tgindex
Tariku Abera

ኦርቶዶክሳዊ የወንጌል አገልግሎት

Последний пост
17 июн.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
4 241
−5 за 4 дн.
Сутки
−4
−0,09%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 588
20 постов
Вовлечённость
37,4%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 17 июн.2 0282

    без подписи

  • 17 июн.1 8379

    † ቅዳሴ ኤጲፋኒዮስ † ★ እጅግ ድንቅና ጥልቅ ምሥጢረ መለኮት ያለበት ቅዳሴ ነው አንብቡት።ለሌሎችም ሼር አድርጉት★ እግዚአብሔር በገናናነቱ ገናና ነው። በቅድስናው የተቀደሰ ነው። በምስጋናው የተመሰገነ ነው። በክብሩም የከበረ ነው። ከመቼ ወዲህ የማይሉት ቀዳማዊ ነው። እስከ ዛሬ የማይሉት ማእከላዊ ነው። እስከዚህ የማይሉትም ደኃራዊ ነው። ለአነዋወሩ ጥንት የለውም። ለአኳኋኑም ፍጻሜ የለውም። ለዘመኑም ቍጥር የለው። ለዓመታቱም ልክ ቍጥር የለውም። ለውርዝናውም ማርጀት የለበትም። ለኃይሉም ጽናት ፣ ድካም የለበትም። ለመልኩ ጥፋት የለበትም። ለፊቱ ብርሃንም ጨለማ የለበትም። ለጥበቡ ባሕር ድንበር የለውም። ለትእዛዙም ይቅርታ መስፈርት የለውም። ለመንግሥቱም ስፋት ዐቅም ልክ የለውም። ለአገዛዙም ስፋት ወሰን የለውም። በኅሊና የማያገኙት ሥውር ነው። በልቡናም የማይረዱት ምጡቅነው። አንሥርት የማይደርሱበት ረጅም ነው። ዓሣዎች የማይዋኙበት ጥልቅ ነው። ከተራሮች ራስ ይልቅ ከፍ ያለ ነው። ከባሕር ጥልቅነት ይልቅ ጥልቅ ነው። ነገሥታት የምይነሣሡበት ጽኑ ነው። መኳንንት የማይቃወሙት አሸናፊ ነው። የጥበበኞችን ምክር የሚያጠፋ ጥበበኛ ነው። የሚመክሩትን ሰዎች አሳባቸውን የሚያስረሳ ዐዋቂ ነው። የጸኑ ልጓሞችን የሚፈታ ኃያል ነው። የኃጥኣንን ጥርሶች የሚያደቅ ፤ የትዕቢተኞችንም ክንድ የሚቀጠቅጥ ብርቱ ነው። የግብዞችን ፊት የሚያዋርድ ክቡር ነው። የዝንጉዎችን ብርሃን የሚያርቅ ከሃሊ ነው። ባልንጀራ የሌለው አንድ ነው። ዘመድ የሌለው ስሉጥ ነው። ሰማያት ይጠፋሉ ፤ የብስም ትጠፋለች ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃል። እርሱ ግን እስከ ዘላለሙ እርሱ ነው። የባሕር መመላለስዋ ድንቅ ነው። ድንቅስ በልዕልናው እግዚአብሔር ነው። የሚመስለው የለም። ከፍጥረትም ሁሉ ከአማልክትም ሁሉ የሚተካከለው የለም። እርሱ ብቻ አምላክ ነው። እርሱም ብቻ ጌታ ነው። ፈጣሪም እርሱ ብቻ ነው። ሠሪም እርሱ ብቻ ነው። ስላሰበው ጥበብ ረዳት አይሻም። ስለወደደውም ሥራ መካር አይሻም። ሳይሆን ቀድሞ እንደ ሆነ አድርጎ ፤ ያልተደረገውንም እንደ ተደረገ አድርጎ ሁሉን ያውቃል። ሳይጠይቅ ኅሊናን ይመረምራል። ሳይመረምር ልቡናን ይፈትናል። ያለ መብራት በጨለማ ያለውን ያያል። ጻድቁን ጽድቅን ሳይሠራ ያውቀዋል። ኃጥኡንም ኃጢአት ሳይሠራ ያውቀዋል። ልበኞችን ከአባታቸው አብራክ ሳይወጡ ያውቃቸዋል። ኃጥኣንንም ከእናታቸው ማኅፀን ያውቃቸዋል። የሚሸሸገው የለም። የሚሠወረውም የለም። ከእርሱም የሚሠወር የለም። ሁሉ በእርሱ ዘንድ የተገለጸ ነው። በዓይኖቹም ፊት የተዘረጋ ነው። ሁሉ በመጽሐፉ የተጻፈ ነው። በሕሊናውም ሁሉ የተጠራ ነው። ቍጥር የሌላቸው ታላላቆችን መመርመር የሌለባቸውን የተደነቁ የከበሩ ሥራዎችን ይሠራል። ሥራው ከአየነው ይልቅ ዕፁብ ነው። ኃይሉም ከሰማነው ይልቅ ድንቅ ነው። ጌትነቱም ከነገሩን ይልቅ ድንቅ ነው። ከጨለማ ለይቶ ብርሃንን ፈጠረ። ደመናውን መለየት ያውቃል። ውኃውን እንደ ወደደ ይከፍለዋል። የተመረጡትን በደመና ይሠውራል። ምድርን ፈጠራት ፤ መጠንዋንም አዘጋጀ ፤ ፍጻሜዋንም እንደምንም ተከተለ ፤ ማዕዘንዋንም አጸና። ባሕርን ከእናትዋ ሆድ በወጣች ጊዜ በበሮች አነጠራት። ልብሷንም ደመና አደረገላት። በጉም ጠቀለላት። ወሰን አደረገላት። በውስጥዋም መዝጊያዎችንና ቁልፎችን አደረገላት። እስከዚህ ድረሺ ከወሰንሺም አትተላለፊ ፤ ማዕበልሽ በውስጥሽ ይመላለስ (ይነቃነቅ) እንጂ አላት። በበላይዋ ላይ የንጋት ብርሃን ተዘጋጀ። የአጥቢያ ኮከብም ትዕዛዙን ዐወቀ። እርሱ ከምድር ጭቃን ነሥቶ ሕያው የሆነውን ፈጠረ። በምድርም ላይ እንዲነጋገር አደረገው። እርሱ እስከ ዓለም ዳርቻ ደረሰ። በጥልቅ ፍለጋም ተመላለሰ። ከግርማው የተነሣ የሞት ደጆች ይከፈታሉ። የሲኦል በሮችም ባዩት ጊዜ ይደነግጣሉ። ከሰማይ በታች ያለውን ስፋቱን ከሰማይ በላይ የሚሆነውንም እርሱ ያውቃል። በእርሱ ትእዛዝ ዋግ ከመዝገቡ ይወጣሉ። ከሰማይ በታች ያለ አዜብ(ነፋስ) ይመላለሳል። ዝናምን በምድረ በዳ ያጸናዋል። ሰው በሌለበትና የሰው ልጅ በማይኖርበት ይዘንም ዘንድ። እርሱ የውኃውን መፍሰሻ ወሰን ፣ ክረምትንም በየዓመቱ ይከፍታል። በጋውንም ኋላ በጊዜው ያመጣዋል። ደመናውንም በቃሉ ይጠራዋል። ውኃም እየተንቀጠቀጠ ይመልስለታል። ብልጭልጭታውን እርሱ ይልከዋል ፤ እርሱም ይሄዳል። ምንድር ነው እያለ ይመልስለታል። እርሱ ደመናን በጥበቡ ይቆጥረዋል። ሰማይን (ጠፈርን) ወደ ምድር ያዘነብለዋል። እርሱ ብቻ የአርያምን ኃይል ለበሰ። በምስጋናና በክብር ተጌጠ። እሳታውያን ኪሩቤል ፣ ብርሃን የለበሱ ሱራፌልም እርሱን ያመሰግኑታል። በማያርፍ ቃል ፣ ዝም በማይል ፣ በማይደክምም አንደበት ሁሉም ተባብረው ተሰጥኦ ባለበት ባንድ ቃል የጌትነትህ ምስጋና በሰማይ በምድር የመላ ፍጹም አሸናፊ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ይላሉ። ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ጸባዖት ፍጹም ምሉዕ ሰማያተ ወምድረ ቅድሳተ ስብሐቲከ። ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ፍጹም አሸናፊ እግዚአብሔር የጌትነትህ ምስጋና በሰማይ የመላ ነው። Holy Holy Holy, perfect Lord of hosts, heaven and earth are full of the Holiness of Thy Glory. ለሌሎችም ሼር አድርጉት

  • 26 мая1 8112

    без подписи

  • 26 мая1 8102

    без подписи

  • 26 мая1 5041

    ሙስሊም ወገኖቼ ሆይ! ዋናው ቁም ነገሩ በሥጋ የተገለጠውን ፣በመንፈስ የጸደቀውን፣ለመላእክት የታየውን፣ በአሕዛብ የተሰበከውን፣በዓለም የታመነውንና በክብር ያረገውን ኢየሱስ ክርስቶስን በፍቅር አምናችሁ በፍቅር ትከትሉት ዘንድ ነው ይህም ለጥቅማችሁ ነው ምንዳዎቻችሁ ሁሉ ይሞላሉ፤ በነፍሳችሁም ክብርን ታገኛላችሁ መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ይላል «እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም»ሮሜ 8፥1 ክብር ለስሙ ይሁን ። ኢየሱስ ክርስቶስ የነፍስ እረፍት ነው ማንም ወደ እርሱ የመጣ እንቆቅልሹ ተፈቶ፣እንባው ከፊቱ ላይ ታብሶ ፣ጨለማው ተገፎ ፣ቀንበር ተሰብሮለት በክብር ይመለሳል።ኢየሱስ ክርስቶስ የማምለጫ ዓለት ነው እርሱን ተከተሉት ከጠላት ፍላጻ በስሙ ትድናላችሁ ፣ኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወት ውሃ ነው እርሱን ተከተሉት የጠወልገች ነፍሳችሁ በቃሉ ትለመልማለች፣ኢየሱስ ክርስቶስ መልካም እረኛ ነው እርሱን ተከተሉት በለመለመ መስክ ያሰማራችኋል ፣ኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ነው እርሱን ተከተሉት ወደ ዘለዓለም ርስት ወደ አባቱ ዙፋን ያደርሳችኋል።ኢየሱስ ክርስቶስ የነፍሳችሁ ቤዛ ነው እርሱን እመኑት ጽድቅን ያለዋጋ እንዲያው በጸጋ በእምነት ትቀበላላችሁ በልጅነት ስልጣንም የመንግስቱ ወራሾች ትሆናላችሁ። ቅዱስ መጸሐፍ እንዲህ ይላል «በልጁ የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው።»ዮሐ 3፥36 ወገኖቼ አንዳች አትጠራጠሩ ቃሉ የታመነ ነው ፤አምናችሁ ተከተሉት ተብላችኋል በእምነት ተከተሉት እርሱ በሰማያት የነፍሳችሁ ምስክር ነው ።«በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በነፍሱ ምስክር አለው ።» ተብሎ ተጽፏል 1ዮሐ 5፥10 የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሆይ ! በኢየሱስ ክርስቶስ የማያምኑና እርሱን የማይከተሉ በምድርም ሆነ በሰማይ ብርቱ ቅጣት እንደ ሚጠብቃቸው ቁርአኑ እንዲህ ሲል በብርቱ ያስጠነቅቃል። فَأَمَّا الَّذِينَ كَفَرُوا فَأُعَذِّبُهُمْ عَذَابًا شَدِيدًا فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ وَمَا لَهُم مِّن نَّاصِرِينَ «እነዚያማ የካዱትን ሰዎች በቅርቢቱ ዓለምና በመጨረሻይቱ ዓለም ብርቱን ቅጣት እቀጣቸዋለሁ፡፡ ለእነርሱም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡»አል ኢምራን 3፥56 ልብ ያለው ልብ ይበል! በክርስቶስ ኢየሱስ የሚገኘውን ጽድቅና የዘለዓለም ሕይወት ካወቁና ከተረዱ በኋላ እንደ ተራ ነገር በማቃለል የተፈጸመልንን የቤዛነት ሥራ ማክፋፋትና መናናቅ ብርቱ ቅጣትን በነፍስም በሥጋ ያስከትላል፤ምክንያቱም የተከፈለልን ዋጋ ከአእምሮ በላይ ነው። ጌታ ልዑለ ባሕርይውን ዝቅ አድርጎ የባሪያን መልክ ይዞ በሥጋ የተገለጠው እኛን ለማክበር ነው።ምራቅ የተተፋበት ፣በአይሁድ እጅ የተንገላታው ፣ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ እርጥብ መስቀል ተሸክሞ 65 ጊዜ እየወደቀ እየተነሳ ለመሰቀል የሄደው፣ ሥጋው አልቆ አጥንቱ እስኪታይ ድረስ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት ጊዜ የተገረፈው፣የእሾህ አክሊል አናቱ ላይ ደፍቶ ፊቱ በደም ጅረት የተጋረደው አንዳችም በደልና ኃጢአት ተግኝቶበት ሳይሆን እኛ የአዳም ልጆች ስለ ኃጢአታችን ልንቀበል የሚገባውን ቅጣት እርሱ በኛ ፈንታ ተቀብሎ የእርሱን ጽድቅ ለእኛ ሊያወርሰን ነው። አንድ ጊዜ የዓለሙን ሁሉ በደል ተሸክሞ በመስቀል ላይ የታየልንና ስለ እኛ እርግማን እርሱ እንደ ተረገመ ሰው መስሎ በመስቀል ላይ የዋለው ላመኑበትና ለተከተሉት ሁሉ ሕያው የሆነ የማስታረቂያ ልመና ለማቅረብ ነው።« አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅርበላቸው» በማለት ከብርቱ ጩኽትና እንባ ጋር ጸሎትና ምልጃን ፡አቀረበ ተሰማለትም ።ዓለምን ከአብ ጋር ለዘለዓለም አስታረቀ አሁን ግን ክርስቶስ በሰማያት በክብር ዙፋኑ አለ ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁትም በአብ ፊት ያለ ኃጢአት ይታይላቸዋል ማለትም ቀድሞ የዓለሙን ሁሉ ኃጢአት ተሸክሞ ነበር የታየልን አሁን ግን የማንንም ኃጢአት ሳይሸከም ያለ ኃጢአት ይታይልናል በመስቀል ላይ የፈጸመው የቤዛነት ሥራም እይታሰበ ዛሬም በእምነት ወደ እርሱ የሚቀርቡትን ሁሉ ሲያድን ይኖራል።ዕብ 9፥28 ክብር ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን። የተከበራችሁ ሙስሊም ወገኖቼ ሆይ! መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ይላል «በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመን አሁን ተፈርዶበታል።»ዮሐ 3፥18 ወገኖቼ ሆይ የመዳን ቀን ዛሬ ነው ይህንን የመዳን ጥሪ በአንድም በሌላም መንገድ እግዚአብሔር ወደ ልባችሁ ያመጣላችሁ ወገኖች ዛሬውኑኑ ወስኑ ወደ ክርስቶስ ተጠጉ በእርሱ እምኑ፣ስሙን ጠርታችሁ ተማጸኑ፣ወደ ልባችሁ እልፍኝም እርሱ እንዲገባ በእምነት በልብ ቋንቋ እርሱን ጠይቁት ዛሬ በቤታችሁ ታላቅ ደስታ ይሆናል በነፍሳችሁም የዘለዓለም ድኅነትን ታገኛላችሁ ።ይህንን የመዳን የምስራች የማይቀበሉ ግን ቁርአኑ እንዳለው ብርቱ ቅጣት ይጠብቃቸዋል መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ይላል።«በልጁ የማያምን የእግዚአብሔር ቁጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም» ዮሐ 3፥36 ሙስሊም ወገኖቼ ሆይ ቀጥሎ ያለውን ጸሎት በእምነት ሆናችሁ ጸልዩት በሕይወታችሁ ድንቅ ነገርን እግዚአብሔር ይሰራል። « ሰማይና ምድርን ባህርና ውቅያኖስን በቃልህ የፈጠርህ የዓለም ፈጣሪ እግዚአብሔር ሆይ አንተን አምናለሁ ለአንተም እገዛለሁ፤ የሰው ልጆችን ይስተምርና ያድን ዘንድ ወደ ድንግል ማርያም ማህጸን ልከህ ሰው ሁኖ እንዲወለድ ባደረግከው በቃልህ በኢየሱስ ክርስቶስም አምናለሁ፤ እርሱንም እከተላለሁ እርሱ የጽድቅ መንገድ ነው፣እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ሁሉ ቤዛ ነው፣በእርሱ ወደ አንተ ወደ እግዚአብሔር እቀርባለሁ፤ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የልጅነት ስልጣንና የወራሽነትን ክብር በጸጋ ሰጥተኽኛልና ስምህ ለዘለዓለም ከፍ ከፍ ይበል፣ እግዚአብሔር ሆይ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ብለህ ቀንበሬን ከላዬ ላይ ስበር፣እንቆቅልሼን ፍታ፣ጨለማዬን ግፈፍ፣ታሪኬን ለውጥ፣ ከቤቴ ጣራ በታች ግባ ማዳንህንም በእኔና በቤተሰቦቼ ላይ አሳይ ክንድህን ዘርጋ በሰማያዊ በረከትም ባርከኝ ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን።» ወድ አንባብያን ሆይ በኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነትና ፈጣሪነት ዙሪያ ከሙስሊም ወገኖቻችን የሚነሱ በርካታ ጥያቄዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አሉ ለሚነሱት ለእያንዳናዳቸው ጥያቄዎች በሙሉ ሰፊ ማብራሪያ መልስ የሰጠሁበት ኢየሱስ ማን ነው? በሚል ርእስ ያዘጋጀሁት መጽሐፍ ስላለ ከመንፈሳዊ መጻሕፍት መደብር እየጠየቃችሁ መጠቀምና ለሚጠይቋች ሁሉ መልስ ለመስጠት ዝግጁዎች ትሆኑ ዘንድ መልእክቴን ማስተላለፍ እፈልጋለሁ። ሙስሊም ወገኖቼም መጻሐፉን ብታነቡት ለበርካታ ጥያቄዎቻችሁ በቂ መልስ ታገኙበታላችሁ። እባካችሁ ይህንን መልእክት ለሙስሊም ወገኖቻችን ሁሉ ሼር በማድረግ የክርስቶስ ወገን ታደርጓቸው ዘንድ በፍቅር እጠይቃለሁ። ለበረከት ሁኑ። ይቀጥላል እባክዎን ፔጁን like ያድርጉ

  • 26 мая1 0641

    † ወንጌል ለሙስሊም ወገኖቼ † ክፍል 2 "ቁርአን ክርስቶስን አምነው የሚከተሉት አማኞች ታላቅ በረከት እንዳላቸው በግልጽ ይመሰክራል።" መ/ር ታሪኩ አበራ وَأَمَّا الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ فَيُوَفِّيهِمْ أُجُورَهُمْ ۗ وَاللَّهُ لَا يُحِبُّ الظَّالِمِينَ «እነዚያ /የመርየም ልጅ አል መሲህ ዒሳን/ ያመኑትማ መልካም ሥራዎችንም የሠሩት ምንዳዎቻቸውን ይሞላላቸዋል፡፡ አላህም በዳዮችን አይወድም፡፡»አል ኢምራን 3፥57 በአገር ውስጥና በውጭ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ወገኖቼ ሁላችሁ በያላችሁበት ሰላምና ጤና ከነቤተሰቦቻችሁ ይብዛላችሁ ። እናንት ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ወገኖቼ ሆይ! አባቶቻችሁና አባቶቻችን በፍቅር እትብት ተሳስረው በደም ሐረግ ተሰናስለው ፣የዘርና የሃይማኖት አጥር ሳይገድባቸው ፍቅርን ዘርተው ፍቅርን ያሳጨዱን ከእምነትና ከተስፋ ይልቅ በፈጣሪ ፊት ታላቅ ዋጋ የሚያሰጠውን የፍቅር ሕይወት ከቃል በዘለለ በተግባር ያሳዩን የሰላም አርበኞች ናቸውና ለቀደሙት የእምነት አባቶቻችሁና አባቶቻችን ከልብ የሆነ ምሥጋናና ክብር ይግባቸዋል። ሙስሊም ወገኖቼ ሆይ! በሌላው ዓለም ካለው የሙስሊም ማህበረስብ ይልቅ የእናንተ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ልባችሁ እጅግ ቅንና ርኅሩኅ የሆነ፣ከክርስቲያን ወንድሞቻችሁ ጋር በማኅበራዊ ሕይወት አብራችሁ ደፋ ቀና የምትሉ ፣ለክርስቲያን እህታችሁ በችግሯ ሰዓት ከማንም ቀድማችሁ የምትደርሱ፣የተቸገረ ምስኪን ክርስቲያን ደጃችሁ ቢቆም ዘካ ከመስጠት የማትነፍጉ ደግና ቀናዎች ናችሁና የኢትዮጵያ አምላክ ከክፉ ይጠብቃችሁ። በሕመማችሁና በችግራችሁ ሰዓት ቅዱሱን ጠበል ፍለጋ ከክርስቲያኑ ጋር ቤተክርስቲያን ገብታችሁ በፍቅር የምትጠመቁ፣ስእለታችሁ ሲደርስ ለቁልቢ ገብርኤል ድባብ ዣንጥላና የእጃችሁን አንባር አውልቃችሁ የምትሰጡ እግዚአብሔርን አክባሪ ጨዋ ማህበረሰብ ናችሁ ። ደሴናከሚሴ፣ ኮምቦልቻና ወልድያ ቤተክርስቲያን ሲታነጽ ድንጋይ ተሸክማችሁ ፣ውሃ ቀድታችሁ የምታመላልሱ ልበ ርኅሩሆች ናችሁና በእውነት የኢትዮጵያ አምላክ ዘራችሁን ይባርክ ።በእኛ እና በእናንተ መካከል ያለውን የፍቅር ግንብ ለመደርመስና ሰላማችንን ለማደፍረስ በእምነት ስም ከባዕዳን የወረሱትን ጽንፈኝነትና አክራሪነትን ይዘው በጂኒ መንፈስ የሚሯሯጡትን ሁሉ የመርየም ልጅ አል መሲ ዒሳ ልባቸውን ይመልሰው አሜን። ሙስሊም ወገኖቼ ሆይ! ዛሬ ለእናንተ ታላቁን የምስራች ቃል አድርስላችሁ ዘንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ልቤን ከወትሮው ይልቅ እጅግ አስጨንቆታል ።ይህ ዛሬ የምትሰሙት የምሥራች ነፍሳችሁ የምትጽናናበት፣ መንፈሳቹ የሚያርፍበት፣ መዳናችሁ የሚረጋገጥበት የጽድቅ ቃል ነው። ሁላችሁ እንደምታውቁት የመርየም ልጅ አል መሲህ ዒሳ በድንግልና ተጸንሶ በድንግልና የተወለደ ሞትና መቃብርን ድል አድርጎ በክብር ተነስቶ በእልልታ ያረገ ድንቅ አባት ነው። ክርስቶስን የሚያምኑትና የሚከተሉት ሁሉ ታላቅ በረከትና ሰማያዊ ዋጋ እንደሚያገኙም ቁራአንና መጽሐፍ ቅዱስ በጋራ በግልጽ ይመሰክራሉ። ቁርአኑ እንዲህ ይላል وَأَمَّا الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ فَيُوَفِّيهِمْ أُجُورَهُمْ ۗ وَاللَّهُ لَا يُحِبُّ الظَّالِمِينَ «እነዚያ /የመርየም ልጅ አል መሲህ ዒሳን/ ያመኑትማ መልካም ሥራዎችንም የሠሩት ምንዳዎቻቸውን/በረከታቸው/ ይሞላላቸዋል፡፡ አላህም በዳዮችን አይወድም፡፡»አል ኢምራን 3፥57 «እነዚያንም የተከተሉህን እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ ከነዚያ ከካዱት በላይ አድራጊ ነኝ፡፡»አል ኢምራን 3፥55 እንግዴህ ልብ በሉ ኢየሱስ ክርስቶስን የሚያምኑትና የሚከተሉት ሁሉ ምንዳዎቻቸው የሚሞላ እስከ ትንሣኤ ዘጉባኤ ዕለት ማለትም የሰው ልጆች ሁሉ ለፍርድ እስከሚቆምባት እስከ መጨረሻይቱ ሰዓት ድረስ ክርስቶስን የተከተሉ ሁሉ ከካዱት በላይ የክብር ባለቤቶች እንደሚሆኑ ቁርአኑ በግልጽ መስክሯል። እውነት ነው ክርስቶስን የሚያምንና እርሱን በእምነት የሚከተል ሁሉ በነፍሱ ዋስትና አለው ከጨለማም ወደሚደነቅ ብርሃን በክብር ይሻገራል ።ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ሲል አስተምሯል ። «ልባችሁ አይታወክ በእግዚአብሔር እመኑ በእኔም ደግሞ እመኑ »ዮሐ 14፥1 «እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ የሚከተለኝ የህይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ።»ዮሐ 8፥12። የተወደዳችሁ ሙስሊም ወገኖቼ ሆይ የመርየም ልጅ አል መሲህ ዒሳ ወደ ዚህች ምድር ያለ አንዳች ዓላማ አልተገለጠም በእግዚአብሔር የዘለዓለም እቅድ ውስጥ ለሰው ልጆች የተዘጋጀውን የዘለዓለም ሕይወትና የጽድቅ ትሩፋት በጸጋ ሊያጎናጽፈን ነው።ክርስቶስ ወደ ዚህች ምድር መጥቶ ኢንጅልን/ወንጌልን/ ከመስበኩ በፊት ዓለም በተውራት/በኦሪት/ና በሙሴ ሕግጋት እግዚአብሔርን ደስ በማሰኘት ጽድቅን ለማግኘት ሞክረው ነበር ፤ሆኖም ግን አልተቻላቸውም ሁሉም ከመርገም በታች ነበሩና ጽድቃቸው ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ተቆጥሮባቸው የሰው ልጅ ሁሉ ሲሞት እድል ፈንታውና ጽዋ ተርታው ወደ ሲኦል መውረድ ነበር ።ሆኖም ግን በሰው ልጆች ሐዘንና ስቃይ የማይደሰተው ርኅሩኅና አዛኝ የሆነው ጌታ ዓለምን የፈጠረበትን ቃሉን ወደ ድንግል ማርያም ማሕጸን ልኮ ሰው ሆኖ እንዲወለድ አደረገው እርሱም ዒሳ/ኢየሱስ/ ተብሎ ተጠራ ። የኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም የመምጣትም ትልቁ ዓላማ በስራቸው መጽደቅ ላልቻሉ የአዳም ልጆች ሁሉ እርሱ የጽድቅ መንገድ ይሆናቸው ዘንድ ነው ።በቁርአኑ አንተን የተከተሉህን ከካዱት በላይ አድራጊነኝ የተባለለትም ለዚህ ነው ።ይህ ከድንግል ማርያም በፍጹም ተዋሕዶ ሰው ሆኖ የተወለደው ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ተብሎ ይጠራል ለምን ቢባል በምድር እናት እንጂ አባት ሳይኖረው በመንፈስ ቅዱስ ድንቅ ግብር በተአምር ተወልዷልና እናቱ ድንግል ማርያም አባቱ እግዚአብሔር ተብሎ ይጠራል ፤ አንድም በልብ ታስቦ በአንደበት የሚገለጥ ቃል ልብ የወለደው የልብ ልጅ ይባላል ።ሙስሊም ወገኖቼ ብዙ ጊዜ ፈጣሪ አይወልድም አይወለድምም ስትሉ እንሰማለን ፤ነገር ግን በደንብ እንድትረዱት የምፈልገው ነጥብ ቢኖር እግዚአብሔር ልጅ አለው ሲባል በሰው የአወላለድ ሥርዓት የሚገለጥ ሳይሆን ከልብ እንደ ሚወለደው ቃል የሚመሰል ነው ።እግዚአብሔር አንድ ነው አብ በልብ ይመሰላል፣ ወልድ በቃል ይመሰላል፣ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ በእስትንፋስ ይመሰላል ሦስት አማልክት ግን አንልም አንድ አምላክ ብለን እናምናለን እንጂ ። ወልድ ከአብ ተወለደም ስንል ቃል ከልብ ተወለደ የማለት ያህል ነው።ለዚህ ነው እግዚአብሔር« ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር» ያለው ሰው ሦስት ነገር አለው ነገርግን አንድ ሰው ይባላል። እያንዳንዳችን ፣ልብ ፣ቃል፣ እስትንፋስ አለን ግን ሦስት ሰዎች አንባልም አንድ ሰው ነን እግዚአብሔርም እንዲሁ ነው ። አብ ፣ ወልድ ፣መንፈስ ቅዱስ ተብሎ ቢጠራም አንድ አምላክ አንድ ጌታ ነው ።( ስለ ምሥጢረ ሥላሴ ወደፊት በስፋት እንማማራለን።)

  • 22 мая1 2762

    без подписи

  • 22 мая1 0962

    ሙስሊም ወገኖቼ ሆይ! ዋናው ቁም ነገሩ በሥጋ የተገለጠውን ፣በመንፈስ የጸደቀውን፣ለመላእክት የታየውን፣ በአሕዛብ የተሰበከውን፣በዓለም የታመነውንና በክብር ያረገውን ኢየሱስ ክርስቶስን በፍቅር አምናችሁ በፍቅር ትከትሉት ዘንድ ነው ይህም ለጥቅማችሁ ነው ምንዳዎቻችሁ ሁሉ ይሞላሉ፤ በነፍሳችሁም ክብርን ታገኛላችሁ መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ይላል «እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም»ሮሜ 8፥1 ክብር ለስሙ ይሁን ። ኢየሱስ ክርስቶስ የነፍስ እረፍት ነው ማንም ወደ እርሱ የመጣ እንቆቅልሹ ተፈቶ፣እንባው ከፊቱ ላይ ታብሶ ፣ጨለማው ተገፎ ፣ቀንበር ተሰብሮለት በክብር ይመለሳል።ኢየሱስ ክርስቶስ የማምለጫ ዓለት ነው እርሱን ተከተሉት ከጠላት ፍላጻ በስሙ ትድናላችሁ ፣ኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወት ውሃ ነው እርሱን ተከተሉት የጠወልገች ነፍሳችሁ በቃሉ ትለመልማለች፣ኢየሱስ ክርስቶስ መልካም እረኛ ነው እርሱን ተከተሉት በለመለመ መስክ ያሰማራችኋል ፣ኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ነው እርሱን ተከተሉት ወደ ዘለዓለም ርስት ወደ አባቱ ዙፋን ያደርሳችኋል።ኢየሱስ ክርስቶስ የነፍሳችሁ ቤዛ ነው እርሱን እመኑት ጽድቅን ያለዋጋ እንዲያው በጸጋ በእምነት ትቀበላላችሁ በልጅነት ስልጣንም የመንግስቱ ወራሾች ትሆናላችሁ። ቅዱስ መጸሐፍ እንዲህ ይላል «በልጁ የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው።»ዮሐ 3፥36 ወገኖቼ አንዳች አትጠራጠሩ ቃሉ የታመነ ነው ፤አምናችሁ ተከተሉት ተብላችኋል በእምነት ተከተሉት እርሱ በሰማያት የነፍሳችሁ ምስክር ነው ።«በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በነፍሱ ምስክር አለው ።» ተብሎ ተጽፏል 1ዮሐ 5፥10 የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሆይ ! በኢየሱስ ክርስቶስ የማያምኑና እርሱን የማይከተሉ በምድርም ሆነ በሰማይ ብርቱ ቅጣት እንደ ሚጠብቃቸው ቁርአኑ እንዲህ ሲል በብርቱ ያስጠነቅቃል። ﻓَﺄَﻣَّﺎ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻛَﻔَﺮُﻭﺍ ﻓَﺄُﻋَﺬِّﺑُﻬُﻢْ ﻋَﺬَﺍﺑًﺎ ﺷَﺪِﻳﺪًﺍ ﻓِﻲ ዓለምና ﺍﻟﺪُّﻧْﻴَﺎ ﻭَﺍﻟْﺂﺧِﺮَﺓِ ﻭَﻣَﺎ ﻟَﻬُﻢ ﻣِّﻦ ﻧَّﺎﺻِﺮِﻳﻦَ «እነዚያማ የካዱትን ሰዎች በቅርቢቱ በመጨረሻይቱ ዓለም ብርቱን ቅጣት እቀጣቸዋለሁ፡፡ ለእነርሱም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡»አል ኢምራን 3፥56 ልብ ያለው ልብ ይበል! በክርስቶስ ኢየሱስ የሚገኘውን ጽድቅና የዘለዓለም ሕይወት ካወቁና ከተረዱ በኋላ እንደ ተራ ነገር በማቃለል የተፈጸመልንን የቤዛነት ሥራ ማክፋፋትና መናናቅ ብርቱ ቅጣትን በነፍስም በሥጋ ያስከትላል፤ምክንያቱም የተከፈለልን ዋጋ ከአእምሮ በላይ ነው። ጌታ ልዑለ ባሕርይውን ዝቅ አድርጎ የባሪያን መልክ ይዞ በሥጋ የተገለጠው እኛን ለማክበር ነው።ምራቅ የተተፋበት ፣በአይሁድ እጅ የተንገላታው ፣ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ እርጥብ መስቀል ተሸክሞ 65 ጊዜ እየወደቀ እየተነሳ ለመሰቀል የሄደው፣ ሥጋው አልቆ አጥንቱ እስኪታይ ድረስ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት ጊዜ የተገረፈው፣የእሾህ አክሊል አናቱ ላይ ደፍቶ ፊቱ በደም ጅረት የተጋረደው አንዳችም በደልና ኃጢአት ተግኝቶበት ሳይሆን እኛ የአዳም ልጆች ስለ ኃጢአታችን ልንቀበል የሚገባውን ቅጣት እርሱ በኛ ፈንታ ተቀብሎ የእርሱን ጽድቅ ለእኛ ሊያወርሰን ነው። አንድ ጊዜ የዓለሙን ሁሉ በደል ተሸክሞ በመስቀል ላይ የታየልንና ስለ እኛ እርግማን እርሱ እንደ ተረገመ ሰው መስሎ በመስቀል ላይ የዋለው ላመኑበትና ለተከተሉት ሁሉ ሕያው የሆነ የማስታረቂያ ልመና ለማቅረብ ነው።« አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅርበላቸው» በማለት ከብርቱ ጩኽትና እንባ ጋር ጸሎትና ምልጃን ፡አቀረበ ተሰማለትም ።ዓለምን ከአብ ጋር ለዘለዓለም አስታረቀ አሁን ግን ክርስቶስ በሰማያት በክብር ዙፋኑ አለ ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁትም በአብ ፊት ያለ ኃጢአት ይታይላቸዋል ማለትም ቀድሞ የዓለሙን ሁሉ ኃጢአት ተሸክሞ ነበር የታየልን አሁን ግን የማንንም ኃጢአት ሳይሸከም ያለ ኃጢአት ይታይልናል በመስቀል ላይ የፈጸመው የቤዛነት ሥራም እይታሰበ ዛሬም በእምነት ወደ እርሱ የሚቀርቡትን ሁሉ ሲያድን ይኖራል።ዕብ 9፥28 ክብር ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን። የተከበራችሁ ሙስሊም ወገኖቼ ሆይ! መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ይላል «በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመን አሁን ተፈርዶበታል።»ዮሐ 3፥18 ወገኖቼ ሆይ የመዳን ቀን ዛሬ ነው ይህንን የመዳን ጥሪ በአንድም በሌላም መንገድ እግዚአብሔር ወደ ልባችሁ ያመጣላችሁ ወገኖች ዛሬውኑኑ ወስኑ ወደ ክርስቶስ ተጠጉ በእርሱ እምኑ፣ስሙን ጠርታችሁ ተማጸኑ፣ወደ ልባችሁ እልፍኝም እርሱ እንዲገባ በእምነት በልብ ቋንቋ እርሱን ጠይቁት ዛሬ በቤታችሁ ታላቅ ደስታ ይሆናል በነፍሳችሁም የዘለዓለም ድኅነትን ታገኛላችሁ ።ይህንን የመዳን የምስራች የማይቀበሉ ግን ቁርአኑ እንዳለው ብርቱ ቅጣት ይጠብቃቸዋል መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ይላል።«በልጁ የማያምን የእግዚአብሔር ቁጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም» ዮሐ 3፥36 ሙስሊም ወገኖቼ ሆይ ቀጥሎ ያለውን ጸሎት በእምነት ሆናችሁ ጸልዩት በሕይወታችሁ ድንቅ ነገርን እግዚአብሔር ይሰራል። « ሰማይና ምድርን ባህርና ውቅያኖስን በቃልህ የፈጠርህ የዓለም ፈጣሪ እግዚአብሔር ሆይ አንተን አምናለሁ ለአንተም እገዛለሁ፤ የሰው ልጆችን ያስተምርና ያድን ዘንድ ወደ ድንግል ማርያም ማህጸን ልከህ ሰው ሁኖ እንዲወለድ ባደረግከው በቃልህ በኢየሱስ ክርስቶስም አምናለሁ፤ እርሱንም እከተላለሁ እርሱ የጽድቅ መንገድ ነው፣እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ሁሉ ቤዛ ነው፣በእርሱ ወደ አንተ ወደ እግዚአብሔር እቀርባለሁ፤ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የልጅነት ስልጣንና የወራሽነትን ክብር በጸጋ ሰጥተኽኛልና ስምህ ለዘለዓለም ከፍ ከፍ ይበል፣ እግዚአብሔር ሆይ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ብለህ ቀንበሬን ከላዬ ላይ ስበር፣እንቆቅልሼን ፍታ፣ጨለማዬን ግፈፍ፣ታሪኬን ለውጥ፣ ከቤቴ ጣራ በታች ግባ ማዳንህንም በእኔና በቤተሰቦቼ ላይ አሳይ ክንድህን ዘርጋ በሰማያዊ በረከትም ባርከኝ ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን።» ወድ አንባብያን ሆይ በኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነትና ፈጣሪነት ዙሪያ ከሙስሊም ወገኖቻችን የሚነሱ በርካታ ጥያቄዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አሉ ለሚነሱት ለእያንዳናዳቸው ጥያቄዎች በሙሉ ሰፊ ማብራሪያ መልስ የሰጠሁበት ኢየሱስ ማን ነው? በሚል ርእስ ያዘጋጀሁት መጽሐፍ ስላለ ከመንፈሳዊ መጻሕፍት መደብር እየጠየቃችሁ መጠቀምና ለሚጠይቋች ሁሉ መልስ ለመስጠት ዝግጁዎች ትሆኑ ዘንድ መልእክቴን ማስተላለፍ እፈልጋለሁ። ሙስሊም ወገኖቼም መጻሐፉን ብታነቡት ለበርካታ ጥያቄዎቻችሁ በቂ መልስ ታገኙበታላችሁ። እባካችሁ ይህንን መልእክት ለሙስሊም ወገኖቻችን ሁሉ ሼር በማድረግ የክርስቶስ ወገን ታደርጓቸው ዘንድ በፍቅር እጠይቃለሁ። ለበረከት ሁኑ። ይቀጥላል መ/ር ታሪኩ አበራ

  • 22 мая1 2464

    † ወንጌል ለሙ*ስ*ሊ*ሞች † ክፍል 1 "ቁርአን ክርስቶስን አምነው የሚከተሉት አማኞች ሁሉ ታላቅ በረከት እንዳላቸው በግልጽ ይመሰክራል።" መ/ር ታሪኩ አበራ ﻭَﺃَﻣَّﺎ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﻭَﻋَﻤِﻠُﻮﺍ ﺍﻟﺼَّﺎﻟِﺤَﺎﺕِ ﻓَﻴُﻮَﻓِّﻴﻬِﻢْ ﺃُﺟُﻮﺭَﻫُﻢْ ﻭَﺍﻟﻠَّﻪُ ﻟَﺎ ﻳُﺤِﺐُّ ﺍﻟﻈَّﺎﻟِﻤِﻴﻦَ «እነዚያ /የመርየም ልጅ አል መሲህ ዒሳን/ ያመኑትማ መልካም ሥራዎችንም የሠሩት ምንዳዎቻቸውን ይሞላላቸዋል፡፡ አላህም በዳዮችን አይወድም፡፡»አል ኢምራን 3፥57 «እነዚያማ የካዱትን ሰዎች በቅርቢቱ በመጨረሻይቱ ዓለም ብርቱን ቅጣት እቀጣቸዋለሁ፡፡ ለእነርሱም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡»አል ኢምራን 3፥56 በአገር ውስጥና በውጭ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ወገኖቼ ሁላችሁ በያላችሁበት ሰላምና ጤና ከነቤተሰቦቻችሁ ይብዛላችሁ ። እናንት ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ወገኖቼ ሆይ! አባቶቻችሁና አባቶቻችን በፍቅር ህትብት ተሳስረው በደም ሐረግ ተሰናስለው ፣የዘርና የሃይማኖት አጥር ሳይገድባቸው ፍቅርን ዘርተው ፍቅርን ያሳጨዱን ከእምነትና ከተስፋ ይልቅ በፈጣሪ ፊት ታላቅ ዋጋ የሚያሰጠውን የፍቅር ሕይወት ከቃል በዘለለ በተግባር ያሳዩን የሰላም አርበኞች ናቸውና ለቀደሙት የእምነት አባቶቻችሁና አባቶቻችን ከልብ የሆነ ምሥጋናና ክብር ይግባቸዋል። ሙስሊም ወገኖቼ ሆይ! በሌላው ዓለም ካለው የሙስሊም ማህበረስብ ይልቅ የእናንተ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ልባችሁ እጅግ ቅንና ርኅሩኅ የሆነ፣ከክርስቲያን ወንድሞቻችሁ ጋር በማኅበራዊ ሕይወት አብራችሁ ደፋ ቀና የምትሉ ፣ለክርስቲያን እህታችሁ በችግሯ ሰዓት ከማንም ቀድማችሁ የምትደርሱ፣የተቸገረ ምስኪን ክርስቲያን ደጃችሁ ቢቆም ዘካ ከመስጠት የማትነፍጉ ደግና ቀናዎች ናችሁና የኢትዮጵያ አምላክ ከክፉ ይጠብቃችሁ። በሕመማችሁና በችግራችሁ ሰዓት ቅዱሱን ጠበል ፍለጋ ከክርስቲያኑ ጋር ቤተክርስቲያን ገብታችሁ በፍቅር የምትጠመቁ፣ስእለታችሁ ሲደርስ ለቁልቢ ገብርኤል ድባብ ዣንጥላና የእጃችሁን አምባር አውልቃችሁ የምትሰጡ እግዚአብሔርን አክባሪ ጨዋ ማህበረሰብ ናችሁ ። ደሴና ከሚሴ፣ ኮምቦልቻና ወልድያ ቤተክርስቲያን ሲታነጽ ድንጋይ ተሸክማችሁ አቀብላችኋል ፣ውሃ ቀድታችሁ አመላልሳችኋል። ልበ ርኅሩሆች ናችሁና በእውነት የኢትዮጵያ አምላክ ዘራችሁን ይባርክ ።በእኛ እና በእናንተ መካከል ያለውን የፍቅር ግንብ ለመደርመስና ሰላማችንን ለማደፍረስ በእምነት ስም ከባዕዳን የወረሱትን ጽንፈኝነትና አክራሪነትን ይዘው በጂኒ መንፈስ የሚሯሯጡትን ሁሉ የመርየም ልጅ አል መሲ ዒሳ ልባቸውን ይመልሰው አሜን። ሙስሊም ወገኖቼ ሆይ! ዛሬ ለእናንተ ታላቁን የምስራች ቃል አድርስላችሁ ዘንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ልቤን ከወትሮው ይልቅ እጅግ አስጨንቆታል ።ይህ ዛሬ የምትሰሙት የምሥራች ነፍሳችሁ የምትጽናናበት፣ መንፈሳቹ የሚያርፍበት፣ መዳናችሁ የሚረጋገጥበት የጽድቅ ቃል ነው። ሁላችሁ እንደምታውቁት የመርየም ልጅ አል መሲህ ዒሳ በድንግልና ተጸንሶ በድንግልና የተወለደ ሞትና መቃብርን ድል አድርጎ በክብር ተነስቶ በእልልታ ያረገ ድንቅ አባት ነው። ክርስቶስን የሚያምኑትና የሚከተሉት ሁሉ ታላቅ በረከትና ሰማያዊ ዋጋ እንደሚያገኙም ቁራአንና መጽሐፍ ቅዱስ በጋራ በግልጽ ይመሰክራሉ። ቁርአኑ እንዲህ ይላል ﻭَﺃَﻣَّﺎ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﻭَﻋَﻤِﻠُﻮﺍ ﺍﻟﺼَّﺎﻟِﺤَﺎﺕِ ﻓَﻴُﻮَﻓِّﻴﻬِﻢْ ﺃُﺟُﻮﺭَﻫُﻢْ ﻭَﺍﻟﻠَّﻪُ ﻟَﺎ ﻳُﺤِﺐُّ ﺍﻟﻈَّﺎﻟِﻤِﻴﻦَ «እነዚያ /የመርየም ልጅ አል መሲህ ዒሳን/ ያመኑትማ መልካም ሥራዎችንም የሠሩት ምንዳዎቻቸውን/ በረከታቸው/ ይሞላላቸዋል፡፡ አላህም በዳዮችን አይወድም፡፡»አል ኢምራን 3፥57 «እነዚያንም የተከተሉህን እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ ከነዚያ ከካዱት በላይ አድራጊ ነኝ፡፡»አል ኢምራን 3፥55 እንግዴህ ልብ በሉ ኢየሱስ ክርስቶስን የሚያምኑትና የሚከተሉት ሁሉ ምንዳዎቻቸው የሚሞላ በትንሣኤ ዘጉባኤ ዕለት ማለትም የሰው ልጆች ሁሉ ለፍርድ በሚቆምባት በመጨረሻይቱ ሰዓት ክርስቶስን የተከተሉ ሁሉ ከካዱት በላይ የክብር ባለቤቶች እንደሚሆኑ ቁርአኑ በግልጽ መስክሯል። እውነት ነው ክርስቶስን የሚያምንና እርሱን በእምነት የሚከተል ሁሉ በነፍሱ ዋስትና አለው ከጨለማም ወደሚደነቅ ብርሃን በክብር ይሻገራል። ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ሲል አስተምሯል ። «ልባችሁ አይታወክ በእግዚአብሔር እመኑ በእኔም ደግሞ እመኑ »ዮሐ 14፥1 «እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ የሚከተለኝ የህይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ።»ዮሐ 8፥12። የተወደዳችሁ ሙስሊም ወገኖቼ ሆይ የመርየም ልጅ አል መሲህ ዒሳ ወደ ዚህች ምድር ያለ አንዳች ዓላማ አልተገለጠም በእግዚአብሔር የዘለዓለም ዕቅድ ውስጥ ለሰው ልጆች የተዘጋጀውን የዘለዓለም ሕይወትና የጽድቅ ትሩፋት በጸጋ ሊያጎናጽፈን ነው።ክርስቶስ ወደ ዚህች ምድር መጥቶ ኢንጅልን/ወንጌልን/ ከመስበኩ በፊት ዓለም በተውራት/በኦሪት/ና በሙሴ ሕግጋት እግዚአብሔርን ደስ በማሰኘት ጽድቅን ለማግኘት ሞክረው ነበር ፤ሆኖም ግን አልተቻላቸውም ሁሉም ከመርገም በታች ነበሩና ጽድቃቸው ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ተቆጥሮባቸው የሰው ልጅ ሁሉ ሲሞት እድል ፈንታውና ጽዋ ተርታው ወደ ሲኦል መውረድ ነበር ።ሆኖም ግን በሰው ልጆች ሐዘንና ስቃይ የማይደሰተው ርኅሩኅና አዛኝ የሆነው ጌታ ዓለምን የፈጠረበትን ቃሉን ወደ ድንግል ማርያም ማሕጸን ልኮ ሰው ሆኖ እንዲወለድ አደረገው እርሱም ዒሳ/ኢየሱስ/ ተብሎ ተጠራ ። የኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም የመምጣትም ትልቁ ዓላማ በሥራቸው መጽደቅ ላልቻሉ የአዳም ልጆች ሁሉ እርሱ የጽድቅ መንገድ ይሆናቸው ዘንድ ነው ።በቁርአኑ አንተን የተከተሉህን ከካዱት በላይ አድራጊነኝ የተባለለትም ለዚህ ነው ።ይህ ከድንግል ማርያም በፍጹም ተዋሕዶ ሰው ሆኖ የተወለደው ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ተብሎ ይጠራል ለምን ቢባል በምድር እናት እንጂ አባት ሳይኖረው በመንፈስ ቅዱስ ድንቅ ግብር በተአምር ተወልዷልና እናቱ ድንግል ማርያም አባቱ እግዚአብሔር ተብሎ ይጠራል ፤ አንድም በልብ ታስቦ በአንደበት የሚገለጥ ቃል ልብ የወለደው የልብ ልጅ ይባላል ።አብ ልብ ነው፣ወልድ ቃል ነው፣መንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ ነው።እግዚአብሔር አንድ ነው። ሙስሊም ወገኖቼ ብዙ ጊዜ ፈጣሪ አይወልድም አይወለድምም ስትሉ እንሰማለን ፤ነገር ግን በደንብ እንድትረዱት የምፈልገው ነጥብ ቢኖር እግዚአብሔር ልጅ አለው ሲባል በሰው የአወላለድ ሥርዓት የሚገለጥ ሳይሆን ከልብ እንደ ሚወለደው ቃል የሚመሰል ነው ።እግዚአብሔር አንድ ነው አብ በልብ ይመሰላል፣ ወልድ በቃል ይመሰላል፣ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ በእስትንፋስ ይመሰላል ሦስት አማልክት ግን አንልም አንድ አምላክ ብለን እናምናለን እንጂ ። ወልድ ከአብ ተወለደም ስንል ቃል ከልብ ተወለደ የማለት ያህል ነው።ለዚህ ነው እግዚአብሔር« ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር» ያለው ሰው ሦስት ነገር አለው ነገርግን አንድ ሰው ይባላል እንጂ ሦስት ሰው አይባልም። እያንዳንዳችን ፣ልብ ፣ቃል፣ እስትንፋስ አለን ግን ሦስት ሰዎች አንባልም አንድ ሰው ነን እግዚአብሔርም እንዲሁ ነው ። አብ ፣ ወልድ ፣መንፈስ ቅዱስ ተብሎ ቢጠራም አንድ አምላክ አንድ ጌታ ነው ።( ስለ ምሥጢረ ሥላሴ ወደፊት በስፋት እንማማራለን።)

  • без подписи

  • 20 мая1 0059

    † የአዲስ ኪዳን ታቦት † ★ ታቦት ማክበር ወንጌል አለመረዳት ነውን?★ ★ የብሉይ ኪዳን ታቦትና የአዲስ ኪዳኑ ለምን ተለያየ ? መ/ር ታሪኩ አበራ #ማሳሰቢያ ይህን ትምህርት ሼር በማድረግ በስህተት ጎዳና ያሉ ወገኖትን ያስተምሩ። ታቦት ቃሉ የግእዝ ሲሆን ትርጓሜውም ማደሪያ ማለትነው።ታቦት በብሉይ ኪዳን ታላቅ መንፈሳዊ አገልግሎትሲሰጥ የቆየ ቅዱስ ንዋይ ሲሆን በሐዲስ ኪዳንም የራሱ የሆነ አገልግሎት ያለው የከበረ መንፈሳዊ የክብር መገልገያ ነው። ይህንን ጽሑፍ ለመጻፍ ምክንያት የሆነኝ አንዳንድ ሰዎች የብሉይ ኪዳን ታቦትንና የአዲስ ኪዳን ታቦትን አንድ አድርገው በማሰብ የአዲስ ኪዳኑ ታቦት ፍጹም ስህተት እንደሆነና መኖርም እንደሌለበት በተሳሳተ ግንዛቤ ሲተቹ ስለተመለከትኩኝ ነው። በጣም ልናስተውለው የሚገባን የብሉይ ኪዳን ታቦትና የአዲስ ኪዳን ታቦት በቅርጽና በይዘት፣በዓላማና በአገልግሎት ፈጽሞ የተለያዩ መሆናቸውን ነው።የብሉይ ኪዳን ታቦት በይዘቱ ትልቅ የሆነና አራት መያዣዎች ያሉት ሲሆን በአራት ሰዎች የሚያዝ ነው።አገልግሎቱ ደግሞ አሰርቱ ትእዛዛት የተጻፈባቸውን ሁለት ጽላቶች ለማስቀመጫነት የሚጠቅም ነው።ታቦት የሚለው ቃል ማደሪያ የሚል ትርጉምንም ያገኘው ከዚሁ ይሰጥ ከነበረው የማደሪያነት አገልግሎት አንጻር የተሰጠ ስያሜ ነው። ይህንን የከበረ የሕግ ማደሪያ(ታቦት) ይሰሩና በወርቅ ይለብጡት ዘንድ ለሙሴና ለአሮን ያዘዛቸው ራሱ እግዚአብሔር ነው።ዘፀ 25፥8 እግዚአብሔር ያለ ዓላማና ያለ ምክንያት አንዳችም ነገር ሰዎች ይሰሩ ዘንድ አያዝም።በዘመነ ብሉይ የታቦቱ መኖር ታላቁ ዓላማ እስራኤላውያን ከግብጽ ወጥተው ወደ ከነዓን ሲጓዙ መንፈስ የሆነውንና በሥጋዊ ዓይን የማይታየውን እግዚአብሔርን በእውነትና በመንፈስ ለማምለክ የእምነት ደረጃቸውና የአምልኮ ልምምዳቸው ገና ስለነበር በሚታየው ታቦት ፊት የማይታየውን እግዚአብሔርን ያመልኩት ዘንድ አዕምሯቸውን የሚያግዝ በፊታቸው የሚያልፍ ፣የሚታይና ግዘፍ ያለው ነገር መኖር ስለነበረበት እግዚአብሔር ታቦት በመካከላቸው ይኖር ዘንድ ወደደ። የሰው ልጅ አእምሮ በሃይማኖት አድጎና በእምነት ጎልምሶ በመንፈስ ማምለክ እስካልጀመረ ድረስ ከኅሊና በላይ ረቂቅ የሆነውን እግዚአብሔርን ለማምለክ በዓይኑ ፊት የሚታዩና የሚዳሰሱ ኅሊናውን ለአምልኮ የሚያግዙ መንፈሳዊ ንዋያት ያስፈልጉታል። በዚህም ምክንያት ነበር የሕጉ ማደሪያ በሆነው በታቦት ላይ የሠራዊት ጌታ ራሱን በክብር እየገለጠ ኃልዎቱን በማሳየት ለክብር የመረጠው ሕዝብ እግዚአብሔር የሚባል አምላክ እንዳለ በእርግጠኝነት እንዲያምንና ለእርሱ በፍቅር እየተንበረከከ የእጆቹን በረከት እንዲመገብ እንዲሁም ከአሕዛብ ጣዖታት ራሱን እንዲጠብቅ ያደርግ የነበረው። " በዚያም ከአንተ ጋር እገናኛለሁ፤ የእስራኤልንም ልጆች ታዝዝ ዘንድ የምሰጥህን ነገር ሁሉ፥ በምስክሩ ታቦት ላይ ባለው በሁለት ኪሩቤል መካከል፥ በስርየት መክደኛውም ላይ ሆኜ እነጋገርሃለሁ።" (ኦሪት ዘጸአት 25:22) ስለዚህም የብሉይ ኪዳን ታቦት የእግዚአብሔር የክብሩ መገለጫ ዙፋንና ኃልዎቱን ማስረጃ የክብር ንዋይ ስለነበር ሕዝቡ ታቦቱ ወዳለበት ወደ መገናኛው ድንኳን እየሄደ በክብር ደመና የሚገለጠውን እግዚአብሔርን በፍቅር ያመልክ ነበር ።በሕዝቡና በእግዚአብሔር መካከል የነበረው ግንኙነትም እንደ አባትና ልጅ የቅርብ ነበር እንጂ እግዚአብሔር መንፈስ እንደ መሆኑ ለሕዝቡ ፈጽሞ ከሕሊናቸው የራቀ አልነበረም። ወደ አዲስ ኪዳን ስንመጣ የአዲስ ኪዳን ታቦት በይዘትና በመጠን በአገልግሎት እና በዓላማ እንደ ብሉይ ኪዳኑ ሳይሆን የከበረውን የክርስቶስ ሥጋና ደም በከበረ ቅዱስ ንዋይ ላይ ለመፈተት የምንጠቀምበት ክቡር ምስዋዕ ነው።በአዲስ ኪዳን እግዚአብሔር ራሱን የገለጠው በአንድ ልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋዌ በኩል ነው ።መልአኩ ለቅድስት ድንግል ከአንቺ የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ብሎ ካበሰረ በኋላ ባሕርያችንን ባሕርይው አድርጎ በአጭር ቁመትና በጠባብ ደረት ተወስኖ በምድራችን በሥጋ የተገለጠው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ከብሉይ ኪዳኑ ታቦት በላቀ ሁኔታ የእግዚአብሔርን ክብር ገልጦልናል፣በአባቱ እቅፍ ያለው የበኩር ልጅ አባቱን ተርኮልናል። የእግዚአብሔርን መኖርና መግቦቱን በግልጽ የክርስቶስ ሰው መሆን ዓለም እንዲረዳው አድርጎታል። ዓይንና ልባችን ወዴትም እንዳያይ ፈጣሬ ፍጥረታት መጋቤ ዓለማት አንዱ እግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ ልባችንን ገልጦ አስተምሮናል። ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለ። " ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ፥ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን።" ዕብ 1፥1 ስለዚህ የብሉይ ኪዳኑን ታቦት ክብርና ዋና ዓላማ ክርስቶስ ኢየሱስ ጠቅልሎ ወስዶታል የእግዚአብሔርን ክብርና መግቦት በልጁ በኩል የበለጠ ተገልጦልናል። " መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው።" (የዮሐንስ ወንጌል 1:18) ሌላው የብሉይ ኪዳን ታቦት አገልግሎት ሕጉ ለተጻፈበት ጽላት ማደሪያ ነበር ዛሬ የአዲስ ኪዳን ታቦት ላይ በየቤተ ክርስቲያኑ ስመ እግዚአብሔር ይጻፍበታል እንጂ አስርቱ ትእዛዛት አይጻፍበትም ምክንያቱም ሕጉን በልባችን ላይ እንደ ሚጽፈው በቅዱስ ቃሉ አስረግጦ ነግሮናል።ክርስትና ደግሞ ከፊደል ሕግ በላይ በመንፈስ ሕግ የምንኖርበት የቅድስና ሕይወት ነው። " እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፥ ሥጋ በሆነ በልብ ጽላት እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው።" (2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3:3) በዚህ በአዲስ ኪዳን ዘመን እግዚአብሔርን በእውነት እና በመንፈስ እናመልካለን ፣በአንድ ልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ያገኘነውን ሕይወትና ጽድቅ በልባችን እያሰብን በኅሊናችን ሕያው ሆኖ የሚኖረውን የእግዚአብሔርን ክብር ለፍጥረት ሁሉ ስናውጅ እንኖራለን። #የአዲስ ኪዳን ታቦት አስፈላጊነት ለምንድነው? የአዲስ ኪዳን ታቦት አስፈላጊነት ለምንድነው?ቢባል መልሱ አጭርና ግልጽ ነው የኃጢአት ሥርየት ያገኘንበትንና ወደ ዘለዓለም ሕይወት የተሻገርንበት የከበረው የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም መፈተቻ አድርገን እንጠቀምበታለን ።ዛሬ በቤተ መቅደስ የሚፈተተው ሥጋና ደም በእለተ አርብ ከፈሰሰው የኪዳን ደም ጋር በእምነት ሕብረት የምንፈጥርበት ስለሆነና ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘለዓለም ሕይወት ያገኛል ያለውን መለኮታዊ ቃል በተግባር የምንፈጽምበት ስለሆነ ለከበረው መንፈሳዊ መስዋዕት የከበረ ቅዱስ መሰዊያ ስለሚያስፈልግ ታቦቱን በክብር እንጠቀምበታለን። « ይህን፡እንጀራ፡በበላችኹ፡ጊዜ፡ዅሉ፥ይህንም፡ጽዋ፡በጠጣችኹ፡ጊዜ፡ዅሉ፡ጌታ፡እስኪመጣ፡ድረስ፡ ሞቱን፡ትናገራላችኹና።ስለዚህ፥ሳይገ፟ባ፟ው፡ይህን፡እንጀራ፡የበላ፡ወይም፡የጌታን፡ጽዋ፡የጠጣ፡ዅሉ፥የጌታ፡ሥጋና፡ደም፡ዕዳ፡አለበት።ሰው፡ግን፡ራሱን፡ይፈትን፥እንዲሁም፡ከእንጀራው፡ይብላ ከጽዋውም ይጠጣ።»1ቆሮ 11፥26

  • አንዳንዶች ‹ታቦት ተሰርቆ ተሸጠ› የሚሉ ዜናዎችን በማራገብ ታቦቱ ኃይል የለውም ሊሉን ይሞክራሉ፡፡ እንኳን የክርስቶስ ስም የተጻፈበት ታቦት ቀርቶ ራሱ ክርስቶስ በሠላሳ ብር ተሸጦ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ እየተተፋበት ፣ እየተደበደበ ተጎትቶ ተሰቅሎ የለምን? ክብር ይግባውና ኃይል የለውም ሊባል ይችላል? ‹‹ታቦቱን ገልጠን እናሳያለን›› ብለው እየፎከሩ ቤተ ክርስቲያንን ያዋረዱ የሚመስላቸው ፣ በታቦቱ እግዚአብሔርን የምታመልከውን ቤተ ክርስቲያን ታቦት ታመልካለች ብለው ያላለችውን በግድ ብላለች ብለው ድርቅ የሚሉ ሰዎች ስናይ ከማዘን ውጪ ምን እንላለን? ቤተ ክርስቲያን ታቦትን የምትሸፍነው ስለሚፈተትበትና ስለሚሠዋበት የጌታችን ሥጋና ደም ክብር እንጂ ቢገለጥ የምታፍርበት ነገር ኖሮ አይደለም፡፡ ቢገለጥ የሚታየው የመድኃኔዓለም ክርስቶስና የቅዱሳኑ ስም ነው፡፡ ጌታዋ ዕርቃኑን በመሰቀሉ ያላፈረች ቤተ ክርስቲያን ስሙ በተጻፈበት ታቦት አታፍርም! የተከበራችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ጽድቅና ድኅነታችን በወንጌል ነው ።በወንጌል ሕይወት እየተመላለስን መንፈሳዊ ትውፊታችንን፣ሃይማኖታዊ በዓላቶቻችንን እና የማንነት መገለጫ ቅርሳችንን አጥብቀን ልንይዝ ይገባል።ዛሬ ሰለጠንን የሚሉት ምዕራባውያን ወንጌልን ተረድተናል በሚል የጀመሩት የአምልኮ ነጻነት መንፈሳዊ ትውፊቶቻቸውን ጠራርጎ አጥፍቶ ዛሬ ላይ እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ትውልዱን ሥርዓት አልባ አድርገውት መንፈሳዊ መዓዛ ተለይቷቸው በመጨረሻም አብዛኞቹ ቤተ መቅደሶች የሚያመልክባቸው ትውልድ ጠፍቶ ወደ ጭፈራ ቤት፣መጠጥ መሸጫና ቡቲክነት እንደተቀየሩ በአውሮፓና አሜሪካ ላይ ዓይናችን እያየ ነው።ትውልዱም እግዚአብሔር የለም በሚል ፍልስፍና ተጠልፎ ለሰይጣናዊ አምልኮ ተጋልጦ ይገኛል። ስለዚህ ሁሉን በሩቅ አጥሮ መያዝ ስለሚገባ አባቶቻችን በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ያቆዩልንን መንፈሳዊ ክብራችንን፣ሥርዓትና አምልኳችንን ሁሉ ጠንቅቀን ልንጠብቅ ይገባል።ክብራችንን እያቀለልን ወንጌል ገብቶኛል ማለት ፍጹም የተሳሳተ አመለካከትና ፍጻሜው የማያምር ሕይወት ነው። አንዳንዶች አለቦታው የሚጠቀስ ጥቅስ በመጥቀስ ታቦት ተሽሯል ሲሉም እንሰማለን ።ይህ የሚያሳየው የግለሰቦቹ በዘመንና በትርጉም ተከፍሎ የሚጠናውን መጽሐፍ ቅዱስ በጥልቀት አለማጥናታቸውን ነው። ቃሉ እንዲህ የሚል ነው። " በበዛችሁም ጊዜ በምድርም ላይ በረባችሁ ጊዜ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በዚያ ዘመን። የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት ብለው ከእንግዲህ ወዲህ አይጠሩም፤ ልብ አያደርጉትም፥ አያስቡትምም፥ አይሹትምም፥ ከእንግዲህ ወዲህም አይደረግም። " (ትንቢተ ኤርምያስ 3:16) ይህንን ቃል በጣም በጥንቃቄ ልናስተውል ይገባል ነብዩ ኤርምያስ በዘመኑ ለነበሩ እስራኤላውያን ይህንን ቃል የተናገረው የሰላም ዘመን መቅረቡን ጦርነትና ስደት ከእነርሱ መራቁን ለማብሰር ነው።እስራኤላውያን በታሪካቸው እንደምናጠናው መከራና ችግር ሲመጣባቸው ታቦቱን አውጡልንና ይዘን እንጓዝ ይሉ ነበር አሁን እንደዚያ የምትጨነቁበት ዘመን አይሆንም ሲላቸው ነው ነብዩ የእግዚአብሔርን የቃልኪዳኑ ታቦት ብለው አይጠሩም ያለው እንጂ ታቦት ጭራሽ አያስፈልግም ለማለት አይደለም። ልብ ካልን ሲጀምር በበዛችሁ ጊዜ በምድር ላይም በረባችሁ ጊዜ ብሎ የሚጀምረው ዘመነ ሰላም እንደ ቀረበላቸው የሚያስረዳ ነው። ደግሞ በጣም ማስተዋል ያለብን ኤርምያስ የነበረው ከክርስቶስ ልደት ስድስት መቶ ዓመታት ቀድሞ ነው ።እስከ ክርስቶስ መወለድ ይህን ሁሉ ዘመን የእስራኤል ሕዝብና ካህናት ያለ ታቦት ኖሩ ብለን ከአምልኮ ውጭ እንደ ነበሩ ማሰብ ትልቅ ስህተት ነው። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ እኛ ነን ስለዚህ ታቦት ማለት ማደሪያ ስለሆነ በዚህ ዘመን አያስፈልግም ይላሉ ይህ ጥራዝ ነጥቅነት ነው። የእኛ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያነትና የሥጋወ ደሙ መፈተቻ ታቦት ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም።ነገሮችን በጥንቃቄ ልንመረምርና ክብራችንን መንፈሳዊ እሴቶቻችንን አጥብቀን ልንጠብቅ ለትውልድም ልናስተላልፍ ይገባል። መንፈስ ቅዱስ ለሁላችንም ትሑት ልቡና ያድለን። እባካችሁ ሰዎች ከተሳሳተ አመለካከት እንዲመለሱ ትምህርቱን ለሌሎችም ሼር አድርጉት። ለበረከት ሁኑ። መ/ር ታሪኩ አበራ

  • 2፡10) በታቦቱ ፊት የሚሰግድ ሰው ለምን እንደሚሰግድ በታቦቱ ላይ የሚጻፈው ይህ ጥቅስ ያስረዳናል፡፡ ምክንያቱ ‹‹ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይሰግዱ ዘንድ›› ስለሚገባ ነው፡፡ የክርስቶስ ሥጋ እንደሚቆረስ ደሙ እንደሚፈስስ የሚያምን ሰው በዚህ መሠዊያ ፊት በፍርሃት ለክርስቶስ ይሰግዳል፡፡ ሥጋ ወደሙን ‹‹ተራ መታሰቢያ ብቻ ነው›› የሚል ሰው ግን በመሠዊያው ፊት እንዲሰግድና መሠዊያውን እንዲያከብር አንጠብቅም፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በታቦቷ ጽፋ ክብር የምትሠጥ የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ልጆች ስለሆንን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡ የታቦቱ ሌላ መጠሪያ የመሠዊያ ታቦት (ታቦተ ምሥዋዕ) የሚል ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ ስለዚህ መሠዊያ ‹‹መሠዊያ አለን በድንኳኒቱ የሚያገለግሉ ከእርሱ ሊበሉ መብት የላቸውም›› በማለት ስለ ሐዲስ ኪዳኑ መሠዊያ ይነግረናል፡፡ (ዕብ. 13፡10) ይህ መሠዊያ በኦሪት ድንኳን የሚያገለግሉ የአሮን ልጆች ከእርሱ ሊበሉ መብት የሌላቸው ለእኛ ክርስቲያኖች ብቻ በመሠዊያው ያለውን ሥጋና ደም እንድንበላ የተሠጠን ታቦተ ምሥዋዕ ነው፡፡ የታቦትን የሐዲስ ኪዳን አገልግሎት ስንናገር የሚቃወሙ ሰዎች ከሚያነሡት ተደጋጋሚ ትችት አንዱ "ታቦት ያላት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ናት›› የሚል ነጥሎ የመምታት ጥረት ነው፡፡ በተለይም የግብፅ ቤተ ክርስቲያንን በመጥቀስ ‹‹ግብፆች ታቦት የላቸውም›› የሚል ንግግር ይዘወተራል፡፡ ለዚህ ጉዳይ እኛ መልስ ከምንሠጥ የራሳቸው የግብፃውያንን ምላሽ ብቻ ማስቀመጥ ይቀልለናል፡፡ ግብፃውያን ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ጋር አቻ የሆኑ ሁለት ንዋያተ ቅድሳት አሏት፡፡ አንደኛው የመሠዊያው ጽላት (ሰሌዳ) /Alter Board/ ሲሆን ሁለተኛው ታቦት /Ark/ ነው፡፡ ቄስ ታድሮስ ማላቲ የተባሉት የቤተ ክርስቲያኒቱ እውቅ ጸሐፊ ‹‹Church The House of God›› በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ ስለ የመሠዊያው ሠሌዳ (Alter Board) አሠራር ሲናገሩ ‹‹ይህ የመሠዊያ ጽላት አንድ መስቀል ወይም ብዙ መስቀሎች ይሳሉበታል ፤ አልፋና ኦሜጋ ተብሎ ይጻፍበታል ፤ ከዚያም መዝ. 86፡1 ላይ ያለው መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው የሚለው የመዝሙረ ዳዊት ቃል ይጻፍበታል፡፡›› ይሉና ስለ አሠራሩ ሲናገሩ ‹‹የግብፅ ቤተ ክርስቲያን መሠዊያው ስለሚሠራበት ቁስ የተደነገገ ሕግ የላትም ፤ እስከ አራተኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ከእንጨት ብቻ ይሠራ ነበር፡፡ ከዕብነ በረድና ከድንጋይም ሊቀረጽ ይችላል፡፡›› ይህንን ካሉ በኋላም እግረ መንገዳቸውን ስለ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦተ ምሥዋዕ ሲናገሩ ‹‹ከእንጨት የሚሠራ ታቦተ ምሥዋዕ እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መሥጠቱን ቀጥሏል›› (Wooden Alters continue in use in the Ethiopian Church at the present time) ብለው ያጠቃልላሉ፡፡ ይህ ስለ መሠዊያ እንጂ ስለ ታቦት አይናገርም፡፡ ስለ ታቦት በእኚሁ ጸሐፊና በቤተክርስቲያኒቱ በኦፊሴላዊ ድኅረ ገጽ ላይ የሚከተለው ተጽፏል። "In the middle of the Alter, there is a wooden box, called in Coptic 'pi totc' which means 'a seat' or 'a throne', and is used as a Chalice- Stand. Usually it is cubicle in shape, about thirty centimetres high and twenty-five centimetres wide, the top is closed with high flaps. The beautiful carving is inlaid with ebony and ivory and is decorated with four small icons. It can be only the Lord in the last supper, St Mary, Archangel Michael, St. Mark and then the patron Saints. It is called 'the Throne' for it represents the presence of the Crucified Lord. Its name also corresponds to the 'Ark of the Old Testament', for it contained the Tablets of Law written with the finger of God to declare God's covenant with man. The new Ark now contains the true Blood of Christ, as the New covenant, that fulfils the Law and the prophets.›› (‹‹ከመሠዊያው መካከል የሚቀመጥ የእንጨት ሳጥን ሲኖር ይህ በኮፕት ቲቶት ተብሎ የሚሠራ ሲሆን ትርጉሙም ‹መንበር› ወይም ዙፋን ማለት ነው፡፡ ጽዋው የሚቆመውም በዚህ ላይ ነው፡፡ ቅርጹ ክበባዊ ሲሆን 13/25 ሴንቲሜትር ነው፡፡ ከላይ በጨርቅ ይሸፈናል፡፡ በጥቁርና ነጭ ኽብረ ቀለማት ያጌጠ ሲሆን አራት ሥዕላት በዙሪያው ይደረጋሉ፡፡ ሥዕላቱ የጌታችን ጸሎተ ሐሙስ ሥዕል የእመቤታችን ፣ የቅዱስ ሚካኤልና የሚታሰበው ቅዱስ ሥዕላት ናቸው፡፡ ‹ዙፋን› ተብሎ የሚጠራው የተሰቀለው ጌታ እንደሚያድርበት በማሰብ ነው፡፡ ይህ ስያሜም ‹ከብሉይ ኪዳኑ ታቦት› ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡ ያ ታቦት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ያደረገው ቃልኪዳን የተጻፈባቸው የሕግ ጽላት ያሉበት ነበር፡፡ አሁን ያለው አዲሱ ታቦት ግን እውነተኛውን የክርስቶስ ደም የያዘ ሲሆን ክርስቶስም ሕግንና ነቢያትን ፈጽሞ አዲሱን ኪዳን የሠጠን ነው፡፡››) http://www.stmarkdc.org/ coptic-sanctuary ይህ ማብራሪያ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ስለ እኛ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ከሠጡት ማብራሪያ ጋር ምንም አይለያይም፡፡ ይህን እንደ ማሳያ ጠቀስን እንጂ ታቦቱ ዑደት ባለማድረጉ እና በሥርዓቱ ይለያያል እንጂ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለሥጋ ወደሙ መሠዊያ ነው ብላ ከምታከብረው ታቦት ጋር በክብርና በአገልግሎት አቻ የሆኑ በቅብዐ ሜሮን የሚከብሩና በመንበር የሚቀመጡ ንዋያተ ቅድሳት በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት አሉ፡፡ ባለንበት ዘመን በሥጋ ወደሙ እውነተኛነት ከማያምኑ ሰዎች ጋር ስለ መሠዊያው አስፈላጊነት በመከራከር ብዙ ጊዜ ሲባክን ይታያል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተጻፈበትን ታቦት ‹ጣዖት› ነው የሚሉ ‹ክርስቲያኖች› እያየን እንደነቃለን፡፡ ‹‹ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይንበርከክ›› ተብሎ የተጻፈበት ‹ጣዖት› እንዴት ይኖራል? ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚል ጣዖት አለ? ወንጌል በላዩ ላይ የተቀመጠበት ፣ በቅብዐ ሜሮን የከበረ ፣ ሥጋ ወደሙ የሚፈተትበት ታቦት እንዴት ጣዖት ተብሎ ይጠራል? አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ተብሎ በሥላሴ ስም የሚቀደስበትን ታቦት ባዕድ አምልኮ ለማለት መድፈር እንዴት ያስደነግጣል፡፡

  • 20 мая1 1188

    አንዳንድ ሰዎች ከእውቀት ማነስ የተነሳ የአዲስ ኪዳኑን ታቦት ሲያጣጥሉና ሲነቅፋ ባልተገራ አንደበትም ጣዖት ነው ሲሉ እንሰማለን ፈጽሞ ስህተት ነው።የከበረው የክርስቶስ ስም የተጻፈበት ታቦት ጣዖት አይባልም።እንኳንስ መንፈሳዊ ምግባችንን ለምንፈትትበት ቅዱስ ምስዋዕ ለሥጋዊ ምግባችን እንኳን ማዕድ የምናስቀምጥበትን ገበታ በክብር እንይዛለን ።የከበረው የክርስቶስ ደምና ሥጋ ለሚቀርብበት ቅዱስ መሰዊያማ የበለጠ ክብር ልንሰጥ ይገባል። ታቦትን ከጣኦት:ብርሃንን ከጨለማ:ክርስቶስን ከቤልሆር መለየት እንደሚገባ ብርሃን ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንቶስ መልእክቱ የነገረን ሲሆን መድኃኔዓለም ክርስቶስም በቅዱስ ወንጌል እንደምናነበው የአባቱ ቤት የእርሱም የጸሎት ቤት ስለሆነች ሸቀጦችን ሲገለባብጥ ታቦት ላይ ግን ይህን አደረገ ተብሎ አልተጻፈም ያዘዘው እርሱ ስለሆነ ነው።2ቆሮ 6፥16 « ያ፡የከበረ፡እንኳ፡እጅግ፡በሚበልጠው፡ክብር፡ምክንያት፡በዚህ፡ነገር፡ክብሩን፡ዐጥቷልና።ያ፡ይሻር፡የነበረው፡በክብር፡ከኾነ፥ጸንቶ፡የሚኖረውማ፡እጅግ፡ይልቅ፡በክብር፡ኾኗልና።» 2ቆሮ 3፥11 አንዳንዶች እኛ ኢትዮጵያውያን ከሌላው የዓለም ማኅበረሰብ ይልቅ በልዩ ሁኔታ ከታቦት ጋር ያለንን ልዩ ሕብረት በመመልከት ሌሎች ሀገሮች የማይጠቀሙትን እናንተ ኦርቶዶክሳውያን እንዴት ትጠቀማላችሁ ይሄ ወንጌልን አለመረዳት ኦሪታዊነት ነው ይላሉ በጣም ስህተት ነው። ታሪክን ወደ ኋላ መለስ ብለን በጥልቀት ልናጠና ይገባል ሌሎች ሀገራት ክርስትናን የተከተሉትና ወንጌልን የተቀበሉት ቀድሞ ከነበሩበት ከጣዖት አምልኮ በሐዋርያት ስብከትና በብዙ ድንቅ ተአምራት ተላቀው ወጥተው ነው ።እኛ ኢትዮጵያውያን ግን ወደ ሕገ ወንጌል የተሻገርነውና ክርስትናን የተቀበልነው ቀድሞ ከነበርንበት ከሕገ ኦሪት ወጥተን ነው።ታሪክ በግልጽ እንደሚያስረዳን ከእስራኤል ቀጥሎ በብሉይ ኪዳን ሕግና መንፈሳዊ ሥርዓት እግዚአብሔርን ስታመልክ የኖረች ብቸኛዋ ሀገር ኢትዮጵያ ነች ።ሌላው ዓለም ጣዖት በሚያመልክበትና በየጋራውና በየወንዙ እንግዳ አማልክትን በሚከተልበት የጨለማ ዘመን የአብርሃም አምላክ እያለች እግዚአብሔርን ታመልክ የነበረች ቅድስት ሀገር ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ነች። ስለሆነም ለታቦት ክብር መስጠታችን ከጥንት ጀምሮ ሲወርድ ከመጣው የአምልኮ ትውፊታችን ጋር የተያያዘ ነው እንጂ እንደ ውሃ ፈሳሽ እንደ እንግዳ ደራሽ የሆነ ዘመን ላይ የተፈጠረ ክስተት አይደለም ። ሌሎች ሀገራት ግን ከጣዖት አምልኮ የመጡ በመሆናቸው እንደ ኢትዮጵያ ያለ ሥርዓት የላቸውም። ይሁን እንጂ አዲስ ኪዳንን ከተቀበሉ በኋላ በየቤተመቅደሳቸው የክርስቶስን ሥጋና ደም የሚፈትቱበት እንደ ታቦት ለመሰዊያነት የሚጠቀሙበት ህየንተ ታቦት /በታቦት ፈንታ የከበረ ንዋይ አላቸው። ልብ እንበል የክርስቶስ ሥጋና ደም መሠጠቱን የሚያምን አንድ ክርስቲያን ይህ የከበረ ሥጋና ደም እንደ ተራ ማዕድ በየቦታው ፣ በየጠረጴዛው ሊቀርብ ይችላል ብሎ ለማሰብ እጅግ ይከብደዋል፡፡ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን ዘመነ ሰማዕታት አልፎ ስደትዋ እስካበቃበት ዘመን ድረስ በሒደት እየተሻሻለ በመጣ የቤተ መቅደስ ሥርዓት የሐዲስ ኪዳኑን መሥዋዕት በክብር ለመሠዋትና ለምእመናን ለማቀበል በቅታለች፡፡ የበግና የፍየል ደም ይሠዋ በነበረበት የኦሪት ዘመን እንኳን ለብቻው ትልቅ መሠዊያ ተዘጋጅቶ ፣ መሠዊያው ተቀድሶ ሰው በማይገባበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በክብር ተቀምጦ ነበር፡፡ በድንኳኒቱ ውስጥ የሚያገለግሉት አሮንና ልጆቹም የተለየ ልብስ ለብሰው የበጉን ደም በመሠዊያው ዙሪያ ባለው ቀርነ ምሥዋዕ (የመሠዊያ ቀንድ) ላይ እየቀቡ ሥርዓቱን ይፈጽሙ ነበር፡፡ ለበግና ለፍየል መሥዋዕት ይህ ሁሉ ክብር ከተሠጠ እንደ በግ ስለ ሁላችን ኃጢአት ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበው የእግዚአብሔር በግ ኢየሱስ ክርስቶስ ፣ እንደ ሊቀ ካህናትነቱ እጁን በመስቀል ላይ ዘርግቶ የሰዋውና ዓለም እንዲድንበት እንካችሁ ብሉ ብሎ የሠጠን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብበት መሠዊያ ምንኛ የከበረ ይሆን? «ጸንቶ፡የሚኖረውማ፡እጅግ፡ይልቅ፡በክብር፡ኾኗል።» 2ቆሮ 3፥11 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሥጋ ወደሙ ‹መሠዊያ› የምትለው ታቦት በቅርጽም ፣ በአገልግሎትም ፣ በክብርም በኦሪት እግዚአብሔር ለሙሴ ከሠጠው ታቦት ጋር አንድ አይደለም፡፡ የቀደመው ታቦት በአራት ካህናት የሚያዝ በውስጡ ጽላት የሚቀመጥበት ሲሆን የአሁኑ ታቦት ግን የጽላት ቅርጽ ያለው ጽሌ (ሰሌዳ) ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሐዲስ ኪዳኑን ታቦት በሦስት ስያሜ ትጠራዋለች - የቃልኪዳኑ ታቦት ፣ ጽላት እና መሠዊያ ብላ፡፡ የቃልኪዳኑ ታቦት የሚባለው እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ስላደረገው ስለ ቀድሞ ቃልኪዳን ሳይሆን ‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው›› ተብሎ ስለተሠጠው እና ‹‹ስለብዙዎች የኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰው የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው›› ብሎ ጌታችን ስለ ሠጠን አዲሱ ኪዳን ነው፡፡ (ማቴ. 26፡ 26-30) የቃልኪዳኑ ታቦት የሚባለው በሥጋ ወደሙ ስለተሠጠን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ታቦት መባሉ ደግሞእግዚአብሔር በረድኤት የሚያድርበት ፣ በሥጋ ወደሙ ደግሞ በአካል የሚገለጥበት ዙፋን ስለሆነ ነው፡፡ ጽላት (ሰሌዳ) የሚባለው ዐሠርቱ ትእዛዛት ተጽፈውበት አይደለም፡፡ የሕግ ሁሉ ፈጻሚ የሆነው የመድኃኔዓለም ክርስቶስ ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚለው የከበረ ስሙ በታቦቱ ላይ ስለተጻፈ ነው፡፡ (ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን /ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ/ ፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ/) አንዳንድ ሰዎች ‹‹የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ከኦሪቱ ጋር አይመሳሰልም!›› ብለው እንደ ትልቅ መከራከሪያ ሲያውጁ ማየት እጅግ ያስገርማል፡፡ አንዴ ‹ኦሪታዊት ነሽ› አንድ ጊዜ ደግሞ ‹‹ለምን እንደ ኦሪቱ አልሆንሽም›› ብሎ ንትርክ ግራ ያጋባል፡፡ የኦሪቱን ያልመሰለው አሁን ያለነው ሐዲስ ኪዳን ላይ ስለሆነና የታቦቱ አገልግሎት የተለየ ስለሆነ ነው፡፡ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ እንዲህ ሲሉ ያብራራሉ ‹‹የኦሪት ጽላት እግዚአብሔር በደመና ተከናንቦ ሙሴንና አሮንን የሚያነጋግርበት ለእስራኤል ብቻ በረድኤት የሚገለጥበት ዙፋን ነበር፡፡ ይህ ግን (የሐዲስ ኪዳኑ ታቦት) የአምላክ ሥጋና ደም የሚፈተትበት ጌታችን ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው ሥጋዬን ብሉ ደሜን ጠጡ እያለ ያመኑትን የሚጠራበት የምሕረት ምሥዋዕ (መሠዊያ) ነው፡፡ ክብርና ስግደትም የሚደረግለት ለዚህ ነው፡፡›› (የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ገጽ 109) በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት በታቦታቱ ሁሉ ላይ የተጻፈው ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚለው የመድኃኔዓለም ክርስቶስ ስም ነው፡፡ በተጨማሪም የእግዚአብሔር ኅቡዕ ስሞች ታቦት ላይ ይጻፋል አልፋ፣ወዖ፣ቤጣ ፣የውጣ ፣ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው የሚሉ ምሥጢራዊ ትርጉም ያላቸው ስሞች ይጻፋሉ።ታቦት ሲወጣ በአክብሮት እጅነስተን የምንበረከከው ከስሞች ሁሉ በላይ ለሆነው ታላቅ ስም ነው። ከስሙ ጋር ደግሞ በሁሉም ታቦታት ላይ የሚከተለው ጥቅስ በግእዝ ተጽፏል፡፡ ‹‹ከመ ለስሙ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይስግድ ኲሉ ብርክ ዘበሰማያት ወዘበምድር›› ‹‹ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ›› የሚል ነው፡፡ (ፊልጵ.

  • 15 мая1 7302

    ሥሉስ ቅዱስ በአብርሃም ቤት ገብተው ደስታና በረከት እንዳደሉት በእኛም ቤት እንዲገቡ እንደ አብርሃም በሦስት ነገር ለእግዚአብሔር እንታዘዝ። ትምህርቱን ከፍተው ያድምጡ https://youtu.be/-YODz5KD3_4?si=EseyfnFF8aMR_vI2

  • 5 мая2 1501

    https://youtu.be/TOYSZFnUOw0?si=rUL6ekc4TVwxXYAG

  • 21 апр.2 4201

    https://youtu.be/WnYzWhmpYlg?si=V3RrF_ILiA0ox6So

  • 19 апр.2 3502

    Holy Trinity Ethiopian Orthodox Church in Atlanta

  • 19 апр.2 3402

    без подписи

  • 11 апр.2 5802

    https://youtu.be/_xavcTi3Hvk?si=D-cJGmeMXzlI0Bmw