tgindex
የአብነት ት/ቤት

የአብነት ት/ቤት

Статистика

በኢ/ኦ/ተ/ቤ ልዩ ልዩ የአብነት ትምህርቶች የሚሰጡበት ምኅላፍ (ቻናል) ነው። ትምህርቶቹም፡ በድምፅ፣ በምስል ወድምፅ፣ በጽሑፍ፣ በመጻሕፍትና በመሳሰሉት ይዘቶች ይቀርባሉ። የመወያያ ቡድን @abenet_online_group Contact @getAbnet

Последний пост
16 мар.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
14 612
−29 за 5 дн.
Сутки
−2
−0,01%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
6 760
19 постов
Вовлечённость
46,3%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • የአብነት ት/ቤት pinned «https://youtu.be/YBxvajOdjSk?si=JiMcHJKyAdZvtIlO»

  • 15 мар.4 43594

    https://youtu.be/YBxvajOdjSk?si=JiMcHJKyAdZvtIlO

  • 6 янв.6 6004

    без подписи

  • 6 янв.6 5804

    без подписи

  • 6 янв.5 845324из janderebaw_media

    без подписи

  • ምስባክ ዘመስከረም ፲፩ ዘሠርክ(ሰንበተ ክርስቲያን)

  • 20 сент. 2025 г.10,2 тыс91

    ግጻዌ ዘመስከረም ፲፩ ዘሠርክ(ሰንበተ ክርስቲያን)

  • ምስባክ ዘመስከረም ፲፩ ዘቅዳሴ(ሰንበተ ክርስቲያን)

  • ግጻዌ ዘመስከረም ፲፩ ዘቅዳሴ(ሰንበተ ክርስቲያን)

  • ምስባክ ዘመስከረም ፲፩ ዘነግህ(ሰንበተ ክርስቲያን)

  • ግጻዌ ዘመስከረም ፲፩ ዘነግህ(ሰንበተ ክርስቲያን)

  • 20 сент. 2025 г.7 561149из DnHaileRaguel

    በነገራችን ላይ ሁለቱን (ሥዕሏንና መስቀልን) የጋራ የሚያደርጋቸው ነገር አለ፤ መስቀል የክርስቲያኖች መለያ ምልክት ነው። ይኸውም ነቢዩ ዳዊት:- ❝ለሚፈሩህ ምልክት ሰጠኻቸው፡፡❞ ብሎ ነግሮናል፡፡ መዝ ፶፱፥፬። በአንጻሩ ደግሞ እመቤታችንም የክርስቲያኖች መለያ ምልክት ናት፤ ነቢዩ ኢሳይያስ:- ❝እነሆ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ ድንግል ትፀንሳለች፣ ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።❞ በማለት ነግሮናል:: ኢሳ ፯፥፲፬። (አንድም): መስቀል ዙፋኑ እንደሆነ እመቤታችንም ዙፋኑ ናት፤ በመስቀል ካሣ እንደተፈጸመ በእመቤታችንም ካሣ ተፈጽሟልና። መስቀሉ የቃል ኪዳን ማጽኛ እንደሆነ እመቤታችንም የቃል ኪዳን ማጽኛ ናትና። (አንድም): መስቀል፣ ኪሩቤልና ማርያም ወዳጅ ቃላት ናቸው። ለምን ቢሉ:- - ፫ቱም የፊደላቸው ብዛት ፬ ነው። - ፫ቱም አምላክን ተሸክመዋል። መስቀሉ በተሰቀለ ጊዜ፣ ኪሩቤል መንበሩን በመሸከማቸው፣ ድንግልም በጸነሰችው ጊዜ። - የእመቤታችን ግን ይለያል፤ ፪ቱ በኅድረት (በማደር/አድሮባቸው) ሲሸከሙት፣ የእርሷ ግን በኩነት (በመሆን፣ ከስጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ በመንሳት) ነው። ለዚህም ነው ከቅዱስ ኤፍሬም ጋር ሆነን በእሑድ ውዳሴ ማርያም:- ❝ ... አንቺ ከኪሩቤል ትበልጫለሽ...❞ የምንላት። - አባ ጽጌ ድንግልም ❝ዝንቱ መስቀል መንበረ ነበልባል ለኪሩቤል ቢፅ — መስቀል የእሳት (የመለኮት) መንበር የኪሩቤልም ወዳጅ ነው❞ ይላል። (፪/፪) ዲ/ን ኃይለራጉኤል

  • 20 сент. 2025 г.4 6931414из DnHaileRaguel

    ጼዴንያ ማርያም መስከረም ፲ ጼዴንያ በምትባል ሀገር ሥጋ የለበሰች ከምትመስል ሥዕል ላይ ከሠሌዳዋ ቅባት እየተንጠፈጠፈ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች የእመቤታችን የድንግል ማርያም ተአምር የተገለጠበት ቀን ነው:: ይህቺን ሥዕል የሣላት ወንጌላዊ ሉቃስ ነው:: ስንክሣሩ እንደ መዘገበው ወደ ጼዴንያ ሀገርም የመጣችበት ምክንያት ቤቷንም ለእንግዳ ማደሪያ ያደረገች ስሟ ማርታ የምትባል አንዲት ደግ ሴት ነበረች። እመቤታችን ድንግል ማርያምን እጅግ ትወዳት ነበር በሚቻላትም ሁሉ ታገለግላት ነበር:: ከዕለታት አንድ ቀን ስሙ ቴዎድሮስ የሚባል መነኵሴ ከእርሷ ዘንድ በእንግድነት አደረ፤ በመልካም አቀባበልም ተቀበለችው በማግስቱም ስትሸኘው:- ❝አባት ሆይ የምትሔደው ወዴት ነው?❞ አለችው፤ እርሱም:- ❝ልሰግድ ወደ ቅድስቲቱ ሀገር ወደ ኢየሩሳሌም❞ አላት። እርሷም:- ❝ከእኔ ገንዘብ ወስደህ የእመቤታችንን ሥዕል ገዝተህ አምጣልኝ❞ አለችው፡፡ እርሱም:- ❝በራሴ ገንዘብ ገዝቼ በአመጣሁልሽ ጊዜ ገንዘቡን ትለጪኛለሽ❞ አላት፡፡ ከዚያም በኋላ ያ መነኵሴ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ተባርኮ ሥዕሏን ሳይገዛ ረስቶት እየተመለስ ላለ፤ በጎዳናው ላይ:- ❝ሰማይ ሩቅ አደራ ጥብቅ እንዲሉ አደራህን ለምን ዘነጋህ? ሥዕል መግዛትህን ለምን ረሳህ?❞ የሚል የሚያስደነግጥ ቃልን ሰማ፤ ደንግጦ ወደ ገበያም ተመልሶ ላሕይዋና መልኳ ያማረና የተወደደ የሆነ የእመቤታችን ማርያምን ሥዕል አግኝቶ ገዛት፤ በሐርና በንጹሕ ልብስም ጠቀለላት። በጎዳናም እየተጓዘ ሳለ ከሚያስፈራ ዱር ውስጥ ወንበዴዎች ተነሡበት ሊሸሽም ወደደ፤ ከዚያችም ሥዕል:- ❝መንገድህን ሂድ!❞ የሚል ቃል ወጣ፤ የተከተለውም ሳይኖር መንገዱን ተጓዘ፡፡ ሁለተኛው ነጥቆ ሊበላው አንበሳ ተነሣበት ያን ጊዜም ከዚያች ሥዕል የሚያስፈራ ድምፅ ወጥቶ እንበሳውን አባረረው:: አባ ቴዎድሮስም ይህን ሁሉ ድንቅ ተአምር ባየ ጊዜ:- ይህቺን ሥዕልማ አሳልፌ ለሌላ አልሰጥም ብሎ ወደ ሀገሩ ሊወስዳት ወደደ፤ ግዛልኝ ላለችው ሴት ይሰጣት ዘንድ ፈጽሞ አልፈለገም:: ከዚህም በኋላ በመርከብ ተሳፍሮ በሌላ አቅጣጫ ሲጓዝ ታላቅ ነፋስ ተነሣበት ወደ ማርታ ሀገር ወደ ጼዴንያም ሳይወድ በግድ ወሰደው ከመርከብም ወርዶ ከብዙ እንግዶች ጋር ወደዚያች ሴት ቤት ገባ ማንነቱንም አልገለጠላትም እርሷም አላወቀችውም፡፡ በማግሥቱም ተደብቆ ወጥቶ ወደ ሀገሩ ሊሔድ ሲል የቅጽሩ መውጫ ደጃፍ ተሰውሮበት ከአጥሩ ጋር ሲታገል ዋለ፤ በመሸም ጊዜም ወደ ማደሪያው ተመለሰ፡፡ ያቺም መበለት ባየችው ጊዜ ትገረም ነበር፤ እንዲህም ሆኖ እስከ ሦስት ቀን ኖረ በመሸ ጊዜ በሩን ያየዋል፤ አሁን ግን በሩ አይጠፋኝም ብሎ በነጋ ጊዜ መሔድ ቢፈልግ የበሩ መንገድ ተሠወረበት፡፡ ያቺም መበለት ነገሩ ቢደጋገምባት ጊዜ ያዝ አድርጋ:- ❝አባቴ ሆይ አእምሮህ ተነክቷልን? ስትቅበዘበዝ አይሃለሁና ምን ሆነህ ነው?❞ አለችው። ከዚህም በኋላ ከዚያች ሥዕል የሆነውን ሁሉ ነገራት ራሱንም ገለጠላት:: ያቺንም ሥዕል ሰጣት ተቀብላም የተጠቀለለችበትን ልብስ ፈታች፤ ወዝ ከሥዕሏ ሲንጠፈጠፍ አገኘች:: ከደስታዋም ብዛት የተነሣ የዚያን መነኵሴ እጆቹንና እግሮቹን ሳመች። ከዚህም በኋላ ያቺን ሥዕል ወደ ጸሎት ቤቷ ወስዳ በታላቅ ክብር የምትቀመጥበትን አዘጋጅታ አኖረቻት፤ ማንም እንዳይዳስሳትም የነሐስ መስኮትን ሠራችላት፤ በቀንና በሌሊትም የሚበሩ መቅረዞችን በፊቷ ለቀለች። ከመቅረዞችም ውጭ የሐር መጋረጃን ጋረደች። ከሥዕሊቱ በታችም እየተንጠፈጠፈ የወዝ ቅባት የሚጠራቀምበት ከዕብነ በረድ የተሠራ ወጭት አኖረች፣ ያም መነኵሴ እስከሚሞትበት ቀን ድረስ የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ሥዕል እያገለገለ ኖረ:: የሀገሩም ሊቀ ጳጳሳት የዚያችን ሥዕል ዜና በሰማ ጊዜ ከኤጲስ ቆጳሳትና ከካህናት ከሕዝቡም ሁሉ ጋር መጥተው አዩአት:: በሰሌዳዋም ውስጥ ሥጋ የለበሰች መስላ አገኙዋት ከዚህ ከአምላካዊ ግብር የተነሣ አደነቁ፤ ከዚያም ቅባት ቀድተው ለበረከት በተካፈሉ ጊዜ ወዲያው በወጭቱ ውስጥ ይሞላ ነበር። ወደ ሌላ ቦታም ሊወስዷት በፈለጉም ጊዜ ታላቅ ንውጽውጽታ ሆኖ ብዙዎች በድንጋጤ ወደቁ፤ ሥዕሊቱም እስከ ዛሬ በዚያች ሀገር ትኖራለች:: ኢትዮዽያዊው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም ተሰምቶ በማይጠገበው በመልክዐ ሥዕል ድርሰቱ:- ❝ሰላም ለሥዕልኪ ሐፈ ማኅየዌ። በጼዴንያ ወግብፅ ዘአውኀዘት በኢሕሳዌ። ለመጸብሐዊ ማቴዎስ ማርያም እንተ ረሰይኪዮ ወንጌላዌ። ይኩነነ ወትረ ጸሎትኪ እምዘመነ ኵሉ ምንሳዌ፡፡ ዓቃቤ ዘመዓልት ወዘሌሊት ሀላዌ — በጼዴንያና በግብፅ ያለ ሐሰት ፈዋሽ ወዝን ላፈሰሰ ሥዕልሽ ሰላምታ ይገባል:: ቀራጭ ማቴዎስን ወንጌላዊ ያደረግሽው ማርያም ሆይ ጸሎትሽ ከጥፋት ዘመን ሁሉ ዘወትር የመዓልትና የሌሊት ቋሚ ጠባቂ ይሁነን::❞ (+) ❝ሰላም ለሥዕልኪ ቦ ጊዜ ዘትትናገር፡፡ ወቦ ጊዜ ዘትክዑ ደመ ተአምር፡፡ ማርያም ስብሕት ወውድስት እመ እግዚአብሔር፡፡ ለማትያስ ሙቁሕ ወለያዕቆብ ውጉር፡፡ እስመ አንቲ ሞገሶሙ በሰማይ ወምድር — ለሥዕልሽ ስላምታ ይገባል፡፡ ሥዕልሽም የምትናገርበት ጊዜ አለ፤ የተአምር ደም የምታፈስበት ጊዜ አለ፣ ፈጽሞ የተመስገንሽ የእግዚአብሔር እናት ማርያም ሆይ ለታለረ ለማትያስና ለተወገረ ለያዕቆብ በሰማይና በምድር ሞገሳቸው አንቺ ነሽ።❞ (+) ❝ሰላም ለሥዕልኪ እንተ ሠዐላ በእዱ፡፡ ሉቃስ ጠቢብ እምወንጌላውያን አሐዱ፡፡ አመ ተቀብዑ ማርያም እምአፈ ሥዕልኪ ቅብዐ ናርዱ፡፡ በሕማም እኩይ እለ ደወዩ ወውኅዱ፡፡ ፅዑራነ ዓለም ጥዕዩ ወጥቀ ፈድፈዱ — ከወንጌላውያን አንዱ የሆነ ጥበበኛ ሉቃስ በእጁ ለሣላት ሥዕልሽ ሰላምታ ይገባል። ማርያም ሆይ ከሽቱ ቅባት ከሥዕልሽ ወዝ የታመሙና በምድር የተጨነቁ በተቀቡ ጊዜ ዳኑ እጅግም በዙ።❞ — ሲል በሚያስደንቅ ሁኔታ አንስቶ ስለዚህች ተዓምረኛ ሥዕል ጽፎላታል። በቅድስት ቤተክርስቲያናችንም ዕለት ዕለት ከኪዳን በፊት በሚደረሰው መልክዐ ሥዕል ቀሳውስቱ ከዲያቆናቱ አዝማች እየተቀባበሉ ያዜሙታል። ስለዚህ ሥዕላ መንፈሳዊ ኀይል ከመጎናጸፋቸው በተጨማሪ ታሪክን ያቆያሉ በወቅቱ የተከሠተውን ድርጊት በሚገባ ያሳያሉ ያስተምራሉ:: ይህን ታሪክ ከመስቀሉ ጋር ቅዱስ ያሬድ በድጓው አዘክሮታል:- ❝አብርሂ አብርሂ ማርያም መስቀሉ ለወልድ እንዘ ትትሞጥሒ ጽዮን ዮም ተፈሥሒ መስቀል ረድኤት ወሕይወት መስቀል አንቅዕት ለጽሙዓን መስቀል አብርሀ ለጻድቃን ዝንቱ ውእቱ መስቀል በአማን ዕፁበ ያቀልል በጽንዓ ኀይል ወበሠናይ ምግባር በዕፀ መስቀሉ ኀጢአት ይሠረይ እስመ ረከብነ ሕይወተ በመስቀልከ በዕፀ መስቀልከ ክቡር ዘአዕበይኮ ለስምከ — የወልድ መስቀል ማርያም ሆይ አብሪ ወርቅን የተጎናጸፍሽ ጽዮን ሆይ ዛሬ ደስ ይበልሽ፣ መስቀል ረድኤትና ሕይወት ነው፤ ለተጠሙት የሕይወት ምንጭ ነው፤ መስቀል ለጻድቃን አበራ፣ ይህ መስቀል በእውነት ዕፁብ ድንቅ ነው፣ በጽኑዕ ኀይል ጭንቀትን ያቀላል፤ በበጎ ምግባርም ያጸናል፣ በመስቀሉ ኀጢአት ይሠረያል! በመስቀልህ ሕይወትን አግኝተናል፤ በዕፀ መስቀልህ ስምህን ከፍ ከፍ አደረግኸው።❞ በማለት እመቤታችንንና ቅዱስ መስቀልን በጋራ አመሰግኗል፡፡ (፩/፪) ⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️

  • без подписи

  • без подписи

  • ምስባክ ዘነሐሴ ፳፩ ዘነግህ

  • ግጻዌ ዘነሐሴ ፳፩

  • ምስባክ ዘነሐሴ ፲፰ ዘሠርክ(ሰንበተ ክርስቲያን)

  • ግጻዌ ዘነሐሴ ፲፰ ዘሠርክ(ሰንበተ ክርስቲያን)

  • ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ከዚህ ይጀምራል👉🏾👉🏾Link👈🏾👈🏾@abenet_online@abenet_online@abenet_online