Ebenezer prayer ministry የአቤንኤዘር የፀሎት ሚኒስትሪ
Статистика+251944081068 "አቤንኤዘር" "ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ፀልዪ"
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 24
- Всего постов
- 25
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 79
- 1/48двое суток
- 90
- 1/72трое суток
- 97
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
Live stream finished (1 hour)
ገጽ 430 ፓ/ር ደስታ ኦንቶሼ
Live stream started
W
Live stream finished (1 hour)
7/13/18 ወ/ዊ ሊቆዩ
Live stream started
Live stream finished (24 seconds)
Live stream started
Live stream finished (42 seconds)
Live stream started
Live stream finished (30 seconds)
Live stream started
Live stream finished (1 minute)
Live stream started
видео или голосовое, без подписи
📅 ነሐሴ 7 አድኖናል፤ ያድነናልም ━━━━━━━━━━━━━ 📖 የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል: 2 ቆሮንቶስ 1-4 "'እርሱም ይህን ከሚያህል ሞት አዳነን፥ ያድነንማል፤ እናንተም ደግሞ ስለ እኛ እየጸለያችሁ አብራችሁ ስትረዱን፥ በብዙ ሰዎች በኩል ስለ ተሰጠን ስለ ጸጋ ስጦታ ብዙዎች ስለ እኛ ያመሰግኑ ዘንድ፥ ወደ ፊት ደግሞ እንዲያድን በእርሱ ተስፋ አድርገናል። ' 2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1:10-11" አድኖናል፤ ያድነናልም፤ ወደ ፊትም እንደሚያድነን ተስፋችን በእርሱ ላይ ጥለናል። አድኖናል ሐዋርያው ጳውሎስ ለጌታ ለኢየሱስ ህይወቱን በመስጠት መታወቂያው ከሆነው ከአሳዳጅነት ወደ ተሳዳጅነት ከተለወጠበት ጊዜ ጀምሮ በብዙ መከራ ውስጥ ያለፈ ሰው ነበር። በእስያ ገጥሞት ስለ ነበረው ከባድ ፈተና ሲጽፍም እንዲህ ብሎአል፦ “በሕይወት ለመኖር እንኳ ተስፋ እስከምንቈርጥ ድረስ ከዐቅማችን በላይ የሆነ ጽኑ መከራ ደርሶብን ነበር። በርግጥም የሞት ፍርድ እንደ ተፈረደብን ይሰማን ነበር፤” (2 ቆሮ. 1: 8፣ 9)። “እንዲህ ካለው የሞት አደጋ አድኖናል” በማለት ሲጽፍ እንዲህ ያለውን ከባድ ልምምድ በማስታወስ ነበር። ያድነናልም ጳውሎስ “አድኖናል” ብቻ በማለት ያለፈውን ታሪክ ዘግቦ አላቆመምም። ይልቁንም “ያድነናልም” በማለት ቀጥሎ በሚገጥመው ተመሳሳይ ከባድ መከራ ውስጥ የእግዚአብሔር እጅ ከማዳን እንደማታጥር አወጀ። በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 27 እና 28 ጳውሎስ በአገልግሎቱ መጨረሻ ወደ ሮም ያደረገውን ጉዞ ያስነብበናል። ይህ የመርከብ ጉዞ እጅግ አስቸጋሪ እና ከባህሩ ላይ ከገጠማቸው ወጀብ የተነሳ መርከባቸው የተሰባበረችበት፣ ጳውሎስም የሞት አደጋን እንደገና ፊት ለፊት የተጋፈጠበት ጊዜ ነበር። ይሁን እንጂ፣ “አድኖናል፣ ያድነንማል” ያለው ጌታ ከጎኑ ሆኖ አበረታው። መልአኩንም በመላክ እንዲህ አለው፦ “ጳውሎስ ሆይ፤ አትፍራ፤ በቄሳር ፊት መቆም ይገባሃል፤ ከአንተ ጋር የሚጓዙትንም ሰዎች ህይወት እግዚአብሔር አትርፎልሃል” (የሐዋ. 27:24)። ጳውሎስም ይህንን ቃል ይዞ በአምላኩ ላይ ተስፋውን በማድረግ በመርከቧ ላይ የተጨነቁትን ሁሉ እንዲህ በማለት አጽናናቸው፦ “ስለዚህ፣ እናንት ሰዎች ሆይ፤ አይዞአችሁ እርሱ እንደ ነገረኝ እንደዚያው እንደሚሆን በእግዚአብሔር አምናለሁና።” (ቁ. 25) ወደ ፊትም እንደሚያድነን ጳውሎስ “አድኖናል” እና “ያድነንማል” ካለ በኋላ ደግሞ “ወደ ፊትም እንደሚያድነን” በማለት ሲናገር ሞት ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚወገድበትን፣ የትንሳኤውን ማለዳ በማሰብ ነበር። በእርግጥም ከየትኛውም አይነት የሞት ሥጋት እግዚአብሔር በተለያየ ጊዜ ቢያድነንም እንኳን ተመልሰን መሞታችን አይቀርም። አልዓዛር ከሞተ ከሦስተኛ ቀን በኋላ በአስደናቂ ተአምር ቢነሳም ሟች ስጋ በመልበሱ ምክንያት እንደገና ሞቷል። ነገር ግን ጌታችን ኢየሱስ ሞትን ድል አድርጎ በመነሳት የሞትና የሲኦልን ቁልፍ በእጁ ስለያዘ በቅርብ ዳግም ሲመጣ “የመጨረሻው ጠላት” የተባለውን ሞት ወደ እሳት ባህር በመጣል በእርሱ ያመኑትን ሁሉ ከሞት ያስነሳቸዋል። ያን ጊዜ የሞት የቀብር ሥነ ሥርአት ይፈጸማል። ከዚያ በኋላ ሞት የሚባል ፈጽሞ አይኖርም። እንግዲያውስ ተስፋችንን ይህንን ማድረግ በሚችለው ላይ ስንጥል፣ ዛሬ የሚታወጁብን የሞት አዋጆች አያስደነግጡንም። ተስፋም አያስቆርጡንም። እርሱ አድኖናል፣ ያድነንማል፣ ወደ ፊትም ደግሞ እንደሚያድነን ተአማኒ የሆነ ተስፋ ሰጥቶናል። 🙏 ጸሎት: አባት ሆይ፣ ዛሬ ላይ መድረሳችን አንተ ስላዳንከን እንደሆነ እንድናስታውስ፣ አሁንም ለገጠመን ችግር የማዳን እጅህ ልትረዳን እንደ ተዘረጋችልን እንድናስብ እና ወደፊትም ተስፋችንን በአንተ ላይ እስካደረግን ድረስ ፍጻሜያችን ድል እንደሚሆን እንድናምን በጸጋህ እርዳን። አሜን! ──────────────── 📱 Ezra Seminary - Daily Devotional 🔗 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.ezraapp&pcampaignid=web_share
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи