፤» ማለት ነው፡፡ ተስፋ ትንሣኤውም በተዋሕዶ ከሥጋ ጋር ወደ መቃብር የወረደ መለኰት ነው፡፡ ነቢዩ ሆሴዕም፡- «ኑ÷ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፤ እርሱ ሰብሮናልና÷ (በሞተ ሥጋ ላይ ሞተ ነፍስን ጨምሮ የፈረደብን እርሱ ነው)÷ እርሱም ይፈውሰናል፤ (መርገመ ሥጋን መርገመ ነፍስን አስወግዶ ከሞት ወደ ሕይወት ያሸጋግረናል)፤ እርሱ መትቶናል÷ እርሱም ይጠግነናል፡፡ ከሁለት ቀን በኋላ ያድነናል፤ በሦስተኛውም ቀን ያስነሣናል፡፡» በማለት ትንሣኤ ክርስቶስ በሦስተኛው ቀን መሆኑን አረጋግጧል፡፡ ሆሴ ፮÷፲፪፡፡ ይልቁንም ጌታችን ራሱ በመዋዕለ ሥጋዌው፡- ከሽማግሌዎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ፥ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀመዛሙርቱ በግልጥ ነግሯቸዋል፡፡ ማቴ ፲፮÷፳፩፡፡ በገሊላም ሲመላለሱ፡- «ወልደ ዕጓለ እመሕያው ክርስቶስ በሰዎች እጅ አልፎ ይሰጥ ዘንድ አለው÷ ይገድሉትማል÷ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል፤» ብሏቸዋል፡፡ ማቴ ፲፯÷፳፡፡ ጻፎችና ፈሪሳውያንም ምልክት በጠየቁት ጊዜ፡- «ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል÷ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም፡፡ ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ፥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደነበረ÷ እንዲሁ የሰው ልጅ (ወልደ ዕጓለ እመሕያው ክርስቶስ) በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል፡፡» ብሏቸዋል፡፡ ማቴ ፲፪፥፴፰-፵። ✞ #ሦስት_መዓልት_እና_ሦስት_ሌሊት_የሞላው እንዴት_ነው?  ✞ ጌታ በከርሰ መቃብር የቆየው ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት ነው፡፡ ይኽንንም ለመረዳት ዕብራውያን ዕለታትን እንዴት እንደሚቆጥሩ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ እኛ በሀገራችን የሌሊቱን ሰዓት መቁጠር የምንጀምረው ከዋዜማው ከምሽቱ አንድ ሰዓት ነው÷ የቀኑን ሰዓት መቁጠር የምንጀምረው ደግሞ ከማለዳው አንድ ሰዓት ጀምሮ ነው፡፡ የሌሊቱ ሰዓት የሚያ ልቀው ከማለዳው አሥራ ሁለት ሰዓት ሲሆን፥ የቀኑ ደግሞ ከምሽቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ሲሆን ነው፡፡ የቀኑም የሌሊቱም ሰ ዓት ተደምሮ ሃያ አራት ሰዓት ይሆናል፡፡ ሁሉም ሰዓት ዕለቱን ይወክላል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው እሑድ ዕለት ከሃያ አራቱ ሰዓ ት በአንዱ ቢወለድ እሑድ ተወለደ ይባላል÷ ቢሞትም እሑድ ሞተ ይባላል፡፡ ዕለቱ በሚጀምርበትም ሰዓት ሆነ፥ በሚያልቅ በት ሰዓት፥ ድርጊቱ ቢፈጸም ያ ሰዓት እንደ አንድ መዓልትና እንደ አንድ ሌሊት ይቆጠራል፡፡ አውሮፓውያን አንድ ብለው ሰዓት መቁጠር የሚጀምሩት በእኛ አቆጣጠር ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ነው፡፡ እስከ ሃያ አራት ይቆጥሩና በእኛ አቆጣጠር ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ሲሆን ይጨርሳሉ፡፡ ሃያ አራት ሰዓት ሲሆን ዜሮ ይሉና እንደገና አንድ ብለው መቁጠር ይጀምራሉ፡፡ በሌላ አነጋገር ከሌሊት እስከ ሌሊት ይቆጥራሉ፡፡ አሜሪካውያን ደግሞ በእኛ ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ሲሆን አንድ ብለው ይጀምሩና በእኛ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ሲሆን አሥራ ሁለት ብለው ይጨርሳሉ፡፡ ከዚያም በእኛ አቆጣጠር ከቀኑ ሰባት ሰዓት እንደገና አንድ ብለው ይጀምሩና በእኛ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ሲሆን አሥራ ሁለት ብለው ይጨርሳሉ፡፡ ዕብራውያን ግን ዕለትን መቁጠር የሚጀምሩት ከዋዜማው ማለትም በአውሮፓውያን ከአሥራ ሰባት ሰዓት÷ በአሜሪካውያን ከአምስት ሰዓት (P.M.) ÷ በእኛ ደግሞ ከምሽቱ አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ ነው፡፡ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት ድረስ ሃያ አራት ሰዓት ቆጥረው አንድ ቀን ይላሉ፡፡ ከላይ እንደተገለጠው እያንዳንዱ ሰዓት የዕለቱን መዓልትና ሌሊት ይወክላል፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ከመስቀል ወርዶ የተቀበረው ዓርብ ቅዳሜ ከመግባቱ በፊት ነው፡፡ ዓርብ ዕለቱ የሚጀምረው ከዋዜማው ሐሙስ በእኛ አቆጣጠር ከቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ ነው፡፡ ስለዚህ ጌታ የተቀበረው በዓርብ ሃያ አራት ሰዓት ክልል ውስጥ በመሆኑ እንደ አንድ መዓልትና ሌሊት ይቆጠራል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ዓርብ ከቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ እስከ ቅዳሜ ቀን አሥራ አንድ ሰዓት ያለው ነው፡፡ ሦስተኛው ደግሞ ቅዳሜ ከቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ እስከ እሑድ ቀን አሥራ አንድ ሰዓት ያለው ነው፡፡ ከዚህ በኋላ የሰኞ ምሽት ይገባል፡፡ ጌታ የተነሣው በሦስተኛው ቀን እሑድ መንፈቀ ሌሊት ነው።

  • без подписи

  • без подписи

  • #ቀዳም_ሥዑር ✝️✝️✝️ ቅዳሜ፡–#ቀዳም ሥዑር ይባላል፡፡ በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ ✝️✝️✝️ #የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም በቀዳም ሥዑር ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጠዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡ ✝️✝️✝️ #ለምለም ቅዳሜ፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ ✝️✝️✝️ #በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡ ✝️✝️✝️ #የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ✝️✝️✝️ #ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡ ✝️✝️✝️ #ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል፡፡ ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡ ✝️✝️✝️ #ምእመናን ሆይ፣ በአጠቃላይ ሥርዓተ ሕማሙን፤ ሰሙነ ሕማማት ብለው የተለየ ሥርዓት አውጥተው አባቶቻችን ተግተው ያቆዩልንን ሥርዓተ መላእክት ልንጠብቀውም ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ የዕለታቱን ክብርና ስያሜ ከማወቅና ከመረዳት ጋር በዕለታቱ የታዘዙትን ሃይማኖታዊ ግዴታዎችን መወጣት ከሁላችንም ይጠበቃል፡፡ ✝️✝️✝️