- Последний пост
- 1 авг. 2025 г.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- am
- Категория
- Музыка (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
🤐ድክም ለምን እንደሆነ ባላቅም ድክም አለኝ ። ለምን አትበሉኝ ግን ስሙ ግራ ሚያጋባ ስሜት ብቻ መቅረት : ከሰው ጋር ሆነህ አለመታየት ; የፈለከውን አለማድረግ ;የሚያመጣው ስሜት ብቻ ስሙን ምን ልበለው ተስፋ መቁረጥ ወይስ ተስፋ ማጣት ? በሁለቱ መሀል ሆኖ መኖር ባልፈልገውም ያደክማል ። ያልፋል እኮ ግን አደከመኝ የኔ በምትላቸው ሰው ተረግጦ መኖር ለችግሩ የደረስክለት ሰው በችግርህ ሲደበር ማየት እና መነሳት አለመቻል ያደክማል ። ድካሜ ሲብስብኝ የሌለኝን ባህሪ መላበስ እየጀመርኩ ነው ነገ ለሚነጋው ዛሬን የለበሱትን ጭንብል አውልቀው እኔ ላይ ማንነታቸውን ለማሳየት ከሞከሩት ጋር አስተዛዘበኝ ግን ለበጎ ነው ብስሉን ከጥሬው መለየቴ ። ፌክ ማንነትን ስግብግብነትን ሳልፈልግ እናንተው አውርሳቹኛ ነገር ግን እራሳቹ የሰጣቹኝን ማንነት እራሳቹ ላይ ሳንፀባርቀው እንዳይደብራቹ ። ግን ላሁኑ ደክሞኛል ✌️😔 🥺ከተወዛገበቺዋ ሂወት የተገኘ ✍ አሚኮ
ዴት አረኩ ለሚል ቃል እንዴት ጥርስ ይወልቃል😁 "ዴት አርግ እንጂ " የሚለው የጓደኞቼ የቀን በቀን ጭቅጭቃጨው እንቅልፍ ሲነሳኝ ከርሜ ከርሜ የአንድ ለሊት ውሳኔዬ የሴጣን እጅ ተጨምሮበት ወኔ ሰጠኝ "ዴት አረጋለው" ማለት ጀመርኩኝ እያወራው ነው ለእኔ ግን አልታወቀኝም እጄን የሆነ ነገር መቶ ሲነካኝ ባነንኩ ድንጋጤዬ ከተኛውበት አልጋ ላይ አፈናጥሮ አወረደኝ ወዲያው የነካኝን ነገር ለማየት ብርድልብሱን ከአልጋው ላይ አንስቼ አየው አልጋው ላይ ምንም የለም ይበልጥ ፈራው የያስኩትን ብርድ ልብስ አራገፍኩ ምንም የለም ቀስ ብዬ እጄን ሳወርድ አሁን እዛው በቆምኩበት አጄን የሆነ ነገር ነካኝ የዚኔ ነበር መጀመሪያም ምን እንደነካኝ ያወኩት ለካ ይሄ መከረኛ እቃዬ ቆሞ ነው ። ንጋቱ እንዴት ይንጋ ባይታወቅም ነጋ የማታው ደንፉ አለቀቀኝም እቃዬም ዘራፍ እያለ ነው ወደ ስልኬ ገብቼ ቀን ከሌት የእናውራ ቴክስት ምትልክልኝን የድሮ የክላሳችን ዱርዬ ልጅ ስልክ ቁጥር አውጥቼ ደወልኩ ወዲያው ተነሳ ዝም ብዬ መቀባጠሬን ነው ማስታውሰው ዱርዬ ብቶንም መግደርደሩዋን አስታውሳለው ግን ወዲያው እሺታዋን አገኘው ። ያለኝን ብር እንዳለ ከ ባንክ አውጥቼ ሩም ይዜ ቁጭ አልኩ አይናፋር መሆኔ ሀገር ያወቀው ጉድ ነው የት ሄደ እሱ ነገር ማለት ጀመርኩ እንደ መረቀነ ሰው አልጋው ላይ ቁጭ ብዬ አፍጥጫለው ። በሩ ተከፈተ እሱዋ ናት ቀጭን ናት ሰላምታ ተለዋወጥን ዝም አልኩዋት አይን አይኔን ታየኛለች ከእሱዋ ፍቅርም መውደድም የለኝም ግን ፊት ለፊቴ ቁጭ ብላለች "ዴት አርግ" እንጂ ሚለው የጓደኞቼ ንግግር አይምሮዬ ላይ ይመላለስ ጀመር ። ዝምታችንን ፈርታው ይሆን እንጃ መቀባጠር ጀምራለች ሲያልበኝ እየታወቀኝ ነው ቀመቅፅበት ተነስቼ ከንፈሩዋን ሳም ሳረገው አፉዋን ወይኔ ብላ ያዘች ደንግጫለው ምን መደንገጥ ብቻ በድን ሆኛለው እራሴን እንዳሎንኩ ታውቆኛል አፏን የያዘችበት እጅ ዝቅ ስታረገው ደም ይወርድ ጀመር በኔ ቤት መሳሜ ነው ለካ በቴስታ ነው ያልኩዋት ዝም አልኩ ተረጋግታ ቀስ ብላ ምትታጠብ አስመስላ ከሞት እንደሚያመልጥ ሰው እየሮጠች በሩን በርግዳ ወጣች ምንም አላልኩም እራሴን መሆኔን ለማረጋገጥ የሩሙ መታጠቢያ ክፍል ገብቼ መስታወቱን ሳይ እራሴን አየው ከንፈሬ ደምቱዋል እስከማየው ድረስ ምንም አልተሰማኝም ነበር እንዴት ለምን የሚል ጥያቄ ምጠይቅበት አቅም ላይ አነበርኩም ፊቴን ታጥቤ ከመታጠቢያ ቤት ወጥቼ ቀጥታ ወደ አልጋው ሄጄ "ዴት አረኩ" የሚል ቃል ከአፌ እንደወጣ ጥቅልል ብዬ ተኛው ። ✍አሚኮ @fonkabcha1 @fonkabcha1
Channel name was changed to «የሂወት ፍልስፍና»
አንዳንዴ የተለየ ነገር እንዳለኝ አስብ እና ከሁሉም የተሻለ ሰው አርጌ እራሴን አያለው ከዛ ያቺን ሰአት እንዳለፍኩ ካሰብኩት ሀሳብ ላይ አንድ እርምጃ አለመራመዴን አስተውላለው አንድ እግሬን ባነሳ እንኩዋን ሁለተኛው እግሬ ማረፊያ እንደሌለው ሳይ እና ቅድም እራሴን ሳይበት በነበረው መነፅር ደግሜ እራሴን ሳይ ስራ ፈት ኮሜዲያን ይታየኛል ። እረጂ ደጋፊ ስለሌለኝ ላማር እልና ለካ ጤነኛ ነኝ እላለው ያሰብኩት መና ሲቀር ሰዎች ሲከዱኝ ሲበልጡኝ ችግሮች ሲፈራረቁብኝ የበታች ስሆን ከፈጣሪ ጋር ልጣላ ላማር እልና ጤነኛ መሆኔን ሳስብ ኩምሽሽ እላለው ፈጣሪዬን እፈራለው ግን እኮ አማኝ አደለውም አክራሪም አደለው እንዲው በዘበዝ ነኝ ግን ሁሉም ነገር ሲበላሽብኝ ሲጨልምብኝ ጤነኛ መሆኔን አስቤ ፈጣሪዬን በሌላ ሀሳብ እደበቀዋለው ይሄ ሆኑዋል ጉዞዬ ይሄ ሆኑዋል እርምጃዬ ። ✍ አሚኮ @fonkabcha1 @fonkabcha1
ትላንትና አንዱ ፌስቡክ ላይ ዳኜ ዋሌ ያወጣው ዘፈን አንደኛ ነው < አይዞሽ ኢትዮጵያውያዬ> ከሚለው ዉጪ አለ ከዛ comment ገብቼ ንዴቴን ገልጬ block አረኩት ከዛ ስለ ሃገሬ ማሰብ ጀመርኩ እንዴት በዚ ልክ ሚጠሉዋት ልጆችን ልታፈራ እንደቻለች ስለ እሱዋ ሲወራ ከሰሙ የሚያማቸው ልጆችን እንዴት ልታፈራ ቻለች እሺ ከምንስ የመጣ ነው አልኩ ጥያቄ ብቻ አሁንም እንደ አባቱ የሚያስብ ልጅ እራሱን ያጣ ነው የ አባቱን ድንቁርና እያስቀጠለ ነው የሰው ልጅ ውደ ምድር የመጣው እሱን እንዲሆን እንጂ የ አባቱን እንዲኖር አደለም ከአባቶቻችን ብልሃትን እንጂ ክፋትን አንዉሰድ መልካም የ አድዋ ድል በአለ ይሁንልን 💪 አመሰግናለሁ @fonkabcha1 @fonkabcha1
By the way ትቶሽ እረስቶሻል ግን አንቺ እስካሁን ልረሺው ኣልቻልሽም ሌላ ሰው ልትቀርቢ አልቻልሽም እሱ ሂወቱን እያጣጣመ እየኖረ ነው ያንቺ ሂወት ግን እዛው ላይ ነው what the fuck are u doing with ur past sis የትላንትናው ሂወትሽ የዛሬን ሂውትሽን ለምን እንዲያበላሽብሽ ትፈቅጃለሽ ያ ሰው እኮ ሌላ ሴት እያቀፈ ነው እየሳመ ነው ዋጋ ለማይሰጥሽ ሰው ሂወትሽን ለምንድን ነው ምትከፍዪው ደደብ አቱኚ ከሂወትሽ አውጪው ከዛ ላንቺ ሚገባሽን ሂወት ኑሪ እሱን ያጣሺው ስለማይገባሽ ነው አለቀ sigma girl ሁኚ 🔥 አመሰግናለሁ🙏 @fonkabcha1 @fonkabcha1
ወንድሜ እህቴ በሰዎች ዘንድ respect እንዲኖርህ ሰዎች ዘንድ value እንዲኖርህ ትፈልጋለህ so ታዳ ለምን ሰዎችን በደምብ ትቀርባለህ ሁሉንም ሰው ለምን በ አንድ አይነት መንገድ ትቀርባለህ በሰዎች ዘንድ value respect ወይም እነሱ ዘንድ ክብር እና ዋጋ እንዲኖርህ ከፈለክ ግንኙነትህን ገድብ hi hi 👋 ከመባባል ዉጪ ብዙ አታውራ ስላንተ እንዲያቁ አትፍቀድላቸው Classic man መሆን ከፈለክ ክብር ዋጋ እንዲኖርህ ከፈለክ እንዳትናቅ ከፈለክ ማንነትህን Open ክፍት አርገህ አትቅረብ ይህ ንግግር ዝም ብሎ ሊመስልህ ይችላል ነገር ግን አለመናቅ መከበር ዋጋ እንዲኖርህ እርካሽ አለመሆን ከፈለክ የኔ ከምትላቸው ሰዎች ዉጪ ከሌሎች ጋር ያለህን ግንኙነት ገድበው ይህ መልእክት ላንቺም ጭምር ነው እህቴ አመሰናለሁ 🙏 @fonkabcha1 @fonkabcha1
አጀብ ነው ሁሉም ይዘርፋል ስለራበኝ ፍቅር ይናገሩታል ይተነብዩታል ፍቅርን ያዩት የኖሩት እያላቸው ምርር ቀን መቶ አንስቷቸው ሲወድቁ ላያቸው ደስታ በስቶባቸው አለም ሲርቃቸው እንዴት አይብጠለጠ ክፉ ሰራቂ ሂወት ይሉታል እርኩስነው ሰራቂ የደስታ የከባድ ሀዘን ቋት አይ ፍቅር ስንቶች ይዘልፉታል በማያልቁ ቃላት እንዲ እንዳ እያሉ ምን ያክል ያሳዝናል አዙረው አንስተው ሲያፈርጡት ግን ሁሉም አልገባቸው በተለይ ላላዩት ከውጭ ቆመው በአሉባልታ የፍቅርን ስም ለሚሰጡት አንድ ነገር አለ አንተ ማትረዳው እነሱ ያዩት ባዶ ሆኖባቸው እኮነው ሲመጡ ወዳንተ ሂወት ብጠይቃቸው የተጎዱትን ፍቅር አውሯቸው በከተማው ሰው ሚባል ማይታያቸውን እንዲ ነው መልሳቸው አዎ ተጎድተናል ተጎሳቁለናል ከሰውነት ማረግ ሹልክ ብለን ወተናል ግን አሁንም ምንድን ነው መፍትሄው ብለህ ብጠይቀው መቼም ጠልተሀታል ብለህ ብጠይቀው እብድ ነው ምትመስለው ስላጣት ተጎድቶ ጠላሀት ስትለው ብር የጠፋበት ሰው ሲናደድ ካየኸው ወይም ሲያለቅስ ምን ያህል ነው ሚደሰተው ብሩ ቢመለስ በፍቅር ተጎድቶ የጨለለውም ፍቅሩ ቢመለስለት ደስታው ገደብ አይኖረውም አዎ ጠልሽቷል የፍቅር ስም ጠፍቷል እንደዛም ሆኖ ግን እየዋለ እያደር ይጣፍጣል ሚገቡበት በዝተዋል ብዙዎቹም ለመግባት አሰፍስፈዋል ለዛም ነው ያፃፈኝ ያስገረመኝን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ፍቅር ሆኖብን ✍ አሚር አደም 11/8/2015 @fonkabcha1 @fonkabcha1
ረመዳን ረመዳን እክ ማመስገኛችን ነው ይሄንን ያመጣልን መማር ሲፈልግ ነው ሀጢያት ሰርተናል አውቀንም ሳናውቀው ተውበት ያላረገ ገሀነም እኮ ነው ነገ ሚጠብቀው መፀፀት አለብን ነብስያን ተገፍቶ አላህ መሀሪ ነው አይጎልበት ከቶ ሀጢያታችን በዝቶ ጣራ እንኳ ቢነካ ፈጣሪ ታጋሽ ነው በሀጢያታችን ፋንታ ሀጅር እስክንተካ በዚ ቀን ካልቶበትን ምኑን ሰው ሆነው ሀጅር መሰብሰቢያ የረመዳን ወር ነው አንድ ሀጢያት ብሰራ አንዱ ነው ሚፃፈው ጥሩ ግን ብሰራ በሺ ተባዝቶ ነው ረመዳን እኮ የተውበት ግዜ ነው አላህን አጥብቀን ምስጋና እንድንሰጠው ረመዳን እኮ የአላህ ስጦታ ነው ለኛማ ሚሻለው እያወደስነው እሱን ማስደሰት ነው ረመዳንን በንፁ ልባችን ከፆምነው አላህማ አዛኝ ነው እሱማ መሀሪ ነው ✍አሚር አደም @fonkabcha1 @fonkabcha1
❦ ══•⊰❂ ጣፋጭ ግጥሞች ❂⊱•══ ❦ 😘አንዴ ብትሰጠኝ🤣 ቀምሼው አላውቅም እያልኳት አትስጭኝ ልብሱን ገለጥ አርጋ መልኩን ብታሳየኝ እኔው ሰፍ ብዬ አልኳት ስጭኝ ስጭኝ እርሷም ሳትሳሳ አንድ ጊዜ ብትሰጠኝ ሁሌም ስጭኝ አልኳት በጣም ነው የጣመኝ ስሙንም ስትነግረኝ እንዳይጠፋኝ ብላ ለካስ የማውቀው ነው ደስታ ከረሚላ!!! 😁😁😁 @fonkabcha1
🔥 እንቅልፍና ሴት 📝 ••••✍✍•••• በአንድ አልጋ ላይና በአንዲት ሴት ላይ ሶስት አይነት አንድነት ህልም-ፍቅር-ህይወት ከነዚህ መሀከል-ህልም የምንለው ፈቺ የሚፈልግ አሳሪ የሌለው የኔና ያንቺ ፍቅር ያልጋ ላይ ህይወት ነው ፍቅሬ ገብቶሽ እንደው ፍቅር እንደዚህ ነው። ከራስ አስበልጦ ሌላ ሰውን መውደድ ባንድ አለም ተከብሮ ባንዲት ሴት መዋረድ ክብር ነው ትርጉሙ በሴት ልጅ ተማርኮ ከዙፋን ላይ መውረድ። ፍቅሬ ገብቶሽ እንደው ህይወት እንደዚህ ነው ተኝቶ መነሳት የታወሰን መርሳት ያሰሩትን መፍታት ኖሮ ኖሮ መሞት። ፍቅሬ ገብቶሽ እንደው ሴትና እንቅልፍ ያው ነው የትኛውም ፍጥረት ባልጋው ያንቀላፋል ማንም ወንድ ነኝ ቢል በሴት ይሸነፋል። @fonkabcha1 @fonkabcha1
ያገር ልጅ ህይወቱ ፣ ከ ጽሁፍ ሲጣቀስ እንዴት ዝቅ ይባላል ፣ ከ ሽንት ቤቱ ጥቅስ? "Work as a slave live as a king" ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ስራው ማለት ኑሮው ፣ በሆነባት ሃገር እንደባርያ ስራ ፣ እንደ ንጉሶች ኑር ይለኛል ገራገር . . ተረግጦ ተረግጦ ተረግጦ ሲብሰው እንደ ነገስታት ኑር ፣ ይለኛል የዋህ ሰው . . የብሶቱን ጽዳጅ ሊጸዳዳው መጥቶ ፣ ባለ ሽንትቤቱ ዝቅ በል ይለኛል ብቸኛ ነው መሰል ፣ ዝቅ ያለው ህይወቱ . . ብቸኛ ነው መሰል ፣ መውረዴን ይመኛል ከዚህ በላይ ዝቅጠት ከዚህ በላይ ውርደት ፣ ከወዴት ይገኛል ፅድድቱን ረስቶ ሽንት ቤት በጻፈው ፣ ንጉሦ ነኝ ይለኛል . . አላወቀም እንጂ... ሳር ሳሩ እየታየ ፣ በተማሰ ቅጥር ጎምበስ ብሎ ሰርቶ ፣ ቀና ማለት ቢጥር ቁልቁል ነው ሚወረድ ፣ ዝቅ ባለ ቁጥር . . ወፊቱ አለቀሰች ፣ ዜማ ወጥቷት ዕምባ መወጣጫ ሲሆን ፣ ያጎንባሽ ሰው ጀርባ ዝቅ አልኩኝ እያለ ፣ ሰው ገደል ሲገባ . . ወፊቱ አለቀሰች ፣ እምባ ወጥቷት ዜማ የለፍቶ አደር መዳፍ ፣ ቀን ተ ቀን ሲደማ ማለዳ ማለዳ ፣ እሮሮ ስትሰማ <ምንአረኩ> እያለ ፣ ሰው አምላኩን ሲያማ። . . ወፊቱ በትዝብት ፣ እንዲ አለች አንድ ቀን <ከፍ ብለን ስናይ ፣ እኛም ከሰው ልቀን አይፍጠርህ እንጂ ፣ ከታችኛው መደብ አንተም ስትረግጥ ነው ፣ ከላይ ምትመደብ> . . አይፍጠር ነው መቼስ [ ቶማስ ትግስቱ ] @fonkabcha1
////የተጠገነ ቃል\\\ ------------------------------- የተሰበረ ልብ በምን ይጠገናል፣ ጊዜ ሽሮት እንኳን ጠባሳውም ያማል፣ በታወሰ ቁጥር ህመም ያገረሻል፣ ስንት ነው ተመኑ ዋጋ ወጥቶለታል፣ ያፈቀረን መግፋት እንደው ስንት ያወጣል። ከረፈደ ነቅተው የቦዘዙ አይኖች፣ በእርጅና የደከሙ የዛሉ ጉልበቶች። ማስተዋል ሲያገኙ ሲነቁ ከህልማቸው፣ እንደው ቢጠየቁ ቢሰማ ድምፃቸው፣ የገፉትን ማግኘት ይሆን ወይ መልሳቸው። እንጃ፣ ብቻ፣ ባላወኩት አለም በሃሳብ ተሰድጄ፣ የጎዳሽኝ አንቺን በሀሳብ አስረጅቼ። ድንገት ባስብ ጊዜ፣ ስለሰበርሽው ልብ ፀፀቱ ሲገልሽ፣ ከሀሳብ መለስ ብዬ ደብዳቤ ፃፍኩልሽ፣ እርሺኝና ኑሪ ሀዘን አይብዛብሽ፣ አለም አሰቃይታ ቁጭት አይግደልሽ፣ ሺህ ብታደሚኝም ይኸው ይቅር አልኩሽ፣ በሄድሽበት ሁሉ መልካሙ ይግጠምሽ፣ በእንባዬ አትሜ ይቅርታን ላኩልሽ፣ እውነት መልካሙ ይግጠምሽ። @fonkabcha1 @fonkabcha1
ምንድን ናት እናት ምንድን ናት ቃል አላት ብቻ ግን ውድ ናት ልትፈታ ማችል ቅኔ ናት ሴት እናት ስትሆን ሂወትም አይኖራት የኔ ለኔ የሚባል ጥቂት ደስታም የላት እና እናት ምንድን ናት ቃል አላት ምን ገልጿት ምን ልንላት ብቻ እናት ውድ ናት በየቦታው ያለች እንቁም ልዩም ናት ገጣሚ አሚር አደም ጥር 21/2015 @fonkabcha1 @fonkabcha1
🤰🤰🤰 ናፍቆትክን በሆዴ 🤰🤰🤰 ድምፅህን ለመስማት ጆሮዎቼ ቋምጠው እጆቼ አንገትክን በእጅጉ ናፍቀው ከንፈሬ ከንፈርህን በጣሙን ተርበው ትመጣለህ እያልኩ ደጅ ደጁን እያየው ግና አንተም የለህ ድምፅንም አልሰማው ይኸው ናፍቆትክን በሆዴ እንዳረገዝኩ አለው። 👇 ------------------------------------------- @fonkabcha1 @fonkabcha1
መቼ ነው ያንን ሁሉ አመሌን ትቼ አንቺን ሳገኝ የአይኔ ብሌን ፍቅርሽ መምሪያ ሆኖኝ ሁሉን እንቃለው ፍቅርሽ መኩሪያ ሆኖኝ መኖሬን ያስመኘኝ ያ የያዘኝ ፍቅርሽ ደስታን ያሳየኛል ሲነጋም ሲመሽ ውዷ የኔ ሂወት ሀላሌ እናቴ መቼ ነው አቅፈሺኝ ሚበራው ሂወቴ እቅፍሽ ውስጥ መኖርን እስክመኝ እስከለተ ሞቴ መቼ ነው......... መቼ ነው ምትስሚኝ በዛ ውብ ከንፈርሽ መች ነው ምታሳዪኝ ለኔ ያለሽን ስሜት ገዳዩን ፍቅርሽ መቼ ነው...... እራቀብኝ ፍቅርሽ ቃል ብቻ ሆነብኝ ብቻ ሞቴን በራሴ እጅ እንዳላረገው አንዱ አንቺን ጠልፎብኝ በጣሙን ናፍቆኛል በአካል ተገናኝተን እኔ ሳወራ አንቺ ስትሰሚኝ ስሜቴን ስገልፅልሽ ካንቺጋ መኖር እንደምመኝ ፈጣሪዬን አመሰገነዋለው እልሻለው አንቺን ስለሰጠኝ ግን መቼ ነው መቼ...... ✍አሚር አደም @fonkabcha1 @fonkabcha1
ማታ ስናወራ ሁሌ በየቀኑ ጧት ሳይሆን ማታ ከ ፍቅሬ ጋር ስናወራ ከዚ በላይ አለ እንዴ ደስታ ጭር ባለ ሰአት ስናወራ እርቀን ከሰው ጫጫታ ከወፎች የድምፅ እሩምታ እርቀን ስናወራ ይሰማኛል ጥልቅ የሆነ ደስታ ዘወትር ምደውለው ጠብቄ ሲመሽ ልነግርሽ እኮ ነው ጅላጅል ስላረገኝ ፍቅርሽ የኔ ጣፋጭ ስትይኝ እማ ከደስታ ብዛት እቀልጣለሁ ልክ እንደ ሻማ ፍቅርሽ እኮ ሀያል ነው ማብረጃ የሌለው ጉልበት እንዳለው ሰው አክት አሳያለው ግን እኮ በፍቅርሽ ሞቻለው ለዛ ነው እማ የውስጤን ለማውጣት ፍቅሬን ለመግለፅ ምሽትን ምመርጠው ከረብሻ እርቀን ጨረቃን እያየን ልገልፅልሽ ነው ይሄንን አቃለሁ እለፈልፋለሁ ብዙ አወራለሁ ስለያዘኝ ፍቅር አንዳንዴ ግን እሰጋለሁ ይሰለችሻል ብዬ ወይ ይልሻል ቅር እጓጓለሁ መሽቶ እስክናወራ ፍቅሬ ሙድ አለውኮ ስለፍቅራችን ማታ ስናወራ ✍አሚር አደም @fonkabcha1 @fonkabcha1
🤱 አንቺ ብቻ! 🤱 ወዳጄን አጣሁት ፡ በቸገረኝ ግዜ ዘመዴን አየሁት ፡ ሲከበኝ ትካዜ ጎረቤቴም ቀና ኑሮዬን ባቃና ወገኔ ነው ያልኩት ሲክደኝ ታዘብኩት አግኝቶ በማጣት ወድቆ በመነሳት አየሁት ሁሉንም ፡ ለካ ሰው የለኝም እማ ካንቺ ሌላ ፡ ዘመድ አይገኝም ልብሽ ያልተከፋ ፡ ፊትሽ ያልጠቆረ በችግር በደስታ ፡ አብሮኝ የነበረ በእዉነተኛ ፍቅር ፡ አብረሽኝ የቆምሽው ያንቺን ኑሮ ትተሸ ፡ ስለኔ የኖርሽው አጣኁልሽ አቻ ፡ ዞሬ በዚህ አለም እናቴ አንቺ ብቻ ፡ ኑሪልኝ ዘላለም፡፡ @fonkabcha1 @fonkabcha1
ለኔ ሀገሬ ነሽ ጧት ማታ ምስልሽ ብእሬን አውጥቼ አንቺን አስባለው ሁሉን እረስቼ መ መብላት አያሰኘኝ ሚጠጣም አይጠማኝ የኔ ህይወት እወቂው ፍቅርሽ ነው የጠማኝ ከሀገሩ ውጪ መሄጃ እንደሌለው አንድ ሚስኪን ሰው እኔም እንደሱ ነኝ ካንቺ ውጪ ምርጫም የለኝ ምለው በሀገር ከመጡ እስከ ጥግ ይኬዳል ባንቺ ከመጡ ግን እራሴን አሎንም ጭንቅላቴም ያብዳል የሀገርን ትርጉም ውጪ ያለ ያውራ ላንቺ ያለኝ ፍቅር ከቶም አያባራ ለኔ ሀገሬ ነሽ ቅያሪ የሌለኝ ከሞት በስተቀር ካንቺ ጋ ምንም አይለየኝ ✍አሚር አደም @fonkabcha1 @fonkabcha1
"" ♥️ፍቅሬ ብለህ ጥራኝ♥️"" አወ አብርን አድገናል አፍርም ፍጭተናል በአንድ ስሀን ብልተን ባንድ አልጋ አድርናል የልጅነት ነገር ሆኖብን ነገሩ ባሌ ሚስቴ ተባብለን ነበር እንዲት ደስ ይል ነበር አወይ ልጅነቴ የስውነት ግዝፍት የእድሜም መርዘም የአእምሮ መብስል ማስብ ማገናዘብም ተጅምሮ ዛሬ አይናፍርነትም መጣ ተከትሎ እንዱ ሲያለቅስ አንዱን ላያስቅ አባብሎ ልክ እንደ ልጅነት እንደጥንቱ ግዜ ድንገት ሳላስበው ነይ እህት አለም በምትለኝ ግዜ ውስጤን ይከፍዋል ከእህትነት ይልቅ ፍቅርህ ከብዶታል እንዳልተነፍስው እንዳልናገርው ልቤ ፍራተባ ይላል እስኪ በል ንገርኝ ልክ እንደልኝነት እንደ መልካሙ ጊዜ እንዲያ እንዳለፍንበት ፍቅሬ ብለህ ጥራኝ ካልሆነልህ ሚስቴ ተንፍስልኝና እኔም እፎይ ልበል ይፍታ ምኞቴ ፍቅሬ ብለህ ጥራኝ እንደ ልጅነቴ ባሌ ብዬ ልጥራህ ይሳካ ምኞቴ @fonkabcha1 @fonkabcha1