tgindex
መንፈሳዊ ግጥሞች ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

መንፈሳዊ ግጥሞች ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

Статистика

ለሀሳብ ለአስትያየት >>>> @Tazena291

Последний пост
26 апр.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
8 824
−17 за 4 дн.
Сутки
−4
−0,05%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
9 267
20 постов
Вовлечённость
105,0%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 26 апр.3 2382

    http://youtube.com/post/UgkxoiaEd89oCyCovEJMvICj76xigQbrbZxg?si=9Q00zbuBAaGjhw8o

  • Channel photo updated

  • 15 апр.3 8723445из Menfesawigetmoch

    ተአምር ምንድነው? +++ ፅድቃችሁ የታለ ተአምር የታለ እኛስ ሙሴ…… በበትሩ ባህር ከፍሎልናል ድንጋይ ተሸክመን በመሀሉ አልፈናል ደመና ከልሎን ከነዓንን ወርሰናል ከሰማይ ላይ መና ወርዶልን በልተናል ከራፍዲም አለት ውሀ ጠጥተናል ፡ አንተ አይሁዳዊ ተአምር ምንድን ነው ትለኝ እንደ ሆነ የትኛው ይደንቃል ትለኝ እንደሆነ በል እንግዲህ ስማ እኔም አለኝ ድንቅ እጅግ የሚጎላ እጅግ የሚረቅ : በሙሴ በትር ባህር መከፈሉ ድንጋይ ተሸክሞ ማለፍ በመሀሉ እርግጥ ነው ይደንቃል ይሄ ግን ይጎላል ይሄ ግን ይረቃል በመስቀሉ በትር ማለፍ ከሞት እሳት በደሙ ማህተም ወደ ርስትህ መግባት ፡ አንተ አይሁዳዊ ፅድቃችሁ ወዴት ነው ትለኝ እንደሆነ ተአምሩ የታለ ትለኝ እንደሆነ  በል እንግዲህ ስማ በህቱም ድንግልና አምላክን መፀነስ የቃል ሰጋ በመሆን የአለም መፈውስ በእናቱ ደመና ከልሎን መሻገር የእዳ ፅህፈት ቀዶ ሲኦልን መበርበር : አንተ አይሁዳዊ…. ከነዓን ስትሻገር ፀሀይ ከከለለህ ከሰማይ ደመና ታምሬ ማርያም ነች ያቺ መሶበወርቅ በውስጧ ያለባት የህይወቴ መና ሙሴ ከከፈለው የኤርትራ ባህር እኔን የሚደንቀኝ በመስቀሉ በትር ገሀነምን ማለፍ ሲዖልን መሻገር ሰዎች ከገነቡት ከኢያሪኮ መፍረስ እኔን ይደንቀኛል በመስቀሉ ጉልበት የእዳ ደብዳቤዬ የሀጢያቴ መደምሰስ አንተን ከሚደንቅህ ከበረሀው መና እኔስ የሚገርመኝ አምላክን መወለዷ በህቱም ድንግልና : ተአምርስ በለኝ የክርስቶስ መስቀል ሞትን ለዘላለም ከሰንኮፉ ሚነቅል : ተአምርስ በለኝ ምጥ ሳይሰማት ወለዳ ድንግል እናት ሆነች ያለዘር ፀንሳ አምላክን ታቀፈች  ይቀጥላል... +++ "ተአምር ምንድነው" ሀይማኖተ አበው  ዘ ቅዱስ ኤራቅሊስ  ም፵፱-ቁጥር ፵፭  ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን እንዳስተማሩት +++ ©ታዜና    ™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች    t.me/Menfesawigetmoch

  • 6 янв.6 4812814

    መተኪያ የሌለው፥ ታላቁ ደስታችን፤ ‎በኤፍራታ ምድር፥ ተወልዷል ጌታችን። ‎ቤተልሔም ሂዱ፥ ዘምሩ በእልልታ፣ ‎ድንቅ መካር ሀያል፥ የሁላችን ጌታ። ‎+++ ‎መልካም የገና በዓል 2018 ‎©ታዜና    ™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች    t.me/Menfesawigetmoch

  • 6 янв.5 5823038из Menfesawigetmoch

    "ምን እላለሁ፤ ምን እናገራለሁ፤ የጌታዬ ልደቱ ድንቅ ነው። የአማኑኤል ልደቱ ድንቅ ነው።"* ፣ አለምን በቃሉ፥ የፈጠረ ጌታ፥ ሁላችንን ሊያድን ሊወስድ፥ የኛን ተርታ። ያለም ጌታ ሆኖ፥ ያየነው በበረት፤ ምን አይነት ፍቅር ነው፥ ምን አይነት ደግነት። ፤ በናቱ እቅፍ ሆኖ፥ በሰማያት አለ፤ በሰማያት ሆኖ፥ በናቱ እቅፍ አለ። ከኪሩቤል ጀርባ፥ ሳይወርድ ከዙፋኑ፤ ይገርማል ይደንቃል፥ በኛ መመስገኑ። ፥ ቅድመ አለም ያለ እናት ተወልዶ ከአባቱ ድህረ አለም ያላአባት  ወለደች እናቱ ይህን ድንቅ ጥበብ፥ ፍጥረቱ ተማክሮ፤ ድንቅ ይባላል እንጂ፥ ማን ያውቃል መርምሮ። ፥ ነብያት የናፈቁት፥ ትንቢታቸው መጣ ፤ ከድንግል ማህፀን፥ ያለድካም ወጣ፤ መለኮት ሳይከፈል፥ ወደ አለም መጣ፤ የጽድቃችን ጸሀይ፥ ከሰማያት ወጣ። ++++++ እንኳን ለብርሀነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ *("ምን እላለሁ ምን እናገራለሁ..." ሐይማኖተ አበው ዘቅዱስ ዮሀንስ አፈወርቅ) ©ታዜና       ™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች       t.me/Menfesawigetmoch

  • 16 дек.6 5833310

    ዳዊት መዝሙረኛው እንዲህ አለ... ከሰማይ ብወጣ፥ አንተ አለህ፤ ከሲዖል ባነጥፍ፥ በዚያ ነህ፤ ፍጹም አትለይም፥ ከልጅህ፤ ከእስትንፋሴ ይልቅ፥ ቅርቤ ነህ፤ +++ ታህሳስ ሥላሴ 2018

  • 6 июн. 2025 г.16,4 тыс120421

    የመዳን ቀን.... ሀጥያት በደል ቢከበኝም፤ ካንተ በቀር ሰው የለኝም። ነውሬ በዝቶ ከዘመኔ፥ ከፀጋህ ቢያጎድለኝም፤ ይቅር የሚል የሚያድነኝ ፥ካንተ በቀር ሰው የለኝም። ሙሉ መስሎ ያለም ደስታ፥ ሞኙን ልቤን ያማለለ፤ ያልወጣሁት የሀጢያት ማጥ፥የጠለቀ ገደል አለ። (አቤቱ...) : ሲጎድልብኝ ላንተ ማልቀስ፥ ሲሞላልኝ ወደ ሀጢያት፤ አንተ ግን አልቸኮልክም፥ ለበደሌ እኔን መቅጣት። ነብሴን ፀፀት እያወካት፥ ሰውነቴ ሰላም አቶ፤ ተስፋ ከልቤ ተሰዶ፥ መጽናናቴ ውስጤ ሞቶ። (ማረኝ...) ፥ አይነ ህሊናዬ ታወሮ፥ ልቦናዬ ድንጋይ ሆኗል፤ በህይወቴ ብርሀን የለም፥ የጨለማዬ ዋሻ ገኗል። ከሀጢያቴ ጉድጓድ እጮሀለሁ፥ ትሰማለህ ስጠራህ፤ እኔን ወዳንተ ሚመመልስ፥ አንድ ቃልስ ታጣለህ? (ይቅር...) ፥ ያሳየኛል ያ ጠላቴ፥ በምናቤ ከፍታዬን፤ ዛሬን ንዶ አደላድሎ፥ ያሳለፍኩት ያን ደስታዬን። የቆሮንጦሱ ፈተናህ፥ ዛሬም እኔን ይገጥመኛል፤ ድንጋይ-ዳቦ ስልጣን-ጀብዱ፥ ይሄን ሁሉ ያስመኘኛል። (በለኝ...) ፥ ጌታዬ ሆይ እባክህን? አምላኬ ሆይ እባክህን፧ ልብ ስጠኝ፤  ጊዜ ስጠኝ፤ አውጣኝ ከዚህ ከቅዠቱ፥ ከከንቱ አለም፤ ካንተ በቀር ሌላ ማንም፥ እውነት መንገድ ህይወት የለም። (እግዚአብሔር...) ፥ ልናዘዛት ያቺን ሀጢያት፥ የማፍራትን የዘውትሬን፤ ልናዘዛት ከኔ ትውጣ፥ በንስሐ ልጠብ ነውሬን። ልናዘዛት ያቺን ሀጢያት፥ ህሊናዬ ነጻ ይውጣ፤ ልናዘዛት እሷን ልተው፥ የመዳን ቀን እንዲመጣ። (በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፥) ፥ በምህረትህ ብዛት፥ ወደ ቤትህ አስገባኝ፤ በተወደደ ጊዜ ስማኝ፥ በማዳንህ ቀን ርዳኝ። እስክወጣ ጥቂት ታገስ፥ በመአትህ አትቅሰፈኝ፣ እስክናዘዝ ጥቂት ታገስ፥ ይቺን አመት ብቻ ተወኝ። (ቀርቦም ሳለ ጥሩት፤) +++ “በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ  በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤  እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።”   — 2ኛ ቆሮ 6፥2 +++ ©ታዜና    ™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች    t.me/Menfesawigetmoch

  • 6 июн. 2025 г.11 тыс1214

    без подписи

  • 1 июн. 2025 г.10,9 тыс2224из Menfesawigetmoch

    #ElmestoAgya #እልመስጦአግያ #Share +++እንኳን ለጌታችን የዕርገት አደረሳችሁ+++ ——ዐረገ በክብር —— ዐረገ በክብር፣ ዘምሩ በእልልታ፤ የነገስታት ንጉስ፣ የሠራዊት ጌታ፡፡ ፀሀዩ በምስራቅ፣ ወደ ምድር መጣ፤ ፀሀዩ በምስራቅ፣ ወደ ሰማይ ወጣ፡፡ ፤ እስከ ቢታንያ፣ ወደ ውጭ አውጥቶ፣ ጌታችን ባረከን፣ እጆቹን አንስቶ፡፡ አይናችንን ተክለን፣ ሰማይን አየነው፣ ከፍ ከፍ እያለ፣ ደመና ሸፈነው፡፡ ፤ ወላጅ እንደሌለው፣ አይተወንም እርሱ፤ ከሠማይ የላከው፣ አፅናኝ ነው መንፈሱ፡፡ እንዲሁ ይመጣል፣ ሲያርግ እንዳያችሁ፤ በአስራ ሁለቱ ዙፋን፣ ትቀመጣላችሁ፡፡ ፤ ዘስልጣኑ ዲበ መትከፍቱ ፤ እጹብ ድንቅ ነው የጌታ ዕርገቱ፡፡ +++++++++++++++++++++++ ™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች ©ታዜና @Menfesawigetmoch @JohnDPT27 @Learn_with_John

  • https://youtu.be/Y1lmGKLFMQQ?si=zdwDb1NitYRZKL2B

  • https://youtu.be/1k2EQ7RSlWo?si=-aJTiaV5O55eaGot

  • አዲስ ዝማሬ ገብረ መንፈስ ቅዱስ https://youtube.com/watch?v=YwXNOp88mGg&si=Dx8t_VvFINn6dEE1

  • 18 апр. 2025 г.10,9 тыс14

    https://youtu.be/F0TVwi8RLNQ

  • 23 мар. 2025 г.10,6 тыс164

    без подписи

  • 15 мар. 2025 г.11 тыс292

    በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።   የደብራችን የያሬድ ሜዳ ብሔረ ጽጌ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን 7 አባላት ያሉት መንፈሳዊ የጉዞ አጓጓዥ ኮሚቴዎችን የአዋቀረ ሲሆን የተዋቀረዉ ኮሚቴ  የተጠራበትን መንፈሳዊ አላማ ከግብ ለማድረስ መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ/ም በአደረገዉ ስብሰባ በሰፊዉ ከተወያዬ በኋላ በጾሙ ዉስጥ 3 የተለያዩ ገዳማት ላይ የበረከት መንፈሳዊ ጉዞዎችን አዘጋጅቷል።             በመሆኑም ጉዞ በተዘጋጀባቸዉ ገዳማት  ተገኝታችሁ በረከትን እንድታገኙ መንፈሳዊ ጥሪያችንን  እያቀረብን ይህ መልዕክት የደረሳችሁ የቤተ ክርስቲያናች ልጆች  ለሌሎችም ቅስቀሳ በማድረግ በጉዞዉ ላይ እንድትሳተፉ በበቤተ ክርስቲያናችን ስም መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን።           ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ጉዞዎች ወደ 1ኛ  ስዉሯ ማርያም ገዳም          መነሻ ቀን እሁድ  መጋቢት 21 ቀን ደርሶ መልስ ምግብን ጨምሮ 700 ብር 2ኛ  ኢቲሣ ተክለ ሃይማኖት ገዳም መነሻ ቀን መጋቢት 28/2017 ዓ/ም ደርሶ መልስ ምግብን ጨምሮ 600 ብር 3  ቤዛዊት ማርያም ገዳም   እሁድ ሚያዝያ 5 ቀን 2017 ዓ/ም ደርሶ መልስ ምግብን ጨምሮ 400 ብር   አዘጋጅ የብሔረ ጽጌ ደ/ምሕረት ቅ/ገብርኤል እና ቅ/ዑራኤል ቤ/ክ ጉዞ አዘጋጅ ኮሚቴ     የምዝገባ ቦታ በደብሩ ጽ/ቤት ለበለጠ መረጃ 0911911601/0986337237 /0941210749/ 0912391324   መነሻ ቦታዎች  1ኛ ብሔረ ጽጌ ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ 2ኛ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ 3ኛ መገናኛ እሥራኤል ኤንባሲ 4ኛ ጣፎ አደባባይ

  • 23 февр. 2025 г.13,1 тыс6990

    без подписи

  • 23 февр. 2025 г.10,7 тыс4513

    እንኳን አደረሳችሁ... ?...መልሺ የነገርኩሽንም ፍጹም እንዳትረሺ ሶስት ሻማ ለኩሼ አንዱ ቀድሞ ቢቀልጥ ምልክት ይሁነኝ ታሪኬ እንዲለወጥ +++ 2017 እሁድ የካቲት ፲፮

  • 19 янв. 2025 г.12,2 тыс246

    без подписи

  • 18 янв. 2025 г.11,6 тыс224

    እንኳን አደረሳችሁ..

  • 31 дек. 2024 г.11,7 тыс172

    በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ክቡራን ደንበኞቻችን የቅዱስ ገብርኤልን አመታዊ ክብረ በዓል በቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል አክብረን በረከትን ተቀብለን በሰላም ተመልሰናል። ጥር 21ቀን የሚከበረዉ የእናታችን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም (አስተርዮን) በግሸን ደብረ ከርቤ ዳግማዊት ኢየሩሳሌም ለማክበር ቅድመ ዝግጅታችንን አጠናቀን ምዝገባ ጀምረናል። መኘሻ ቀን ጥር 18/ መመለሻ ቀን ጥር 23/2017 ዓ/ም ጉዞዉ ትራንስፖርት ምግብና ማረፊያን ያካትታል። አዘጋጅ ማኅበረ ሙሴ ዘኦርቶዶክስ ተሕዶ 09 04 212121/0910 27 2601 /0911911601/0938621717 መነሻ ቦታ በዓሉበት አካባቢ ትኬት ለማግኘት በዓሉበት ሆነዉ 1000530555668