Sheger Times Media️
Статистикаበማትሪክስ ኢንተርቴይመንትና የፕሬስ ስራዎች ኃ.የተ.የግ.ማ እየታተመ በየ15 ቀኑ ለአንባቢያን የሚደርሰው የ #ሸገር_ታይምስ መፅሄት ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
- Последний пост
- 12 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 5
- Всего постов
- 74
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 373
- 1/48двое суток
- 427
- 1/72трое суток
- 461
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
💥#ከተከላካይነት_ወደ_አጥቂነት! የመከላከያ ስልቷን ወደ 🚀አጥቂነት💥 የቀየረችው ቴህራን የማጥቃት ትእዛዝ አስተላልፋለች። የኢራን አብዮታዊ ዘብ ጦርነቱን ከሀገር ድንበር ባለፈ በጠላት ምድር ላይ ለማካሄድ የሚያስችለውን አቅም እንዲገነባ ታዟል። ዋሽንግተን ቴህራንን ለማንበርከክ የከፈተችውና “ከፍተኛ ጫና መፍጠር” የሚለው ስትራቴጂዋ ቴህራንን በተቃራኒው ይበልጥ ክንፎቿን እንድትዘረጋና የጦር መሣሪያ አቅሟን እንድታፈረጥም አድርጓታል። ትራምፕ 'ኢራን እጅ ትሰጣለች' ብለው ቢጠብቁም፣ የሆነው ግን በተቃራኒው ነው። ቴህራን የጦር መሣሪያዎቿን በሀገር ውስጥ የማምረት አቅሟን አሳድጋ፣ የባሊስቲክ ሚሳኤል ዝናብ ለማዝነብ መዘጋጀቷን አውጃለች። 💥💥ይመልከቱት👇🏿 https://youtu.be/z2DqpPE0l-s?si=ey_BUzDsFGCzKX1R
🔴ማብቂያ_የሌለው_ውርደት❗️ ነውጠኛው የአሜሪካ መሪ ከቴህራን ጥቃት ለማምለጥ እንደ አይጥ ለመሹለክለክ ተገደው እንደነበር ሲዘገብ ዓለም በግርምት እጁን በአፉ ጫነ፡፡ በርካቶችም በቀውሱ አዛውንት ፕ/ት ድርጊት ተሳለቁ፡፡ በእስራኤል ጋላቢነት የለኮሱት እሳት ወላፈኑ እየለበለባቸው የሚገኙት ትራምፕበቱርክ ሳሉ ኢራን ትገለኛለች ብለው፣ ተሹለክልከው መፈርጠጣቸው ተሰምቷል፡፡ ትራምፕ ከኢራን ጥቃት ለመዳን የምግብ ማመላለሻ መኪና ውስጥ በመደበቅ በሚስጥር አውሮፕላን መቀየራቸውን ማን ማመን ይችላል? እውነታው ግን ፕሬዝዳንቱ በቴሌቪዥን ካሜራዎች ፊት ወደ Air Force One ቢገቡም፣ በጀርባ ተሹለክልከው በምግብ ማመላለሻ መኪና ተደብቀው ወደ ሌላ ወታደራዊ አውሮፕላን መዘዋወራቸው ዓለምን እያነጋገረ ነው። በገዛ እጃቸው ተንኩሰው ማለቂያ የሌለው ስጋት ውስጥ የገቡት ትራምፕ ነፍሳቸውን ለማዳን ኩሽና ለኩሽና መሽሎክሎክ ግዴታ ሆኖባቸዋል። #ይመልከቱት⬇️ https://www.youtube.com/watch?v=szFZG7mAQ-k
🔴ብልፅግና ወሰነ‼️ https://youtu.be/eIRE4UKYAS0?si=iZjBieIHfmKmjDze
💥የሰአቱ መረጃ‼️ ⬇️ https://youtu.be/7CGDP6X4SpY?si=IDXKcMQAEWJ74_kd
በምስራቅ ሊቢያ የሚገኘው የሊቢያ ብሔራዊ ጦር የወታደራዊ ስለላ ሃላፊ ብርጋዴር ጀነራል ፎዚ ማንሱሪ በቦምብ ጥቃት ተገደሉ። ጀነራሉ ሰኞ ምሽት በመኖሪያ ቤታቸው ውጭ በቆመች መኪናቸው ውስጥ በፈንጂ ህይወታቸውን አልፏል ። የደህንነት ምንጮች ጥቃቱ ማን እንደፈፀመው የታወቀ መረጃ እንደሌለ ገልፀዋል ። ስለ ፈንጂው አይነትም ሆነ ስለ ጥቃቱ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ አልተሰጠም። እስካሁን ለጥቃቱ ሃላፊነት የወሰደ አካልም የለም።
🆕ከሀዲው_ሰላይ‼️ ከዘመኑም፣ ከባልደረቦቹም ሆነ በአለም ላይ ከነበሩት ሰላዮች በላይ ስለላ ላይ የተራቀቀ ወደር የለሽ ሰላይ ነው። በስለላ ብቃቱ የነገሰ፣ ኬጂቢ የሚመካበትና የሚኮራበት፣ ሩስያም እንደ አይን ብሌኗ የምታየው ሰላይ ነበር። ሞሳድ፣ ሲ አይ ኤና Mi6 ይህን ከማድነቅ በላይ ይፈሩታል። የኛ በሆነ ብለውም ዘወትም ይመኙ ነበር። ምኞታቸውም ሰምሮ ይህ ሰላይ ሩስያን በመክዳት ከኬጂቢ በተጨማሪ ለእንግሊዙ Mi6ም በድብቅ መሰለል ጀመረ። በተለይ ለMi6 የሰጣቸው እጅግ ወሳኝና በርካታ መረጃዎች ሩስያን በጅጉ ዋጋ አስከፍሏል። ይህ ሰላይ የኬጂቢና የሩስያ እጅግ ወሳኝ መረጃዎችን በየግዜው ከስር ከስር ለMi6 ባይሰጥ ኖሮ ሊከሰት የሚችለውን ለማመን ይከብዳል፡፡ ለመሆኑ ብቻውን ሆኖ አለማችን አሁን ያላትን መልክ ሼፕ ያደረገው ይህ ሰላይ ማን ነው? 💥በተከታዩ ሊንክ ሙሉ ታሪኩን ይመልከቱት!⬇️ https://youtu.be/GtVeD8MvOf8
በወልቂጤ ከተማ ባጃጅ በማስቆም የኮቴ ሲቀበሉ የነበሩ ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ በወልቂጤ ከተማ ባጃጆችን በማስቆም “የኮቴ” በሚል አላስፈላጊ ገንዘብ ሲቀበሉ በነበሩ ተከሳሾች ላይ የጉራጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የእስራት ውሳኔ ማስተላለፉን የጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ኤልያስ ነገሩኝ ሲል የዘገበውብስራት ራዲዮ ነው። 1ኛ ተከሳሽ ሪባቶ ታጁ እና 2ኛ ተከሳሽ ጀሚል ዘይኑ የማይገባቸውን ጥቅም ለማግኘት በማሰብ ከሐምሌ 2017 ዓ.ም እስከ መስከረም 2018 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በተለያዩ ቀናት ወንጀሉን ሲፈጽሙ ቆይተዋል። ተከሳሾቹ ከጉብሬ ወደ ወልቂጤ የሚጓዙ ባጃጆችን “ካምፕ ሰፈር” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በማስቆም “የኮቴ ካላመጣችሁ አታልፉም” በማለት የተለያየ መጠን ያለው ገንዘብ ሲቀበሉ እንደነበር ተገልጿል። የወልቂጤ ከተማ ፖሊስ ከጉራጌ ዞን ፖሊስ ጋር በመተባበር ተከሳሾችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራውን አጣርቶ ለዞኑ ፍትህ መምሪያ አስረክቧል። የጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ዐቃቤ ሕግ ክስ መስርቷል።በዚህም በ1ኛ ተከሳሽ ላይ 5 ተደራራቢ የወንጀል ክስ በ2ኛ ተከሳሽ ላይ 2 ተደራራቢ የወንጀል ክስ መስርቶባቸዋል። ተከሳሾች በችሎቱ ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሲጠየቁ ድርጊቱን አልፈጸምንም በማለት የካዱ ቢሆንም፣ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ቀርበው የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል። ተከሳሾች ያቀረቧቸው መከላከያ ምስክሮች ግን የዐቃቤ ሕግን ክስ ማስተባበል ባለመቻላቸው ፍርድ ቤቱ በጥፋተኝነት ውሳኔ ላይ ደርሷል፡፡ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት 1ኛ ተከሳሽን በ3 ዓመት ከ9 ወር እስራት እና 2ኛ ተከሳሽን በ1 ዓመት ከ2 ወር እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ መተላለፉን አቶ ኤልያስ ጨምረው መናገራቸውን ዘግቧል።
#መካከለኛውምስራቅተቀጣጠለ‼️ የመካከለኛው ምስራቅ ነገር ከዲፕሎማሲያዊ ቃላት ምልልስ ወደ ወታደራዊ እርምጃ ተሻግሯል። የዓለም የነዳጅ ንግድ የደም ሥር የሆነው የሆርሙዝ ወሽመጥ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ይገኛል። ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የወሰደችው አዲስ አቋም በንግድ መርከቦች ላይ ጥቃት እስከመሰንዘር ደርሷል። ኢራን ወሽመጡን ዳግም ለመክፈት ያቀረበችው ጠንካራ ቅድመ ሁኔታ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መርከብ ላይ የተሰነዘረው የሚሳይል ጥቃት፣ የቀጣናውን ስጋት ወደ አዲስ ምዕራፍ አሸጋግሮታል። አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ ያላት የበላይነት እየተሸረሸረ መሆኑ በሚነገርበት በዚህ ወቅት፣ የቴህራን ቁርጠኝነት እና የክልሉ አገራት አዲስ ጥምረት የዓለምን ፖለቲካዊ ሚዛን ሊቀይረው ይችል ይሆን? የሚሉ ጥያቄዎችም እየተነሱ ነው፡፡ ወቅታዊ መረጃ የያዘውን መሰናዶ ይመልከቱት! ⬇️ https://www.youtube.com/watch?v=ECNVfRXI8Vo
የሊዮኔል ሜሲ አባት ጆርጅ ሜሲ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ የታዋቂው እግር ኳስ ተጫዋች ሊዮኔል ሜሲ አባት ጆርጅ ሜሲ በ68 ዓመታቸው ማረፋቸውን የአርጀንቲና መገናኛ ብዙኃንን ዋቢ አርጎ ኢቢሲ ዘግቧል። ላለፉት ወራት በከባድ የጤና እክል ሲታገሉ የቆዩት ጆርጅ ሜሲ፣ የልጃቸው ወኪልና ለስኬቱ ትልቁን ድጋፍ ያደረጉ ጠንካራ ሰው ነበሩ። ሜሲ ከአባቱ ጎን ለመሆን ሲል በቅርቡ የተካሄደውን የሜጀር ሊግ ሶከር (MLS) የኮከቦች ጨዋታ ሳይሳተፍ መቅረቱ የሚታወስ ሲሆን፣ መላው የእግር ኳስ ቤተሰብ ለሜሲና ለቤተሰቦቹ አጋርነቱን እየገለጸ ይገኛል። የሜሲ ቤተሰቦች በበኩላቸው በሕክምናው ሂደት አብረዋቸው ለነበሩና ላጽናኗቸው ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
🆕በአዲስ አበባ ያልተጠናቀቁ ሕንፃዎችን የሚያከራዩ አከራዮች የ100 ሺሕ ብር ቅጣት እና የወንጀል ተጠያቂነት ይጠብቃቸዋል‼️ 📋የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ያዘጋጀው አዲስ የአደጋ ሥጋት ደኅንነት መመሪያ ወደ ሥራ ገብቷል። በመመሪያው የተካተቱ ክልከላዎች፦ 🔴በሕንፃ ግንባታ ወቅት የሠራተኞች ደኅንነት መጠበቂያ መስፈርቶችን አለማሟላት፣ 🔴ለአደጋ የሚያጋልጡ የተቆፈሩ ጉድጓዶችን አለመከለልና ምልክት አለማድረግ፣ 🔴ለአደጋ የሚያጋልጡ ጠንካራ ያልሆኑ የማደላደያ ቁሳቁሶችን መጠቀም፣ 🔴በቀላሉ ሊደረመስ የሚችል አፈርና የግንባታ ተረፈ ምርቶችን ማከማቸት። 💥እርምጃው ግንባታቸው ሳይጠናቀቅና የደኅንነት ማረጋገጫ ሳያገኙ ለአገልግሎት የሚውሉ ሕንፃዎች በዜጎች ሕይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ አደጋ ከመደቀናቸው ጋር ተያይዞ የመጣ ነው።
‼️በአለታ ወንዶ ከተማ ትናንት ምሽት በደረሱ ሁለት የተሽከርካሪ አደጋዎች የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ በሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ እንዳስታወቀው አደጋዎቹ ትናንት ምሽቱ የደረሱት በከተማው ቡልቱማ በተባለ ቀበሌ ውስጥ ነው ፡፡ አደጋው የደረሰው ከቦረና አቅጣጫ ወደ ሀዋሳ ሲጓዝ የነበረና የመለያ ኮዱ 1190 የሆነ የፌዴራል ፖሊስ ተሽከርካሪ በቀበሌው ሲደርስ በመገልበጡ ነው ፡፡ በአደጋው የ6 ሰዎች ሕይወት ማለፉን በመምሪያው የትራፊክ አደጋ መከላከልና ምርመራ የሥራ ሂደት ኃላፊ ኢንስፔክተር መለሰ ቡኑራ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል ፡፡ በአደጋው ህይወታቸውን ያጡት ስድስቱ ሰዎች በተሽከርካሪው ተሳፍረው የነበሩ የፌዴራል ፖሊስ አባላት መሆናቸውን ኢንስፔክተር መለሰ ገልጸዋል። በተጨማሪም በዚሁ ቀበሌ ሌላ ሲኖትራክ የጭነት ተሽከርካሪ መንገድ ስቶ በመኖሪያ ቤት ውስጥ በመግባቱ የአንድ ሰው ሕይወቱ ማለፋን ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል ፡፡ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው አምስት ሰዎች ለህክምና ዕርዳታ ወደ ሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል መወሰዳቸውን የጠቀሱት ኢንስፔክተሩ የሁለቱም አደጋዎች መንስዔ እየተጣራ ይገኛል ብለዋል ፡፡
7 የክሪፕቶ ካረንሲ መተግበሪያዎች በሀገር ውስጥ እንዳይሠሩ ሙሉ በሙሉ መታገዳቸውን መንግሥት በይፋ አሳውቋል። መተግበሪያዎቹ ለሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ሽፋን ይሰጡ እንደነበር አመልክቷል። ከዚህ ቀደም የተለያዩ የክሪፕቶ ከረንሲ መተገበሪያዎች የኢትዮጵያን ብር ከP2P መድረክ ላይ ማስወጣታቸው የሚዘነጋ አይደለም። ይህ በእንዲህ እንዳለ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (EEP) ተገቢው መመሪያ በሌለበት ሁኔታ ከ36 የዳታ ማይኒንግ ድርጅቶች ጋር ሕገ-ወጥ የኃይል ሽያጭ ውል የፈጸሙ 4 ከፍተኛ አመራሮች ላይ እርምጃ መወሰዱን አመልክቷል። በሌላ በኩል፤ በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ በሐዋላ እና በጥቁር ገበያ ተሳታፊ የሆኑ 169 ኢትዮጵያውያንና የውጭ ሀገር ዜጎች በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረጉን አሳውቋል። በተጨማሪ በተደራጀ መንገድ ከንግድ ባንክ ደንበኞች አካውንት ላይ በማጭበርበር ገንዘብ የወሰዱ 36 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው የባንክ ሒሳባቸው እንዲታገድ ተደርጓልም ብሏል። ከዚህ ባለፈ፣ ከቤቲንግ እና ፊንቴክ ቢዝነሶች ጋር በተገናኘ የደንበኞችን መረጃ በመደበቅ መንግሥትን ግብር ያጭበረበሩ፣ ገቢያቸውን የሰወሩ እና ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር በፈጸሙ 38 የቤቲንግ ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወስዶ ባለቤቶቻቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እና የእነዚህ ሕገ-ወጥ ተቋማት የባንክ ሒሳብ መታገዱን መንግሥት አሳውቋል።[ቲክቫህ]
በፊንቴክ ኢንቨስትመንት ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶችና ቲክቶከሮች በክስ መቃወሚያቸው ላይ ብይን ተሰጠ:: 🔴ተከሳሾቹ በማህበራዊ ሚዲያ የሰጡትን መግለጫ በተመለከተም ዐቃቢ ህግ አቤቱታ አቅርቧል። በ"ፊንቴክ" ኢንቨስትመንት ሽፋን በተፈጸመ መጠነ-ሰፊ የማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ ታዋቂ አርቲስቶችና ቲክቶከሮች፣ የዋስትና መብታቸው ተከብሮላቸው በውጭ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ መወሰኑ ይታወሳል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ተከሳሾች ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ እና ዐቃቤ ሕግ የሰጠውን መልስ መርምሮ ብይን ለመስጠት ለዛሬ፣ ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር። በዛሬው የችሎት ውሎ፣ ተከሳሾቹ "እኛ የሠራነው የማስታወቂያ ሥራ እንጂ ኮምፒውተር ተጠቅመን የፈጸምነው የማጭበርበር ወንጀል የለም" ሲሉ 1ኛ ተከሳሽ በ5 ገጽ፣ ሌሎች ተከሳሾች ደግሞ እያንዳንዳቸው በ6 ገጽ ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ ፍርድ ቤቱ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጎታል። በሌላ በኩል፣ ተከሳሾቹ ሰሞኑን "እግረኛው" በተሰኘ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ ላይ ቀርበው መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ ባለ 5 ገጽ የክስ አቤቱታ ለችሎቱ አቅርቧል። ዐቃቤ ሕግ በአቤቱታው፦ በፍርድ ቤት በሂደት ላይ ባለ ጉዳይ ላይ መግለጫ መስጠት በፍትሕ አሰጣጥ ሂደቱ ላይ ተጽዕኖ ስለሚያሳድር፣ ፍርድ ቤቱ ለሁለት ወራት ያህል ከመዘጋቱ በፊት አቤቱታው ታይቶ ውሳኔ እንዲሰጥበት፤ ወይም ይህ ድርጊት ወንጀል በመሆኑ ፍርድ ቤቶች በተዘጉበት ወቅትም ቢሆን ችሎቱ አስቸኳይ ብሎ በሚያያቸው ጉዳዮች ውስጥ ተካቶ እንዲታይለት ጠይቋል። የተከሳሾች ጠበቃ በበኩላቸው አቤቱታውን አንብበው ለመረዳት ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው በመግለጽ፣ እንዲሁም መግለጫ የተሰጠበት ማህበራዊ ሚዲያ ጋዜጠኛ የሆነው ተክለሃይማኖት አዳነ እና በመግለጫው ወቅት የተገኙት ጠበቃ አበባው አበበ በችሎቱ ባለመገኘታቸው ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ግራ ቀኙን ያደመጠው ችሎቱ፣ የማንኛውም ሰው የመናገርና ሀሳብን የመግለጽ መብት ሕገ-መንግሥታዊ ቢሆንም፣ በሕግ በተያዘ ጉዳይ ላይ መግለጫ መስጠትን በተመለከተ ዝርዝሩን ለማጣራት ጋዜጠኛ ተክለሃይማኖት አዳነ እና ጠበቃ አበባው አበበ በችሎት ተገኝተው የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ ለጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።[Sheger FM 102.1]
💥🔴ከኢራን ዝምታ ጀርባ!🔴💥 በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት አሁን ወደ ከፋ ደረጃ ተሸጋግሯል፡፡ በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ያለው ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ ሽኩቻ የዓለምን የኢኮኖሚ እና የሰላም መረጋጋት ስጋት ላይ ጥሎታል፡፡ እንደልቡ የሆኑት ጤና አልባው መሪ በዋይት ሀውስ በሰጡት መግለጫ፣ ኢራን አሁን ከፊቷ የቀረበላትን የሰላም ስምምነት እንድትፈርም "ይህ የመጨረሻ ዕድሏ ነው" ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ ትራምፕ ኢራን የኒውክሌር ፕሮግራሟን እና በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የምታደርገውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ካላቆመች ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ እርምጃ ይጠብቃታል ሲሉም ነው የተደመጡት፡፡ መካሪ አልባው መሪ ለድብድብና ለጸብ እንደሚገላገል የመንደር ጎረምሳ ያዙኝ ልቀቁኝ እያሉ ባለበት ሰዓት ስለ ኢራን ወታደራዊ ዝግጅት በተለይም ከመሬት ስር ስላሉት የሚሳኤል ከተሞቿና ስለ አስፈሪ ወታደራዊ ዝግጅቷ የተሰማው መረጃ ግን እጅግ አስደንጋጭ ሆኗል፡፡ ወቅታዊ መረጃ የያዘውን መሰናዶ ይመልከቱት! ⬇️ https://youtu.be/XXZysh8KjQA?si=Ayn06L8_SnkuoFKS
🆕የቡርኪናው ምስራች! ከወደ ቡርኪናፋሶ የተሰማው ልብን የሚያሞቅ መረጃ ለምዕራባውያኑ በተለይም ለፈረንሳይ የመርዶ ያህል ሆኗል፡፡ በቡርኪና በረሀማ ሜዳዎች ላይ ግምቱ 50 ቢሊዮን በርሜል የሚደርስ እጅግ ግዙፍ የነዳጅ ክምችት ተገኝቷል። ለዘመናት ሀገሪቷን እንደ ግል ንብረቷ ቆጥራ ማዕድናቷን ስትበዘብዝ የቆየችው ፈረንሳይም ሆነ የቡርኪናን ሀብት ሲያግዙ የኖሩት የምዕራባውያን ባለሙያዎች ያላገኙትን ይህን ነዳጅ በጥልቅ ምርምር ያገኘው የሩስያው ግዙፉ የነዳጅ ካምፓኒ ጋዝ ፕሮም ከወዲሁ የጥናት የቁፋሮ ስራውንና ተያያዥ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን ጀምሯል። ይህ የትራዎሬና የፑቲን ጥምረት ፍሬ ማፍራት ለቡርኪናቤዎች የምስራች ለማክሮንና ለምዕራቡ ዓለም ሹማምንት ደግሞ አስደንጋጭ ሆኗል፡፡ ⬇️ሙሉ ዘገባውን ይመልከቱት!⬇️ https://youtu.be/RraHBT-DpNE?si=ZoBkXKK73aOFs9AV
💥የሩሲያ ድሮኖች የዩክሬን የመሳሪያ መጋዘኖችን አወደሙ በሰው አልባ አውሮፕላኖች (Kamikaze/FPV Drones) የሚታወቀው የሩሲያው ዲኔፕር ክፍለ ጦር በነዳጅ፣ በጥይት እና በመሳሪያዎች የተሞሉ የዩክሬን ጦር ድብቅ ቦታዎች ላይ ጥቃት ፈጽሟል። በዩክሬን የአቅርቦት መጋዝኖችን ላይ ጥቃት የፈጸመው በደቡባዊው ግንባር በተለይም በዲኔፕር ወንዝ አካባቢ፣ በክሊፕሌ እና በዛፖሮዢያ ክልሎች የሚገኘውና የዩክሬንን ወታደራዊ መሠረተ ልማቶች፣ የጦር መሣሪያ ማከማቻዎችን እና ምሽጎችን በተደጋጋሚ በድሮን በማውደም የሚታወቀው ይሄው ክፍል ከፍተኛ ክምችት ያለባቸው በተተኳሽና በታክቲካል መሳሪያዎች የተሞሉ የዩክሬን መጋዘኖች ላይ የወሰደውን እርምጃ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል አጋርቷል፡፡ https://www.youtube.com/@Meshualekia
https://youtu.be/tikPuDzQj44?si=u2CUtlWBag2CQsIh
💥🆕አታድናችሁም!💥🔴 “አሜሪካ አታድናችሁም! የምትሰጣችሁ የደህንነት ዋስትናም ከኢራን ባለስቲክ ሚሳኤሎችና የረጅም ርቀት ድሮኖች አያተርፏችሁም፣ የሚመጣው ከባድ እሳት አይምራችሁም!” ይህን ማስጠንቀቂያ ያስተላለፉት የኢራን ጦር ከፍተኛ ዕዝ አዛዥ ሜጀር ጀነራል አሊ አብዱላሂ ናቸው፡፡ ከአሜሪካ ጋር የቆማችሁ ሀገራት ወየዉላችሁ፣ ከሚመጣው የእሳት ማዕበል አትተርፉም ሲሉ እየመጣ ያለው የኢራን አደገኛ ማዕበል የሀገሪቷን ጠላቶች ለመጠራረግ እንደተዘጋጀ ጠቁመዋል፡፡ ጀነራሉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ “ለወንጀለኛውና ወራሪው የአሜሪካ ጦር መከላከያ ጋሻ በመሆን የሚያገለግሉ ቀጣናዊ አገራት በሙሉ ኢራን በምትወስደው መጠነ-ሰፊ እርምጃና የእሳት ማዕበል እንደሚወድሙ ዝተዋል፡፡ 💥ሙሉ ዘገባውን ይመልከቱት! ⬇️ https://youtu.be/OfWuFe4R1Hw?si=rwmFcvtrfim970Dw
🆕የ800 ሺ ብር ዋስትና ተፈቀደለት! በ'ፊንቴክ' የኢንቨስትመንት ማጭበርበር ወንጀል ጋር በተያያዘ ተጠርጥሮ በእስር ላይ የሚገኘው ቲክቶከሩ መንሱር ጀማል፣ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የ800 ሺህ ብር ዋስትና እንደተፈቀደለት ዘሀበሻ ዘግቧል፡፡ ተጠርጣሪው በተጠረጠረበት ጉዳይ ከዚህ ቀደም በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና በጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረ ቢሆንም፣ ሁለቱም ፍርድ ቤቶች የዋስትና መብቱን ከልክለውት በማረሚያ ቤት ቆይቷል። ይሁን እንጂ መንሱር ጀማል "ዋስትና ልከለከል አይገባም፤ የህግ ስህተት ተፈጽሞብኛል" በማለት አቤቱታውን ወደ ሰበር ሰሚ ችሎት አቅርቦአንደነበርም ዘገባው አስታውሷል፡፡ አቤቱታውን የመረመረው ሰበር ሰሚ ችሎት፣ ዛሬ ሐምሌ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ባዋለው ችሎት ግለሰቡ በ800 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈታ ውሳኔ አሳልፏል ያለው ዜና ምንጩ ከገንዘብ ዋስትናው በተጨማሪም ተጠርጣሪው ከሀገር እንዳይወጣ ፍርድ ቤቱ እግድ ጥሎበታል ብሏል። ምንም እንኳን ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብቱን ቢፈቅድለትም፣ የዋስትና ማረጋገጫ የማስያዝና ተያያዥ ህጋዊ ሂደቶች እስካሁን ባለመጠናቀቃቸው ምክንያት፣ አቶ መንሱር እስከ ቀጣዩ ሳምንት መጀመሪያ ድረስ በማረሚያ ቤት በእስር ሊቆይ እንደሚችል የቤተሰብ ምንጮች ነገሩኝ ሲል ዘ-ሐበሻ አስነብቧል። #Ethiopia #FinTech #courtcase #ShegerTimesMedia
💥🔴ግብፅ በድሮን ነደደች!💥🔴 የተፈራው ደርሷል፡፡የኢራንና አሜሪካ ጦርነት ከመካከለኛው ምስራቅ ተሻግሮ ወደ አፍሪካ ምድር ተሻግሯል፡፡ “የጦርነቱ አድማስ ይሰፋል” በማለት ሲወተውቱ የነበሩ ወታደራዊ ተንታኞች ስጋታቸውን ተናግረው ሳይጨርሡ ጎረቤት ግብፅ በአጥፍቶ ጠፊ ድሮኖች ነድዳለች፡፡ እሳቱን ለማጥፋት ከ12፡00 በላይ እንደፈጀ በተነገረውና በግብፁ ዳሚየታ ወደብ ላይ የተፈጸመው ጥቃት በዋናነት የአሜሪካ ኩባንያ ንብረት በሆነ የነዳጅ መርከብ ላይ ያነጠጠረ ነበር፡፡ 👀 ዘገባውን ይመልከቱት! ⬇️ https://youtu.be/MCQS5VWPtSY?si=M-dbOGHfHrlKqjOy