Adventist information አድቬንቲስት መረጃ
Статистикаሰላም ለሁላችሁም! የዚህ ቻናል አላማው ለ7ተኛ ቀን አድቬንቲስት አባላት ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ሰው የሚሆን መንፈሳዊ መልዕክቶችን ማካፈል። የ7ተኛ ቀን አድቬንቲስት አለም አቀፋዊ እና ሀገር አቀፋዊ መረጃዎችን እንዲሁም ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎች ከታማኝ ምንጮች በማረጋገጥ ማድረስ ነው። የቻናሉ መቀላቀያ @AdventistEthio ለጥያቄ እና ለጥቆማ @metagesy 0923943365
- Последний пост
- 11 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 10
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 225
- 1/48двое суток
- 257
- 1/72трое суток
- 278
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
የምሥራቃዊ ኢትዮጵያ ዩኒየን ዓመታዊ ካምፖሪ በሀዋሳ ከተማ በደመቀ ሁኔታ በመካሄድ ላይ ይገኛል! «ጌታ ሆይ ተናገር!» በሚል አነቃቂ መሪ ቃል በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ያለው የምሥራቃዊ ኢትዮጵያ ዩኒየን ዓመታዊ የፓዝፋይንደር (Pathfinder) ካምፖሪ በርካታ መንፈሳዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎችን በማቀናጀት በታላቅ ድምቀት ቀጥሏል። የመርሐ ግብሩ ዋና ዋና ሁነቶች፦ አለምአቀፍ የልምድ ልውውጥና ስልጠና፦ ከውጭ ሀገር የመጡ ከ30 በላይ የAngaza West (AGW) Pathfinder Drum Corps የቡድን አባላት በሀዋሳ አድቬንቲስት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ለካምፖሪው የልምድ ልውውጥ ስልጠና እየሰጡ ይገኛሉ። የደም ልገሳ መርሐ ግብር፦ የወጣቶችን የማህበረሰብ አገልግሎት ፍቅር በሚያሳይ መልኩ በካምፖሪው ግቢ ውስጥ የበጎ ፈቃድ የደም ልገሳ ስራ ተከናውኗል። የጎዳና ላይ የወንጌል ስርጭት፦ በሀዋሳ ከተማ ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ የወንጌል መልእክት ለህዝቡ የማድረስና አወንታዊ ተፅዕኖ የመፍጠር ስራ ተካሂዷል። ይህ ታላቅ ካምፖሪ የወጣቶችን ህብረት፣ የመንፈሳዊ አገልግሎት ቁርጠኝነት እና የወንጌል ስራን በስፋት ማጠናከርን ዓላማ ያደረገ ሲሆን፣ እስከ ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ የተለያዩ አነቃቂ መርሐ ግብሮችን በማካተት የሚቀጥል ይሆናል። #PathfinderCamporee #EasternEthiopiaUnion #Hawassa #SpeakLord #AngazaWestDrumCorps #SDA #YouthMinistry #Pathfinders #Ethiopia Via:- HopechannelEthiopia @AdventistEthio @metagesy
ቅዳሜ ከሰዓት ሌላ ቀጠሮ እንዳይዙ! 261 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በሕፃናትና በታዳጊዎች አንደበት በቃል ሊቀርቡ፤ * ሐምሌ 18፣ ከ 8፡30 ጀምሮ * በወመዘክር ቅጥር ግቢ * በብላቴን ጌታ ኅሩይ ወ/ሥላሴ አዳራሽ ተቀጥሯል። በዕለቱም በጥንታዊ የብራና ጥቅልል ላይ በጥንቃቄ ከመከ'ተብ ጀምሮ አሁን በዘመናችን ስማርት ስልኮች ላይ በቀላሉ እስከመገኘት ድረስ መጽሐፍ ቅዱስ ያለፈበት የብዙ ዘመናት ታሪክ በረዳት ፕሮፌሰር መስፍን ማንደፍሮ አማካኝነት ትንታኔ ይሰጥበታል። መግቢያ በነጻ ነውና ኪስዎን አንድም ሳይዳብሱ ጊዜዎትን ብቻ አመቻችተው ከወዳጆችዎ ጋር በመምጣት ይህንን መልካም ይጠቀሙ! ©️ፍኖተ ብራና አገልግሎት ጉርሻ page 🌴🌴🌴 https://www.facebook.com/share/p/18xps9X3qA/?mibextid=wwXIfr
Via:- ጉርሻ Tube @AdventistEthio @metagesy
የአቃቂ አድቬንቲስት ት/ቤት በተለያየ የስራ መስክ ክፍት የስራ ቦታ አለው፡፡ መስፈርቱን የምታሟሉ የትምህርት እና የስራ ልምድ መረጃ በማቅረብ መወዳደር የምትችሉ መሆን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡ @AdventistEthio @metagesy
አንዳንዴ የተባረኩ ሰዎች ሲያገለግሉ ወይም ሲተጉ አብረን ብንገኝ መልካም ነው፡፡ ቅዳሜ ሀምሌ 18/2018ዓ.ም ከ ረ/ፕ መስፍን ማንደፍሮ ጋር ጥሩ ጊዜ ይኖራል፡፡ አትቅሩ፡፡ @AdventistEthio @metagesy
📌 "ሰው ከቸርች ለመጥፋቱ ምክንያት አትኹኑ!" ሰዎች ወደ ቤተክርስቲያን የሚመጡት ጌታን ለመስማትና ለማምለክ ብቻ ሳይኾን፣ ቅዱስ ኅብረት ለማድረግም ጭምር መኾኑ የታወቀ ነው። ከሰው ልጆች መሠረታዊ ፍላጎቶች አንዱ "የእኔ" የሚሉትና "የእኛ" ተብለው የሚታቀፉበትን ማኅበረሰብ ማግኘት ነው። ለዚኽ መሠረታዊ ፍላጎት ደግሞ ቤተክርስቲያን አንዷና ዋነኛዋ መጠለያ ናት። ነገር ግን ሰው በዚኽ ንጹሕ ልብ ኾኖ ሲመጣ፣ ተመልሶ እንዲኼድና በቤተክርስቲያን እንዳይቆይ ምክንያት የሚኾኑ አሰናካይ ሰዎች ያጋጥሙታል። በኖኅ መርከብ ውስጥ እባብም እርግብም፣ ጅብም አህያም፣ ፍየልም ነብርም አብረው እንደነበሩት ኹሉ፤ በጌታ ቤትም (በቤተክርስቲያን) ውስጥ የዋሆች ብቻ ሳይኾኑ አሰናካዮችም አሉ። በዚህም ምክንያት ዐዳዲስ አማኞችና ወደ ቤተክርስቲያን የመጡ ምስኪን ሰዎች የእነዚኽ አሰናካዮች ሰለባ ይኾናሉ። አንዳንዶች ቸርች ሲቀይሩ፣ አንዳንዶች ግን ሙሉ በሙሉ ተስፋ ቆርጠው ወደ ቀደመ ሕይወታቸው ይመለሳሉ፤ ወይም የትም ሳይሄዱ በቤታቸው ይቀመጣሉ። ለመኾኑ ሰዎችን ከቤተክርስቲያን የሚያስወጡትና ማሰናከያ የሚኾኑት እነዚህ ሰዎች ምን ዓይነቶች ናቸው? ⚠️ ሰዎችን ከቸርች የሚያጠፉ 9 አሰናካይ ምክንያቶች፡- 1. ዘረኝነት (ወገንተኝነት)፦ ዘረኝነት ትልቁና ዋነኛው አሰናካይ ጉዳይ ነው። የአንድ አካባቢ ልጆች ወይም የአንድ ብሔር ሰዎች ብቻ ከፊት ኾነው መድረኩንና ቤቱን በበላይነት በያዙ ጊዜ ሌላውን ያገለላሉ። ይኼን ጊዜ ቤቱን የጌታ ቤት ሳይኾን የ"ሰው ቤት" ያደርጉታል፤ በዚህም ምክንያት መጤው ሰው በብሔሩ ምክንያት ወደ ማይገለልበት ስፍራ ለመሄድ ወይ ተሰናክሎ ለመቅረት ይገደዳል። 2. ሐሜተኞች፦ ሰው በተለያየ ድካምና ውጣ ውረድ ውስጥ ያልፋል። ከጀርባ ኾነው የሚያሾከሹኩ ሐሜተኞች ግን የዚያን ሰው ነጻነት ይነጥቃሉ። ይልቁንም ሰውየው ከወደቀበት ውድቀት ይልቅ በወሬና በሐሜት ሕይወቱን ስለሚያስመርሩት ከቸርች እንዲቀር ምክንያት ይኾናሉ። 3. አድመኞችና ምቀኞች፦ አድመኝነት ማለት የታሰበበት ዐመፅና ሴራ ማለት ነው። ይኽም ምዕመኑ በአገልጋዮች ላይ፣ ወይም አገልጋዮች እርስ በርስ በአገልጋዮች ላይ የሚሸርቡት ሊኾን ይችላል። ይኽ ስውር ደባ መገለጡ ስለማይቀር፣ ይኽንን ድራማ የሚያዩ ምስኪን ምዕመናንና ጌታን የሚፈሩ አገልጋዮች ሳይቀሩ ተሰናክለው ከቸርች ይቀራሉ። 4. ዝሙት (የግብረገብነት መበላሸት)፦ ልክ እንደ ዔሊ ልጆች ያሉ አገልጋዮች ዛሬም አሉ። ለጸሎትና ለትምህርት የሚመጡ እኅቶችን የሚያሰናክሉ፣ ለብዙዎች ልብ ስብራትና ለእምነት መርከስ ምክንያት የኾኑ ወንድሞችና እኅቶች በቤቱ ውስጥ መኖራቸው ሰዎችን ያሰናክላል። 5. አጭበርባሪዎችና ስግብግቦች፦ ገንዘብን የሚወዱና ያገኙትን አጋጣሚ ኹሉ ለዚኽ ከንቱ ምድራዊ ረብ የሚጠቀሙ ሰዎች አሉ። በቸርች ውስጥ እንዲኽ ዓይነት ሰው ይኖራል ብለው የማይጠረጥሩ የዋህ ክርስቲያኖች በቀላሉ ይታለላሉ፤ በዚኽም ማጭበርበር ምክንያት ተስፋ ቆርጠው ከቸርች ይቀራሉ። 6. ልዩነትን አለማስተናገድ፦ በአለባበስ፣ በባሕል፣ ወይም በተለያዩ ማኅበራዊ ዳራዎች (Background) ምክንያት ሰዎችን ማግለልና "እኛን አይመስሉም" በሚል መንፈስ ማራቅ ሰዎችን ገፍቶ ያስወጣል። 7. የስልጣንና የጥቅም ሽኩቻ፦ በቤተክርስቲያን መሪዎች ወይም አገልጋዮች መካከል የሚፈጠሩ የአስተዳደር ግጭቶች፣ የገንዘብ አያያዝ ጉድለቶችና የስልጣን ፉክክሮች የምዕመናንን እምነት ሙሉ በሙሉ ያጠፋሉ። 8. በሰዎች ውጫዊ ገጽታ ላይ ማተኮር (ፈራጅነት)፦ ሰዎችን በውጫዊ ማንነታቸው፣ በአለባበሳቸው ወይም ካለፉበት የሕይወት ታሪክ (ለምሳሌ ሱሰኝነት ወይም ደካማ ታሪክ) በመነሣት የመኮነንና የማግለል ዝንባሌ ሲኖር፤ ግለሰቦች እረፍት ፍለጋ የመጡበት ቦታ "የፍርድ ወንበር" ኾኖ ስለሚያገኙት ይርቃሉ። 9. የዶክትሪን ወይም የስርዓት ግጭቶች፦ በአንዳንድ መሰረታዊ ባልኾኑ፣ ለድነት ወሳኝ ባልኾኑ ስነ-መለኮታዊ አመለካከቶችና ሥርዓቶች ላይ የሚደረጉ መከፋፈሎችና አላስፈላጊ ክርክሮች ሰዎችን ያሰልቻሉ፣ ያርቃሉም። 📌 ማጠቃለያ በእነዚኽ ኹሉ ሰዎችና አስከፊ ምክንያቶች የተነሣ ብዙዎች ከቸርች ይቀራሉ። ከዚኽ ሲከፋ ደግሞ ከራሱ ከጌታም ይርቃሉ። ስለኾነም፣ እንደዚኽ ባሉ ክፋቶችና ዐመፆች ተካፋይ ባለመኾን፣ በእኛም ስውርም ኾነ ግልጽ ጠባይ ምክንያት ማንም እንዳይሰናከል እያንዳንዳችን ልንጠነቀቅ ይገባል። ቤተክርስቲያን ለማንም ሰው ክፍት የኾነች የፍቅርና የደኅንነት ማዕከል እንጂ፣ ፍጹማን ነን ባዮች ብቻ የሚደሰቱባት የተመረጡ ሰዎች ክበብ መኾን የለባትም!" ጌታ በነገር ኹሉ ማስተዋልን ይስጠን። አሜን። © ከማህበራዊ ሚዲያ ላይ ካነበብኩት https://t.me/AdventistEthio @Metagesy
ትክክለኛ ውሳኔ፡፡ የምዕራብ ኬንያ ዩኒየን በቅዳሜ( በሰንበት አምልኮ ሰዓት) ምንም አይነት የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ እንዳይከናወን አዘዘ፡፡ ምን ትላላችሁ፡፡ @AdventistEthio @metagesy
መልካም ሰንበት! "..ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው..."።መዝሙር 127፡3 አዲሶቹን የHope Channel Ethiopia የዩቲዩብ ቻናሎች subscribe, share, Like ማድረግ አይርሱ! እናመሰግናለን!
https://youtu.be/cBsHEC7i5-w
📌መልካም ዜና!📌 ለ2018 ዓ.ም. የአድቬንቲስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎች በሙሉ! SEAL (Society of Ethiopian Adventist Lay-members) ለአራተኛ ጊዜ ባዘጋጀው ዓመታዊ የምርቃት መሰናዶ ላይ እንዲገኙ በአክብሮት አድመንዎታል:: ቦታ:- አቃቂ አድቬንቲስት ቤ/ክርስቲያን (ት/ቤት ግቢ ውስጥ) ቀን:- ሰኔ 27/2018 ዓ.ም. (July/04/2026) ሰዓት፦ ሙሉ ቀን ከጠዋት 2፡30 ጀምሮ 📌ውድ ተመራቂያን 300 ብር ብቻ የመመዝገቢያ በመክፈል ድምቅ ባለ የምርቃት ሥነ-ስርዓት ጌታን ለማመስገን ባዘጋጀነው ድግስ ላይ ለመሳተፍ አሁኑኑ ይመዝገቡ:: 📌ምዝገባው ተጀምሯል እስከ ሰኔ 20 ይቆያል:: 📌ለምዝገባ የተዘጋጀውን የGoogle Form በመሙላት ስትመዘገቡ ላላችሁ የትኛውም ጥያቄ የሚከተሉትን ስልኮች ተጠቀሙ። መታገስ የኔነህ:- +251923943365 ኤባ ደከቦ:- +251948154603 ዶ/ር ዳዊት ካሳ +251 91 343 7865 👇🏼 ለምዝገባ የተዘጋጀውን የGoogle Form በመጫን ይመዝገቡ https://forms.gle/MhueadFSDXjXUh1o8 ማሳሰቢያ‼️ ላልተመዘገበ ቦታ አይኖረንም፡፡
የማይቀርበት የአምልኮ ቀን ስለዚህ ምክንያት በሰማይና በምድር ያለ አባትነት ሁሉ ከሚሰየምበት ከአብ ፊት እንበረከካለሁ ኤፌሶን 3:15 በቃሊቲ 7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ-ክርስቲያን ግንቦት 15,2018 ኑ የተለየ የአምልኮ ጊዜ አብረን እናሳልፍ፡፡ 🧎♂➡️ ፀሎት 🎤 ዝማሬ 📖 የእግዚአብሔር ቃል ( ስብከት ) https://t.me/AdventistEthio @metagesy