tgindex
Sda Songs

Owner @Robelzewde

Последний пост
24 апр.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 936
+8 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
2 591
20 постов
Вовлечённость
133,8%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • Sda Songs pinned «ስሜትና ራስን ማሸነፍ “... በመንፈሱም ላይ የሚገዛ ከተማ ከሚወስዱ ይበልጣል” ምሳሌ 16:32  ጀግና ማለት፤ ኃይለኛ፣ ተፋልሞ የጣለ፣ ተዋግቶ የረታ አይደለም። ጀግና ማለት ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል ቢለወጥ፣ ወፍጮን ወይንም የፋብሪካን “ማሽን” ሊያንቀሳቅስ የሚችለውን በጭንቅላት ውስጥ የተጠመደውን የስሜት ቦንብ፣ ከአንጎል ተነስቶ ወደ እጅህ፣ ወደ እግርህ፣ ወደ አፍህ የሚፈሰውን ጠነካራ …»

  • 24 апр.1 379223

    በስሜ የተጠራው ሕዝቤ ራሱን አዋርዶ ቢጸልይ፣ ፊቴን ቢፈልግና ከክፉ መንገዱ ቢመለስ፣ ከሰማይ እሰማዋለሁ፤ ኀጢአቱን ይቅር እላለሁ፤ ምድሩንም እፈውሳለሁ። 2 ዜና 7፥14 መቅደሱ የእግዚአብሔር ሕዝብ ወደ እርሱ ቀርበው ራሳቸውን ቢያዋርዱ፣ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱና ወደ እግዚአብሔር ጸጋ፣ምሕረት፣ ጥበቃና ፍቅር ቢመለሱ ጸሎታቸው የሚሰማበት ቦታ እንደ ሆነ እግዚአብሔር ለሰለሞን ይነግረዋል። የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በአካል አሁን ባይኖርም፣ ይህ ተስፋ ዛሬም እውነት ነው። የእግዚአብሔር መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ በሕዝቡ መሰባሰብ (1 ቆሮንቶስ 3፥16፤ ማቴ 18፥20) እና በእያንዳንዳችን ሰውነት ውስጥ (1ቆሮንቶስ 6፥19-20) ይገኛል። እንዴት ያለ በረከት ነው። ለእኛም እንዴት ያለ ታላቅ ስጦታ ነው! ከአማኞች ጋራ ስንሰበሰብ፣ በእግዚአብሔር ፊት ራሳችንን ስናዋርድ፣ ከራስ ወዳድነታችንና ከክፉ መንገዳችን ስንመለስና የርሱን መገኘት ስንፈልግ አብ ይሰማናል። ራሳችንን ለማዋረድና ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ ዓለም ዐቀፍ መነቃቃት ከመጠበቅ ይልቅ በዚህ ጥረት ውስጥ ሊያግዙን ከሚችሉ ሌሎች ሰዎች ጋራ ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ለምን አንጸልይም? በጸሎትና ወደ እግዚአብሔር በመመለስ ዓለም ዐቀፍ መነቃቃት፣ መታደስና ለውጥ እናስጀምር! መልካም ሰንበት 😊🙏

  • 18 апр.1 565172

    ወጣትነትህን ማንም አይናቅ፤ ነገር ግን ለሚያምኑት በንግግርና በኑሮ፣ በፍቅር፣ በእምነትና በንጽሕና አርኣያ ሁንላቸው። 1 ጢሞቴዎስ 4፥12 የወጣቶቻችንን ትላልቅ ሐሳቦችና ፍላጎቶችን ችላ ማለት የለብንም። ወጣት ከሆንክ፣ የቤተ ክርስቲያን የወደ ፊት አካል ብቻ ሳትሆን የእግዚአብሔር የዛሬ ሠራተኛ ነህ። እርሱን በሙሉ ልብህ አገልግል፤ በዕድሜ ከፍ ላሉትም ምሳሌ ሁን! በዕድሜ የገፋህ ከሆንክ ደግሞ፣ ወጣቱን አትናቅ። የመሥራት ጕጕታቸውን አታጣጥል። ይልቁንም ወጣት አማኞችን አበረታታ። ጕልበታቸውን፣ ስጦታቸውንና እግዚአብሔርን ለማክበር ያላቸውን ዐቅም ይበልጥ አሳድግ። የተወሰኑ ድንቅ የእምነት ምሳሌዎቻችን በጠንካራ እምነት ጌታችንን የሚያገለግሉ ወጣቶች እንደ ሆኑ አስታውስ። መልካም ሰንበት!!😊🙏

  • 2 дек.2 513159

    አዲስ መዝሙር አንተ ግን አስቀድመህ ከፈር የተሰራ https://youtu.be/NRlxLmapEuo?si=jQh9SIAGkCxubmlv

  • 4 нояб.3 119364

    “እስቲ እንስሶችን ጠይቁ፤ ያስተምሯችኋል፤ የሰማይ ወፎችንም ጠይቁ፣ ይነግሯችኋል፤  ለምድር ተናገሩ፤ ታስተምራችኋለች፤ የባሕርም ዓሣ ይነግራችኋል።  የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንዳደረገ፣ ከእነዚህ ሁሉ የማያውቅ ማን ነው? የፍጥረት ሁሉ ሕይወት፣ የሰውም ሁሉ መንፈስ በእጁ ናትና፤  ምላስ የምግብን ጣዕም እንደሚለይ፣ ጆሮ ቃላትን አይለይምን? ጥበብ ያለው በአረጋውያን ዘንድ አይደለምን? ማስተዋልስ ረዥም ዕድሜ ባላቸው ዘንድ አይገኝምን? “ጥበብና ኀይል የእግዚአብሔር ናቸው፤ ምክርና ማስተዋልም በእርሱ ዘንድ ይገኛሉ።" 🥰 ....... ኢዮብ 12:7-13 መልካም ቀን 🙏

  • 28 окт.2 945142

    📌 የፊታችን እሁድ ጥቅምት 23 ከምሽቱ 2:30 ጀምሮ "ፖርኖግራፊ እና መሰል ሱሶችን እንዴት ማሸነፍ ይቻላል?"🤔 👉ከወንድም አቤኔዘር ወርቁ ጋር 1. የፖርኖግራፊ ታሪካዊ አመጣጥ እንዴት ነው? ዓላማውስ ምንድነው? 2. ፖርኖግራፊ በአካል፣ በአእምሮ፣ በማኅበራዊና በመንፈሳዊ ሕይወት ላይ የሚያደርሳቸው ጉዳቶች ምንድናቸው? 3. ከፖርኖግራፊ ሱስ መውጣት የምንችለው እንዴት ነው? https://t.me/AYBCLUB

  • ኢሳይያስ 66 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²² እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ከፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፥ እንዲሁ ዘራችሁና ስማችሁ ጸንተው ይኖራሉ፥ ይላል እግዚአብሔር። ²³ እንዲህ ይሆናል፤ በየመባቻውና በየሰንበቱ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በፊቴ ይሰግድ ዘንድ ዘወትር ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር። Happy Sabbath 😊🙏

  • «መተላለፉ ይቅር የተባለለት፧ኃጢአቱም የተሸፈነለት፣እንዴት ብሩክ ነው!እግዚአብሔር ኃጢአቱን የማይቆጥርበት፣በመንፈሱም ሽንገላ የሌለበት ሰው፣ እርሱ ብሩክ ነው::» መዝ 32:1-2 Melkam senbet 😊🙏

  • እንዲህም ብሎ መመስከር ይችላል፡- «እርዳታ ፈልጌ ሳለ ኢየሱስን አገኘሁት፡፡ ፍላጎቶቼን ሁሉ አሟላልኝ፡፡ የነፍሴ ረሐብ በጥጋብ ተተካ፡፡ አሁን ለእኔ መጽሐፍ ቅዱስ የክርስቶስ መገለጥ ነው፡፡ ለምን በክርስቶስ ታምናለህ; ብትሉኝ እርሱ ለእኔ መለኮታዊ አዳኜ ስለሆነ ነው፡፡ ለምን በመጽሐፍ ቅዱስን ታምናለህ; ብትሉኝ ለነፍሴ የእግዚአብሔር ድምጽ ሆኖ ስላገኘሁበት ነው፡፡» መጽሐፍ ቅዱስ እውነት እንደሆነና ክርስቶስም የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ለራሳችን ምስክርነቱን ልናገኝ እንችላለን፡፡ በጥበብ የተቀነባበረ ውሸት እንደማናምን እናውቃለን፡፡ ክየመ 108.3 ቅዱስ የሰንበት እረፍት😊🙏

  • “እርስ በርሳችሁ ትዕግሥትን አድርጉ፥ ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው፥ ይቅር ተባባሉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ፤”   — ቆላስይስ 3፥13 ቅዱስ ሰንበት መልካም እረፍት😊🙏

  • በቤተሰብ የጸሎት ጊዜ ሊኖረን ይገባል፤ ከሁሉም በላይ ግን በግል በስውር የምንጸልየውን ጸሎት ቸል ልንለው አይገባም፤ የነፍስ ህይወት ያለው በዚያ ነውና፡፡ ጸሎት ቸል ተብሎ ነፍሳችን ፈጽሞ ሊያብብ አይችልም፡፡ የቤተሰብ ወይም የጉባዔ ጸሎት ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ ለብቻችን በመሆን ሁሉን ለሚመረምሩት የእግዚአብሔር ዓይኖች ህይወታችንን መገላለጥ ያስፈልጋል፡፡ የምስጢር ጸሎታችን የሚሰማው ጸሎት ሰሚ በሆነው አምላክ ብቻ ነው፡፡ ክየመ 93.null.null - ክየመ 93.2 ቅዱስ ሰንበት መልካም እረፍት😊🙏

  • የአዲስ አመት ስጦታ😊📦

  • "የዛሬው ቀን [እግዚአብሔር] የሰጠን የመጨረሻ ቀን እንደሆነ አድርገን እንድንመለከት፣ እንድንሠራ እና እንድንጸልይ ይገባናል::" 5T 200.3 መልካም ቀን መልካም ሳምንት🙏

  • ዕብራውያን 2 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁷ ስለዚህ የሕዝብን ኃጢአት ለማስተስረይ፥ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን፥ በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው። ¹⁸ እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለ ተቀበለ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና። ቅዱስ ሰንበት መልካም እረፍት😊🙏

  • ሃይማኖት ከችግር ወዲያ ተሻግሮ ደስታን ይመለከታል፡፡ እግዚአብሔርንም ስለሚመለከት አይደነግጥም፡፡ ሃይማኖት በማንኛውም ድንገተኛ የችግር ጊዜ የእግዚአብሔርን አጅ ይጨብጣል፡፡ GWAmh 167.3 ቅዱስ ሰንበት መልካም እረፍት😊🙏

  • 1ኛ ቆሮንቶስ 16 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹³ ንቁ፥ በሃይማኖት ቁሙ፥ ጎልምሱ ጠንክሩ። ¹⁴ በእናንተ ዘንድ ሁሉ በፍቅር ይሁን። ቅዱስ ሰንበት መልካም እረፍት😊🙏

  • መዝሙር 121 ¹ ዓይኖቼ ወደ ተራሮች አነሣሁ፤ ረዳቴ ከወዴት ይምጣ? ² ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። ³ እግርህን ለመናወጥ አይሰጠውም፤ የሚጠብቅህም አይተኛም። ⁴ እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም አያንቀላፋምም። ⁵ እግዚአብሔር ይጠብቅሃል፥ እግዚአብሔርም በቀኝ እጅህ በኩል ይጋርድሃል። ⁶ ፀሐይ በቀን አያቃጥልህም ጨረቃም በሌሊት። ⁷ እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፥ ነፍስህንም ይጠብቃታል። ⁸ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም እግዚአብሔር መውጣትህና መግባትህን ይጠብቃል።                ብሩክ ሰንበት😊🙏

  • ግሩም መዝሙር ............. ጽኑ ጋሻዬ 💪 🎤  ዘማሪያን:- ውዳሴ ኳየር ለምን እጨነቃለሁ ተስፋ እንደሌለው ሰው... @sda_songs

  • “ሰውም፦ ይህ በእጅህ መካከል ያለ ቍስል ምንድር ነው? ይለዋል። እርሱም፦ በወዳጆቼ ቤት የቈሰልሁት ቍስል ነው ይላል።” ዘካርያስ 13፥6 “በየቀኑ የክርስቶስን ህይወት በማሰላሰል የተወሰነ ሰዓት ብናሳልፍ መልካም ነበር። እያንዳንዱን ነጥብ በተለይም የህይወቱን መዝጊያ ክፍል በምናባችን እናሰላስለው። ስለዚህ ለእኛ በተከፈለው ታላቅ መስዋዕትነት ላይ ስንነጋገር፣ በእርሱ ላይ ያለን እምነት ይበልጥ ጽኑ ይሆናል፣ ፍቅራችን ሕያው ይሆናል፣ በመንፈሱ በጥልቅ እንሞላለን። በመጨረሻ ለመዳን የምንፈልግ ከሆነ በመስቀሉ ሥር የንስሐን እና የትህትናን ትምህርት መማር አለብን።” The Desire of Ages, p 83 Happy Sabbath 😊🙏

  • “እነሆ፥ ቶሎ ብዬ እመጣለሁ፤ ማንም አክሊልህን እንዳይወስድብህ ያለህን አጽንተህ ያዝ።”   — ራእይ 3፥11 Happy Sabbath 😊🙏

Sda Songs — tgindex