Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)
Статистика- Последний пост
- 12 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 5
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 407
- 1/48двое суток
- 466
- 1/72трое суток
- 503
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
без подписи
“በ2019 በጀት ዓመት የ13.4 ቢሊዮን ዶላር የወጪ ንግድ ገቢ እቅድን ለማሳካት በትኩረት ይሰራል” - ክቡር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) (አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክቡር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ከወጪ ምርት ላኪዎች ጋር በ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምና በ2019 ዕቅድ ዙሪያ ሰፊ ውይይት አካሂደዋል። ክቡር ሚኒስትሩ በመክፈቻ ንግግራቸው ወቅት እንደገለጹት፣ የወጪ ንግድ ዘርፉ በበጀት ዓመቱ ሀገራዊ የማክሮ-ኢኮኖሚ መረጋጋትን ለማምጣት ከፍተኛ እምርታ ነው። ለዚህ ውጤት መመዝገብ ላኪዎች ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን የጠቀሱት ክቡር ዶ/ር ካሳሁን፣ በቀጣይም የኢትዮጵያን ምርቶች በዓለም አቀፍ ገበያ በጥልቀት ለማስተዋወቅ በቁርጠኝነት እንደሚሠራ ገልጸዋል። በመድረኩ ላይ እንደተገለጸው፣ ኢትዮጵያ በ2018 በጀት ዓመት ከጠቅላላ የወጪ ንግድ ከ11.2 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ ማግኘት የቻለች ሲሆን፤ ይህም የዕቅዱን 119.14% ያሳካ የላቀ አፈጻጸም ነዉ። በ2019 በጀት ዓመት የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ይበልጥ ለማሳደግ የ13.4 ቢሊዮን ዶላር የወጪ ንግድ ግብ የተቀመጠ ሲሆን፣ ይህንን ለማሳካትም በሥራ ሂደት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታት ስምምነት ላይ ተደርሷል። እቅዱን እዉን ለማድረግም ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ላኪዎችን በመደገፍና አመቺ ሁኔታዎችን በመፍጠር በትኩረት እንደሚሰራ ክቡር ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ በውይይቱ ወቅት ከተሳታፊ ላኪዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን፣ ክቡር ሚኒስትሩ ሰፊ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል። ክቡር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) መድረኩን ሲያጠቃልሉም ለ2019 በጀት ዓመት ስኬታማነት ሰባት ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችን ያስቀመጡ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል ምርቶችን በብዛት ከመላክ ባለፈ እሴት በመጨመርና ጥራትን በማረጋገጥ ተወዳዳሪ መሆን፤ ነባር ገበያዎችን ከማጠናከር ጎን ለጎን አዳዲስ ዓለም አቀፍ የገበያ መዳረሻዎችን መፈለግ፤ የወጪ ንግድን በዘመናዊ ዳታና ዲጂታል አሰራር በመደገፍ መምራት የሚሉት ይጠቃሳሉ፡፡ ይህ የውይይት መድረክ በላኪዎችና በመንግሥት መካከል ያለውን የጋራ ግንኙነት ይበልጥ ያጠናከረና ለ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ስኬታማነት ትልቅ መነሳሳትን የፈጠረ መሆኑ ተመልክቷል። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር https://web.facebook.com/share/p/1DHUvN82DE
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
ኮርፖሬሽኑ የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበረከተለት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባለፈው በጀት ዓመት የክረምት በጎ ሥራዎች ላይ ተሰማርተው ለከተማው አቅመ ደካማ ነዋሪዎች ከፍተኛ ድጋፍ ላደረጉ ተቋማት ባዘጋጀው የምስጋና እና እውቅና መርሀ ግብር ላይ የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽንን የእውቅና የምስክር ወረቀት በመስጠት አመስግኗል፡፡ ኮርፖሬሽኑ ከመደበኛ ስራው ጎን ለጎን ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይም ይህን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል::
без подписи
የሕንጻ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
ኮርፖሬሽኑ ሰሚት በሚገኘው ለሚ የገበያ ማዕከል ውስጥ የከፈተው ሱፐር ማርኬት በቻናል 1 የቴሌቪዥን ጣቢያ ሲቃኝ ይምጡ! ይጎብኙ! ይሸምቱ!
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
የኮርፖሬሽኑ አመራርና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አካሄዱ እንደ ሀገር 800 ሚሊየን ችግኞች የሚተከሉበት የዘንድሮው የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን አመራርና ሰራተኞችም በዚህ ታሪካዊ ቀን የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ቃሊቲ በሚገኘው በኮርፖሬሽኑ የቡና ማደራጃና ማዘጋጃ ማዕከል አካሂደዋል፡፡ የችግኝ ተከላውን መርሃ-ግብር ያስጀመሩት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በኃይሉ ንጉሴ እንኳን ለዚህ በአንድ ጀንበር 800 ሚሊየን ችግኞች ለሚተከሉበት ታሪካዊ ቀን አደረሳችሁ በማለት እንደ ሃገር ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ ኢኒሺዬቲቭ አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለማሳካት ከፍተኛ ጥረት መደረጉን ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም እንደ ኮርፖሬሽን ባለፉት ዓመታት የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ሲካሄድ መቆየቱን በመጥቀስ በዛሬው ቀንም በኮርፖሬሽኑ እና በቅርንጫፍ ማዕከላት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ አክለውም ችግኝ ከመትከል ባለፈ ዋናው ተግባር መንከባከብና እንዲጸድቁ መከታተል በመሆኑ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ አስገንዝበዋል፡፡ ዛሬ በሃገር አቀፍ ደረጃ ከሚተከሉት 800 ሚሊየን ችግኞች ውስጥ እስከ 60 በመቶ የሚይዘው የማንጎ፣ ፓፓያ፣ አቮካዶና ቡና ችግኝ ነው፡፡ ይህም ኮርፖሬሽኑ ለገበያ የሚያቀርባቸው የግብርና ምርቶችን መጠንና ጥራት በማሳደግ ረገድ የጎላ አዎንታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረውይጠበቃል::
без подписи