Adhanom Mitiku / አድኃኖም ምትኩ
Статистика- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 4
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 955
- 1/48двое суток
- 1 094
- 1/72трое суток
- 1 180
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
አንዳንዱ አይሆንም ብለን የጣልነውን፤ አልፈልገውም ብለን የገፋነውን ተንከባክቦ ያስወድደዋል። አንዳንዱ ፀልየን ያጣነውን፤ ሽተን ያልተቸረንን አግኝቶ ያራክሰዎል። የሶሊያና ሰርግ ላይ ተገኝቼ ድብርት እየናጠኝ ነው። የደበረኝ ቀኑ ዱካካም ስለሆነ ነው!! የደበረኝ እሁድ ስለሆነ ነው!! ትራፊክ ፖሊስ አርብ ለ'ታ ስለቀጣኝ ነው!! የደበረኝ ስለደበረኝ ነው... ግን... ሶልያና እንዲህ ደርባባ ነበረች !? ስትስቅ እንዲህ ደስ ትላለች !? የፊቷ ቀለም እንዲህ ያምራል !? ሶልያናን ምኗን ነበር ያልወደድኩት?? እኔንጃ!! ሶልያና አማራጭ እንዳላት አላውቅም ነበር? መውደዷ ስስት አልነበረውም፤ ሙላቴ ላይ ነው የምታተኩረው፤ ችስታነቴ አሳስቧትም፥ አሳታውሰኛም አታውቅም። ሶልያና አሪፍ ነበረች !! ፍቅሯ ጥበብ ስላልነበረው ነው !? በጣም ስለፈለገቺኝ የምታንሰኝ መስሎኝ ነው!? ትዳር ስለምፈራ ነው !? ዝምብ'ሎ ስለሆንኩኝ ነው!? ለምን ሶልያናን እኔ አላገባኋትም? ለምን የኔ እንድትሆን ልቤ ተመቀኘ? አእምሮዬ ምን አባቱ ሆኖ ነው ይቺ ሶልያና ያቺ ሶልያና እንደሆነች ያልገለፀልኝ?? ካልተከለከልኩ ውድነትን፥ ውበትን መመልከት አልችል ይሆን?? 'ልጅ እያለሁ አማኑ ዛሬን ብቻ ነው የሚያየው' ይል ነበር አባቴ። አባቴ ስለሆነ አዝኖልኝ ነው እንጂ ዛሬንም በደንብ ማየት አልችልም። ዛሬን በደንብ ያ'የ ነገ ይታየዋል ኣ !! የአሸነፍነው በመሰለን ውጤት ላይ መውደቅ ደስስ አይልም !! ሶልያናን ስታገባ ጠብቄ ወደድኳት። ባሏ ሲያስጠላ፥ እሷ ስታስጠላ፥ እድምተኛው ሲያሽቃብጥ ሲያስጠላ ... ቀስ ብዬ ከስርግ አዳራሹ ወጣሁ.....አወጣጤ እና ሁኔታዬ ከለቅሶ ቤት ይመስል ነበር ... በርግጥ .....ሰፍራ ብቻውን ውጤት አይቀይርም!! © Adhanom Mitiku
без подписи
без подписи
በመኖር በኩል መፅሃፋችን እውቀት የሚለው part እንዲ ተተውኖል❤ enjoy❤
без подписи
ዛሬ ማታ 12:30 ጀምሮ እምንወዳቸው ሰዎች ተሰባስበዋል ስለመፅሃፎቻቾን እንጨዋወታለን ። ቆንጆ ምሽት ይኖረናል ሰዓታችሁን አመቻችታቹ ከስር ባለው ሊንክ በኩል ጎራ በሉልን 🙏❤
https://www.youtube.com/live/7SRDr8vKT7E?si=m2RFPYwA-1n4qL5q
без подписи
“ምነው አምና በሞትኩ፥ እንዲያ እንዳማረብኝ!?” ዝምታ ይረብሸኛል። ለዚያም ነው፥ መንገድ ስሔድ መጽሐፍ ይዤ የምዞረው፣ ሁሌም ጆሮዬ ውስጥ ‘ኤርፎን’ የምወትፈው፣ ልተኛ ስል፥ ያለችውን ፀጥታ እንኳን ላለማስተናገድ፥ የኾነ ነገር ከፍቼ ነው የምተኛው ... በዝምታ ውስጥ ከመኾን፥ ዝም ብሎ ከሚቀደደው ቱሪናፋው ከቤ ጋር ብውል እመርጣለሁ። ዝምታ ሽሽት የማልደውልበት፣ የማላነበው፣ የማልሰማው ዜና የለም። ዝምታ እፈራለሁ! መንገድ ስሔድ… ስቀመጥ! የማነበው መጽሐፍ ካልያዝኩ፣ ስራመድ የምሰማበት ኤርፎን ካልወተፍኩ…. ፖሊሶች አቻኩለው ከቤት አስወጥተውኝ ነው የሚሆነው! ዝምታ እፈራለሁ! አስታውሳለሁ፤ 12ኛ ክፍል ነበርኩ። ሙዚቃ ከፍቼ እያጠናሁ፥ የአጎቴን የለቅሶ ሳግ ሰምቼ ደንግጬ “ምነው አመመህ?” አልኩት፤ እሱ ሙዚቃ እየተጫወተበት ያለውን ‘ቴፕ’ ዐየት አድርጎ፥ ወደ ጣርያው አፍጥጦ፣ እምባው ቁልቁል ወረደ! አሞት መስሎኝ ነበር… ከዚህ በፊት ሲያመው ያቃስታል፤ ሲብስበትም ማስታገሻ ይውጣል እንጂ አያለቅስም ነበር። አጎቴ ጥቁር ነው፤ ፊቱ ክስክስ ያለ… ሲያወራ ግን እንደሚታየው ኮስተር ያለ ማንነት እንደሌለው የሚያስታውቅበት፥ ቁጥብ፣ ደስ የሚል ሰው ነው። ልጅ እያለሁ የገዛልኝን ቼኮሌት እና ብስኩት፥ ታሞ አልጋ ሲይዝ ሲጋራ እያመጣሁ ክሼዋለሁ ። ቤቢ፥ “ያቺን ነገር አትገዛልኝም?” ይላል፤ እገዛለታለሁ። ሲጋራውን በእጁ እያገላበጠ ካያት በኃላ፥ አፉ ላይ እንዳለ እለኩሰለታለሁ። ዐብሮን ማንም በሌለበት ጊዜ ሁሉ፥ “አትብላ” የተባለውን፣ “አትንካ” የተባለውን ሁሉ እሰጠው ነበር። እያጠናሁ ስለነበረ፣ ሲያለቅስ አይቼው ስለማላውቅ፣ ደንግጬ ስለነበረ፣… ዘፋኟን ባውቃትም ግጥሙን አላጤንኩትም ነበር፤ ዘፈኑ እንደረበሸው ሲገባኝ፥ ወተት እንደገነፈለበት ሰው፥ ስበር ሔጄ የቴፑን ሶኬት ነቀልኩለት ። የማባብልበት መንገድ ስለጠፋኝ፥ “ምግብ ላምጣልህ?”፤ “ውሃ ላምጣ” አልኩት። ጣርያ ጣርያ ዕያየ ዝም ሲለኝ ከፊቱ ዞር አልኩለት። በዚያው ሰሞን፣ ሲብስበት ሐኪም-ቤት ደግመው አስገቡት፤ አልቆየም፤ ሞተ! የኾነ ቀን ... አባቴ፥ ስለወንድሙ ቸርነት፣ ዘናጭነት፣ ስፖርተኛነት፣ ሰው ወዳድነት፣ አለኝታነት፣ ስለጓደኞቹ ብዛት፣… ሲተርክልኝ ያስለቀሰቺው ዘፋኝ፥ የዝና ነጋሽ ትዝ አለቺኝ። ያስለቀሰውን የዘፈን ካሴት ከፈትኩት፤ ሆዱን ያባባው “ገዳሙ” ዘፈን ጋ ደረስኩ። እስክስታ ሚያስመታ ‘ሪትም’ ያለው ዘፈን ነው “.........አሆዬ እኔ ላንተ ብዬ፣ መጣሁኝ ጠቅልዬ አዬዬ፥ እኔ ላንቺ ብዬ፥ መጣሁኝ ጠቅልዬ “እሀሀ ገዳሙ፥ አሀሀ ገዳሙ እሀሀ ገዳሙ፥ አሀሀ ገዳሙ “አላስኬድ፣ አላስኬድ አለኝ፥ ይሄ ጫማ እኔም ልበቢስ ነኝ፥ ቢመክሩኝ አልሰማ “እሾህ ብቻ ኾኖ፥ እግሬን ብዳብሰው እንዴት መራመጃ፥ መሔጃ ያጣል ሰው? “ኧረግ እናናዬ፣ አረግ እናናዬ ኧረግ እናናዬ፣ አረግ እናናዬ “አሄ አሄ አሄ አሄ አሄ ኡሁ “ይወዘውዘኛል፥ ይወዝውዝ አባቱ እህል አሸክሞኝ አርጎኝ ጎረቤቱ አሞኝ፣ አሞኝ ውሎ፥ አሞኝ ሊያድር ነወይ? እህል ሰርቶ መብላት፥ ጤና ላይሆን ነወይ? “ምነው አምና በሞትኩ፥ እንዲያ እንዳማረብኝ መለየት በሽታ፥ እንዲ ሳይጠናብኝ “ያመኝ የነበረው፥ አያመኝም ተውኩት ያስታማሚ ነገር ሲቸግር አየሁት “እህህህ ገዳሙ ጠይሙ፣ ጠይሙ..........” ይላል ከዛ ቀን በኋላ፥ ተረጋግቼ ሥራዬ ብዬ ሰምቼው ዐላውቅም፤ ነገር ግን ሁሉም ስንኞች ልቤ ውስጥ በአግባቡ ከመሰነድ አላዳነኝም ድንገት ከተከፈተ፥ የሚረብሸኝ ዘፈን ኾነ .... “ድል ስቀዳጅ፣ ደስ ብሎኝ ስጠጣ፣ እንዳማረብኝ ግደለኝ አስታማሚ ሳታሳየኝ!” ማለት ጀመርኩ። “ያደረ የዋለ በሽታ አትሰጠኝ” እለው ጀመር “ይህ ዘፈን ምን ያህል ይረብሽሃል?” ስባል “ከዝምታ በላይ!” ማለት ጀመርኩ። የግጥሙ ኀይል ነው፥ ወይስ የአጎቴ ኹኔታ ሕይወትን እንድፈራት ያደረገኝ? ሕይወትን ምን ያህል ባካብዳት ነው፥ እያሸነፍኩ እንኳን “ምነው አምና በሞትኩ፥ እንዲያ እንዳማረብኝ…” የምትል ስንኝ የምታሳድደኝ? ፈሪ ሰው እንዲህ ነው፤ ከ ጠ’መንጃ በላይ ፥ ቃል ያሳድደዋል! © Adhanom Mitiku
የፊታችን ቅዳሜ ከ 12:30 ጀምሮ ከምወደው ከ Tewodros Tsegaye ጋር ቆንጆ ቆይታ እናደርጋለን ። ፕሮግራሙን በቀጥታ መከታተያ ሊንክ አስቀምጣለሁ ❤🙏 ኑልን❤
без подписи
እመንገድ ላይ አየኋት ። ወፍራለች ፣ ጡቷ እንድድሮው አይደለም ። ቦርጫም ሆናለች፣ ትልቅዬ የጭቃ መከላከያ ጫማ ተጫምታለች ልጅ አቅፋለች ። ብዙ አመት አብረን ተንዘላዝለን ተጨቃጭቀን .. ተዋደን ... ተዳርተን... ተማምተን፣ ተሳስበን ሙሉ ቀን ተጠፋፍተን ምነው የት ጠፋህ የት ጠፋሽ ተባብለናል ። ተለያየን ብለን ታርቀናል ፣ተበዳድለን ይቅርታ ተባብለናል ትክዝ አልኩ ፦ ልጅነቷ ውስጥ ልጅነቴ ነበር። ጠረኗ ውስጥ ትዝታዬ ተወሽቋል ። እንድተለያየን ሁለት ወር ሳንቆይ ከኔ ጋ እያለች ከሚጀነጅናት ጋ መሰለኝ አብራው መኖር ጀመረች አራት ወር እንደቆዩ ተለያዩ ሲጣሉ አርግዛ ነበር መሰለኝ ብዙ ሳትቆይ ወለደች ልጁም የሱ ነው ተባለ ። ምን አለ ልጁ የኔ ቢሆን ...! አባትህ እንዲ መጥቶ፣ ሰርቶ ፣ሄዶ ፣በድሎኝ፣ ጠቅሞኝ፣ ገለመሌ እንዲ ሆነን ተጣብሰን ተዋደን ብዙ ግዜ ቆይተን ገለመሌ ትላለች እኔም የልጄ እናት እንዲ አድርጋ እንዲ ሄደን፣ ወጥተን ወርደን እንዲ አቶድም እሷ እንዲ ናት እያልኩ ለልጄ እነግረው ነበር ። ምን አለ እኔጋ እያለች ሙሉ እንድሆንላት ተመስጣ ባትደምር ባትቀንስ ፣ ምናለ እኔስ ባልፈለሳሰፍ ዝም ብዬ ገፋፍቼ አታልዬ አስርግዣት ቢሆን ። ህፃን ልጅ አቅፋ ጎስቁል ብላ ልጅነቷን በልጇ ተሸሽጋ እየሸኘችው ነው ። ውዱን ጊዜያችንን አብረን ነበርን ። ምን አለ ያቀፈችው ልጅ ከኔ ቢሆን፣ ምን አለ ያረገብኩት ጡቷ በኔ ልጅ ምክንያት ቢወድቅ ። ልጇ እሷን አይመስልም። ምን አለበት ሌላው ይቅር ልጆ እሷን ቢመስል ። ውድድ ...ሳምምም... እቅፍፍ ...ባደርገው ። አብሮነታችን ምንም ቋሚ የሚናገር ነገር ሳይገነባ አለፈ ። እሷ ግን ታድላ መኖርያ ምክንያት አገኘች ። በድርበቡ ሰላም ብያት ልጆን እጁን ስሜው አይን አይኖን እያየሁ ከላይ ከላይ ካወራን ቀጥሎ "ለኔም ውለጂልኝ" አልኳት ሳቀች ሳቋ ውስጥ ልጅነቷ ወጣ ፣ በማርያም.... እ....?🙏 ስለት አሳዘንኳት መሰለኝ ፊቷ ቅር አለው፣ "በዚህ ልጅ የበላውት ፍዳ ብታቅልኝ ኖሮ.... "አለች መንገዷ አባጣ ጎርባጣ እንደነበረው ብዙ ነገሯ ይናገራል ግዴለም ሁን ያለው ነው የሚሆንው ።እኔም ስንት መከራ ሳይገለኝ ምሮኛል ፣ሰንት ሞት አምልጫለሁ መጥፎ ነገር ብቻ የሚያልፈኝ በእውነቱ እኔ ማነኝ?! ባይልልን ነው ! © Adhanom Mitiku
ሁለቱም መፅሀፋችን ፥ በአማዞን "አዎ! እሱ ጋ ያመኛል!" https://a.co/d/0e0zLEXY በመኖር በኩል https://a.co/d/0cxJAyE6
без подписи
без подписи
ልደት ❤ ዓመቱ ውብ ነበር። ደስታ ያልተለየው ጉዞ ነበር። "ድንቅ አድርጎልኛል የሠራዊት ጌታ" የሚለውን መዝሙር በየሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ....ስምንት ሰዓት እየዘመርኩ ጎረቤቶቼን ሳልረብሽ አልቀረውም። እንኳን ጎረቤቶቼ አልሆናችሁ።🤗 መኖር ደስ ይላል፤ ነገ የተሻለ ይመጣል ብሎ መሥራት ደስ ይላል። ይቅር ማለት ደስ ይላል። በአሸናፊ ወዳጆች መከበብ፣ ድላችን በሚያስፈነጥዛቸው ወዳጆች መታጀብ ደስ ይላል። የሚመርቁንና የሚጸልዩልን ወላጆች ማየት። የማንወደው ላይ አለማተኮር። ደስታን ችላ አለማለት፣ ድልን ማጣጣም፣ ችግር ላይ ክችች አለማለት ደስ ይላል። በልደት ቀን እንኳን ተወለድኩ ማለትም ደስ ይላል። መልካም ልደት Adhanom Mitiku ባልተያያዘ ዜና፤ ሁለቱም መጻሀፋችን በአማዞን ገበያ ላይ ከዛሬ ጀምሮ ማግኘት ይቻላል ። ለጥቂት ጊዜ ገበያ ላይ ያልነበረው መጽሐፋችን "አዎ እሱ ጋ ያመኛል" ለ9ኛ ጊዜ፣ "በመኖር በኩል" ደግሞ ለ5ኛ ጊዜ ዛሬ ለገበያ ቀርቧል። ችርስ ለደስታችን❤
በመኖር በኩል https://a.co/d/0iQ8DWY7
ደስታ ❤ ከዛሬ ጀምሮ መፅሀፋችን በመኖር በኩልን አማዞን ላይ ያገኙታል
без подписи