GEBEYA MEDIA
Статистикаየገበያ ሚዲያ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ወቅታዊና የተረጋገጡ መረጃ እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ! Follow us on: Facebook፦ facebook.com/share/1Z6NASMxns/ YouTube፦ youtube.com/@gebeyamedia Gebeya Business YouTube፦ youtube.com/@gebeyabusines ለመረጃ እና መልዕክት፦ 0948622222 ማርኬቲንግ ፦ 0963380000
- Последний пост
- 13:58
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 5
- Всего постов
- 69
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 108
- 1/48двое суток
- 1 269
- 1/72трое суток
- 1 369
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
በኮሪደር ልማት የተተከለ የመብራት ምሰሶ የገጨ አሽከርካሪ ፖሉን ወደ ነበረበት መልሶ አንድ ሚሊዮን ብር ተቀጣ ነሀሴ 1 /2018 (ገበያ ሚዲያ) በአርባምንጭ ከተማ ሲቀላ ክፍለ ከተማ በኮሪደር ልማት ሥራ የተተከለ ስማርት የመንገድ ዳር መብራት ምሰሶ (ፖል) በመግጨት ጉዳት ያደረሰ አሽከርካሪ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገልጿል። በዚህም አሽከርካሪው ላደረሰው ጉዳት ፖሉን ወደ ነበረበት በማስተካከል 1 ሚሊዮን ብር ቅጣት መቀጣቱን የአርባምንጭ ከተማ ደንብ አስከባሪ ጽ/ቤት አስታውቋል። የከተማው ደንብ አስከባሪ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰራዊት ገዛኸኝ ለተሽከርካሪ ባልተፈቀደ ቦታ ላይ በማሽከርከር በኮሪደር ልማት ሥራ የተተከለ ስማርት የመንገድ ዳር መብራት ምሰሶ (ፖል) በመግጨት ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ አሽከርካሪ የከተማው ደንብ አስከባሪ ከከተማ ትራፊክ ፖሊስ ጋር በመተባበር አሽከርካሪውን በቁጥጥር ሥር ማዋል መቻሉን አስረድተዋል። ጥፋተኛ የሆነው አሽከርካሪ ባደረሰው የጉዳት መጠን ካሣ ክፍያ መሰል ጥፋቶችንና በቸልታ የሚደርሱ የሕዝብ ሀብት ውድመትን ለማስቀረት አስተማሪ የሆነ ፖሉን ወደ ነበረበት በማስተካከል ሕጋዊ የአንድ ሚሊዮን ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጣ መወሰኑን የከተማው ደንብ አስከባሪ ኃላፊ አቶ ሰራዊት ገዛኸኝ ገልጸዋል። ለዚህ እርምጃ መሳካት ከህብረተሰቡ የደረሰው ጥቆማ ከፍተኛ ሚና እንደነበረው የገለጹት አቶ ሰራዊቱ ነዋሪው ላደረገው ትብብር ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ለከተማ እድገትና ለነዋሪዎቿ ጥቅም ሲባል በከፍተኛ ሀብት ወጪ ሆነው የተሰሩ የኮሪደር ልማት ጥቅል ሥራዎችንና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን በሚያበላሹና ደንብ በሚተላለፉ አካላት ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አቶ ሠራዊት አክለው አስገንዝበዋል፡፡
24 ሚሊዮን ዜጎች የንባብ አገልግሎት ማግኘታቸውን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ገለጸ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ2019 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ ላይ የሚመክር ሀገራዊ ጉባኤ በዛሬው እለት ማካሄድ ጀምሯል። በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ 24 ሚሊዮን ዜጎች የንባብ አገልግሎት ማግኘታቸውን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቋል፡፡ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ፣ የሦስት ዓመት መካከለኛ ዘመን ዕቅድና የ2019 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ ላይ የሚመክር ሀገራዊ ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል። በጉባኤው መክፈቻ መርሃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የባህል እና ስፖርት ሚኒስትሯ ሸዊት ሻንካ፤ ባለፈው አንድ ዓመት በባህል፣ በኪነ-ጥበብና በስፖርት ዘርፎች የተመዘገቡ ዋና ዋና ስኬቶችን ለታዳሚዎች አቅርበዋል። ሚንስትሯ በንግግራቸው እንደጠቆሙት፣ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት ባደረገው ጉልህ እንቅስቃሴ 24 ሚሊዮን ዜጎች የንባብ አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉ ትልቅ ስኬት ሆኖ ተመዝግቧል። በባህልና ኪነ-ጥበብ ረገድም ባለፈው አንድ ዓመት 47 የብሔር ብሔረሰቦች የዘመን መለወጫ በዓላትና አምስት ሀገራዊ ክብረ በዓላት በድምሩ 52 በዓላት የሕዝቦችን አብሮነት በሚያጠናክር መልኩ በሰላም መጠናቀቃቸውን ጠቁመዋል። ከዚህ ባሻገርም የኢትዮጵያን ብዝኃነትና ጥበብ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ በሚከናወነው “ኪን ኢትዮጵያ” መርሃ-ግብር አማካኝነት በቻይና በሦስት መድረኮች፣ በሩሲያ በሁለት፣ በጃፓንና ኬንያ በእያንዳንዳቸው በአንድ መድረክ እንዲሁም በሀገር ውስጥ በ15 መድረኮች ስኬታማ የኪነ-ጥበብ ትውውቅ ተደርጓል ብለዋል።
https://am.gebeyaethiopia.com/p/144 ኢትዮጵያ በዲጂታል ጥቃት ተጋላጭነቷ ከአፍሪካ 5ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን የኢንተርፖል ሪፖርት አመላከተ | Geb… ኢትዮጵያ በዲጂታል ጥቃት ተጋላጭነቷ ከአፍሪካ 5ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን የኢንተርፖል ሪፖርት አመላከተ ኢትዮጵያ በዲጂታል ጥቃት ተጋላጭነት እ.አ.አ በ2025 ከአፍሪካ 5ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን ኢንተርፖል አዲስ ባወጣው የሳይበር ስጋት ግምገማ ሪፖርት አመላክቷል። ኢትዮጵያ በአህጉሪቱ በ2025 ከተመዘገቡት የዲጂታል ጥቃት ተጋላጭነቶች 3.3 በመቶ የሚሆነውን የምትሸፍን ሲሆን ይህም ፈጣን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞዋ ከሳይበር ደህንነት መከላከያ እና ተቋማዊ ዝግጁነት ጋር አለመጣጣሙ ተገልጿል። ዝርዝሩን ያንብቡ!
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
በሰሜን ሸዋ ጻድቃኔ ማርያም ገዳም በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት አለፈ ሐምሌ 27/2018 (ገበያ ሚዲያ) በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሥር በሚገኘው ታሪካዊው የጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም በከሰተ ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ። አደጋው ከክረምቱ ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ሳቢያ የተከሰተ ሲሆን ለጸበል፣ ለሱባኤና ለንግሥ ከአራቱም አቅጣጫዎች በገዳሙ ተገኝተው በነበሩ ምዕመናን ላይ ጉዳቱ መድረሱ ታውቋል። ከሟቾቹ በተጨማሪ በ5 ሰዎች ላይ የከባድና ቀላል አካል ጉዳት መድረሱ የተገለጸ ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች በአሁኑ ወቅት የሕክምና እርዳታ እየተደረላቸው ይገኛል። የአደጋውን መባባስ ተከትሎ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በአካል በመገኘት ሕይወታቸው ላለፉት ወገኖች ጸሎተ ፍትሐት ያደረሱ ሲሆን፤ ለተጎዱትና ለተጨነቁት ምዕመናን አባታዊ ቃለ በረከትና የማጽናኛ ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል። ሀገረ ስብከቱ በደረሰው ድንገተኛ አደጋ ጥልቅና መሪር ኀዘን የተሰማው መሆኑን ገልጾ ለሞቱት ዕረፍተ ነፍስን ለተጎዱት ፈጣን ፈውስን እንዲሁም ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ተመኝቷል።
አሁን እየሠራን ያለነው ለልጆቻችን ነው፤ ተስፋን ነው የምንተክለው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ/ር ) ሐምሌ 27 /2018 (ገበያ ሚዲያ) አሁን እየሠራን ያለነው ለልጆቻችን ነው፤ ተስፋን ነው የምንተክለው፤ ነገን ነው የምንተክለው፤ ኢትዮጵያን ነው የምናለብሰው፤ ይሄ ደግሞ የሚሆነው በትብብር እና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወጥቶ በሚያደርገው ጥረት ነው" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ። ኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ዓመታት በተከታታይ ስታከናውነው የቆየውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር አስቀጥላ ዛሬ በአንድ ጀምበር ከ800 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን የመትከል ታላቅ ሀገር አቀፍ ዘመቻ በማካሄድ ላይ ትገኛለች። ተስፋን እንትከል በሚል መሪ ቃል ከማለዳው ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ በተጀመረው በዚህ ንቅናቄ እስካሁን ባለው ሂደት በርካታ ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸው ተገልጿል። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት በመደመር ኤ አይ ዩኒቨርሲቲ ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ከኮፕ32 ብሔራዊ ኮሚቴ ጋር በመሆን የራሳቸውን ዐሻራ አኑረዋል። ኢትዮጵያ መብላት፣ መልማት፣ ማደግ እና መሠልጠን አለባት የሚሉ ትላልቅ ህልሞች ሊሳኩ የሚችሉት አስተማማኝ መሠረት ሲጣል ብቻ መሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር ዐቢይ ይህም በኢኮሎጂ መሠረተ ልማት አፈርን፣ ውኃንና ተራራን በመጠበቅ እውን እንደሚሆን አስረድተዋል። እንዲሁም ዛፍ ለዛሬ ሳይሆን ለነገ ትልቅ ትርጉም እንዳለውና ምግብ፣ ጥላ፣ ውበት እንዲሁም የሚሸረሸርና የሚጠፋ ሃብትን የሚጠብቅ ዘብ መሆኑን አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ ላለፉት ዓመታት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ያስመዘገበችው ተጨባጭ ውጤት ዓለም አቀፍ ትኩረት ማግኘቱን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህም ኮፕ32 የተሰኘው ትልቁ የዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ስብሰባ በኢትዮጵያ እንዲዘጋጅ ውሳኔ ላይ መደረሱ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ከሀገር ውስጥ አልፎ ሌሎችም ሀገራት የኢትዮጵያን ተሞክሮ እንዲከተሉ አበረታች ሁኔታዎችን መፍጠሩን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያውያን በጀመሩት የተባበረ መንገድ ቀኑን ሙሉ በመረባረብ የዕለቱን የ800 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ ግብ ከፍጻሜ እንዲያደርሱ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
https://am.gebeyaethiopia.com/p/143 የኦላ ኢነርጂ እና የቶታል ኢነርጂ የግዢ ስምምነት ታገደ | Gebeya Media የኦላ ኢነርጂ እና የቶታል ኢነርጂ የግዢ ስምምነት ታገደ የኦላ ኢነርጂ እና የቶታል ኢነርጂ ማርኬቲንግ ኢትዮጵያ የግዢ ስምምነት በኢትዮጵያ የነዳጅ ማደያ ገበያ ላይ ከፍተኛ የሞኖፖል አደጋ ሊፈጥር ይችላል በሚል ስጋት በቁጥጥር ባለስልጣናት መታገዱ ተገለጸ። የኢትዮጵያ ንግድ ውድድርና የተጠቃሚዎች ጥበቃ ባለስልጣን ሁለቱ ዓለም አቀፍ የኢነርጂ ድርጅቶች በፓሪስ ያደረጉትን የዚህ ግዙፍ ስምምነት የማጽደቅ ሂደት በጊዜያዊነት ማራዘሙ ተነግሯል። እገዳው የተጣለው የታቀደው ውህደት የሀገሪቱን የነዳጅ ችርቻሮ ገበያ ግማሽ ያህል ድርሻ በአንድ ኩባንያ እጅ ብቻ እንዲገባ በማድረግ ገበያውን ሊቆጣጠር ይችላል በሚል ስጋት ነው። ዝርዝሩን ያንብቡ!
የመኖሪያ ቤት አከራይ ተከራይ የውል እድሳት ጊዜ እስከ ነሐሴ 30 ተራዘመ ሐምሌ 25 /2018 (ገበያ ሚዲያ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመላው ከተማዋ የሚገኙ የግል መኖሪያ ቤቶች የአከራይ ተከራይ የውል እድሳት እና ምዝገባ ጊዜ እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ማራዘሙን አስታውቋል። ቀደም ሲል የነበረው የውል እድሳት ማጠናቀቂያ ጊዜ እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ተወስኖ የነበረ ቢሆንም ከህብረተሰቡ በተነሱ ጥያቄዎች እና በተፈጠረው መጨናነቅ ምክንያት ቀኑ ሊራዘም እንደቻለ ተጠቅሷል። የዕድሳት ጊዜ መራዘሙ ነዋሪዎች ያለምንም ጫና እና መጨናነቅ ሂደቱን እንዲያጠናቅቁ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ተገልጿል። የከተማ አስተዳደሩ ይህንን የውል እድሳት የጀመረው የዜጎችን የኑሮ ጫና ለመቀነስ እና በኪራይ ገበያው ላይ የሚስተዋሉ ሕገ-ወጥና ዘፈቀዳዊ አሰራሮችን በዘላቂነት ለመግታት በማሰብ የቤት ኪራይ ጭማሪ ጣሪያ 11.5 በመቶ እንዲሆን ከወሰነ በኋላ መሆኑ ይታወሳል። አከራዮች እና ተከራዮች ይህንን የተራዘመ ጊዜ በመጠቀም አስፈላጊውን መረጃ በመያዝ በሁሉም ክፍለ ከተማዎች ቤቶች አስተዳደር ጽህፈት ቤቶች፣ በየወረዳው በተዘጋጁ የውል ቦታዎች እንዲሁም በሁሉም ክፍለ ከተማ አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በመገኘት የውል እድሳት አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ የቢሮው መረጃ አመልክቷል።
https://am.gebeyaethiopia.com/p/141 በግል ትምህርት ቤቶች የክፍያ ጭማሪ እና ምዝገባ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ | Gebeya M… በግል ትምህርት ቤቶች የክፍያ ጭማሪ እና ምዝገባ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ 👉 በ2019 የትምህርት ዘመን የክፍያ ጭማሪ ማድረግ የሚችሉት 166 የግል ትምህርት ቤቶች ብቻ ናቸው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች የ2019 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ሂደት፣ የክፍያ ጭማሪ እና የተለያዩ የግብዓት ጥያቄዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ። ባለፉት ዓመታት የግል ትምህርት ቤቶች በሚጥሏቸው የወርሃዊ ክፍያ ዋጋዎች፣ የምዝገባ ዋጋዎች፣ የዩኒፎርም ሽያጮች እንዲሁም እንደ ሳሙና እና ሶፍት ባሉ በዓይነት በሚጠየቁ የትምህርት ቤት ግብዓቶች ምክንያት በወላጆች ዘንድ ሰፊ እና ተደጋጋሚ ቅሬታዎች ሲነሱ መቆየታቸው ይታወሳል። ዝርዝሩን ያንብቡ!
አርሰናል በታሪኩ ከፍተኛውን የተጫዋች ሽያጭ ዋጋ ያስመዘገበበት አኃዝ እስከ አሁን ድረስ እንዳልተሰበረ ታቃላቹ? ሐምሌ 18/2018 (ገበያ ስፖርት) እጅግ ተወዳጅነትን ባተረፈውና በርካታ ታላላቅ ዝውውሮች በሚከናወኑበት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ አርሰናል ከዚህ ቀደም ከፈጸመቻቸው የተጫዋቾች ሽያጮች ሁሉ እጅግ ከፍተኛው ገንዘብ የተገኘበት በአሌክስ ኦክስሌድ ቻምበርሊን ነው። አርሰናል በ2017 ቻምበርሊንን ለሊቨርፑል አሳልፎ የሸጠበት የገንዘብ መጠን 35 ሚሊየን ፓውንድ ሲሆን ይህ ዝውውር ከተፈፀመ ዓመታት ተቆጥረው አዳዲስ ተጫዋቾች ገቢና ወጪ ቢደረጉም .... እስከ አሁን ድረስ በአርሰናል ታሪክ ውስጥ በክለቡ ተጫዋች ሽያጭ የተገኘ ትልቁና ክብረ ወሰኑን ይዞ የሚገኝ ብቸኛ ከፍተኛ ዋጋ ሆኖ መዝገቡ ላይ ዘልቆ ቀጥሏል። ይህንን ሪከርድ ማንን ሽጠው ማሻሻል ይችሉ ይሆን የሚለው በቀጣይ የሚጠበቅ ነው ! በ ሮቤል አብርሃም
ከ2.5 ሚሊዮን በላይ የትራፊክ ደንብ ተላላፊዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ ሐምሌ 18 /2018 (ገበያ ሚዲያ) በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ወራት በተከናወነ የቁጥጥር ሥራ ከ2.5 ሚሊዮን በላይ የትራፊክ ደንብ በፈጸሙ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን አስታውቋል። የተወሰደው እርምጃ በድግግሞሽ የተቀጡ አሽከርካሪዎችን ቁጥር ያካተተ መሆኑን የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አማረ ታረቀኝ ገልጸዋል። ከጠቅላላው የደንብ ጥሰቶች መካከል ከ300 ሺህ በላይ የሚሆኑት የትራፊክ መብራት የጣሱ አሽከርካሪዎች መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን እርምጃ ከተወሰደባቸው ተሽከርካሪዎች መካከልም ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት እነዚህ አካላት ናቸው። በከተማዋ እየተከሰተ ላለው የትራፊክ አደጋ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዘው ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር መሆኑን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት በ9 ወራት ውስጥ ብቻ በትራፊክ አደጋ ከ287 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የገለጹት አቶ አማረ አደጋውን ለመቀነስ ሰፊ የቅንጅት ሥራዎች መሠራት እንዳለባቸው አሳስበዋል። በሌላ በኩል ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በአሽከርካሪዎች ላይ ብቻ ሳይገደብ ሕገ-ወጥ ንቅናቄ በፈጸሙ እግረኞች ላይም እርምጃ ወስዷል። በዚህም መሠረት የደንብ ጥሰት በፈጸሙ 60 ሺህ 528 እግረኞች ላይ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን ከ100 እስከ 150 ብር ቅጣት መቀጣታቸው ተገልጿል። ከተቀጡት እግረኞች መካከልም የጆሮ ማዳመጫ በማድረግ መንገድ ያቋረጡ እግረኞች እንደሚገኙበት አሃዱ ሬድዮ ዘግቧል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ለክረምት ወቅት ወንጀሎች ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳሰበ ሐምሌ 17 /2018 (ገበያ ሚዲያ) የክረምት ወቅት መግባቱን ተከትሎ ሊከሰቱ የሚችሉ የወንጀል ድርጊቶችን ለመከላከል ህብረተሰቡ ልዩ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳስቧል። የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ቶማስ እሸቴ እንደገለፁት በክረምት ወቅት የሰዎች እንቅስቃሴ በመገደቡ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ወንጀለኞች ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ሊፈጽሙ ይችላሉ። በተለይም የመኖሪያ ቤት ሰብሮ መግባትና የቤት ውስጥ ንብረቶችን የመስረቅ ወንጀሎች በዚህ ወቅት በብዛት ሊያጋጥሙ እንደሚችሉ ኮማንደሩ አስረድተዋል። ከግል መኖሪያ ቤቶች በተጨማሪ በተለያዩ ተቋማትና መጋዘኖች ላይ ያነጣጠሩ የስርቆት ድርጊቶች ሊከሰቱ እንደሚችሉ በመረዳት ተገቢው ጥበቃ ሊደረግ ይገባል ተብሏል። በሌላ በኩል ደግሞ የተሽከርካሪዎች መለዋወጫ ዕቃዎችን መዝረፍና ከተሽከርካሪ ውስጥ ንብረቶችን መስረቅ በክረምት ወቅት በስፋት ከሚታዩ የወንጀል አይነቶች መካከል የሚጠቀሱ መሆናቸውን ኮማንደር ቶማስ አስታውሰዋል። እነዚህን ህገ-ወጥ የወንጀል ድርጊቶች በዘላቂነት ለመከላከል ፖሊስ ከማህበረሰቡና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል። ፖሊስ ወንጀልን አስቀድሞ ለመከላከል የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለፁት ኃላፊው፤ ለዚህ ስኬት የህዝቡ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
እውቁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እና የፊፋ ዋና ዳኛ አንቶኒ ቴይለር ከእግር ኳስ ዳኝነት በይፋ ጡረታ መውጣቱን አሳወቀ! ሐምሌ 14/2018 (ገበያ ስፖርት) የ47 ዓመቱ ዳኛ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ግርማ ሞገስ በተሞላ የዳኝነት ህይወቱ አጠቃላይ 831 ጨዋታዎችን መርቷል። ለ16 ዓመታት በፕሪሚየር ሊጉ ቆይታው 432 ጨዋታዎችን መርቷል። እንደ ኤፍኤ ዋንጫ (2017 እና 2020) እና ሊግ ካፕ ፍጻሜዎችን የመሳሰሉ ትልልቅ የሀገር ውስጥ ግጥሚያዎችን ዳኝቷል። ለ14 ዓመታት በፊፋ ዓለም አቀፍ መደብ ውስጥ የቆየ ሲሆን፤ በሁለት የዓለም ዋንጫዎች (2022 እና 2026)፣ በሁለት የዩሮ ዋንጫዎች (2020 እና 2024) እንዲሁም የዩሮፓ ሊግ እና የኔሽንስ ሊግ ፍጻሜዎችን በመምራት ታላላቅ ሃላፊነቶችን ተወጥቷል። የዳኝነት ጉዞውን ያጠናቀቀው በዩናይትድ ስቴትስ በተደረገው የ2026 የዓለም ዋንጫ የፖርቹጋል እና ስፔን ፍልሚያን በመምራት ነው። አንቶኒ ቴይለር እኔደተናገረው "በከፍተኛ ደረጃ ዳኛ ሆኖ ማገልገል እጅግ ትልቅ ክብር ነበረው ነገር ግን ጫናው ከፍተኛ እና ክትትሉ የማያቋርጥ ነው ፤ አሁን አዳዲስ ስራዎችን ለመጀመር እና ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ለመሸጋገር ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው" በማለት የውሳኔውን ምክንያት ገልጿል። በሮቤል አብርሃም @gebeyasport
видео или голосовое, без подписи