tgindex
Shine mental health consultancy

Shine mental health consultancy

Статистика
@SMHC12английский

Sidirak.j(mental health professional) DON'T BE AFRAID TO ASK FOR HELP!! ☎️+251936851296 @Ananiaaaaa -telegram account

Последний пост
22 янв.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
283
0 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
316
17 постов
Вовлечённость
111,7%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • Mental health is not a choice; seeking help is an act of strength. we are available  @ Addis Ababa and Online

  • Stuttering (betelemdo mentebateb) tebilo miteraw metakem endmichil yawkalu?

  • https://www.youtube.com/watch?v=os1EDBmgJrY Melkam Zena alegn. Sile aimiro himemina meftewochu astemari videochn lemagignet you tube channelachinin subscribe yadrgu...... coming soon!!!!!!! Enameseginalen🙏

  • Ye aimiro himem begize wede hikimina ketewesede yitakemal. Tismamaleh/sh?

  • Begna community west sile aimiro himem yalew astesaseb mendnew? Yersos? Melsotn https://t.me/SMHC122 lay asawkun🙏

  • Ye aimiro himem ergman nw alu Tismamaleh/sh?

  • ke 150 belay ye aimiro himem aynetoch endalu yawkalu?

  • 🚬የአደንዛዥ እፅ ተጠቃሚነት (Substance Use Disorder) ምንድን ነው? የአደንዛዥ እፅ ተጠቃሚነት በተደጋጋሚ አልኮል ወይንም ሌሎች አደንዛዥ ዕፆችን በመጠቀም የሚመጣ  የተለያየ ችግር ነው። እነዚ ችግሮች: ችግሮቹ ምንድን ናቸው? 🚬ራስን መቆጣጠር አለመቻል 🚬ቶሎ ቶሎ አደንዛዥ ዕፁን መፈለግ 🚬የቤተሰብ ፣የስራ እና የማህበረሰብ ግኑነቶች ላይ ከባድ ጫና ማሳደር 🚬ጉዳቱን እያወቁ መውሰድ 🛠 እንዴት ከዕፅ ትጠቃሚነት መላቀቅ እንችላለን ? 1. ወደ ሱስ ማገገሚያ ቦታዎች በመሄድ 2. የሚሰጡ ማገገሚያ መድሃኒቶችን በአግባቡ መውሰድ 💊 3. የስነልቦና ህክምና ማግኘት 🧠 4. የቤተሰብ እና ማህበረሰብ ድጋፍ ማግኘት እንዲሁም 5. እራስን መንከባከብ አስፈላጊ ነው🧘‍♂️። 💬0936851296

  • Shine mental health consultancy pinned Deleted message

  • የእንቅልፍ አስፈላጊነት አንድ የ 24 አመት ግለሰብ በህይወት ዘመናቸው ለ 8 አመታት ተኝቷል:: እንቅልፍ ለሁለቱም የአካል እና የአእምሮ ጤና አስፈላጊ ነው:: በአማካይ አንድ ሰው በቀን ወደ 8 ሰአታት ይተኛል:: ይህም ከጠቅላላው ህይወቱ ውስጥ በግምት አንድ ሶስተኛ ነው:: ይህ የሚያሳየው እንቅልፍ ለአጠቃላይ ደህንነት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ነው። ይህ በጣም ብዙ ሊመስል ይችላል፣ ነገር ግን ሰውነቱ እንዲያገግም፣ እንዲጠግነው እና እንዲሞላ አስፈላጊ ነው። በእንቅልፍ ወቅት ሰውነት ጉልበትን ያድሳል:: የሰውነትን በሽታ የመከላከል ስርዓትን ያጠናክራል:: የአንጎል ተግባራትን እንደ ትውስታ እና መማርን ይደግፋል:: እንቅልፍ በስሜታዊ ቁጥጥር ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል:: እንቅልፍ ማጣት ጭንቀትን፣ ጭንቀትን አልፎ ተርፎም ድብርትን ሊያስከትል ይችላል፣ ምክንያቱም አንጎል ስሜትን በአግባቡ ለማስተናገድ እና ለመቆጣጠር እረፍት ስለሚያስፈልገው። በተጨማሪም፣ እንቅልፍ በአካላዊ ጤንነት ላይ ተጽእኖ ያሳድራል፣ ይህም እንደ የልብ ህመም፣ የደም ግፊት እና ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያሉ ችግሮችን ለመቀነስ ይረዳል። በማጠቃለያው እንቅልፍ የእረፍት ጊዜ ብቻ ሳይሆን ጤናን ለመጠበቅ አስፈላጊ ሂደት ነው:: ጤናማ እና ሚዛናዊ ህይወት ለመኖር እያንዳንዱ ሰው ለእንቅልፍ ቅድሚያ መስጠት እና በእያንዳንዱ ምሽት በቂ እረፍት ማግኘቱን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው:: Yohannes Yaya (Mental health specialist, Wolaytta Sodo University) ሌሎችንም ያጋሩ http://t.me/SMHC12

  • ስሜታዊ ትስስር በትዳር ውስጥ ‎================= ‎ባለትዳሮች እርስ በእርስ  በጋራ መግባባት, መተሳሰብ, መተማመን እና መቀራረብ  ጤናማ እና እርካታ ያለው ግንኙነት እንዲኖራቸው ያግዛል። ‎ ስሜታዊ ግንኙነትን እንዴት መገንባት ይቻላል ? 👇👇👇👇👇👇👇👇 ‎ ‎1. ንቁ የማዳመጥን ችሎታ ማዳበር( ‎ አጋርዎ በሚናገሩበት ጊዜ ያልተከፋፈለ ትኩረት ይስጡ)። ‎ ‎👉ምላሽ ከመስጠትዎ በፊት ሃሳባቸውን ያስጨርሱ። ‎ ‎2. ስሜትዎን ያካፍሉ ማንንም ሳትወቅስ ስሜትህን ግለጽ። ‎ ‎3. አንዱ ለሌላው ስሜት  እውቅና መስጠት  ለምሳሌ፡ “ለምን እንደዚያ እንደሚሰማህ ተረድቻለሁ”። ‎ ‎4. ሁለታቹ ብቻ አብራችሁ የምታሳልፉበት ጊዜ ይኑራችሁ። ‎ ‎👉አንዳችሁ ለሌላው ቅድሚያ ስጡ። ‎ ‎👉ለጋራ ተግባራት ትኩረት መስጠት  (ሁለታችሁም የሚትወዷቸውን ነገሮች) ለምሳሌም እንደ ምግብ ማብሰል፣ የእግር ጉዞ ማድረግ ወይም ፊልም መመልከት። ‎ ‎5. አጋርዎ ለሚሰራቸው ትንሽ ነገሮች እውቅና ይስጡ።  የምታደንቃቸውን ጥንካሬዎቻቸውን እና ባህሪያቸውን ጠቅሰው አመስግኗቸው። ‎ ‎6. አለመግባባቶች በሚፈጠሩበት ጊዜ ከመጮህ ወይም ከመውቀስ ይልቅ በመፍትሔዎች ላይ በማተኮር ችግሮችን ለመፍታት በጋራ ይስሩ። ‎ ‎7. ስለ ህልሞቻችሁ፣ እሴቶቻችሁ እና ለወደፊትህ ምን እንደምትፈልጉ በጋራ ተነጋገሩ። ‎ ‎👉ለሁለታችሁም ትርጉም ያላቸው ወጎችን ወይም ልማዶችን ያዘጋጁ (ለምሳሌ፡ ሳምንታዊ የቀን ምሽቶች፣ ዓመታዊ ጉዞዎች)። ‎ ‎8.  ስሜታዊ ትስስር የሚገነባው በተከታታይ ጥረት እና በመተማመን ነው። ‎ ‎👉ተስፋ አለመቁረጥ:  ግንኙነትን እንደገና መገንባት ጊዜ እና ትዕግስት ይጠይቃል። ‎ለምንድነው ስሜታዊ ግንኙነት አስፈላጊ የሆነው?👇👇👇👇👇👇👇👇 ‎ ‎👉ጠንካራ ስሜታዊ ትስስር ያላቸው ጥንዶች የበለጠ እርካታ  ይሰማቸዋል። ‎ ‎👉ስሜታዊ ግንኙነት ግልጽ፣ ታማኝ እና ትርጉም ያለው ውይይቶችን ያበረታታል። ‎ ‎👉ጠንካራ ስሜታዊ ትስስር ባለትዳሮች ግጭቶችን እና ተግዳሮቶችን የበለጠ ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲፈቱ ይረዳቸዋል። ‎ ‎👉ስሜታዊ መቀራረብ ብዙ ጊዜ ወደ ጥልቅ አካላዊ ግንኙነት ይመራል። ‎ ‎👉በስሜት መተሳሰር እርስ በእርስ እንዲከባበሩ ያግዛል፣ የመገለል ስሜትን ይቀንሳል። ‎ ‎ ‎ ‎Derebe Madoro (senior mental health specialst) Contact us to get the service +251936851296

  • Channel name was changed to «Shine mental health consultancy»

  • Channel name was changed to «Sidirak jiregna»

  • без подписи

  • 22 дек. 2024 г.3492из psychiatry1

    እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ 🙏 ሰላም ይብዛላችሁ ውድ የሀገሬ ልጆች እንኳን  ለNEBIYU PSYCHIATRY E-CLINIC ቴሌግራም ቻናል ሁለተኛ ዓመት ክብር በዓል አደረሰን አደረሳችሁ🙏 ይህን አስመልክቶ በተለያዩ የስነ አእምሮ ርዕሰ ጉዳዮች በተለያዩ ባለሙያዎች በየሳምንቱ ቅዳሜ ከምሽቱ 3:00 ላይ ነፃ የOnline live stream ትምህርት አዘጋጅቷል። የዚህን ሳምንት የፊታችን ቅዳሜ ማለትም ታህሳስ 19 Overcoming Depression በሚል ርዕሰ የተሰናዳ ትምህርት በነፃ ተጋብዛችኋል። ማጋራት አይረሳ እናመሰግናለን ቦታው : https://t.me/psychiatry1 ነብዩ ጃግሶ (ስነ አእምሮ ባለሙያ)

  • ኦቲዝም 🩺 ኦቲዝም ምንድነው? ኦቲዝም ማለት የአንጎል ዕድገት ዉስንነት ተብለዉ ከሚታወቁ ህመሞች ዉስጥ አንዱ ነዉ፡፡ ኦቲዝም በአንጎል እና በአእምሮ የነርቭ ሥርዓት ዕድገት ዉስንነት የተነሳ በሚፈጠር የጎላ የማህበራዊ ተግባቦት ችግር ከሌሎች ጋር ለመግባባትና አብሮ ለመሆን የመቸገር ህመም ነዉ፡፡ የኦቲዝም ህመም ያለባችዉ ልጆች ከጤናማ ልጆች በተለየ መልኩ ተደጋጋሚ ነገሮችን የማድረግ ልምድ እና በጣም ዉስን የሆኑ ፍላጎቶች አላቸዉ። 🩺 ለኦቲዝም አጋላጭ የሆኑ ሁኔታዎች ምንድናቸው? 1. ዘረመል/ተፈጥሯዊ 🔹በቤተሰብ/ቅርብ ዘመድ የኦቲዝም ህመም ተጠቂ ካለ 🔹ዕድሜ ከገፋ በኃላ ልጅ መዉለድ (አባት ከ40 ዓመት በላይ ፤ እናት ከ35 ዓመት ሲበልጡ) 🔹ልጆችን በጣም አቀራርቦ መዉለድ (ከሁለት አመት በታች በሆነ ልዩነት የተወለዱ ህፃናቶች ይበልጥ ተጋላጭ ይሆናሉ) 🔹የመጀመሪያ ልጅና ወንድ ልጅ ይበልጥ ተጋላጭ ይሆናሉ 2. አካባቢያዊ/አስተዳደጋዊ ምክንያቶች 🔹በእርግዝና ወቅት ➛ እናት የአካላዊም ሆነ የእእምሮ ህመም ተጠቂ ከሆነች ➛ ከመጠን በላይ ዉፍረት ➛ የተለያዩ መድሀኒቶችን መዉሰድ ➛ ለኬሚካሎች ተጋላጭ መሆን ➛ የአልኮል መጠጦችን ደጋግሞ መዉሰድ 🔹በወሊድ ወቅት ➛ መወለድ ካለበት ግዜ ቀድሞ የተወለደ ልጅ ➛ አነስተኛ ክብደት 🔹ህፃናት ከተወለዱ በኃላ ➛ በወሊድ ግዜ የሚከሰቱ ማንኛዉም ጉዳቶች ➛ ደም መፍሰስ ➛ የተራዘመ ምጥ ➛ የማጅራት ገትር ህመም ➛ የሚጥል ህመም ➛ የምግብ እጥረት 🩺  የኦቲዝም ምልክቶች 🔸ከሰዎች ጋር አብሮ መሆን አለመፈለግ/ለብቻ መሆንን መምረጥ 🔸ለሰዎች ምንም አይነት ፈገግታ እና አካላዊ እንቅስቃሴዎችን አለማሳየት 🔸ከሰዉ ይልቅ ለመጫወቻና ለሌሎች ቁሳቁሶች ፍላጎት ማሳየት 🔸ቃል ለማዉጣት እና በንግግር ለመግባባት አለመቻል 🩺 የኦቲዝም ምልክት ደረጃዎች 1. አነስተኛ/ዝቅተኛ ደረጃ ➨ ዕድሜቸዉ እስከሚገፋ / እስከ 6 ዓመት ድረስ ላይታወቅ ይችላል፡፡ 2. መካከለኛ ደረጃ ➨ ከ4-6 ዓመት ዉስጥ ሊታወቅ ይችላል፡፡ 3. ከፍተኛ ደረጃ ➨ ከ1 ዓመት ጀምሮ ሊታወቅ ይችላል፡፡ 🩺 የኦቲዝም የህክምና አማራጮች የኦቲዝም ህመም ህክምና ዓላማ ማህበራዊ ግንኙነትን/ መስተጋብርን ማሻሻልና የህመሙ ተጠቂዎች ከሰዎች ጋር ግዜ እንዲያሳልፉ ማድረግ ፣ የቃላትና የምልክት ተግባቦትን ማዳበር ፣ ወደ ትምህርት ቤት እንዲቀላቀሉ እና እንዲማሩ ማድረግ ነው። የኦቲዝም ህመም የህክምና አማራጮች ፦ 1. የመድሃኒት ህክምና ➨ የመድሀኒት ህክምና በታማሚው ላይ አስቸጋሪ ባህሪ ሲኖር ፣ የምግብ ፍላጎት ሲቀንስ እና የእንቅልፍ ችግር ሲኖር የሚሰጥ ነው፡፡ 2. የስነ-ልቦና ፣ የማህበራዊ እናና የባህሪ ህክምና ➨ ይህ ህክምና ከፍተኛ ለዉጥ የሚገኝበት ሲሆን ትዕግስት እና ከፍተኛ ክትትል የሚጠይቅ ነው፡፡ ያስታውሱ ፦ ሁሉም ወላጅ ልጆቹን ማዳመጥና በተለያዩ ማህበራዊ ግንኙነቶች ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ✍️ በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል የጤና ትምህርት እና የስነ-አእምሮ ክፍል የተዘጋጀ © ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም! Ethio Psychiatry (ኢትዮ ሳይካትሪ) ✅Join Us @ethiopsychiatry @ethiopsychiatry

  • 🗞 የሚጥል ሕመም ለሚያጋጥማቸው የቤተሰብ አባላሌ በቤት ውስጥ ሊደረጉ የሚችሉት 10(፲) ጠቃሚ ምክሮች እነሆ:- 1. ቅድሚያ ለደህንነት (Safety First) ስጡ፦ የሰውነት መንቀጥቀጥና እንፍርፍሪት በሚከሰትበት ጊዜ ታማሚው እንዳይጎዳ ማራቅ፤ መጠበቅ 2. ማረጋጋት (Keep Calm):- ታማሚው ንቁ ከኾነ አይዞህ ባይነት አይለያችሁ፤እናንተም ተረጋጉና የመንቀጥቀጥ ነገሩ እስኪቆም አብራችሁት ቆዩ 3. ራስን የመሳት ነገር ካለ በስተጎኑ አስተኙት (Positioning):- ይኸውም የአየር መተላለፊያዎች እንዲከፈቱ እና የመታፈን ነገሮችን ያስቀራል። 4.አጠቃላይ የእንፍርፍሪት ጊዜውን መዝግባችሁ (Timing) ያዙና በተለይ ታማሚው ከ5 ደቂቃ በላይ ከቆየበት በአፋጣኝ ወደ ሆስፒታል ውሰዱት 5. የሚከተለቱትን ነገሮች በፍጹም እንዳታደርጉ (Avoid Restraints) ፦ 🪢  እንዳይንቀሳቀስ ማሰር 👄 በአፍ ውስጥ ምንም ነገርን መጨመር ➻ ክብሪትን ማጨስና ማጠን 🤔 ክፉ መንፈስ፤ እርግማን ወዘተርፈ ብሎ ለማስወጣት አካላዊ ጫናዎችን በመፍጠር፤ መተኮስ መደብደብና መግረፍ፤ ከመጠን በላይ በውኃ መዝፈቅ ወዘተ... 6. ከማንቀጥቀጥ እና የእንፍርፍሪት በኋላ ድካምና መወዛገብ፤ የእንቅልፍ መተኛት፤ እንዲሁም ራስን ስቶ መቆየት ሊኖር ይችላሉና ድህረ እንፍርፍሪት እንክብካቤ (Post Convulsions care) ማድረግ ያስፈልጋል፤ እሊኽም ፦ ➻ አብሮ መቆየት ➻ እረፍት እንዲያርጉ ማድረግ፤ ➻ አለሁልህ ባይነትን ማሳየት ➻ችግሩ የተከሰተው በታማሚው ጥፋት እንዳልኾነ በመንገር ራስን መውቀስ እንዳይኖር መንከባከብ ➻ ጊዜ ሰጥቶ አብሮ መኾንና ለወደፊት ታክመው ደህና እንደሚኾኑ ተስፋ መስጠትን የመሳሰሉትን ማድረግ ያሻል። 7. ታማሚው ሕክምና ጀምሮ ከነበርና ከተቋረጠ የፀረሚጥል ሕመም መድኃኒቶቹን ማስቀጠል፤ ተደጋጋሚ ከኾነ ደግሞ ሕክምናቸውን የመቆጣጠር ኹነት ለማስቻል በአዲስ ያልጀመረም ከኾነ ደግሞ ሐኪም ጋር በመውሰድ ሙሉ ምርመራን እንዲደረግላቸው ማገዝና አለኝታነትን ማሳየት 8. በአባባሽነት የሚጠቀሱና በውል የሚታወቁ ነገሮችን (Avoid Triggers) ያስወግዱ። ለምሳሌም እንደ ፦ ጭንቀት፣ የእንቅልፍ መዛባት፣ የምግብና መጠጦች ፣መድኃኒትን በአግባቡ ሳይወስዱ መርሳትን የመሳሰሉትን ኹሉ ለማስተካከል መጣር 9. አካታች የሕክምና እቅድ (Comprehensive Plan) ያዘጋጁ፦ ይኸውም በአስቸኳይ የማንቀጥቀጥ ነገር ቢከሰት ምን መደረግ እንዳለበትና እንደሌለበት፤ አጠቃላይ ስለሕመሙ ኹኔታ ከቅርብ ካሉ ቤተሰብዎት ጋር በግልጽ ተወያዩበት። 10. መደበኛውን ክትትል መቀጠሉ አይዘንጋ (Regular Follow ups): በመደበኛነት ሐኪምዎን እንዲያገኙ ያድርጉ፣አብረው በመመካከር ሕክምናውን ያሻሽሉ። @SMHC @SMHC

  • Good news!!!!!!!!! እንዴት ናቹ የ shine mental health consultancy ተከታታዮች። ዛሬ አስደሳች ዜና ይዤላቹ መጥቻለዉ 👉 ማንኛዉንም ጤና ነክ ጥያቄ specialist ሃኪሞችን ለማማከሪ ኣስበዋል?  እንግዳዉስ 👇👇👇👇👇👇👇 tena frist plus ያዘጋጀዉን platform በመጠቀም ባሉበት ሆኖ በተመጣጣኝ ክፈያ ማለትም ከ 150 ብሪ ጀምሮ አገልግሎቱን ማግኘት እንደምትችሉ ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነዉ ።።። የአገልግሎት ማግኛ አማራጮች 1.tena first plus app 2.call center at 6037 🗣🗣🗣🗣🗣🗣 የአዕምሮ ሃኪሞችን ጨምሮ ከ 500 በላይ specialist doctors በዝህ platform አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ!!!!!

  • 👇👇👇👇👇👇 "An excellent and normal release from heartache is to give way to grief. There is a foolish point of view current today that one should not show grief, that it is not proper to cry or express oneself through the natural mechanism of tears and sobbing. This is a denial of the law of nature. It is natural to cry when pain or sorrow comes. It is a relief mechanism provided in the body by Almighty God and should be used. 🗣I should warn, however, that this mechanism should not be used unduly nor allowed to become a habitual process" @SMHC12

  • የአእምሮ ጤና - በዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳለማው! እንደ አለም የጤና ድርጅት የጤነኝነት መስፈርት መሰረት አንድ ሰው ጤናው ተጠብቋል  የሚባለው አካላዊ፣ አዕምሯዊ እና ማህበራዊ ጤንነቱን ማሟላት ሲችል ነው:: ሰዎች የአዕምሮ ጤናቸው ሲጠበቅ የተለያዩ የሂወት መስኮቻቸውን በአግባቡ ማሳለጥ ይቻላቸዋል :: በዚህም መሰረት የሰዎች መስራት እና ተግባብቶ ለመኖር መቸገርን የአዕምሮ ጤና ህመም ተከስቷል ለማለት እንደ አንድ ቅድመ ሁኔታ ይቀመጣል ይላሉ በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳማው ። የአለም ጤና ድርጅት እንዳስታወቀው ከ8 ስዎች መካከል  በአንዱ የአዕምሮ ህመም ሊኖርበት ይችላል ተብሎ ይገመታል ያሉት ባለሞያው፤ ከ360 በላይ የአዕምሮ ህመሞች ሲኖሩ፤  ከቀላል ጭንቀቶች እሰከ ከባዱ አዕምሮ መቃወስ(Schizophrenia) ድረስ ያሉትን ያካትታል ብለዋል:: የአዕምሮ ህመም የተለያዩ አጋላጭ እንዲሁም አባባሽ ምክንያቶች ያሉት ሲሆን በዋናነት በሶስት ከፍሎ ማየት ይቻላል፤ ስነ ሂወታዊ(Biological)፣ ስነ ልቦናዊ(Psychological) እና ማህበራዊ(Social) ምክንያቶች:: አንጎል ላይ የሚከሰቱ ችግሮች ወይም አደጋዎች :ሱስ ተጠቃሚነት ( ጫት አልኮል የመሳሰሉት ) ፣dopamine እና የመሳሰሉ የጭንቅላት መልዕክት አስተላላፊ ንጥረ ቅመሞች በተለያየ ምክንያት መዛባት፣  የስኳር: ግፊት: አዙሪት(epilepsy) እና ሌሎች  አካላዊ ህመሞች አንድን ሰው ለአዕምሮ ህመም ሊጋለጥባቸው ከሚችሉት ስነ- ሂወታዊ  ምክንያቶች መካከል ተጠቃሸ ናቸው ብለዋል ዶ/ር እስጢፋኖስ። ከልጅነት ግዜ ጀምሮ በሂወታችን የሚያጋጥሙን  ክስተቶች (ለምሳሌ  አካላዊ: ጾታዊ እና መሰል ትንኮሳዎች) ወላጅን በተለያዩ ማጣት ምክንያቶች ፣ የወላጅ ፍቅርን ሳያገኙ ማደግ የመሳሰሉት ስነ ልቦናችን ላይ ጫና በመፍጠር ለአዕምሮ ህመም  ስነ- ልቦናዊ  መነሻ ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ  ብለዋል። ማህበራዊ ምክንያቶች ሶስተኛው መንስኤ ሲሆን በርካታ ማህበራዊ ቀውሶች; ማለትም እንደ ጦርነት፣ መፈናቀል፣ ግጭት፣ የኢኮኖሚ ችግር እና የመሳሰሉት ጫናዎቸ ለአዕምሮ ህመም መንስኤ እንዲሁም አባባሽ ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ ያሉት ዶ/ር እስጢፋኖስ ባህላዊ/መንፈሳዊ ምክንያቶች እንደ አንድ መነሻ ምክንያት የሚያቀርቡም ይኖራሉ ብለዋል። የአዕምሮ ህመም ምልክቶች        በሃሳብ መዛነፍን ማስተዋል        በስሜት መለዋወጦች         በባህሪ መለወጦች የሚታዩ ሲሆን:- አንድ ሰው እንግዳ እና ግራ የሚያጋባ  አስተሳሰብ ማለትም ለሌሎች የማይሰማ ድምፅ መስማት፣ የማይታይ ነገር ይታየኛል ማለት፣ ሰዎች ይከታተሉኛል በሎ ማሰብ፣ ከሌሎች የተመረጥኩ ነኝ ሲል፣  ስለ ራሱ አሉታዊ ነገር መሰብ( እኔ አልጠቅምም ማለት: አለፍ ሲልም ራስን ሰለማጥፋት ማሰብ) ፣ የስሜት መለወጥ፣ ከማህበረሰቡ ወጣ ያሉ ባህሪዎችን ማሳየት የአዕምሮ ህመም ምልክቶች መሆናቸውን ዶ/ር አስጢፋኖስ ተናግረዋል። የአዕምሮ ህመም  በሚከተሉት መልኩ ማከም ይቻላል የሚሉት ዶ/ር እስቲጢኖስ          እነዚህም መንገዶች ▪️   ስነ ህይወታዊ( አስፈላጊውን መድሃኒት በመስጠት፣ ተጓዳኝ ህመሞችን በማከም) ▪️ሰነ ልቦናዊ(psycho therapy) ▪️ማህበራዊ ጉዳዮችን በመፍታት ባህላዊ እና መንፈሳዊ ህክምናዎችን በማካተት ነው:: የአዕምሮ ህመም መታከም የሚችል ህመም በመሆኑ ምልክቱ የታየበት ማንኛውም ሰው ቤት ውስጥ እሮ ከማቆየት ይልቅ ወደ ህክምና ተቋም በፍቅርና እንክብካቤ መውሰድ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል ዶ/ር እስጢፋኖስ ። https://t.me/SMHC12 https://t.me/SMHC12