- Последний пост
- 2 июл.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና ጠንካራ መሠረት ለመጣል የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ በETOL (Education Transformation for Learning) ፕሮግራም የሚገነቡ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የቅድመ ዝግጅትና የአፈጻጸም ሂደትን የሚመለከት የግምገማ መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ ተካሂዷል። በመድረኩ መክፈቻ ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የትምህርት ልማት ዕቅድና ሀብት ማፈላለግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ዘሪሁን መሰለ እንደገለጹት፣ መድረኩ በፕሮግራሙ የሚገነቡ ትምህርት ቤቶች የቅድመ ዝግጅትና የአፈጻጸም ሂደትን በመገምገም ቀጣይ ሥራዎችን ለማቀላጠፍ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል። አቶ ዘሪሁን እንዳሉት፣ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና ለተማሪዎች ጠንካራ የመማር መሠረት ለመጣል የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው። በክልሉ በተመረጡ 70 ወረዳዎች 140 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚገነቡ ጠቅሰው፣ ከእነዚህ መካከል 70ዎቹ በETOL ፕሮግራም እንደሚገነቡ አስታውቀዋል። ቀሪዎቹ 70 ትምህርት ቤቶች ደግሞ በመንግሥት የሚገነቡ ሲሆን፣ የግንባታ ወጪው 50 በመቶ በክልሉ፣ 30 በመቶ በዞኖች እና 20 በመቶ በየወረዳዎቹ እንደሚሸፈን ገልጸዋል። አቶ ዘሪሁን አክለውም፣ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት በመሥራት የተገኘውን ዕድል በአግባቡ ሊጠቀሙበት እንደሚገባ ገልጸው፣ ግንባታውም በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ በ2019 የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ተቀብሎ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምር መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ ወ/ሮ ወዳጄነሽ አሸንጎ በበኩላቸው፣ የሚገነቡት ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሕፃናት ምቹና ደረጃቸውን የጠበቁ የመማሪያ አካባቢዎችን በመፍጠር የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ገልጸዋል። እንዲሁም የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቹ ግንባታ "ትምህርት ለትውልድ" ፓኬጅ አካል መሆኑን በማስታወስ፣ ጉዳዩ የሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ኃላፊነት በመሆኑ ከፍተኛ ትኩረትና ቀጣይነት ያለው ክትትል ሊደረግበት እንደሚገባ ጠይቀዋል። በETOL ፕሮግራም የአካባቢ ጥበቃና ደህንነት ከፍተኛ ባለሙያ ወ/ሪት ፍሬወይኒ አባይነህ በጉዳዩ ላይ የመወያያ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን፣ በተሳታፊዎች መካከል ሰፊና ገንቢ ውይይት ተካሂዷል። ተሳታፊዎቹም የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቹ ግንባታ በወቅቱ ተጠናቆ አገልግሎት እንዲጀምሩና የታለመላቸውን ዓላማ እንዲያሳኩ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። በመድረኩ ላይ ትምህርት ቤቶቹ ከሚገነቡባቸው ወረዳዎች የተውጣጡ የትምህርት ቤት መሻሻል ቡድን መሪዎች፣ የክልል ትምህርት ቢሮ ባለሙያዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
без подписи