የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር-Amhara Fano Unity in Gonder
Статистика👉ይህ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የቴሌግራም ገጽ ነው። 💪ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
- Последний пост
- 15 апр. 2025 г.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ቀን፦ሚያዝያ 07/2017 ዓ.ም ከአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር፦ የጥቁር አንበሳ ክፍለ ጦር ምስረታን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ አብይ አሕመድ መራሹ ብልጽግና ለ27 ዓመታት ያህልበኢሕአዴግ መንግሥት ተጸንሶ፣ ተወልዶና አድጎ የአማራንሕዝብ ማጥፋት መንግሥታዊ መርኁ አድርጎ ከ6 ዓመታትየተሻገረ ማንነት ተኮር የዘር ጭፍጨፋ ፈጽሟል። ከምንምበላይ ደግሞ ላለፉት አንድ ዓመት ከ8 ወር በመላው የአማራክልል የሀገሪቱን ጦር አዝምቶ የአማራን ሕዝብ በማንነቱ ዘሩንየማጥፋት ተግባሩን አጠናክሮ መቀጠሉን ተከትሎ አማራውራሱን አደራጅቶ በትጥቅና በስንቅ የደረጀውን ወታደራዊአደረጃጀት በሁሉም መስክ እያፍረከረከ የፖለቲካ መዋቅሩንእያፈራረሰ ለኅልውናው መረጋገጥ ውድ ሕይወቱን አስይዞብርቱ ትግል ላይ መሆኑ ይታወቃል። ሥርዓቱ በአማራ ጥላቻ የሰከረ፣ በእብሪት ያበደ፣ በትዕቢትየተወጠረ ቢሆንም አሁን ላይ በዓለም አደባባይ በሥነ ልቡና፣በውጊያ፣ በፖለቲካ እና በሚዲያም ጭምር የሽንፈት ካባመከናነቡን ተከትሎ የመጨረሻ እድሉን በሁሉም ዘርፍ ሙከራላይ ነው። የአብይ አሕመድ ከውድቀት መትረፊያ ሙከራዎችደግሞ ፖለቲካዊ መፍትሔዎች ላይ ያተኮሩ ሳይሆኑ ግልብነትን፣ግብዝነትን፣ አላዋቂነትን በይፋ የሚያሳዩ ከምንም በላይመንግሥታዊ መዋቅሩ በጽኑ ደዌ ውስጥ መሆኑን አጉልተውየሚያሳዩ ማንጸሪያዎች ናቸው። የአማራ ፋኖ የሕዝባችንን ኅልውና በዘላቂነት ለማረጋገጥ ቀጠናዊ አደረጃጀቶችን እየፈጠረ በድል እየገሰገሰ ይገኛል። የተበታተኑ አደረጃጀቶችን በመሰብሰብ አመች የመታገያ መንገዶችን መፍጠር አስፈላጊ ነው። ፋኖ በአንድ በኩል አፈሙዙን፣ በሌላ በኩል አደረጃጀቱን እየፈጠረ መጓዝ የየዕለት ተግባሩ ነው። ለዚህ ማሳያ የሚሆነው ጎንደር ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የብርጌድ አደረጃጀቶችን በክፍለ ጦር ማዋቀርና መጠርነፍ ለትግሉ የጎላ አስተዋጽኦ አለው። በዚህ መሠረት ዛሬ የመሠረትነው የጥቁር አንበሳ ክ/ጦርን የመሠረቱት ብርጌዶችና ሻለቃዎች 1ኛ. ሸማቂው ብርጌድን 2ኛ. ድል በር ብርጌድን 3ኛ. ንሥር ብርጌድን 4ኛ. ወርቅአምባ ብርጌድን 5ኛ. ራስ አሞራው ውብነህ ብርጌድ እና 6ኛ. ደቦል ሻለቃ በመሥራችነት የያዘ ሲሆን የሚከተሉት የሥራ አሥፈጻሚ አመራሮችንም መሰየም ተችሏል። 1. ወታደራዊ አዛዥ..አርበኛ አንተነህ ብርሃን 1 ምክትል አዛዥ ልባርግ ሙላት 2 ፓለቲካ መሞሪያ : እሸቱ ፉቃዱ 3 ዘመቻ ሙምሪያ : አትርሳው አወቀ 4 ም/ ፓለቲካ መምሪያ :አለምሰገድ ደጉ 5 ህዝብ ግንኙነት: ናትናኤል ሙሉአለም 6 የሰው ሃይል ሀብት : ሀብቴ ጥጋቡ 7 ም/የሰው ሃይል ሀብት: ወዳጀ አንባቸው 8 አደረጃጀት : ቴድሮስ ታርቆ 9 ስልተና ክፍል : ደስታው ጥጋቡ 10 ም/ስልተና ክፍል : ሳሙኤል ጌታቸው 11 ቀተናዊ ትሰሰር : ጋሻው ጌታሁን 12 ምክትል ቀጠናዊ ትስስር …ገብርየ ጎሳ 13 ፋይናን ክፍል ….ወንዳል ሀይሌ 14 ም/ ፋይናንስ…ተስሁን ጥጋቡ 15 ሎጀስቲክ : አማኑኤል መልሰዉ 16 መረጃ እና ደህንነት ???? 17 ም/መረጃ እና ደህንነት??? እናሌሎች የክፍለ ጦር ኃላፊዎችና ምክትል ኃላፊዎችን በመሰየም ክፍለ ጦራችንን አቁመናል። የጥቁር አንበሳ ክፍለ ጦር በአጠቃላይ ጠላት ያቀደው የኅልውና ታጋዩን እየነጠለ ከፍተኛ ቁጥርባለው ሠራዊት ለመምታት፣ ፋኖን በትኘዋለሁ የሚል የበትኘዋለሁፕሮፓጋንዳ የመሥራት ፍላጎቱን ያፈረስንባቸው፣ ከፍተኛ የትጥቅቁሳቁሶችን የታጠቅንባቸው፣ በወራሪ ሠራዊቱ ላይ የውጊያየበላይነትን የወሰድንባቸው፣ የሥነ ልቡና ስብራትን ያደረስንባቸውየድል የአሸናፊነት ውጊያዎች አድርገናል፤ እንደ ዘመቻ አንድነት የመሰሉ ድንቅ ተናባቢ ወታደራዊ ኦፕሬሽኖችን ጭምር የመከወን ተግባራችንን በተለያዬ ብርጌድም ውስጥ ሆነንም አስደናቂ ተልዕኮዎችን ፈጽመናል። ከምንም በላይ በቀጠናው በኩታ ገጠም ከሚገኙ ክ/ጦሮች ጋር ጓዳዊ አንድም መዋቅራዊ ቅንጅቶችን በመፍጠር የጀመርነውን ጠላትን ረፍት የመንሳትና የመደምሰስ ተግባራችንን በተጠና፣ በታቀደና በተቀናጀ መንገድ እንደምንፈጽም ጽኑ እምነታችን ነው። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር፦ ጥቁር አንበሳ ክ/ጦር ጎንደር፣ አማራ፣ ኢትዮጵያ/// https://t.me/fanozgonder
без подписи
ሦስተኛው ኮር በጎንደር ተመሰረተ💪 ከአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር፦ ራስ አሞራው ውብነህ (፫ኛ ኮር) የኮር ምሥረታ መግለጫ በአርበኛ ሀብቴ ወልዴ የሚመራው የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር አደራጃጀቱን እያሰፋና እያዘመ 3ኛ ኮሩን “ራስ አሞራው ውብነህ” ኮር በሚል ስያሜ መሰረተ፡፡ እንደሚታወቀው የአማራ ሕዝብ ስርአት መር በሆነ መንገድ እያፈናቀለው እየገደለው ከቤት ንበረቱ ከእምነቱ ከዕርስትና ማንነቱ እየነቀለው ከዚህም አልፎ የመኖር ያለመኖር የህልውና ትግል ተጋርጦበት ይገኛል፡፡ ስለሆነም የአማራ ሕዝብ በአማራ ፋኖ መሪነት ከላይ ከተገለጹት ችግሮች ለመውጣት ከጓድ እስከ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር እንደ ተቋም ሆኖ ሁለንተናዊ ተጋድሎ እያደረገ ቆይቶ በዚህ ጊዜ ከክፍለጦር ከፍ ያለ ከአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር መሀከል አገልግሎት እንዲያሳልጥ አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ በሰሜን ቀጠና የሚገኙ 6 ክፍለጦሮችን ወደ አንድ ኮር ገብተው እዝና ሰንሰለቱን ጠብቀው እንዲንቀሳቀሱ ራስ አሞራው ውብነህ ኮር ተመስርቷል፡፡ ራስ አሞራው ውብነህ ኮርን የመሰረቱ ክፍለጦሮች 1.ሰሜን አምባ ራስ ክፍለጦር 2.ጭና ክፍለጦር 3.ድብ ጠለምት ክፍለጦር 4.ደጃች አያሌው ብሩ ክፍለጦር 5.ራስ ደጀን ክፍለጦር 6.ሰሜን ክፍለጦር የራስ አሞራው ክፍለጦር እንዲመሩ ከታች የተዘረዘሩት ስራ አስፈጻሚዎች ተመርጠዋል ሰብሳቢ ፡ እባቡ ካሳ ም/ሰብሳቢ ፡ ወርቁ ሙሉ ወታደራዊ አዛዥ ፡ ይርጋ ክቡሬ ፖለቲካና ማህበራዊ ጉዳይ ፡ ዮሀንስ ተመመ ጽ/ቤት ኃላፊ ፡ መምህር አብርሃም እያሱ ሕ/ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ፡ ጻዲቁ ዋለልኝ ወታደራዊ አስተዳደር ፡ ጌትነት መሳፍንት ዘመቻ ኃላፊ ፡ መቶ አለቃ አምላኩ ጌታቸው አደረጃጀት መምሪያ ኃላፊ ፡ ማርሸት ዘውዱ የሕዝብ አስተዳደር ፡ ጌታቸው ጌጡ ሎጄስቲክ ፡ ንጋት ሰሙ ቀጠና እና ትስስር ፡ ወልዴ ሲሳይ ሕግና ስነምግባር መምሪያ ፡ ለምለሙ ደርቦ ስልጠና መምሪያ ኃላፊ ፡ እያያው ተዘራ መረጃና ደህንነት፡------- ኅልውናችን በተባበረ አንድነታችን!!! የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር፦፫ኛ (ራስ አሞራው ውብነህ) ኮር ጎንደር፣አማራ፣ኢትዮጵያ https://t.me/fanozgonder
🔥#ዘመቻ_አንድነት_የጎንደር_ግንባር_ድሎች‼️ በሁሉም የአማራ ግዛቶች መጋቢት 10/2017 ዓ.ም የተጀመረው የፋኖ ወታደራዊ ማጥቃት በጎንደር ግንባር አንፀባራቂ ድሎችን አስገኝቷል። ከተጀመረ 3ኛ ቀኑን ባስቆጠረው ዘመቻ አንድነት የጎንደር ግንባር.... 3ኛ ቀን ረፋድ 4:00 ሰዓት ድረስ የተገኙ የአውደ ውጊያ ድሎች መካከል የሚከተሉት በተጨባጭ ተሳክተዋል። 🔸በማዕ/ጎንደር ዞን የምስ/ደንቢያ ዋና መቀመጫ ቆላድባ ከተማን በመቆጣጠር መሽጎ የነበረውን ጠላት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ጀብዱ የፈፀሙት የአፋአጎ የታድሎ ብርሃን ክ/ጦር ሲሆን በጎንደር ከተማ ቅርብ ርቀት በተመሳሳይ ጥቃት ማድረስ ልዩ ስሙ ጉንብሪት በሰፈረ ጠላት ላይም የታድሎ ብርሃን ክ/ጦር አካል ሻለቆች ጥቃት አድርሰዋል።በዚህም በድምሩ ከ31 በላይ ሙት ከ18 በላይ ጠላት ቁስለኛ የሆነበት ድል የተመዘገበ ሲሆን ቆላድባ ከተማን ነፃ መሆኗም ተረጋግጧል። 🔸 በማዕከላዊና ሰሜን ምዕራባዊ የጎንደር ቀጠና በተከታታይ ቀናት በደረሰበት ምትና የአፋአጎ ወታደራዊ ቁመና በመገምገም ቀጠናውን ቸቆ ለመውጣት የወሰነው የጠላት ሀይል የሚከተሉት ከተሞችን በመልቀቅ ሲፈረጥጥ የወገን ሀይል ከተሞችን ተረክቧል። *ታች አርማጭሆ ወረዳ ሙሴባምብ፣ኩርቢ፣ማሂን፣ዋሊያ፣እርጎየ፣ጅንግር ከተሞች በዘመቻ አንድነት ነፃ ሁነዋል። *በማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ዳንጉራ ፣ታጉርና ሞገሴ ከተሞች ከጠላት ነፃ ሁነዋል። *በጠገዴ ወረዳ ሰጋሉና አዴት ከተሞች በዘመቻ አንድነት በወገን ቁጥጥር ስር የገቡ የጎንደር ግንባር ከተሞች ሲሆኑ ህዝቡ ሰራዊታችን በደስታ እየተቀበለ ይገኛል። *በሰሜናዊ ጎንደር ቀጠና የአዳርቃይ ወረዳ አዳርቃይ ከተማና ዛሪማ ከተማ አቅራቢያ በተደረገ ማጥቃት ጠላት ሙትና ቁስለኛ ሁኖ ለመልቀቅ የተገደደበት የዘመቻ አንድነት ወታደራዊ ንቅናቄ ተጠቃሽ ድሎች ተገኝተዋል። በደቡባዊ ጎንደር ቀጠና ደራ ሀሙሲት በአገዛዙ ሹመኞች ላይ ያነጣጠረ ማጥቃት ከ7 በላይ ተደምስሰዋል። ዘመቻ አንድነት ወታደራዊ ማጥቃት በጎንደር እንደቀጠለ ሲሆን ከ4:00 ሰዓት በኃላ የሚኖረውን መረጃ ከ10:00 ሰዓት በኃላ እናደርሳለን። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ህ/ግንኙነት መምሪያ መጋቢት 12/2017 ዓ.ም "ዘመቻ አንድነት" ይቀጥላል!!! https://t.me/fanozgonder
"የዘመቻ አንድነት'' ድሎች በጎንደር ግንባር መጋቢት 10/2017 ዓ.ም ለነፃነትና ለአንድነት ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በጎንደር ሁሉም ማዕዘናት በፋሽስቱ ዓብይ አህመድ ሰራዊት ላይ የተጀመረው ወታደራዊ ማጥቃት በጠላት ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል። የዘመቻው አካል የሆነው የጎንደር ሰ/ምዕራብ ቀጠና በተለይም በጅንግር እና መሬና በጠላት ላይ በተወሰደ ወታደራዊ ማጥቃት 06 ብሬን፣ 01 ስናይፐርና ከ112 በላይ ነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያ፣ ከ4000 በላይ ተተኳሽ ጥይት፣ 81 ፈንጅዎች፣ ከጠላት የተማረከ ሲሆን ከ116 በላይ ጠላት ተደምስሷል። 35 ጠላት በህይወት ተማርኳል። የጎቤ ክ/ጦር፣ የተከዜ ክ/ጦር፣ የዘራይ ክ/ጦር፣ የሰ/አምባራስ ክ/ጦሮ የድሎ ባለቤቶች ናቸው። ከጠዋቱ 11:00 ሰዓት የጎንደር ዙሪያ ወረዳ መቀመጫ ማክሰኝት ከተማ የመሸገው የጠላት ሀይል ላይ ማጥቃት የከፈተው የጎንደሬ በጋሻው ክፍለጦር አካል ብርጌድና ሻለቆች፣ ዞዝ አምባ ንጉሥ እና የጥቁር አንበሳ ብርጌድ ከጎንደር ባህ/ዳር ዋና መንገድ በመቁረጥ ከተማዋን የተቆጣጠረ ሲሆን የጠላትን ማጎሪያ እስር ቤት በመስበር እስረኞችን ነፃ አድርጓል። በተጨማሪ ከ30 በላይ ሙት እና ከ20 በላይ ቁስለኛ ሁኗል። በደበቡባዊ የጎንደር ቀጠና ሰፊ ቀጠና የሸፈነ አውደ ውጊያ እየተደረገ ሲሆን የሜ/ጀ/ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ኢንጂነር ስመኘው ተዋርዋሪ ክፍለጦር፣ እና መብረቁ ክፍለጦር፣ በአምበሳሜ፣ ወረታ፣ ጋሳይ፣ ዓለም በር ፣ ጎላሀ እና አዲዘመን የሰፈረው የጠላት ሀይል ሙሉ በሙሉና በከፊል የተደመሰሰ ሲሆን የወረደ መቀመጫ የሆነችውን አምበሳሜ ከተማ ሰፍሮ የነበረው ጠላት ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል። በወገን ቁጥጥርም ትገኛለች። በዚህ አውደ ውጊያ ግንባር ከ160 በላይ የተደመሰሰ ከ95 በላይ ቁስለኛ ሁኗል። ምርኮኛ፦ ከጠላት ከ100 በላይ የጦር መሳሪያ ተማርኳል። በቀጠናው የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ሜ/ጀ ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር አካል ክ/ጦሮች 1-ጉና ክ/ጦር 2-ሜ/ጀ/ውባን አባተ ተወርዋሪ ክ/ጦር 3-ጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር 4-ፋሲል ክ/ጦርና 5-ኢ/ስመኘው ክ/ጦሮች የድሉ ባለቤቶች ናቸው። በቋራ እና መተማ ግንባር፦ በዘመቻ አንድነት በተሰራ ልዩ ኦፕሬሽን በምዕራብ ጎንደር መተማ ወረዳ ሽንፋ ከተማ ገበያ ማዕከል አካባቢ ስብሰባ ባደረገበት ብሶት የወለዳቸው የአማራ ተወላጆች በቀረበላቸው አጀንዳ ዙሪያ ማለትም "የአማራ ሕዝብን እናጥፋ" በማለታቸው በዚህ የተናደዱ ወታደሮች በቦንብ 39 ሲገድሉ፤ 50 አቁስለዋል። በተጨማሪ በቋራ ወረዳ በሙር እርስበእርሳቸው ከፍተኛ እልቂት ላይ ናቸው። ጠቅላላ በጎንደር ግንባር በዘመቻ አንድነት የተገኙ ድሎች የተደመሰሰ 345 የቆሰለ 155 ክላሽ፦ 212 ብሬን፦ 6 ስናይፐር፦ 1 ፈንጂ፦ 81 አሁንም በቀጠናው ዘመቻ አንድነት ተጠናክሮ ቀጥሏል። አንድነት ኃይል ነው! ድል ለአማራ ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ጎንደር /አማራ/ ኢትዮጵያ https://t.me/fanozgonder
ሰበር ዜና! ዘመቻ አንድነት በመላው አማራ ታወጀ የአማራ ሕዝብ የገጠመውን መንግሥት መር የዘር ጭፍጨፋ ለማስቆም የኅልውና ትግል ከጀመረ ሃያ ወራትን አስቆጥሯል። በእነዚህ ወራት በተበታተነ መልኩ ይሁን እንጅ በጠላት ላይ ቁሳዊ፣ ሰዋዊ፣ አዕምሯዊና መሰል ኪሳራዎችን ማድረስ ተችሏል። በስም መከላከያ የሚባለውን ወራሪ ሠራዊት በማፍረስ በኩልም አስደናቂ ተግባራት ተከናውነዋል። አማራውን በማጥፋት እብደት ውስጥ ቀጥተኛ ሱታፌ እያደረገ የሚገኘው የአብይ አሕመድ ደንገጡር የክልሉ ካድሬ መዋቅር ብትንትኑ ወጥቶ እንቅልፍ አልባ የዛፍ ላይ ሕይወትን በመግፋት ላይ ይገኛል፤ ጥቂት የማይባሉትም እጃቸውን ሰጥተዋል። "ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን" ነውና ከቀጠናዊ አደረጃጀቶች የተሻገረ ወጥ የሆነ አንድ ተቋም በመቋጨት ዋዜማ ላይ አንድ አማራዊ ተቋም መገንባት ያለውን ፋይዳ አመላካች ተግባርን ዛሬ መጋቢት 10/2017 ዓ.ም ላይ በመላው የአማራ ግዛቶች ጠላት በሚገኝባቸው ካምፖችና ምሽጎች ሁሉ ከሌሊቱ 10:00 ጀምሮ ማጥቃት ጀምረናል። ይህ በአንድነት እየተከናወነ የሚገኘው የማጥቃት ኦፕሬሽን በቀጣይ ገቢራዊ ለምናደርገው አንድ አማራዊ ተቋም እንደመስፈንጠሪያ ጉልበት ይሆነናል። የድላችን መቋጠሪያ፣ የኅልውናችን ማረጋገጫ መንገዱም ስልተ ጥበቡም አንድ ነው፤ እሱም አንድነት። መታገያ ጉዳያችን "ኅልውናችን" ዓለማና ግባችንም የታወቀ አንድ ጉዳይ እንደያዘ አካል አንድ አታጋይ ተቋምን ገቢራዊ ማድረግ ለነገ የማንለው ቁልፍ ጉዳይ እንደሆነ ብናምንም በትግል ሜዳችን የተሰገሰጉ ከኅልውና ትግላችን በተቃራኒ የቆሙ በታጋይነት ጭንብል የተጀቦኑ አስተሳሰቦች፣ ቡድኖችና አደረጃጀቶች ገቢራዊ ከምናደርገው አንድነታችን እንድንዘገይ አደረገን እንጅ አማራዊ አንድነቱን ገቢራዊ ከማድረግ አያስቆሙንም። በአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል የሚቆምሩትን፣ የሚቀልዱትን ግብራቸው፣ እኔነት አስተሳሰባቸው፣ ከፋፋይነታቸው፣ ግጭት ጠማቂነታቸው፣ ከሥርዓቱ ጋር ድብቅ ጋብቻቸው፣ የሥልጣንና የገንዘብ ፍትወታቸው ሕዝባችንም ታጋዩም በውል የተረዳበት ሰዓት ላይ እንገኛለን። እንደዚህ ያሉትን ጸረ አንድነት ኃይሎችን እያራገፍን የሕዝባችንን ኅልውና በአንድ ተቋምነት ማረጋገጥ ደግሞ በየቀጠናችን የተወሸቁ እንቅፋቶችን ተራምደን፣ ሳይረዱ በጠላት ጎራ የተሰለፉትን ጉዳዩንም መርምረው እንዲመለሱ ጥሪ እናቀርባለን። በአጠቃላይ ከዛሬ መጋቢት 10/2017 ዓ.ም ጀምሮ በጠላት ላይ ጥቃት የመሰንዘር ወታደራዊ ኦፕሬሽን በአራቱ ጠቅላይ ግዛቶች በሚገኙ ወታደራዊ አዛዦች ቅንጅት እየተከናወነ የሚገኝ አኩሪ ተግባር ነው። በዚህ ተናባቢና የአንድነት ዘመቻ የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አማራ)፣ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር፣ የአማራ ፋኖ በሸዋ እና የአማራ ፋኖ በጎጃም ቀጥተኛ ተሳታፊዎች ናቸው። ዛሬ በወታደራዊ አዛዦች ፊታውራሪነት አፈሙዛችንን በአንድ እለት፣ በአንድ ሰዓት የማስተባበርና የማቀናጀት ተግባር ብርቱ ጉልበታችንን ከማሳዬት ባሻገር አንድ አስተሳሰብ ያለን መሆናችንን በገቢር ያሳየንበት የሠራዊታችንን እንዲሁም የሕዝባችንን ተስፋ ያለመለምንበት ድንቅ ሥራ መሆኑ ሥራችን ምስክር ነው። "ዘመቻ አንድነት" ዛሬን ጨምሮ ለሚቀጥሉት ተከታታይ ቀናት ተጠናክሮ የሚቀጥል ሆኖ አንድ አማራዊ ተቋም በመገንባትም የሕዝባችንን ኅልውና ያረጋግጣል። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! "ዘመቻ አንድነት" የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የአማራ ፋኖ በሸዋ የአማራ ፋኖ በጎጃም የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አማራ) https://t.me/fanozgonder
без подписи
ከአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር፦ መይሳው ካሳ ኮር (፪ኛ ኮር) የኮር ምሥረታ መግለጫ የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል ቅኝቱ ፣ መነሻና መድረሻውም የሕዝባችንን ዘለቄታዊ ኅልውና ማረጋገጥ ነጻነቱን ፣ እኩልነቱን ፣ ሰብዓዊ ክብሩን ማጎናጸፍ እንደሆነ መላው ወገናችን የሚገነዘበው ሐቅ ነው ። እዚህ ግብ ላይ ለመድረስ ባለፉት ወራት በደማቸው ጠብታ ፣ በሕይወታቸው መስዋዕትነትት ትግላችን በሁሉም ዘርፍ በአለት ላይ እንደታነጸ ቤት የጥፋት እጆች የማይንዱት ፣ የደም ነጋዴዎች የማያፈርሱት ጽኑ ሆኗል። "ከሰል የተሸከመ እና እንቁላል የተሸከመ እኩል አይጠነቀቅም" እንዲሉ አበው እንደ እንቁላል የምንጠነቀቅለትን ትግላችንን በከሰለና በጠቆረ ስሁት ግብራቸው ጥላሸት ሊቀቡን ያልፈነቀሉት ድንጋይ ያለጠፉት ጭቃ አልነበረም። ዳሩ ግን ትግሉ የተመሠረተበት አለት ጽኑ ነው ትግሉ የተወለደበት ማሕጸን ለምለም ነው ትግሉ ያደገበት ቀዬ አማራዊ እሴት ሃይማኖትና ባሕል የተሸመኑበት ሐቅ ነው ትግሉ በትጉህ የጦር ገበሬዎች በንጹህ ደማቸው ዘርነት የበቀለ የሕዝባችን ከሞት የመዳኛው ሰብል ነው። ስለሆነም ይህን ትግል በሁሉም ዘርፍ መጠበቅ፦ የሕዝብን አደራ፣የወጣንለትን ዓላማ፣የመዳረሻ ግባችንን መጠበቂያ መልኅቃችን መሆኑን በውል መግለጽ እንወዳለን። አማራን በሁለንተናዊ ማንነቱ የማጥፋት ብልጽግና መር ጄኖሳይድ አስገድዶን ግፍ ጭቆና አፈና አንገፍግፎን ከመኖሪያ ቀያችን ከሞቀ ጎጇችን በአባቶቻችን የጀግንነት ውርስ በመፈነን ረፍት የለሽ ጠላትን የመቅበር ተግባራችንን በጠንካራ አደረጃጀት እየፈጸምን እንገኛለን።ይህን የመሰለውን በደም በአጥንትና በመስዋዕትነት ጭምር የታጀበ ትግላችንን፦የያዘውን ዓላማ እንዳያሳካ ጎታች ፣ከፋፋይ ፣ጎጠኛ፣ እኔነት፣ ገፊነት፣ ባንዳነት፣ አስመሳይነት እና መሠል አጥፊ አስተሳሰቦችን ሁሉ እንደ ትቢያ እያራገፈ ወደ ፊት ብቻ መጓዝን የፋኖነት መታወቂያ የድላችን መድመቂያ አድርጎ መንቀሳቀስ ነው የሕዝባችን ኅልውና ማረጋገጫ።ትግላችንን ለአጭበርባሪዎች አሳልፈን አንሰጥም፤ትግላችንን በገንዘብ አንሸጥም፤ትግላችንን ከሳልሳይ ብአዴን ምንጣፍ አንጣፊዎች እንቅልፍ አጥተን እንጠብቀዋለን ምክንያቱም ይህ ትግል የሕዝባችንን ኅልውና በሐቀኛ ሥርዓት ማረጋገጫ የአማራ ሕዝብ በሙሉ በሕይወት መጓዣ መንገድ ነውና ከምንም በላይ በትግላችን ውስጥ ከግለሰብ እስከ ቡድን እሚፈጠር አፈንጋጭነት ማጥሪያ ወንፊታችን እንደሆነም በጽኑ እናምናለን።በአጭር ጊዜ የትግል ሜዳችንም በዐይናችን ያየነው በሕይወት የኖርነው እውነት ይህ ብቻ ነው። ስለሆነም እንደወቅቱ የጠላት አሰላለፍ አደረጃጀቶችን መፍጠር፣አእምሯዊ እና አካላዊ ሥልጠናዎችን አጠናክሮ መቀጠል አንዱ የድል መንገድ እንደሆነ በጽኑ እናምናለን።ይህን ጽኑ እምነት ገቢራዊ ለማድረግም ከ10 ቀናት በላይ ውይይቶችን በማድረግ በጎንደር ቀጠና ሁለተኛውን የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ኮር ስንመሠርት ታላቅ ኩራት ይሰማናል። የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር፦ጎንደር ላይ ያሉ አደረጃጀቶችን ወደ አንድ አደረጃጀት ሰብሰብ አድርጎ መንቀሳቀስ ሲጀምር አንዱ ጉዳዩ በየቀጠናው ያሉ የክ/ጦር እና የብርጌድ አደረጃጀቶችን አስተሳስሮ የጋራ ተነባቢ ትግል የሚደረግበትን የኮር አደረጃጀት መፍጠር የወታደራዊ ዘርፉ አቅጣጫ ነው። ይህንን የተቋማችንን አቅጣጫና ይሁንታ ተቀብለን ወደ ሥራ የገባን የቀጠናው የክፍለ ጦር አደረጃጀቶች የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር" 2ኛ መይሰው ካሳ ኮርን" ን በስድስት ክፍለጦሮች አዋቅረናል። የኮሩ መሥራች ክፍለ ጦሮችም፦ 1ኛ.አድዋ ክ/ጦር 2ኛ.ቋራ ኦሜድላ ክ/ጦር 3ኛ.ዞብል ጃኖ ክ/ጦር 4ኛ.ቴዎድሮስ ክ/ጦር 5ኛ.አጣናው ዋሴ ክ/ጦርእና 6ኛ.ልዑል ዓለማዬሁ ክ/ጦሮች ናቸው። ከላይ የተገለጹት ክፍለ ጦሮች በከፊል ማዕከላዊ ጎንደርና ምዕራብ ጎንደር ቀጠናዎችን በኩታ ገጠም አንድም በቀጠናዊ ትስስር በማስተሳሰር 2ኛ (መይሰው ካሳ) ኮርን የመሠረቱ ናቸው።በዚህ መሠረት የ2ኛ (መይሰው ካሳ) ኮር አመራሮችን እንደሚከተለው ሰይመን በተቋማችን የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር እውቅናና ይሁንታ አግኝተን እንደሚከተለው እንገልጻለን። 1.የኮር ሰብሳቢ..............አርበኛ ተስፋ ጌታሁን 2.የኮር ም/ሰብሳቢ.........አርበኛ አለምቀን መለሰ 3.የኮር ወታደራዊ አዛዥ....አርበኛ ዳዊት ዘመነ 4.የኮር ም/ወ/አዛዥ........አርበኛ የሽነህ ታደሰ 5.የኮር ፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ......አርበኛ በላይሁን ይትባረክ 6.የኮር ም/ፖ/መምሪያ ኃላፊ........አርበኛ አስተዋለ አቀኔ 7.የኮር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ........አርበኛ አስተውል አምሳሉ 8.1.የኮር ም/ሕ/ግንኙነትኃላፊ.....አርበኛ አንደበት ፍቀዱ 9.የኮር ዘመቻ አዛዥ..........አርበኛ አገናኝ ካሱ 10.የኮር ም/ዘመቻአዛዥ....አርበኛ አየልኝ ደግፈው 11.የኮር አሥተዳደር..........አርበኛ እንግዳው መዝገቡ 12.የኮር ም/አሥተዳደር.....አርበኛ አንደበት አለባቸው 13.የኮር ሎጀስቲክስ መምሪያ ኃላፊ.......አርበኛ ታዲዮስ በለጠ 14.የኮር ም/ሎጀስቲክስ........አርበኛ መንጋው በላይ 15የኮር ሕዝብ አሥተዳደር መምሪያ ኃላፊ...አርበኛ ሳሙኤል ሙላው 16.የኮር ም/የሕዝብ አሥተዳደር............አርበኛ ቻላቸው ንጉሴ 17.የኮር ሕግናሥነ ምግባር መምሪያ ኃላፊ...........አርበኛ ብርሃኑ አቡሃይ 18.የኮር ም/ሕግናሥነምግባር............አርበኛ ንጋት መዝገቡ 19.የኮር ሥልጠና መምሪያ ኃላፊ...........አርበኛ እስጢፋኖስ ሙላት 20.የኮር ም/ሥልጠና... 21.የኮር አደረጃጀት መምሪያ ኃላፊ.........አርበኛ ሃብታሙ ብዙአየሁ 22.የኮር ም/አደረጃጀት... 23.የኮር ጽ/ቤት ኃላፊ...........አረበኛ ወልደ አረጋይ ሸርብ 24.የኮር ም/ጽ/ቤት...............አርበኛ ርስቱ አባይ 25.የኮር መረጃና ደኅንነት ኃላፊና ም/ኃላፊዎች.. መዋቀራቸውን እያሳወቅን በቀጣይ ጊዜያት ቅንጅታዊ እዝና ሰንሰለትን በጠበቀ መልኩ የምንፈጽማቸውን ወታደራዊ ግዳጆች በተግባር የምናሳይ መሆኑን ማስገንዘብ እንወዳለን። በመጨረሻም እርቃኑን የቀረውን የብልጽግና ሥርዓት በእራፊ ጨርቅ ለመሸፈን በሚመስል መልኩ በገሃድ ከተገለጠው ጠላታችን በማይተናነስ መልኩ የጎንዮሽ መጓተት የምትፈጥሩብን አካላት ከሥርዓቱ ጋር የተደበቀ ጋብቻ ከሌላችሁ በስተቀር ከገባችሁበት በታኝ ድርጅታዊ ጭንብል ወጥታችሁ ወደ ጎንደር አንድነት እንድትመጡ ጓዳዊ ጥሪያችንን አናቀርብላችኋለን። በዓላማ ከሥርዓቱ ጋር ተናበው የሚሠሩትን በግብራቸው እናውቃቸዋለን ብዙኃኑን ታጋይ ግራ አጋብተውታል ትልልቅ አርበኞችን ሳይቀር መሬት ላይ የሌለ በሬ ወለድ የሴራ ድራቸው ጠልፈው አላላውስ አላንቀሳቅስ ብለው አንገታቸውን አስደፍተዋቸዋል በዚህም ትግሉንና ታጋዩን በማይመጥን እኩይ መንገድ ላይ ተጠምደዋል። ዳሩ ግን ሁሉም በግብራቸው እየተገለጡ፣ የተታለሉት ታጋዮች እውነቱን መርምረው ወደ አንድነት እየተመለሱ ያሉበት ወቅት ነው።ስለሆነም እውነተኛ አንድነት፣ሐቀኛ አንድነት፣በቅንነት የሚጓዝ አንድነት፣ከሴራ ቡትቶ የጸዳ አንድነት ትክክለኛው የድል ሐዲድ መሆኑን አውቃችሁ ወደ አንድነት እንድትመጡ በድጋሜ ጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን። ኅልውናችን በተባበረ አንድነታችን!!! የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር፦፪ኛ (መይሳው ካሳ) ኮር ጎንደር፣አማራ፣ኢትዮጵያ
🔥#ሰበር_ዜና‼️ 60 የመከላከያ ሰራዊት ሲማረክ፤ 110 ክላሽንኮቭ፤ 10 ብሬን፣ 12 ስናይፐር ተማርኳል‼️ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ድብ ጠለምት ተከዜ ክፍለጦር እና ጭና ክፍለጦር መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት የጀመረ ውጊያ እስከ ዛሬ መጋቢት 3 ቀን 2017 ዓ.ም በሰሜን ጎንደር ዞን ማዕከላዊ ደባርቅ እና አዲርቃይ ወረዳ ከባድ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን የድብ ጠለምት ተከዜ ክፍለጦር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ፋኖ እሸቱ ዘነበ ገልጿል። የተደረገው ውጊያ ከባድ የሚባል ቢሆንም ሸማቂዎች የጎንደር አማራ አናብስቶች የምርኮኛው ብርሃኑ ጁላን ሰራዊት ድባቅ በመምታት 60 የመከላከያ ሰራዊት ሲማረክ፤ 110 ክላሽንኮቭ፤ 10 ብሬን፣ 12 ስናይፐር ተማርኮ ወደ ፋኖ ቋት መግባቱን ፋኖ እሸቱ ዘነበ ገልጿል። ከጠላት ሰራዊት ምን ያህል እንደተደመሰሰ ለማወቅ ባንችልም ከዚህ በፊት በጎንደር ቀጠና ከመደምሰስ የተረፉ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ክፍለጦሮች የተውጣጡ የሰራዊት አባላት ይሄን ቃለመጠይቅ በመስጥበት ሰዓትም ገሚሱ እየተደመሠሠና ቀሪውን ደግሞ እጅ የማሰጠት ሥራ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የድብ ጠለምት ተከዜ ክፍለጦር እና የጭና ክፍለጦር የሰራዊት አባላት እየሰሩ ነው፤ የህልውና ትግላችንና ተጋድሏችንም ተጠናክሮ ይቀጥላል!!! ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የሚዲያና ሕ/ግንኙነት መምሪያ https://t.me/fanozgonder
ሰበር ዜና! የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር በምዕራብ በለሳ ወራህላ ከተማ ዙሪያ ልዩ ቦታው ፈንጣ ሀዋሪያት ከሚባል ዛሬ መጋቢት 1/2017 ዓ/ም ከጥዋቱ አራት ስዓት ጀምሮ የብልፀግናን ጥምር ወንበር አስጠባቂ ሀይል ማለትም መከላከያ፣ አድማ በታኝ እና ሚኒሻን በተለመደው የውጊያ ምት ቁም ስቅሉን አያበሉት ለእነሱ ቀኑ ወር ያህል እረዝሞባቸው መውጫ ቀዳዳ አሳጥቷቸው ውሏል። ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር በለሳን ሙሉ ለሙሉ ከአገዛዙ ለማፅዳት ዘመቻ ከጀመረበት የካቲት 20 ጀምሮ ገጠሮችን ሙሉ ለሙሉ አስለቅቀን አርባያ ከተማ እና ከመኪና መንገድ ብቻ ተወስኖ እንዲቀመጥ አድርገናል ሲል የክፍለጦሩ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ፋኖ ታድሎ ደሴ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ተናግሯል። የአገዛዙ ሀይል በማንኛውም ስአትና ሁኔታ ፣ ቀንም ሆነ ለሊት ከጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር የሚገጥመነን እርምጃ አናውቅም በማለት እንቅስቃሴአቸውን ሁሉ በዙ 23 የታጀበ ቢያደርጉም ከጀግኖች ምት እና ሞት መዳን አልቻሉም ማንም እንደ ማያድናቸውም እያሳየናቸው እንገኛለን፣ በዛሬው ውጊያ ጠላት ዳግመኛ ከፍተኛ ሰባዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበት በሽንፈትና በውርደት ተመልሷል ብሏል። ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ሰሞኑን በበለሳ ከመከላከያ፣ከአድማ ብተና፣ እንዲሁም የተለያየ ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ከአገዛዙ በግፍ የተባረሩ በርካታ አዲስ ሀይሎች ወደ ክፍለ ጦራችን እየተቀላቀሉ ጉልበት እየሆኑን እንዲሁም ለአማራ ህዝብ ተጨማሪ ጥንካሬ በመሆን ከነባሩ ሀይል ጋር በቅንጅት እየተዋጉ ይገኛሉ። የበለሳ ህዝብ ከጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ጎን በመሆን የብልፅግናን ስርዓት ከስሩ ነቅሎ ለመጣል ቆርጦ ተነስቶ አብሮ ተሰልፎ የህይወት ዋጋ እየከፈለ ይገኛል። መንግስትን ጎትተን ቤተ መንግስት አስገብተነው ዋጋችን እረስቶ አመድ አፋሽ አድርጎን በለሳን በማንኛውም ልማት ወደ ኋላ አስቀርቶን የሚኖረውን ስርዓት ከዚህ በላይ እንዲቀጥል አንፈቅድለትም በማለት ከፋኖ ጋር እየታገሉ ያሉ አርሶ አደሮች እና ልጆቻቸው ቁጥር እጅግ ብዙ ናቸው። የደጃች ዳኛው ተሰማ ልጆች እንደ አያቶቻቸው የህልውና ፣ የነፃነት እና የፍትህ ተጋድሎ እያደረጉ ዳግመኛ ታሪክ እየሰሩ ይገኛሉ። ጠላት በአሁኑ ስአት ሀይሉን ተራራ ላይ እንደ ዝንጀሮ መንጋ ሰብስቦ በሞርተር እና ዲሽቃ ነብሱን ለማትረፍ እየጣረ በከፍተኛ የድረሱልን ጥሪ እየጮኸ ይገኛል። ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ጥቁር አስፓልትና ከተማ ዙሪያ የማይለቀውን የአንባገነኑን ስርዓት እግር በእግር እየተከታተለ እግሩን እያሳጠረለት፣ ቁጥሩን እየቀነሰለት፣ ሞራሉን እየሰበረው ይገኛል:: ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የሚዲያና ሕ/ግንኙነት መምሪያ https://t.me/fanozgonder
ሰበር የድል ዜና‼️ ዛሬ ሰኞ መጋቢት 1/2017 በሰሜን ጎንደር ዞን አዲ አርቃይ ወረዳ ዛሪማ ቀበሌ በአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር በድብ ጠለምት ተከዜ ክፍለጦር በተጣለ ደፈጣ የወረዳውን ሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊና የብል*ግና ጽ/ቤት አደረጃጀት ምክትል ኃላፊ ጨምሮ ሦስት አመራሮችና በርካታ ወንበር አስጠባቂ ሠው በላ አራ*ዊት ሰራዊት ተደምስሷል‼️ ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የሚዲያና ሕ/ግንኙነት መምሪያ https://t.me/fanozgonder
የአደረጃጀት ዜና! ከአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር፦ ንሥር በለሳ ቅጣው እጅጉ ክ/ጦር የተሰጠ መግለጫ የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል ትናንት ከነበረበት ደረጃ ገዝፎ፣ የአደረጃጀት አንድነትን ፈጥሮ፣ በመርኅ መተታገልን አጠናክሮ ከሚጓዝበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ትግላችን የዐይን ብሌናችን ነው፤ ትግላችን ከነፍሳችን ጋር በአቻነት የምንሳሳለት ነው፤ ትግላችን የሕዝባችንን ኅልውና ማረጋገጫችን ነው። ስለሆነም ይህን ትግል በሁሉም ዘርፍ መጠበቅ፦ የሕዝብን አደራ፣ የወጣንለትን ዓላማ፣ የመዳረሻ ግባችንን መጠበቂያ መልኅቃችን መሆኑን በውል መግለጽ እንወዳለን። ወደ ጫካ የወጣነው፣ ከተመቻቸ ጎጇችን የወጣነው፣ ከልጆቻችን፣ ከወላጆቻችን በነጻ ፈቃዳችን የተለየነው ግፍንና ገፈኞችን ተቃውመን፣ ኅልውናችን መንግሥት መር በሆነ መንገድ አደጋ ውስጥ ገብቶብን፣ ነጻነት፣ ፍትሕና እኩልነት እንደ ሰማይ ርቀውን በአባቶቻችን በፋኖነትና በአርበኝነት ቁጭት እንጅ የግልና የቡድን ፍላጎት ልናስፈጽም አይደለም። በዚህም የፋኖነት ትግል የወል ጉዳይ የአማራን ሕዝብ ኅልውና ማረጋገጥ መሆኑን ለሕዝባችን ለመላው የትግል ጓዳችን አስረግጠን መግለጽ እንወዳለን። እኛ በንሥር በላሳ ቅጣው እጅጉ ክፍለ ጦር አደረጃጀት ውስጥ የምንታገል አርበኞች የትግሉን መራርነት ትናንት በጀግንነት ጠላትን እንደቅጠል ጎዝጉዘው በተሰውት አርበኛ ሳላምላክ ነጋሽ፣ አርበኛ ጉልላት ጸጋዬ እና ሌሎችም ጓዶቻችን በዐይናችን ተመልክተናል። የተሰውለትን የትግል ዓላማም በታማኝነትና በጽናት አንድያ ኅያው ነፍሳችንን ሰጥተን ከዳር ለማድረስ በኅያው እግዚአብሔር ስም መሐላ አለብን። በዚህ መሠረት ንሥር በለሳ ቅጣው እጅጉ ክ/ጦርን በመሠረቱት ብርጌዶች ሙሉ ይሁንታነት የወቅቱን የጠላት አሰላለፍ በወጉ ፈትሾ የሚያታግሉ አርበኞችን ወደፊት አምጥቶ ከ10 ቀናት በላይ ውይይቶችንና ሥልጠናዎችንም ጭምር አድርጎ ሪፎርም ሠርቷል። ይህንን ሪፎርምም ተቋማችን የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር በላካቸው የተቋሙ ልኡካን አማካይነት እውቅና ተፈጥሯል። በዚህ መሠረት፦ 1. የክ/ጦሩ ዋና አዛዥ.............አርበኛ ሙሉቀን ካሳሁን 2. ም/አዛዥ........አርበኛ አብራራው ፀጋዬ 3. የዘመቻ መምሪያ …አርበኛ አበበ ገብሬ 4. ም/ዘመቻ አዛዥ....አርበኛ መሳፍንት ደጉ 5. የፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ............ አርበኛ ጣዕማለው ወልዴ 6. ም/ፖ/መምሪያ ኃላፊ ...........አርበኛ መላክ ደሳለኝ 7. የሕ/ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ........... አርበኛ ሻምበል ኤርሚያስ 8. ልዩ ኦፕሬሽን መምሪያ ኃላፊ...........አርበኛ ሙሉቀን ዮሐንስ 9. ወታደራዊ አሥተዳደር...........አርበኛ አሠፋ በላይ 10."ሎጀስቲክስ መምሪያ ኃላፊ.............አርበኛ ይግዛው ጥጋቡ 11. ሥልጠና መምሪያ ኃላፊ.............አርበኛ ይበልጣል ምላሽ 12. አደረጃጀት መምሪያ ኃላፊ............አርበኛ ማስረሻው አለምነው 13. ፋይናንስ አሥተዳደር..............አርበኛ በላይ መልካም እና ሌሎችን ኃላፊና ምክትል ኃላፊዎችን ያካተተ ሪፎርም ሠርተናል። በመጨረሻም የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር፦ ንሥር በለሳ ቅጣው እጅጉ ክፍለ ጦር ማስተላለፍ የሚፈልገው ጉዳይ ከጎንዮሽ መጓተት ወጥቶ መሬት ላይ ለሕዝባቸው ውድ ሕይወታቸውን የገበሩ የትግል ጓዶቻችንን አደራ ከዳር ማድረስ የሚቻለው በቅንነትና በእውነት ሐቀኛውን የአንድነት መንገድ መከተል ብቻ እንደሆነ ጽኑ እምነታችንን። ከምንም በላይ ክ/ጦራችንን በራሳቸው ፍላጎት ያለሠራዊታችን ይሁንታ የአፋሐድ ሚሊሻ ለማድረግ የፕሮፓጋንዳ ሥራ የምትሠሩ ሚዲያዎች ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ ማሳሰብ እንወዳለን። በዚህ መሠረት ንሥር በለሳ ቅጣው እጅጉ ክ/ጦር ትናንት በተበታተነ አደረጃጀት የነበረውን ታጋይ ለመሰብሰብ ጎንደርን በአንድ አታጋይ ተቋም የማታገሉ ሰናይ ተግባር እጅጉን ያስደሰተን መሆኑን እየገለጽን የአንድነት ተቋማችንም "የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር" በሚሰጠን አቅጣጫ፣ አሠራርና መርኅ ለመታገል ያለንን ቁርጠኝነት ሳንገልጽ ማለፍ አንፈልግም። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር፦ ንሥር በለሳ ቅጣው እጅጉ ክፍለ ጦር
ሰበር ዜና! “60 የጠላት ኃይል ሲደመሰስ፣ 49 ክላሽንኮቭ መሳሪያ ማርከናል።” የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ቋራ ኦሜድላ እና አድዋ ክፍለጦር በምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ ጦር ጋር በተደረገ ውጊያ በጠላት ከፍተኛ ኪሳራ መድረሱን የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የቋራ ኦሜድላ ክፍለጦር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ፋኖ አስቻለው አለባቸው ለኢትዮ 251 ሚዲያ በሰጠው ቃለመጠይቅ ገልጿል። በዛሬው ዕለት የካቲት 27 ቀን 2017 ዓ.ም በምዕራብ ጎንደር ቋራ ወረዳ አልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ ዙሪያ በተደረገ ውጊያ የምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ 60 ሰራዊት ሲደመሰስ፣ 49 ክላሸንኮቭ መሳሪያ ወደ ፋኖ ገቢ የሆነ ሲሆን በተጨማሪም ወደ አልጣሸ ብሔራዊ ፓርክ መደበኛ መኪና መግባት ስለማይቻል በትራክተር ተተኳሽና ስንቅ ለማሰጋገር ሲሞክር ትራክተሩ ከእነሙሉ ተተኳሽና ስንቁ በፋኖም እንደተማረከ ፋኖ አስቻለው አለባቸው ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጿል። ውጊያው አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የቋራ ኦሜድላ ክፍለጦር አካል የሆኑት ዳግማዊ ቴዎድሮስ ብርጌድ፣ ነብሮ ብርጌድ እና የአድዋ ክፍለጦር አካል የሆነው ነብሮ ብርጌድ የጠላትን ኃይል ድባቅ እየመቱት ይገኛሉ፣ የጠላት ኃይል ከመደምሰስና ከመማረክ የተረፈው ወደ ገለጎ ከተማ እየፈረጠጠ ይገኛል ሲል የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የቋራ ኦሜድላ ክፍለጦር ሕዝብ ግንኙነት ፋኖ አስቻለው አለባቸው ገልጿል። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የሚዲያና ሕ/ግንኙነት መምሪያ https://t.me/fanozgonder
የካቲት 26/2017 ዓ.ም የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ሜ/ጀ ውባንተ አባተ ኮር 👉 ሜ/ጀነራል ውባንተ አባተ በተመሠረተ ውሥን ቀናት ውሥጥ ኮሩ በሚንቀሣቀሥባቸው መዳረሻዎች ሁሉ ከፍተኛ የሆነ ድል እየተመዘገበ ነው የሚገኘው። ጦራችን በታላቁ እሥቴ ከቆማ እሥከ መካነ ኢዬሡሥ፣ ከሸምበቆች እሥከ ገና መምቻ፣ ከሾለክት እሥከ ደንጎልት፣ ከማጎት እሥከ ምክሬ፣ ከአጎና እሥከ ጉና፣ ከሊባኖሥ እሥከ ጥናፋ፣ ከልዋዬ እሥከ ግንዳ ጠመም፣ ከማሕደረ ማርያም እሥከ ልጫ፣ከጅብ አሥራ እሥከ ገላውዴዎሥ ከጋሣኝ እሥከ ደብረ ታቦር ከተማና መሠል መዳረሻዎች ላይ ለተከታታይ 4 ቀናት አውደ ውጊያ ማድረጉ ይታወቃል። ፈለገ ውባንተዎች ሀብት ንብረትን የናቁ፣ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች የማያናውጧቸው፣ ለዳያሥፖራም ሆነ ለጠምዛዥ እጆች የማይምበረከኩ፣ ለአገዛዙ ወምበር ጠባቂ አራዊት ሠራዊት የእግር እሣቶች፣ ጎጠኝነትን ተጠይፈው ፩ አምሐራነት ልዕልና ላይ የተቀመጡ ናቸው። ለአማራዊ አንድነት ሰናይ የሆነ ምልከታን ተላብሰው ለአንድነት በራቸውን ክፍት አድርገው ለሴረኞች ቤታቸውን ጠርቅመው የዘጉ ናቸው። በዛሬው ዕለትም የካቲት 26/2017ዓ.ም ✅የሜ/ጀ ውባንተ አባተ ኮር የሆኑት ጉና ክ/ጦር፣ ኢንጅነር ሥመኘው ክ/ጦር እና ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር አለም በር ከተማ ንጋት 10:30 የጀመረው አውደ ውጊያ አድማሡን አሥፍቶ አለም ሣጋ፣ ኮሶ ማርያም፣ አምቦ፣ አሞራ ገደል፣ ሱራይ ካምፕ፣ አለም በር፣ ወጂ፣ ሥንቆና ወርቅ ሜዳ ላይ ውጊያ የተደረገባቸው ቦታዎች ናቸው። ጠዋት 1:00 ላይ አለም በር ከተማን ከአገዛዙ ወምበር ጠባቂ አካላቶች ነጻ ማድረግ ተችሏል። ጠላት ለወራት የሰራው ምሽግ በውቤ ልጆች ተደረማምሧል። ጥበበኛው የጥበብ ልጅ ታላቁ የአማራ ፋኖ መናበብን ሢከውን የሚያቆመው ኃይል እንደሌለ ከሰሞኑ እየተገኙ ያሉ ድሎች ምሥክር ናቸው። ✅ጋሳኝ ጉና ክፍለ ጦር/መቅደላ አምባ ብርጌድ/ናደው ሻለቃ 👉 ጋሳኝ ከተማ ንጋት 12:00 ጀምረው ከፍተኛ ትንቅንቅን በማድረግ የአገዛዙን አራዊት ሠራዊት ከጋሣኝ ከተማ አሥለቅቀው ከጋሳኝ ዙሪያ ባሉ መዳረሻዎች ውጊያ ሢያደርጉ አርፍደዋል።በዚህ ሠዓታትን የፈጀ አውደ ውጊያ ጠላት በቁሥም በአካልም ከፍተኛ የሆነ ኪሣራን አሥተናግዷል። ከጋሳኝ ወደ ደብረ ታቦር የአገዛዙ አገልግሎት ሠጪ አምቡላንሶች ቁሥለኞችን በማመላለሥ ተጨናንቀው አርፍደዋል። ጠላት ሊያደርገው የነበረው ትልቅ ራዕዩ ቅዠት ሆኖ እንዲቀር ተደርጎበታል። ከንጋት 12:00 እሥከ ቀኑ 6:00 በቆዬው አውደ ውጊያ ታጋዮች ጠላትን አምበርክከዋል፤ ረፍርፈዋል። 👉 በድቅድቁ ጨለማ አብሪ ኮከብ የሆኑ የአማራ ፋኖዎች በብዛት እየተከሰቱ ነው። በዚህ ትግል ሻማ ሆነው እየቀለጡ ብርሐን እዬሠጡን፤ ክቡር መሥዋዕትነትን እየከፈሉና ለአማራነት ታምነው እየታገሉ እያለ አንዳንድ አዳፍኔዎች እና የፋኖነትን የተቀደሰ የትግል መንገድ ያልተረዱ አካላት የተሰሩ ድሎች ለሕዝብ አንዳይቀርቡ አለፍ ሢልም ባልዋሉበት ኩበት ለቀማን ሢከውኑ ይታያል። የአማራ ፋኖ መራራ ዕውነታን ይጋፈጣል። ያልሰራውን እንደሰራ አድርጎ አያቀርብም። ምክንያቱም ይህ ሠራዊት ለዕውነትና ለፍትሕ፣ ለታላቁ አማራ ሕዝብ ማንነትና ዘርፈ ብዙ ተጠዬቆች መልሥ ለመሥጠት እሥከ ሙሉ ቤተሰቡ ክቡር መሥዋዕትነትን የከፈለው ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፈለግ ተከታይ የሆነ የታጋይ ሥብሥብ ነውና። በተጨማሪም ደግሞ ከሕዝብ በላይ ምሥክርነትን የሚሰጥ የለም። ማን እንደሚታገልለት ሕዝባችን ጠንቅቆ ያውቃል። ሕዝብ ዳኛ ነው ይመዝናል። በሕዝብ ቀልሎ ላለመገኘት የፋኖን የተቀደሰ የትግል መንገድ እንከተል። ሥለሆነም ለሕዝብ የወጣ አካል ሕዝባዊነትን ብቻ መሠረት አድርጎ መታገል እንዳለበት የሜ/ጀ ውባንተ አባተ ኮር አበክሮ ማሣሠብ ይፈልጋል። የፋኖነትን ዕንቁ የትግል መንገድም እንዲከተሉ ያሥገድዳል። አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ፋኖነትን ምሽግ ላደረጉ አካላት ቅድሚያ ልክ አለመሆናቸውን ያሥገነዝባል፤ ካልተመለሱም ተገቢውን የማሥተካከያ ርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል። ✅ የሥማዳው ከተማ ወገዳ ላይ የጉና ክፍለ ጦር አካል የሆነው ሐገረ ቢዘን ብርጌድ ከቀኑ6:00 ሠርጎ በመግባት ከተማው ላይ በነበረው የአገዛዙ አራዊት ሠራዊት በሁሉም አቅጣጫ ማጥቃት ከፍቶበታል። በዚህ ውጊያ የተነሳ የብልፅግና አመራሮች መግቢያ አጥተው የመሸሸጊያ ያለሽ ሢሉ ደፈጣ ይዞ የነበረው የአገዛዙ ጥምር ጦር ካድሬዎችን ለማዳን ቢሯሯጥም አልተሳካለትም። የባሰ አታምጣ ሢል ይዝት የነበረውን ምሽግ ሁሉ እየለቀቀ ፈርጥጧል። እሥከ ምሽት የቀጠለው ውጊያ ጥቃቅንና አነሥተኛ ካድሬዎችን ጭንቅ ውሥጥ ከትቷቸዋል። ✅ሌላኛው የጉና ክ/ጦር አካል አንዳ ቤት ብርጌድ ጃራ ከተማ ላይ ከ 6:00 ጀምሮ ለሰዓታት የፈጀ አውደ ውጊያን አድርጓል። ኅልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የሚዲያና ሕ/ግንኙነት መምሪያ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ኮር (፩ኛ ኮር) https://t.me/fanozgonder
የካቲት 26/2017 ዓ.ም የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ሜ/ጀ ውባንተ አባተ ኮር 👉ኮራችን በተመሠረተ ውሥን ቀናት ውሥጥ ኮሩ በሚንቀሣቀሥባቸው መዳረሻዎች ሁሉ ከፍተኛ የሆነ ድል እየተመዘገበ ነው የሚገኘው። ጦራችን በታላቁ እሥቴ ከቆማ እሥከ መካነ ኢዬሡሥ፣ ከሸምበቆች እሥከ ገና መምቻ፣ ከሾለክት እሥከ ደንጎልት፣ ከማጎት እሥከ ምክሬ፣ ከአጎና እሥከ ጉና፣ ከሊባኖሥ እሥከ ጥናፋ፣ ከልዋዬ እሥከ ግንዳ ጠመም፣ ከማሕደረ ማርያም እሥከ ልጫ፣ከጅብ አሥራ እሥከ ገላውዴዎሥ ከጋሣኝ እሥከ ደብረ ታቦር ከተማና መሠል መዳረሻዎች ላይ ለተከታታይ 4 ቀናት አውደ ውጊያ ማድረጉ ይታወቃል። ፈለገ ውባንተዎች ሀብት ንብረትን የናቁ፣ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች የማያናውጧቸው፣ ለዳያሥፖራም ሆነ ለጠምዛዥ እጆች የማይምበረከኩ፣ ለአገዛዙ ወምበር ጠባቂ አራዊት ሠራዊት የእግር እሣቶች፣ ጎጠኝነትን ተጠይፈው ፩ አምሐራነት ልዕልና ላይ የተቀመጡ ናቸው። ለአማራዊ አንድነት ሰናይ የሆነ ምልከታን ተላብሰው ለአንድነት በራቸውን ክፍት አድርገው ለሴረኞች ቤታቸውን ጠርቅመው የዘጉ ናቸው። 👉በዛሬው ዕለትም የካቲት 26/2017ዓ.ም ✅የሜ/ጀ ውባንተ አባተ ኮር የሆኑት ጉና ክ/ጦር፣ ኢንጅነር ሥመኘው ክ/ጦር እና ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር አለም በር ከተማ ንጋት 10:30 የጀመረው አውደ ውጊያ አድማሡን አሥፍቶ አለም ሣጋ፣ ኮሶ ማርያም፣ አምቦ፣ አሞራ ገደል፣ ሱራይ ካምፕ፣ አለም በር፣ ወጂ፣ ሥንቆና ወርቅ ሜዳ ላይ ውጊያ የተደረገባቸው ቦታዎች ናቸው። ጠዋት 1:00 ላይ አለም በር ከተማን ከአገዛዙ ወምበር ጠባቂ አካላቶች ነጻ ማድረግ ተችሏል። ጠላት ለወራት የሰራው ምሽግ በውቤ ልጆች ተደረማምሧል። ጥበበኛው የጥበብ ልጅ ታላቁ የአማራ ፋኖ መናበብን ሢከውን የሚያቆመው ኃይል እንደሌለ ከሰሞኑ እየተገኙ ያሉ ድሎች ምሥክር ናቸው። ✅ጋሳኝ ጉና ክፍለ ጦር/መቅደላ አምባ ብርጌድ/ናደው ሻለቃ 👉ጋሳኝ ከተማ ንጋት 12:00 ጀምረው ከፍተኛ ትንቅንቅን በማድረግ የአገዛዙን አራዊት ሠራዊት ከጋሣኝ ከተማ አሥለቅቀው ከጋሳኝ ዙሪያ ባሉ መዳረሻዎች ውጊያ ሢያደርጉ አርፍደዋል።በዚህ ሠዓታትን የፈጀ አውደ ውጊያ ጠላት በቁሥም በአካልም ከፍተኛ የሆነ ኪሣራን አሥተናግዷል። ከጋሳኝ ወደ ደብረ ታቦር የአገዛዙ አገልግሎት ሠጪ አምቡላንሶች ቁሥለኞችን በማመላለሥ ተጨናንቀው አርፍደዋል። ጠላት ሊያደርገው የነበረው ትልቅ ራዕዩ ቅዠት ሆኖ እንዲቀር ተደርጎበታል። ከንጋት 12:00 እሥከ ቀኑ 6:00 በቆዬው አውደ ውጊያ ታጋዮች ጠላትን አምበርክከዋል፤ ረፍርፈዋል። 👉 በድቅድቁ ጨለማ አብሪ ኮከብ የሆኑ የአማራ ፋኖዎች በብዛት እየተከሰቱ ነው። በዚህ ትግል ሻማ ሆነው እየቀለጡ ብርሐን እዬሠጡን፤ ክቡር መሥዋዕትነትን እየከፈሉና ለአማራነት ታምነው እየታገሉ እያለ አንዳንድ አዳፍኔዎች እና የፋኖነትን የተቀደሰ የትግል መንገድ ያልተረዱ አካላት የተሰሩ ድሎች ለሕዝብ አንዳይቀርቡ አለፍ ሢልም ባልዋሉበት ኩበት ለቀማን ሢከውኑ ይታያል። የአማራ ፋኖ መራራ ዕውነታን ይጋፈጣል። ያልሰራውን እንደሰራ አድርጎ አያቀርብም። ምክንያቱም ይህ ሠራዊት ለዕውነትና ለፍትሕ፣ ለታላቁ አማራ ሕዝብ ማንነትና ዘርፈ ብዙ ተጠዬቆች መልሥ ለመሥጠት እሥከ ሙሉ ቤተሰቡ ክቡር መሥዋዕትነትን የከፈለው ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፈለግ ተከታይ የሆነ የታጋይ ሥብሥብ ነውና። በተጨማሪም ደግሞ ከሕዝብ በላይ ምሥክርነትን የሚሰጥ የለም። ማን እንደሚታገልለት ሕዝባችን ጠንቅቆ ያውቃል። ሕዝብ ዳኛ ነው ይመዝናል። በሕዝብ ቀልሎ ላለመገኘት የፋኖን የተቀደሰ የትግል መንገድ እንከተል። ሥለሆነም ለሕዝብ የወጣ አካል ሕዝባዊነትን ብቻ መሠረት አድርጎ መታገል እንዳለበት የሜ/ጀ ውባንተ አባተ ኮር አበክሮ ማሣሠብ ይፈልጋል። የፋኖነትን ዕንቁ የትግል መንገድም እንዲከተሉ ያሥገድዳል። አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ፋኖነትን ምሽግ ላደረጉ አካላት ቅድሚያ ልክ አለመሆናቸውን ያሥገነዝባል፤ ካልተመለሱም ተገቢውን የማሥተካከያ ርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል። ኅልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የሚዲያና ሕ/ግንኙነት መምሪያ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ኮር (፩ኛ ኮር) https://t.me/fanozgonder
የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ተጋድሎ መረጃዎች! 👉የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ከደብረ ታቦር እስከ ባ/ዳር ያካለለ አውደ ውጊያ እያደረገ ነው:: አውደ ውጊያው የአለም ሳጋ አጋቾችን: የብልፅግና ሚሊሻ: አድማብተና: ካድሬና የብርሃኑ ጁላን ወራሪ ሰራዊትን ኢላማ ያደረገ ነው:: 👉ዛሬ የካቲት 26/2017 አም ከሌሊቱ 10:00 በጀመረው በዚህ እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር:- የሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ ኮር በታቀደ መልኩ እየተከናወነ ሲሆን በስርአቱ ጦር ላይ ቁሳዊ: አካላዊ: የህይወት መስዋእትነትና ስነ ልቡናዊ ስብራት ደርሶበታል:: በተለይ ደግሞ የአለም ሳጋው: የአለም በሩ እና የወጅው ድል ጠላት ሙሉ ለሙሉ የተደመሰሰበትና ካድሬ እስከውዲያኛው የተሸኘበት መሆኑን ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል:: 👉በሌላ መረጃ የ አማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር:- ዞዝ አምባ ንጉስ ክ/ጦር: ጥቁር አንበሳ ብርጌድ: ነብዩ አሳምነው ብርጌድ በቅንጅት ሚካኤል ደብርን ለመቆጣጠር የመጣን ወራሪ ሰራዊት ሲበትኑት ውለው በመጣበት እግሩ ፈርጥጦ ተመልሱዋል:: 👉ሌላው መረጃ ወደ በለሳ ያለው የጀግኖቹ ትንቅንቅ ነው:: የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ንስር በለሳ ቅጣው እጅጉ ክ/ጦር ጉሃላ: ስላሬ: አርባያና ሌሎችም ቀጠናዎች ላይ ጠላትን ሙትና ቁስለኛ አድርጎታል:: ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር https://t.me/fanozgonder
የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር አዲሱ ሎጎ ጥንታዊ የጥበብ: የቅርስ: የታሪክ: የጀግንነት: የቴክኖሎጅ: እንዲሁም የትምህርት ማእከልነታችንን በጎላ የሚያስረዳውን መታወቂያ ማንነታችንን የሚያሳዬውን እንካችሁ ተዋወቁት ብለናል። https://t.me/fanozgonder
የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር አዲሱ ሎጎ ጥንታዊ የጥበብ: የቅርስ: የታሪክ: የጀግንነት: የቴክኖሎጅ: እንዲሁም የትምህርት ማእከልነታችንን በጎላ የሚያስረዳውን መታወቂያ ማንነታችንን የሚያሳዬውን እንካችሁ ተዋወቁት ብለናል። https://t.me/fanozgonder
በወቅታዊ ጉዳይ ከማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ መግለጫ፤ ትግላችንን ለዳግም ባርነት ለሚያመቻቹን የብልጽግና እሳቤ አራማጆች አሳልፈን አንሰጥም!!! ቀን፦ ጥር 18/2017 ዓ.ም ትግላችን የኅልውና፣ የፍትሕ፣ የነጻነት፣ የሰብዓዊ ክብር ሆኖ እያለ ከፋፋይነት፣ ብልጣብልጥነት፣ አወናባጅነት፣ ከምንም በላይ በሕዝባችን ላይ የፖለቲካ ቁማርተኝነት እሳቤዎችን ከጀርባቸው አንግበው የአማራን ሕዝብ ለዳግም ባርነት ለመዳረግ በሞቱ የሚደራደሩ የአይሁድ ሸንጎ ማኅበርተኞችን ትናንት በአደባባይ ሕዝባችንም ሠራዊታችንም የተመለከተው የአደባባይ ሐቅ ነው። የብልጽግና ሥርዓት በቅብብሎሽ የተረከበውን አማራ ጠልነት አተልቆ፣ አደርጅቶ፣ አጎምርቶ በሰው ልጆች ታሪክ ታይቶ ተሰምቶ የማያውቅ እልቂት በአማራ ሕዝብና በአማራዊ ማንነት ላይ ውርጅብኝ በሆነበት በዚህ ሰዓት ላይ የአርበኝነት፣ የሐቅና የፍትሕ ትግላችንን በድርድር ሰበብ ለማይጠረቃ የፖለቲካ ፍትወታቸው መወጣጫ መሰላል ለማድረግ የሚሞክሩ አካላትን ለሠራዊታችንና ለሕዝባችን መግለጥ እንወዳለን። ከፋፋይነት፣ ይሉኝታ የለሽ ነጣቂነት፣ ልጓም አልባ የሥልጣን ፍትወት ላይ የሚናውዙ አካላት ትግላችንን ትናንት በሕዝባዊ ግንባር፣ ሕዝባዊ ሠራዊት፣ ፋሕፍዴን ዛሬ ላይ ደግሞ በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ጭንብል ተሸፍነው ትግላችንን ለማቃለል፣ ለማሳነስ የሄዱበት ርቀት እጅጉን አሳዝኖናል። በደቡብ ወሎ ዞን፣ ዳውንት ወረዳ ልዩ ቦታው ኩርባክ በተባለ ቦታ የጎንደር፣ የጎጃም፣ የሸዋና የወሎ የፋኖ ተወካዮች በሚል ከአፍሪካ ኅብረት፣ ከኢጋድ፣ ከአብይ አሕመዱ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን ተወካዮች ጋር ንግግሮች መደረጋቸውን ከሂደቱ ጀምሮ በየተቋሞቻችን የመረጃና ደኅንነት ዘርፎቻችን በኩል ስንከታተለው የቆየነው ጉዳይ መሆኑን ሳንገልጽ አናልፍም። እሚገርመው ደግሞ እነዚህ አካላት ድርድሩን ሚዲያ ላይ ወጥተው በመሪያቸው በአቶ እስክንድር ነጋ እና በፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊው በረ/ኘ/ር ጌታ አስራደ በኩል ገልጸውልናል። በዚህ መሠረት ከራሳቸው የሚዲያ ማብራሪያ ብቻ ተነስተን ተጠይቆችን በማቅረብ ሕዝባችንም ሆነ ሠራዊታችን ከዚህ እኩይ እሳቤ ራሱን እንዲጠብቅ እንፈልጋለን። የመጀመሪያው ተጠየቅ፦ አቶ እስክንድር ነጋ፣ ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ፣ ረ/ፕ/ር ጌታ አስራደ፣ ኮሎኔል ፋንታሁን ሙሃቤ እና ከሸዋ ማንነቱን በውል ያላወቅነው ግለሰብ በድርድር ሰበብ የኅልውና ትግሉን የማይመጥን፣ የአማራን ሕዝብ ጥያቄዎች በተወሰኑ ቡድኖች ፍላጎት ላይ ብቻ አንጠልጥሎ የጥድፊያው አንድምታ ምንድነው?፤ ያለሕዝብና ያለፋኖ ውክልና አማራውን ቀራንዮ አደባባይ ያቆመው ሥርዓት በተገኘበት መድረክ ላይ ለመገኘት ለምን ደፈራችሁ? ሁለተኛው ተጠየቅ፦ የአማራ ፋኖ በጎጃም ሙሉ በሙሉ፣ የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አማራ) ከሁለት ክፍለ ጦር ውጭ ሙሉ ለሙሉ፣ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ከሦስት ክፍለ ጦር ውጭ ሙሉ ለሙሉ፣ የሸዋ ፋኖም አንድነት ለመፍጠር የንግግር ሂደት ላይ መሆኑ እየታወቀ ድርጅት የምትሉት ተቋም በምንታገልበት የአማራ ሰማይ ሥር የት ነው ያለው? ሕዝባዊ ድርጅት በሚል በዲጂታል ሚዲያው የሚለፈፈው ከሐቅ የራቀ፣ ሙሉ ለሙሉ ከፋፋይ፣ መሪዎቹም ከተወሰኑት ወታደራዊ መሪዎች በስተቀር በግብር የተገለጠ ጸረ አማራ አቋም ያላቸው ስለመሆናቸው ማብራሪያና መግለጫችው ኅያው ምስክር ነው። ታዲያ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ዘጠና በመቶ የሚሆነውን የፋኖ ኃይል የያዘ ተቋም ነው የሚለው የእስክንድር ነጋ ንግግር የአማራን ሕዝብ የኅልውና ትግል ለማይጠረቃ ግለሰባዊ የሥልጣን ፍትወቱ መጠቀሚያነት እንጅ በእውነት ለአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል የወጣ ታጋይ አለመሆኑን ዳግም አረጋግጦልናል። ምክንያቱም የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት መሬት ላይ የሌለ የትግላችን መከፋፈያነት መጠቀሚያ ካርድ ለመሆኑ በየቀጠናው የሚገኙ ፋኖዎችን ጫፍና ጫፍ አቁሞ እስከማታኮስ የዘለቀ ርካሽ የፖለቲካ መቆመሪያ ድርጅት ስለመሆኑ የትናንት ገሐዳዊ ሁነቶች ያረጋግጣሉ። ድርድርም ውይይትም በመርኅ ላይ የተመሠረተ፣ ሐቀኛ የፖለቲካ ውክልናን የያዘ፣ የትግሉ መሠረተ ሃሳቦች ላይ የቆመ፣ የትግል ፍኖተ ካርታን በግልጽ በማስቀመጥ እነዚህን ሳይነጣጠሉ ሃሳብን የማቅረቢያ አመከንዮዎችን፣ ገሐዳዊ ሐቆችን ያለአንዳች የፖለቲካ ውስልትና በማቅረብ የሕዝብ ጥያቄ ማሸነፍ የሚችልባቸውን መደላድሎች መፍጠር ነው። ቅሉ አቶ እስክንድር ነጋ፣ ረ/ፕ/ር ጌታ አስራደ፣ ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ፣ ኮሎኔል ፋንታሁን ሙሃቤ እና ከሸዋ አንድ ግለሰብ በጋራ የተገኙበት ሸንጎ በመርኅ ደረጃ የድርድርን መሠረተ ሃሳቦችን ያላሟላ መሆኑን ማረጋገጥ እንወዳለን። ከዚህ ጋር ተያይዞ በዚህ የንግግር ሂደት ላይ የተገኙ ዓለምአቀፍ ተቋማት መሬት ላይ ከሌለ ስብስብ ጋር መቀመጣቸው ሥርዓታዊ የዘር ማጥፋት ድርጊት እየተፈጸመበት ያለውን የአማራን ሕዝብ ያላከበረና የማይመጥን አካሄድ በመሆኑ በቀጣይ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሐቀኛ እንዲሁም አካታች ውክልና ከሚሰጣቸው ልሂቃን ጋር ብቻ እንዲሆን መግለጥ እንወዳለን። በጥቅሉ ዳውንት ላይ የተካሄደው ድርድርም ይሉት ውይይት ሠራዊታችን የማያውቀው ምናልባትም የሚያወግዘው፤ ሕዝባችንን ያሳዘነ የፖለቲካ ቁማር ነው። ይህንን በድፍረት ለማለት የሚያስገድደን ጉዳይም ከእውነት የራቁ ድርጅታዊ ተረኮች (90% የፋኖ ኃይል የድርጅታችን አካል ነው፣ የወከልነውም ይህንን ግዙፍ ኃይል ያለው ፋኖ ነው) የሚሉ፣ የመርኅ፣ የፖለቲካ ውክልና፣ የተዓማኒነት እንዲሁም የአካታችነት የሚሉት ጥያቄዎችና መሰል ጉዳዮች ሲነሱ ውሃ የሚያነሳ ምላሽ የለም። መላው የአማራ ሕዝብ፣ መላው ሠራዊታችን፣ የሚዲያ አካላት ይህ ጉዳይ በቀላል የሚታይ ባለመሆኑ የአማራ ፋኖ በሸዋ፣ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር፣ የአማራ ፋኖ በጎጃም፣ የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አማራ) እና የአማራ ፋኖ ቢዛሞ እዝ ሕዝባችንን ለዳግም ባርነት አሳልፎ የሚሰጥ አደረጃጀትንም ሆነ አስተሳሰብ አጥብቀን ከማውገዝ ባሻገር የምንታገለው ጉዳይ ነው። የአማራ ፋኖ በጎጃም የአማራ ፋኖ በሸዋ የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አማራ) የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር እና የወለጋ ክፍለ ሃገር ፋኖ እዝ (ቢዛሞ)
ጥር 12/2017 ዓ.ም 🔥🔥ሻሁራ፣ አምቻሆ የደም ምድር🔥🔥 ዛሬ ጥር 12/2017 ዓ.ም የአገዛዙ ወራሪ ሠራዊት አለፋ ጣቁሳ ወረዳ፣ አምቻሆ ከተማ ላይ 12 ንጹሐንን በአደባባይ በመረሸን የሽብር ተግባሩን አጠናክሮ ቀጥሏል። በእለቱ ከሻሁራ ከተማ በ7 ኦራል ተጭኖ ወደ ደልጊ በጉዞ ላይ የነበረን ጨፍጫፊ ሠራዊት በአድዋ ክ/ጦር፦ ንጋት ጮራ ብርጌድ አማካይነት ከፍተኛ ምት ሲደርስበት በብስጭት አምቻሆ ከተማ ላይ ከጦርነት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸውን ሕጻናት፣ ሴቶች፣ አረጋውያንም ጭምር የተካተቱበት በቁጥር 12 ያህል ንጹሐንን በጠራራ ፀሐይ ረሽኖ ወጥቷል። በሞት አፋፍ ላይ የሚገኘው አብይ አሕመድ መራሹ ብልጽግና እና ጀሌዎቹ በጦር ወንጀል የሚጠየቁበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ በጎንደር የሚዲያና ሕ/ግንኙነት መምሪያ የአማራ ፋኖ በጎንደር ዋና ሰብሳቢ አርበኛ ባዬ ቀናዉ https://t.me/fanozgonder