ጤናዎ በእጅዎ /Your Health on your Hands❤/
Статистика- Последний пост
- 11 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 9
- Всего постов
- 29
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 825
- 1/48двое суток
- 945
- 1/72трое суток
- 1 019
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የጤና ባለሙያነት በዓለም ላይ እጅግ አደገኛ ከሆኑ የሥራ ዘርፎች ወይም ኢንዱስትሪዎች ቀዳሚው ነው። የሥራው አደገኝነት ደግሞ በቀላሉ የሚለካ አይደለም። ለምሳሌ ያህል፣ በዋናነት የሚጠቀሱትን ጥቂቶቹን ልጥቀስ፦ 👉ረጅም እና አስጨናቂ የሥልጠና ዓመታት፦ ዶክተር ወይም ሌላ የጤና ባለሙያ ለመሆን የሚጠየቀው ረጅም ዓመታት የሚፈጅ እና አድካሚ የትምህርትና የልምምድ ሂደት። 👉ረጅም የሥራ ሰዓታት፦ ያለ እረፍትና ያለ እንቅልፍ ለ36 ሰዓታት እና ከዚያ በላይ አልፎ አልፎም ከዚያ ለሚበልጥ ጊዜ የሚቆይ የሥራ ሰዓት። 👉የተገደበ ማህበራዊ እና ቤተሰባዊ ሕይወት፦ በበዓላት፣ በሳምንት መጨረሻ (ዊኬንድ) እና በምሽት የሥራ ተረኝነት (ዲዩቲ) ምክንያት የሚፈጠር የጊዜ እጥረት። 👉ተላላፊ ለሆኑ በሽታዎች የመጋለጥ ዕድል፦ ከታካሚዎች ወይም ከሆስፒታል አካባቢ በቀጥታ ወደ ባለሙያው ሊተላለፉ የሚችሉ እና ለሞት ሊዳርጉ የሚችሉ እንደ ሄፓታይተስ ቫይረስ፣ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ፣ ሳንባ ነቀርሳ (ቲቢ) እና መድኃኒት ለለመዱ (MDR) የሆስፒታል ተላላፊ በሽታዎች መጋለጥ። 👉ከባድ ኃላፊነት እና ጫና፦ በከባድ ሁኔታ የታመሙ ሰዎችን በአስጨናቂ የሥራ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ የመንከባከብ ከፍተኛ የሥነ-ልቦና ጫና እና ኃላፊነት። 👉የአእምሮ ጤና መቃወስ፦ ለረጅም ጊዜ የሚከማች የሥራ ጫና ለከባድ ድብርት (Major Depression) እና ለሌሎች የአእምሮ ሕመሞች ሊዳርግ መቻሉ። 👉ራስን የማጥፋት አደጋ፦ በተለያዩ ጥናቶች እንደተረጋገጠው፣ በጤና ባለሙያዎች ዘንድ ራስን የማጥፋት አጋጣሚ ከሌሎች ሙያዎች በበለጠ ከፍተኛ ሆኖ መገኘቱ። ስለሆነም፣ በሲቪል ሰርቪስ አዋጅ መሠረት የሚከፈለውን የጤና ባለሙያዎች የትርፍ ሰዓት (የዲዩቲ) ክፍያ እና የሥራ ላይ አደጋ አበልን መቀነስ ወይም መገደብ ፍጹም ፍትሃዊ አይደለም። የሚመለከታቸው አካላት በሕግ የተደነገገውን እና የጤና ባለሙያዎች እንደ ካሳ ሊያገኙት የሚገባውን ጥቅማጥቅም ተግባራዊ ሊያደርጉ እና ሊከፍሉ ይገባል። ይህ ካልሆነ ግን፣ ተነሳሽነታቸው በቀነሰ እና በድብርት ውስጥ ባሉ የጤና ባለሙያዎች ምክንያት ለህዝባችን የሚሰጠው የጤና አገልግሎት ጥራት በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳል።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
#ሪማቶይድ #አንጓ #ብግነት (rheumatoid arthritis) ሪማቶይድ አንጓ ብግነት የሰውነታችን በሽታ የመከላከል ህዋሶች በራሳቸው ላይ በሚያደርሱት ጉዳት የሚፈጠርና በመላው አካል የሚሰራጭ የብግነት በሽታ ሲሆን መገለጫውም በአንድ ጎን የሚከሰት የእጅና የእግር አንጓ ብግነት ነው ቀስ በቀስም አንጓዎችን ከጥቅም ውጪ የሚያደርግ በሽታ ነው። ከመገጣጠሚያ በተጨማሪ ሳንባን ፣ደምን፣ ቆዳንና የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን የሚያጠቃ ነው። በአብዛኛው ሴቶችን የሚያጠቃ ሲሆን በየትኛውም የዕድሜ ክልል የሚፈጠር ነው። የሚያሳየው ምልክቶች ☘ ከአምስት በላይ በአንድ ጎን ያሉ አንጓዎች ህመም 👉 የአንጓ እብጠት 👉 ጠዋት ሲነሱ ሰውነትን ማጠፍ አለመቻል 👉 የመገጣጠሚያ እንቅስቃሴ መቀነስ ☘ የድካም ስሜት ☘ አጠቃላይ የጡንቻ ህመም ☘ የክብደት መቀነስ 🍏 ከመገጣጠሚያ ውጪ ሲከሰት 👉 ሳል ፣ የትንፋሽ ማጠር፣ የደረት ህመም 👉 የአይን እንባ መድረቅ፣ የዓይን ህመምና መቅላት 👉 ቆዳ ላይ እብጠት፣ መጥቆርና መቅላት 👉 የእግርና እጅ መደንዘዝ 🍏🍏🍎 የሚታዩ ምልክቶች🍏🍎🍏 👉 እብጠት 👉 ሲነካ ምንም 👉 የመገጣጠሚያ ጉዳት 🍏🍎🍏የሚሰጡ ምርመራዎች🍎🍏🍎 ✍ ምርመራው በአብዛኛው ከታካሚው በሚወሰደው ተረክ እና ሀኪሙ በሚያየው ምልክቶች ይለያል በተለይ ከሌሎች የአንጓ ብግነት የሚለየው የጣቶቻችን የመጨረሻውን አንጓ ባለማጥቃቱ ነው። ✍ የላብራቶሪ ምርመራ ማድረግ (rheumatoid factor, anti -CCP , ESR/CRP, CBC) ✍ ራጅ ምርመራ 🍏🍎🍏 የሚሰጡ መድኃኒቶች 🍎🍏🍎 ✍ የህመም ማስታገሻ ✍ የሪማቶይድ መድኃኒቶች ፈጽሞ ያለሀኪም ትዕዛዝ መወሰድ የለባቸሁም ምክንያቱም የጎንዮሽ ጉዳታቸው የከፋ ስለሆነ ከዛም ባሻገር ክትትል በየጊዜው መደረግ አለበት። 🍏🍎 ሪማቶይድ አንጓ ብግነት ያለበት ሰው ምን መመገብ የለበትም 🍎🍏 👉 አልኮል መጠጣት የለበትም 👉 ቀይ ስጋ 👉 ቅባት የበዛበት ምግብ 👉 ለስላሳ 👉 የእንስሳት ተዋጽኦ ( ወተት ፣ እርጎ ፣አይብ) 👉 ጨው የበዛበት ምግብ 👉 ስንዴ ገብስ እና 👉 በፋብሪካ የተቀናበረ ምግብ መውሰድ የለበትም።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
#የዓይን_መቅላት_መንስኤዎችና_ምልክቶች ===== 👉 የአይን መቅላት የተለመደና የብዙ ሰው ችግር ነው የአይን መቅላት አይን ውስጥ ያሉ የደም ስሮች ወደ ላይኛው የአይን ክፍል በተለያዩ ምክንያቶች ተለጥጠው (dilated) በሚወጡበት ወቅት ይፈጠራል፡፡ 👉 #የዓይን መቅላት ገጽታ ሊለያይ ይችላል። ✍️ በነጩ የዓይን ክፍላችን ላይ ሮዝ ወይም ቀይ መስመሮች ያሉ ይመስላሉ ወይም ሙሉውን ሮዝ ወይም ቀይ ሆኖ ሊታይ ይችላል። ✍️ #ምልክቶች ➥ የአይን መቅላት ➥ ማሳከክ ➥ አይን ማዝ መያዝ ➥ ዉሃ የመሰለ የአይን ፈሳሽ( እንባ መብዛት) ➥ ማቃጠል ➥ ድርቀት ➥ ህመም ➥ ብርሃን አለመቻል ➥ የዓይን ብዥታ ✍️ #መንስኤዎቹ ➥ ለፀሐይ ብርሃን ከመጠን በላይ መጋለጥ ➥ የዓይን መድረቅ ➥ የዓይን አለርጂዎች ➥ የዓይን ብግነቶች (conjunctivitis) ➥ የአየር ብክለት ➥ የተለያዩ ጭሶች ➥ ደረቅ አየር ➥ አቧራ ➥ የኬሚካል ተጋላጭነት ➥ ለእረጅም ሰዓት ስክሪኖችን መጠቀም ➥ በሃኪም ያልታዘዙ የዕይታ መነፅሮችን መጠቀም ✍️ #የዐይን መቅላት ካለብዎት የሚከተሉትን ይጠንቀቁ ➥ ዓይን አለማሸት ➥ ችግር ያለበት ዓይን ነክቶ ሌላኛዉን ዓይን አለመንካት ➥ አለርጂ ካለብዎ የአይን መዋቢያዎችን አለመጠቀም ➥ ምንም ዓይነት የባህል የዓይን መዳኒት አለመሞከር ➥ በሃኪም ያልታዘዘ ምንም አይነት የዓይን ጠብታ አለመጠቀም ➥ አለርጂ ከሚሆኑቦት ነገሮች መራቅ