tgindex
Gebeya Media - ገበያ

Gebeya Media - ገበያ

Статистика

Welcome to Gebeya media ! Gebeya Media is an internet media company provides you with various business ideas, job options and market research, as well as various ideas that our unemployed citizens can benefit from.

Последний пост
17 июл.
Последнее чтение
12:48
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
английский
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
3 584
+1 за 3 дн.
Сутки
+1
+0,03%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
902
20 постов
Вовлечённость
25,2%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 17 июл.51022из gebeyanews

    አዲስ አስመጪዎችና ላኪዎች የብሔራዊ ባንክ የሂሳብ ቁጥርን በአንድ መስኮት አገልግሎት እንዲያገኙ ተፈቀደ ሐምሌ 10/2018 (ገበያ ሚዲያ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ አስመጪዎችና ላኪዎች የብሔራዊ ባንክ የሂሳብ ቁጥርን በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአንድ መስኮት አገልግሎት በኩል እንዲያገኙ ፍቃድ ሰጥቷል፡፡ ባንኩ ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር አዲስ ፍቃድ ላወጡ አስመጪዎችና ላኪዎች የብሔራዊ ባንክ የሂሳብ ቁጥር አሰጣጥን የሚያቀል አዲስ የዲጂታል አገልግሎት አስተዋውቋል፡፡ አገልግሎቱ የባንኩ የሂሳብ ቁጥሮች በጉምሩክ ኮሚሽን አንድ መስኮት አገልግሎት በኩል ያለምንም ውጣ ውረድ እንዲሰጥ በማስቻል አስተዳደራዊ ሂደቶችን የሚቀንስና ፈጣን የንግድ አሰራርን የሚደግፍ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ አዲሱ አገልግሎት የሚመለከተው ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሂሳብ ቁጥር ለሚያወጡና አዲስ ፍቃድ ላገኙ አስመጪዎችና ላኪዎች ብቻ መሆኑም ተገልጿል። ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሂሳብ ቁጥር ያላቸው የንግድ ተቋማት ለሁሉም የገቢና የወጪንግድ ግብይቶቻቸው ይጠቀሙበት በነበረው ነባር ቁጥር መጠቀም እንደሚችሉ ባንኩ ገልጿል፡፡ በተጨማሪም ይህ አሰራር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከገቢና ወጪ ንግድ ጋር የተያያዙ አገልግሎቶችን ለማዘመን፣ የንግድ አሰራርን ምቹ ለማድረግ እንዲሁም የዲጂታል የሕዝብ አገልግሎት አሰጣጥን ለማጠናከር እያከናወነ ያለው ጥረት አካል መሆኑንም አመልክቷል፡፡

  • 14 июл.5841из gebeyasport

    የዳኝነት ውዝግብ በእንግሊዝ እና በአርጀንቲና ግማሽ ፍፃሜ በእንግሊዝ ሚዲያዎች የቀረበው የሰላ ትችት ! ሐምሌ 07፤2018 (ገበያ ስፖርት) ለአርጀንቲና እና ለእንግሊዝ የዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ አሜሪካዊው ዳኛ ኢስማኤል ኤልፋት መመረጣቸው በእንግሊዝ ሚዲያዎች ዘንድ ከፍተኛ መነጋገሪያ እና ቅሬታን ፈጥሯል። የብሪታኒያ ታዋቂ ጋዜጦች በየግንባር ገጾቻቸው ላይ እንደዘገቡት የዳኛው መመረጥ አድሏዊነት የተሞላበት መሆኑን በመግለጽ ጥርጣሬያቸውን እያሰሙ ይገኛሉ። ዴይሊ ሜይል በዘገባው በዓለም ዋንጫው ላይ "ማጭበርበር አለ" የሚሉ ወሬዎችን በመጥቀስ፣ ሊዮኔል ሜሲ በግማሽ ፍጻሜው "የራሱን ተወዳጅ ዳኛ" ማግኘቱን በግልጽ አስፍሯል። በበኩሉ ዘ ሰን የተሰኘው ጋዜጣ "ከኳታር እስከ ሚያሚ የዘለቀው የአለም ዋንጫው ወዳጅነት ዛሬም ሊቀጥል ተቀጥሯል" በማለት ፊፋ ሜሲን ቀደም ብለው ከታደጉት ዳኞች መካከል መምረጡ አጠያያቂ መሆኑን በመጠቆም ትችቱን ሰንዝሯል። ዴይሊ ሚረር እንዲሁ "አርጀንቲና የፈለገችውን አግኝታለች" ሲል፣ የዳኛው መመረጥ ለቡድኑ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር መሆኑን ገልጿል። ይህ ውዝግብ እንዲቀጣጠል ያደረገው ዋና ምክንያት ሊዮኔል ሜሲ የሚጫወትባቸው ቡድኖች ኢንተር ሚአሚን ጨምሮ ኢስማኤል ኤልፋት በዳኝነት የመሩት ጨዋታዎች በሙሉ አሸናፊ መሆናቸው ሲሆን ይህ ስታቲስቲካዊ መረጃ በእንግሊዝ ሚዲያዎች ዘንድ በዳኛው ገለልተኝነት ላይ ትልቅ ጥርጣሬ እንዲያድርባቸው አድርጓል። በ ሮቤል አብርሃም @gebeyasport

  • 13 июл.553из gebeyanews

    https://gebeyaethiopia.com/p/127 ሳዑዲ አረቢያ 1 ሺህ 971 ኢትዮጵያውያንን በንጉሣዊ ምሕረት እንደለቀቀች ተገለጸ በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ለመታደግ በተደረገው የዲፕሎማሲ ጥረት 1 ሺህ 971 ኢትዮጵያውያን የንጉሣዊ ምሕረት ተጠቃሚ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። እነዚህ ዜጎች በሳዑዲ አረቢያ የሕግ ሒደትና የፍርድ ውሳኔ ላይ የነበሩ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት በተከታታይ በረራዎች ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ እንደሚገኙ ሚንስቴሩ ገልጿል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት እንደገለጸው የኢትዮጵያ መንግሥት በውጭ አገር ለሚኖሩ ዜጎቹ ደኅንነት፣ ጥበቃና የቆንስላ ድጋፍ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣል። ዝርዝሩን ያንብቡ!

  • 12 июл.5601из gebeyasport

    ዝላታን ሰለ ለሊቱ ጨዋታ ዳኝነት ...! ሐምሌ 04፤2018 (ገበያ ስፖርት) የእግር ኳስ ኮከቡ ዝላታን ኢብራሂሞቪች በዓለም ዋንጫው የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ላይ የሲውዘርላንዱ ተጫዋች ኤምቦሎ በፈጸመው የተጋነነ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ዳኛው የወሰዱትን እርምጃ አድንቋል። ዝላታን በሰጠው አስተያየት ዳኛው የወሰዱት ውሳኔ ትክክለኛ መሆኑን በመግለጽ፣ እንደ ኤምቦሎ ያለ የሰውነት ቁመና እና ልምድ ባለው ተጫዋች በዓለም ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ደረጃ እንዲህ አይነት ህጻንነት የሚታይበት ድርጊት መፈጸም ተገቢ አለመሆኑን ተናግሯል። በቅርብ ጊዜያት ብዙ ሰዎች የቪዲዮ ረዳት ዳኛንት (VAR) በተመለከተ አሉታዊ አመለካከት እያሳዩ ቢሆንም፣ በዚሁ ጨዋታ ላይ የታየው የቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና የዳኞች ውሳኔ ግን ፍጹም ትክክለኛና ተገቢ ነበር ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል። በ ሮቤል አብርሃም @gebeyasport

  • видео или голосовое, без подписи

  • 9 июл.6861из gebeyasport

    መድፈኞቹ ከጉማሬሽ ጋር ስምምነት ላይ ደረሱ! ሐምሌ 2/2018 ዓ/ም (ገበያ ስፖርት) አርሰናል ከብሩኖ ጉማሬሽ ጋር በአምስት ዓመት ኮንትራት መስማማቱ ተዘግቧል። በዝውውር መስኮቱ በአርሰናል የዝውውር ራዳር ክትትል ውስጥ የነበረው ብራዚላዊው ቡርኖ ጉማሬሽ ወደ ሰሜን ለንደን ለማምራት ከመድፈኞቹ ጋር የተስማማ ሲሆን ለክለቡ ኒውካስትልም የልቀቁኝ ጥያቄ ማቅረቡ ተሰምቷል። አሁን ላይ ቡርኖ ጉማሬሽ ወደ አርሰናል ለማምራት የሚያስችለውን ስምምነት ለመፈጸም የክለቦች ስምምነት ብቻ ይቀራል። ኒውካስትል አርሰናል ያቀረበውን የ70 ሚሊዮን ዩሮ የመጀመሪያ ዙር የዝውውር ጥያቄን ውድቅ ማድረጉ ይታወቃል። ሆኖም ግን የተጫዋቹ ጫና እና የመድፈኞቹ አዲስ የተሻሻለ የዝውውር ጥያቄ ለማቅረብ መንቀሳቀሳየው ኒውካስትል ቡርኖን ለመሸጥ ሊያስገድደው እንደሚችል ይጠበቃል። ተጨዋቹ አርሰናልን መቀላቀል እንደሚፈልግ በግልጽ ይፋ ያደረገ ሲሆን ፣ ክለቡ ግን እሱን ለመሸጥ እስካሁን ፍላጎቱን በግልጽ አላሳየም። ሆኖም አርቴታ ተጨዋቹ ወደ ስሜን ለንደን እንዲመጣ ትልቅ ግፊት እያደረገ እንደሚገኝ በርካታ አለም አቀፍ የመረጃ ምንጮች በስፋት እየዘገቡት ይገኛል። በመኮነን አልማው! @gebeyasport

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 5 июл.7432из gebeyasport

    የኢትዮጵያ አትሌቶች በዓለም አቀፍ መድረኮች የሚያስመዘግቡትን ድንቅ ድል አጠናክረው ቀጥለዋል። ሰኔ 28/2018 ዓ.ም (ገበያ ስፖርት) በአሜሪካ በተካሄዱት የ2026 ፕሪፎንቴይን ክላሲክ (ዩጂን ዳይመንድ ሊግ) እና የ57ኛው የፒችትሪ የጎዳና ሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊ በመሆን የላቀ ብቃታቸውን አሳይተዋል። ዩጂን ዳይመንድ ሊግ (የሴቶች ሁለት ማይል) በዩጂን በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር፣ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ብርቱ ፉክክር አድርገዋል። አትሌት አለሺኝ ባወቀ ውድድሩን በ9:20.02 በማጠናቀቅ አንደኛ ስትወጣ፣ አትሌት ሒሩት መሸሻ በ9:20.20 በሆነ ሰዓት በቅርብ ልዩነት ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች። በዚሁ ውድድር አትሌት ማርታ አለማየሁ በ9:21.42 አራተኛ፣ አትሌት የኔዋ ንብረት በ9:22.93 ሰባተኛ እና አትሌት አሳየች አይቼው በ9:23.04 ስምንተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል። እንዲሁም በሴቶች የአንድ ማይል ሩጫ አትሌት ሳሮን በርሀ በ4:22.50 አስራ አንደኛ፣ አትሌት ወርቅነሽ መሰለ በ4:36.80 አስራ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ፈጽመዋል። 57ኛው የፒችትሪ የጎዳና ሩጫ በሌላ በኩል የአሜሪካ የነፃነት ቀን ክብረ በዓል አካል ሆኖ በተካሄደው 57ኛው የፒችትሪ የጎዳና ሩጫ፣ የኢትዮጵያ አትሌቶች የበላይነታቸውን አረጋግጠዋል። ለረጅም ርቀት ሩጫ አትሌቶች ፈታኝ በሆነው በዚህ ውድድር፣ አትሌት ፅጌ ገብረሰላማ በመጨረሻዎቹ ሜትሮች ላይ ባሳየችው አስደናቂ ፍጥነት 31:02 በሆነ ሰዓት አሸናፊ ሆናለች። አትሌት መልክናት ውዱ ደግሞ በሰከንድ ልዩነት ማለትም በ31:03 በመግባት ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቃለች። በሮቤል አብርሃም @gebeyasport

  • 3 июл.78811из gebeyasport

    ላሚን ያማል ለጨዋታ ወደ ስታዲየም ሲደርስ ያደረገው ውድ የጌጣጌጥ ምርጫ መነጋገሪያ ሆነ ! ሰኔ 25፤2018 (ገበያ ስፖርት) የስፔኑ ወጣት ኮከብ ላሚን ያማል ከኦስትሪያ ጋር ላለባቸው ወሳኝ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ለማድረግ ወደ ስታዲየም ሲያቀና በአንገቱ ላይ አርጎት በነበረው ሀብል ርዕስ ሁኗል። ያማል ከቅርብ ጊዜ ወዲ በሚያሳየው የአለባበስ ዘይቤ ተከታዮቹን እያስገረመ ቢገኝም በአሁኑ የለበሰው የለበሰው የBatman ቅርጽ ያለው የአንገት ጌጥ ከፍተኛ ትኩረትን ስቧል። ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ይህ በብዙዎች ዘንድ ባትማን ተብሎ እየተጠራ ያለው የአንገት ጌጥ ዋጋ 350 ሺ የአሜሪካ ዶላር ወይም በግምት 62 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር እንደሆነ ተገልጿል። በሮቤል አበርሃም @gebeyasport

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 28 июн.9503из gebeyasport

    ማኑኤል ኡጋርቴ ለ9 ወር ከሜዳ ይርቃል ! ሰኔ 21፣2018 (ገብያ ሚዲያ) የማንቸስተር ዩናይትድ እና የኡራጓይ ብሔራዊ ቡድን አማካይ ማኑኤል ኡጋርቴ በዓለም ዋንጫው የምድብ ጨዋታ ወቅት በደረሰበት የACL ጉዳት ለብዙ ወራት ከሜዳ ተሰናብቷል። እንደ ጋዜጠኞቹ ሮድራ ቫዝኬዝ እና ዴቪድ ኦርንስታይን ዘገባ ፥ ኡጋርቴ በዓለም ዋንጫው የምድብ ጨዋታው ላይ ከስፔን ጋር በተደረገው ፍልሚያ ከፔድሪ ጋር በተፋጠጡበት አጋጣሚ የጉልበቱ ፊት ላይ ያሉት ጅማቶች መበጠሳቸው ተግልጿል። ምርመራዎች እንደሚያሳዩትም ጉዳቱ ከባድ በመሆኑ ተጫዋቹ ከ6 እስከ 9 ወራት ከሜዳ እንደሚርቅ ተረጋግጧል። ይህ አሳዛኝ ክስተት ኡጋርቴን ከዓለም ዋንጫው ውጪ ብቻ ሳይሆን ለማንቸስተር ዩናይትድ የውድድር ዘመን እቅድ ላይም ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጥሯል። ተጫዋቹ በቀጣይ ቀናት ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ተመልሶ የቀዶ ጥገና ህክምና የሚያደርግ ሲሆን ከዚህ ወር መጨረሻ አንስቶ ኡጋርቴ ወደ ሜዳ እስኪመለስ ድረስ ያለውን የህክምና ወጪ ሆነ የተጫዋቹ አጠቃላይ የ10 ወር ደሞዝ በፊፋ እንደሚሸፈን ተያይዞ ተገልጿል። በ ሮቤል አበርሃም @gebeyasport

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 26 июн.1 0201из gebeyasport

    አርሰናል የኒውካስትል ዩናይትድ ተጫዋቾችን ለማስፈረም ተዘጋጅቷል! አርሰናል ብሩኖ ጉማሬሽን እና ቶናሊን ከኒውካስትል ዩናይትድ በአንድ የዝውውር መስኮት መውሰድ እንደሚፈልግ ተዘግቧል። ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ አርሰናል ለብሩኖ ጉማሬሽ ድንገተኛ የ55 ሚሊዮን ፓውንድ የቃል ጥያቄ ቢያቀርብም በኒውካስትል ወዲያውኑ ውድቅ ተደርጓል። ኒውካስል ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ ብሩኖን በቡድኑ ውስጥ ማቆየት እንደሚፈልግ ገልጿል። በተጨማሪም ተጨዋቹ ለሽያጭ ቢቀርብ እንኳን በዚህ የዋጋ መጠን እንደማይሸጥ ለአርሰናል ግልፅ አድርጎለታል! ሆኖም ግን ጥያቄው ውድቅ የተደረገበት አርሰናል ለጉማሬሽ ሁለተኛ ጥያቄ ለማቅረብ እየተዘጋጀ ስለመሆኑ ታውቋል። የማርቲን ኦዴጋርድ ቆይታ ላይ ጥርጣሬ ያለባቸው መድፈኞቹ ከጉማሬሽ በተጨማሪ ሌላኛውን የኒውካስትል ኮከብ ሳንድሮ ቶናሊን ማስፈረም ይፈልጋል። ይህንን በተመለከተም አርሰናል ሁለቱን የኒውካስትል የመሃል ሜዳ ሞተሮች በአንድ ላይ ማስፈረም በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ጥልቅ ውይይት ማድረጋቸው ተሰምቷል። አርሰናል ቶናሊን ለረዥም ጊዜ ሲከታተለው እንደቆየ የሚታወቅ ሲሆን በጉማሬሽ ጉዳይ ደግሞ ከወኪሉ ጋር በቀጥታ መነጋገራቸው ተዘግቧል። የመድፈኞቹ አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ የሁለቱም ተጫዋቾች አድናቂ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን አንድሬ ቤርታ በበኩላቸው የተጫዋቾቹ የተላመደ ጥምረት በመድፈኞቹ ቤት ውጤታማ እንደሚሆን ተማምነዋል። ኒውካስትል በበኩሉ ደህና የዝውውር ገንዘብ ከቀረበለት ጉዳዩን በትኩረት ሊመለከተው እንደሚችል የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል። @gebeyasport

  • 4 мая1 3674из gebeyanews

    መልካም ቀን! #ገበያ_ሚዲያ #gebeyanews

  • 29 апр.1 3321из gebeyanews

    ከዛሬ ጀምሮ የናፍጣ አቅርቦት ወደነበረበት እንዲመለስ ተወሰነ ሚያዚያ 21 /2018 (ገበያ ሚዲያ) የናፍጣ አቅርቦት ከዛሬ ጀምሮ ቀድሞ ወደ ነበረበት እንዲመለስ መንግሥት መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ። በኢትዮጵያ የአንድ ቀን የናፍጣ አቅርቦት ከመካከለኛው ምሥራቅ ግጭት በፊት ወደ ነበረበት 9 ሚሊዮን ሊትር እንዲመለስ መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። በመካከለኛው ምሥራቅ ግጭት ምክንያት የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ መጨመር እና አቅርቦት ላይ መስተጓጎል መፈጠሩን ተከትሎ በኢትዮጵያ የአንድ ቀን የናፍጣ አቅርቦት ወደ 4.5 ሚሊዮን ሊትር ወርዶ እንደነበር ይታወሳል። ሆኖም አሁን ላይ የአንድ ቀን የናፍጣ አቅርቦት ወደ ቀደመው 9 ሚሊዮን ሊትር እንዲመለስ መወሰኑን ተከትሎ ከዛሬ ጀምሮ ከጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ መጓጓዝ እንደሚጀመር የገለጹት የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ወደ ክልሎች ደግሞ ከነገ ጀምሮ መጓጓዝ ይጀምራል ብለዋል። እስካሁን የቤንዚን እና የአውሮፕላን ነዳጅ ሙሉ በሙሉ ቀድሞ በነበረው መጠን እየቀረበ መሆኑንም የገንዘብ ሚኒስትሩ አክለዋል። አክለውም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የነዳጅ አቅርቦት መስተጓጎል ኢኮኖሚው ላይ የሚያደርሰውን ጫና ለመከላከል መንግሥት በልዩ ግዢ በከፍተኛ ዋጋ ነዳጅ ገዝቶ እያቀረበ መሆኑንም አስረድተዋል። ይህ እርምጃ በሀገሪቱ ያለውን የትራንስፖርት እና የግብርና እንቅስቃሴ ለማቀላጠፍ ከፍተኛ እገዛ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል። #ገበያ_ሚዲያ ገበያ ሚዲያ | ገበያ ቢዝነስ | Facebook #ገበያ_ሚዲያ #gebeyamedia #gebeyanews #ገበያ #Ethiopia #ኢትዮጵያ #addisababa #አዲስአበባ #ነዳጅ #ናፍጣ #የነዳጅ_አቅርቦት

  • 13 апр.1 5093из gebeyanews

    የአሜሪካን እገዳ ተከትሎ የዓለም የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ናረ ሚያዚያ 5/2018 (ገበያ ሚዲያ)አሜሪካ በኢራን የወደብ መስመሮች ላይ ጥብቅ የባህር ላይ እገዳ እንደምትጥል ማስታወቋን ተከትሎ በዓለም አቀፍ ገበያ የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ አሳየ። በዚህም የአሜሪካ ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በ8 በመቶ በመጨመር በአንድ በርሜል 104.24 ዶላር ደርሷል። የዓለም አቀፍ መለኪያ የሆነው የብሬንት (Brent) ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋም በተመሳሳይ የ7 በመቶ ጭማሪ በማሳየት በአንድ በርሜል 102.29 ዶላር ሆኖ ተመዝግቧል። ይህ የዋጋ ንረት የተከሰተው ዋይት ሀውስ ከዛሬ ጀምሮ በኢራን ወደቦች ላይ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ለማገድ መወሰኑን ይፋ ካደረገ በኋላ ነው። እንደ አሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ የነዳጅ ዋጋ በኢራን ጦርነት ወቅት ከፍተኛ መለዋወጥ እያሳየ የሚገኝ ሲሆን ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት በየካቲት ወር መጨረሻ 70 ዶላር አካባቢ የነበረው የብሬንት ነዳጅ ዋጋ በተለያዩ ጊዜያት እስከ 119 ዶላር ደርሶ ነበር። ባለፈው አርብ የሰላም ንግግሩን ተስፋ በማድረግ የሰኔ ወር ርክክብ የብሬንት ነዳጅ ዋጋ በ0.8 በመቶ ቅናሽ አሳይቶ 95.20 ዶላር ላይ ተረጋግቶ የነበረ ቢሆንም የአሜሪካው ውሳኔ ገበያውን በድጋሚ አናውጦታል። የአሜሪካው የባህር ላይ እገዳ ተግባራዊ መሆን ሲጀምር የነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለቱ ይበልጥ ሊስተጓጎል እንደሚችል የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። #ገበያ_ሚዲያ ገበያ ሚዲያ | ገበያ ቢዝነስ | Facebook #ገበያ_ሚዲያ #gebeyamedia #gebeyanews #ገበያ #Ethiopia #ኢትዮጵያ #addisababa #አዲስአበባ #የነዳጅዋጋ #አሜሪካ #ኢራን

Gebeya Media - ገበያ — tgindex