tgindex
SABBATH SCHOOL (ሰንበት ትምህርት)

SABBATH SCHOOL (ሰንበት ትምህርት)

Статистика

@TekalignSorato +251913070430 Daily Spiritual & Religious Education. Live Q&A Sessions & Daily Training. YouTube Content & Livestreams!

Последний пост
15 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
9
Всего постов
26
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Видео
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
9 361
+25 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
2 387
20 постов
Вовлечённость
25,5%
к подписчикам
Постов в день
1,3
всего 26
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1 522
1/48двое суток
1 744
1/72трое суток
1 881

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • Live stream finished (1 hour)

  • Live stream started

  • 14 авг.1 624407

    ዓርብ ነሐሴ 8 Aug 14 ተጨማሪ ሀሳብ ኤለን ጂ ኋይት፣ “The Need of Love፣” ገጽ 545፣ 546፣ Re- view and Herald፣ ነሐሴ 28፣ 1888። “የሰውዬው ምስክርነት ምንም ያህል ከፍ ያለ ቢሆንም፣ ልቡ ለእግዚአብሔርና ለባልንጀራው በፍቅር ካልተሞላ እርሱ እውነተኛ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር አይደለም። ምንም እንኳ ታላቅ እምነት ቢኖረውና ተአምራትን የመሥራት ኃይል ቢኖረውም፣ ያለ ፍቅር ግን እምነቱ ከንቱ ነው። ታላቅ ለጋስነት ሊያሳይ ይችላል፤ ነገር ግን ከእውነተኛ ፍቅር ውጭ በሌላ ምክንያት ያለውን ሀብት ሁሉ ለድሆች ቢሰጥ፣ ያ ድርጊቱ በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስን አያስገኝለትም። በቅንዓቱ ምክንያት እስከ ሰማዕትነት ሞት ድረስ ሊደርስ ይችላል፤ ሆኖም በፍቅር ካልተገፋፋ፣ በእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ተታለለ ቀናተኛ ወይም እንደ ትዕቢተኛ ግብዝ ይቆጠራል።” — ኤለን ጂ ኋይት፣ የሐዋርያት ሥራ፣ ገጽ 318፣ 319። “የስብከት ብዛት አለን። ከሁሉ በላይ የሚፈለገው ግን... ለሚጠፉ ነፍሳት የሚሆን ፍቅር ነው፤ ይህም ከእግዚአብሔር ዙፋን በተትረፈረፈ ፈሳሽ የሚመጣው ፍቅር ነው። እውነተኛ ክርስቲያንነት ፍቅርን በመላው ማንነት ውስጥ ያስርጻል። እያንዳንዱን ወሳኝ ክፍል— አንጎልን፣ ልብን፣ ረዳት እጆችንና እግሮችን ይነካል፤ ይህም ሰዎች እግዚአብሔር እንዲቆሙ በሚፈልግበት ቦታ በጽናት እንዲቆሙ ያስችላቸዋል፤ በዚህም እግራቸው እንዳይሰናከልና አንካሳው ከመንገድ እንዳይወጣ ቀጥተኛ መንገድ ያደርጋሉ። ለሚጠፉ ነፍሳት የሚሆን የሚነድና የሚበላ የክርስቶስ ፍቅር፣ የመላው ክርስቲያንነት ሥርዓት ሕይወት ነው” (ኤለን ጂ ኋይት፣ Lift Him Up፣ ገጽ 134)። “መፈወስ የሚችለው ከክርስቶስ ልብ የሚፈሰው ፍቅር ብቻ ነው። የቆሰለችን ነፍስ ወደ ቀድሞ ሁኔታዋ ሊመልስ የሚችለው ያ ፍቅር ልክ በዛፍ ውስጥ እንደሚፈስ ፈሳሽ ወይም በሰውነት ውስጥ እንደሚዘዋወር ደም በእርሱ ውስጥ የሚፈስለት ሰው ብቻ ነው፡፡” (ኤለን ጂ ኋይት፣ ስነ ትምህርት፣ ገጽ 114)። የመወያያ ጥያቄዎች 1. ጳውሎስ የዘረዘራቸው በጎ የፍቅር ባሕርያት ሁሉንም ያካተቱ ይመስላችኋል? ካልሆነ፣ በዝርዝሩ ላይ ምን ሌሎች ነገሮችን ትጨምራላችሁ? 2. ጳውሎስ “ፍቅርን ተከታተሉ” (1ኛ ቆሮ. 14፡1) ሲል ምን ማለቱ ይመስላችኋል? ይህ በ1ኛ ቆሮንቶስ 13፡4–7 ላይ ከገለጸው ሐሳብ ጋር ምን ግንኙነት አለው? 3. በዕለት ተዕለት ሕይወታችሁ ውስጥ ይበልጥ በተግባር ላይ ማዋል የሚገባችሁ የፍቅር ባሕርይ የትኛው ነው? በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናችሁ ውስጥ ይበልጥ አስፈላጊ የሆኑትስ የትኞቹ ናቸው? ለመሆኑ ጳውሎስ ፍቅርን እንደ ትንቢት፣ ልሳን እና እውቀት ካሉ ስጦታዎች ጋር ለምን ያነጻጽረዋል (1ኛ ቆሮ. 13፡8)? 4. ጳውሎስ በቆሮንቶስ አባላት መካከል ላለው የአንድነት ማጣት ዋነኛው መፍትሔ ፍቅር እንደሆነ ይጠቁማል። ለምን? ይህ ዛሬ ለቤተ ክርስቲያናችን እንዴት ይሠራል? @SabbathSchool @TekalignSorato

  • 13 авг.1 686369

    ሐሙስ ነሐሴ 7 Aug 13 እምነት፣ ተስፋና ፍቅር እስካሁን ድረስ የሱስ እነዚህን ሁሉ በመሆኑ ፍቅር ታጋሽ፣ ቸር፣ ደስተኛ፣ ጽኑ፣ አማኝ፣ ተስፋ የሚያደርግ እና የሚጸና (ወይም የማይለወጥ) መሆኑን ተምረናል። እነዚህን ባሕርያት በየሱስ ውስጥ ካየን በኋላ፣ የሚቀጥለው እርምጃ እርሱን መምሰል ነው። ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች የነበረው ምኞትም ይህ ነበር። ሆኖም፣ በስምንቱ አሉታዊ የፍቅር ባሕርያት ውስጥ ያለውን “አይ” የሚለውን ቃል ብናስወግድ፣ “በቤተ ክርስቲያን ክበባቸው ውስጥ የነበረውን የቆሮንቶስ ሰዎችን ባሕርይ የሚያሳይ ጥሩ መግለጫ እናገኛለን፦ ቀናተኞች፣ ተመካሪዎች፣ ትዕቢተኞች፣ ባለጌዎች፣ የራሳቸውን ጥቅም ፈላጊዎች፣ ቶሎ የሚቆጡ እና ሌሎች ምን ስህተት እንደሠሩ የሚከታተሉ ነበሩ። ጳውሎስ እዚህ ጋ የተጠቀመባቸውን ግሶች ለቆሮንቶስ ሰዎች ሁኔታ እንዲመጥኑ አድርጎ ነው የቀረጸው።” — ቨርሊን ዲ. ቨርብሩግ፣ “1ኛ ቆሮንቶስ፣” “1 Corinthians,” in The Expositor’s Bible Commentary: Romans–Galatians, re- vised edition (Grand Rapids, MI: Zondervan, 2008)፣ ገጽ 372። የቆሮንቶስ ሰዎች ብዙ የሚማሩት ነገር ነበረ። እኛም እንዲሁ። ጳውሎስ ፍቅር ምን እንደሚያደርግና ምን እንደማያደርግ ከገለጸ በኋላ፣ እውነተኛ ፍቅርን በተግባር ለማዋል እንዲያነሳሳ የፍቅርን ዘላለማዊ ባሕርይ በማጉላት ክፍሉን ያጠቃልላል። አንድ ቀን ትንቢቶች አስፈላጊ መሆናቸው ያቆማል፤ የምንናገረውም አንድ ቋንቋ ብቻ ይሆናል፤ ጉድለት ያለበት የሰው ልጅ እውቀትም ቦታውን ለአዲስና ፍጹም ለሆነው ለእግዚአብሔር እውቀት ይለቃል (1ኛ ቆሮ. 13፡12)። የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች የሚቀሩት የተሰጡበት ዓላማ ግቡን ሲመታ ብቻ ነው (1ኛ ቆሮ. 13፡10)። “ፍቅር ግን ለዘላለም ይኖራል!” (1ኛ ቆሮ. 13፡8)። በተመሳሳይ መልኩ፣ ክርስቶስ ሲመለስ እምነት ቦታውን ለማየት (sight) ይለቃል (2ኛ ቆሮ. 5፡7)፤ ለረጅም ጊዜ ተስፋ ያደረግነውም ነገር እውን ይሆናል (ሮሜ 8፡24)። ከሁሉ በላይ ደግሞ፣ ፍቅር የአምላካችን የአብ፣ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ የባሕርይ መለያ ሆኖ ለዘላለም ይጸናል። ይሁን እንጂ እምነትና ተስፋም ለዘላለም የሚኖሩበት ሁኔታ አለ። እምነት እንደ ደኅንነት ተሞክሮ (ሮሜ 4፡3)፣ ተስፋ ደግሞ በአዲሲቱ ምድር ስለሚኖሩ አዳዲስ ደስታዎችና እውቀቶች እንዳለን ናፍቆትና ጥበቃ ሆኖ የዳኑትን ሰዎች ተሞክሮ ለዘላለም ያጅባል። ሆኖም ፍቅር፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፣ ለዘላለም ነግሦ ይኖራል። በጣም በቅርቡ ጌታችንን ፊት ለፊት እናየዋለን (1ኛ ቆሮ. 13፡12)። ያ ቀን እስኪመጣ ድረስ፣ ሕይወታችንን በእነዚህ ሦስት በጎ ባሕርያት ልንገልጽ ይገባል፦ እምነት፣ ተስፋ እና ፍቅር። ይህ ሦስትነት በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት የሚገኘውን የክርስቲያናዊ ሕይወት ሙላትን ይወክላል። በክርስቲያኖች መካከልም በተደጋጋሚ ይጠቀስ የነበረው ለዚህ ነው (ሮሜ 5፡1–5፤ ገላትያ 5፡ 5፣ 6፤ ኤፌሶን 1፡15፣ 18፤ 4፡1–5)። ሆኖም ፍቅር ከሁሉ ይበልጣል፤ ደግሞም የእግዚአብሔርን ማንነት ለመግለጽ ጥቅም ላይ የዋለ ብቸኛው በጎ ባሕርይ እርሱ ነው (1ኛ ዮሐ. 4፡8)። “እግዚአብሔር ፍቅር ነው” በሚለው አገላለጽ ላይ አሰላስሉ። የዚህን ቃል ትክክለኛ ትርጉም እንዴት ልንረዳው ይገባናል? ሐሳቡን በከፊል ብቻ መረዳት ብንችልም እንኳ፣ ይህ ሐረግ ለእኛ እንዲህ ያለ የምሥራች የሆነው ለምንድን ነው? @SabbathSchool @TekalignSorato

  • 12 авг.1 749376

    ረቡዕ ነሐሴ 6 Aug 12 የክርስቶስ ምስል በ1ኛ ቆሮንቶስ 13፡4–7 ላይ የተዘረዘሩትን ስንመለከት፣ እነዚህን ሁሉ የፍቅር ባሕርያት በተሟላ ሁኔታ ባለመግለጣችን በተወሰነ ደረጃ የተሸነፍን ሊመስለንና ተስፋ ሊያስቆርጠን ይችላል። ጳውሎስ 1ኛ ቆሮንቶስ 13ን ሲጽፍ ምናልባትም በአእምሮው የነበረው የየሱስ ማንነት ሳይሆን አይቀርም። በእርግጥም እነዚህን ሁሉ የፍቅር ባሕርያት ፍጹም በሆነ መንገድ የገለጠው ክርስቶስ ብቻ ነው። ስለዚህ፣ በመጨረሻው ትንታኔ፣ የጳውሎስ የፍቅር መግለጫ የየሱስ ሥዕል ነው። ዮሐንስ 13፡1፣ 34፤ ዮሐንስ 15፡9፣ 12፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡14፤ 2ኛ ጢሞቴዎስ 1፡7፣ 13፤ 1ኛ ዮሐንስ 3፡16፤ እና 1ኛ ዮሐንስ 4፡7–12፣ 19–21ን አንብቡ። ከእነዚህ ክፍሎች ስለ ፍቅር ምን እንማራለን? Save Notes እግዚአብሔር ፍቅር ነው (1ኛ ዮሐ. 4፡8)። እርሱ አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ እጅግ ወደደን (ዮሐንስ 3፡16)። የሱስ የዚህ ፍቅር ሙሉ መግለጫ ነው (ዕብ. 1፡3)። ፍቅር ራሱን እንዴት እንደሚገልጥ ማወቅ ከፈለግን፣ ወደ የሱስ ረዘም ያለ እይታ ማድረግ አለብን። በአዲስ ኪዳን ውስጥ ለተሳለው የየሱስ ሥዕል ትኩረት ከሰጠን፣ በ1ኛ ቆሮንቶስ 13 ላይ የተጠቀሱት ሁሉም በጎ የፍቅር ባሕርያት በእርሱ ውስጥ የታዩ መሆናቸውን እንረዳለን። • የሱስ ይታገሣል፦ “ነገር ግን የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት በእርሱ ለሚያምኑ ምሳሌ እንድሆን፣ ከሁሉ ይልቅ ኃጢአተኛ በምሆን በእኔ ላይ የሱስ ክርስቶስ የነበረውን ትዕግሥቱን [makrothymia] ሁሉ ያሳይ ዘንድ ስለዚህ ምሕረትን አገኘሁ” (1ኛ ጢሞ. 1፡16)። • የሱስ ቸር ነው፦ መጽሐፍ ቅዱስ “ጌታ ቸር [kind] መሆኑን” ይናገራል (1ኛ ጴጥ. 2፡ 3)። በዚህ ክፍል ውስጥ “ጌታ” የሚለው ቃል የሱስን ያመለክታል። “ቸር” የሚለው ቃል በ1ኛ ቆሮንቶስ 13፡4 ላይ “ቸርነት ያደርጋል” (chrēsteuomai) ከሚለው ግስ ጋር አንድ ዓይነት ሥርወ ቃል ካለው “ክሬስቶስ” (chrēstos) ከሚለው የግሪክ ቃል የተገኘ ነው። • የሱስ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል፦ የሱስ የአባቱን ፈቃድ ሲከተል እና የአባቱን ፍቅር ሲለማመድ ደስታን አግኝቷል (ዮሐንስ 15፡9–11፣ ዮሐንስ 17፡12–14)። • የሱስ ሁሉን ይታገሣል/ይጸናል፦ ዕብራውያን 12፡2፣ 3 የሱስ “መስቀሉን የታገሠ... በነፍሳችሁ ዝላችሁ እንዳትደክሙ፣ ከኃጢአተኞች በደረሰበት በእንዲህ ያለ ተቃውሞ የጸናውን አስቡ” ይላል። እንደ የሱስ ብዙ የታገሠ ማንም የለም (ፊልጵ. 2፡8)። ይህንንም ያደረገው በፊቱ ስላለው ደስታ ነው! • የሱስ ሁሉን ያምናል፦ ሐናንያ የጳውሎስን መለወጥ እውነተኛነት በተጠራጠረ ጊዜ (ሐዋ. 9፡13፣ 14)፣ የሱስ፦ “ይህ... ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና” ብሎ መለሰለት (ሐዋ. 9፡15)። የሱስ ሰዎችን የሚያያቸው ባሉበት ሁኔታ ሳይሆን፣ በእርሱ ኃይል ወደፊት በሚሆኑት ማንነት ነው። የሱስ እውነተኛ ፍቅር ምን እንደሆነ ለእኛ የሚገልጥባቸው ሌሎች መንገዶች የትኞቹ ናቸው? @SabbathSchool @TekalignSorato

  • 11 авг.1 71719

    ዛሬ Live ባለመኖሩ ይቅርታ እንጠይቃለን ዓርብ ማታ በኢትዮጵያ ስዓት 2:30 እንገናኝ ተባረኩ @SabbathSchool @TekalignSorato

  • 11 авг.2 093386

    ማክሰኞ ነሐሴ 5 Aug 11 ፍቅር የማያደርጋቸው ነገሮች 1ኛ ቆሮንቶስ 13፡4–7ን እንደገና አንብቡ። ጳውሎስ ስለ ፍቅር በጎ ባሕርያት ብቻ ከመጥቀስ ይልቅ፣ ፍቅር የሌለባቸውን አሉታዊ ባሕርያት ጭምር የጠቀሰው ለምንድን ነው? Save Notes ትላንት ፍቅር በሚያደርጋቸው ሰባት ነገሮች ላይ ትኩረት አድርገን ነበር፤ ዛሬ ደግሞ የማያደርጋቸውን ስምንት ነገሮች እንመለከታለን። ፍቅር፦ 1. አይቀናም (zeloō)፦ “ዜሉኦ” የሚለው ቃል እንደ “የሚበልጠውን ስጦታ በጽኑ ፈልጉ [zeloō]” (1ኛ ቆሮ. 12፡31)፣ “መንፈሳዊ ስጦታን በጽኑ ፈልጉ [zeloō]” (1ኛ ቆሮ. 14፡1) እና “ትንቢት ለመናገር በጽኑ ፈልጉ [zeloō]” (1ኛ ቆሮ. 14፡39) ባሉት ክፍሎች ውስጥ በአዎንታዊ መልኩ ሊሠራበት ይችላል። እዚህ ጋ ግን፣ በሐዋርያት ሥራ 7፡9 ላይ እንዳለው ሁሉ አሉታዊ ነው። መንፈሳዊ ስጦታዎችን መፈለግ መልካም ቢሆንም፣ ስጦታ ባላቸው ሰዎች ላይ መቅናት ግን ተገቢ አይደለም። ይህ መከፋፈልን ያመጣል (1ኛ ቆሮ. 3፡3)። 2. አይመካም (perpereuomai)፦ “ፔርፔሬውኦማይ” የሚለው ግስ የትዕቢትንና ከሌሎች ምስጋና የመፈለግን ሐሳብ ያስተላልፋል። ፍቅር ግን እንደዚያ በራስ ላይ ያተኮረ አይደለም። ይህ ደግሞ በሚቀጥሉት ነጥቦች ላይ ይበልጥ ግልጽ ይሆናል። 3. በትዕቢት አይነፋም (physioō)፦ “ፊሲኦ” የሚለው ግስ በ1ኛ ቆሮንቶስ 8፡1 ላይ ጳውሎስ፦ “እውቀት” በትዕቢት ይነፋል፣ ፍቅር ግን ያንጻል” በሚለው አስደናቂ አገላለጹ ውስጥ ይገኛል። ይህ በገዛ ራሱ አስፈላጊነት የተወጠረን ሰው ያመለክታል። 4. የማይገባውን አያደርግም/ጨዋነት የጎደለው ባሕርይ አያሳይም (aschēmo- neo)፦ “አስኬሞኔኦ” የሚለው ግስ ሰፊ የትርጉም ክልል ሊኖረው ይችላል። በአጠቃላይ ግን፣ ከማኅበራዊና ከሥነ-ምግባር ደንቦች ውጭ በሆነ፣ ክብር በሌለው፣ አሳፋሪ፣ ነውረኛ ወይም ተገቢ ባልሆነ መንገድ መንቀሳቀስ ማለት ነው። ምናልባትም ጳውሎስ እያመለከተ ያለው በቆሮንቶስ የነበሩት “ጠንካራ” ወገኖች በ”ደካማ” አባላት ላይ ያሳዩት የነበረውን ትዕቢትና ሻካራ ባሕርይ ሊሆን ይችላል (1ኛ ቆሮ. 4፡10፣ 1ኛ ቆሮንቶስ 8)። 5. የራሱን [መብት] አይፈልግም (zēteo)፦ ይህ ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮንቶስ 10፡24 ላይ፦ “እያንዳንዱ ለባልንጀራው የሚጠቅመውን እንጂ ማንም የራሱን አይፈልግ” ካለው ጋር ተመሳሳይ ነው። ፍቅር ስለ ሌሎች ሲል የገዛ መብቱን ይተዋል (5ኛ ትምህርትን ይመልከቱ)። እያንዳንዱ ሰው የሌላውን መብት በሚያስከብርበት ሁኔታ ውስጥ ሁሉም ተጠቃሚ ይሆናሉ። 6. አይበሳጭም (paroxynō)፦ “ፓሮክሲኖ” የሚለው ግስ ለአንድ ሰው ለቁጣ መቸኮልን የሚያመለክት የውስጥ መነሳሳትን ያሳያል። ይህ ማለት ፍቅር ግልፍተኛ ወይም ቶሎ የሚቀየም አይደለም ማለት ነው። 7. ክፉን አይቆጥርም (logizomai)፦ “ሎጊዞማይ” የሚለው ግስ እዚህ ጋ የሂሳብ አያያዝ ስሜት አለው፤ ይህም ማለት ፍቅር የሰውን በደል በዝርዝር መዝግቦ አይይዝም ማለት ነው። በሌላ አነጋገር፣ ፍቅር ማለት ይቅር ማለትም ጭምር ነው። 8. በዓመፅ ደስ አይለውም (chairō)፦ ፍቅር የሌላውን ሰው በደል መዝግቦ የማይይዝ ብቻ ሳይሆን፣ በበደሉም ደስ አይሰኝም። ሌሎችን በእውነት ስንወድ በስህተታቸው አንደሰትም፤ ይልቁንም እነርሱን ለመርዳት እንጥራለን። ከእነዚህ ከላይ ከተጠቀሱት አሉታዊ ባሕርያት መካከል እናንተን ይበልጥ የሚፈታተኗችሁ የትኞቹ ናቸው? በክርስቶስ ኃይል እነዚህን እንዴት ማሸነፍ ትችላላችሁ? @SabbathSchool @TekalignSorato

  • 10 авг.2 108466

    ሰኞ ነሐሴ 4 Aug 10 ፍቅር የሚያደርጋቸው ተግባራት 1ኛ ቆሮንቶስ 13፡4–7 የዚህ ምዕራፍ እምብርት ነው። ጳውሎስ ትኩረት የሚያደርገው በፍቅር ባሕርያት ላይ ነው፤ ፍቅር ምን እንደሆነና ምን እንዳልሆነ፣ ወይም ፍቅር ምን እንደሚያደርግና ምን እንደማያደርግ ያሳያል። በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ ፍቅር ያለው ሰው እንዴት እንደሚመላለስ ፍንጭ ይሰጠን ዘንድ ፍቅርን እንደ ሰው አድርጎ ይስለዋል። ጳውሎስ ፍቅርን በሚገልጽበት ጊዜ ተከታታይ ግሶችን ይጠቀማል። ለእርሱ ፍቅር ከስሜት ይልቅ ከተግባር ጋር የተያያዘ ነው። ታዲያ ፍቅር ምን ያደርጋል? 1. ይታገሣል (makrothymeō)፦ “ማክሮቲሜኦ” ማለት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢኖሩም እንኳ ትዕግሥትን ማሳየት ማለት ነው። ትዕግሥት ደግሞ እርስ በርስ የመቻቻልን ችሎታ ያጎላል (ኤፌ. 4፡2)። 2. ቸርነት ያደርጋል (chrēsteuomai)፦ “ክሬስቴዎማይ” የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን ውስጥ እዚህ ቦታ ላይ ብቻ ነው የሚገኘው፤ ነገር ግን ከዚሁ ሥርወ ቃል የወጡ ሌሎች ቃላት በሌሎች ቦታዎች በስፋት ይገኛሉ። በብሉይ ኪዳን የግሪክ ትርጉም (Septuagint)፣ ከዚህ ሥር የተገኙ ቃላት በመዝሙር መጽሐፍ ውስጥ ከእግዚአብሔር ምሕረት ጋር የተያያዘውን የእግዚአብሔርን ቸርነት ለመግለጽ በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ ውለዋል (መዝ. 145፡9)። ጳውሎስ ፍቅር ቸርነት ያደርጋል ሲል፣ አንድ ሰው ለሌሎች ያለው ፍቅር እግዚአብሔር ለእኛ ያሳየውን ርኅራኄና ምሕረት መምሰል አለበት ማለቱ ነው። 3. ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል (synchairō)፦ “ሲንካይሮ” ከአንድ ሰው ጋር አብሮ ደስ የመሰኘትን ችሎታ ያመለክታል (ሉቃስ 1፡58፤ ሉቃስ 15፡6፣ 9፤ 1ኛ ቆሮ. 12፡26፤ ፊልጵ. 2፡17፣ 18)። 4. ሁሉን ይታገሣል/ይሸፍናል (stegō)፦ “ስቴጎ” ማለት “መሸፈን” ይኸውም አንድን ነገር በሚስጥር መያዝ (ይህም ጥበቃ የማድረግ ስሜት አለው) ማለት ነው ወይስ “መጽናት” በሚል የጥንካሬ ስሜት በሚለው ላይ ምሁራን ይከራከራሉ። የመጽናት ጽንሰ-ሐሳብ በ1ኛ ቆሮንቶስ 9፡12 ላይ በግልጽ ስለሚታይ፣ አብዛኞቹ ተርጓሚዎችና የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን ሁለተኛውን አማራጭ ይበልጥ ተመራጭ ያደርጉታል። 5. ሁሉን ያምናል (pisteuō)፦ “ፒስቴዎ” የሚለው ቃል “እምነት” (pistis) ከሚለው የግሪክ ቃል ጋር አንድ ዓይነት ሥርወ ቃል አለው። በ1ኛ ቆሮንቶስ 13 አውድ ውስጥ፣ ሁሉን ማመን ማለት ለሌሎች በጎ ግምት መስጠት ማለት ነው። 6. ሁሉን ተስፋ ያደርጋል (elpizō)፦ በአዲስ ኪዳን “ኤልፒዞ” የሚለው ግስ ሁልጊዜም አንድ መልካም ነገር እንደሚከሰት ማመንን ወይም መጠበቅን ያመለክታል። 7. በሁሉ ይጸናል (hypomenō)፦ በ1ኛ ቆሮንቶስ 13፡7 ላይ “ስቴጎ” እና “ሂፖሜኖ” በሚሉት ግሶች መካከል ልዩነት የለም ሊባል ይችላል። ሁለቱም ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆን፣ እዚህ ጋ በመከራ ውስጥ መጽናትን ያመለክታሉ። ጳውሎስ “ስቴጎ” የሚለውን ቃል ላለመድገም በቁጥሩ መጨረሻ ላይ “ሂፖሜኖ”ን ተጠቅሟል። ተመሳሳይ ሐሳብን በተለየ ቃል በመድገም፣ ማመንንና ተስፋ ማድረግን እንደ ማዕከላዊ ነጥብ ትኩረት እንዲሰጣቸው ያደርጋል። በሌላ አነጋገር፣ ፍቅር በመታመንና በተስፋ ይጸናል። 1ኛ ቆሮንቶስ 13፡4–7ን ከገላትያ 5፡22፣ 23 ጋር አነጻጽሩ። በሁለቱ ክፍሎች መካከል ምን ዓይነት የሚያመሳስሉ ሐሳቦችን ያያሉ? ይህንን የፍቅር ዓይነት በራሳችን ሕይወት እንዴት ልንገልጠው እንችላለን? @SabbathSchool @TekalignSorato

  • 9 авг.2 257379

    እሑድ ነሐሴ 3 Aug 9 የፍቅር መሠረታዊነት ባለፈው ሳምንት በ1ኛ ቆሮንቶስ 13 ላይ እንደሚታየው ስለ ፍቅር ጭብጥ ጥቂት ዳስሰናል። አሁን የጳውሎስን ቃላት እዚህ ጋ ይበልጥ በጥልቀት መመርመር ያስፈልገናል። 1ኛ ቆሮንቶስ 13ን አንብቡ። ስለ ፍቅር እየነገረን ያለውን ሐሳብ በአጭሩ አጠቃልሉ። Save Notes ጳውሎስ በአዲስ ቋንቋ መናገር (1ኛ ቆሮ. 13፡1)፣ ትንቢት፣ ማስተዋል፣ እውቀት፣ እምነት (1ኛ ቆሮ. 13፡2) እና ምጽዋት (1ኛ ቆሮ. 13፡3) ዋጋ የሌላቸው ናቸው ማለቱ አይደለም። እነዚህ ነገሮች ዋጋ ቢስ የሚሆኑት በፍቅር ካልተመሩ ብቻ ነው። ጳውሎስ እየተናገረ ያለው የፍቅር ዓይነት እንደ “እንጆሪ እወዳለሁ” ወይም “ጓደኞቼን እወዳለሁ” ወይም ደግሞ “ባለቤቴንና ልጆቼን እወዳለሁ” እንደሚባለው ዓይነት አገላለጽ አይደለም። እንዲሁም በፊልሞች ላይ እንደሚታየው ዓይነት ፍቅር አይደለም። ምንም እንኳ ይህ ክፍል በሰርግ ስብከቶች ላይ በብዛት ጥቅም ላይ ቢውልም፣ ስለ ወሲባዊ ፍቅር እየተናገረ አይደለም። ይህ ፍቅር በስሜታዊነት፣ በቸርነት፣ በበጎነት ወይም በምጽዋት ብቻ ሊገደብ አይችልም። ሆኖም እነዚህ ሁሉ በተለያየ ደረጃ ይወክሉታል። ይህ ፍቅር በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ለእኛ የተሰጠ ልዩ ጸጋ ነው። በእርግጥም በ1ኛ ቆሮንቶስ 13 ላይ ያለው ፍቅር በስሜት፣ በቸርነት፣ በበጎነት እና በምጽዋት እንድንሠራ የሚገፋፋን በመንፈስ ቅዱስ የሚሰጥ መነሻ ኃይል ነው። ይህም ለክርስቶስ እና ለባልንጀሮቻችን የምናሳየው የተግባራችን፣ የስሜታችን እና የአስተሳሰባችን ሙሉ ቁርጠኝነት ነው። ማቴዎስ 24፡12ን አንብቡ። የሱስ እዚህ ጋ ምን ዓይነት ማስጠንቀቂያ ይሰጠናል? Save Notes “አጋፔ” (agapē) እንዲህ አስፈላጊና መሠረታዊ የሆነው ለዚህ ነው። በክርስቶስ ኃይል፣ በቤቶቻችን፣ በቤተ ክርስቲያኖቻችን እና በአካባቢያችን ፍቅር እንዲቀዘቅዝ መፍቀድ የለብንም። ለእኛ ሲል በመስቀል ላይ የሞተልን የክርስቶስ ምሳሌ አለን። ከዚህ የላቀና ይበልጥ ኃይለኛ የሆነ የዚህ ዓይነት ፍቅር መግለጫ ምን ሊኖር ይችላል? እርግጥ ነው፣ ያንን ዓይነት ፍቅር እኩል መግለጽ ባንችልም፣ በእግዚአብሔር ጸጋ በምንችለው መጠን በገዛ ሕይወታችን ለመግለጥ መጋደል አለብን። ይህንን ፍቅር ከምንም በላይ ለሚፈልግ ሰው፣ እንዲህ ዓይነቱን የፍቅር መግለጫ ማሳየት እጅግ ጠቃሚና አዎንታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር የሚችልባቸው አንዳንድ አጋጣሚዎች የትኞቹ ናቸው? @SabbathSchool @TekalignSorato

  • 8 авг.2 326438

    ነሐሴ 2 - 8 7ኛ ትምህርት Aug 8 - 14 የፍቅር ምሥል ሰንበት ከሰዓት በኋላ ለዚህ ሳምንት እንዚህን ክፍሎች አንብቡ፦ 1ኛ ቆሮንቶስ 13፤ ማቴዎስ 24፡12፤ ገላትያ 5፡22፣ 23፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡14፤ 1ኛ ዮሐንስ 4፡8። የመታሰቢያ ጥቅስ፡ «እንዲሁም እምነት፣ ተስፋ፣ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው» (1ኛ ቆሮንቶስ 13፡13)። ፍቅር ሁሉንም ነገር ማሸነፍ ይችላል። ጳውሎስ ስለ ፍቅር ብዙ የተናገረው ለዚህ ነው። በአዲስ ኪዳን ውስጥ የፍቅርን ጽንሰ-ሐሳብ ለመግለጽ በብዛት ጥቅም ላይ የዋለው “አጋፓኦ” (agapaō) የተሰኘው የግሪክ ቃል በጳውሎስ ደብዳቤዎች ውስጥ ከ135 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል። ይህም በአጠቃላይ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ከተጠቀሰው ግማሽ ያህሉን ይወክላል። ይህ ሁኔታ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን በጻፈው ደብዳቤ ውስጥ ስላለው ማዕከላዊ ጭብጥ አንድ ነገር ሊነግረን ይገባል። በአዲስ ኪዳን ውስጥ ስለ ፍቅር የሚናገሩ ብዙ አስደናቂ ክፍሎች አሉ—ለምሳሌ ሮሜ 8፡35–39፣ 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡9፣ 1ኛ ቆሮንቶስ 8፡3፣ ገላትያ 2፡20፣ ቆላስይስ 1፡13፣ 1ኛ ተሰሎንቄ 3፡12 እና ሌሎችም። ሆኖም ከ1ኛ ቆሮንቶስ 13 ጋር የሚወዳደር ምንም ነገር የለም። ባለፈው ሳምንት፣ ያለ ፍቅር ሁሉም ነገር፣ መንፈሳዊ ስጦታዎች እንኳ ሳይቀሩ ዋጋ ቢስ መሆናቸውን አይተናል። በዚህ ሳምንት ደግሞ፣ 1ኛ ቆሮንቶስ 13ን እና በውስጡ ያለውን አስደናቂ የፍቅር ስዕል በጥልቀት እንመለከታለን። በምናየው መሠረት፣ ፍቅር ከስሜት ይልቅ አመለካከት ነው፤ ይህም አመለካከት በሕይወት፣ በተግባር እና በቃል መገለጥ አለበት፤ አለበለዚያ ትርጉም አይኖረውም። ፍቅር በእውነት ምን እንደሆነና ምን እንደሚያደርግ በየሱስ ሕይወት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተገልጧል።  @SabbathSchool @TekalignSorato

  • 7 авг.2 729182

    видео или голосовое, без подписи

  • Live stream finished (2 hours)

  • 7 авг.2 997161

    ኑ የእግዚአብሔርን ቃል አብረን እናጥና @SabbathSchool @TekalignSorato

  • 7 авг.3 04166

    https://t.me/sabbathschool?livestream=839ef045062856362d

  • Live stream started

  • 7 авг.3 120198

    ዓርብ ነሐሴ 1 Aug 7 ተጨማሪ ሀሳብ ሮዝዌል ኤፍ. ኮትሬል፣ “መንፈሳዊ ስጦታዎች”፣ ገጽ 5–16፤ ኤለን ጂ ኋይት፣ Spiritual Gifts፣ ቅጽ 1። “ሰዎች በጌታ በመታመን ወደ ሥራ ይውጡ፤ እርሱም ነፍሳትን በመውቀስና ወደ ንስሐ በማምጣት ከእነርሱ ጋር ይሄዳል። አንዱ ሠራተኛ አንደበተ ርቱዕ ተናጋሪ፣ ሌላው ፈጣን ጸሐፊ፣ ሌላው ደግሞ ከልብ የመነጨ፣ ጥልቅና ትጋት የተሞላበት የጸሎት ስጦታ ያለው፣ ሌላው ደግሞ የዝማሬ ስጦታ ያለው ሊሆን ይችላል። ሌላው ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃል በግልጽ የመተርጎም ልዩ ኃይል ሊኖረው ይችላል። እግዚአብሔር ከሠራተኛው ጋር አብሮ ስለሚሠራ፣ እያንዳንዱ ስጦታ ለእግዚአብሔር ታላቅ ኃይል ይሆናል። ለአንዱ እግዚአብሔር የጥበብን ቃል ይሰጣል፣ ለሌላው እውቀትን፣ ለሌላው ደግሞ እምነትን ይሰጣል። ነገር ግን ሁሉም በአንዱ ራስ ሥር መሥራት አለባቸው። የስጦታዎች ልዩነት ወደ ልዩ ልዩ አሠራር ይመራል፤ “ሁሉን በሁሉ የሚያደርግ ግን ያው አምላክ ነው” (1ኛ ቆሮ. 12፡6)። “ማንም ሰው ያነሱ ናቸው ተብለው የታሰቡትን ስጦታዎች አይናቅ። ሁሉም ወደ ሥራ ይውጡ። ትልቅ ሥራ መሥራት እንደማይችል በማሰብ ማንም እጆቹን በአለማመን አጣጥፎ አይቀመጥ። ወደ ራስህ መመልከትን ትተህ ወደ መሪህ ተመልከት። በየዋህነት፣ በቅንነትና በፍቅር የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ።” — ኤለን ጂ ኋይት፣ The Advent Review and Sabbath Herald, April 12, 1906። “እያንዳንዳችን ከሌሎች አእምሮ የምናገኘው እርዳታ ያስፈልገናል። እግዚአብሔር ከእኛ ውጭ ባሉ ሌሎች አእምሮዎች ውስጥ ይሠራል። ለተለያዩ ሰዎች የተሰጡ ልዩ ልዩ ስጦታዎች “ቅዱሳን ለአገልግሎት ሥራ እንዲዘጋጁና የክርስቶስ አካል እንዲታነጽ” (ኤፌ. 4፡12) እርስ በርሳቸው መዋሃድ አለባቸው.... “ሁልጊዜም ከፊታችን እንቅፋቶች ይኖራሉ፤ እኛ ግን መሪያችንን መከተልና ችግሮቻችንን እጅ ለእጅ ተያይዘን በአንድነት መጋፈጥ አለብን።” — ኤለን ጂ ኋይት፣ The Upward Look፣ ገጽ 141። የመወያያ ጥያቄዎች 1. ስለ ትንቢት ስጦታ ጥቂት ተጨማሪ ነገሮችን አስቡ። በአዲስ ቋንቋ የሚነገሩ ነገሮች ካልተተረጎሙ በስተቀር፣ ትንቢት ከእነርሱ ይልቅ ይበልጥ አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድን ነው? አስፈላጊ ሆኖ ካገኛችሁት፣ የጳውሎስን መከራከሪያዎች ለመከለስ 1ኛ ቆሮንቶስ 14ን እንደገና አንብቡ። 2. በውይይት ቡድናችሁ ውስጥ ስለ ኤለን ጂ ኋይት ሕይወትና አገልግሎት፣ እንዲሁም እኛ እንደ ቤተ ክርስቲያን በእርሷ ላይ የትንቢት ስጦታ በእውነት መገለጡን ለምን እንደምናምን ተወያዩ። ከዚህ ስጦታ የተነሳ ለቤተ ክርስቲያን የመጡት ታላላቅ በረከቶች ምንድን ናቸው? እንዲሁም ይህን ስጦታ በተሻለ ሁኔታ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ለማወቅ የሚገጥሙት ፈተናዎች ምንድን ናቸው? 3. በእውነት የሚወዷችሁን ከሦስት እስከ አምስት የሚሆኑ ሰዎችን አስቡ። ለእነርሱ ያላችሁ ፍቅር እውነተኛ መሆኑን እንዴት ታውቃላችሁ? ይህስ ጳውሎስ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች በሚያደርገው ውይይት ውስጥ ስለ ፍቅር ለምን ያህል በስፋት እንደተናገረ ምን ያስረዳችኋል? 4. ምንም ያህል ፍቅር አስፈላጊ ቢሆንም፣ አንድ ሰው እውነትን እየተናገረ መሆን አለመሆኑና ሊደመጥ የሚገባው መሆኑን ለመወሰን ፍቅር ብቸኛው መመዘኛ መሆን የሌለበት ለምንድን ነው? @SabbathSchool @TekalignSorato

  • 6 авг.2 719259

    ሐሙስ ሐምሌ 30 Aug 6 የትንቢት ስጦታ የትንቢት ስጦታ ጳውሎስ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች በሚያደርገው ውይይት ውስጥ ትልቅ ቦታ ይይዛል። የሚገርመው፣ የትንቢት ስጦታ አብዛኛውን ጊዜ በአዲስ ቋንቋ ከመናገር ስጦታ በፊት ይጠቀሳል (1ኛ ቆሮ. 12፡10፣ 28፤ 1ኛ ቆሮ. 13፡8)። በአዲስ ቋንቋ የመናገር ስጦታ አስቀድሞ በሚጠቀስበት ጊዜም ቢሆን፣ ይህ የሚደረገው ከትንቢት ስጦታ ጋር ሲነጻጸር ያለውን አነስተኛ ጠቀሜታ ለማጉላት ብቻ ነው (1ኛ ቆሮ. 14፡4፣ 5፣ 6፣ 22)። ኤፌሶን 4፡11–13 እና 1ኛ ቆሮንቶስ 14፡3፣ 4ን አንብቡ። እነዚህ ክፍሎች በአጠቃላይ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ዓላማ፣ በተለይም ደግሞ ስለ ትንቢት ስጦታ ምን ይላሉ? Save Notes የትንቢት ስጦታ የታለመው ለማነጽ፣ ለመምከርና ለማጽናናት ነው (1ኛ ቆሮ. 14፡ 3፤ ከሐዋርያት ሥራ 15፡32 ጋር ያነጻጽሩ)። ይህም ትንቢት ስለ ወደፊቱ ጊዜ አስቀድሞ ከመናገር ይልቅ በአሁኑ ጊዜ እንዴት መኖር እንዳለብን የሚያመላክት መሆኑን ይጠቁማል። “ፕሮፌቴውኦ” (prophēteuō) የሚለው የግሪክ ግስ “አንድን ነገር አስቀድሞ መናገር” ወይም “በሌላ ሰው ስም አንድን ነገር መናገር” የሚሉ ትርጉሞች ሊኖሩት ይችላሉ። ለምሳሌ የመጀመሪያው ትርጉም በሐዋርያት ሥራ 2፡29–31 ላይ ይታያል (ከአሞጽ 3፡7 ጋር ያነጻጽሩ)፤ እዚያም ዳዊት ነቢይ መሆኑ “አስቀድሞ በማየት” ተብራርቷል። ሁለተኛው ትርጉም ደግሞ ይሁዳና ሲላስ ነቢያት ተብለው በተጠቀሱበት በሐዋርያት ሥራ 15፡32 ላይ ይታያል። ይሁን እንጂ የእነርሱ “ትንቢት” ያተኮረው ወንድሞችን “በብዙ ቃል መክረውና አጽንተው” በሚለው ላይ ነበር። ከኤፌሶን 4፡11–13 እንደምንረዳው፣ መንፈሳዊ ስጦታዎች በሐዋርያት ዘመን አላበቁም። እስከ መጨረሻው ድረስ ሊቀጥሉ ይገባል (ሐዋ. 2፡39)። ይሁን እንጂ አንድ ሰው ነቢይ ነኝ ብሎ ቢነሳ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት መመዘን አለበት። በጠቅላላው አራት ደንቦች መሟላት አለባቸው። አንደኛ፣ ትንቢቶቹ ይፈጸማሉ (ዘዳ. 18፡22፤ ኤር. 28፡8፣ 9)። ሁለተኛ፣ መልእክቱ ቀደምት ነቢያት ካስተላለፉት መልእክት ጋር ይስማማል (ዘዳ. 13፡1–3፤ ኢሳ. 8፡ 20)። ሦስተኛ፣ የዕለት ተዕለት ሕይወቱ ለክርስቶስ ያለውን ታማኝነት ያሳያል (1ኛ ዮሐ. 4፡ 1–3)። አራተኛ፣ የሱስ ሐሰተኛ ነቢያት በፍሬያቸው እንደሚታወቁ የተናገረውን የሚመለከት ነው (ማቴ. 7፡15–20)። ይህም ለእውነተኛ ነቢያትም ይሠራል። የዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ የትንቢት ስጦታ የቅሬታዋ ቤተ ክርስቲያን መለያ ባሕርይ መሆኑን ያመለክታል (ራእይ 12፡17፤ ራእይ 19፡10)። እኛ እንደ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች፣ የትንቢት ስጦታ ለኤለን ጂ ኋይት እንደተሰጣትና በጽሑፎቿም ውስጥ እንደሚንጸባረቅ እናምናለን። በኤለን ጂ ኋይት የትንቢት ስጦታ እንድናምን የሚያደርጉን ምክንያቶች ምንድን ናቸው? ስለ እርሷ ሚና እና ሥልጣን ምን ዓይነት ጥያቄዎች ይነሳሉ? @SabbathSchool @TekalignSorato

  • 5 авг.2 6372911

    ረቡዕ ሐምሌ 29 Aug 5 በአዲስ ቋንቋ የመናገር ስጦታ በአዲስ ቋንቋ የመናገር ስጦታ ጉዳይስ ምንድን ነው? ይህ ስጦታ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሌሎች ቦታዎች ከተገለጠበት ሁኔታ ጋር በሚስማማ መልኩ (ማርቆስ 16፡17፤ ሐዋርያት ሥራ 2፡1–13፤ ሐዋርያት ሥራ 10፡44–48፤ ሐዋርያት ሥራ 19፡6)፣ በ1ኛ ቆሮንቶስ ላይ የተጠቀሰው በአዲስ ቋንቋ የመናገር ስጦታ በአብላጫው በመንፈስ ቅዱስ ረዳትነት በባዕድ ቋንቋዎች የመናገር ችሎታ ሊሆን ይችላል። ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮንቶስ 12፡8–10 ባለው የስጦታዎች ዝርዝር ውስጥ በአዲስ ቋንቋ የመናገር ስጦታን ይጠቅሳል (1ኛ ቆሮ. 12፡28፣ 30፤ 1ኛ ቆሮ. 13፡1፣ 8ን ይመልከቱ)። ሆኖም በ1ኛ ቆሮንቶስ 14 ላይ ደጋግሞ ይጠቅሰዋል። እንዲያውም “ግሎሳ” (glōssa - “ልሳን/ ቋንቋ”) የሚለው የግሪክ ቃል በ1ኛ ቆሮንቶስ 12–14 ውስጥ ከሃያ ጊዜ በላይ የታየ ሲሆን፣ አሥራ አምስት ጊዜ የተጠቀሰው በ1ኛ ቆሮንቶስ 14 ላይ ብቻ ነው። ከነዚህም በተጨማሪ “ሄቴሮግሎሶስ” (heteroglōssos - “ሌላ ልሳን”) የሚለው የግሪክ ቃል በ1ኛ ቆሮንቶስ 14፡21 ላይ ተገኝቷል። በአዲስ ቋንቋ የመናገር ስጦታ እንዲህ በብዛት መጠቀሱ፣ ጉዳዩ ለጳውሎስ ልዩ ትኩረት የሚሻ መሆኑን ያሳያል። በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የዚህ ስጦታ ያለ አግባብና ከልክ በላይ ጥቅም ላይ መዋል፣ በሕዝባዊ አምልኮ ላይ ሥርዓት አልበኝነትንና ግራ መጋባትን ፈጥሮ ነበር (1ኛ ቆሮ. 14፡23፣ 27፣ 33፣ 40)። 1ኛ ቆሮንቶስ 14፡5፣ 13፣ 26፣ 27 እና 1ኛ ቆሮንቶስ 12፡10፣ 30ን አንብቡ። ጳውሎስ በአዲስ ቋንቋ የመናገር ስጦታን በተመለከተ ምን ዓይነት ልዩ መመሪያ ሰጠ? Save Notes በአዲስ ቋንቋ የመናገር ስጦታ ቋንቋውን ከመተርጎም ስጦታ ጋር አብሮ መሄድ ያለበት ምክንያት፣ የሚነገሩት ቋንቋዎች ሊስተዋሉ የሚችሉ መሆን ስላለባቸው ነው (1ኛ ቆሮ. 14፡9)፤ አለበለዚያ ስጦታውን መጠቀም ምንም ጥቅም አይኖረውም (1ኛ ቆሮ. 14፡6)። ይህም ጳውሎስ በትርጓሜና በማስተዋል ላይ ለምን ያን ያህል አፅንዖት እንደሰጠ ያብራራል። እርሱ እየነቀፈ ያለው በአዲስ ቋንቋ የመናገር ስጦታን ሳይሆን፣ ነገ በምናየው መሠረት የቆሮንቶስ ሰዎች ለዚህ ስጦታ የሰጡትን ከልክ ያለፈ ቦታን ነው፤ ይህም የትንቢት ስጦታ እንዲዘነጋ አድርጎ ነበር። በዚህ ነጥብ ላይ፣ ጳውሎስ የቆሮንቶስ ሰዎች ሁሉ በባዕድ ቋንቋዎች እንዲናገሩ ቢመኝም (1ኛ ቆሮ. 14፡5)፣ ይህ እንዲሆን ግን አልጠበቀም (1ኛ ቆሮ. 12፡10)። ስለዚህ “በመንፈስ ቅዱስ ተጠምቀናል ለማለት ሁሉም በልሳን መናገር አለባቸው የሚለው አሳብ፣ በ1ኛ ቆሮንቶስ 12 እና 14 ላይ ያለውን የጳውሎስን ትምህርት ማጣመም ነው።” Raoul Dederen, Handbook of Sev- enth-day Adventist Theology, electronic ed., vol. 12 of Commentary Reference Se- ries (Hagerstown, MD: Review and Herald Publishing Association, 2001), p. 620። በቤተ ክርስቲያናችሁ ውስጥ ሌሎች ቋንቋዎችን የሚናገሩ ሰዎች አሉ? ሌሎች ሰዎችን ወደ ክርስቶስ ለማምጣት ይህን ችሎታቸውን እንዴት ሊጠቀሙበት ይችላሉ? ይህ እውነታ ጳውሎስ ስለሚያብራራው በአዲስ ቋንቋ የመናገር ስጦታ እውነተኛ ባሕርይ ለመረዳት እንዴት ይረዳናል? @SabbathSchool @TekalignSorato

  • Live stream finished (1 hour)

SABBATH SCHOOL (ሰንበት ትምህርት) — tgindex